#Ejjeetto Times @sidamaejjettotimes Channel on Telegram

#Ejjeetto Times

@sidamaejjettotimes


Sidama Regional State
Quick Referendum..

#Ejjeetto Times (English)

Are you looking for the latest news and updates from the Sidama Regional State? Look no further than #Ejjeetto Times! This Telegram channel, with the username @sidamaejjettotimes, is your go-to source for all things related to the Sidama region. Whether you are a resident, a visitor, or simply interested in staying informed about this vibrant and diverse area, #Ejjeetto Times has you covered. From quick referendum updates to important announcements, community events, and more, this channel is the one-stop-shop for all things Sidama. Stay connected, stay informed, and stay engaged with #Ejjeetto Times. Join us today and be a part of the conversation!

#Ejjeetto Times

24 Dec, 16:03


Ejjeetto
Ateti Maganoho leelto!
==================
Barcimma kokkete mittu mitto morke
Mitu mito kare sa"ara okke
Mitu assaado maaxi'no fokke
Yinoomme yaatto haraho songe
Sidaamimmate hasaawe torbe
Coyi'no qaale SMNira soqqe
Coyi'notey hosalla giwa loqoxe lophe?

Gosooma, moora gargarro yii Dase
Dase qaale fuli baadu gafote qase
Kaadire ikkiina wonaa ay afi'no
Moorunna gosoomu lase
Lasensara konni ka'a nooyya base?

Mannu biiloonyeho duddure
Tifoozo lassi'rino gure
Awalletenni afoo usure
Usurammohu mitto faarsanno
Sidaama uulla agure
Ra"anno yanna mitu gimbo bu're
Bu'riha yinayya "Aanne'e mukkure!"?

Sadaasano sa'annowe
Ejjeetto baro
Afaaleeyyete songo
Ofolla mittowa wodana koottalo
Koottalu wodanihu tirayya Ejjeetto
TeEjjeettoti Maganoho leelto!!

@SBQ 11: 30
Hawaasa, Sidaama | Ethiopia

#Ejjeetto Times

18 Mar, 10:14


ኤጄቶ (የሲዳማ የህዝብ ድምፅ ስለሆነ) በሚወስነው ውሳኔ ሁሉ በሲዳማ ክልል ውስጥ ያለ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ፓርኮችንም ጨምሮ የሚወስነው ውሳኔ እነሱንም ይመለከትል።
##ባለፈው ሳምንት ኤጄቶ ወስኖ በተደረገው የስራ ማቆም አድማ ላይ ተሳትፈው የነበሩ በኢንዱስትሪ ዞን የሚሰሩ የሲዳማ ልጆች ዛሬ እንደሰማነው ከሆነ በ3ቱ ቀናት በስራ ገበታችሁ አልተገኛችሁም በሚል የ3 ቀን ደመወዝ እንደተቀነሰባቸው ጭምጭምታዎች ሰምተናል።
##ይሄ ትልቅ ሴራ ሴራ እና ተንኮል አዘል ድርጊት ነው። ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሐዋሳ ውስጥ እስካለ ድረስ የህዝባችን ውስኔ 100 በ100 እነሱንም ይመለከታል። ##ስለዚህ በዚህ ውሳኔያችሁ እንዳትፀፀቱ ቆም ብላችሁ አስቡበት።
##ደኢህዴን ከሚባለው ቡችላ ድርጅት ጋር ተነጋግታችሁ ያደረጋችሁት ከሆነ ደግሞ የሲዳማ ህዝብ እስከ ወዱያኛው ይፋረዳችሁአል።

##አስቡበት...

#Ejjeetto Times

18 Mar, 09:10


ውቢቷ ሃገራችን ሁሌም ደና ናት

#Ejjeetto Times

17 Mar, 06:05


ኤጄቶኒዝም...

#Ejjeetto Times

16 Mar, 20:08


በክልላችን ውስጥ የከተሞች ግንባታን ማፋጠንና ያሉንን አቅሞችና ተፈጥሯዊ እሴቶችን በሚገባ አሟጠን አውጥተን ወደ ሚገባን ስፍራ ለመድረስ እያንዳንዳችን የሚጠበቅብንን ሃላፊነት መወጣት አለብን።

