MTU Postgraduate Directorate @mtupg Channel on Telegram

MTU Postgraduate Directorate

@mtupg


MTU Postgraduate Directorate (English)

Are you a postgraduate student at the Modern Technical University (MTU)? If so, you need to join the MTU Postgraduate Directorate Telegram channel, with the username @mtupg. This channel is dedicated to providing valuable information, resources, and support specifically tailored for postgraduate students at MTU. Who is it? The MTU Postgraduate Directorate is a channel created by the university to connect with and support postgraduate students. Whether you are pursuing a Master's degree or a PhD, this channel is designed to cater to your needs and help you navigate the challenges of postgraduate studies. What is it? The MTU Postgraduate Directorate Telegram channel serves as a virtual hub for postgraduate students to access important announcements, academic resources, event updates, networking opportunities, and more. By joining this channel, you will stay informed about key dates, deadlines, and academic policies that impact your postgraduate journey at MTU. As a member of the MTU Postgraduate Directorate, you will also have the chance to engage with fellow postgraduate students, share your experiences, seek advice, and build a supportive community within the university. Additionally, the channel administrators regularly post valuable tips, study resources, and career opportunities to enhance your postgraduate experience and help you achieve your academic and professional goals. Don't miss out on this valuable resource for postgraduate students at MTU. Join the MTU Postgraduate Directorate Telegram channel today by searching for @mtupg and clicking on the 'Join' button. Stay connected, informed, and empowered on your postgraduate journey with MTU!

MTU Postgraduate Directorate

13 Jan, 13:38


ለአገርአቀፍ ድህረምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈታኞች በሙሉ
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ እንደመፈተኛ ማህከል መርጣች የተመዘገባችሁ ተፈታኞች ፈተናው የሚሰጠው በቀን 7/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ሲሆን፤ የፈተናው ቦታ በሚዛን ዋናው ግቢ መሆኑን አውቃችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ:- ተፈታኞች የመፈተኛ ክፍላችሁን በቀን 6/05/2017ዓ.ም ከሰዓት ከድህረምረቃ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አቅራቢያ በሚለጠፈው ማስታወቂያ ቀድማችሁ እንድታውቁ እንዲሁም በፈተናው ወቅት የተከለከሉ ቁሳቁሶችን ማለትም ሞባይል ስልክ፣ ስማርት ሰዓት እንዲሁም ካልኩሌተር በፈተናው ወቅት ይዛችሁ እንዳትመጡ በጥብቅ እናሳስባለን::

MTU Postgraduate Directorate

13 Dec, 17:40


ማስታወሻ
ነገ ቅዳሜ ጠዋት MBA General የቅዳሜ እና እሁድ መርሃግብር ትምህርት እንደሚጀምር ለማስታወስ እንወዳለን።
ቦታ:- የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አጠገብ የሚገኘው ብሎክ 32 ህንፃ ላይ

MTU Postgraduate Directorate

11 Dec, 08:23


የMaster of Business Administration (MBA General ) አዲስ ተማሪዎች
ሲሰጥ የነበረው የብሪጂንግ ኮርስ ስለተገባደደ፤ ከፊታችን ቅዳሜ ( 5/04/2017ዓ.ም) ጀምሮ የሴሚስተሩ ትምህርት የሚጀምር ይሆናል። ስለሆነም እስከ አሁን ምዝገባ ያላደረጋችሁ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ቀድማችሁ በማከናወን በእለቱ ለትምህርት እንድትገኙ እናሳውቃለን።

