آخرین پست‌های Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) در تلگرام

پست‌های تلگرام Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 مشترک
727 عکس
95 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 17:16

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Roha Tv/ሮሃ ቴቪ در تلگرام

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

06 Mar, 14:23

1,273

ከሁሉ አስቀድሜ   የትጥቅ ትግላችን ለተለኮሰበት 3ኛ ዓመት  ለዚች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

  የትጥቅ ትግል ባልታሰበበት ማንም  ባልነቃበት ሁሉም በተኛበት የትጥቅ ትግል ባልተለመደበት በዚያ ጨለማ ጊዜ   የአማራን ሕዝብ ከጭቆና ለማላቀቅ  ሞጣና  አካባቢዋ  ወጣቶችን  አንቅቶና አደራጅቶ አሰልጥኖ  የትጥቅ ትግል በማስጀመር  የካቲት  27 _ 2014  አመተ ምህረት  የመጀመረያዋን  ጥይት  ወደ ካድሪ በመተኮስ   አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ የትግላችን ችቦ ለኳሽ ጀግና አርበኛ ነበር።  የመጀመሪያው የትጥቅ ትግል የጀመርን ዕለት በዚያች ቀን አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ቢሰዋም 4 ባንዳዎችን በመቀንደሽ 9 ክላሽ   1 ጂም ስሪ በመማረክ ነበር በሞጣ ቀጠና የትጥቅ ትግሉን አሐዱ ብለን የጀመርን።   ልክ በዛሬዋ ዕለት  የካቲት 27-2014 የትጥቅ ትግሉን በይፋ የጀመርን ዕለት  አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ከእኛ ቢለይም   ትግል ቅብብሎሽ በመሆኑ የእሱን አደራ ተቀብለን ከ እነ ተፈራ ዳምጤና  ከሌሎች ከተሰው  ጀግኖች ጋር ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው  ትግሉ  ከሞጣ ቀጠና አልፎ   በመላ ጎጃም የትጥቅ ትግሉ  እንዲቀጣጠል አድርገናል።

የትጥቅ ትግሉን ስንጀምረው  የብልጽግና ካድሬዎች አጥተው  ቸግሯቸው  ይሉን ነበር። አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝም" እኛ የምንታገለው አጥተን አይደለም ለነጻነት ነው"  ሲል ነበር ።

ዛሬም  የምንታገለው  አጥተን ቸግሮን ገንዘብ ለማግኘት የሚመስላቸው አሉ።  ገንዘብ ሳይሆን ነጻነት አጥተን ነጻነትን ፍለጋ ወደ ጫካ ከወጣን እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጠርን።

ጓድ ቀዳሚ ሰማዕት መዝገቡ ዋለልኝ  ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲል ሞጣ ከብት ገበያ  ከጎናችን ወድቋል። ጓዳችን ከተሰዋ በበነጋው  ጀምረን የተሰዋለትን ለአማራ ነጻነትና አንድነት  ለማምጣት እየታገልን እንገኛለን።

በትግላችንም  መጠነ ሰፊ ውጊያ በመክፈት የብልጽግና ሰራዊት ተቆጣጥሯቸው የነበሩ  ሰፊ ቀጠናዎችን ተቆጣጥረናል። የተቆጣጠርናቸውን ቀጠናዎችንም  ከውጊያ ጎን ለጎን የሲቪል አስተዳደር በማዋቀር ሕዝብ እያስተዳደርን እንገኛለን።
ወቅቱ በጠየቀው ትግል  ከጋንታ  እስከ ክፍለጦር  እየተዋጋን እስከዛሬ ያለውን አመርቂ  ድል አግኝተናል።  አሁን ላይ ግን ከጠላት አሰላለፍ አኳያ ይህ በአውራጃ  የተመሰረተ የፋኖ አደረጃጀት ወደ አንድ የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ተቋም በማሳደግ  በወታደራዊ አንድነትና ቅንጅት ጠላቶቻችንን ደምስሰን ለሕዝባችን የመጨረሻዋን ድል ልናበስረው ይገባል እላለሁ።

