𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ @kewser_post Channel on Telegram

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

@kewser_post


✔️ In this channel :
📌 Qur'an
📌 hadiths
📌 stories
📌 Tilawa

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ (English)

Welcome to Keewser_Post, a Telegram channel dedicated to sharing inspirational content related to the Qur'an, hadiths, stories, and Tilawa. If you are looking for a source of spiritual guidance and motivation, this channel is perfect for you. With a curated collection of posts that aim to uplift and enlighten, Keewser_Post offers a platform for individuals to engage with sacred texts and teachings. Whether you are seeking daily reminders, insightful reflections, or simply a community of like-minded individuals, this channel has something for everyone. Join Keewser_Post today and embark on a journey of spiritual growth and discovery. Let the wisdom of the Qur'an and hadiths inspire you, the stories touch your heart, and the beauty of Tilawa elevate your soul. Stay connected with Keewser_Post and let the light of knowledge guide your path.

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Jan, 19:18


اللهم مُنزل الكتاب، وهازم الأحزاب، ومُجري السحاب، اللهم يا من لا يُرد أمرك، ولا يُهزم جندك، اللهم عليك #بأمريكا!

اللهم اهزمهم وزلزلهم اللهم أرِنا فيهم عجائب قدرتك!

اللهم كُن لأهل #غزة عوناً ونصيرا اللهم ارحمهم برحمتك واغثهم بغيثك وانصرهم بنصرك وثبت أقدامهم وانصرهم على القوم الظالمين!

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Jan, 19:18


📚አንድ ሰው በሀሳብና በጭንቀት የተወጠረ ከሆነ፡ በወሏጆቹ ፊት ጭንቀቱን ይፋ ማድረግ ማንፀባረቅ የለበትም።

ምክነያቱም ይህ ነገር ወላጆቹን ይረብሻቸዋል ያስተክዛቸዋል።

በልባቸው ውስጥ ደስታን ለማስገባት በተቻለው መጠን ሰላም እንደሆነ ማስመሰል አልለበት።

ይህ ለወላጆች መልካም ከመዋል ነው።

ሸይኽ ሷሊህ አል-ሉሀይዳንን አሏህ ይዘንላቸውና አዳምጡዋቸው።

ደህና እደሩ።
والسلام عليكم ورحمة الله وبركاته.

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

10 Jan, 19:20


ከ24 ሰዓታት በፊት የዓለማችን ወብ ከተማ የምትባል ነበረች። በፈሳድ ተግባሯ ግን የሆሊውድ መናገሻ ብቻ መሆኗ በቂ ነው። አላህ በከፍተኛ ንፋስ በከፍተኛ ፍጥነት በሚዛመት ሰደድ እሳት ለበለባት። እነዛ ውብ ህንፃዎቿ ወደ አመድነት ተቀየሩ። ያ ጽዱ ጎዳናዋና አረንጓደ ዛፎቿ፣ ሳቢ መንገዶቿ… እንዳልነበር ሆኑ። ሌሎች የሃገሪቱ ከተሞችም በረከቷ ይደርባቸው¡

ያቺ እንኳን ለራሷ ለሌሎች ደራሽ የምትባለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለ ጦርና ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሃገር፤ እነዛ ዘመናዊ ድሮኖቿ፣ የባለሃብቶቿ መንኮራኩሮች… ሊታደጓት አልቻሉም። ትዕዛዙ ከላይ ነው!

ንጹሐን ብቻ እንዳይጎዱ። ጃንዋሪ 20 ጋዛ ላይ ገሀነም እንከፍታለን ሲሉ፤ እዛው እጉያቸው አላህ ቀድሞ ከፍቶላቸዋልና የሚገባቸውን ሰዎች ሳታዳርስ እንዳትበርድ በዱዓእ ወጥሩ!




" فأصبح هشيماً تذروه الرياح " ..
‏قبل 24 ساعة كانت هذه المنطقه هي أغلى عقارات العالم لوس أنجلوس والان صارت رماد
مدينة #لوس_أنجلوس


قال تعالى:

(إِنَّمَا مَثَلُ الْحَيَاةِ الدُّنْيَا كَمَاءٍ أَنزَلْنَاهُ مِنَ السَّمَاءِ فَاخْتَلَطَ بِهِ نَبَاتُ الْأَرْضِ مِمَّا يَأْكُلُ النَّاسُ وَالْأَنْعَامُ حَتَّىٰ إِذَا أَخَذَتِ الْأَرْضُ زُخْرُفَهَا وَازَّيَّنَتْ وَظَنَّ أَهْلُهَا أَنَّهُمْ قَادِرُونَ عَلَيْهَا أَتَاهَا أَمْرُنَا لَيْلًا أَوْ نَهَارًا فَجَعَلْنَاهَا حَصِيدًا كَأَن لَّمْ تَغْنَ بِالْأَمْسِ ۚ كَذَٰلِكَ نُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ)

«የቅርቢቱ ሕይወት ምሳሌ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ፣ በእርሱም ሰውና እንስሳዎች ከሚበሉት የምድር በቃይ ተቀላቅሎበት (እንደ ፋፋ) ምድርም ውበትዋን በያዘችና ባጌጠች ጊዜ ባለቤቶችዋም በርሷ ላይ እነርሱ ቻዮች መኾናቸውን ባሰቡ ጊዜ ትእዛዛችን ሌሊት ወይም ቀን መጥቶባት ትላንት እንዳልነበረች የታጨደች እንዳደረግናት ብጤ ነው፡፡ እንደዚሁም ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች አንቀጾችን እናብራራለን፡፡»
[ዩኑስ: 24]



فكل ما ترى  أية من آيات الله ....فسبحان الملك !

ጥራት የተገባህ ነህ፣ የአሸናፊዎች አሸናፊ፣ የኃያላኖች ኃያል የሆንከው ጌታችን አላህ
||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

03 Jan, 21:23


አንድ ጥያቄ… ለአክሱም "ጽዮን ማሪያም" ሒጃብ ከልካዮች፦

ምንም እንኳ ፎቶው ትክክል ባይሆንም፤ ጸጉሯ የተገለጠበት የማሪያም ፎቶ ካላችሁ ላኩልኝ።
ከሌለ፤ ለምንድን ነው የሌለው?

"ቅድስቲቷን" ከተማችሁን የሚያረክሳት ጸጉርን መሸፈን ነው ወይንስ ጸጉርን ገልጦ መራቆት?
ዝሙት፣ ናይት ክለብ፣ ሴተኛ አዳሪዎች፣ አስካሪ መጠጥ… ይህ ሁሉ ጸያፍ ተግባር ነው ከተማዋን ማርከስ ያለበት ወይንስ መሸፈን?

እሺ! ጸባችሁ "ኢስላም" እና "ሙስሊም" ከሚለው ጋር ነው ብንል፤ ሙስሊምነት ነው ወይንስ እነዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውና ሌሎችም ያልተጠቀሱ ወንጀሎች የሚያረክሱት?
በርግጥ አጠጣጣችሁ እና መራቆታችሁ በመጽሐፋችሁ የታዘዛችሁ በሚመስል ደረጃ ነው። ግን በእናንተም መጽሐፍ መራቆት የተፈቀደ አልነበረም'ኮ!

ቅንጭላታችሁ ግን ከምንድን ነው የተሠራው?

እስኪ ጸጉሯ የሚታይበትን ፎቶ ቶሎ ላኩልኝ!

ጥያቄው ካልደረሳቸው አድርሱልኝ!

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

31 Dec, 18:48


ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል ወይ?

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ።

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَنْ تَشبَّهَ بقومٍ فهوَ مِنهُمْ﴾

“ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እሱ ከነሱ ነው።”

📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡ 4831

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

27 Dec, 12:26


DW Amharic እና VOA Amharic ለአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የዜና ሽፋን ስለሰጣችሁ እናመሰግናለን።

እነዚያ የሴቶች መብት ተብዬዎች፣ የሰብዓዊ መብት ተብዬዎች… ሙስሊም አጥፊ ሲመስላቸው እንጂ ሲበደል የት አሉ?
እነዚያስ የህዝብ ድምፅ ነን የሚሉ አክቲቪስቶች፣ ሚዲያዎችና የሚዲያ ሰዎች የት አሉ?

