ኢትዮጵያ የግጥም ቤት @mr_trump_poems Channel on Telegram

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

@mr_trump_poems


እኔና ቤቴ ግጥም የህያው ስሜት መግለጫ ከብቸኝነት ግዞት ማምለጫ መሆኑን እናምናለን፡፡ እኔና ቤቴ ግጥም ከቃላት ስደራ በላይ የእውነትና የእምነት ውጤት መሆኑን የነቆራ እና የምስጢር ዋሻ መሆኑን እናምናለን፡፡ አምነንም እነንፅፋለን!
አባላችን ይሁኑ!
°
°
°
@mr_trump_poems
ግጥሞትን ለመላክ እና ለማንኛውም አስተያየት
@termo_dynamics ን ይጫኑ።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት (Amharic)

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት የምኞቴ የፊልዝ እና ከፍታ የሚመጣጥፍ ግጥሞችን ለማንኛውም የተሻለ ውጤትና ምርመራን እና ከቃሌ ስደራ በላይ የእውነትና እምነት የሚገኝ መረጃዎችን ለመምረጥ የሚያስችልና በአስተያየት በኢትዮጵያ የተሰጣቸው ግጥም ደንቦችን እና ተለዋዋጭዎችን ይጫኑ። እናመሰረቱን @mr_trump_poems ን እና በምንም ሳይከናወኑ እንዲረዳ ለ@termo_dynamics ን ይጫኑ።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

10 Jan, 13:57


How beautiful to find a heart that loves you,without asking you for anything, but to be okay.

-Khalil Gibran

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

16 Oct, 17:56



እግሬ ወደ ጉድጓድ ፥ ነፍሴ ወደ አምላኳ ፥ ልቤ ወደ ሞቱ፥ ለመሄድ ሲቻኮል
እንደ እንቅፋት ሆኖ፥ መንገዴ ላይ አለ፥ መኖር ይሉት ተንኮል
ሞቴን እንዳልጨብጥ ፥ ለሙሉ እኔነቴ ነፍሴን እንዳልወክል
መኖር እግሬ ስር ፥ እንደ ታኮ አለ ፥ እንደ መስናክል

(ከመኖርም እሷ : ከህይወትም ፍቅሯ
እሷ እያለች ላልሞት የገባሁላት ቃል : እንዲሁም መኖሯ )

ልቤን ያደረገው...
ለሞት እንዳይጨክን ፥ እንዳይርቅ ከነፍሱ
ከቤቱ ግድግዳ ፥ ከልቡ አፀድና፥ ከፃፈው ደብዳቤ፥ በጉልህ አድምቆ ያስቀመጠው ጥቅሱ

(እንዲህ ይላል ጥቀሱ...)

''አንቺ ኖረሽ እንጂ ~ መኖር የጣፈጠ
አንቺን አይቶ እንጂ ~ ይህ ቀድሞ ሟች ልቤ ~ ህይወት የቋመጠ
መኖርማ እንደሆን !
የሟቾች እዳ ነው ~በለት ዕለት መቅለጥ ~ በጊዜ ሚከፈል
መኖርማ እንደሆን !
ልክ እንደ ጫጩት ነው ~ በትዕግስት የሚገኝ መሞት ሲፈልፈል ''

ይል ነበረ ጥቅሱ
(እውነቴን እኮ ነው...)
እሷ ኑራ እንጂ፥ ለነፍሴማ እንደሆን...
ይሻላት ነበረ፥ ሁሌ ከመታመም ፥ ያንድ ቀን ሙት መሆን ።

፦ ግዑዝኤል

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

07 Sep, 06:38


🖤💧⚰️💀

አስር ሞት ቁሟል ከ'ደጄ ~
አይኔ ላይ ያንዣብባሉ ~ በርካታ ውል አልባ ቅርፆች
በቀየው ህይወት የለችም ~
ሚሰማው...
በሬሳ ያጥንት ትፍግፍግ ~ ሚወጡ የሙታን ድምፆች።

ላሽወይና ያሟሟቀ አፍ ~ ያወርዳል የዘመን ሙሾ
ሰዉ ከሰው ቂም ተቆጣጥሯል ~ አፍርቷል የበቀል እርሾ
ለሰርግ የጣሉት ዳስ ላይ ~ ሞት ወረደበት እስክስታ
አባት በልጁ ሞት አለቀሰ ~ እናት ወደቀች ራሷን ስታ።
ተስፋ መቁረጥ ንጉስ ሆነ ~ ተስፋ ራሱ ተስፋን አጣ
ደህና ውሎ ቤቱ አይገባም ~' ደህና አውለኝ ' ሲል የወጣ።
ቄስና ሼኩም አንድ ላይ ~ ፈጣሪ ላይ አኮረፉ
" ወይ ፍረድ፤ ወይ ስልጣን ልቀቅ "~ ሲሉ ጌታቸውን ወረፉ።

ይሄውልሽ እኔ ቤት ነኝ ~ ሰፈሩ በሞት ሲታጠብ
የሟቹ ቁጥር አይሎ ~ የቀብር ቦታ ሲጣበብ
አካሌን ቀቢፀ ተስፋ ~ የስጋት ደረመን ሲያጥር
በነፍሴ ትርትር እላለሁ ~ ዙሪያዬ ኮሽ ሲል ቁጥር።

ቆይማ...
( ምንድነው እዚህ ሚሰማኝ?)

መባርቅት ያጀቡት ክላሽ ~ የመሞት አዋጅ ለፈፈ
ይሄውልሽ...
በጎኔ ጥይት አለፈ።
(ደንገጥኩ )
መስኮቴን ከፍቼ ወጣሁ ~ መንገዱን በትኩረት ማተርኩ
ወዲያው ግን (አንድ ቀን የነገርሽኝን )
'' በሬ ሳላይ መጣሁ ከዛ'ስከዚ ድረስ "
ምትል ቅኔ አስታወስኩ።

ሰፈሩ እንዳለ ወድሟል ~  አንድ ቤት የለም
የቀረ (አንድ ሰዉ የለም የቀረ)
ያ ዋርካ (አድባራችንም )...
አንገቱን ደፍቶ ለሚያየው ~ ይመስላል ያቀረቀረ።

[ ወዳንቺ ልመጣ ወሰንኩ ]

