የቦንጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ ክንውን ሪፖርት በጣቢያው የልማት ዕቅድ ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ክንፈ ገብሬ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።
በመድረኩ የተሳተፉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ባለሙያዎች እንዳነሱት የሚቀረጹ ይዘቶች ተደማጭነትና የስርጭት አድማስ በማስፋት ሊሠራ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ተቋሙ አንዳንድ ከሰው ሃይል፣ ከበጀትና ከሚዲያ ቁሳቁስ እጥራት ጋር ያሉ ችግሮችን መፍታት እና ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር የውስጥ ገቢውን ለማሣደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡
ያረጁ የሚዲያ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች እንዲቀየሩ ጠይቀዋል።
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ተደማጭ ሆኖ እንዲቀጥል ከወትሮው የበለጠ ለመስራት የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጅ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራአስኪያጅና የይዘት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አሸናፊ አየለ እንደገለጹት በጣቢያው የሚሰሩ ዜናዎችና ፕሮግራሞች ከወትሮው በተሻለ ጥራት ደረጃ እየተሰሩ በመሆናቸው ተደማጭነቱ በዚያው መልኩ እየተሻሻለ መምጣቱን ተናግረዋል።
ከሰው ሃይል፣ ሚዲያ ቴክኖሎጂ ቁሳቁሶችና የውስጥ ገቢ አቅሙን ለማሣደግ በሚደረገው ጥረት ጣቢያው በቀጣይ የበለጠ ውጤታማ ለመሆን በልዩ ሁኔታ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
የጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ ሳልልህ በበኩላቸው የቦንጋ ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያ ዜናዎችን፣ ፕሮግራሞችንና ወቅታዊ ጉዳዮችን የማምረት ስራ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው በሚዲያው ዘርፍ የተሻለ ሥራዎችን ለመሥራት እንዲቻል በጽሕፈት ቤቱ በኩል ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
የተቋሙ ተግባራት ዘለቄታዊ የሆነ እይታ የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህም የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውንና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አንስተዋል፡፡
የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊና የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ ቢሮው አጀንዳ የሚመግብ ተቋም በመሆኑ ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ጋር አብሮ መስራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው አንዳንድ የሚታዩ ችግሮችን በማረም በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ይዘቶች በተቋሙ ተቀርጸውና ተገቢው ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊሰሩበት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ በበኩላቸው ጣቢያው በ6 ወር ወስጥ የተሻለ አፈፃፀም መኖሩን ገልጸው በቀጣይ የክልሉ ሕዝብ የመረጃ ተደራሽነት ለማስፋት የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን መጠቀም ይገባል ብለዋል።
ተቋሙ ከኮሙኒኬሽን ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በመጠናከር መረጃዎችን በተሻለ በጥራት ደረጃና በወቅታዊነት መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ቅርንጫፍ ጣቢያዉ የውስጥ ገቢ አቅሙን የበለጠ ለማሳደግ የአየር ሰዓት ሽፋኑን በመጨመርና የተለያዩ አማራጭ መንገዶች በመከተል መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።
የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እያደረገ ያለዉን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ የሚያጠናክር መሆኑንም አንስተዋል።
የቦንጋ ቅርንጫፍ ጣቢያ ተደማጭነቱን ለማሳደግ ቅንጅታዊ አሰራርን በመጠናከር መረጃዎችን በተሻለ በጥራት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል ፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇
📌በፌስቡክ https://www.xn--facebook-f86aoi9fn7aq6e.com/sowestcommunication/
📌ድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
📌በትዊተር twitter.com/sweprs
📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication