Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) Kanalının Son Gönderileri

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ Telegram Gönderileri

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 Abone
727 Fotoğraf
95 Video
Son Güncelleme 06.03.2025 17:16

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ tarafından Telegram'da paylaşılan en son içerikler

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

23 Feb, 18:09

2,835

ከ20 በላይ የኬኒያ ዜጎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሚሊሻዎች ጥቃት መገደላቸው ተገለፀ!

በኢትዮጵያና ኬንያ አዋሳኝ በቱርካና ሀይቅ ዳርቻ በቶዶንያንግ የድንበር መሻገሪያ ቦታ ላይ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ታጣቂዎች በትናንትናው ዕለት በኬንያ ዓሣ አጥማጆች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የኬኒያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።

ሪፖርቱ "ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሳነች ሚሊሻዎች ዓሣ አጥማጆቹ በቱርካና ሀይቅ ላይ በሚሰሩበት ወቅት አካባቢውን በመውረር በዘፈቀደ ተኩስ ከፍተዋል" ይላል።

በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከአካባቢው ፖሊስ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ ቅዳሜ ማለዳ በቱርካና ውስጥ አንድ የታወቀ ሽፍታ ሶስት የዳሳነች ዓሣ አጥማጆችን በመግደሉ ምክንያት የተፈጸመ የበቀል እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

"የውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ሚኒስቴር በዳሳነች ሚሊሻዎች በቱርካና ሀይቅ ቶዶንያንግ አካባቢ ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የሚያሳዝኑ ሪፖርቶችን እየደረሰን ነው። ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ ይችላል" ሲሉ ናቡይን ተናግረዋል።

"ሁኔታው በጣም የከፋ ነው፣ አዳኞች ህዝባችንን ለመጠበቅ በፍጥነት መንቀሳቀስ አለባቸው። እልቂቱ በኬንያ ምድር ላይ እየተፈጸመ ነው፣ በደንብ በታጠቁ ሚሊሻዎች (ዳሳነች) የተያዘው።" ሲሉም አክለዋል። ክስተቱ ትናንት ቅዳሜ ምሽት በሎፔይሙካት እና ናቲራ በኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ ተከስቷል።

በጥቃቱ አምስት ጀልባዎች ተደብድበው በጀልባዎቹ ላይ የነበሩት በሙሉ ተገድለዋል።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

23 Feb, 17:30

2,569

https://youtu.be/fMPgmGFUrVo?si=p_SLMh9MrLpeT2mk
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 18:07

1,114

https://youtu.be/yhqH5ElDNBQ?si=mBCbSjUZoICJ6uT3
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 16:27

1,480

https://youtu.be/Nq6nJfMsDEQ?si=XUA7ntmyTt7cr-kt
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 15:32

1,510

በኮምቦልቻ ጮሬሳ  ካምፕ የፖለቲካ እስረኞች ሞቱ ።

የአማራ ፋኖን ትግል  ትደግፋላችሁ በሚል ከመላው የአማራ ክልል በብልፅግና የፀጥታ ኃይሎች ታፍሰው በኮምቦልቻ አቅራቢያ ጮሬሳ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች በውሃ እና በምግብ መመረዝ ምክንያት በርካቶች መሞታቸውን የእስረኛ ቤተሰቦች ለአማራ ድምፅ ገለፁ ።

በማጎሪያ ካምፑ ውስጥ 890 እስረኞች የሚገኙ ሲሆን በሦስት ቀናት ውስጥ አስር እስረኞች በዚሁ ድንገት በገባው የውሃ ወለድ ወረርሽኝ መሞታቸውን ነው ቤተሰቦቻቸው የገለፁት።

የበሽታው መነሻ ነው የተባለው ደግሞ እስረኞቹ የሚጠጡት ከወራጅ ወንዝ የተቀዳ ውሃ በመሆኑ በዚሁ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ነው የተናገሩት።

ወደ ካምፑ የጤና ባለሙያዎች  እንዳይገቡ በመከልከሉ ምክንያት  በሽታው እየተባባሰ መሆኑን ነው የተገለፀው።

በአንድ አነስተኛ ክፍል ውስጥ ከመቶ በላይ እስረኞች የታጎሩ ሲሆን መፀዳጃ ቤት እና በቂ ውሃ ባለመኖሩ ወረርሽኙ ወደ ሁሉም እስረኞች እየተዛመተ ነው ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 15:24