መሬት ላይ መንፏቀቅ ጀመርኩ ~ በቁሜ መራመድ ፈራሁ
ከፊቴ ያለን ሬሳ ~ ቀስ ብዬ ወደ ጎን ገፋሁ
ታውቂያለሽ....
ቢበዛ ሰባት ዓመት ልጅ ~ ሰባቴ ጥይት መቶታል
[ መንግስት ላይ ተስፋ ብንቆርጥም ~ ነገር ግን እግዚሩስ የታል?]
ከኢየሱስ ስቃይ በማያንስ - ብዙ ሰዉ እዚህ ተሰቅሏል
ያውልሽ እዛ ጋ ደግሞ
የኢዮብን ቁስል በሚያስንቅ ~አንድ ሰዉ አካሉ ቆስሏል።

ይህንን 'የሞት ደብዳቤ ' ቢቀናኝ (በህይወት ብተርፍ)
ራሴው እነግርሻለሁ
አሊያ ግን ሞት ከቀደመኝ...
ራስሽ እንድተነቢው ~ ኪሴ ውስጥ አኖረዋለሁ።
ከደረት ኪሴ ስላለ -ስትቀብሩኝ መሬት ይወድቃል
ያን ጊዜ በፍጥነት አንሺው
{ አደራ እንዳትረሺው }

፦ ግዑዝኤል
28/12/16
ረፋድ 4:37

{መኖር ሲናፍቁ ሞት ለቀደማቸው በሙሉ...}
 

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

06 Sep, 17:54


https://youtu.be/8uJExztfrJY

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

03 Sep, 10:31


አሪቲ ጎፈሬ ፡ ቄጠማ ከመከም፣
ያስራ አንዱን ደዌ ፡ ዳብሼ ልታከም
ተውረግርጋ መጣች፡ ኮረዳ መስከረም።

የሰኔ ምንጣፍ ላይ
ሃምሌን ተንተርሳ
ነሀሴዋን ለብሳ
ባያት ደሜ ሞቀ፡
አምና መጣች ብዬ
ጥላኝ መኮብለሏ፡ ካቅሌ ላይ ተፋቀ።
ጣለኝ ያልኩት ገዴ፡ ቅኔ ቀን ሲያዝብኝ፡
ጭቃዋ ላይ ወደቅሁ፡ አደይ በቀለብኝ።

ኮረዳ መስከረም...

ይቺ በላዔ-ሰብ
ይቺ ድራኩላ...
ይቺ ድራ ኩላ
የዘመን መንትያ
ክራንቻዋን ስላ፡
ያረጁ ዐይኖቿን
እንደልጅ ተ´ኩላ
አምናና ካቻምና
ያስተረፈችውን
እድሜዬን ልትበላ፤.
መጣች እፍረት የላት
መጣች ረፍት የላት።
እሷ ምን ቸገራት?
ደንግላ ስትመጣ
አቅፌ የምለቀው
ቆዳዋ ይፋጃል...
እሷ እየታደሰች
እሷ እየደምቀች
የኔ ቀን ያረጃል።

መጣች ነጋ ደግሞ
መጣሽ ነጋ ደግሞ...
ኮረዳ መስከረም...

አወይ ጅል መሆኔ
ጡትሽን ማመኔ
ዳሌ ቅንፍሽን
ልታቀፍ ማለሜ፡
ለሚሸሸኝ ገላ
እድሜ መሸለሜ፡
ባከምሽኝ በወሩ
አርጅተሽ ስትሄጂ
ደግሞ መታመሜ፣
በያመት ስትደምቂ
በያመት መክሰሜ።
መስከረም ኮረዳ
ውበትሽ ሊከዳ
ሊሄድ ሊሸሽ ገላሽ
ለምን ይሞቀኛል
ደስ ደስ ይለኛል
አካለ ቢስ ጥላሽ?

ኮረዳ መስከረም
ምን አለሽ አደንዝዝ
ያምና ክዳትሽን
ካይምሮ የሚደልዝ
«ነበር!» የሚያስረሳ
የወደቀን ፍሬ
አብዝቶ ሚያስነሳ፤

ያበረድሽው ደሜን
ከራርሞ የሚያግል
ዝንትዓለም ተኝቼሽ
ያስመሰለሽ ድንግል።

አፍዝ ምን አለሽ?

መስከረም ኮረዳ፡
በአሮጊት እስትንፋስ
በልጅ ልስልስ ቆዳ፣
የሚያውረገርግሽ
ችክችካ ድለቃው
ሄደሽ ተደምስሶ
ትዝታ እስኪቀዳ፡
እንደ አምና ካቻምናው
እስክንከዳዳ፡
እድሜ ምናባቱ
ይሄው ረጲሳ
ይኸው ረገዳ።

(ቼቼ... ሼሼ... ቼቼ)

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

02 Sep, 03:33


ያሰኘኛል ደርሶ
አቅፌሽ ባልመሸ ጊዜ ባልቆጠረ
አይንሽን እያየሁ
ጠረንሽ ዘላለም በላየ በኖረ

የት እንደሰማው ያላስታወሰውን ግጥም ለራሱ ሲያነበንብ ነው የደረሰችበት። ሲያያት ፈገግ አለ። ሳቀች።


ይዋደዳሉ
እሱ ሲነሳ ስራው ስለእሷ ማሰብ ነው።
እሷ ስትተኛ ጸሎቷ እሱን ሰላም አንቃልኝ ነው።

ሲመጣላት በአክብሮት ጎንበስ ትላለች
ግንባሯን ይስማታል
እጁን ታስታጥበዋለች
ታጥቦ ያጎርሳታል
እሷ ጎርሳ እሱ ይጠግባል
እሱ ጠግቦ እሷ ታገሳለች

ይመሻል  ይተኛሉ  ይነጋል
ህይወት ይቀጥላል
እሷ ስትነሳ የእሱ ቀን ወገግ ይላል።
ሲነጋላት ይንጠራራል
ሲንጠራራ ትነቃለች
ስትነቃለት ቀኑን ይጀምራል
ቀኑን ሲጀምር ህይወት ይጣፍጣታል

እራሱ አስነጥሶ ይማርሽ ይላታል
ህይወት ይቀጥላል
ሲሰራ ትበረታለች
ስትበረታለት ጉልበት ይሆነዋል
ጉልበት ሲያገኝ ትደሰታለች
ስትደሰት ሳቁ ይዋባል
ሳቁ ሲዋብ የበለጠ ነገዋን ያስናፍቃታል
ነገን ሲናፍቁ...    ህይወት ይቀጥላል።


