Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ @macohs2023 Channel on Telegram

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

@macohs2023

The official Telegram channel of the college!!

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (Amharic)

አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ (MACOHS) ከሚዛን ወደ ዓለም ድምጽ ሚኒስትራተን የጤና ሳይንስ ተማሪ ምሁር በሆነ መልኩ ሳይንስ ተማሪቆች በአዲስ አበባ ሆቴር እና የእስር ቤቱ ሥራ ቦታ አወዳድሮ ለመውሰድ እና በእንቅስቃሴ ያለ ማስታወቅ ማድረግ በጣም የጤና ሳይንስ ሰዩልክ አገልግሎት ላይ በምርመራ ለሆቴርና እስር ቤቱ በጅምላ አዋጁን በድጋሚ ኮሌጅ ሊኖረው ድረስ እንችላለን። ኢሜል: macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

13 Feb, 13:39

በኮሌጃችን በ 2017 ዓ.ም በግል ድግሪ ለመማር ላመለከታችሁ በሙሉ :

የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር በቂ ባለመሆኑ ፕሮግራሙ የተሰረዘ መሆኑን እናሳውቃለን::

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

13 Feb, 07:32

ለ2017 አዲስ የግል ዲኘሎማ ተማሪዎች በሙሉ :

ሰኞ 10/06/2017 ዓ.ም ኦረንቴሽን ስለሚኖር ሁሉም ተማሪ በሰዓቱ እንዲገኝ እናሳስባለን።

ማሳሳቢያ: በሰዓቱ ያልተገኘን ተማሪ ኮሌጁ የማያስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

11 Feb, 16:39

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞች ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት የሚዉል ደጋፍ ለማድረግ ያለመ ውይይት አደረጉ።
04/06/2017ዓ.ም ሚዛን አማን
***

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞች ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት የሚዉል ደጋፍ ለማድረግ ያለመ ውይይት አደረጉ። ማክሰኞ 04/06/2017ዓ.ም ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት ድጋፍ ለማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ አጠቃላይ የኮሌጁ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይም የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ እንደተናገሩት የከተማችን ኮሪደር ልማት የሁላችንም ነው በሚል ከተማችንን ዉብ እና ማራኪ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ እንደተቋም በኮሌጅ ደረጃ የድርሻችንን ለማበርከት ያለመ መድረክ መሆኑን አስታውሰው ይህን የኮሪደር ልማት ለመደገፍ ሰራተኛዉ ማንም ሳያስገድደው በባለቤትነት ስሜትና በፍቃደኝነት ድጋፍ እንዲያድርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ላይ ሀሳብና አስተያየታቸዉን የሰጡት የኮሌጁ አመራሮች፣ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞች ይህ የኮሪደር ልማት ከተማችንን ዉብ እና ምቹ ለማደረግ ያለመ በመሆኑ በግል ደረጃ በየአካባቢያችን የምናደርገው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ እንደተቋም የበኩላችንን መወጣት አለብን በማለት ሀሳባቸዉን አካፍለዋል።

በመጨረሻም ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኛ ከየካቲት ወር ደሞዝ የሚቆረጥ የደሞዙን 7% ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት ድጋፍ ለማድረግ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

03 Feb, 09:52

ለኮሌጃችን አዳዲስ መምህራን የማስተማር ስነ-ዘዴ(ETS/CTS) ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ጥር 26/2017 ዓ.ም ሚዛን አማን
*******

ለኮሌጃችን አዳዲስ መምህራን የማስተማር ስነ-ዘዴ(ETS/CTS) ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የስልጠናውን መጀመር አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ምርምርና ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ መሰረት ገ/ማርያም እንዳሉት ኮሌጁ ጥራት ያለው የጤና ባለሙያ ለማፍራት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ ኮሌጁን ለሚቀላቀሉ አዳዲስ መ/ራን እንዲሁም ከት/ት ለሚመለሱ የኮሌጁ መ/ራን የማስተማር ስነ-ዘዴ (Effective teaching skill and Clinical Teaching Skill) ስለጠና መስጠት ነው ያሉ ሲሆን ስልጠናው ለተማሪዎች በቂ እና ጥራት ያለው ዕውቅት ለማስጨበጥ የማይተካ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

ለተከታታይ አራት ቀናት የሚቆየው ይህ ስልጠና በኮሌጁ ት/ት ማበልፀጊያ ማዕከል(EDC) እና ተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ (CPD) ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን ከአዳዲስ መምህራን በተጨማሪ የት/ት ደረጃቸውን አሻሽለው የመጡ የኮሌጁ መምህራንም ተሳትፈውበታል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

