Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) Kanalının Son Gönderileri

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ Telegram Gönderileri

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 Abone
727 Fotoğraf
95 Video
Son Güncelleme 06.03.2025 17:16

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ tarafından Telegram'da paylaşılan en son içerikler

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 10:51

2,335

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር ልዩ መረጃዎች

ኮራችን በተመሠረተ ውሥን ቀናት ውሥጥ ኮሩ በሚንቀሣቀሥባቸው መዳረሻዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነ ድል እየተመዘገበ ነው የሚገኘው። ጦራችን በታላቁ እሥቴ ከቆማ እሥከ መካነ ኢዬሡሥ፣ ከሸምበቆች እሥከ ገና መምቻ፣ ከሾለክት እሥከ ደንጎልት፣ ከማጎት እሥከ ምክሬ፣ ከአጎና እሥከ ጉና፣ ከሊባኖሥ እሥከ ጥናፋ፣ ከልዋዬ እሥከ ግንዳ ጠመም፣ ከማሕደረ ማርያም እሥከ ልጫ፣ከጅብ አሥራ እሥከ ገላውዴዎሥ ከጋሣኝ እሥከ ደብረ ታቦር ከተማና መሠል መዳረሻዎች ላይ ለተከታታይ 4 ቀናት አውደ ውጊያ ማድረጉ ይታወቃል። ፈለገ ውባንተዎች ሀብት ንብረትን የናቁ፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የማያናውጧቸው፣ ለዳያሥፖራም ሆነ ለጠምዛዥ እጆች የማይምበረከኩ፣ ለአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት የእግር እሣቶች፣ ጎጠኝነትን ተጠይፈው ፩ አምሐራነት ልዕልና ላይ የተቀመጡ ናቸው። ለአማራዊ አንድነት ሰናይ የሆነ ምልከታን ተላብሰው ለአንድነት በራቸውን ክፍት አድርገው ለሴረኞች ቤታቸውን ጠርቅመው የዘጉ ናቸው።
   
በዛሬው ዕለትም የካቲት 26/2017ዓ.ም የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር የሆኑት ጉና ክ/ጦር፣ ኢንጅነር ሥመኘው ክ/ጦር እና ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
አለም በር ከተማ ንጋት 10:30 የጀመረው አውደ ውጊያ አድማሡን አሥፍቶ አለም ሣጋ፣ ኮሶ ማርያም፣ አምቦ፣ አሞራ ገደል፣ ሱራይ ካምፕ፣ አለም በር፣ ወጂ፣ ሥንቆና ወርቅ ሜዳ ላይ ውጊያ የተደረገባቸው ቦታዎች ናቸው። ጠዋት 1:00 ላይ አለም በር ከተማን ከአገዛዙ ወምበር ጠባቂ አካላቶች ነጻ ማድረግ ተችሏል። ጠላት ለወራት የሰራው ምሽግ በውቤ ልጆች ተደረማምሧል። ጥበበኛው የጥበብ ልጅ ታላቁ የአማራ ፋኖ መናበብን ሢከውን የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ከሰሞኑ እየተገኙ ያሉ ድሎች ምሥክር ናቸው።

ጋሳኝ
ጉና ክፍለ ጦር/መቅደላ አምባ ብርጌድ/ናደው ሻለቃ

ጋሳኝ ከተማ ንጋት 12:00 ጀምረው ከፍተኛ ትንቅንቅን በማድረግ የአገዛዙን አራዊት ሠራዊት ከጋሣኝ ከተማ አሥለቅቀው ከጋሳኝ ዙሪያ ባሉ መዳረሻዎች ውጊያ ሢያደርጉ አርፍደዋል።በዚህ ሠዓታትን የፈጀ አውደ ውጊያ ጠላት በቁሥም በአካልም ከፍተኛ የሆነ ኪሣራን አሥተናግዷል። ከጋሳኝ ወደ ደብረ ታቦር የአገዛዙ አገልግሎት ሠጪ አምቡላንሶች ቁሥለኞችን በማመላለሥ ተጨናንቀው አርፍደዋል። ጠላት ሊያደርገው የነበረው ትልቅ ራዕዩ ቅዠት ሆኖ እንዲቀር ተደርጎበታል። ከንጋት 12:00 እሥከ ቀኑ 6:00 በቆዬው አውደ ውጊያ  ታጋዮች ጠላትን አምበርክከዋል፤ ረፍርፈዋል።