ፍቅሩ ይባላል። ፍቅርተ ትባላለች።

መኖሪያ አድራሻቸውን እንዲህ ብሎ መናገር ያስቸግራል። ለዚህም ነው አንድ ቀን በድንገት ወደፈሳሽነት የተቀየሩት።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምርምር ጣቢያው ውስጥ ሦስት ነጭ ጋውን የለበሱ ሰዎች ይነጋገራሉ። ፀጉሯ መሀል ጥቁር ጣል ጣል ያለባት ፣ 50 አጋማሽ ላይ የምትገመት ትንንሽ ግን ንቁ አይኖች ያላት ሴት መናገር ጀመረች። የቡድኑ መሪ እንደሆነች ያስታውቃል።
"እንደተነጋገርነው አሁን ወሳኙ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። የምንፈልጋቸውን ሁለት ናሙናዎች አግኝተናል። አለችና 2 የናሙና መያዣ(test tube) ቀና አድርጋ አሳየቻቸው በቀኜ የያዝኩት ሴቷ ስትሆን የተቀየረችውም ወደ F8 ሞለኪውል ነው በግራ እጄ ያለው ደግሞ ወንዱ ሲሆን እሱንም ወደ B9 ቀይረነዋል። አሁን ቀጣይ ሂደቶችን መቀጠል እንችላለን አለችና ሁለቱንም ናሙናዎች አራርቃ አስቀመጠቻቸው።  ከዛም ሦስቱም ስለቀጣዩ ደረጃ እየተነጋገሩ ከክፍሉ ወጡ። ያስቀመጡበት ክፍል ግድግዳ ላይ በትልቁ የተቀመጠ ጽሑፍ እንዲህ ይላል

አቢይ አላማ : ፍቅርን በላብራቶሪ ማበልፀግ
ንዑስ አላማ : ስለ ፍቅር ባህሪያት ጥናት ማድረግ

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

በየቀኑ እየተመላለሱ በናሙናዎች ላይ የሚፈጠሩ ለውጦች ካሉ ይመዘግቡ ጀመር

የመጀመሪያ ቀን : ምንም ለውጥ የለም
ሁለተኛ ቀን : ምንም ለውጥ የለም
ትንሽ አቀራርበዋቸው ሄዱ
ሦስተኛ ቀን : ምንሞ ለውጥ የለም
አራተኛ ቀን : የተለየ ትንሽ ለውጥ ያለ መሰላቸው። ሲያጠኑትም  B9 የነበረው B8 F8 የነበረው F9 ሆኗል። ይሄም አንድ ሽራፊ አካል ከB ወደ F ሄዷል ማለት ነው።

ከዚህ ምን አየን ተባባሉ።
ከሦስቱ ውስጥ ልጅ እግር የሆነው ሁለቱንም እጆቹን ከነጩ ጋዎን ኪስ ውስጥ ከትቶ እንዲህ አለ
"ይሄ ለመፈጠር ቀናትን ወስዷል። ትንሽ ነገሮቹ እስኪስተካከልለት ባለበት ሆኖ ጠብቋል። ከዚህም ተነስተን 'ፍቅር ይታገሳል' ማለት እንችላለን ብየ አስባለሁ"
"እሺ መልካም አንተስ"  አለችው ሴቷ የቀረውን ራሰ በራውን ሰውየ። እሱም መነጸሩን እያስተካከለ
"መገኛቸውን የፈለገ ብናራርቃቸውም ለመገናኘት አላስቸገራቸውም ከዚህ በመነሳት እኔ ደግሞ 'ፍቅር ርቀት አይገድበውም' እላለሁ"

"ጥሩ  የኔን ሀሳብ ለጊዜው እናቆየውና እንቀጥል።"

ጥናቱ ቀጠለ። F እስከ 10 B እስከ 7 ይደርሳሉ አንዳንዴ። ይገለባበጣሉ። ይቀባበላሉ። አንዳንዴ B ከነበረበት 9 ሲጎድል ሌላ ጊዜ ደግሞ F ከነበረበት 8 ያንሳል። ከዚህ ተነስተውም ተጨማሪ ሀሳብ አስቀመጡ
"ፍቅር የሁለቱንም ወገን ይሁንታ የሚፈልግ መስተጋብር(reaction) ነው።"

ማቀራረባቸውን በቀጠሉ ቁጥር የሞለኪውሎቹ ግንኙነት የበለጠ እየፈጠነም እየጨመረም ሄደ። አንድ ቀን ቦታ አቀያይረዋቸው ሄደው ሲመለሱ F7 B7 ሆነው ቆዩኣቸው። ይህ ማለት ከሁለቱም የወደቀ የጎደለ ቅንጣት አለ ማለት ነው። ሲፈለጉም ከናሙና ማስቀመጫዎቹ ውጭ ወድቀው አገኟቸው። ፈስሰዋል። ከዚህ ተነስታም ሴቷ የቡድን መሪ እንዲህ አለች
"ፍቅር ሁሌም የመሳሳብ የመፈላለግ ስሜት ነው። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ያንን አካል ከመናፈቅና ለማግኘት ከመጓጓት ስሜት ምንም ነገር ሊያርቅህ አይችልም።"
ራሰ በራውም በተራው
"ቦታ አቀያይረናቸው እንኳን የመገናኘት ሙከራቸውን አላቋረጡም። በየትኛውም ሁኔታ ሆነው ጥረታቸውን ቀጥለዋልና 'ፍቅር ተስፋ አይቆርጥም' ማለት እንችላለን ብየ አስባለሁ"

ልጅ እግሩን ባልደረባቸውን አንተስ ምን ትላለህ ሲሉት ፈገግ አለና "አይ ምንም" ብቻ ብሎ አለፈ። ያሰበውን ግን ማስታወሻ ደብተሩ ላይ አሰፈረ።
"ለመሄድ ቢፈልግም ያሰበው ቦታ አልደረሰም። መንገድ ተሳስቷል። መድረሻውን ስቷል በዚህ ተነስቼም 'Love is blind' ለማለት እገደዳለሁ።" ብሎ አስቀመጠ።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ምርምሩ አለቀ።
አቢይም ንዑስ አላማውንም አሳክተናል ይላሉ ተመራማሪዎቹ። እነዛ ሞለኪውሎች ሽቶ ተሰርቶባቸው በውድ ዋጋ ይሸጣሉ። F&F ሽቶ የከተማዋን ገበያ እያጨናነቀው ነው። ሲመረት ጥንድ ጥንድ ሆኖ የራሱ መለያ ያለው ሲሆን አንዱ የወንድ አንዱ የሴት ሽቶ ነው። በዘፈቀደ ይበተናል ያንን ጥንድ ያገኙ ሰዎች በየትኛውም ሰበብ ሆነው ይገናኛሉ። ፍቅር ይጀምራሉ።
የሽቶው ካርቶን ስር በቀይ የተጻፈ ማስጠንቀቂያ እንዲህ ይላል።