#Ejjeetto Times

16 Mar, 20:05


##ብዙ ስራ ይጠብቀናል##
ኤጄቶ ታይምስ

...ህዝባችን የብዙ እሴትና ባህል ባለቤት ነው። ከሲዳማ ጫፍ እስከ ጫፍ ብናስስ ብዙ ያልተነገሩና ቢዘከሩ ግን ዓለምን የሚያስደምሙ የራሳችን መገለጫ የሆኑ አኩሪ ትውፊቶችም አሉን።
...በቀደሙት ጊዜ ባህልንና እሴትን በማስተዋወቁ ዘርፍ በፐርሰንት ምን ያህል እንደተሰራ ባላውቅም። እንዲሁ በሚታየው ብቻ ገምግም ብባል በፐርሰንት 10% ይሆናል ባይ ነኝ። ለምን አልክ ብትሉኝ... ቅድም ከላይ እንደገለፅኩት በህዝባችን በእያንዳንዱ ቄዬ ዞር ዞር ብለን ብንቃኝ ብዙ ሊታዩና ጎልተው ሊወጡ የሚገቡ ነገሮች ሞልተውናል። ግን እስካሁን አይደለም ዓለም እኛው የሲዳማ ተወላጅ የሆንን እራሱ ስለ እሴቶቻችን፤ ባህሎቻችንና ትውፊቶቻችን በሚገባ አላወቅንም። ይሄ ለምን ሆነ ቢባል በሚገባ ትኩረት ሰጥተን ስላልሰራንበት ነው።
##ከአሁን በሁአላ ግን ያለፈውን እንደ ትምህርት ወስደን ያሉንን እሴቶች፤ ትውፊቶችና ባህሎቻችንን በሙሉ ለመላው ዓለም እንደ ጫምባላላ በዓላችን ልናስተዋውቅ ይገባናል።
ለዚህ ደግሞ ጀግናው አዲሱ ትውልድ ለህዝብ ጥያቄ በጀግንነት እየታገለ እንዳለው ሁሉ ለዚህ ያለንን በማስተዋወቅ ስራ ላይ በጋራ ሆነን ልንሰራ ይገባል።
###ድል ለሰፊው ህዝባችን###

#Ejjeetto Times

16 Mar, 19:26


የሚያቆመን የለም።

#Ejjeetto Times

12 Mar, 22:55


#ሲዳማነታችንን ማዜማችንን ከስህተት የሚቆጥሩ ሰዎች እነሱ እጅግ ትልቅ ችግር ያለባቸው ሰዎች ናቸው። ይሄ #ከሃይማኖት ጋር ከቶ አይገናኝም፤ ፍፁም #ከፖለቲካም ጋር አቻ ለአቻ አይቀመጥም። ስለተሰጠንና በእጃችን ስላለው ነገር እለት እለት ማውራትና ማሰብ ችግር ሳይሆን እጅግ ጤነኛነት ነው። ሲዳማነት ከፈጣሪ የተሰጠን ልዩ መገለጫችን ነው። ዘወትር ስለሲዳማነታችን ብናወራና እለት እለት ብናስብ የተሰጠንን ነገር ማክበራችን ነው። ስላልተሰጠን ነገር አናወራም አሊያም ጊዜ ሰተን አናስብም። ሲዳማነት ማንም ሊነጥቀን የማይችል ልዩ መገለጫችን ናትና ዘወትር እናወራላታለን። ምክንያቱም ክብራችን ነውና።
#ሲዳማነት ይለምልም
#ድል ለሰፊው ህዝብ
#ኤጄቶ ታይምስ