አንድነት ኃይል ነው”  እንደሚባለው። የመጨረሻውን ድልና ግብ ለሕዝባችን ለማብሰር   አንድነት ፈጥሮ ተቀናጅቶ መዋጋት የደረስንበት የትግል ደረጃ   ይጠይቃል። ደካማ አገርና ትውልድ የሚወለደው አንድነትን በማጣት በመሆኑ  እንደ አማራ  አንድ  የአማራ ፋኖ  ወታደራዊ ተቋም ያስፈልጋል።

ጠላቶቻችን እኛን ለማጥፋት ለእኩይ ግብር ሕብረት ፈጥረው አማራን ለማጥፋት ወደ ሰፈራችን ሲመጡ እኛ  ለቅዱስ ዓላማ ለአማራ ፋኖ አንድነት ሲባል የግል ፍላጎትን ገርቶ ወደ አንድነት መምጣት አሸናፊነት  እንጂ ውርደት አይደለም ።
እንደ መብረቁ የትጥቅ ትግል ከጀመርንበት ከየካቲት 27- 2014 ዓ.ም  ጀምሮ  ከአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መስዋዕትነት በኋላ የትግሉ አስቀጣይና የመብረቁ ፊታውራሪ የነበሩትን እነ ሻለቃ ተፈራ ዳምጤንና  ብዙ ጓዶችን በትግሉ ገብረናል። ጓዶቻችን የተሰ_ውት ደግሞ ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲሉ ነው።   ጓዶቻችን የተሰውለትን  ለአማራ ሕዝብ ነጻነትና  አንድነት   የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ እየከፈልን የምናስፈጽም ይሆናል።

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
(የአማራ ፋኖ በጎጃም )
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

06 Mar, 13:05

1,407

ሰበር ዜና!

“60 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣ 49 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማርከናል።” የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ቋራ ኦሜድላ እና አድዋ ክፍለጦር በምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጦር ጋር በተደረገ ውጊያ በጠላት ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልጿል።

በዛሬው ዕለት የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ በተደረገ ውጊያ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ 60 ሰራዊት ሲደመሰስ፣ 49 ክላሸንኮቭ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ የሆነ ሲሆን በተጨማሪም ወደ አልጣሸ ብሔራዊ ፓርክ መደበኛ መኪና መግባት ስለማይቻል በትራክተር ተተኳሽና ስንቅ ለማሰጋገር ሲሞክር ትራክተሩ ከእነሙሉ ተተኳሽና ስንቁ በፋኖም እንደተማረከ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አካል የሆኑት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና የአድዋ ክፍለጦር አካል የሆነው ነብሮ ብርጌድ የጠላትን ኃይል ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ፣ የጠላት ኃይል ከመደምሰስና ከመማረክ የተረፈው ወደ ገለጎ ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ አስቻለው አለባቸው  ገልጿል።

© ኢትዮ 251 ሚዲያ
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

06 Mar, 12:35

1,570

ሰበር ዜና!

አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር ጉና ክ/ጦር፣ ሐገረ ቢዘን ብርጌድ የካቲት 26 ለ27 ሌሊት 2017ዓ.ም ሥማዳ ወረዳ ወገዳ ከተማ ላይ በተደረገ የተጠና ኦፕሬሽን የወገዳ ከተማ ዋና ከንቲባ ኃላፊ ''ጥላሁን አውለው''ን ኢላማ ያደረገ የቦምብ ጥቃት ተፈጽሟል።

በተመሣሣይ በዚሁ ወረዳ የኳሳ ከተማ ላይ ምሽግ ላይ ዋርድያ የነበሩ አካላት ከነመሣሪያቸው እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ድላችን በተባበረ ክንዳችን
አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

06 Mar, 08:21

1,824

https://youtu.be/U5-UMfLYgBE?si=XkM-GfCH5GZ9mrSN
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

06 Mar, 04:43

2,100

ሁሉም ሰው ይህ መልእክት እንዲደርሰው ይርዱን። እህታችን ትዝታ ባህላችን፣ ወጋችን እና ሐይማኖታችን በሚያዘው መልኩ የቀብር ስነ ስርአትዋን ማስፈጸም የሁላችንም ኃላፊነት ስለሆነ የቻልነውን ያህል እንርዳ።
Please share with your network!
It is on us to make sure that she will have a fitting farewell to her creator.