ባል/ሚስት የማይደርስበት ቦታ ይቀመጥ።


             አለቀ
       በአቤኒ የተጻፈ

ከዘመናት በአንዱ አመት በሆነ ወር የሆነች ቀን ላይ በሆነ ቦታ ይህ ተጽፎ ነበር።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

24 Aug, 08:16


እዩዋት
መንግሥተ ሰማያት፡
በባሕር መካከል፡ በአጥማጅ የተጣለች
በዓይነት በዓይነት፡ ዓሣዎች የያዘች
መረብ ትመስላለች፤»
ብሎ በምሳሌ ፡ ነግሮን ነበርዝ ጌታ
እንኳንም የመጣሽ
ሚስጥሩ በሙሉ፡ ስናይሽ ተፈታ።

መንግስተ ሰማያት፡ በጻድቃን ልመና
ጅማትሽ ሳይደድር፡ ቋጠሮሽ ሳይፀና
እኛኑ ለማጥመድ፡ ገና ከመጣልሽ
ስንቱን መልካምና፡ የረከሰ ለየሽ?

ተውጦ ድምፃቸው
ለስልሶ ቆዳቸው
ዓሳ ከመሰሉን፡ ከእባቡ ከጊንጡ
ስውር መርዛቸው ፡ ሊነድፉሽ ሲያወጡ
ባንቺ የተነሳ ስንቱ ተጋለጡ?

መንግስተ ሰማያት ፡ ታናሺቱ መረብ
ደፋ ቀና እያሉ፡ በዓሦቹ ወረብ
ከሚያዜሙት መሀል፡ ያጠመድሽው ዓዞ
ሲበጥስሽ አይተን፡ በጥርሱ ገዝግዞ
ከአውሬነቱ ጋር ፡ ባንቺ ተዋውቀናል
የይምሰል ሀዘኑን፡ እንባውን ንቀናል
ከእንግዲህ በኋላ፡
ያንቺ እድል ቢጠምም፡ የዘርሽ ይቀናል።

መንግስተ ሰማያት ፡
Kingdom of heaven፡ የሰውነት ወንፊት
በክብር ስትቆሚ፡ ካበጀሽ ጌታ ፊት
በምኞት በሀሳብ፡ ድርጊት በወሬ
ላቆሰለሽ ፀላይ፡ ለነከሰሽ አውሬ
Heaven መንጓለያ ፡ መረብ ነሽ ለክሱ
የጣልሽው ነውና ፡ የሚፋጨው ጥርሱ።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

21 Aug, 13:05


ያልፉልኛል ብዬ፣ ተማሪ ቀኖቼ
አስተማሪ ሆኜ ፣ ጀርባዬን ሰጥቼ
ሰሌዳው ላይ ፊቴን፣ ስቋጥር ስፈታ
ድንገት መንሾካሾክ ፣ ከጀርባ ሰምቼ፡ ዞር ስል ዝምታ...
«ማነው የሚያወራው? ወይስ ሁሉን ልምታ?»

ጥቂት ፀጥ አለና፡ ሹክሹክታው ቀጠለ 
በንዴት በግኜ፡ ዞር ስል አየሁት
«አንተ ነህ አይደለ? ...»
«የምትረብሸኝ?» ነደድኩኝ በቁጣ

«ና! ግጥም ና! ውጣ!»

(ጧ! )

ዘርጋ! ግጥም ዘርጋ!
በቀን`በር የኋሊት ፣ የታሰርኩኝ ፊጋ
ሳቢውን ጎትቼ ፣ ላሳልፍ ስፈጋ
ለምን ነው ጀርባዬ፡
ታሪክ እያነሳህ፡ የምትፈተፍተው?
ዞሬ ስሟገትህ ፡ የፊቴን እንድተው?
ኧረ ተው? ኧረ ተው... ?!

ያረድኩትን ፍስክ፡ ትናንት ቋጭቼ
ዛሬ ልፆም ብዬ፡ እህል ውሃ ትቼ
ማጣጣም ስጀምር፡ የረሀብን ጸጋ
አ'መህ ለመታወስ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ
'ካፍ አድረህ ለማግደፍ፡ ጥርስ የቀረህ ስጋ...!
ባደረ መጠዝጠዝ ፡
ባለፈ መነዝነዝ ፡ ዘርጋ ግጥም ዘርጋ...!
ዝቅ አርገው እጅህን፡ ወደኔ አታስጠጋ

(ጧ! ጧ! )

ያለፈን ለመጪው ፡ እንዳላስቆጥረው
የማላውቀውን ነው ፡ ልፅፍ የምጥረው
እድሜ ላንተ ግጥም፡ ልቅጣ ብዬ ቀረሁ!
ዝጋ ግጥም ዝጋ፣
ቆሽቴን አታጭሰው
ስትጮህ ስመታህ
ሲነደኝ ብደፋህ፡ ቤትህን ባፈርሰው
መመጠን የማይችል? ጀማሪ ሊለኝ ሰው?

ግጥም ተው! ግጥም ተው!
ሲቃህን ዋጥ አርገው
አፍንጫህን አብስ፡ እንባህን ጥረገው
ጥረግና ስማ...

ያልመጡ ቀናቴን፡ ላለፉት ልታማ
ጥበቃን በስንኝ፣ መቅረትን በዜማ
ለውሰህ ልትግተኝ፡ እረፍ አትታገል
ከአፈር ነው «እፍፍፍ» እንጂ ፣ አይወራም ከገል
ከሙት አትሟገት፡ ቀብረህ ተገላገል
ቀንጥሰው ሀረጉን፣ ስንኝህን ቀልጥም
እያልኩኝ ስዳረቅ...
ዞሬ ቀረሁ ባንተ፣ ዝጋ ዘርጋ ግጥም!

(ጧ! ጧ! ጧ! )

የፊቴ ጥቁር ነው፣ የጠፋ ሰሌዳ፡ ያልተደነገገ
ከሚሞቀኝ ትናንት፣ የማላውቀው ነገ
እፈጥራለሁ ብዬ፣ ሳወርድ ሳወጣ
በቃል ስታስቀረኝ፡ ሰይጣኔስ ቢመጣ?
በስሜት ስይዝህ
እጄ ላይ ብትሞትስ?
ውጣ ግጥም ውጣ!