አሁንም እንላለን… መገላለጥን የፈቀደች ሃገር እምነትን አክብሮ መሸፈንን ልትከለክል አይገባም።

ሁል ጊዜ በየአመቱ በወሳኝ የትምህርት እርከኖች ላይ ቀን እየጠበቁ የሙስሊሞችን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ጉዞ ማሰናከል ለአንዴና ለመጨረሻ ሊያከትም ይገባል።


የቪኦኤ የአማርኛ ድምፅ ዘገባ በዚህ ሊንክ ይገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/38910

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

27 Dec, 07:08


ኒቃብን የሚከለክሉ ትልልቅ የትምህርትና መሰል የመንግስት ተቋማት የሚያቀርቡት አሳማኝ የሚመስላቸው ትልቁ ምክንያትና ማስተባበያ «ማንነታቸውን ለመለየት አስቸጋሪ ስለሆነ በነርሱ ተመሳስሎ ያልተፈቀደለት አካል ይገባል!» ይላሉ።

እኛ ደግሞ ምንም እንኳ ኒቃብ የከለከሉት ለዚህ ሳይሆን ከጥላቻና ትምክህተኝነት የመነጨ መሆኑን ጠንቅቀን ብናውቅም፤ በሴት ጥበቃዎች ማንነታቸው ከመታወቂያቸው ጋር ተመሳክሮ ይፈተሽ፣ አንዳንድ ጊዜ የግድ ከሆነም ተገልጣ ማንነቷን አሳይታ መልሳ መሸፈን ትችላለች… ብለናል። ግን የክልከላው ምንጭ ጥላቻ ስለሆነ አይሰሙም።

የኒቃብ ክልከላ ምንጩ ጥላቻ መሆኑን ማሳያው ሒጃብ መከልከሉ ነው። ምክንያቱም ሒጃብ ፊትን ስለማይሸፍን፤ ከትምህርት ቤቱ ዩኒፎርም ጋር የተመሳሰለ ሒጃብ መልበስ ምንም ከልካይ ነገር አልነበረውም። ጭራሽ ሒጃብ አልከለከልንም፤ እኛ ያልነው ጸጉራቸውን ይግለጡ ነው። ጸጉራቸው ውስጥ ምን ደብቃችኋል የኛ ደናቁርቶች? ለስሙ በትምህርት ተቋም ውስጥ ርዕሰ መምህር፣ መምህር፣ አስተዳደር… ተብላችሁ ተሰይማችኋል። ግን ት/ቤቱ ጭንቅላታችሁ ላይ ቢገነባም የሚገባችሁ አትመስሉም። እና ጸጉራቸው ከተገለጠ ሒጃቡን እንደ ስካርቭ አንገታቸው ላይ አድርገው ዘንጠው ይግቡበት? ምን ጉድ ናችሁ? በየቀኑ ስንት በያይነት የሆነ ጅል ነው የምናስተናግደው ጓዶች?

«ሞኝ ባያፍር፣ የሞኝ ዘመድ ያፍር!» እንዲሉ፤ እናንተ ለተናገራችሁት እኛ መስማት ተሳቀቅን።
አሁንም ከዚህ በላይ ድንቁርናችሁ ሳይጠናበት ቶሎ ፍቀዱላቸውና ይግቡ።

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

26 Dec, 06:32


ሴኩላሪዝም ማለት መንግስትን ከሃይማኖት መነጠል ማለት ነው። ኢትዮጵያ ሲደርስ ግን ትርጉሙን ይቀይራል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሴኩላሪዝም ማለት ሙስሊም ተማሪዎችን እምነታዊ አለባበሳቸውን ሰበብ እያደረጉ ከትምህርት ማእድ ማራቅ ነው። ሴኩላሪዝም ለሽፋንነት ይነሳል እንጂ አላማው በአፄው ዘመን የነበረውን ሙስሊሞችን ከትምህርት ማእድ የማራቅን ክፋት ማስቀጠል ነው። ሴኩላሪዝም ማመሀኛ ብቻ ነው። ከድሮው በተሻለ ወደ ትምህርት የዞረው የሙስሊም ቁጥር በአንፃራዊነት ጨምሯል። ይሄ ሐቅ እንቅልፍ የሚነሳቸው፣ የተማረውን ሙስሊም እንደ ስጋት የሚያዩ አካላት ታዲያ ስልጣናቸውን በመጠቀም ሰበብ እየፈለጉ ሙስሊሙን ከትምህርት ለማራቅ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም።

ፈተናዎቹን ሁሉ እንደ ምንም ተቋቋመህ ተማር ወገኔ። ጠላት መማርህን እንደ ስጋት ቆጥሮ በዚህ ልክ ተግቶ ከትምህርት ሊያፈናቅልህ የሚተጋው ለምን እንደሆነ ይግባህ። ራስህንም ሆነ ልጆችህን ከትምህርት ገበታ በማራቅ ባላሰብከው አቅጣጫ የጠላት አጀንዳ እያሳካህ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

23 Dec, 07:49


የተገላለጠችዋን ሲሆን "ምን ታውቃለህ ውስጧ ንፁህ ሊሆን ይችላል" ይላል።
ኒቃብ የለበሰችውን ግን "ከጀርባዋ ምን እንዳለ ምን ታውቃለህ?" ይላሉ።

(لَقَدِ ابْتَغَوُا الْفِتْنَةَ مِنْ قَبْلُ وَقَلَّبُوا لَكَ الْأُمُورَ)

"ከዚህ በፊት ሁከትን በእርግጥ የፈለጉ ሲሆን ነገሮችንም ሁሉ ገለባብጠውልሀል፡፡"
[አተውባ: 48]

ተነካክቶ የተተረጎመ
=
https://t.me/IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

23 Dec, 07:49


ጀምዕ የሚደረጉ ሶላቶች
~
1- ጀምዕ ማለት ሁለት ተከታታይ ሶላቶችን በአንደኛው ወቅት መስገድ ነው። ጀምዕ የሚደረጉት ሶላቶች የሚከተሉት ናቸው፦
- ዙህር እና ዐስርን በአንደኛው ወቅት
- መግሪብ እና ዒሻእን እንዲሁ በአንደኛው ወቅት መስገድ ይቻላል።
ከዚህ ውጭ ጀምዕ የለም። የሱብሕ ሶላት ከየትኛውም ሶላት ጋር ጀምዕ አትደረግም። እሷም ወደ ሌላ ወቅት አትውወሰድም። ሌሎችም ሶላቶች ወደሷ አይውወሰዱም። 0ስርን ከመግሪብ ጋር ጀምዕ ማድረግም አይቻልም።

2- ጀምዕ በሁለት መልኩ ሊፈፀም ይችላል።
1ኛው፦ የኋለኛውን ሶላት ወደ መጀመሪያው በማምጣት። ይሄ ጀምዑ ተቅዲም ይባላል። ዐስርን ከዙህር ጋር በዙህር ወቅት ፤ ወይም ዒሻእን ከመግሪብ ጋር በመግሪብ ወቅት መስገድ ነው።
2ኛው ጀምዑ ተእኺር ይባላል። የመጀመሪያውን ሶላት ወደ ኋለኛው ወስዶ መስገድ ነው። ይህም ዙህር እና ዐስርን በዐስር ወቅት ፤ መግሪብንና ዒሻእን በዒሻእ ወቅት መስገድ ነው።

3- ጀምዕ ከሐጃ ጋር የተያያዘ ነው። መንገደኛም ይሁን በሃገሩ ኗሪ ሶላትን በወቅቱ መስገዱ የሚከብደው ከሆነ ሁለቱን ሶላት በአንደኛው ሶላት ወቅት ጀምዕ ማድረግ ይችላል። ህመምተኛ፣ ነፍሰ ጡር፣ አጥቢ፣ ሌሎችም እያንዳንዱን ሶላት በወቅቱ መስገዳቸው የሚከብዳቸው አካላት በዚህ መልኩ ሊፈጽሙ ይችላሉ። ልብ በሉ! ያለ ተጨባጭ ምክንያት ልማድ እንዲያደርጉ አይደለም።

4ኛ፦ በጀምዕ ጊዜ የሶላቶቹን ቅደም ተከተል መጠበቅ ይገባል። ዙህር እና ዐስርን ጀምዕ የሚያደርግ ሰው ጀምዑ ተቅዲምም ይሁን ጀምዑ ተእኺር መጀመሪያ ዙህርን ያስቀድማል። ካሰላመተ በኋላ 0ስርን ይሰግዳል። መግሪብ እና ዒሻእን ጀምዕ የሚያደርግም ሰው እንዲሁ መጀመሪያ መግሪብን ይሰግዳል። ካሰላመተ በኋላ ዒሻእን ያስከትላል።