If you get account name doesn't match message, please put account name as Ethiopian Community Association in Victoria.
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 18:12

2,223

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር  ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር የተለያዩ ኦፕሬሽኖችን በመፈፀም  በአገዛዙ  ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ ድል ተቀዳጀ ።

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር  የመጀመሪያ የሆነውና የካቲት 18/2017ዓ.ም የተመሰረተው ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር  ቀዳሚ የሆነውን አስደማሚውን ኦፕሬሽን አካሔደ።

ይህ ኮር በጎንደር ክፍለ ሀገር የመጀመሪያ ኮር ሲሆን በስሩ 5 ግዙፍ ክፍለጦሮችን አካቶ የተመሰረተ ከመሆኑም ባሻገር ታሪካዊቷንና ቀዳሚዋን ጉና ክፍለጦርን ያካተተ እና ሌሎች ኢንጂነር ስመኘው ክ/ጦር፣ጣና ገላውዲወስ ክ/ጦ፣ ሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር እና አፄ ፋሲል ክ/ጦር በጋራ በመሆን የአናብስቶችን መናገሻ ደቡባዊ ጎንደርን አካሎ የተቋቋመ ኮር ነው።

በዚህም በየካቲት 22 በተካሄደ ኦፕሬሽን እስቴ ዴንሳ ብርጌድ በወሰደው እርምጃ ሾለክት ላይ አንድ የመከላከያ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። በየካቲት 23 አንዳቤት ላይ በተሰዋው ጀግናው ፋኖ ፋሲካው ስም በተካሄደው ዘመቻ ፋሲካው ኦፕሬሽን  እስቴ ከተማ በመግባት  የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ከማድረጉም በተጨማሪ በርካታ ትጥቅና ተተኳሽ መማረክ ተችሏል። በየካቲት 24 መቅደላ ብርጌድ ናደው ሻለቃ በአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ላይ እርምጃ በውሰድ ቁጥሩ ያልታወቀ በርካታ የጠላትን ኃይል ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ጋሳኝ ከተማን አስለቀቆ መቆጣጠር ችሏል።

በተመሳሳይ ሜጀር ጄነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከጀ/ል ነጋ ተገኘ ክ/ጦር ጋር በቀጠናዊ ትስስር በመቀናጀት በደብረታቦር የገብርዬ ክፍለከተማ ፀጥታ ኃላፊን ጨምሮቨ በርካታ የአድማ ብተና፣ ሚሊሻና ፖሊስ አመራር ላይ እርምጃ ተወስዷል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር  ከጀ/ል ነጋ ተገኘ ክ/ጦር ጋር በቀጠናዊ ትስስር በመተሳሰር በኮረኔል ታደሰ እሸቴ ስም ባካሄደው ዘመቻ ኮረኔል ታደሰ እሸቴ ኦፕሬሽን በዛሬው ዕለት ማለትም 26/06/2017 ዓ.ም ከጋሳኝ እስከ ወረታ ከተማ በመዝጋት የአሸባሪውን ሰራዊት መግቢያ መውጫ አሳጥቶ ግማሹ እግሬ አውጠጭኝ ብሎ ማሳ ለማሳ ሲፈረጥጥ ቀሪውን ደግሞ ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል።

ነገሩ እንዲህ ነው በጦር ጠበብቶቹ የሚመራው የሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ 1ኛ ኮር ዘመቻ አዛዥዘ እና የጉና ክ/ጦር ም.አዛዥ በሆነው በሻለቃ ቢራራ ደምሴ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሎጂስቲክ መምሪያ ሀላፊና የጉና ክ/ጦር ዋና አዛዦዥ ሻምበል አምሳሉ ማዘንጊያ፣ በጉና ክ/ጦር ም/ዘመቻ መመሪያ ኃላፊ  አርበኛ ሐብታሙ አጠቃ፣ በሜ/ጄ/ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ዋያ አዛዥ በታዳጊው አርበኛ ተመስገን ውባንተ አባተ እንዲሁም እንደ ቀጠናዊ ትሥሥር በጄ/ነጋ ተገኝ ክ/ጦር ዋና አዛዥ በሥመ ጥሩ ጀግና ሻ/ፀዳሉ ደሴ የተመረዉ ይህ ዘመቻ ከጋሳኝ እስከ ወረታ ያለውን ጥቁር አስፓልት እንደ ቆዳ ወጥረው የጠላትን ሀይል በጋሳኝ (መቅደላ ብርጌድ)፣በአለምሳጋ (በሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር፣ አለም በር ( አርበኛ ገ/መስቀል ብርጌድና ሜ/ጀ/ል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር)፣በጃራገዶና በሙቀጭ(አንዳቤት ብርጌድ)፣ ወጂ (ኢ/ር ስመኘው በቀለ ተወርዋሪ ክ/ጦር) ከተባሉ ቦታዎች የእናት ጡት ነካሽ የሆነውን ምኒሻ፣ፖሊስና አድማ ብተና ሙትና ቀስለኛ አድርገውታል።
በዚህም አውደውጊያ የአለምበር እና የወጂ የሚሊሻና የአድማ ብተና ካምፕ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።