               በድቅድቁ ጨለማ አብሪ ኮከብ የሆኑ የአማራ ፋኖዎች በብዛት እየተከሰቱ ነው። በዚህ ትግል ሻማ ሆነው እየቀለጡ ብርሐን እዬሠጡን፤ ክቡር መሥዋዕትነትን እየከፈሉና ለአማራነት ታምነው እየታገሉ እያለ አንዳንድ አዳፍኔዎች እና የፋኖነትን የተቀደሰ የትግል መንገድ ያልተረዱ አካላት የተሰሩ ድሎች ለሕዝብ አንዳይቀርቡ አለፍ ሢልም ባልዋሉበት ኩበት ለቀማን ሢከውኑ ይታያል። የአማራ ፋኖ መራራ ዕውነታን ይጋፈጣል። ያልሰራውን እንደሰራ አድርጎ አያቀርብም። ምክንያቱም ይህ ሠራዊት ለዕውነትና ለፍትሕ፣ ለታላቁ አማራ ሕዝብ ማንነትና ዘርፈ ብዙ ተጠዬቆች መልሥ ለመሥጠት እሥከ ሙሉ ቤተሰቡ ክቡር መሥዋዕትነትን የከፈለው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፈለግ ተከታይ የሆነ የታጋይ ሥብሥብ ነውና። በተጨማሪም ደግሞ ከሕዝብ በላይ ምሥክርነትን የሚሰጥ የለም። ማን እንደሚታገልለት ሕዝባችን ጠንቅቆ ያውቃል። ሕዝብ ዳኛ ነው ይመዝናል። በሕዝብ ቀልሎ ላለመገኘት የፋኖን የተቀደሰ የትግል መንገድ እንከተል። ሥለሆነም ለሕዝብ የወጣ አካል ሕዝባዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ መታገል እንዳለበት የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር አበክሮ ማሣሠብ ይፈልጋል። የፋኖነትን ዕንቁ የትግል መንገድም እንዲከተሉ ያሥገድዳል።  አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፋኖነትን ምሽግ ላደረጉ አካላት ቅድሚያ ልክ አለመሆናቸውን ያሥገነዝባል፤ ካልተመለሱም ተገቢውን የማሥተካከያ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል።


ትግላችን መራራ
መነሻችን መገፋት፤ መዳረሻችን ነጻነት
ድላችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን

፩ አምሐራ


አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

05 Mar, 09:08

2,335

https://youtu.be/YyasKpm--7c?si=gAFjGY0qccdsKTKo
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

04 Mar, 14:18

2,851

የብርሃኑ ጁላ ሠራዊት ሌቱን ሙሉ ሲቀጠቀጥ አደረ ።
የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ/3ኛ/አበራ ሙጨ ሻለቃ ገትራው አድራለች።
ከሁለት ቀን በፊት ብራቃት  ጋፊት ገብሬኤል አካበቢ ሰፍሮ የነበረውን ጠላት የአበራ ሙጨ ተናዳፊ ልጆች ካንፑን አሥለቅቀው   ወደ ብራቃት ከተማ አሥፈርጠው ሬሽኑን ተማርኮ የነበረው ጠላት ለቆት የነበረውን ቦታ ጨለማን ተገን አድርጎ ጋፊት ገብሬኤል ተመልሦ የሠፈረ በመሆኑ አንበሣዋ አበራ ሙጨ ሻለቃ ዛሬም ተሥባ በመግባት ቀዶ ብተና ኦፕሬሽን በተሣካ ሁኔታ ሰርታ ወጣለች።በዚህም ቁጥሩ ያልታወቀ የጠላት ሀይል ሙትና ቁሥለኛ ማድረግ ተችሏል።
ሌቱን ሙሉ ሢቀጠቀጥ ያደረው ጠላት በደረሠበት ምት  ጥዋት በማህበረሰባችን ላይ ዲሽቃ እንዲሁም የሞርተር  ቅንቡላ ሢወረውር አርፍዷል።
የኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ህ/ግንኘነት ሀላፊ
ሄኖክ አሸብር
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