#Ejjeetto Times

12 Mar, 05:11


ጋዶ 2 ታውጇል
።።።።።።።።።።
ይህ ጽሁፍ ሲዳሚኛ ለማያነቡ የተዘጋጀ ነው!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሚቀጥሉት ረቡዕ፣ ሀሙስና ዓርብ(4-6/7/11ዓም/
ሥራ አይኖርም።
የሲዳማ ብሔር ራስን በራስ ለማስተዳደር ካለው ጽኑ
እምነት ብዙ ዋጋ ከፍሎአል። ህገ-መንግስት ተከብሮ
ለማየትም የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ሰላማዊ ትግሉንም
በአሁኑ ወቅት እየገፋ ይገኛል። በዚህ ወቅትም
የረፈረንደም ቀን ይቆረጥልኛል በሚል ጽኑ እምነት
የተለያዩ መድረኮችንና ሰላማዓዊ ሰልፎችን በማድረግ ቀኑ
መዝገየቱን አሳውቋል።
ይሁን እንጂ ይኼ ታሪካዊ ጥያቄን በህገ-መንግስታዊ
መንገድ ይመለሳል ብሎ ሲጠባበቅ ለቆየው ብሔርም ሆነ
ትግሉን በፊለፊት እየመሩ ላሉት ኤጄቶዎች በማያገባቸው
እየገቡ ከዚህ ቀደም ደም እንዳፈሰሱ እንደለመዱት ያንን
ለመድገም የሚያሰሩ ፖለቲከኞች ስብስብ መደራጀቱንና
ጥያቄውን ለማድብዘዝ አመራር በማሸማቀቅ ጥያቄውን
ለመቀልበስ የሚከጅሉ እንዳሉ ደርሰንባቸዋል።
ደኢህዴን ጭምር ለዚህ ዋና ተዋናይ መሆኑን አምነን
በቅርቡ የነበራቸው ስብሰባ እንዲበትኑ ሆኖአል።
በቀጣይም ስብሰባውን አቃርጦ የወጡትን ጀግና
አመራሮቻችንን በአጉል ስብከት ለማስማማትና ይቅርታ
ጠይቁ በማለት በማስገደድ ላይ ይገኛል።
ደኢህዴን በኢህገ-መንግስታዊ አካሄድ እድሜውን
ለማራዘም የሲዳማን ክልል የመሆን ያለቀ ጥያቄ ጋሬጣ
እየሆነ ስለሆነ # የረፈረንደም ቀን ተቆርጦ እስካልተነገረ
ተከታታይ አቋሞችን ኤጄቶ ለመያዝ ይገደዳል።
የሽማግሌ ሾንጎም ኤጄቶን መርቆ የትግሉን ችቦ
በማስረከቡ በሲዳማ ምድር ለ3 ቀናት የሚጸና የስራ
ማቆም አድማ እናደርጋለን።
# ቀኑ:- መጋቢት 4-6/2011 ዓ.ም ነው።
# የማይሰሩ መስራያ ቤቶች
...በሀዋሳ ምድርና በሲዳማ ዞን ውስጥ ያለ የፈዴራል፣
የአሮገ ክልል፣ በከተሞችና በዞኑ ወረዳ እስከቀበሌ ያሉ
የመንግስት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
ባንኮች፣ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከ LKG፣ የግል
ድርጅቶች ጨምሮ ለሶስቱም ቀን ካለምንም ማስጠንቀቂያ
መዝጋት ይጠበቅባቸዋል።
# በቀኑ የማይዘጉ አገልግሎቶች
የህክምና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ፖሊስ መስሪያ
ቤቶች ፣ ፍርድ ቤቶች፤ የንግድ ሱቆችና የምግብ መጠጥ
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ ገበያዎች፣ የመንገድና
ትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ በንሳ ኤፍ
ኤም፣ የውሃ፣ የመብራትና የቴሌ አገልግሎቶች
በተለመደው አኳሃን ሥራቸውን ለመስራት ይገደዳሉ/
በእነዚህ ቀናትም የተለመደ ሥራቸውን ያከናወናሉ።
ማስጠንቀቂያ!
# የደኢህዴን ቢሮችና ጽ/ቤቶች ከቅዳሜ ጀምሮ
እንደተዘጉ ይቀጥላሉ።
# ማንኛውም በደኢህዴናዊ ዓይን የተቃኘ ስብሰባ
ለመሰብሰብ ይቅርና ያሰበ ጠሪም ሆነ ተጠሪ የተከለከለ
ነው። የሲዳማን ክልል ጥያቄ ጉዳይን ለመወያየት እንደ
አጀንጃም ሆነ እንደመነጋገሪያ ተደርጎ የሚቀርብ ስብሰባ
ላይ መገኘት የተከለከለ ነው። ከዚህ ውጪ እንቀሳቀሳለሁ
የሚል የሲዳማም ሆነ ሌላ ተለጣፊ አመራር ካለ
ካለምንም ቅድሜ ማስጠንቀቂያ ኤጄቶ እርምጃ
ይወስዳል።
# በሶስቱ ቀናት ውስጥ በተዘጉ መ/ቤቶች ቢሮ ገብቶ
ሲሰራ የተገኘ አካል ወይም ቡድን ላይ ኤጄቶ ባለው
አደረጃጀት ተመጣጣኝ እርምጃ ይወስዳል።
# በእነዚህ ቀናት ውስጥ የማንኛውም ግለሰብ ንብረት
ኤጄቶዎች ከያዙት አቋም ውጪ ሆኖ ሲሰርቅ፣ ሲዘርፍ፣
ከግለሰቦች ጋር ለጥልና ለስድብ ለሚነሳ፣ የሰውን አካል
በማጉደል የሚሳተፍ ማንኛውም ግለሰብና ቡድን ላይ
እርምጃ ይወሰዳል። አስፈላጊ ሆኖ ስገኝም ለህግ-ተላልፎ
ይሰጣል።
# ባለሀብት ነን በማለት ሰርቀው በልጽገው የሚኩራሩትንና
ሲዳማን የሚጎዳ ደኢህደናዊ ስራ የሚደግፉ አካላት ላይ
ጠንካራ እርምጃ ይወሰዳል። የሚኩራሩትን ሀብታቸውን
ከጥቅም ውጪ እስከማድረግ።
# ስልጣን በመመካት የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፖለቲከኛ
ሆነ አደረጃጀት ላይ መረጃ ጎን ለጎን በመላክ እርምጃ
ይወሰዳል።
# የረፈረንደሙ ቀን ባለነው ሳምንት ቀኑ ተቆርጦ
ለህዝባችን ካልተገለጸ ድረስ ቀጣይ ተከታታይ እገዳና
የባሰ ማዕቀብ ለማወጅ ጨርሰን እየተጠባበቅን
እንገኛለን። ኤጄቶም በየቦታው በተጠንቀቅ ይንቀሳቀሳል!
ታግለን መብታችንን የሚናስከብር እንጂ በችሮታና
በድርጅቶች መልካም ፈቃድ የሚሰጥ መልስ ተቀባይነት
የለውም!
"ይህ ለሲዳማ ህዝብ አርነት የሚታገል የመጨረሻው
ህዝብ ነው!"
እውነት ትፍረድ!
# ኤጄቶ
# ሀዋሳ_ሲዳማ_Iኢትዮጵያ