27 Jan, 16:46

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ሼድ ለመገንባት ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጋር የቦታ ርክክብ አካሄደ።
ጥር 19/2017 ዓ/ም: ሚዛን አማን
***

የሚ
ዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ሼድ ለመገንባት ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጋር የቦታ ርክክብ አካሄደ። ኮሌጁ በማሕበረስብ አገልግሎት ዘርፍ ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ከ10 በላይ ሼድ ለመገንባት በጋይድ ማፕ የተደገፈ የቦታ ርክክብ አድርጓል።

የቦታ ርክክቡን የሚዛን አማን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሞገስ ሻምበል፣ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ፣ የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ቤሪን ጨምሮ የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የከተማ አስተዳደሩ ስራ ክህሎት ንግድ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ምትኩ ጢሞቲዮስ ተገኝተዋል።

የግንባታ ወጪው በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚከናወነው የሼድ ግንባታ ሲጠናቀቅ ከ60 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑ ተጠቅሷል።

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከመማር ማስተማር ስራው በተጨማሪ በርካታ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን እያከናወነ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ኮሌጁ በስራ እድል ፈጠራው ዘርፍ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ጋር 180 ካ/ሜ በላይ ቦታ ርክክብ ተፈጽሟል ብለዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

27 Jan, 09:30

በግል ዲፕሎማ ለመማር የመግቢያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ስለማሳወቅ:

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

26 Jan, 09:42

ማስታወቂያ
የቅጥር ፈተና ቀን ስለማሳወቅ

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

25 Jan, 06:09

እንኳን ለሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል "ቲካሻ ቤንጊ" በሰላም አደረሳችሁ!!

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

24 Jan, 14:29

ማስታወቂያ
በግል ዲፕሎማ ለመማር ለተመዘገባችሁ በሙሉ :

ፈተናው የሚሰጠው ቅዳሜ በቀን 17/05/2017 ዓ.ም ሲሆን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት በኮሌጁ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ማሳሳቢያ
1. ማንኛውም ተፈታኝ መታወቂያ መያዝ አለበት
2. ሞባይል ይዞ መግባት አይቻልም
3. ካልኩሌተር ይዞ መምጣት ይጠበቅባችኃል ።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

20 Jan, 13:47

ማስታወቂያ
በኮሌጃችን በግል ለመማር ላመለከታችሁ በሙሉ፡

የመግቢያ ፈተና የሚስጠው ዓርብ በቀን 16/05/2017 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቀን በተጠቀሰው ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 ላይ መታወቂያ በመያዝ በኮሌጁ አዳራሽ አንድትገኙ እናሳስባለን ።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

18 Jan, 09:27

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ እንመኛለን!!
መልካም በዓል!!

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

12 Jan, 08:18

እንኳን ለቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ እና የምስጋና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
Digam Bist Bareshn
Yint Hatsasie!

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

11 Jan, 14:19

#የሀዘን_መግለጫ

ወጣት ምስጋና ሙላት ከአባታቸው ከአቶ ሙላት ጋዥንቴት እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ኮሹ የምስ በሰሜን ቤንች ወረዳ ያሊ ቀበሌ በ1992 ዓ.ም ተወልደው ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ25 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በባልደረባችን ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።

ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

11 Jan, 06:34

የሀዘን መግለጫ

የኮሌጃችን የስራ ባልደረባ አቶ ጌታሁን አባቡ ከአባታቸው ከአቶ አባቡ ዓሊ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ እታገኝ ስጦታው በ1978 ዓ.ም በቴፒ ከተማ ተወልደው በገጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው በቀን 02/05/ 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ።

ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን !

ሚዘን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

10 Jan, 12:01

#የቅጥር_ማስታወቂያ
Public Health-1
BSc Nursing-2
Medical Laboratory-1
Midwife-1

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

07 Jan, 04:49

ለክርስትና እምነት ተከታይ የኮሌጃችን መምህራን፣ አስ/ር ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው ኢትዮጲያዊያን እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

28 Dec, 07:42

#ማስታወቂያ
የብቃት ማረጋገጫ ምዘና (COC) ለመውሰድ የተመዘገባችሁ በሙሉ፡
ምዘናው የሚሰጠው በቀን 25/04/2017 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን ።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

26 Dec, 06:53

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፡
ዲፕሎማ (ደረጃ IV)

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

23 Dec, 17:32

ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ደረጃ IV (ዲኘሎማ) ተማሪዎች ገለፃ (Orientation) ሰጠ።
ታህሳስ 14/2014 ዓ.ም ሚዛን አማን

ሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ዲፕሎማ ተማሪዎች ገለፃ (Orientation) ሰጠ። የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ እንዳሉት ወደ ኮሌጃችን የሚመጡ ተማሪዎች ከተለያየ ቦታ የሚመጡና እርስ በዕርሳቸው ብዙም የማይተዋወቁ ቢሆንም በኮሌጃችን በሚኖራቸዉ ቆይታ እርስ በዕርስ በመተዋወቅ ከመማር ማስተማሩ ባሻገር ማሕበራዊ ኑሮን የሚላመዱበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

ገለፃው የኮሌጁ ዲን ፣ ምክትል ዲኖች ፣ ሬጅስትራር ፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች እና የፕሮግራም አስተባባሪዎች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን አጠቃላይ ተማሪዎች በቆይታቸው በኮሌጁ ውስጥ ስለሚኖራቸው መስተጋብር ፣ የትምህርት አሰጣጥና ተከታታይ ምዘና ፣ ስነ ምግባርና የአለባበስ ስርዓት፣ የላይበረሪ አገልግሎት( ማኑዋል ፣ ዲጅታል እንዲሁም የምሽት ላይብረሪ አገልግሎት) እና መሰል ጉዳዮች ላይ በኮሌጁ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እና በኮሌጁ ተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን በአቶ ሽመልስ ወንድሙ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።

በመጨረሻም ከተማሪዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

06 Dec, 19:02

በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓለም የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ቀን ፣ የሀገራችን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንዲሁም የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን በጣምራ በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ ።
ህዳር 27/ 2017 ዓ.ም ሚዛን አማን
************
በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓለም የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ቀን ፣ የሀገራችን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንዲሁም የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን በጣምራ በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ ። ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ የተማሪዎች አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት አቶ ሽመልስ ወንድሙ እንዳሉት ኤች. አይ.ቪ ኤድስን አስመልክቶ እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚያስጠብቁ ጉዳዮችን በተመለከተ  የሚሰጡ መረጃዎችን ወደራሳችን በመወሰድ ልንተገብራቸው ይገባል ብለዋል። አቶ ሽመልስ አክለውም የሴቶችን ፆታዊ ጥቃት የመከላከል እንቅስቃሴ ላይ የወንዶችም ንቁ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

የኮሌጁ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን የሆኑት አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ በመልዕክታቸው የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት በአለም አቀፍ ደረጃ ፣ በሀገራችን እንዲሁም በክልላችን ቀላል በማይባል ደረጃ እየጨመረ መሆኑን አስታውሰው ተማሪዎችም ከዚህ ፕሮግራም ብዙ ዕውቀት በማግኘት እራሳችሁን ከበሽታው መከላከል አለባችሁ ሲሉ ተደምጠዋል።

ዝግጅቱ በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት የተከበረ ሲሆን የኤች. አይ.ቪ ኤድስን አስመልክት የአንድ ግለሰብ የህይወት ተሞክሮ ቀርቦ ለታዳሚያን ልምዳቸውን አካፍለዋል ።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

05 Dec, 12:23

ለኮሌጃችን ሰራተኞች በሙሉ

በነገው ዕለት ማለትም ዓረብ 27/03/ 2017 ዓ.ም የዓለም የኤች. አይ.ቪ ኤድስ ቀን ፣ የሀገራችን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንዲሁም የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀንን በጣምራ በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ ስለምናከብር በዕለቱ 8፡00 ላይ የተለያዩ የብሄር ብሄረሰብ አልባሳትን በመልበስ በኮሌጃችን መሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን ::

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

03 Dec, 05:06

የኮንታ ዞን ተፈታኞች ውጤት

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

03 Dec, 05:02

የቤ/ሸኮ ዞን ተፈታኞች ውጤት

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

02 Dec, 19:04

የዳውሮ ዞን ተፈታኞች ውጤት

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

02 Dec, 18:57

የም/ኦሞ ዞን ተፈታኞች ውጤት

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

02 Dec, 18:29

የካፋ ዞን ተፈታኞች ውጤት

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

03 Nov, 13:38

ለኮሌጃችን ሰራተኞች በሙሉ ፡

አገልግሎት እየሰጠ ያለው ሰርቪስ ብልሽት ስላጋጠመው በነገው ዕለት ማለትም ሰኞ ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም ጠዋት የሰርቪስ አገልግሎት እንደማይኖር እናሳውቃለን።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

29 Oct, 08:05

የብቃት ማረጋገጫ ፈተና (COC) መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ፡
የምዝገባ ጊዜ : ከ 20-22/02/2017 ዓ.ም