1,428

<<የአማራ ፋኖ በጎጃም 8ኛ በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር>>

®ከፍትህ አልባ፣ከመርህ የለሽ፣ከ666 ተዋናይ ከግብረ ሰዶም አቀንቃኝ፣ከአማራ ህዝብ ጨፍጫፊ ጋር በመሆን የምታገለግሉና የአማራን ህዝብ ለጠላት አሳልፎ በመስጠት የሰይጣን ተላላኪ በመሆን የምታቆጠቁጡ የአመራር፣የፖሊስ፣የአድማ ብተና፣የሚኒሻና አንዳንድ ተላላኪ ባንዳ ተውኔቶች ያለፈ ህይወታችሁ፣የወደፊት ታሪካችሁ፣የኋላ ሞታችሁ ሳይከፋ ከድርጊታችሁ በመቆጠብ ከህዝባችሁ ጎን ልትቆሙ ይገባል፡

1ኛ.ሆድን እንደ አምላክ፣ነውርን እንደ ክብር በመቆጠር በማይጠቅም ወንበር ላይ በመቀመጥ የአብይ አህመድን የጥፋት ሾተላይ በመቀበል በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ተልዕኮ የምትሰጡ የአመራር አካላት ቀኑ ሳይሄድ፤ሰዓቱ ሳይመሽ ከአማራ ፋኖ ጎን በመቆም የአማራን ህዝብ ከጥፋት እንድትታደጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡

2ኛ.በምታውቁት የስርቆት ዘዴ በመደበቅ የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረት ከመዝረፍ ባሻገር ለአገዛዙ ስራዊት ተልዕኮ በመስጠት የምታገለግሉ የፖሊስና የአድማ ብተና አካላት ከዚህ አስነዋሪ ተግባር ራሳችሁን ጠብቃችሁ፤የሰይጣን አባሪ ከመሆን ወታችሁ ከታሪካዊ ስህተት ለመውጣት ከአማራ ህዝብ ጎን ለመቆም በጥሩ ቁመና እውነተኛ መንገድ ከአማራ ፋኖ ጎን በመቆም የአማራን ህዝብ ከጠላት ዳንኪራ ለማትረፍ  ከአገዛዙ በመውጣት እንድትተባበሩን መልእክታችንን እናደርሳለን፡

3ኛ.በደንቆሮ ስነ-ልቦናችሁ፣በማያውቅ አመለካከታችሁ፣ባልተማረ ግንዛቢያችሁ ከአገዛዙ ስራዊት ጋር በማበር የአማራን ህዝብ በጥቆማ፣በጥላቻ መንገድ በመምራት እያጠፋችሁ ካለው ድርጊት በመቆጠብ ህዝባችሁን ከተደቀነበት የጥፋት አደጋ ልታወጡ እንደሚገባ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡

4ኛ.ስራችን አልታወቀም፣ተግባራችን አልታየም ብላችሁ በውስጥ መስመር በጥቅማጥቅም በመታለል፣በገንዘብ በመሸጥ ለአገዛዙ የጥፋት ጦር፣ለአማራ ህዝብ የሞት ወጥመድ በማዘጋጀት የምታገለግሉ ተላላኪ ባንዳ በአስቸኳይ ከድርጊታችሁ ወጥመድ በመውጣት የአማራ ፋኖን በመደገፍ የአማራን ህዝብ ከገባበት የአብይ አህመድ ሴራና ተልዕኮ ለማውጣት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባችሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

5ኛ.በአንዳንድ አካባቢዎች የምትገኙ የአመራር፣የፖሊስ፣የሚኒሻ፣አድማ ብተናና ተላላኪ ባንዳ የቅርብ ቤተሰቦች የአማራን ህዝብ በመከራ ወጥመድ ለማጥፋት ቆርጠው ከተነሱ የአረጋ ከበደና የተመስገን ጥሩነህ የሽንት ቤት ጠራጊ እሽኮኩላ ለሆኑ ለአመራር፣ ለፖሊስ፣ ለሚኒሻ፣ ለአድማ ብተናና ለተላላኪ ባንዳ ግለሰቦች በመወገን መረጃ የምታቀብሉ አካላት ከዚህ ድርጊታችሁ መታቀብ እንዳለባችሁ መልእክታችንን እናሳውቃለን፡

