Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ / @miacomputech Channel on Telegram

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

@miacomputech


በቴክኖሎጂ ዙሪያ የማማከር ሰራዎችን እንዲሁም የኮምፒውተርና የቢሮ ማሽን ጥገና፣የኔቶርክ ዝርጋታ፣የደህንነት ካሜራና የአሻራ ማሽን አቴንዳንስ ገጠማ ሌሎች የቴክኖሎጂና ተዛማች እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሁሉንም አገልግሎቶች በድርጀታችን ሚያ ኮምፒውቴክ ያገኛሉ።
👉 አስተያየትና ጥያቄ ይጻፉልን
@MiaComputechSupport
👉 በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ
📞 0933674790

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ™ / ሚያ ኮምፒውቴክ / (Amharic)

ምንድን ነው ይህ ጀንነት? ሚያ ኮምፒውቴክ ማንኛውም ኮምፒውተር የሆነውን እውነተኛ ባህሪ እና ቅናት አገልግሎቶች እንዲስበስባው ማስተርኬና መረጃዎችን በሚቀጥለው በቴክኖሎጂ ማሳያ ለመምጣት ተጠቅመን። ይህን መረጃ በድርጀታችን ያግኙ። ስለዚህም የሚያ ኮምፒውቴክ የተዛማጆችን ጠቃሚ እና መረጃዎችን ከታች እንዴት መረጃ እንደሚያበረከት አስተካክለን። በድርጀታችን የቴክኖሎጂ ብዙሪያና የእናፓና ማሽን አቴንዳንስ እና አካባቢ ፊልሞሽን ላይ መረጃዎችን ሚያ ኮምፒውቴክ ለመስራት እንዴት ሊሆን ነው ይህን እንጠቀምበት። የተዛማጅችን እስከዚህ ቻል በሚኖሩበለይ ማህበረሰብን ከተመለከተ ጊዜ አካልነሽ ታች ተቀምጧል።

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

27 Jul, 12:51


የኢትዮጵያ መንግስት ከተባበሩት አረብ ኢምሬት መንግስት ጋር በመተባበር በቀጣይ 3 አመታት 5 ሚሊየን ፕሮግራመሮችን ለማፍራት እቅድ ይዘው እንደነበር ይታወቃል።

ይህ program በEthiopia እና በunited Arab Emirate አማካኝነት ለኢትዮጵያዊያን የየቀረበ initiative ነው።

ይሄንን course አሁን ላይ በሶስት አይነት topic ታገኙታላችሁ።
1.Android developer fundamentals
2.Data scince fundamentals
3.programming fundamentals ናቸው።(detail ማብራሪያ ይዘን እንመጣለን።)

♻️ ይሄንን course ወደ ethiocoders.et በመሄድ ታገኙታላችሁ።

♻️ በየcourse መሀል technical ጥያቄዎች አሉት።

♻️ ይህ course አማካኝ ከ6-7 ሳምንት ሊፈጅ ይችላል።

♻️ መጨረሻ ላይ official certificate በነፃ ማግኘት ትችላላችሁ። ነገር ግን የሰርተፊኬሽን አሰስመንቱን ማሟላት ይኖርባችኋል።


♻️ በቀላሉ የማይገኝ ዕድል ስለሆነ እንደቀልድ አትዩት።

@MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

06 Jan, 18:10


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት እና የደስታ ይሁንላችሁ።
መልካም የገና በዓል!!


ሚያ ኮምፒውቴክ

ልዩነታችን ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት መስጠታችን ነው !!!

ስለ አገልግሎታችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
👉 አስተያየትና ጥያቄ ይጻፉልን

Telegram Inbox @MiaComputechSupport

📞 0933674790

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

24 Nov, 08:24


Toshiba
Satellite C55
Core i3
HDD 500 GB
Ram 4 GB
HAVE 4 LOGICAL PROCESSOR
Screen size 15.6"
Ultra Slim
Battery stays more than 4hr

DUBAI USED laptop
PERFECT CONDITION
👍 WITH 1 YEAR WARRANTY

💵 Price: 18,000 birr


Telegram Inbox @MiaComputechSupport

📞 0933674790 / 0940396851

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

16 Apr, 05:32


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም በጤና አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የበረከት እና የደስታ ይሁንላችሁ።
መልካም የፋሲካ በዓል!!