MTU Postgraduate Directorate

02 Dec, 11:09


Progressive Report (Intention to submit) format

MTU Postgraduate Directorate

02 Dec, 06:46


በተለያየ ምክንያት ምረቃችሁ ለዘገየባችሁ (late graduate) ተማሪዎች
ታህሳስ 19-24/04/2017 ዓ.ም የመመረቂያ ፅሁፍ ተቋቁሞ ሳምንት ( thesis defense week) ለማድረግ ታቅዷል።
ስለሆነም የመመረቂያ ፅሁፋችሁን በቀን 11-14/04/2017ዓ.ም ማስረከብ የምትችሉ፤ የማስረከብ ፍላጎታችሁን እና የደረሳችሁበትን ደረጃ ( intention to submit/ progressive report) በሚያሳይ ቅፅ ላይ አማካሪያችሁን እና ትምህርት ክፍላችሁን በማስፈረም፤ ለድህረ-ምረቃ ዳይሬክቶሬት ቢሮ እና ለትምህርት ክፍል በቀን 30/03/2017 ዓ.ም እና 01/04/2017 ዓ.ም እንድታስረክቡ እናስታውቃለን።
ማሳሰቢያ:- ይህ ማስታወቂያ የሚመለከተው late graduate ተማሪዎችን ብቻ ነው።

MTU Postgraduate Directorate

30 Nov, 05:34


በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ባልደረባ ዶክተር ሚሊዮን አዳፍሬና ዶክተር አንዱዓለም በጋሻው የሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታችሁን በስኬት አጠናቃችሁ በመምጣታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!

MTU Postgraduate Directorate

23 Nov, 05:15


የመሸጋገሪያ ኮርስ (bridging course ) የምትወስዱ የቅዳሜ እና እሁድ የMBA General ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት Management theory and Practice፤ ነገ እሁድ Basic Economic concepts መሰጠት እንደሚጀምር ለማስታወስ እንወዳታለን።

MTU Postgraduate Directorate

20 Nov, 07:31


በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው እና በቅዳሜ እና እሁድ መርሃግብር ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ፤ ምዝገባ የሚከናወነው ሐሙስ እና ዓርብ (12&13/03/2017ዓ.ም) ሲሆን የMPH in Epidemiology ተማሪዎች በአማን ካምፓስ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪጅስትራር፤ የቅዳሜ እና እሁድ የMBA General ተማሪዎች በዋናው ግቢ ሪጅስተራር መሆኑን እናሳውቃለን።
ምዝገባ ክፍያ = 200ብር
በግል የምትማሩ የMPh in Epidemiology መደበኛ መርሃግብር የአንደኛ መንፈቅ ዓመት የትምህርት ክፍያ 400 ብርx 16 ክሬዲት ሃወር = 6,400 ብር፤
በግል የምትማሩ የMBA General የቅዳሜ እና እሁድ መርሃግብር ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ:-
bridging courses የምትወስዱ 700ብር x 6 ክሬዲት ሃወር =4,200 ብር
የአንደኛ መንፈቅ ዓመት ዋና ኮርስ የምትወስዱ = 700ብር x 11 ክሬዲት ሃወር = 7,700 ብር ሲሆን፤
በተቋማት ስፖንሰርነት የምትማሩ የምዝገባ ክፍያ እና የስፖንሰር የተደረጋችሁበትን ደብዳቤ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን።
ትምህርት የbridging course (መሸጋገሪያ ኮርስ) የምትወስዱ ቅዳሜ (14/03/2017ዓ.ም)፤ የመደበኛ መርሃ ግብር ሰኞ (16/03/2017ዓ.ም) ይጀምራል።

MTU Postgraduate Directorate

12 Nov, 15:12


List of Accepted Applicants for Registration for Master of Business Administration (MBA General) Graduate Study for the Year 2017 in Weekend Program Mizan Center