5ኛ፦ ጀምዕ እና ቀስር ተያያዥ አይደሉም። ቀስር ማለት ባለ አራት ረከዐ ሶላቶችን ሁለት አድርጎ አሳጥሮ መስገድ ነው። ይሄ ጉዞ ላይ ላለ ሰው ብቻ የሚፈቀድ ነው። በሃገሩ ኗሪ የሆነ ሰው አራቱን ረከዐ ሁለት አድርጎ ማሳጠር አይፈቀድለትም። እንዲሁም ማሳጠር ሱብሕ እና መግሪብን አይመለከትም። በየትኛውም ሁኔታ የረከዐቸው ቁጥር አይቀየርም።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

22 Dec, 14:59


♥️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ♥️

⚡️ቁርዓንን የተሰጠው ነብይ ማነው

♥️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና📨

🎀መልሱን በመንካት ውሰዱ 🎁🎁🎁

♥️ ሙሀመድ [ﷺ]

♥️ ሙሳ [عليه السلام]

♥️ ኢብራሒም [عليه السلام]

♥️ ዒሳ [عليه السلام]


⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ፡ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው⚠️

♥️♥️መልካም እድል♥️♥️

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

20 Dec, 14:57


🌱ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌱

⚡️የአላህ መልዕክተኛ ነቢዩ ሙሀመድ ﷺ የት ተወልደው የት ሞቱ

🌸ከትክክለኛው መልስ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና Add የሚለውን በመንካት ውሰዱ🎁🎁🎁

⚡️ ሪያድ ፣ መካ 『 رياض ، مكة 』

⚡️ መካ ፣ መዲና『  مكة ، مدينة 』

⚡️ ጣኢፍ ፣መዲና『  طائف ، مدينة 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ፡ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

✅️መልካም እድል✅️

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

19 Dec, 06:59


﴿وَيَرَى الَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ الَّذِي أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ هُوَ الْحَقَّ وَيَهْدِي إِلَى صِرَاطِ الْعَزِيزِ الْحَمِيدِ﴾.

«اللَّهُمَّ اهْدِنَا إلَيْكَ صِرَاطًا مُّسْتَقِيمًا».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

18 Dec, 14:53


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

😀ለፆመኞች የተዘጋጀው የጀነት በር ምን ይባላል

ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና Add የሚለውን በመንካት ውሰዱ🎁🎁🎁

🅰️ ባቡል ጂሃድ『 باب الجهاد 』

🅱️ ባቡል ሀጅ 『   باب الحج』

🔠ባቡ-ር-ረያን 『  باب الريان  』

🔠 ባቡ-ስ-ሶላት『  باب الصلاة 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል😀

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

14 Dec, 12:19


💐💐ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💐💐


🔘ባለን ዕውቀት ወደ ዲን መጣራት በሚል ርዕስ፡


🔈በወንድም ኢብኑ ያሲን  [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።

ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00
🔜ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡


📱 https://t.me/tewhedandsuna

⭐️በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

14 Dec, 12:19


የደመቀች ፀሀይ ውበቷ ቢጣራም
ፀሀይ ካልጠለቀች ጨረቃ አታበራም
አዕላፍ ቢመስሉም በቁጥር ቢልቁም
ጨረቃም ካልጠፋች ከዋክብት አይደምቁም
ህይወትም እንዲህ ነች...
እንሰጋለን እንጂ በችግር ሲጨልም
ካልጨለመ በቀር ብርሃን አናይም።

Suda

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Dec, 17:15


ሁልጊዜም አስታዉሱ ሱጁድ ላይ ያለ ባሪያ ዙፋን ላይ ካለ ንጉስ ይበልጣል።

t.me/IbnuHashm

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Dec, 12:17


• ﴿فَٱذۡكُرُونِیۤ أَذۡكُرۡكُمۡ﴾.

- «سُبْحَانَ اللهِ».
- «الحَمْدُ للهِ».
- «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ».
- «اللهُ أكْبَرُ».
- «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ».
- «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ».
- «رَبِّ اغْفِرْ لِي وَتُبْ عَلَيَّ إنَّكَ أنْتَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Dec, 03:26


የጁመአ ስጦታ
#ሱረቱል ኻህፍ
#ቃሪእ ምርጥ ድምፅ የለው *ሚሻሪ ራሺድ አል_አፋሲ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

12 Dec, 14:59


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

😀ለፆመኞች የተዘጋጀው የጀነት በር ምን ይባላል

ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና Add የሚለውን በመንካት ውሰዱ🎁🎁🎁

🅰️ ባቡል ጂሃድ『 باب الجهاد 』

🅱️ ባቡል ሀጅ 『   باب الحج』

🔠ባቡ-ር-ረያን 『  باب الريان  』

🔠 ባቡ-ስ-ሶላት『  باب الصلاة 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል😀

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

12 Dec, 13:44


💐💐ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💐💐


🔘ባለን ዕውቀት ወደ ዲን መጣራት በሚል ርዕስ፡


🔈በወንድም ኢብኑ ያሲን  [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።

ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00
🔜ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡


📱 https://t.me/tewhedandsuna

⭐️በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

06 Dec, 20:42


﴿وَلِأَهْلِكَ عَلَيْكَ حَقًّا،﴾

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

06 Dec, 10:56


ለጓደኛው «እስኪ የጀነትን ጸጋ ግለፅልኝ?» አለው።

ጓደኛውም «በርሷ ውስጥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ አሉ!» አለው።


اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

05 Dec, 14:51


🌱ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ🌱

🔘ጁማዓ ቀን ሱና የሆነው የቱ ነው

⚠️ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌹Add የሚለውን በመንካት  ውሰዱ🤌

⚡️ 🚿 ሻወር መውሰድ 🧼

⚡️ 👕ጥሩ ልስ መልበስ👟

⚡️🧴ሽቶ መቀባት ለወንዶች

⚡️ ጥፍርን መቁረጥ

⚡️ ሲዋክ መጠቀም🪥

⚡️🕋በጊዜ ወደ መስጂድ መሄድ🕌

⚡️ሱረቱል ካህፍን መቅራት

⚡️በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድ

⚡️ሁሉም መልስ ናቸው


🔘🩵መልካም እድል🩵😀

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

04 Dec, 19:02


የምድራችን ውብ ቦታ❤️

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

03 Dec, 16:28


ℹ️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄℹ️

💎በእስልምና 『በሂጅራ』 አቆጣጠር 9️⃣ኛው ወር ምን ይባላል⁉️

⚡️ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⚡️

🔥Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  ረጀብ 『 رجب 』

ለ}  ረመዷን 『رمضان 』

ሐ}  ሸዕባን  『 شعبان 』

መ}   ሸዋል   『شوال 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

03 Dec, 08:47


አንድ ሰው ለዐብደ-ል'ሏህ ኢብኑ ዲናር "ምከረኝ!" አለው።
ዐብደ-ል'ሏህም እንዲህ አለው፦ "ለብቻህ በምትሆንባቸው ጊዜያቶች ላይ አላህን ፍራ!"

[ሒልየቱ-ል-አውሊያእ: 10/359]

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

03 Dec, 08:33


عن أبي هريرة رضي الله عنه قال :
قال رسول الله ﷺ :

"مَنْ نَفَّسَ عَنْ مُؤْمِنٍ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ الدُّنْيَا نَفَّسَ اللهُ عَنْهُ كُرْبَةً مِنْ كُرَبِ يَوْمِ القِيَامَةِ ، وَمَنْ سَتَرَ مُسْلِمًا سَتَرَهُ اللهُ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ ، وَمَنْ يَسَّرَ عَلَى مُعْسِرٍ يَسَّرَ اللهُ عَلَيْهِ فِي الدُّنْيَا وَالآخِرَةِ ، وَاللهُ فِي عَوْنِ العَبْدِ مَا كَانَ العَبْدُ فِي عَوْنِ أخِيهِ".