(ጧ! ጧ ! ጧ! ጧ! )

Red-8

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

19 Aug, 23:04


ፃድቅ አያደርግም፡
በገዳይ መቀደም
ዝም በይ ያ'ቤል ደም!
ደርሰሽ አትጩኺ፡ እንደተበደለ
ለሁለት የጣሉት፡ ላንዱ እየታደለ
ፍቅር መተማመን፡ በእጣ ከጎደለ
የፉክክር ሜዳ፡ ከተደለደለ
ከዚያ በኋላማ፡ ሞት በዘር አይደለ?
ለሟች እና ገዳይ፡ ምን ይሰራል ድንበር
መጮህ አስቀድሞ፡
የደረሱበት ጋር፡ ላለመድረስ ነበር።

ፅጌሬዳ ቀንበጥ ፡ እሾኋ ሲወጋት
ብትጮህ እሪ ብትል፡ ተካይ ምን ያድርጋት?
እንዴት ትፀድቃለች?
እሷ ብትለሰልስ፡ ሌላውን ባትጎዳ
በዘሯ አይደለም ወይ ፡የመጣባት እዳ?

ፃድቅ አያሰኝም
በገዳይ መቀደም
ደርሰሽ አትጩኺ፡ዝም በይ ያ'ቤል ደም

እየበጠበጠ፡ ለጣለው ወላጁ
አንዴ እንደ ብርሌ፡ ከተበጀ ልጁ
ቢነቃም ባይነቃም፡ ለጠጅ የሚጋጭ
ሟችም ያው ገዳይ ነው፡ አልቀናውም እንጂ።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

19 Aug, 18:23


እንኳን ለደብረ ታቦር በዓል አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

18 Aug, 13:17


ከ'ሳተ ገሞራ
እንደማር ወለላ
በጣት
ዝቆ ማውጣት
አውጥቶ ጣት መጥባት፣
መላስ ሲንጠባጠብ
በዲን ምላስ ማርጠብ
ቀላጭ ፍሙን ማኘክ
ማኘክና ማድቀቅ
ማድቀቅና ማላም
እንደዚያች ወላድ ላም
ላስ አርጎ እሳቱን
ቻል አርጎ ፍጅቱን
መዋጥ በዝምታ
እንዲያ ነው ይቅርታ።

በእግሮቻችን ዳና
ባተምነው ጎዳና
ስንጓዝ የቀና
እንቅፋት ሲቀስፈን
ጥጉን ተደግፈን
ቁስላችንን ማፈን፤

እግራችን ምስኪኑን
ዝምታ ክኒኑን
ዋጥ አርጎ የግዱን
ተወግቶ እንዳይደማ
አቁሳዩ ሳይሰማ
ግሽልጡን ደምድሞ
ቁስል ላይ ጠምጥሞ
ካህን መሆን መፍታት
ጸሎት ለእንቅፋት
ማድረስ በዝምታ፣
እንዲያ እንጂ... መች ዋዛ?
መች ቀላል ይቅርታ?

ይቅርታ መች ቀላል?
ለሰጪ ይከብዳል
ለሰጭ ካልከበደ፡ ተቀባይ ያለምዳል
ለማዳ ተቀባይ ፡ ከርሞ ያቃልላል
ከርሞ የቀለለ፡ ይነሳል ይወድቃል
ከዚያ በኋላማ ፡ምኑ ይጠየቃል?

እንቅፋት ይረክሳል፡ እግር ይደነዝዛል
የተጠመጠመው፡ ቁስል ያመረቅዛል
ድንጋይ የበዛበት፡ ድንጋይ ልብ ያፈራል
ከዛ በኋላማ ፡ ምኑ ይነገራል?
ማን ማንን ይፈራል? ማን ለማን ይራራል?
ጠጠር ያናቀፈው፡ ዓለት ሆኖ ያድራል።

ወድቀው ሳይነሱ
ሳይዘሩ ሳያርሱ
እንደ ኦሪት መና
ይቅር ከደመና
አይውረድ ከሰማይ፤
ሲያቀሉት ይከብዳል
ይቅርታና ሲሳይ።

የሬት የኮሶና
የግራዋ ድቃይ
ሲቀምሱት በስቃይ
«ሁለተኛ!» ብለው
እንደምጥ ላይደግሙት
በወለዱት ምለው
ፍም እሳት ተረግጠው
በጥፍር አፈሩን፡ሳር ቅጠሉን ቧጥጠው
ከፍሙ ማር ቆርጠው
ጎመራ እሳት ውጠው
አምጠው አምጠው
ማቅቀው ተንሰቅስቀው፡ በጊዜ ይሁንታ
እስኪነሱ ድረስ፡ መሞት ነው ይቅርታ።

(Red-)

ይቅርታ መች ቀላል?

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

15 Aug, 20:31


https://bit.ly/3Z4mTaX

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

21 Apr, 18:13


https://youtu.be/iNaYObLUniw?si=egx88s9plKKei_fZ

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

14 Apr, 18:26


https://youtu.be/cdgwObZomNQ

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

14 Apr, 07:27


Channel photo updated

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

14 Apr, 07:26


እንኳን ደህና ቀሩ
[Red-8]

ዘጠና ዘጠኙን፡  አልጋዬ ስር ትቼ
አንዳንድ የምናፍቅ፡ ከጠፉት ሉኮቼ
ሥጭር ላቆሰሉኝ፡ ሙቼ ለፃፍኳቸው
አንድ ቀን አግኝቼ፡ ዳግም ላነባቸው፡
ወደ ወደቁበት ፡ ሀገርና  ቅዬ
ያተጫነብኝን፡ ብዕሬን ፈንቅዬ፡
መጣለሁ ያልኩኝ፡ ከሞት ተነስቼ
እኔም ክርስቶስ ነኝ፡ ለጠፉት ግጥሞቼ።

ቢሆንም ቢሆንም፡

አዳማ ፍራንኮ፡ ከእርጎ ቤቱ በቀኝ
ይመጣል እያለች፡ የምትጠብቀኝ
ያቺ ወረቀት ግን ፡ ግጥም የፃፍኩባት
እንኳን ጠፍታኝ ቀረች፡ እንኳን ቀረሁባት።

ያቺ ኮብላይ ግጥሜ፡
መነሀሪያ አጠገብ፡ ቅጥቅጡ እስኪሞላ
ፍቅሩን በመጠበቅ፡ ለፈረሰ ገላ
ለማይረካ ናፍቆት፡ ለማይቆረጥ ጥም
ሻንጣዬን አዝዬ፡ በውሃ ጥም ዝዬ፡ የደረስኳት ግጥም
ሲበቃኝ ከኪሴ፡ አጥፌ ያኖርኳት
እንኳን የወደቀች፡ እንኳንም የጣልኳት።

