Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ @maryjoyethiopia Channel on Telegram

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

@maryjoyethiopia


Mary Joy Ethiopia , an Ethiopian resident charity organization, works to empower vulnerable and undeserved community groups.

Phone number 0987626262/0983636363/0983646464

facebook- Mary Joy Ethiopia

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ (English)

Mary Joy Ethiopia is a charitable organization based in Ethiopia that is dedicated to empowering vulnerable and underserved community groups. Through various initiatives and programs, Mary Joy Ethiopia aims to make a positive impact on the lives of those in need. Their work focuses on providing support and resources to individuals and families who are facing challenges and difficulties. With a mission to create a more inclusive and supportive society, Mary Joy Ethiopia is committed to making a difference in the lives of the people they serve. For more information and to get involved, you can contact them via phone at 0987626262/0983636363/0983646464 or connect with them on Facebook at Mary Joy Ethiopia.

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

11 Feb, 08:14


#ህፃናት_በልተው_ለብሰው_ደምቀው_በፍቅር_ያድጉ_ዘንድ_አለኝታ_እንሁናቸው::
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
0983636363/0911208518 ይደውሉ!
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

09 Feb, 09:31


ለአረጋውያን ምርቃትና ደስታ ምክንያት እንሁን።
መልካም ሰንበት !
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

07 Feb, 19:13


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለፍኖተ ጽድቅ መስራችና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት እያደረጉት ላለው የላቅ አስተዋፅኦ እና ድጋፍ ፍኖተ ጽድቅ ባዘጋጀው የነዳያን ምገባ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ሰርተፍኬት አበረከተ። የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ አእላፍ ጸጋዬ ደበበ ስላደረጉት መልካም ተግባር በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ህፃናት እና አረጋዊያን ሰም ከልብ እናመሰግናለን።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

07 Feb, 13:16


የዳሸን ባንክ የሰራ ሃላፊዎች በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን" ማስተባበርያ ፅ/ቤት፣ የጎዳና ህፃናት ማቆያ ማዕከል እና እየተገነባ ያለውን አስኮ ሜሪ ጆይ የመጀመርያ ደረጃ ህክምና ማዕከልን እየተስሩ ያሉ መልካም ሰራዎች ጉብኝት አድርገዋል። ስለ መልካም ተግባራችሁ በህፃናቱ እና አረጋዊያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

07 Feb, 09:49


የቻይና ፋውንዴሽን ፎር ሩላር ዴቨሎፕመንት (CFRD) የስራ ሃላፊዎች በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝታቸው ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ስነልቦናዊ እና በማህበረሰብ ድጋፍ ላይ ያደርገውን መልካም ተግባሮች ተመላክተዋል።

China Foundation for Rural Development (CFRD) Ethiopia Office visited Mary Joy Ethiopia, a local NGO with 31 years of impactful work in social, economic, and psychological support and community development. CFRD Ethiopia’s Program Manager and team engaged with Mary Joy Ethiopia’s ongoing initiatives, gaining insights into their extensive experience and contributions.
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
0983636363/0911208518 ይደውሉ!
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

06 Feb, 07:02


#ህፃናት_በልተው_ለብሰው_ደምቀው_በፍቅር_ያድጉ_ዘንድ_አለኝታ_እንሁናቸው፡፡

#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
0983636363/0911208518 ይደውሉ!
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ http://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

05 Feb, 06:50


እኛ ኢትዮጵያውያን በመልካም ስራ ስንተባበር፣ ስንረዳዳ፣ ስንተሳሰብ፣ በፍቅር፣ በአንደነት ስንኖርና ስንሰራ ብዙ በመንገድ የወደቁትን እናግዛለን፡፡
#መልካምነት_ለራስ_ነው፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
#በበጎፍቃድ #ለመመዝገብ ይህን የጎግል ፎርም ሊንክ ይጠቀሙ https://maryjoyethiopia.org/volunteer/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

26 Jan, 11:59


የኪዳነምህረት ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ማህበር አባላት የገብረስላሴ ሙት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ፒያሳ ገዳም ሰፈር የማህበረሰብ ህፃናት ማቆያ ማዕከል ከማዕከሉ አረጋውያን ጋር የምሳ ግብዣ በማድረግ አሳልፈዋል፡፡ የኪዳነምህረት ወንድማማቾች እና እህትማማቾች ማህበር አባላት በሙሉ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ነፍስ_ይማር!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

24 Jan, 08:42


አረጋውያንን በህይወት አጋጣሚ የሚደርስባቸውን ችግር ተባብረን ቤት ለቤት እንመግብ::
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