ሚያ ኮምፒውቴክ

ልዩነታችን ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት መስጠታችን ነው !!!

ስለ አገልግሎታችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
👉 አስተያየትና ጥያቄ ይጻፉልን

Telegram Inbox @MiaComputechSupport

📞 0933674790 / 0940396851

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

11 Apr, 07:54


በቴክኖሎጂ ዙሪያ የማማከር ሰራዎችን እንዲሁም የኮምፒውተርና የቢሮ ማሽን ጥገና፣የኔቶርክ ዝርጋታ፣የደህንነት ካሜራና የአሻራ ማሽን አቴንዳንስ ገጠማ ሌሎች የቴክኖሎጂና ተዛማች እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ሁሉንም አገልግሎቶች በድርጀታችን ሚያ ኮምፒውቴክ ያገኛሉ።
👉 አስተያየትና ጥያቄ ይጻፉልን

Telegram Inbox @MiaComputechSupport

📞 0933674790 / 0940396851

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

21 Mar, 06:36


Toshiba
Satellite C55
Core i3
HDD 500 GB
Ram 4 GB
HAVE 4 LOGICAL PROCESSOR
Screen size 15.6"
Ultra Slim
Battery stays more than 4hr

DUBAI USED laptop
PERFECT CONDITION
👍 WITH 1 YEAR WARRANTY

💵 Price: 18,000 birr


Telegram Inbox @MiaComputechSupport

📞 0933674790 / 0940396851

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

17 Mar, 10:47


ፓስፖርት ይፈልጋሉ?
Ethiopian Passport

♻️በአዲስ አሰራር እርሶ በሚፈልጉት ፍጥነት እንዲሁም በመደበኛ አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን።

የክፍያው ዝርዝር

    1.▪️ወረፋውን ጠብቀው የሚስተናገዱ ከሆነ አስቸኳይ ያልሆነ የሚፈጀው ጊዜ  Online ባለው schedule time.

☞ለአዲስ ፓስፖርት 2000 ብር
☞ለማደስ 2000 ብር
☞ የተሰርቀ/የጠፋ 4000 ብር
☞ለህፃናት 2000 ብር
☞ የተቀደደ 2000 ብር
☞ እድሜ እና ስም ለመቀየር ጊዜ ገደቡ ካለፈ 2000 ብር ካላለፈ 4000ብር

       2.▪️አስቸኳይ ከፈለጉ ያለምንም ማስረጃ/   Urgent service without any evidence letter.

🔳 For 5day price......5000birr

🔳 For 2day price......6500birr

📌 ጊዜዎን እና ብሮን ይቆጥቡ።

በአካል በመምጣት ወይም ያሉበት ቦታ ሆነው ማስሞላት ይችላሉ።


ወረፋ ለማስያዝ

http://t.me/MiaComputechSupport

         

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

17 Feb, 10:02


♻️ ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን 11 ተግባሮች
1 በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮች ማጥፋት (Airplane mode ላይ ማድረግ) Bluetooth ,main network መብረቅ ይስባል)

2 FM (ኤፍ ኤም) (በErphon) አለማዳመጥ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደአንቲና ነው የሚጠቀሙት ስለዚህ በኢርፎን ስናዳምጥ Electro magnetic ራዲየሸኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

3 ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይ አለመደመጥ ( Wifi አለመጠቀም Gaming አለመጫወት፡፡

4 Earphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ ( ምክንያቱም Normal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል የHz አለመጣጣም፡፡

5 ትልልቅ magnetic field ያላቸውን ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁ አለማስቀመጥ፡፡

6 የስልክ እስክሪን Bluelight የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brigtness መቀነስ( Blue light Fiter APp መጠቀም)

7 የባትሪ ቻርጅ በጣም low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው ጨረር መጠን ይጨምራል፡፡