አንዴ በፃፈው ልክ፡ እየተሰፈረ፡
ላንዴ ባፈለቀው፡ ጥቅስ እየታሰረ
ስንቱ ፈጣሪ ነው፡ ባለበት የቀረ?
ፍጡር ተነቦ ነው ፡ አምላኩ ሚከበር ፡
ፍጡር ተነቦ ነው፡  አምላኩ ሚቀበር
እንኳንም ወደቀች...
ብትኖር እሷን ብዬ፡ እዚያው እቀር ነበር።

አፈር ልሆን ሄድኩኝ፡ እሷን ከአፈር ጥዬ
በዝናብ ርሳ፡ በጣይ ተቃጥዬ
ያስተዋወቀንን፡ መልካችንን ትተን
ተላልፈን ይሆናል፡ ይሄኔ ተያይተን።

በተፃፃፍንበት፡  በነበር መች ቆየን?
በየደረስንበት፡ እንዳዲስ ተቃኘን
እሷ በሷ ሆዬ፡ እኔ በትዝታ
ከንግዲህ በኋላ፡ ባገኛትም እንኳ ፡ ከጣልኩበት ቦታ
አትሆነኝም ሎሌ ፡ አልሆናትም ጌታ።

እሷም ብቻ አይደለች፡ ያኮራችኝ ጠፍታ...

ከሶስት ቁጥር ቶታል ፡ በታቦት ማደሪያ
ለፀሀይ ዩኒፎርም ፡ ጋርደን ሰደርያ
ሲመሽ ከገብርኤል፡ እስከ አቦ ማዞሪያ
መንገዳችን እንጂ፡ ወሬያችን ሳይበቃን
መካኒሳን አልፈን ፡ ሳርቤት በቫቲካን
ለሚያረማምዱኝ፡ ለወክ አጣጮቼ
የታጠፈች ግጥሜን፡ ከኬሴ አውጥቼ
ቆም ሄድ እያልን፡ የመንገድ ባውዛው፡ በየደመቀበት
ያነበብኩላቸው ፡ የላመች ወረቀት...
ያቺ የዋህ ግጥም፡ «አንድም ሰው እንዳይሞት!» የሚል መዝጊያ ያላት
እንኳን የትም ጠፋች፡ እንኳን የትም ጣልኳት!

« አንድም ሰው እንዳይሞት? »
አረ ባክሽ?... እውነት?
የልጅነት ግጥሜ፡ ስሚኝ ተረት ተረት...

ዮኒፎርም አውልቀው፡ ከአብሮ አደግ ርቀው
በዓለም ስቃይ ልክ፡ ልብን አተልቀው 
ከምኞት ደመና፡ በግፍ ወንጭፍ ወርደው
በወክ ካካለሉት ፡ካደጉበት ሰፈር፡ ተነቅለው ተሰደው
ተቃጥለው ከፃፉት ፡ በሀቅ በፍትሕ ጥም
«አንድም ሰው እንዳይተርፍ!»  ይማፀናል ግጥም።

እንኳን ጠፋታ ቀረች፡ ግጥሜ እንደልጅነት
ዓለሙን ሳታውቀው ፡ የተፃፈች ጀነት
በምኞት ቡርሿ፡ ሲዖል ለማቆንጀት
ስትጣጣር ያኔ፡ እንኳን ነቃሁባት፡
እንኳን የትም ጣልኳት፡ ይቺ ተረት ተረት...
የወተት ግጥሞቼ፡ እየተነቀሉ፡ ሲበቅል የስጋው
ለነከሰኝ ሁሉ፡ ሰው ብዬ ስጠጋው
እንኳንስ ልታገል፡ ስለት እንዳይወጋው...
ሞት አንሷል ብዬ ነው፡ አሁን የምሰጋው።

ምን ያቺ ብቻ...?

እየደረሳቸው፡ የመሰወር እጣ
ከሀይስኩል መድረክ፡ ፑሽኪን እስክመጣ
ከአዳማ ክበብ፡ ከግቢ እስክወጣ
ከጦቢያ በጃዝ ፡ከፒክኒክ በረንዳ
ጆሮ እየጠመድኩኝ፡ በስንኝ ልነዳ
ከኪሴ እየሳብኩኝ፡ መመለስ ዘንግቼ
የትም የጣልኳቸው ፡ ባይተዋር ግጥሞቼ

ያጡትን ለማግኘት፡ ጠፍቶ ከመመኘት
ተነፋፍቆ  ኖሮ፡ ተጣባብቆ መቅረት
ከሚባል መንትያ ፡ቀንበር ነፃ ይውጡ
ከእንግዲህ ግጥሞቼ ፡ ወደኔ እንዳይመጡ...

'ጠፍተን ያልተገኘን፡ ልጆችም ነን' ቢሉ
እንድውጣጣባቸው፡ ለተደለደሉ
ሆኜ ለተውኳቸው፡ ሆኜ ላለፍኳቸው፡ አልቀው ለተጣሉ
ላለፉት እኔዎች፡ መቃብሮች ናቸው፡ የፃፍኳቸው ሁሉ።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

11 Apr, 14:30


🥀🥀🥀ልሳምሽ🥀🥀🥀🥀🥀


ያንቺ የመልክ ቁልፍ ከናፈርሽ ውብ ነው
አንቺን ባየሁ ቁጥር ብስማት እላለው
መሳም ትችያለሽ
ሰውን ከምኞት ህልም ታነቂያለሽ
አይ አይመስለኝም
ስመሽ አታነቂም አንቺ
በዚ ውብ ከናፈር ትገያለሽ እንጂ
ግራ ተጋባሁኝ የቱ ነው እውነቱ
አንዴ እሺ በይኝ ልበል የታባቱ
የታባቱ የማር ጣእም መሳይ ከንፈር
የትናቱ የፅድቅ መንገድ የገነት በር
አይሽ አይደል ከንፈርሽን እያሰብኩኝ
ሺ ወጣሁኝ ሺ ወረድኩኝ
እንዴት ይሁን በየት በኩል ብዙ አሰብኩኝ
ከንፈርሽ ጋር እሩብ ሳልደርስ በ ምእናብ ደከምኩኝ
መላ በይኝ እሺ በይኝ
ወደ ጉንሽ ሳቢኝ ና አንዴ ሳሚኝ
ህልም መሳይ የደስታ አለም ብዙ ሀሳብ
አይገርምም ግን ይሄ ሁሉ ባንድ መሳም
አንዴ ስመሽ ይሄንን ሁሉ ካስባልሺኝ
ብትደግሚማ ሰላም ሀገር ላይ አሳበድሺኝ
ይሁን ልበድ ልባል በሽተኛ
ከንፈርሽ መዳኒት ተስሜ ልተኛ