[مسند الإمام أحمد].
--------
በአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ላይ እንዲህ አለ፡-
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡-

" ሙእሚንን ከዱንያ ችግር ያወለቀ አላህ የቂያማ ቀን ጭንቀትን ያገላግልለታል ሙስሊምንም የጠበቀ አላህ በዱንያ ይጠብቀዋል።" የመጨረሻይቱም ዓለም በችግር ውስጥ ላለ ሰው ነገሩን የሚያቃልል ሰው አላህ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻው ዓለም ያገራለታል፡ ባሪያውም ወንድሙን እስከረዳ ድረስ አላህ ይረዳዋል።

(የኢማም አህመድ ሙስነድ)።

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

01 Dec, 11:21


ረስቶ ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና ይሰግዳል። ምክንያቱም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا تقبل صلاة بغير طهور
"ያለ ውዱእ ሶላት ተቀባይነት የላትም።" [ሙስሊም]

لا تقبل صلاة أحدكم إذا أحدث حتى يتوضأ
"ያንዳችሁ ሶላት - ውዱእ ካጠፋ - ውዱእ እስከሚያደርግ ድረስ ተቀባይነት የለውም።" [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]

* ሳያውቅ ወይም ረስቶ በተነጀሰ ልብስ ወይም ጫማ ከሰገደ በኋላ ያስታወሰ ግን ሶላቱን አይመልስም። መሀል ላይ ካስታወሰ የሚመቸው ከሆነ የተነጀሰውን ጥሎ ባለበት መቀጠል ይችላል። ማስረጃው ነብያችን ﷺ በአንድ ወቅት እያሰገዱ እያሉ ጂብሪል ጫማቸው ላይ ነጃሳ እንዳለ ሲናግራቸው አወለቁ። ሶላታቸውን እንደገና ከመጀመር ይልቅ ባለበት መቀጠላቸው ያላወቀ ሶላቱ እንደማይበላሽ ይጠቁመናል።
©IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

30 Nov, 21:13


ጉዳዩን ለአላህ የተወ ሰው፤ አላህ ከተመኘው በላይ ይሰጠዋል።

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

30 Nov, 07:04


በህዝባዊ መጓጓዣ ላይ ያን የጅል ሳቅ ያለበትን ቲክቶክ ጭምር እየከፈታችሁ ሰው አትረብሹ። ቢቻል ለራሳችሁም ይቅርባችሁ፤ አሊያ ግን ሰው አትረብሹ፤ ኤርፎን ተጠቀሙ።

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

28 Nov, 15:47


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

የጀነት ገበያ የምትቆመው በየትኛው ቀን ነው

🌱ትክክል መሆናቹን የምታቁት ከመልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

add በማለት ውሰዱ

🔘መልካም እድል🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

27 Nov, 20:57


«ጊዜ ለሰጠን አላህ "ጊዜ አጣሁ!" ከማለት ይጠብቀን!»🤲

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

27 Nov, 19:34


ለኒቃቢስቶች ክብር ለሚሰጡ ሁሉ አክብሮት አለን።

ቤተል በ40 ሜትሩ እናት/ፓሽን ካፌና ሬስቶራንት

(ከነ ባለቤታቸው (መሕረማቸው) ለሚወጡ ነው እሺ! ብቻሽን ከቤት ወጥተሽ ተጠቀሚ አላልኩም!)

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

26 Nov, 15:03


🌹የምስራች ለ ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️

⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️ ባለቤቶች🌷

💜አላማችን የሱና ቻናሎችን ለሁሉም ማዳረስ ነው💜

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

⚠️ያለን ቦታ አነስተኛ ስለሆነ ሳይቀደሙ ይቅደሙ⚠️

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

⚠️ማሳሰቢያ❗️

1️⃣ኛ፡ ከ 1k በታች አንቀበልም
2️⃣የሱና ቻናል ብቻና ብቻ
ነው የምንቀበለው

3️⃣ምዝገባ በነፃ ነው

🌱ለመመዝገብ ➪ @ibnurahmeto🌱

🔠🔤🔤🔠   ⚡️🔤🔤🔠

🔘መልካም እድል🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

25 Nov, 04:17


ትልቁ ጭንቀታችን አኼራ መሆን አለበት

የሰውልጅን ከኢማን ለማሶጣት የሚያደርጉት የተለያዩ ዘዴዎች አሉ
ቀጥተኛ መንገድ ሚመራው አላህ ብቻ ነው
አላህ እውቀት ሰቶክ እውቀትህን በአጋግቡ ተጠቀምበት አለበዛህ ግን የቃሩን እ ጣፉንታ ይደርስካል 
ሰለፎች ደአዋ ለማንም ያደርጋሉ
እውቀትን ግን አደብ ላለው አማና ለሚወጣ ነው ሚያስተምሩት
ሰሀቦች  (መጀመሪያ የተማርነውኢማን ነው ቁርአን ከማመር በፊት)
መላሂካ ላንተ ስጁድ አርገዋል ላንተ ክብር ሲባል
( በኡስታዝ ማህሙድ አሰን)

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

24 Nov, 15:33


ℹ️ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄℹ️

💎በእስልምና 『በሂጅራ』 አቆጣጠር 9️⃣ኛው ወር ምን ይባላል⁉️

⚡️ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና⚡️

🔥Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  ረጀብ 『 رجب 』

ለ}  ረመዷን 『رمضان 』

ሐ}  ሸዕባን  『 شعبان 』

መ}   ሸዋል   『شوال 』

መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላችሁም ማለት ነው

🔘መልካም እድል🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

21 Nov, 15:34


ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ

አባታችን አደም 『عليه السلام』 የተፈጠሩት በየትኛው ቀን ነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

Add🎁የሱና ቻናሎች📥 የሚለውን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ}  እሁድ 『الأحد 』

ለ}  ሐሙስ 『الخميس 』

ሐ}  ጁሙዓህ 『 الجمعة 』

መ}   ሰኞ  『الاثنين 』

⚠️መልስ ስትመልሱ ምንም ነገር ካልመጣ ትክክል አይደላቹም ማለት ነው⚠️

🔘🩵መልካም እድል🩵🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

21 Nov, 05:06


#ሽርክ

#ሽርክ ማለት አምልኮን ከአላህ ውጪ ለሆነ አካል ማካፈል ማለት ነው።

ሽርክ አላህ ዘንድ ምህረት ከሌላቸው ትላልቅ ወንጀሎች አንዱ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَنْ يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَلِكَ لِمَنْ يَشَاءُ وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَى إِثْمًا عَظِيمًا " سورة النساء 48

"አላህ በርሱ ማጋራትን በፍፁም አይምርም፤ ከዚህ ሌላ ያለውንም

(ኀጢአት) ለሚሻው ሰው ይምራ...

#የጧት ዚክር

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

▪️የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

ውሎህን በዚክር ጀምር

〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡
اللّهـمَّ أَنْتَ رَبِّـي لا إلهَ إلاّ أَنْتَ ، خَلَقْتَنـي وَأَنا عَبْـدُك ، وَأَنا عَلـى عَهْـدِكَ وَوَعْـدِكَ ما اسْتَـطَعْـت ، أَعـوذُ بِكَ مِنْ شَـرِّ ما صَنَـعْت ، أَبـوءُ لَـكَ بِنِعْـمَتِـكَ عَلَـيَّ وَأَبـوءُ بِذَنْـبي فَاغْفـِرْ لي فَإِنَّـهُ لا يَغْـفِرُ الذُّنـوبَ إِلاّ أَنْتَ
    
               #ፈዘኪር   
                 

   💐ሰባሃል ... ኸይር 🥀🥀

https://t.me/ibnuyasir11

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

20 Nov, 20:01


﴿اشْتَرَوْا بِآيَاتِ اللهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَصَدُّوا عَن سَبِيلِهِ إِنَّهُمْ سَاءَ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ﴾.

«‏اللَّهُمَّ بَرِّئْ قُلُوبَنَا مِنَ الشِّرْكِ وَالكِبْرِ وَالنِّفَاقِ وَالرِّيَاءِ وَالسُّمْعَةِ وَالرِّيبَةِ وَالشَّكِّ فِي دِينِكَ .. ‏يَا مُقَلِّبَ القُلُوبِ ، ثَبِّتْ قُلُوبَنَا عَلَى دِينِكَ ، ‏وَاجْعَلْ دِينَنَا الإسْلَامَ القَيِّمَ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

20 Nov, 19:04


<< ቁርአንም በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ።ጸጥም በሉ። ይታንዘንላችኋልና!!!
ጌታህንም በምስጥር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው።ከዘንጊዎች አትኹን። እነዚያ ጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክትም) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም። ያወዱሡታልም።ለእርሱ ብቻ ይሰግዳሉ።>>
Ibnu Hashim
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuHashm

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

17 Nov, 19:12


ሰኞና ሀሙስ ስራዎች ወደ አሏህ ይቀርባሉ።

ፆመኛ ሁነን ስራችን ወደ አሏህ እንዲቀርብ ነገ ሰኞ ነውና እንፁም።

እንፁም፡
እናስፈጥር፡
እናስታውስ፡

ሙእሚን ከመልካም ነገር አይጠግብምና።

https://t.me/abufurat
https://t.me/abufurat

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

17 Nov, 15:31


💜ቀላል እና አስተማሪ የሆነ ጥያቄ💜

የነቢዩ 『 ﷺ』 አጎት እና የጥቢ ወንድም ማነው

🌱ከትክክለኛው መልሱ በስተጀርባ ጠቃሚ ሊንክ ይሰጣችኋልና🌱

መልሱን በመንካት ውሰዱ🌹

ሀ〗ሐምዛ 『رضي الله عنه 』

ለ〗ዐባስ 『رضي الله عنه 』

ሐ〗ዑመር 『رضي الله عنه 』


🔘⭐️መልካም እድል⭐️🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

17 Nov, 07:06


አንድ ሰው ካማኸው ምንድን ነው መፍትሄው?