04 Mar, 10:40

2,988

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ) ተጠናክሮ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ ምዕራብ ወሎ ኮር በአርበኛ ጀማል ብሬን የሚመራው ልዩ ዘመቻ ከሸህ ሁሴን ጅብሪል ክፍለጦር በቶ ብርጌድ እና ዳግም ክተት ወረ ኢሉ ክፍለጦር የተውጣጡ አሃዶች በጋራ ልጓማ ከተማ ሌሊቱን ዘልቀው በመግባት የተሳካ የከተማ ኦፕረሽን በመፈፀም ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

የካቲት 24 ለ 25/2017 ዓ.ም ልጓማ ከተማ ሌሊቱን በተደረገ ተጋድሎ በርካታ ሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና ሲደመሰስ በርካታው ቁስለኛ ሆኗል:: በዚህ ተጋድሎ ጀግኖቹ በፈፀሙት ከባድ የጉሬላ ዉጊያ የልጓማ ከተማ ሚሊሻ ፅ/ቤት ሃላፊ ከባድ ቁስለኛ ሆኗል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ ሆድ አደር ሚሊሻና አድማ ብተና የሚባሉ የአማራ ሃይሎች ከብልፅግናው መንግስት ጋር መተባበራቸዉን እስካላቆሙና ዘር ማጥፋት ከሚፈፀምበት ወገናቸው የአማራ ህዝብ  ጎን እስካልቆሙ ድረስ “ጅብ ከሚበላህ በልተኸው ተቀደስ ነውና” ለሰፊዉና ብዙሃኑ ህዝብ ህልዉና ሲባል ጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፋኖ አመራሮች ገልፀዋል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ድል ለአማራ ህዝብ
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አምሓራ)
የካቲት 25/2017 ዓ.ም
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

03 Mar, 19:30

2,991

🔥#የአማራ_ፋኖ_አንድነት_በጎንደር_ትንቅንቅ‼️

የአድዋ ክቡር ሥጦታ ዘመቻ አድዋ ኮሎኔል ታደሰ እሸቴ በዮቶር ምድር የአባቶቹን ድል እየዘከረ የራሱን አድዋ በክቡር መሥዋዕትነቱ እየጻፈ ይገኛል

በቅርቡ የተመሰረተው ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር በውሥጡ 5 ክፍለ ጦሮችን ይዟል። ጣና ገላውዴዎሥ ክ/ጦር፣ ጉና ክ/ጦር ፣ አፄ ፋሢል ክ/ጦር፣ ኢንጅነር ሥመኘው በቀለ ተወርዋሪ ክፍለ ጦርና ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር  በአንድነት ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮርን መመሥረታቸው ይታወቃል። ተቋማችን አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ባወጣው ሕግ መሠረት አንደኛ ኮሩ በተመሠረተ በትንሽ ቀናት ውስጥ ከጋሳኝ እስከ ቦምባት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለማሥቆምና የሕዝባችንን ሠላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ በመሥራት ላይ ይገኛል። ይሕንን ተከትሎም ኮራችን ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር በተለያዩ መዳረሻዎች አውደ ውጊያን እዬፈጸመ ይገኛል። ለአብነትም፦

1. ጉና ክፍለ ጦር እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ
(ከየካቲት 21-የካቲት 23/2017ዓ.ም)

በአማራ ምድር አንድ ታላቅ የነጻነት ተፋላሚ ኃይል አለ። እሱም ውባንተ አባተ ያሰለጠነው የእሥቴ ዴንሳ ተዋጊ ኃይል።
 
በአማራ ምድር ለመጥራት የከበደ ሥም አለ። እሡም እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ ይባላል። እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ የጉና ክፍለ ጦር ዋና ሕዋሥ ነው። የግሩም ተዋጊዎች ስብስብ። የግሩም አማራ ፖለቲከኞች ሥብሥብ፣ አምሐራነታቸውን አሣልፈው የማይሰጡ የዝጎራ ዕንቁ ልጆች አሉ እሥቴ ዴንሳ ላይ ዝቅታቸው አምሐራዊ ልዕልና ላይ የተቀመጠ። የወገን ጠላትም የለዬለት ጠላትም ሞክሮ አልሣካልህ ያለው በታላቁ እስቴ ዴንሣ ምድር ላይ ነው።

 እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ከፋሽስተ ናዚዝሙ የአቶ አቢይ አሕመድ አገዛዝ ጋር መደበኛ ውጊያ ከጀመረ 3 ቀናትን አሥቆጥሯል። በመጀመሪያው ዕለት አውደ ውጊያ ከመካነ ሠላም እሥከ ሾለክት፣ ከብር አደጌ እሥከ ዋንቃ ከደንጎልት እሥከ ማጎት፣ ከምክሬ እስከ ገና መምቻ ከገና መምቻ እሥከ ቆማ ፋሲለደስ አድርጎ በአገዛዙ አሉ የተባሉ ካድሬዎችን አምበርክኳል፤ ደምሥሧል። ከመካነ ሠላም በቅርብ ርቀት ፈንድቃ ከተማ ላይ የአገዛዙ ኃይል ሙሉ በሙሉ
#ተደምስሷል። የመዋጋት ሞራሉ ወድቋል። ወምበር ጠባቂ ወታደሮች ተምበርክከዋል፤ ለታላቁ አምሐራ ፋኖ እጃቸውን ሰጥተዋል። ጉና ክፍለ ጦር በአርበኛ ቢራራ ደምሤና በአርበኛ ሻምበል አምሳሉ ይመራል። ታላቁ እሥቴ ዴንሳ ብርጌድ ደግሞ በጀግኖቹ አርበኞች ወንዱአንተ አሰፋና ሻለቃ ''አዛዥ ደሣለኝ'' ይመራል። ሻለቃ ብርቃዬኹ ደምሤ፣ ሻለቃ አብራራው የሗላ፣ ሻለቃ ገብርዬ(ሸጋው ውበት)፣ ሻለቃ ፍቃዴ አለባቸው፣ ሻለቃ ገደፍ ሥንታዬሁ፣ ሻለቃ ተመሥገን ቢራራ፣ ሻለቃ ሙሉዬ፣ ሻለቃ አበበ አንለይ፣ ሻለቃ ዳንኤል ደምሤ፣ ሻለቃ ሱሪ(እንዳልክ ክፍሌ) እና ሌሎች ሻለቆች ብርጌዷን ይመራሉ በአምሐራዊ ቁመና ይመራሉ። እሥቴ ዴንሣ ለጠላትም ለወገን ጠላትም እንደ ኮሶ ትመራለች። ጠላትን በሚገባው ቋንቋ ታናግራለች።

 ዕለተ ዕሑድ የካቲት 23/2017ዓ.ም ታላቁና የዕምዬ ምኒልክ አድዋ በሚከበርበት ዕለት ለ3ኛ ቀን ተከታታይ መደበኛ አውደ ውጊያን አድርጓል ታላቁ እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ። በ3 ቀናት ተከታታይ አውደ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ኃይል ተምበርክኳል። እሥቴ ዴንሣ ጠላትን ከእሥቴ ዴንሣ ዙሪያ እሥከ መካነ ኢዬሡሥ መሐል ከተማ አሣድዷል። የመካነ ኢዬሡሥ መሐል ከተማ አደባባዮች በጥቋቁር አናብሥቶቹ እሥቴ ዴንሳዎች ተይዟል። ከአገዛዙ ወምበር ጠባቂ ታጣቂ ወታደር እሥከ ብአዴን ብልጽግና ካድሬዎች ድረሥ የተደመሰሰ ወርቃማ ድል አለ። አምሐራነት ከእሥቴ ዴንሣ ተራሮች ግርጌ አፍ አውጥቶ ይናገራል። እግር አንሥቶ ይራመዳል። ዕውነት እያሸነፈና ሐሳዊያን እየተምበረከኩ በክቡር መሥዕዋትነታችን ታላቁ አምሐራዊ የነጻነት መንገድ በአማራ የተባበሩ ክንዶች እየተሰራ ይገኛል።