22 Jan, 14:08


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ዛሬም እንደበፊቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን በዛሬው ዕለት የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፋውንዴሽን ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

21 Jan, 09:01


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከኤምኤንጅ ፊልም ፕሮዳክሽን እና ኢንቨስትመንት ጋር በመተባበር የበዓል ድጋፍ ላይ ምርቃት
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

20 Jan, 09:13


#ደግ_ለመስራት_መቼም_ረፍዶ_አያውቅም!💚💛♥️
ኑ የርሶን ድጋፍ ሚሹ አረጋዊያን እና ህፃናትን እናግዝ።
መልካም ቀን!
#በሜሪ_ጆይ_ኢትዮጲያ_ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
#ሁሌም_ስሰጥ_የምቀበለዉ_አለ!!!
#ስፖንሰር_ለማደረግ_ይህንን_ሊንክ_ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/sponsor-child/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

18 Jan, 10:41


#እንኳን_ለብርሃነ_ጥምቀቱ_አደረሳችሁ!
****
#ሜሪጆይኢትዮጵ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም፣ በፍቅርና በአንድነት አደረሳችሁ! እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ታላቅ ምኞቱን እየገለፀ በዓላትን ስናሳልፍ ያለንን ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል እንዲሆን የዕለቱ መልዕክት ነው!

መልካም የጥምቀት በዓል ይሁንልዎ፡፡
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ!
ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

17 Jan, 11:09


*** #መደጋገፍ_ባህላችን_እናድርግ!
የአዋጭ ፋውንዴሽን በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ቤተሰቦችን ወርሃዊ ስፖንሰርሽፕ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆኑ በዛሬው ዕለት ደግሞ ተጨማሪ 22 ቤተሰቦችን በመተዋወቅ ድጋፍ የሚያደርጉላችው ቤተሰቦችን ከ100 በላይ አድርገዋል። አዲስ የተዋወቋቸውን ቤተሰቦችን ጉብኝት አድርገዋል::
የአዋጭ ፋውንዴሽን የስራ አመራሮች ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

16 Jan, 11:13


የሁለቱ አዋሾች የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 2.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። አዋሽ ባንክ እና አዋሽ ኢንሹራንስ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በአረጋውያኑና በህፃናቱ ስም እናመሰግናለን፡፡
******
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
ለበለጠ መረጃ ዌብሳይታችንን ይጎብኙ ፦ https://maryjoyethiopia.org/

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

27 Dec, 10:51


#የደስታቸው_ምንጭ_እንሁን!
ህፃናት እና አረጋዊያን ፈካ ሲሉና ሲደሰቱ ማየት እንዴት ደስ ይላል፤ የነገ ሃገር ተረካቢ ህፃናትና አረጋውያን የሚረዱበት ፕሮግራማችንን “ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያን” ብለው ይርዱ ይደግፉ አሻራዎን ያሳርፉ!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

24 Dec, 06:45


ሰዎችን ለመርዳት ገንዘብ ሳይሆን መልካም ልብ ነው የሚያሰፈልገው፡፡ ሁላችንም በአቅማችን የምንችለውን አልባሳት፣ የቤት መገልገያ ቁሳቁሶች፣ አስቤዛዎች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በጥሬ ገንዘብ እና ሌሎችን ድጋፍ በማድረግ ማሀበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ለሌሎችም መልካም አርአያ እንሁን፡፡
#ካለን_ላይ_በመስጠት_አስከፊ_ድህነትን_ድል_እናድርግ!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
0983636363/0911208518 ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

21 Dec, 05:19


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር
በክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ በይፋ ተመርቋል።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ በታሪክ አጋጣሚ ፈጣሪ በሰጠን ጊዜ የአርባ ምንጭ ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነውን ፕሮጀክት ለማስመርቅ ችለናል ብለዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ አባይነህ አበራ በበኩላቸው መልካምነት ለራስ ነው እንደሚባለው በጎነትን በማድረግ ለሌሎች አርአያ ለሆኑና በጎ ተግባር እየፈፀሙ ለሚገኘው የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያና ለመስራች እናት ለሆኑት ለሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በዞኑ ሕዝብ ስም የከበረ ምስጋና አቅርበዋል።

የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራአስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ በመጀመሪያው ምዕራፍ
10 ሺ ካሬ ላይ ለሚያርፈው የማዕከሉ ግንባታ የመስሪያ ቦታ ከመስጠት ጀምሮ ከፍተኛ የሀብት ድጋፍን ለሰጡ አካላትን አመስግነዋል።
የሜሪ ጆይ የበጎ ፍቃድ አምባሳደሮች የሆኑ አርቲስት አብራር አብዶና አርቲስት ይገረም ደጀኔ መልክት አስተላልፈዋል።

በ450 ካሬ ቦታ ላይ ያረፈው የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ የማረፊያን ክፍሎችን ጨምሮ፣የመመገቢያ አደራሽ፣ቢሮዎች፣ የዕቃ ግምጃ ክፍል፣ መፀዳጃና መታጠቢያ ክፍሎች የተካተቱበት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጨማሪ ገቢ ማስገኛና የሀብት ምንጭ የሚሆኑ የላሜራ ሱቆች የተሰሩለት ሲሆን ከ8 ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል።

በምረቃው ፕሮግራም የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ የክልል፣የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑ አርቲስቶች፣ የጋሞ አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

ምንጭ፦አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

27 Nov, 07:50


አንድ ስፖንሰር ለአንድ ህፃን
ኑ ህፃናትን ይደግፋ

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
"ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን"
"ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ"
ንግድ ባንክ አካውንት
1000005063907

በ0983 63 63 63
በ0987 62 62 62
በ0911 20 85 15
ይደውሉ

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

26 Nov, 11:51


ሲጋራ ማጨስ የሳንባ ካንሰርን ያስከትላል, ምክንያቱም
እንደ ታር፣ ፎርማለዳይድ እና ቤንዚን ያሉ ካንሰር አምጪ ኬሚካሎችን ወደ ሳንባዎች በማስተዋወቅ የሳንባ ሴሎችን ዲ ኤን ኤ ይጎዳል።
ይህ የሴል እድገትን በሚቆጣጠሩ ጂኖችን በመቀየር ካንሰርን ያበረታታል፡፡
የሳንባ ላይ እብጠትን ያስከትላል፡፡
በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያዳክማል, ይህም የካንሰር ሕዋሳት እንዲኖሩ ያስችላቸዋል፡፡
በእነዚህ ምክንያቶች ምክንያት አንድ ሰው ሲጋራ ባጨሰ ቁጥር የሳንባ ካንሰር የመያዝ እድሉ ከፍ ያለ በመሆኑ ሲጋራ ማጨስን ማቆም እንዲሁም ከሚያጨስ ሰው መራቅ አለበት፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

25 Nov, 10:02


የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራአስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ ከዶ/ር ወዳጄነህ መሀረነ ጋር በኢቲቪ ከሀ-ሶስት ፕሮግራም ላይ
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

25 Nov, 08:06


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከመርሲ ሃንድስ ኢሮፕ (Mercy Hands Europe) ግብረ ሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበር በሜሪ ጆይ ሐዋሳ ወጣቶች ማዕከል ሙሉ የዲጅታል ላይብረሪ የኢንተርኔት፣ የኮምፒውተር፣የአጋዥ መፀሀፍ እና የላይብራሪ ቢሮ እድሳት ድጋፍ አድርገዋል።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

21 Nov, 10:06


በአዲስ አበባ ምክርቤት አፈ ጉባኤ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የህግ አማካሪ የተከበሩ አቶ ተክሌ ዲዱ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን" ማስተባበርያ ፅ/ቤት፣ የጎዳና ህፃናት ማቆያ ማዕከል እና እየተገነባ ያለውን አስኮ ሜሪ ጆይ የመጀመርያ ደረጃ ህክምና ማዕከልን እየተስሩ ያሉ መልካም ሰራዎች ጉብኝት አድርገዋል። ስለ መልካም ተግባራችሁ በህፃናቱ እና አረጋዊያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

20 Nov, 10:51


እምቧ ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ከአሁን ቀደም ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለሚገኙ ህፃናት እና አረጋዊያን ድጋፍ ያደርጋል። አሁንም እንደበፊቱ ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ 200,000 ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። እምቧ ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት አባላት በሙሉ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በአረጋውያኑና በህፃናቱ ስም እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

20 Nov, 09:07


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ስፓንሰርሽፕ እና የራስ አገዝ ማህበሮችን ማቋቋም ዙርያ በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ከሚገኙ ቤተሰቦች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በስፓንሰርሽፕ (በትምህርት፣ በጤና እና በቤት ለቤት ምገባ) ዙርያ የመጡ ለውጦች እንዲሁም የራስ አገዝ ማህበሮችን ማቋቋም ዙርያ በአዲስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ከሚገኙ ቤተሰቦች ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