።።።።።።።።።። ገጣሚ ጆ።።።።።።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

27 Mar, 18:24


።።።።።።  የኔ ሴት ይሁዳ ።።።።። 


እሷን ማን እንደኔ ብዬ ፎክሬያለሁ
ስልርሷ ባህሪ ከማንነቷ ጋር ተፎካክሬያለሁ
ይሄን ትበላልች ይሄን ትለብሳለች ይሄንማ ተውት እያልኩኝ
እኔ ና እሷማ ድስት እና ክዳን ነን ብዬ እዳልፎከሩኩኝ
ከኔ ውጪ ሌላ ወንድም ወንድ አይመስላት መስሎ እንዳልተሰማኝ
ግራ ጎኔ የኔ ሴት ያልኳት ልጅ ክደቷ አደማኝ
የኔነት ስሜቱ ጠልቆ እዳልተሰማኝ ስሟ ስሜ እስኪሆን
ዛሬ ሁሉም ውሸት ሁሉም ባዶ ቢሆን
  ልክ እደአፍቃሪ ትላንትን አሳቢ ትዝታ እንደያዘ እመርቃታለሁ
ያኔን አስታውሼ ቆሜ ሸኛታለሁ
አሜን በይኝ እቴ👩‍🦱
ትላንት ከልቤ ነው ያልሽበት አንደበት
ዛሬ ስትሄጅ እውነትን አያውራ ቃላት ይዛባበት
አሜን በይኝ እቴ👩‍🦱
ትላንት በቀልዶቼ ፈገግ ያልሽባቸው እኚ ውብ ጥርሶችሽ
አደል ቀልድ ሰምተው ደስታ መሀል እንኳን አይከፈቱልሽ
ትላንት መኖርያክ ነው ልቤ እንዳለልሺኝ
ዛሬ መኖርያዬን እንድጠላ አረግሺኝ
አምነቴን በልተሽ ውሸት አስተምረሽ
ፍቅርን ከልቤ ላይ ገጥለሽ አጥፍተሽ
መሄድሽ ሳያንስሽ
ካለሽበት ሆነሽ እንዴት ነው ትያለሽ
ከሄድሽ ጀምሮ እጅጉን ደልቶኛል
እንድል አጠብቂ ክደትሽ ገሎኛል
ተሰማማው አትበይ ገላይ ወዝ አለው
ህመምን የያዘ ውስጤ ግን ባዶ ነው
ብቻ ካለሽበት ከሄድሽበት ከቆምሽበት
ሀሰትን ክደትን ተይ እና እውነትን ኑሪበት


።።።።።።።። ገጣሚ ጆ @Delsima4 ።።።።።።።።።።

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

07 Mar, 20:54


! ፍቅር ለዘለአለም ትኑር !

ጀንበር መአዛ አለው ልብን የሚያበራ
ጨረቃ ቋንቋ አለው ፍቅርን የሚጠራ
እግዜር ዘመን አለው ውበት ሚሰራበት
አንቺን መሳይ ቆንጆ የሚያበጃጅበት
እያንዳንዱ ሰዐት
አንቺን ይባርካል
እያንዳንዱ ጊዜ
ለፍቅር መውደዴ
ዘለዓለም ኑሪልኝ መልካም ልደት ውዴ።