ታላቁ እሥቴ ዴንሣ ብርጌድ ብር አደጌ እና መካነ ኢዬሡሥ የመከላከያ ምሽግ ላይ ገብቶ የመከላከያዎቹን፦
ም/ሻለቃ መሪ
ሻምበል መሪ
የወረዳው የሚሊሻ ጠርናፊ ኃላፊ
የብአዴን ብልጽግና የወረዳውን ካድሬዎች
የፋሽሥቱ አገዛዝ ወምበር ጠባቂ መደበኛ ወታደሮችን አምበርክኳል፤ ደምሥሧል፤ ብዙዎችን ምርኮ አድርጓል።

የአሣምነው ፅጌው ኮማንዶ ሠጩ ዋለ ሠልጣኞች ይችላሉ ይላል ታላቁ የእሥቴ ሕዝብ

ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር

1.ደብረ ታቦር ከተማ

የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ከጠዋቱ 2:00-ቀኑ 6:00 ድረሥ በደብረ ታቦር ከተማ አውደ ውጊያ አድርገዋል። የአማራ ፋኖ ውጊያውን የጀመረው ፀጉር አዲኮ፣ አዲኮ ገብርኤል፣ አዲኮ ሣር ፣ ደብረ ሢና፣ ፀጉር ኪ/ምሕረት፣ ፀጉር ሚካኤል፣ ኮሌጅ፣ መንፈሥ(መሎ ኮንዶሚኒዬም)፣ ቀበሌ 04 አሥተዳደር ፅ/ቤት፣ የድሮው ከርቸሌ ቤት(ወህኒ ቤት)፣ ኪቢአድ ሠፈር፣ ቴዎድሮሥ ክፍለ ከተማና ሌሎች መዳረሻዎች ላይ ውጊያ ፈጽሟል። በዚህ ውጊያ የአገዛዙ ጥምር ጦር በውባንተ አባተ ልጆች ተነድቷል። የአገዛዙ አራዊት ሠራዊትም የውቤን በጣም ውሥን ልጆች መቋቋም ተሥኖት ዩዜን ቦልትን ሆኖ ውሏል። የአገዛዙ ጥምር ጦር የሚባለው ወምበር ጠባቂ አራዊት ሠራዊት ሁሉ በትዕዛዝ በሚመሥል መልኩ ከአዲኮ እሥከ  ቴዎድሮሥ ክፍለ ከተማ ሮጦ ለመድረሥ ደቂቃዎችን ብቻ ፈጅቷል። በዚህ ውጊያም የተገኙ ድሎች፦
የክፍለ ከተማው ፀጥታና ደህንነት ኃላፊ የነበረው ''ደመወዝ'' ተደምሥሧል።
ድረሥልኝ ዘውዴና ሌሎች ፖሊሶችና አማራ በታኞች ከቀላል እሥከ ከፍተኛ የመቁሰል ዕጣ ፋንታ ደርሷቸዋል።
8 ሚሊሻዎችም ተማርከዋል።
ቁጥራቸው ያልታወቁ የጥምር ጦር አካላት ተደምሥሠዋል፥ ቆሥለዋል።
የብአዴን ብልፅግና አገዛዝ ያሠማራቸው አጋችና ገዳይ ታጣቂዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

በዚህ ውጊያ መሐል የፎገራ ወረዳ ፍርድ ቤት ሠራተኛ በአገዛዙ ሆነ ተብሎ ተገድሏል። የተገደለበትም አመክንዮ ከዓመት በፊት በዚህ ገዳይ ሥርዓት አላገለግልም ሢል የመንግሥት ሥራውን አቋርጦ ነበር። ለሥራ ደብረ ታቦር ከተማ በመጣበት ጊዜ አገዛዙ በቂም በቀል በዛሬው ዕለትም ርምጃ ወሥዶበታል።

