አዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በ7/24 ስራ ባህል ፣የከፍተኛ አመራሩ ልዩ ድጋፍና የቅርብ ክትልል በፍጥነትና ጥራት በመገንባት ለአዲስ አበባ ተጨማሪ ገፀ በረከትና አለም አቀፍ የቱሪዝምና ኮንፍረንስ ደረጃ ያሟላ እንዲሁም የአዲስ አበባን የቱሪዝም መስህብ በትልቅ ደረጃ በመጨመር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል የተባለው ማዕከል ነው።
ይህ ማዕከል ለ38ኛው የአፍርካ መሪዎች ጉባኤ የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች ዙሪያ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፍ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥራቱ በየነ ፣የከተማ ደጋፊ አመራሮች የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ እና ሌልች አመራሮች በተገኙበት የመስክ ምልከታ እና ጉብኝት አድርገዋል። ።
በግምገማው ለ38ኛው የአፍርካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ የተሻለ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን በማረጋገጥ የቀሩ ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫ ተቀምጧል ።
ለሚ ኩራ ኮሙኒኬሽን
የካቲት 04/2017 ዓ.ም