6ኛ.ከአማራ ፋኖ ጎን በመሰለፍ ትግሉን ለመጥለፍ በከፋፋይ አጀንዳ ደፋ ቀና በማለት የአረጋ ከበደንና የተመስገን ጥሩነህን ተልዕኮ በመቀበል የአማራ ፋኖን ትግል ለመጥለፍ በመጥፎ ጥላሸት በማጣጣል ጎምበስ ቀና የምትሉ የውስጥ ጠላቶች የውጭ ሾተላዮች ከድርጊታችሁ በመታቀብ የአማራ ፋኖን ትግል በድል ለመምራት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡

7ኛ.የሀይማኖት አባቶች በአማራ ህዝብ ላይ እየተሰራ ያለውን ሴራና ተልዕኮ ልብ በማለት የአማራ ፋኖን ትግል በሀሳብና በስነ-ልቦና በመደገፍ በተሰጣችሁ ፀጋና በረከት የአብይ አህመድን ድርጊት ልታወግዙ ይገባል፡

8ኛ.የአካባቢው ማህብረሰብ፣የአካባቢው ወጣት ዛሬ በዝምታ የተመለከትከው የአብይ አህመድ የጥፋት ቡድን ነገ ጠራርጎ ለመቃብር አፈር አጋልጦ መስጠቱ አይቀርምና ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በፋኖ መዋቅር በመደራጀት የአብይ አህመድን የጥፋት እቅድ ለማክቸፍ"ሆ"ብሎ መነሳት ይገባል፡

9ኛ.የተደረገላችሁን ጥሪ ወደ ጎን በመተው ከአገዛዙ ጎን በመቆም የምትንቀሳቀሱ የጥፋት አሽክላዎች ከድርጊታችሁ መታቀብ የማትችሉ ከሆነ የማያዳግም የእርምት ርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን እናሳስባለን፡"

ድል ለአማራ ፋኖ🙏🙏
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 14:01

1,519

የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር የቢትወደድ አያሌዉ መኮነንን ብርጌድ ለ6 ተከታታይ ወራት ያሰለጠናቸዉን ልዩ ኮማንዶዎች በዛሬዉ ዕለት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ  ላይ የክ/ጦርና ከፍተኛ የእዝ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚህም መሰረት የአማራ ፋኖ በጎጃም ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ስልጠና መምሪያ ሃላፊ ኮማንዶ ናቲ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የሚዲያ ክፍል ባልደረባ ፋኖ ቃል ኪዳን ግርማዉ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም የዉጭና ዲያስፓራ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ፋኖ ሃይለ ሚካኤል ባየህ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ ግሩም ምሳሌ በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ የምረቃ ፕሮግራሙ ተከናዉኗል።

ፋኖነት አሸናፊነት

የብርጌዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ይበልጣል የዉነቱ (እሳቱ)
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

16 Feb, 11:15

1,835

🔥የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ዓርማ እና የዓርማ ትርጉም‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ የድርጅቱ ዓርማ እና የዓርማው ትርጉም ቀጥሎ ተገልጿል፤ ዓርማው የአማራን ሕዝብ መሰረታዊ መገለጫዎች ማለትም የስነ መንግሥት፣ ታሪክ፣ የኢኮኖሚ ስምሪት፣ ፍልስፍና (እሳቤ)፣ የሰላምና ነፃነት ጥበቃ፣ የመሪነትና ሀገር የማስተባበር ሚና የሚወክሉ ይዘቶች ይኖሩታል፡፡ ይህም ጋሻ፣ ክላሽ፣ ብዕር፣ የስንዴ ዘለላ፣ ዘንባባ፣ ንስር፣ መጽሐ እና ጥቁር አንበሳ ይኖረዋል፡፡ የዓርማው መደብ በጥቁርና አረንጓዴ ቀለም የሚቀመጥ ሆኖ የስያሜ ጽሑፉ በወርቃማ ቀለም ተጽፎ የመደቡ ዙሪያ ወርቃማ ቀለም ሆኖ የውስጠኛው መድብ ዙሪያ ደግሞ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ይሆናል፡፡

1.የአሳምነው ምስል፦ የሚያመለክተው አሳምነውነት የአማራ ሕዝብ ትግል ምልክትነትና ርዕዮታችን መሆኑንና ለአማራ ሕዝብ ሲባል በክብር መሰዋት ክብርና ኩራት መሆኑን ለማሳየት የተቀመጠ ነው።