2.ልጫ ከተማ
ከሣምንት በፊት የውባንተ አባተ የአብራክ ክፋይ አራት ራሡን ''ልጫ''  ከተማ ላይ በድንገት ከ40 በላይ የአገዛዙ ወምበር ጠባቂ ቡድን ፊት ለፊት ገጥሞታል። ጥበበኛው የውባንተ አባተ ልጅና 3 አጃቢዎቹ ቦታ ለመያዝ ናኖ ሰከንዶች አልፈጀባቸውም። አሥቡት 4 ለ40+ ነው። የውባንተ ግርፎች የተኮሱት 12 የጥይት አረር ብቻ ነው። 12ቱም ኢላማውን ጠብቋል። ድንገተኛ ነገር ግን ውጤታማ የሆነ። በዚህ የደቂቃዎች ውጊያ ከወገን የአማራው ኮማንዶ ሣሙኤል ባለድል ኮማንዶ ምሩቅ አንድ ደማችን ወጣት ''አዲሡ'' እጅግ በጣም ቀላል ቁሥለኛ ሆኗል። አሁን ወደ መደበኛ ትግሉ ተመልሷል።  ጠላት በ4 የውባንተ ልጆች ብርክ ብርክ ብሎት እሥቴ መካነ ኢዬሡሥ ከተማ ለመግባት ተገድዷል።

በመጨረሻም እኛ የአማራ ፋኖዎች በኢትዮጵያዊነት ሥም ፀረ አምሐራነትን የሚያራምዱ ጭምብል አጥላቂ ተኩላዎች ጊዜው እንደመሸባቸው ማሣሠብ እንወድዳለን።  አማራው አማራ ነኝ ብሎ ከመጣ አማራጩ መቀበል ነው።

ድላችን በተባበረ አምሐራዊ ክንዳችን

©የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

03 Mar, 17:32

2,884

https://youtu.be/ZQirK6oiw0Y?si=qmS-Rhlm6Pevx6uA
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

03 Mar, 14:54

3,075

የድል ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ተከታይ ውጊያ አካሂዶ በአብይ አህመድና አረጋ ከበደ ጥምር ሀይል ላይ ከፍተኛ ሰባዊና ቁሳዊ ኪሳራ አደረሰ!

በኮሎኔል ባህሩ ሚባል ዘራፊ ግለሰብ የሚመራው ምስራቅ ዕዝ 76ኛ ክፍለጦር ወደ ሜጫ ገርጨጭ ከተማ ከገባ ውዲህ እንደ ጨው እየሟሟ ይገኛል።

በትናንትናው እለት የጤና ምድህን አስከፍላለሁ ብሎ ወደ ግንባታ ቢንቀሳቀስም በቀጠናው የምትንቀሳቀሰው የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አለማየሁ ከቤ ሻለቃ አስፈርጥጣ ሰዳው ነበር። በዛሬው እለትም በድጋሜ ዘረፈ ለመፈፀም የተንቀሳቀሰውን ዘራፊ ሀይል ነበልባሏ የአለማየሁ ከቤ ሻለቅ አይቀጡ ቅጣት ቀጥታ ሙትና ቁስለኛውን አዝረክርኮ ሁሌም ወደሚደበቅበት ገርጨጭ ከተማ ገብቷል።

ከገርጨጭ ከተማ እንዳይወጣ ሽባ አድርጋ ያስቀመጠቸው አለማየሁ ከቤ ሻለቃ ሲወጣም በነበልባል መሪዎችና ተዋጊዎች እንደተርብ ነድፈው አስክሬና ቁስለኛ አስታቅፈው ይሰዱታል። ክፍለ ጦር ይዞ የገባው ሴት አጋቹ ኮሎኔል ባህሩም የክፍለ ጦሩን ቁጥር ስታንዳርድ እየቀየረው ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ሙሉሰው የኔአባት

251 ሚዲያ
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 17:17

587

የድል መረጃ!