16 Nov, 06:43


ወጣት ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ "ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን" ማስተባበርያ ጽ/ቤት እየተሰሩ ያሉ መልካም ስራዎችን ጉብኝት አደረገ። በጉብኝቱም ሁለት ድጋፍ የሚሹ ህፃናትን በቋሚነት ወርሃዊ ስፖንሰርሺፕ ድጋፍ አድርጓል። ወጣት ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ስላደረግኸው በጎ ተግባር በህፃናቱ እና አረጋዊያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን።
#ሜሪጆይኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ"

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

15 Nov, 18:29


የአቶ እንዳለ ገብረስላሴ (ፍቅረ ስላሴ) 1ኛ ሙት አመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በጎ ፍቃደኛ አምባሳደር ጋዜጠኛ ስሜንህ ባይፈርስ እና ቤተሰቦቻቸው ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አረጋውያን ጋር የምሳ ግብዣ በማድረግ አሳልፈዋል፡፡ እንዲሁም የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።
ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ነፍስ_ይማር!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

15 Nov, 09:35


የአዲስ አበባ ቦሌ ክ/ከ አስተዳደር ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ዋና ስራ አስከያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ 30 ዓመታት ላደረጉት መልካም ተግባር( የበጎ ፍቃድ ተሳትፎ) የምስጋና ሰርተፍኬት እና የክብር ጋቢ አበርክተዋል፡፡ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

08 Nov, 07:26


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ለቢሾፍቱ ከተማ ደካ ቦራ ወረዳ ላደረገው የተቀናጀ ድጋፍ የምስጋና የምስክር ሰርተፍኬ አበረከተ። የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ የምስጋና ሰርተፍኬቱን ለቢሾፍቱ ከተማ ደካ ቦራ ወረዳ ተወካዮች አበርክተዋል። ቢሾፍቱ ከተማ ደካ ቦራ ወረዳ የስራ አመራሮች ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በህፃናቱ እና አረጋዊያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

28 Oct, 08:21


ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ህፃናት ጋር የበጎ ምግባር ጊዜዎትን በፍቅር በመረዳዳት በአንድነት የማይረሳና ጣፋጭ በማድረግ ለነገ ሀገር ተረካቢ አለኝታ ይሁኑ!
#ሳምንቱን_በመለገስ_ያሳልፉ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907
0983636363/0983646464/0911208518 ይደውሉ!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

24 Oct, 13:14


በእናንተ በጎነት' የመተሳሰብ' የመረዳዳትና የመጠያየቅ ባህል የአብሮነትን የእድገት ደረጃ ማየት ተችሏል፡፡ አሁንም ድጋፍዎ አይለን!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

23 Oct, 12:25


የደቡብ እዝ መከላከያ ሰራዊት ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ሃዋሳ አረጋዊያን ማዕከል ጉብኝት በማድረግ በማዕከሉ ለሚገለገሉ አረጋዊያን ቤተሰቦች የአልባሳት ድጋፍ አድረገዋል፡፡
በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ እና የደቡብ እዝ መከላከያ ሰራዊት ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ የደቡብ እዝ መከላከያ ሰራዊት አባላት ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

21 Oct, 08:28


ሁላችንም በአቅማችን የምንችለውን በማድረግ ማሀበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት ለሌሎችም መልካም አርአያ እንሁን፡፡
ማንኛውም ድጋፍ!
5) በስፖንሰርሽ
6) በበጎ ፍቃድ አገልግሎት
7) በቁሳቁስና በገንዘብ
8 በአልባሳት በመደገፍ አጋር ይሁኑ!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907
0983636363/0983646464/0911208518 ይደውሉ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

19 Oct, 10:14


#እንኳን_ደስ_አለህ!
*
የ10ኛው ጉማ አዋርድ አርአያ ሰብ ከያኒ አሸነፊ ተዋናይ የገረም ደጀኔ እንኳን ደስ አለህ። በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ እና በሌሎች በጎ አድራጓት ድርጅቶች የበጎ ፍቃደኛ አምባሳደር በመሆን ስለ መልካም ተግባርህ እና አገልግሎትህ ከልብ እናመሰግናለን።
#እንኳን ደስ አለህ

#ሜሪጆይኢትዮጵያ
#ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ"

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

18 Oct, 12:33


ልዩ ጋሞኛ የእናታችን ምርቃት
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907
0983636363/0983646464/0911208518 ይደውሉ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