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

24 Oct, 10:42

በኮሌጃችን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እየተመራ በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የልምድ ልዉዉጥ ያደረገው ልዑክ የልምድ ልዉውጡን ሪፖርት ለኮሌጁ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮምሽን አባላት አቀረበ።
ጥቅምት 14/2017 ሚዛን አማን
**********
በኮሌጃችን አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እየተመራ በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የልምድ ልዉዉጥ ያደረገው ልዑክ የልምድ ልዉውጡን ሪፖርት ለኮሌጁ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮምሽን አባላት አቀረበ። ከተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች የተዋቀረው ልዑክ በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያደረገውን ልምድ ልዉዉጥ ሪፖርት ለኮሌጁ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮምሽን አባላት አቅርቧል።ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሰፊ ውይይት የተደረገበት ይህ ሪፖርት ከማናጅመንትና አካዳሚክ ኮምሽን አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ልምድ ልዉውጡን ካደረገዉ ልዑክ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
ከመድረኩ ላይ እንደተነሳው ከጊዜ ወደ ጊዜ መሰል የልምድ ልዉዉጦች ማከናወን ምርጥ ተሞክሮዎችን ከኮሌጃችን ነባራዊ ሁኒታዎች ጋር በመቀመር የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ጉልህ ሚና እንዳላችውም ተገልጿል።

በመጨረሻም መልዕክታቸዉን ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ይህ ልዑክ በርካታ አዳዲስ ነገሮች ይዞ የመጣ መሆኑን ገልጸው ኮሌጃችን ከሌሎች ተቋማት አንጻር የተሻለ ሆኖ የተገኘባቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸዉንም ገልጸዋል። አቶ ፀጋዬ አክለዉም የመማር ማስተማሩን እንዲሁም የአስ/ር ዘርፉን ስራ ይበልጥ ለማቀላጠፍ በቀጣይም በተጠናከረ ሁኔታ ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር የሚደረጉ ልምድ ልዉዉጦች ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ ብለዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

16 Oct, 11:57

የሀዘን መግለጫ
ወጣት ሀና በኃይሉ በቀለ ከአባቷ ከአቶ በኃይሉ በቀለ እና ከእናቷ ከወ/ሮ ታደለች ግዛው ነሐሴ 27/ 1995 ዓ.ም ተወለደች ። ወጣት ሀና የ2ኛ ዓመት ፍርማሲ ተማሪ ስትሆን ባደረባት ህመም በህክምና ስትረዳ ቆይታ በተወለደች በ22 ዓመቷ ጥቅምት 06/ 2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች!!
ለቤተሰቦቿ እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን እንመኛለን።

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

05 Oct, 11:53

3ተኛ ዙር የጥሪ ማስታወቂያ

Mizan Aman College of Health Science- የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

04 Oct, 19:22

የኮሌጃችን የስራ አመራር አባላትን የያዘዉ ልዑክ በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲያደርግ የነበረዉን የልምድ ለዉዉጥ አጠናቀቀ።
መስከረም 24/01/2017 ዓ.ም ሚዛን አማን
**********

በኮሌጃችን አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እየተመራ የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ በሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተገኘው የኮሌጃችን የስራ አመራር አባላትን የያዘዉ ልዑክ ሲያደርግ የነበረዉን የልምድ ለዉዉጥ አጠናቀቀ። የልምድ ልዉዉጡን መጠናቀቅ ተከተሎ የኮሌጃችን አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እንደገለጹት ከኮሌጁ አካላት ለተደረገላቸዉ አቀባበልና መረጃዎችን በመስጠት ረገድ ላሳዩት በጎ ተግባር የኮሌጁን አመራሮች እንዲሁም መላዉን የስራ አመራር አባላትን ያመሰገኑ ሲሆን በቆይታቸው ወቅት ልዑኩ በርካታ ጥሩ ተሞክሮዎችን እንዳገኘ እና እንኚህን ተሞክሮዎች ወደ ኮሌጃችን በመውስድና ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዋሀድ ለተሻለ ለዉጥ እንሰራለን ብለዋል።

በመጨረሻም የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደሰ ሐምደላ እንዳሉት በተለያዩ ተቋማት የልምድ ልዉዉጥ ማድረግ የተሻሉ ልምዶችን በመቀመር በመማር ማስተማሩ እንዲሁም በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላይ የተሻለ ዉጤት ለማምጣት አይነተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው በቀጣይም ወደ ኮሌጃችን በመምጣት የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023

2,562

subscribers

1,276

photos

1

videos