እንዳማኸው ካወቀ በግልፅ ወዳማኸው ሰው ሂድና ይቅርታ (ዐውፍታ) ጠይቀው።

ካላወቀ፦ አላህ ወንጀሉን እንዲምርለት ዱዓእ አድርግለት፣ በዛ ባማኸው ቦታ ስለርሱ ጥሩ ጎን አውራና አወድሰው። መልካም ሥራ መጥፎን ያብሳልና!

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

16 Nov, 17:02


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

16 Nov, 16:56


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

15 Nov, 18:55


💜ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም💜

نور التوحيد وظلمات الشرك
የተውሒድ ብርሃን እና የሺርክ ጨለማዎች በሚል ርዕስ

🩵በኡስታዝ ፉኣድ ከማል [حفظه الله] የዳዕዋ ፕሮግራም በአሏህ ፈቃድ ይቀርባል።


ሰአት፡ ቅዳሜ ከምሽቱ 3️⃣🔤3️⃣0️⃣ ጀምሮ።

የሚተላለፍበት ቻናል፡

https://t.me/abufurat

🔘በሱና ቻናሎች ጀመዓ የተዘጋጀ🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

15 Nov, 11:04


🌷 የምስራች ለ 🔠🔤🔠🔤🔠

🔤🔠🔠🔠🔠🔤🔠 ባለቤቶች 🌹

⭐️ የሱና ቻናሎችን የማስፋፋት ፕሮጀክት ⭐️

ያለን ቦታ አነስተኛ ነው 20 ቻናሎችን ብቻ አየተጠባበቅን እንገኛለን

🆘ሳይቀደሙ ይቅደሙ🆘

🌸የሱና ቻናል ባለቤቶች  ቻናላቹን ማሳደግ  የምትፈልጉ በነፃ መመዝገብ ትችላላቹ🌸

🔤🔤🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤

1k+ Subscribers    🔘
5k+ Subscribers   🔘
10k+ Subscribers  🔘
15k+ Subscribers  🔘
20k+ Subscribers  🔘

የሱና ቻናል ያላችሁ ሰዎች ጥሩ አጋጣሚ ነው ኑ ተቀላቀሉን

ከ 1k በታች አንቀበልም

🩷ለመመዝገብ ➪ @IbnuRahmeto 🩷

🔠🔤🔠🔤   🔠🔤🔠🔤  

🤎መልካም እድል🤎

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

15 Nov, 08:37


ሶለዋቱ ረቢ ዐለይሂ ሰላሙ!

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

15 Nov, 03:03


ሱረቱል  ካፍ   
ከጁመዓ ቀን ሱናዎች
↩️‏ سنن_يوم_الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐ الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي ﷺ
🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት  ማብዛት
اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

15 Nov, 03:01


﴿إِنَّ اللهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾.

«اللَّهُمَّ اجْعَلْ صَلَوَاتِكَ وَبَرَكَاتِكَ وَرَحْمَتَكَ عَلَى سَيِّدِ المُرْسَلِينَ وَإمَامِ المُتَّقِينَ وَخَاتَمِ النَّبِيِّينَ مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ وَرَسُولِكَ إمَامِ الخَيْرِ وَقَائِدِ الخَيْرِ وَرَسُولِ الرَّحْمَةِ ، اللَّهُمَّ ابْعَثْهُ مَقَامًا مَحْمُودًا يَغْبِطُهُ بِهِ الأوَّلُونَ وَالآخِرُونَ ، اللَّهُمَّ تَقَبَّلْ شَفَاعَتَهُ الكُبْرَى وَارْفَعْ دَرَجَتَهُ العُلْيَا وَآتِهِ سُؤْلَهُ فِي الآخِرَةِ وَالأُولَى كَمَا آتَيْتَ إبْرَاهِيمَ وَمُوسَى .. اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

14 Nov, 16:06


በቴሌግራም ምርጥ ምርጥ የሱና ቻናሎችን
ይፈልጋሉ
⁉️

⚡️🤎ስልኩን በመጫን ይቀላቀሉን🤎⚡️

💐🌹ለመ🀄️🀄️🌹💐
       ≼👇👇👇
┌───────────┐╯
‌│⫸╭─━━━━━━╮⫷│╯
│⫸│  ╰─ ━ ─╯    │⫷│╯
│⫸│▅▅▅▅▅▅▅│⫷│╯
‌│⫸│╰╮ • ★•╭╯   │⫷│╯
│⫸┃┊  ŝùñãĥ ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊ channal     │⫷│╯
│⫸┃┊  ŵãvê  ┊    ┃⫷│╯
‌│⫸┃┊  ▓🌹▓  ┊    ┃⫷│╯
│⫸┃╰─◦◇◦╯    ┃⫷│╯
‌│⫸┃██████    ┃⫷│╯
│⫸│→         ━        ←┃⫷│╯
│⫸╰━━━━━━━╯⫷│╯
╰━━━━━━━━━━━╯╯
𝐀𝐝𝐝 𝐘𝐨𝐮𝐫 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
        👇👇👇👇
🔘WAVE :- @ibnurahmeto🔘

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

14 Nov, 12:47


ሸይኽ ሳሊህ አል ፈውዛን እንዲህ ብለዋል፡-

“አንድ ሙስሊም ከመናገሩ በፊት ቃላቱን መመዘን ይኖርበታል፣  ንግግሩ ሊያስከትል የሚችለውን አዎንታዊ እና አሉታዊ  ውጤታቸውን ማጤን አለበት፣ ቃላቱን በትክክለኛ ሚዛን መዝኖ ሲያበቃ፣ ቃላቱ ለመልካም ሰበብ ከሆነ ይናገር፣ አሊያ ግን  ሸርን የሚያስከትል እና ለሸር ሰበብ ከሆነ ክፋቱን ከሰዎች ሊከላከል ይገባል።”

📚 ["ሸርሑ ኪታቢ አልፊተን ወል ሓዋዲስ" (ገጽ 239)]

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/FuadKemal

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

13 Nov, 20:38


﴿فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ﴾.

«اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِلمُؤْمِنِينَ وَالمُؤْمِنَاتِ ، وَالمُسْلِمِينَ وَالمُسْلِمَاتِ ، وَألِّفْ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ، وَأصْلِحْ ذَاتَ بَيْنِهِمْ ، وَانْصُرْهُمْ عَلَى عَدُوِّكَ وَعَدُوِّهِمْ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

12 Nov, 03:39


ረሱል «صَلَّى اللهُ عَلَيهِ وَسَلَّم» እንዲህ ብለዋል፦

"የአማኝ ጉዳይ አስገራሚ ነው። ነገሩ ሁሉ መልካም ነው። ይህ ደሞ ለአማኝ እንጂ ለማንም አይደለም።

መልካም ነገር ሲያጋጥመው ያመሰግናል ለሱ መልካም ይሆንለታል።
ችግር ሲያጋጥመው ይታገስና ለሱ መልካም ይሆንለታል።"

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

12 Nov, 03:17


﴿وَالْبَاقِيَاتُ الصَّالِحَاتُ خَيْرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابًا وَخَيْرٌ أَمَلًا﴾.