16 Oct, 08:29


ደግ ደጉን እናስብ፤ በጎ በጎውን እንስራ መልካምነት መልሶ ይከፍለናልና።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
"ኢትዮጵያዊያን ለኢትዮጵያዊያን"
ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

14 Oct, 07:11


የልጅና የልጅ ልጅ ወግ ሲርቃቸው የአረጋውያኑም ጧሪ እንሁናቸው፡፡ሜሪጆይ አንድ ልጅ ለአንድ ቤተሰብ ጌጡ አንድ አረጋውይ ደግሞ የምርቃቱ ማህድር ነው፡ ፡ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን ብለን እንደግፍ፡፡
ማንኛውም ድጋፍ!
1) በስፖንሰርሽ
2) በበጎ ፍቃድ አገልግሎት
3) በቁሳቁስና በገንዘብ
4) በአልባሳት በመደገፍ አጋር ይሁኑ!
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907
0983636363/0983646464/0911208518 ይደውሉ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

12 Oct, 09:20


የሳንባ ካንሰር ህክምና እንደ ካንሰር አይነቱ እንዲሁም እንደሚገኝበት የስርጭት ደረጃ በብዙ መንገዶች ይታከማል፡-
በቀዶ ህክምና
በኬሞ ቴራፒ
በጨረር ህክምና
እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ህክምናዎች በማጣመር ማከም ይቻላል፡፡
#የሳንባ_ካንሰር_ህክምና_ምንን_ያካተተ_ነው?
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

10 Oct, 13:58


የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በየም ዞን ጉብኝት ባድረገበት ወቅት የሳጃ ሆስፒታል የብርድ ልብስ ችግር እንዳለበት በመረዳታቸው የዲኤችገዳ ብርድ ልብስ ፋብሪካ በማነጋገር በሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በኩል ለየም ዞን ሳጃ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ሁለት ቦንዳ ብርድ ልብስ ድጋፍ አድርጓል።
የዲኤችገዳ ብርድ ልብስ ፋብሪካ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

10 Oct, 07:47


#ትውልድን_የሚያንፀው_ትምህርት_ቤት!
💚💛❤️
#ፍሊፐር ኢንተርናሸናል ት/ቤት ለሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በየ አመቱ በቋሚነት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ አሁንም ለህፃናት እና አረጋውያን የሚሆኑ የትምህርት፣ የምግብ ቁሳቁሶችን እና አልባሳትን ድጋፍ አድርጓል፡፡ የፍሊፐር ኢንተርናሸናል ት/ቤት አስተዳድር ሰራተኞች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር ሁሉ በአረጋውያኑና በህፃናቱ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር
1000005063907
0983636363/0983646464/0911208518 ይደውሉ!

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

09 Oct, 08:19


ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ አሰኮ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ለማጠናቀቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ሰባት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር አሰባሰበ፡፡
*****
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አስኮ እየተገነባ ላለው የሜሪ ጆይ አሰኮ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ለማጠናቀቅ የሜሪ ጆይ የቦርድ አባላት፣ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና ባለሀብቶች ጋር በተደረገው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 7,350,000.00 ( ሰባት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) ማሰባሰብ ተችሏል::
ይህ ሆስፒታል ሲጠናቀቅ በአመት ከ25000 በላይ አቅመ ደካማ እንዲሁም ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው አረጋዉያን በነፃ የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል::
በዚህ የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም ላይ ለተሳተፋችሁ ሁሉ በሜሪ ጆይ ህፃናትና አረጋዊያን ስም ከልብ እያመሰገንን አሁንም በገንዘብም ሆነ በአይነት ለመደገፍ ከታች በተቀመጠው አካውንት የአቅማችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ እና ከአረጋውያኑ ጎን እንድትቆሙ ስንል የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን::
#ለበጎ_ስራ_እንነሳ
የንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000006578385
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

Mary Joy Ethiopia/ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ

09 Oct, 07:09


#ህፃናት_ይማሩ_ሀገር_ይረከቡ!
💚💛❤️
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ መልካም ኢትዮጵያውያን ያሰባሰባቸውን የትምህርት ቁሳቁሶች በከምባታ ዞን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉን ያስተባበራችሁ በሙሉ ስላደረጋችሁት መልካም ተግባር በህፃናቱ እና አረጋውያኑ ስም ከልብ እናመሰግናለን፡፡
#ሜሪጆይኢትዮጵያ #ኢትዮጵያዊያን_ለኢትዮጵያዊያን
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”