የአማራ ፋኖ በሸዋ ሁለት ክፍለጦሮች ለሁት ተከታታይ ቀናት ባደረጉት የተቀናጀ ኦፕሬሽን በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ወሳኝ የተባለ ድል ተቀዳጁ።

የአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር ፣ ናደው ክፍለ ጦርና በቅርቡ የአማራ ፋኖ በሸዋን የተቀላቀለው እና መንዝ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ናደው ብርጌድ ከትናንት የካቲት 18/2017 ዓ/ም ነጋት ጀምሮ እስከዛሬ የካቲት 19/2017 ዓ/ም በሞረትና ጅሩ ወረዳ ከእነዋሪ ከተማ እስከ ጅሁር ከተማ ፣በደብረብርሃን ከተማ አፄ-ዘርዓያዕቆብ ክፍለከተማ ጎሸባዶ ቀበል እና እቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ለቼ ቀበሌ ፣ ኩክየለሽ ፣ ባቄሎና በርዩ ቀበሌ በባሶና ወራና ወረዳ ጭራሮ ደብር ቀበሌ በእንሳሮና ዋዩ ወረዳ አልባሳ ደነባ አንጭቆረርና መሰል አካባቢዎች ይንቀሳቀስ የነበረውን የአማራ ፋኖ በሸዋ ለመደምሰስና የሰበሰቡትን ሀብት ለወመውረስ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ቡድን በቁጥር ለመግለፅ በሚያዳግት መልኩ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አስተናግዷል።

በተለይም ትናንት መነሻውን እነዋሪ ከተማ አድርጎ መድረሻውን ጅሁር በማድረግ የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ጥምር ኃይል በአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር አባይ ሻለቃ፣በአማራ ፋኖ በሸዋ ናደው ክፍለጦር እራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ሻለቃ እና በቅርቡ የአማራ ፋኖ በሸዋን የተቀላቀለው በፋኖ ይልማ የሚመራውና መንዝ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ናደው ብርጌድ አንድ ሻለቃ በወሰዱት ስቦ በማስገባት መምታት የጠላትን ቅስም ሰብረውታል።

በዚህ ምት የተበሳጨው የአገዛዙ ጥምር ጦር ትናንት አመሻሹን ያለ የሌለ ኃይሉን በማግተልተል ዙ23 ሞርተር ዲሽቃና ብረት ለበስ ከበርካታ የቡድን መሳሪያዎች ጋር ጅሁር የገባ ቢሆንም ከንጋት 11:00ሰዓት ጀምሮ የአማራ ፋኖ በሸዋ አካል የሆኑት አባይ ሻለቃ በቅርቡ የአማራ ፋኖን የተቀላቀለው ናደው ብርጌድ አንድ ሻለቃ ወደ ጅሁር ከተማ ዘልቀው በመግባት እና ሰዓታትን የፈጀ የጨበጣ ውጊያ በማካሄድ የአገዛዙን ኃይል በርካታውን በሞት እና ከፊሉን ቁስለኛ አድርጎ በፋኖ ድል ተደምድሟል።

በቦሎ ፣ በወይራምባ ፣ በሰርጠሶስ ፣ በጫሶ ፣ በጣሶና በሌሎች ቀበሌዎች ቅንጅት የተደገው ይህ ድንቅ ኦፕሬሽን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ህዝብ አገዛዙን አንቅሮ የተፋውና ከአብራኩ ከወጡት ልጆቹ ከፋኖዎች ጋር መሆኑን የሚያሳይ ክስተት ሆኖ አልፏል።

በሌላ በኩል የአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር አዳኞቹ ሻለቃ በደብረብርሃን በቅርብ ርቀት ከምትገኘዋ ጭራሮ ደብር በመነሳት ወደ ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር እቴጌ ጣይቱ ክፍለከተማ ባቄሎና በርዩ ቀበሌዎች በመንቀሳቀስ አገዛዙን ሲያስጨንቁት ከበዞና ዘንዶጉር ቀበሌ የተነሱት የአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር መብረቁ ብርጌድ 3ኛ ሻለቃና አንበሳው ብርጌድ ነብሮ ሻለቃ ደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ልቼ ቀበሌ የሚገኘው ካምፕላይ መጠነኛ ጥቃት በመሰንዘር ኩክየለሽ ሳርያና አካባቢው የሚንቀሳቀሰውን የጠላት ኃይል ሲያርበደብዱት ውለዋል።