8 ሞባይል ሲነጋገሩ ከጆሮዎ የተወሰነ ሴንቲሜትር ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡

9 የሞባይል ስልክ ታቅፈው አይተኙ ከአልጋ 1.8 meter ማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡

10 ነፍሰጡር ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ የጽንሱ ሕዋሳት ለ Electronics Radation እጅግ በጣም አለርጅክ ናቸው ስለዚህ አጠቃቀሙ ከጽንሱ ራቅ ባለ ስፍራ ይሁን አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረዥም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለብዎ፡፡

11 ብረት ነገር ባሉበት ቦታዎች ዙርያ ሞባይል አይጠቀሙ( ብረት የኤሌክትሪክ ማግኔቲክ ራድየሹን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል( ስለዚህ መኪና ውስጥ አውሮፕላን ውስጥ ሊፍት ውስጥ ባቡር ውስጥ ጋራጅ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ የሚጠቀሙም ከሆነ በአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡

በተለይ እድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይመረጣል፡፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎችን በእጅጉ ይጎዳል፡፡ በበለጸጉ ሃገሮች ከ15 ዓመት በታች የልጆች ሞት የሚከሰተው በጭንቅላት እጢ አማካኝነት ነው፡፡አባክዎ በተቻለ መጠን ራስዎን ይጠብቁ።

ለተጨማሪ መረጃ ወደ ቻናላችንን ጎራ ይበሉ
https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

28 Nov, 02:41


አንድ የሞባይል አገልግሎት ቁጥርን አሁን በአንድ ጊዜ በተለያዩ ስልኮች/ መሳሪያዎች መጠቀም ተችሏል!

እጅዎ ላይ ባለው ቁጥር ወይም በአዲስ ቁጥር ለመጠቀም ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ጐራ ብለው መልቲ ሲም ብለው ይጠይቁ!

አገልግሎቱ አንድን የሞባይል ቁጥር በመጠቀም በአንድ ጊዜ በተለያዩ ቀፎዎች/ዲቫይሶች በተመሳሳይ ጊዜ የድምጽ ጥሪ፣ መልዕክት እና ዳታ አገልግሎቶችን መጠቀም የሚያስችልዎ ሲሆን ለግለሰብ ደንበኞች እስከ 3 ለድርጅት ደንበኞች ደግሞ እስከ 10 ተመሳሳይ ቁጥር ያለው ሲም ካርድ በመግዛት መጠቀም ይቻላል።

👉 Contact us @MiaComputechSupport

📱 Call us +251933674790

https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

22 Nov, 12:54


Dell 755 Power Supplay

ETB 1100 Birr

Desktop Dell 755,760,780 Orginal Power Supply

Description Desktop Dell 755,760,780 Orginal Power Supplay

Electronics type accessory

Brand Dell

Usage condition slightlyused

Latitude 9.032284487663224

Longtude 38.842337764799595

👉 Contact us @MiaComputechSupport

📱 Call us +251933674790

https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

12 Nov, 11:38


👉 ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ በአግባቡ ሊተገብሯቸው የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች
በመጀመሪያ ደረጃ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ደንበኞች የባንክ ቅርንጫፍ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው ሳምንቱን ሙሉ በአመቻቸው ሰዓት ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ ያስቻሉ ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ አማራጮች ናቸው፡፡

ሁሉም ባንኮች እንደ ሞባይል ባንኪንግ፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም፣ ፖስ፣ ሲቢኢ ብር የመሳሰሉ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ለደንበኞቻቸው ያቀርባል፡፡

የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ከማድረሳቸው አንፃር ህብረተሰቡ በስፋት እየተጠቀመባቸው ይገኛል፡፡

የዲጂታል የባንክ አገልግሎቶቹ ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን የተጠናከረ የደህንነት ስርዓት አለው፡፡ ደንበኞች ከዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ የሚያጋጥም የምዝበራ ወንጀልን ለመከላከል የሚጠበቅባቸውን የደህንንት ተግባራት አውቀው በአግባቡ ሊተገብሩ ይገባል፡፡

ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የደህንንት መጠበቂያ ተግባራት ልብ ይበሉ።

♻️ የሚስጢር ቁጥርዎን በስልክዎ ውስጥ አለማስቀመጥ፣ በወረቀት ወይም በማስታወሻ ደብተር ላይ አለመፃፍ እና በአጠቃላይ ለሌላ ሰው አለማሳየት ወይም በቀላሉ በሚታይበት ቦታ ላይ አያስቀምጡ፤
♻️ የተንቀሳቃሽ ስልክዎን በተቻለ መጠን ለሌላ ሰው አይስጡ (አያውሱ)፡፡ ነገር ግን ለሌላ ሰው የሚሰጡ ወይም የሚቀይሩ ከሆነ ግን ስልኩ ላይ ያለውን የየዲጂታል ባንክ አገልግሎት መጠቀሚያ መተግበሪያ እና ሌሎች የግል መረጃዎን የያዙ ጽሑፎችንና ኢሜሎችን ያጥፉ፡፡
♻️ የሚስጢር ቁጥርዎን በየጊዜው ይቀያይሩ፤
♻️ ተከታታይ የሆኑ ወይም የስልክ ቁጥርዎን የመጨረሻ ዲጂቶች የሚስጥር ቁጥር አድርገው አይጠቀሙ፣
♻️ በስልክ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎን አይስጡ፣
♻️ ሞባይል ሲጠፋብዎ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲቋረጥ ያስደርጉ፣
♻️ የሚጠቀሙበት ኮምፒዩተር ሁሌም የቫይረስ መከላከያ እንዳለው ያረጋግጡ፤
♻️ ሂሳብዎ ላይ ስላለ እንቅስቃሴ ጥርጣሬ ሲኖር ለባንኩ ወዲያውኑ ያሳውቁ፤
♻️ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን (links) አይክፈቱ፤
♻️ የባንክ አገልግሎት በሚጠቀሙባቸው ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ የማይታወቁ መተግበሪያዎችን አይጫኑ፤
♻️ አገልግሎት ካገኙ በኋላ አስፈላጊውን ቅደም ተከተል በመከተል ዘግተው ይውጡ፡፡
https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

14 Oct, 06:59


DV 2024 እንዴት ራሳችን መሙላት እንችላለን?
በጥያቂያቹ መሰረት ዲቪ 2024 ለመሙላት መከተል ያለብንን መንገዶች እነሆ
›በመጀምሪያ ዲቪ መሙላት የምንችለዉ ከ መስከረም 27,2015 በኢትዮጵያ ወይም በፈረንጆች ኦክቶበር ሀሙስ 07/2022 ጀምሮ ህዳር 09/2022 ለሊት 6፡00 ድረስ ብቻ ነው።
DV-2024 Program: Online Registration
DV-2024 Program: The online registration period for the DV-2024 Program begins on Wednesday, October 7, 2022 at 12:00 noon, Eastern Daylight Time (EDT) (GMT-4), and concludes on Tuesday, November 09, 2022 at 12:00 noon, Eastern Standard Time (EST) (GMT-5). Individuals who submit more than one entry during the registration period will be disqualified.
DV-2024 Program Instructions