✍🏽 ዳዊት

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

07 Mar, 20:52


የልደቷ ቀን ነው
(በሰለሞን ሣህለ)
ጥቁር ደመና ነው ሰማዩን የሞላው
ነዝናዛ ዝናብ ነው ደመናው የያዘው
ፀሀይ አትታይም
የአውራ ዶሮው ጩኸት ንጋት አያበስርም
አእዋፍ በዜማ ቀኑን አልባረኩም
ይ … ህ … ሁ… ሉ … ቢሆንም
ዛሬ ልደቷ ነው
የልደቷ ቀን ነው
ስንቴ ልደት ሆነ? ስንት ቀን አለፈ?
ቃሉን ስንቴ ኑሮ ስንት ነገር ጻፈ?
ዛሬም ቃል ሊጠብቅ
ካልጋው ላይ ተነሳ እጆቹን ታጠበ ፊቱን አረጠበ
ሼልፉ ላይ ምስሏ አለ ምስሏን ሊያየው ዞረ
ምስሏ ላይ ሳቅ አለ ሳቋ ሳቁን ጫረ
ሳቋ ውስጥ ነፍስ አለ ነፍሱ ለቃል ኖረ
ጥቁር ሱፍ ለበሰ ከረባት አሰረ
መስታወት ፊት ቆመ ጸጉሩን አበጠረ
እናም እንደገና ቀናቱን ቆጠረ
መስከረም ጥቅምት ህዳር
እሑድ ማክስኞ ሐሙስ
አንድ … ሶስት … አምስት…
ልክ ነው ልክ ነው
ዛሬ ልደቷ ነው
የልደቷ ቀን ነው!!!
እንቡጥ ጽጌረዳ
ቀይ ወይን የያዘ የወይን ጠጅ ጠርሙስ
ቃል ኪዳኑ ይህ ነው እንዲ ነው ያስለመዳት
ልክ የልደቷ ቀን ይህን ነው ሚሰጣት
ዛሬ ልደቷ ነው …
ጥቋቁር ደመና ሰማዩን ቢከብም
የዘማሪ አእዋፍ ዜማ ባይሰማም
የአውራ ዶሮው ጩኸት ንጋት ባያበስርም
ይሄ ነዝናዛ ቀን የነጋ ባይመስልም
ደመናው ሸፍኗት ፀሀይ ባትታይም
ቀኑ ግን ቀኗ ነው …
ዛሬ ልደቷ ነው
የልደቷ ቀን ነው!!!
ሁሌ አስለምዷታል …
ወይን የያዘ ጠርሙስ ቀይ እንቡጥ አበባ
እኝህን ይዞ ነበር …
ከነ ሙሉ ሳቁ ከነ ሙሉ ሱፉ እቤቷ ሚገባ
እናም
ጥቁር ሱፍ ያደረገ ክራባት ያሰረ
መስታወት ፊትቆሞ ጸጉሩን ያበጠረ
ካንድም ሁለት ሶስቴ ቀናት የቆጠረ
ይህ ቃሉን አክባሪ ይህ አፍቃሪ ወጣት
ወይን የያዘ ጠርሙስ ቀይ እንቡጥ አበባ
እነዚህን ይዞ ከልቧ እንደገባ
እነዚህን ይዞ እቤቷ ሊገባ
ይሄው ከቤት ወጣ እርምጃ ጀመረ
ቀኗን ቀን ሊያደርገው ከራሱ መከረ
ቢቻል ቢሆንማ
ፀሀይን ለማውጣት ይህንን ደመና ይጠርገው ነበረ
እንዲህ ነው የሰው ልጅ ልቡ ካፈቀረ
እንዲህ ነው የሰው ልጅ ቃሉን ካከበረ
የልደቷ ቀን ነው …!
………………..
በጠዋት ተነስታ ውሀ እምትቀዳ ሴት
ከባዶ እንስራ ጋር መንገዱን አለፈች
እርሱን አቋረጠች
ደግሞም እዚያ ማዶ …
ከኳስ ሜዳው ፖል ላይ ያረፈው አሞራ
ጥቁር መንቆር ከፍቶ …
ከምጽአት ይሁን ከድንገት ሞት ጋራ
በቋንቋው አወራ በጩኸት ተጣራ
ጎዳና የሚኖር አንድ ጥቁር ውሻ …
አፉን ሽቅብ ከፍቶ አላዝኖ እያማጠ
ባንካሳ አረማመድ እርሱን አቋረጠ
ወደ ጢሻው ገባ ሄደ ሸመጠጠ
እናም ይህ አፍቃሪ ቃሉን አክባሪ ሰው
እኝን ሁሉ ምልኪ …
ባንድነት ስላየ ባሳብ ተመሰጠ
የምልኪውን ፍች ለማወቅ ቋመጠ
“ምንድን ነው? ምንድን ነው ይህ ሁሉ?”
መልስ የለም
እኝህ ሁሉ ንግር …
የንግር ፈረሶች እውነት ቢናገሩም
ሱፉ ለባሹ ወጣት አንዱን አላመነም
ቀይ እንቡጥ አበባ
ወይን የሞላው ጠርሙስ እነዚህን ይዞ
መንገዱን ቀጠለ በእምነት ታግዞ
እንቡጥ አበባ ወይን …
ወይኑ ወይኔ አበባ
አበባ -ሳቅ- እንባ
የልደቷ ቀን ነው!!!
የአእዋፋት ዜማ ለምን አልተሰማም?
በምንስ ምክንያት …
የአውራ ዶሮው ጩኸት እንደ ጥንቱ አልሆነም?
ስለምን ደመናው ፀሀይዋን ከበበ?
አንድም ምላሽ የለም ሁሉንም አሰበ
የልደቷ ቀን ነው!!!
ፀሀይ ያጣ ሰማይ ….
ድምጽ የሌለው ዶሮ …
የአእዋፋት እንጉርጉሮ…
ከባዶ እንስራ ጋር አንዲት ሴት አለፈች
አሞራ ተጣራ ጥቁር ውሻ ሄደ
ባንድነት በብዛት የሚሆነው ሁሉ
ባንድነት በብዛት የሚሆኑት ሁሉ
የልደት ቀን ሊያከብር
የሚሄድን ፍቅር እንዴት ያስከፋሉ?
ቃሉን አክባሪ ሰው …
ቃል ኪዳን ጠባቂን እንዴት ይጠላሉ?
እንደዚህ ቃል ገብቷል …
እንዲህ አስለምዷታል …
ቀይ እንቡጥ አበባ ከቀይ ወይን ጋር
ከዛ ደግሞ ፍቅር …
ከ-ዛ-ደ-ግ-ሞ- ፍ-ቅ-ር …
ከዛ … ደግሞ … ፍ...ቅ…ር…
ሁለቱም ባንድነት ይህን ያደርጋሉ
በፍቅር አንድ ሆነው እንዲ ይከውናሉ
በደመና አይደለም ባሳብ ያርጋሉ
ያን ግዜ ይሆናል የማይሆነው ሁሉ
ወጣቱ ደረሰ ያለችበት ገባ …
ቀይ ወይን አስቀመጠ ከዛም ቀይ አበባ
ከተቀመጠበት
ከዘንባባው መሃል ከጽዱ ከዝግባ
ቃል ጠባቂነቱን በእርካታ እያሰበ
ከምስሏ ዝቅ ብሎ ይህን አነበበ
“ሩጫየን ጨርሻለሁ!!!”
ቢሆንም የልደቷ ቀን ነው …
ይህን ለማድረግ ነው …
በጣር ላይ እያለች ስሟት ቃል የገባው
ቃሉን ለማክበር ነው መቃብሯ የመጣው
እናም ….
ቃሉን ያከበረ …
በዚህ ጨፍጋጋ ቀን በምልኪዎች መሀል
ቃሉ ስጋ ሲለብስ ሞትን ድል ይነሳል
የልደቷ ቀን ነው!!!

ኢትዮጵያ የግጥም ቤት

07 Mar, 20:51


ነገ ልደቷ ነው!(ልዑል ሀይሌ)

ነገ ልደቷ ነው!

ልቤ ወዴት ሄዶ ዳቦ አይቆረስም፤
አሰናዳሁላት ትቁረሰው በሷ ስም፤
.
በዕድሜዋ ቁጥር ሻማም አይበራላት፤
ምን ይጎልባታል
ብርሃን የሚያፈልቁ ጥርሶቿ እያሉላት፤
.
ነገ ልደቷ ነው!
አሰናድቻለሁ ሚቆረሰው ልቤን፤
አሰናድታዋለች
ደማቅ ፈገግታዋን ልትሰርቀው ሐሳቤን፤
.
መቼ ነው ሚነጋው?
እሱ ነው የኔ ሐሳብ የሌሊት ጥበቃ፤
መች ነው ማገኛት
ከፀሐይዋ በፊት የምትወጣው ደምቃ፤
.
እንቅልፍም አልተኛም ቢያዳፋኝም ደርሶ፤
ሕልም ሆኖ እንዳይነጥቀኝ ምኞቴን አፍርሶ፤
.
እጠብቃታለሁ
በልደቷ ዕለት ሚቆረስ ልብ ይዤ፤
ለሷ አይደለም ወይ
ግሳንግስ ኑሮዬን የመጣሁ ተጉዤ፤