በሌላ መረጃ ከመሀል ደብረብርሃን ተነስቶ ወደ ሞረትና ጅሩ እነዋሪና ጅሁር ኃይል ለመጨመር የተንቀሳቀሰው የአገዛዙ ኃይል በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር አፄ-ዘርዓያዕቆብ ክፍለ ከተማ ጎሸባዶ ቀበሌና አካባቢው የአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጠር አሊ ሻለቃ በከፍተኛ ደረጃ ለአገዛዙ ስጋት በመሆኗ አገዛዙ በጭንቀት እንዲወጠር ከእንቅስቃሴው እንዲገታ አድርጋው ውላለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከመንዲዳና እና አካባቢው ለእነዋሪና ጅሁር ተጨማሪ ኃይል ያንቀሳቀሰው አገዛዙ በሲያ ደብርና ዋዩ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ደነባ ከተማ በአማራ ፋኖ በሸዋ ነጎድጓድ ክፍለጦር መብረቁ ብርጌድ 3ኛ ሻለቃ ልዩ ተወርዋሪ ቡድን በአንበሳው ብርጌድ አስራት ሻለቃ ተወርዋሪ ቡድንና በፊትአውራሪ ገበየሁ ሻለቃ ተወርዋሪ ቡድን እስከዚህ ሰዓት ድረስ እያስጨነቁት ይገኛሉ።

ክብር ለተሰውት!
"ድላችን በክንዳችን"
የአማራ ፋኖ በሸዋ የህዝብ ግንኙነት ክፍል
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 17:13

606

https://youtu.be/Lezr5ZWD1Q0?si=5e7aGfGLBZ2BxcRE
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 16:21

934

የአማራ ፋኖ በጎጃም የ24 ስዓት አበይት ሁነቶች
===ሀ/ አውደ ውጊያዎች
1/ 1ኛ ክፍለጦር  ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ በሜጫ ወረዳ ብራቃት ጋፊት ገብሬኤል በተባለ ቦታ ሰፍሮበት የነበረውን ካንፕ መቆጣጠር ችሏል።
2/ ሀዲስ አለማየሁ 7ኛ ክፍለጦር  አባይ ብርጌድ እና የክለጦሩ ተወርዋሪ ሃይል ደብረማርቆስ ቁይ መገንጠያ ላይ የነበረውን የአብይ አህመድ አሸባሪ ሃይል በደፈጣ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል።
3/በላይ ዘለቀ 8ኛ ክፍለጦር የሶማ ብርጌድ የብልፅግና ተጠባባቂ ሃይል በመሆን ያገለግሉ የነበሩ የአረጋ ከበደ እና ሸገው ምናለ ቤተሰቦች  ከፋኖ ጋር ሁኑ ተቤለው ከአመት በላዬ ቢጠየቁም እንቢ ብለው የነበር በመሆኑ ህግ ለማስከበር እቅስቃሴ በማድረግ 6 ቱን በመማረክ ፣7ክላሽ ፣1 ኢንፎርቲ እና የበርካታ ተተኳሽ ሲማረኩ ቀሪዎቹ ሩጠው መከላከያ ገብተዋል።
4/ በ5ኛ ራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም ክፍለጦር ወደ ገጠሩ ክፍል እወጣለሁ ያለው ያሰበው አሸባሪው ሃይል በጀግኖቹ ሲቀጠቀጥ ውሏል።  ከሽንዲ የተነሳው አሸባሪ ሃይል አስፍቶ ቢንቀስም ወላውሊት፣ ቆጥላን ፣ሎማን እና አንበር ላይ ከፍተኛ ምት ደርሶበታል።
=====ለ/ አቅምን የመገንባት ስራዎች ተሰርተዋል።
በ2ኛ ተፈራ ዳምጤ ክፍለጦር  ደጋዳሞት ብርጌድ  አመራርን የማብቃት ስልጠና እና የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል።
====ሐ/ ህዝብን የማንቃትና ማህበረሰባዊ ችግሮችን መፍታት

የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር በአዋበል ወረዳ የየሰንበት ቀበሌ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ አዘጋጂቶ ህዝብ እና ፋኖ  ያለውን መስተጋብር:የጎበዝ አለቆች የስራ እንቅስቃሴ እና ህዝብ ለፋኖ እያደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ አመርቂ ውይይት አድርጓል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም
አዲስትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!