›የዲቪ ፎርሙን ከመሙላታችን በፊት ማሟላት ያሉብን ነገሮች፦
እያንዳንዱ የ DV አመልካች የትምህርት / የሥራ ልምድ ማሟላት አለበት
ማለትም
በ ፕሮግራሙ መሰረትም-
• ቢያንስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ተመጣጣኝ, የ 12 ዓመት ትምህርት
በሚገባ ያጠናቀቀ / ያጠናቀቀች።
ወይም
• ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የሁለት አመት የሥራ ልምድ ያለው።
•ጉርድ ፎቶ ግራፍ
በመቀጠልም
www.dvlottery.state.gov በሚለው ዌብ ሳይት መግባት
›ዌብ ሳይቱ ዉስጥ ገብተን Entry ሚለውን በመጫን መቀጠል
በፎቶ መልክ የተቀመጠልንን Authentication code በድጋሚ በመጻፍ ወደ
ፎርም መሙያዉ መግባት።
ፎርም አሞላል
1. Name - ስም - Last/Family Name (የመጨረሻ/የቤተሰብ ስም ወይም
የአያት ስም) ፣ Middle Name- (የመካከለኛ ስም ወይም የአባት ስም) ፣
First Name (የመጀመሪያ ስም ወይም የእርሶን ስም) በፓስፖርትዎ ላይ
ያለውን ስም ሳያሳስቱ በእንግሊዝኛ መጻፍ።
2. Gender - ፆታ - ወንድ (Male) ወይም ሴት(Female) መምረጥ።
3. Birth date - የልደት ቀን - መጀመሪያ Month (ወር) ፣ Day (ቀን) ፣ Year
( ዓመት) በፈረንጆች አቆጣጠር በተሰጠው ቦታ መጻፍ።.
4. City Where You Where Born - የተወለዱበትን ከተማ.
5. Country Where You Were Born - የተወለዱበትን ሀገር
6. Country of Eligibility for the DV Program - ለ DV መርኃ-ግብር
ብቁ የሆነ ሀገር ማለትም yes ሚለዉ ላይ በመተው ማለፍ
7. Entrant Photograph - የመግቢያ ፎቶግራፍ ማስገባት
- የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ -ፎቶ ግራፉ በደንብ የሚታይ ልኬቱ 600ፒክስል
* በ600 ፒክስል የሆነ መጠኑ ከ 240 ኪሎባይት የማይበልጥ ከለር ፎቶ ግራፍ
፣JPEG Format መሆን አለበት።
8. Mailing Address - የፖስታ መላኪያ አድራሻ መሙላት
9. Country Where You Live Today - አሁን የምንኖርበትን ሀገር መምረጥ
10. Phone Number - ስልክ ቁጥር ማስገባት ለኢትዮጲያ +251 ብለን
በመጀመር ስልካችንን ማስገባት / አለማስገባትም ይቻላል
11. E-mail Address - የ ኢሜል አድራሻንን ማስገባት
12. What is the highest level of education you have achieved,
as of today?
የትምህርት ደረጃችንን መምረጥ
13. What is your current marital status?- በአሁን ሰአት ያለን የትዳር
ሁኔታ መምረጥ
14 . Number of Children - የልጅ ብዛት በቁጥር መጻፍ
እያንዳንዱ የተወለዱ ሕጻናት እንዲሁም የማደጎ ልጆች፣ የእንጀራ ልጆች
በእርስዎ ፎርም ውስጥ እያንዳንዱ ያላገቡ ህጻናት, ምንም እንኳን ልጅዎ
ከእርስዎ ጋር አብረው ባይኖሩም መሞላት አለባቸዉ።
»በመጨረሻም continue በማለት Confirmation Number ያለበትን
ወረቀት ፕሪንት በማድረግ ማስቀመጥ እና በ Confirmation Number ን
DV-2024 ሲወጣ ማየት እንችላለን።
DV-2024 Submission Confirmation : Entry success
በዚ መሰረት ፎርሙን በመሙላት እድላችሁን መሞከር ትችላላችሁ።
መልካም እድል

https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

15 Aug, 05:15


♻️ ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!



እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

30 Jun, 15:08


💻 SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?
SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።

HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው።
ኤችዲዲ መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው።

መረጃውን ለመድረስ በክንድ ላይ የተነበበ/የፃፈ ጭንቅላት ከተሽከረከረው ሳህን በላይ ይንሳፈፋል።
ሳህኑን ለማሽከርከር እና ክንዱን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግል ሞተርን ያካትታል።

ለHDD ላፕቶፖች 2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን ለዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች 3.5 ኢንች ነው።
HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።

SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።

ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም።

SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።

እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ።

አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።

HDD ከSSD ርካሽ ነው
HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው
HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል
HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል
HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው
HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል

⚠️ ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ Enter ይጫኑ.
Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