በርካታው የባንዳ ሬሳ ያልተነሳ ሲሆን ወደ ደብረታቦር ከተላከው ሙሉ ሁለት መኪና ቁስለኛ ደ/ታቦር ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ 7ቱ ወደ ላይመለሱ ሲሸኙ ወጂ ከነበረው አወደ ውጊያ ደግሞ 8ቱ አድማ ብተና አባላት ወደ ፋኖ  ተቀላቅለዋል። ወጂ ከተደረገው አውደውጊያ 1ፓትሮሎል ቁስለኛ ወደ ወረታ ጭኗል። የተሰዋው ግን የትየሌሌ ነው።

የሚያሳዝነው የምኒሻ እና የአድማ ብተና አስከሬን ክምር ቀኑን ሙሉ ሳይነሳ መዋሉን ስናይ ስርአቱ የሞቱትን አማራዎች እንኳን ክብር  እንደማይሰጣቸው ለቀሪዎቹ አሳይቷል።

ክብር ለተሰዉት ጀግና የአማራ ልጆች
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር  ሜጀር ጀኔራል ውባንተ አባተ ኮር
የካቲት 26/2017
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 17:32

2,119

የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ዛሬም አኩሪ ጀብዱ ሰርቷል

በዛሬው እለት ማለትም በየካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም  በበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል  ውጊያ ተደርጓል።

በብርጌዱ ዘመቻ መሪ በኮማንዶ አስር አለቃ አብርሃም ጸጋየ የተመራው የዛሬው ኦፕሬሽን አኩሪ ድል አስገኝቷል።

በውጊያ ስልታቸው  በጀግንነታቸው የተመሰከረላቸው ተናዳፊወቹ የቀስተ ደመና
ፋኖ አባላት እንደሚያውቁበት የወንበዴውን ስብስብ በክላሽ በብሬን በስናይፐር ሲያጫውቱት አርፍደዋል ።

          ሌሊቱን ሲሳቡ ያደሩት ተናዳፊዎቹ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ  ፋኖዎች
   በወረዳችን ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ ባለው በየቀጋት ቀበሌ በኪዳነ             ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተደበቀውን  ጠላት ምሽጉን በመክበብ  ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት  ላይ መብረቃዊ ጥቃት በማድረግ እንደፈለጋቸው በመውቃትና ድባቅ በመምታት ሙትና ቁስለኛ አድርገውት ተመልሰዋል። በቆፈረው ምሽግ ቀብረውታል ማለት ነው።

    ይህ ራሱን መከላከያ እያለ የሚጠራው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የወንበዴ ስብስብ  በዚህ ስፍራ ከ 1 ወር በላይ መሽጎ እንደቆየ ይታወቃል።

             ውጊያው ለ1 :30 ያህል የቆየ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የታየበት ነበር።
   ጠላትም የተናዳፊዎች ምት ሲበረታበት አድኑኝ ብሎ በጠየቀው መሰረት አዳረሩን ከጎዛምን ወረዳ ከማይ አካባቢ  ሲጓዝ አድሮ ወደ ኤልያስ ከተማ  የደረሰው ከ400 በላይ የሚሆን ሀይል ተጨምሮለት  ሊታደገው ችሏል።

     እንግዲህ በዚህ አውደ ውጊያ ከጠላት ወገን  2ፓትሮል እና  1ኦራል   ሙትና ቁስለኛ አንስተዋል ።በአካባቢው ያሉ እማኞችም እንደነገረሩን እስከ ረፋዱ 5:00 ድረስ በየጢሻው የወደቀውን አሰከሬን እና ቁስለኛ እየለቀሙ ነበር ተብሏል።

        በቀስተ ደመናወቹ ከባድ ምት የተበሳጨው ጠላትም ወደጎፍጭማ ቀበሌ አሰሳ በመሄድ በመንደር በመግባት አንድ ንጹሀን ገበሬ መረሸኑን በአካባቢው ከነበሩ መረጃችን ለመረዳት ችለናል ።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 17:01

2,135

https://youtu.be/ockkEdmAYNw?si=Jy3wu0j6FVf8XQSU
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 13:11

2,408

የአደረጃጀት ዜና!