2.ጋሻ እና ክላሽ፡ እነዚህ ምልክቶች ጀግንነትን እና አርበኝነትን የሚወክሉ ሲሆን ከትናንት እስከ ዛሬ የተከፈለን መስዋዕትነት እና በዘላቂነትም የህዝባችንን የሰላም እና ደህንነት ጥበቃ ባህርይ ይገልጻሉ፡፡

3.የስንዴ ዘለላ፡ ይህ ምልክት የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እና ምጣኔ ሀብትን የሚወክል ሲሆን የሕዝባችንን አራሽነት ይገልጻል::

4.ንስር፡- ዓርማው ላይ ያለው ንስር የሚያመለከተው የአማራ ሕዝብ ያለውን አርቆ አሳቢነት፣ አስተውሎትና ጠላትን የማጥቃትና የመከላከልን አቅም ለማሳየት ነው።

5.ብዕርና መጽሐፍ፡ ይህ እውቀትን፣ ምርምርን፣ ሐሳብን እና ፍልስፍናን የሚወክል ሲሆን የአማራን ዓለማዊም ሆነ መንፈሳዊ የዳበሩ ፍልስፍናዎች ይገልጻል፡፡

6.አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የቀለማት ሕብር፡ የሚያመለክተው የኢትዮጵያዊያንን የጋራ ነባራዊ ትስስርን፣ አሁናዊ ትብብርንና የወደፊት ተያያዥ እጣ ፈንታን ነው።

7.ጥቁር አንበሳ፡ የሥነ መንግሥት ወካይ ምልክት ሲሆን በሕዝብ አስተዳደር ውስጥ የመሪነትን እና ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ሚና ይገልጻል፡፡ ከኢትዮጵያዊው ጥቁር አንበሳ ጋር ሲጣመር ደግሞ ከሀገረ መንግሥት ግንባታ ጀምሮ ያለንን የመሪነት ሚና ያመለክታል፡፡

8.ወርቃማ ጽሑፍና ክብ፡ የሚያመለክተው በብሩህ ተስፋ የታጀበ እምቅ ሀብትን፣ ረቂቅ ስልጣኔን፣ ጥበብን፣ ኃይልን፣ ግብረ ገባዊነትን፣ ክብርንና እርግጠኝነትን ነው።

9.ጥቁርና አረንጓዴ መደብ፡ አረንጓዴው መደብ የሚያመለክተው የሕዝባችንን የገጸ-ምድርና የከርሰ-ምድር ሐብትና የምድሩንም አረንጓዴነት ሲሆን ጥቁሩ መደብ ደግሞ ባለፉት አምሳ ዓመታትና እስካሁን በሕዝባችን ላይ በኢትዮጵያውያንና በዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ፊት የደረሰበትን የዘር ማሳሳት፣ የዘር ማጽዳትና የዘር ፍጅትን ለማመልከት የተቀመጠ ነው፡፡

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)
ወሎ፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ፤
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 19:01

2,258

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር  ጎንደሬ በጋሻው ከፍለ ጦር ቴዎዴሮሰ ብርጌድ አሳምነው ሻለቃ በሻለቃ ይርጋ ደሴ እየተመራ በገደብጊያ ዙሪያ መሸጉ በነበረው  የጠላት ጥምር ሀይል  ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታው ሞት እና ቁሰለኛ አድርጎታል።

በተመሣሣይ  ሰዓት የጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ናሁሰናይ አዳርጌ ብርጌድ በሸለቃ ዋናው እሙሀይ እየተመራ በዳባት በመሸገው የጠላት ሀይል ላይ  መብረቃዊ ጥቃት በመክፈት ቁጥሩ ለግዜው የልታወቀ ጠላትን ሙት እና ቁሰለኛ በማድርግ አንድ የዳባት  ከተማ ክፍተኛ የብልፅግና  በልሰጣንን አንቀው የዘውት ሄደዋል::                                                                                     

በሌላ መረጃ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አደዋ ክፍለ ጦር እና  ቋራ ኦሜደላ ክፋለ ጦር በጋር በቋራ ግንባር ከጠላት ጋር  ሲፋለሙ ውለዋል ::
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 17:52

2,190

https://youtu.be/62lKQbYUuwo?si=5YMsDhA8YV3KG1u7