19 Jan, 13:43


♻️በጣም ጠቃሚ የሆነ 20 የኮምፒውተር አቋራጮች
------------------------------
CTRL + A - Select all
CTRL + Z – Undo
CTRL + Y - Redo
CTRL + S – Save
CTRL + C - Copy
CTRL + V - Paste
CTRL + U - Underline
CTRL + X - Cut
CTRL + B - Bold
CTRL + D - Fill down cell
CTRL + E - Center Alignment
CTRL + F - Find
CTRL + G - Go to current
CTRL + H - Replace
CTRL + I -. Italic
CTRL + J - Full justification
CTRL + K - Create hyper link
CTRL + L - Left Alignment
CTRL + M - Tab
CTRL + N - New page
CTRL + O - Open
CTRL + P - Print
CTRL + R - Fill right cell
CTRL + S - Save
CTRL + U - Underline
CTRL + V - Paste
CTRL + X - Cut
CTRL + Y - Redo
CTRL + Z - Undo
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://youtube.com/channel/UC1p52jTI9znj-4tGkTIG67A

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

17 Jan, 06:36


#ነፃ_ዋይፋይ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ፣ እንጦጦ ፣ አንድነት ፓርክ እና የወዳጅነት አደባባዮች በከፍተኛ ወጪ የዋይፋይ (WiFi) አገልግሎት ገንብቶ በነጻ ማቅረቡን ዛሬ ገልጿል።

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

15 Jan, 15:18


የምስራች ለድርጅት ደንበኞቻችን!
በርከት ላሉ ተከፋዮች በቀላሉ በአንድ ጊዜ ክፍያ በቴሌብር መፈፀም ተቻለ!

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech

Mɪᴀ Cᴏᴍᴘᴜᴛᴇᴄʜ / ሚያ ኮምፒውቴክ /

31 Dec, 19:26


♻️ቴሌግራም በተጠናቀቀው 2021 / እ.አ.አ. / ድንቅ የሚባል አመትን እንዳሳለፈ የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ ዛሬ ምሽት አሳውቀዋል።

ጥር ወር ላይ በመላው ዓለም ላይ በብዛት ዳውንሎድ የተደረገ መተግበሪያ ፣ በጥቅምት ወር በአንድ ቀን ብቻ ከ70 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተጠቃሚዎችን መቀበል የቻለ እንዲሁም በታህሳስ ወር በፍጥነት እያደገ ያለ መተግበሪያ ተብሎ መታወጁ ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ፥ " የእድገቱ ሁሉ ባለቤቶች ተጠቃሚዎቹ እንደሆኑ እናውቃለን " ያሉ ሲሆን በተጠቃሚዎች የሚሰጡትን አስተያየቶች በጥሞና በማድመጥ አመቱን ሙሉ ቴሌግራም ለተጠቃሚዎቹ የተሻለ እንዲሆን አድርገናል ብለዋል።

ቴሌግራም በተጠቃሚዎች ጥያቄ መሰረት በቻናሎች፣ ግሩፖች እንዲሁም የአንድ ለአንድ መልዕክ ልውውጥ ወቅት ሪአክሽን መስጫ (👍👎❤️😢...) እንዲሁም የመልዕክት መተርጎሚያ የተካተተበት በዓመቱ 12ኛ ዋና ማሻሻያ ተደርጎበት ተለቋል።

አዲሱ የሪአክሽን ማሻሻያ የሚሰራው የቻናሉ ወይም የግሩፑ ባለቤቶች ክፍት ሲያደርጉ ነው። እንዴት ? (ወደ ቻናሉ /ግሩፕ በመግባት Edit የሚለውን መጫን ፣ በመቀጠል Enable Reactions የሚለውን ON ማድረግ እና የሚሰጡትን Reaction መምረጥ)

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ዋናውን የቴሌግራም መተግበሪያችሁን (ባለ ሰማያዊ ምልክቱን) Update በማድረግ ማሻሻያዎቹን እንድትመለከቷቸው መልዕክት እናስተላልፋለን።

የቴሌግራም መተግበሪያችሁን Update ለማድረግ👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=org.telegram.messenger

Inbox https://t.me/MiaComputech_bot

Join us on https://t.me/MiaComputech