#Ejjeetto Times

12 Mar, 05:11


ሰበር ዜና
በኤጄቶ በሚቀጥሉት 2 ቀናት ማለትም ረቡዕ፣ ሀሙስና
ዓርብ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቷል።
# Gaado 2 / #ሁለተኛ ዙር ዘመቻ!!
```````````````````````````````

የስራ ማቆም አድማ
አሁንም ሲዳማ ሰላማዊ ትግሉን እንደቀጠለ ነው።
በምዕራፍ ሁለት ዘመቻው ከፊታችን እሮብ ጀምሮ እስከ
አርብ ድረስ ማለትም ከመጋቢት 4-6/2011 ዓ.ም ድረስ
የስራ ማቆም አድማ በመላው ሲዳማ ምድር ይደረጋል።
አድማው የማይመለከታቸው ተቀዋማት:-
===========
የጤና ተቁዋም፣ ፖሊስ፣ ማብራት ሀይል፣ ውሀ ልማት፣
ቴሌ፣ ፍርድ ቤት፣ ማንኛውም አይነት ንግድ ተቁዋም፣ እና
የትራንስፖርት አገልግሎት ይሆናል።
ማስታወሻ : በዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆች የሚገኙ ካፌዎች
አገልግሎት ይሰጣሉ።
ሰላማዊ ትግላችን ተጠናክሮ ይቀጥላል። ለዚህም ኤጄቶ
በቂዉን ዝግጀት አድርጓል።
ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ጠያቂዎች ላይ የእስር፣ ግድያና
ሌሎች እርምጃዎች ለመውሰድ እያሰበ ያለ አካል ካለ
ትግሉን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንጂ
"በተለመደ" ኢህአዴጋዊ/ደኢህዴናዊ ሴራ ወደቤቱ
የሚመለስ አንድም ሲዳማ የለም።
አልፎ ለሚመጣ ነገር ሲዳማ ከጫፍ እስከ ጫፍ እስከ
ደም ጠብታ ድረስ የከረረና ፈታኝ እና እልህ አስጨራሽ
ትግል ለመቀጠል ዝግጅት አጠናቋል፡፡
ማስታወሻ;
1. በተለያየ ደረጃ የምትገኙ ጥቂት ሲዳማዊ ባንዳዎች
ትግላችንን ለማጨናገፍ የተለየ እንቅስቃሴ እያደረጋችሁ
ያላችሁ ታቀቡ!! ካልሆነ ግን የታገስነውን ያህል የክንዳችን
ብርታት ያርፍባችኃል።
2. የሲዳማ ተወላጆች ያልሆናችሁና በሃዋሳና በመላው
ዓለም የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከህገመንግስታዊ
ጥያቄያችንና ትግላችን ጋር ተደመሩ። ካልቻላችሁ ግን
ታቀቡ። ይህ ካልሆነ ግን የቆረጠው ኤጄቶና ስራችሁ
ያወጣችኃል።
መጋቢት 3/2011 ዓ.ም
# ኤጄቶ !!
# ሼር

#Ejjeetto Times

10 Mar, 20:11


መፅናናትን እንመኛለን

#Ejjeetto Times

09 Mar, 21:04


ደኢህዴን አሁን ላይ ተበጣጥሶ የሰውነት አካላቶቹ የት የት እንደወዳደቁ የሚያፈላልግ ኮሚቴ ተዋቅሮለት እየተፈለገ ነው።
###ለህወሓት መፅናናትን እንመኛለን###

#Ejjeetto Times

09 Mar, 21:00


##ኤጄቶ የእኛ##
ይሄን አውሬ ድርጅትን በጣጥሶ ጣለልን

#Ejjeetto Times

09 Mar, 20:59


ድል ለሰፊው ህዝባችን

#Ejjeetto Times

09 Mar, 20:47


ኢንቫይት...

#Ejjeetto Times

09 Mar, 20:25


ማንም ማይነጥቀኝ ውዱ መታወቂያዬ.... ሲዳማ