የጁ ክፍለጦር ተመሰረተ!

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) ልጅ እያሱ ኮር የጁ ክፍለጦር ተመስርቷል።

የክፍለ ጦሩ ሙሉ መግለጫ    
ቀን  26/6/2017 ዓ/ም

በአማራ  ህዝብ ላይ የከፈተዉን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመቀልበስ የህልዉና ትግል  ዉስጥ የገባዉ የአማራ ፋኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወታደራዊ እና ፖለቲካ አደረጃጀቶችን በብቃትና በጥራት እያሻሻለ አሁን ካለበት ደረጃ መድረስ ችሏል።

በዚህም መሰረት ዛሬ የካቲት 26/2017ዓ/ም  በይፉ የተመሰረተዉ የጁ ክፍለ ጦር በስሩ የተለያዩ አደረጃጀት መሪዎችን ሰራዊቱ መርጧል።

በዚህም መሰረት
1. አርበኛ አምሳ አለቃ ሞላ አባተ የክፍለ ጦሩ ዋና አዛዥ
2. አርበኛ ቢኒያም ሰኢድ የክፍለ ጦሩ ምክትል አዛዥ
3. አርበኛ ተገኘ ስጦት የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መሪ
4. መምህር አማረ ተገኘ የክፍለ ጦሩ አስተዳደርና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
5. አርበኛ ሀሰን ሙሄ ህዝብ ግንኙነትና ኦድተር ኃላፊ
6. አርበኛ ተስፋየ አለባቸዉ የፋይናንስ ኃላፊ
7. አርበኛ ግዛዉ ሰለሞን ሎጅስቲክ ሀላፊ
8. አርበኛ ዮናስ አሉላ የክፍለ ጦሩ ፐርሶኔል ኃላፊ ሆነዉ ተመርጠዋል።

ከላይ በተዘረዘሩት አደረጃጀቶች መሰረት ህዝባችንን ከጥቁር ጣሊያን የአፓርታይድ ማነቆ ስርዓት ለማዉጣት በሚደረገዉ የህልዉና ትግል በፅናት  ለመስራት  ቃል እየገባን በዚህ ትግል የሚመለከታችሁ ሁሉ በምትችሉት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድል ለፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 10:53

2,323

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ተጠናክሮ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ምዕራብ ወሎ ኮር በአርበኛ ጀማል ብሬን የሚመራው ልዩ ዘመቻ ከሸህ ሁሴን ጅብሪል ክፍለጦር በቶ ብርጌድ እና ዳግም ክተት ወረ ኢሉ ክፍለጦር የተውጣጡ አሃዶች በጋራ ልጓማ ከተማ ሌሊቱን ዘልቀው በመግባት የተሳካ የከተማ ኦፕረሽን በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የካቲት 24 ለ 25/2017 ዓ.ም ልጓማ ከተማ ሌሊቱን በተደረገ ተጋድሎ በርካታ ሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና ሲደመሰስ በርካታው ቁስለኛ ሆኗል:: በዚህ ተጋድሎ ጀግኖቹ በፈፀሙት ከባድ የጉሬላ ዉጊያ የልጓማ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሃላፊ ከባድ ቁስለኛ ሆኗል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና የሚባሉ የአማራ ሃይሎች ከብልፅግናው መንግስት ጋር መተባበራቸዉን እስካላቆሙና ዘር ማጥፋት ከሚፈፀምበት ወገናቸው የአማራ ህዝብ  ጎን እስካልቆሙ ድረስ “ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ነውና” ለሰፊዉና ብዙሃኑ ህዝብ ህልዉና ሲባል ጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፋኖ አመራሮች ገልፀዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)
የካቲት 25/2017 ዓ.ም