MTU Postgraduate Directorate

06 Nov, 06:17


ማብራሪያ ሌሎች የድህረምረቃ አመልካቾችን በተመለከተ:-
በመደበኛው መርሃግብር Environmental Science ለመማር ያመለከቱት
1. Hussen Kedir Adem
2. Tesfatsion Doforo
3. Shambel G/Mariam
4. Solomon Teka ሲሆኑ፤
በቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብር MPH in Epidemiology ለመማር ያመለከቱ:-
1. Yimer Yimam
2.Betelihem Getachew
3. Wasihun Alemayehu
4. Zerubabel Girma Tesso
5. Hasna Solomon Fereja
በMBA General የቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብር ለመማር ያመለከቱ:-
1. Esubalew Assefa
2. Gichew Abera
3. Dr. Ashebir Kochito
4. Abrham Ayalew
5. Besumiheret Birhanu
6. Eyob Tesfaye Desalegn
7. Amrawit Abese ናቸው። ይህም በመደበኛው መርሃግብር የሚያስፈልገው 5 ተማሪዎች እንዲሁም በቅዳሜ እና እሁድ 10 ተማሪዎች በሁሉም ትምህርት መስክ አልተገኘም።
ስለሆነም ለአመልካቾች እድል ለመስጠት እስከ ነገ ሐሙስ ድረስ ለመጨረሻ ጊዜ ተጨማሪ አመልካቾችን የምንጠብቅ ይሆናል ከዚህ ውጪ ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች በመደበኛው መርሃ ግብር ቀይረው መማር እንዲችሉ እናመቻቻለን።

MTU Postgraduate Directorate

05 Nov, 18:15


List of Eligible applicants for registration

MTU Postgraduate Directorate

31 Oct, 12:53


ማስታወቂያ
በተለያየ ምክንያት (በውጤት ማነስ፣ ህመም፣ ወሊድ፣ ማህበራዊ ችግር እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች) በህጋዊ መልክ የድህረምረቃ ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁ ተማሪዎች መረጃችሁን በመያዝ ነገ አርብ (22/02/2017ዓ.ም) የድህረምረቃ ቢሮ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

MTU Postgraduate Directorate

28 Oct, 06:32


ሰላም
ከላይ በአስታወቅነው ማመልከቻ መማር የምትፈልጉ አመልካቾች፤ ስም ዝርዝራችሁን ለሬጅስትራር ለማስተላለፍ ያመች ዘንድ
1. ስም እስከ አያት
2. ፆታ
3. የመረጣችሁት የትምህርት አይነት
4. ፕሮግራም (Regular/weekend)
ዛሬ በ0911911808 በአጭር ፅሁፍ መልህክት ሁላችሁም አሳውቁኝ።

MTU Postgraduate Directorate

25 Oct, 05:50


ከዚህ ቀደም በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ መጠየቃችን ይታወቃል። ነገር ግን በሁሉም የትምህርት አይነቶች ላይ በቂ አመልካች (5 ለመደበኛ፤ 10 ለቅዳሜ እና እሁድ) አልተገኘም። ስለሆነም በመደበኛው መርሃ ግብር በአንፃራዊነት የተሻለ አመልካች በተገባቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የትምህርት አይነቶች አምስት እና ከዛ በላይ አመልካች በተገኘባቸው ለመማር የሚያመለክቱ ከሆነ የሚከፈቱ መሆኑን እንገልፃለን:-
1. MPh in Epidemiology
2. MSc in Environmental Science
3. MBA General
በቅዳሜ እና እሁድ መርሃ ግብር 10 እና ከዛ በላይ አመልካች የሚገኝ ከሆነ እነዚህ በአንፃራዊነት የተሻለ አመልካች ያመለከተባቸው የትምህርት አይነቶች የሚከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን:-
1. MPh in Epidemiology
2. MBA General
ስለሆነም የማይከፈቱ ትምህርት አይነቶች ላይ የአመለከታችሁ አመልካቾች ከላይ በተዘረዘረት የትምርት አይነቶች ላይ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የምዝገባው ጊዜ ሰኞ እና ማክሰኞ (18&19/02/2017) መሆኑን እንገልፃለን።

MTU Postgraduate Directorate

10 Oct, 14:11


በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
እንደሚታወቀው በዚህ እና በባለፈው ዓመት ኤንጋት (NGAT) ያለፉ እና በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የድህረምረቃ ለመማር ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ለድህረምረቃ ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማስታወቃችን ይታወሳል። ነገር ግን የሪፖርት ቀኑ ካለፈም በኃላ አመልካቾች እየጠየቁን ስለሆነ፤ እስከ ነገ አርብ ድረስ ከዚህ ቀደም ሪፖርት ያላደረጋችሁ አመልካቾች በዚህ(0911911808) ስልክ ቁጥር ስማችሁን፣ መማር የምትፈልጉትን ትምርህት እና ፕሮግራም በመግለፅ በአጥር ፅሁፍ መልህክት (SMS) ብቻ እንድታሳውቁን እናሳስባለን።

MTU Postgraduate Directorate

30 Sep, 18:26


ጤና ይስጥልኝ
በዩኒቨርስቲያችን ለመማር ከዚህ ቀደም ያመለከታችሁም ሆነ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተፈትናችሁ የድህረምረቃ የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ እና የድህረምረቃ ትምህርታችሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ፍላጎት ያላችሁ መማር የምትፈልጉን የትምህርት ዓይነት እንዲሁም ፕሮግራም በመግለፅ የኤንጋት ሰርተፍኬታችሁን በመያዝ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን።
ሪፖርት የማድረጊያ ቀን:- 22-24/01/2017ዓ.ም

MTU Postgraduate Directorate

23 Sep, 05:39


ውድ የድህረምረቃ ተፈታኞች የፈተና ውጤት በተቀመጠው መስፈንጠሪያ በመግባት መመልከት እንደምችሉ እናሳውቃለን።
#NGAT_Result

Link:
https://result.ethernet.edu.et/ngat_result

በማስፈንጠሪያው በመግባት በPdf የውጤት ሰርተፍኬቱን ያውርዱ
Stay tuned for updates and Share

MTU Postgraduate Directorate

23 Sep, 05:30


#NGAT_Result

Those of you who took NGAT can now access your results using the link below by inserting your NGAT "username" found on your ticket

Pass mark፡ 50/100

Link:
https://result.ethernet.edu.et/ngat_result

MTU Postgraduate Directorate

18 Sep, 09:23


ውድ የድህረምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈታኞች እስካሁን የፈተናው ውጤት በትምህርት ሚኒስቴር ያልተገለፀ ሲሆን፤ ውጤት ከማህከል ሲገለፅ በተመዘገባችሁበት ፖርታል ገብታችሁ እንድታረጋግጡ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

MTU Postgraduate Directorate

15 Sep, 08:34


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ 1499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

MTU Postgraduate Directorate

10 Sep, 17:57


🌼🌼Wishing you a happy new year with the hope that you will have many blessings in the year to come!🌼🌼

MTU Postgraduate Directorate

07 Sep, 09:40


NGAT ለመፈተን በዩኒቨርስቲያችን ከተመዘገቡት 412 ውስጥ 360 ተፈትነዋል
በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በሚዛን ዋናው ካምፓስ ለሁለት ቀናት በሶስት ዙር የNGAT ፈተና በ7 መፈተኛ ክፍሎች ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ተሰጥቷል።
በዚሁም መሰረት በፈተና ጣቢያ በመጀመሪያው የፈተና ቀን ነሐሴ 30/12/2016ዓ.ም ለፈተና የሚጠበቀው 182 ለፈተና የተቀመጡ 156 ናቸው።
በሁለተኛ ቀን ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ለፈተና የሚጠበቀው 230 ሲሆን 204 ተፈታኞች ፈተናውን በፈተና ጣቢያ ተገኝተው ተፈትነዋል።
በድምሩ በ2016 ዓ.ም ዩኒቨርቲያችንና ትምህርት ሚኒስቴር በመተባበር የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ያሳተፍን ሲሆን ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 412 ውስጥ 360 ተፈትነዋል።
👉ለተፈታኞች የተሳካ ውጤት የድህረምረቃ ዳይሬክቶሬት ይመኛል