«سُبْحَانَ اللهِ ، وَالحَمْدُ للهِ ، وَلَا إلَهَ إلَّا اللهُ ، وَاللهُ أكْبَرُ ، وَلَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

08 Nov, 09:58


ጣፋጭ ኩርኩም
~
ህንዳዊ ሃኪም ነው። ፂሙ ከደረቱ ደርሷል። አንድ ፂሙን የላጨ በቁርኣንና ሱና ላይ የጠለቀ እውቀት ያለው የአዝሀር ሊቅ ጋር ተገናኘ። ህንዳዊው ስለ ፂም ጠየቀው።

የአዝሀሩ ሊቅ፡ "ፂም ማሳደግ የፈፀመው የሚመነዳበት፣ የተወው የማይቀጣበት ሱና ነው" ብሎ መለሰለት።

ህንዳዊው ሃኪም፡ "እኔ ምንም እንደምትል አላውቅም። ግን የአላህ መልእክተኛ እንደኔ ናቸው? ወይስ እንዳንተ? " አለው።

አዝሀሪዩ ፡ "አይ እንዳንተ ናቸው" ብሎ መለሰ።

[ሸርሑል ሙሐረር፡ 114]

* አንዳንዱ በእውቀት ካንተ ቢያንስ እንኳ አሻራው እድሜ ልክህን የማይጠፋ ቁንጥጫ ይሰጥሃል።
እይታህ ቢለይ እንኳ ከፍ ያለውን መምረጥ ላይ አይንህን አትሽ።
{ أَتَسۡتَبۡدِلُونَ ٱلَّذِی هُوَ أَدۡنَىٰ بِٱلَّذِی هُوَ خَیۡرٌۚ }
"ያንን እርሱ ዝቅተኛ የሆነውን በዚያ እርሱ በላጭ በሆነው ነገር መለወጥን ትፈልጋላችሁን?" [አልበቀረህ፡ 61]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

22 Oct, 05:34


ንብረት እየተቃጠለባቸው ያሉ እህቶችና ወንድሞች፤ ዘመዶቻቸው ወይም ጓደኞቻቸው ካላችሁ አብራችኋቸው ሁኑ። በዚህ ሰዓት ስለሚደነግጡ እና ስለሚደናገራቸው እንዳይጎዱ። ሸይጧንም ስላለ!
በአካል ባታገኟቸው እንኳ በስልክ። ደብሯቸው ስልክ ካላነሱ በቴክስት አብሽር ብላችሁ ላኩላቸው። «ብቸኝነትና ትካዜ ቀንሶ ሰው አለኝ!» የሚል ስሜት ይፈጠራል።

ግን ሙስሊም አላህን ከያዘ ለዱኒያ አይጨነቅም። እስከ መቼ እንደምንቆይ የማናውቅ ፍጡሮች ነን። ነገ ለወራሽ ጥለነው እንሄዳለን እንጂ ተከትሎን አይሄድም። ለኛ የሚጠቅመን ዛሬ የሰደቅነውና መልካም ሥራችን ነው። እዚህ የሚቀረው የኛ አይደለም። አታስቡ! ትናንት ምንም ሳይኖረን ሰጥቶን የነበረው አላህ፤ ኢንሻ አላህ ነገም የተሻለ ይተካናል። አብሽር ከልብህ በአላህ ተማምነህ ሶብር ካደረግክ ከነ ሪዝቅህ የፈጠረህ አላህ ጥሎ አይጥልህም። እርሱ የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋው አያድርም። አትጨነቅ ምን እንደተያዘልህ አታውቅም። ካልታገስክ ግን ንብረትህንም ምንዳህንም ታጣታለህ። ከታገስክ ደግሞ ምንዳህን ከዚያ ንብረትህንና የተሻለ ነገርን ታገኛለህ።

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

21 Oct, 19:24


አይይ…
አብሽሩ እዛ ሱቅ ያላችሁ ወንድምና እህቶች!
አሁን ላይ እንኳን እሳት ተከስቶ ወቅቱም እሳት ሆኗል። አብሽር! አላህ የወሰነው መሆኑ አይቀሬ ነው። ጥበብ አለው። አታስቡ። ስንቶች ወድቀው ተነስተዋል። በመናደድና በመተከዝ የሚቀየር ነገር ስለማይኖር በአላህ ላይ ከልባችሁ ተመኩና ወደርሱ ስሞታችሁን አቅርቡ።

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

21 Oct, 19:24


አሁን ባለንበት የፈሳድ ተጨባጭ፤ እንኳን በንብረታችን ላይ በእኛ ላይ እሳት አለመዝነቡ የአላህ እዝነት ነው።

እንደት ሰው ይህን የግርግር አጋጣሚ ተጠቅሞ እሳት ለማጥፋት መረባረብና ማዘን ሲገባው ይሰርቃል? ወሏሁ-ል-ሙስተዓን! የሰረቅከውን ሳትበላ ይውሰድህ አንተ እርጉም!

ምን አይነት የስብዕናና የፈሳድ ጥግ ላይ ብንደርስ ነው እንዲህ ከግብረ ገብነት የወጡ፣ ለማሰብ እንካ የሚከብዱ ገራሚ ገራሚ ወንጀሎችን የምንፈፅመው?

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

19 Oct, 08:07


ልብ የሚያሞቅ ፎቶ
===============
አዎ! ደስ የሚል ፎቶ ነው። የአላህ ሰላም በዚህ ቤት ባለቤት (ባል) ላይ ይሁን። አንዳንዶች ይህን ፎቶ ተንተርሰው «የህፃኗ መብት ተጨቆነ!» እያሉን ነው። ታዲያ "deformed males" ወደሚሉሽ ወደነ አርስቶትል፣ "Woman was God’s second mistake." (ሴቶች መፈጠራቸው የፈጣሪ ሁለተኛ ስህተት ነው!" ወደሚሉሽ እነ Friedrich Nietzsche አይነት ደፋር መሄዱ ይሻላል? የነ ኢማኑዔል ካንት፣ የነ ኦቶ ዌይኒንገርና ዳርዊንንማ ባላነሳው ይሻላል።

ለማንኛውም ህፃናት ወላጆቻቸው ከሚናገሩት በላይ የሚተገብሩትን ይቀስማሉ። ውዱዕ ሲያደርጉ ቅደም ተከተሉን ባይጠብቁም አዘበራርቀው ቢሆንም ይታጠባሉ፣ ሲሰግዱ ወላጆቻቸው የሚያደርጉትን እያዩ ለመስገድ ይሞክራሉ። ሴት ህፃን ልጅ እናቷ ኒቃብ ለባሽ ከሆነች የእናቷን ኒቃብ እያነሳች ለመልበስ ትሞክራለች፤ ባታውቅበትም። ይህ የተለመደና በተለይ ልጅ ያለው ሰው የሚያውቀው ነው።

ታዲያ ይህቺ ከታች በፎቶው የምንመለከታት ህፃን ኒቃብ መልበሷ ምንድን ነው ወንጀሉ? ከፎቶው እንደምንመለከተው እርግጥ ነው እድሜዋ ኒቃብ ዋጂብ በሚሆንባት ደረጃ ላይ አይደለችም። ግን ሳትገደድ በፈቃዷ ልልበስ ካለችና መልበሷ በርሷ ላይ የሚያመጣው አካላዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ አዕምሯዊና ከጤና ጋር የተያያዘ ችግር እስከሌለው ድረስ በራሷ ፈቃድ ደስ ብሏት ብትለብስ ምንም ችግር የለውም። «እናቴ አስገድዳ አልብሳኝ ነው!» ብላ ለናንተ ያሰሞተች ይመስል በዚህ ደረጃ መወረፉ ለኒቃብ ካለ ክብር ማነስ ወይም ጥላቻ ወይም አለማወቅ ካልመነጨ በስተቀር ሌላ አይሆንም።

በርግጥ አልፎ አልፎ አንዳንድ በግድ የሚያስለብሱ ካሉ አላህን ሊፈሩ ይገባል። ማስገደዱ ኋላ ሲያድጉ እንዲጠሉት ሊያደርግም ስለሚችል ጉዳቱ የከፋ ነው።

ነገር ግን በፈቃዳቸው ከለበሱና ችግር ካላስከተለባቸው ኋላ መልበስ የሚገባቸው እድሜ ላይ ሲደርሱ በቋሚነት ሲለብሱት ቀድመው የለመዱት ስለሆነ አይቸገሩም።
ይህ ደግሞ ከመልካም ተርቢያ ነው። ኒቃብ መልበስን ጨምሮ ሶላት፣ ጾም፣ ሐጅ፣… ግደታ እድሚያቸው ላይ ሳይደርሱ ማላመድ ጥሩ ነው።

ውዱ ነቢይ ﷺ:
("مروا الصبي بالصلاة إذا بلغ سبع سنين، فإذا بلغ عشر سنين فاضربوه عليها")
[አቡ ዳውድ: 418]

«አንድ ህፃን 7 አመቱ በደረሰ ጊዜ ሶላት እንዲሰግድ እዘሱት፤ 10 አመቱ በደረሰ ጊዜ ግረፉት!» ያሉት ቀድሞ በ7 እንዲሰግድ መታዘዙ ግደታ ስለሆነበት ሳይሆን ለማለማመድ ነው።

ልክ እንዲሁ ጾምም ገና ግደታ ሳይሆንባቸው ማለማመድ ያለ ነው። ረቢዕ ቢንት መዕወዝ በጾም ወቅት ልጆቻቸውን አስጹመዋቸው ወደ መስጅድ እንደሚሄዱና እዛ መጫዎቻ አድርገውላቸው አንዳቸው ርቦት ሲያለቅስ ኢፍጣር ባይደርስም እንኳ ምግን ይሰጡት እንደነበር ተናግራለች።
"... ونصوّم صبياننا الصغار منهم، ونذهب إلى المسجد فنجعل لهم اللعبة من العهن (الصوف) فإذا بكى أحدهم من الطعام أعطيناه ذاك حتى يكون عند الإفطار"

[አል-ቡኻሪይ: 1824፣ ሙስሊም: 1919]

የዘንድሮው ረመዿን የሆነ ቀኑን ከጠዋት 5:00 ላይ እያፈጠረ፣ የሆነውን ከቀኑ 8:00፣ የሆነውን ከቀኑ 11:00፣ የሆነውን በኢፍጣር ወቅት… ወዘተ እያለ ሲለማመድ ልክ ግደታ ሲሆንበት ሙሉ ወሩን ለመፆም አይቸገርም።

ይህቺ ታዳጊም ዛሬ ጁሙዓህ እንደዚህ ለብሳ ከሆነ ነገ ሰፈሯ ብትሄድ ሱሪ ሁላ ለብሳ ከእኩዮቿ ጋር እቃ እቃ እየተጫዎተች ልታገኛት ትችላለች። ከፈለገችም እስካልተገደደች ድረስና ኢንጆይ እስካደረገችው ድረስ ከወደደችው በዚሁ ሁኔታዋ እድሜዋ ዋጂብ እስከምትሆንበት ልትደርስ ትችላለች። መብቷ ነው።

ግን አሁን ባለችበት እድሜ ኒቃብ ለብሳ እቃ እቃ ስትጫዎት ብታያት፤ «እንደት ኒቃብ ተለብሶ እቃ እቃ!፣ ሳያውቁ ዝም ብለው ኒቃብ እየለበሱ…!» ካልክ፤ ህፃኑ አንተ ነህና ተቀበላትና አንተ እቃ እቃ ተጫወት። አንዳንዶች ትልቅ ሆነውም ኒቃብ ለብሰው አደብ የሌላቸውና ከነርሱ የማይጠበቅ ነገር የሚፈፅሙ ልታይ ትችላለህ። ያኔ በጅምላ ኒቃቢስቶችን ከመፈረጅና ሳያውቁ እየለበሱ ከማለት፤ ለዚያ እኩይ ድርጊት የዳረጋቸው ኒቃብ መልበሳቸው ሳይሆን የራሳቸው እኩይነት ነው። እነዚህ ቢለብሱም ባይለብሱም ድርጊቱን ከመፈፀም ወደ ኋላ አይሉም ነበር ማለት ነው።

ለማንኛውም እይታችንን እንገርዝ። ሁሉም በኛ ጫኛ ገብቶ ካልተለካ አንበል። አንዳንድ ጊዜ አለማወቃችንን ብንደብቀው አዋቂ መስለን በኖርም ነበር። እረፉ! በተለይ ኒቃብ ለባሽ ሆናችሁ ይህን በደፈናው የምትተቹ ሰዎች ሳታውቁ የለበሳችሁት እናንተ መሆናችሁን ያሳብቃል። እንደ ኢስላም ሴት ልጅን ያከበረ እና ነፃነት የሰጣት የለውም። የበፊቱ የፍልስፍናው ዘመን ሴት ልጅን በእንስሳነት፣ የአሁኑ የሳይንስና የስልጣኔ ተብዬ በነፃነት ስም ለጾታዊ ብዝበዛና መጠቃቀሚያነት አውሎ ያከበረ መስሎ አዋርዷታል። በእስልምናሽ ኩሪ፣ አብቢ፣ ንገሺ።

ሰላም በነዛ በዚህ የፈሳድ ዘመን ተቆጥበውና ሁሉን ቻሌንጅ ተቋቁመው ኒቃብ በለበሱ የዘመናችን እንቁዎች ላይ ይሁን!
ሰላም በነዛ ሴት ልጆቻቸውን፣ እህቶቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ኒቃብ ባለበሱ ወንድ የሆኑ ወንዶች ላይ ይሁን!

||
t.me/MuradTadesse
x.com/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

18 Oct, 14:17


ይህ ከጀርመን ጎዳናዎች አንዱ ነው።

ሰዎች ለድሆች እና በልተው ማደር ላቃታቸው ችግረኞች ምግብ በፌስታል አምጥተው ያንጠለጥላሉ።

ቦታው ላይ ምንም አይነት ይህንን የሚገልጽ ማስታወቂያ የለም፣ ካሜራም አልተገጠመም፣ ምግቡን ሲያስቀምጡ እና ችግረኞችም ምግቡን ሲወስዱ አብረን ፎቶ ካልተነሳን የሚላቸው የለም። ሲመገቡ ቪዲዮ እየቀረፀ የሚያጎርሳቸው የለም።

ምግቡ፣ ፌስታሉ እና ችግረኞቹ ብቻ ነው የሚተዋወቁት።

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው!!

የተቀዳ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

17 Oct, 18:11


عن طلحة بن عبيدالله رضي الله عنه قال :

قُلْتُ : يَا رَسُولَ اللهِ ، كَيْفَ الصَّلَاةُ عَلَيْكَ؟. قَالَ : "قُلِ «اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إبْرَاهِيمَ إنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ»".

[مسند الإمام أحمد].

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

11 Oct, 05:24


በኪንታሮት ህመም ለምትሰቃዩ ሁሉ
እኔ በምጥ ምክንያት ተባብሶብኝ ብዙ ተሰቃይቻለሁ መኖር እስክጠላ ድረስ በሀበሻ መድሀኒትም አስወጥቼ ነበር መልሶ ተካ ስቃዩን የምታቁ ታቁታላችሁ ድንገት ቲክቶክ ሳይ አንድ ኡስታዝ ስለኪንታሮት ያስተማረው ትኩረቴን ሳበው እድንበታለሁ ብዬ ነይቼ እሱ ባዘዘው መሰረት ሰርቼ ተጠቀምኩት ወላሂ አልሃምዱሊላህ እንደዚህ ጤንነት ተሰምቶኝ አያቅም በ5 ቀን ውስጥ ህመሙ ተወኝ አልሀምዱሊላህ እናንተም አምናችሁ ከተጠቀማችሁ ትድናላችሁ እሱም ብዙ ሰው ድኖበታል ብሏል የሚያስፈልገው 1ጥቁር አዝሙድ ዘይት(ንፁህ)እኔ ፍሬውን በደንብ ፈጭቼ ነው የተጠቀምኩት 2 ሽታ የሌለው ቫዝሊን 3 የወይራ ዘይት
መጠን ሩብ ግማሽ ሊትር ሀይላንድ የወይራ ዘይት ጥቁር አዝሙድና ቫዝሊኑን በግምት ነው ያረኩት እነዚህን አቀላቅለን 7 የቁርዓን ምዕራፎችን 7 ጊዜ መቅራት
1.ሱረቱል ፋቲሀን 7 ጊዜ ቀርተን ውህዱ ላይ 3 ጊዜ ቢስሚላህ እያልን መተንፈስ ኡፍፍ ማለት
2.አያተል ኩርሲን 7 ጊዜ ቀርተን 3 ጊዜ መተንፈስ
3. አመነ ረሱሉን 7 ጊዜ ቀርተዘን እንደዛው👆
4.ለው አንዘልና ሀዘል ቁርዓን 7 ጊዜ ቀርተን እንደዛው
5ቁልሁወላሁ አሀድ (ሱረቱል ኢኸላስ)7ጊዜ ቀርተን በተመሳሳይ
6 ቁል አኡዙ ቢረቢል ፈለቅ(ሱረቱል ፈለቅ)7 ጊዜ ቀርተን በተመሳሳይ
7 ቁል አኡዙ ቢረቢናስ(ሱረቱ ናስ )7 ጊዜ ቀርተን በተመሳሳይ ከዛ ውህዱን በደንብ ካቀላቀልነው በኋላ ማታ ማታ በቀዝቃዛ ውሃ እየታጠብን መቀባት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ትንሽ ይለበልባል መቻል ነው ጠዋትም በውሃ ብቻ ታጥበን መቀባት ኢንሻአላህ በአጭር ቀን ትድናላችሁ በደንብ እስከሚሻላችሁ ድረስ አታቋርጡ
ማሳሰቢያ ውህዱ ቁርዓን የተቀራበት ስለሆነ ሽንት ቤት ውስጥ መቀባት አይቻልም ቁርዓኑን እራሳችሁ መቅራት ካልቻላችሁ ሌላ ሰው ይቅራላችሁ አላህ ሰበብ ያድርግላችሁ

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

10 Oct, 19:48


﴿فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ﴾.

«اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِلمُؤْمِنِينَ وَالمُؤْمِنَاتِ ، وَالمُسْلِمِينَ وَالمُسْلِمَاتِ ، وَألِّفْ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ، وَأصْلِحْ ذَاتَ بَيْنِهِمْ ، وَانْصُرْهُمْ عَلَى عَدُوِّكَ وَعَدُوِّهِمْ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

08 Oct, 05:15


እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ!
~
እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው። ለማን ነው ይህን ያደረግሽው? አላህ ምን ይለኛል ብለሽስ አስበሻል? ተይው አላህ ዘንድ ሰው ዘንድ ራሱ ያስንቅሻል። ከጌታሽ ተጣልተሽ፣ ሰዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ወድቀሽ ምን ትርፍ ታገኛለሽ?

ለማንኛውም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا ؛ قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُءُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا "
"ሁለት አይነት ሰዎች ከእሳት ጓዶች ውስጥ ናቸው። እኔ አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ።)
* እንደ ከብት ጅራት ያለ መግረፊያ ይዘው ሰዎችን በነሱ የሚደብድቡ ሰዎች እና
* ለብሰው የተራቆቱ፣ ለሌሎች ጥፋታቸውን የሚያስተምሩ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ፣ ፀጉሮቻቸው እንዳዘነበሉ የተከመሩ የግመል ሻኛዎች የሆኑ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነትን አይገቡም። ሽታዋንም አያገኙም። ሽታዋ ከብዙ ርቀት የሚገኝ ነው።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

08 Oct, 04:15


#ተውሂድን_ለአላህ_ብቻ_ባሪያ_መሆንን_ለየት_ባለ_አገላለፅ_የቀረበ
   👉በኡስታዝ ማህሙድ ሀሰን
የአላህን ኒዕማ ለመቁጠር ብትሞክሩ…
        የነርቭ ሲስተሙ
    መረጃ የሚያስተላልፉ
 
#በሰውነታችን_ውስጥ_ያለውን_የአላህን ኒዕማ እንቁጠር ብንል እንኳን ቢያንስ 3 ሚሊየን አመት መኖር አለብን
    
   ድሮ ሰው የፈለገው ሀገር ያለማንም ፍቃድ መኖር ይችል ነበር
   አለም ሰለጠነ ተብሎ አንተ እስረኛ ነህ
      #አለም_በሰለጠነች_ቁጥር_በሆነ_ሰው_ቁጥጥር_ስር_ትሆናል

    የወንጀል ውጤት እዚህ ታየዋለህ
      👉ላንተ የሚጠቅምህ ነገር ሁሉ ያስጠላሃል
   #በአሁን ሰአት ብዙዎቻችን ከአላህ ሀቅ ይልቅ ስለራሳችን ሀቅ ነው የምንጨነቀው
  

     👉ነብያቶች በዱንያ ተሸንፈው ያውቃሉ በኢማን ግን በፍፁም

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

08 Oct, 04:12


እልፎች በሕመም ሲዳክሩ አንግተዋል .... አፊያ የነበሩት ታመው አድረዋል ..... የነበራቸው አጥተው አድረዋል .... የከበሩት ከስረዋል ፣ ያቀዱት ወድሞባቸዋል .... ከሁሉም ደግሞ ሐ-ይ የነበሩት ጀናዛ ሆነዋል። ሌላ እድል ስለተሰጠን፣ የትናንት አዳፋችንን ማፅጃ ስለተቸረን፣ ከጀሊል እዝነት መዳረሻ እስትንፋስ ስለተለገስን ... አልሐምዱሊላህ!


አልሐምዱሊላህ.... ስላነጋን!

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

08 Oct, 04:10


ወዳጄ ሲበዛ የዋህ አትሁን ፤ በተለይም ሰዎች ይወዱኛል ብለህ በማሰብ ራስህን የዋህ አታድርግ ፤ ምክንያቱም ሲበዛ የዋህ በሆንክ ቁጥር ይበልጥ አንተ ላይ እየተጠቀሙብህ እና ጉልበትህን እየጨረሱ ይሄዳሉ ።

➨ አስተውል ፦

አንዲት ንብ አንድን አበባ የምትወደው ውስጡ ላይ ያለው መአዛ እስኪያልቅ ድረስ ብቻ ነው ፤ ልክ መአዛው ሲያልቅ ንቧ ወደ ሌላ አበባ ትሄዳለች ።

ስለዚህ አንተም ሲበዛ የዋህ በሆንክ ቁጥር የአበባው እጣ ፈንታ እንደሚርስ እወቅ ።

መልካም ቀን!

t.me/IbnuHashm

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

07 Oct, 15:04


﴿وَلَوِ اتَّبَعَ الْحَقُّ أَهْوَاءَهُمْ لَفَسَدَتِ السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ وَمَن فِيهِنَّ بَلْ أَتَيْنَاهُم بِذِكْرِهِمْ فَهُمْ عَن ذِكْرِهِم مُّعْرِضُونَ﴾.

«اللَّهُمَّ أرِنَا الحَقَّ حَقًّا وَارْزُقْنَا اتِّبَاعَهُ ، وَأرِنَا البَاطِلَ بَاطِلًا وَارْزُقْنَا اجْتِنَابَهُ».

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

06 Oct, 04:09


ነገ ኢሬቻ ለመሄድ አስበሃል⁉️
====================
ሙስሊም ሆነህ ሳለ ነገ ለሚከበረው የኢሬቻ (የዋቄፌታ ኃይማኖታዊ በዓል) ለመሄድ ዝግጅትህን አጠናቀሃል? የሚገዙ ልብሶችንና የሚያዙ ነገሮችን ሸማምተሃል?

እንግዲያውስ ሸይኽ ኣደም ቱላ (ረሒመሁ-ል'ሏህ) እንዳሉት፤ በዓሉን አክብረህ ስትመለስ ቀጥታ ወደ መስጅድ ገብተህ ከመስገድህ በፊት ሸሃዳ ያዝና ገላህን ታጥበህ ግባ።

*
ለማንኛውም ወንድሜ፤ መቼ እንደምትሞት አታውቅምና የጓደኞችህ ቀጠሮም ሆነ ውስወሳ ሳይሸነግልህ ለአላህ ብለህ ማክበሩን ተወው።
ብሔርህንና ማንነትህን አትጥላ። ግን ከእምነትህ ጋር የሚጋጭን ከማንነትና ብሔር ጋር የተያያዘን ነገር ተው።

ለአላህ ብለህ ከተውከው ውዱ ነቢይ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
( إنك لن تدع شيئاً لله عز وجل إلا بدلك الله به ما هو خير لك منه )
«አንተ ላቅና ከፍ ላለው አላህ ብለህ አንድን ነገር አትተውም፤ ለአንተ በርሱ ከርሱ የበለጠ የተሻለን የቀየረልህ ቢሆን እንጂ!»
[አሕመድ: 21996]
*
በል! እንግዲያስ የተሻለን ነገር አላህ እንዲለውጥልህ ከፈለግክ የስሜትን ውስወሳና ሞቅታ ተወውና ከዲንህ ጋር ከሚጋጭ ነገር ራቅ።
«እኔ እዛ ሂጀ አላከብርም!» ብለህ አትሸንግል።
እዚያ መሄድ የምትችለው አቅሙ ካለህ ሰዎችን ለማስተማር እንጂ ባትተገብርም ለመታደም አይደለም።
አላህ ያግራልህ።


ስለ ኢሬቻ በዝርዝር ማንበብ የፈለገ ይህን በዚህ አስፈንጣሪ ያገኛል።
https://t.me/MuradTadesse/31980

||
t.me/MuradTadesse

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

06 Oct, 04:08


Irraa if-eegaa ይጠንቀቁ! ያስጠንቅቁ!

የኦሮሚያ ታላቁ ዐሊም እና ሙፍቲ የሆኑት ሸይኽ አደም ቱላ ኢሬቻን አስመልክቶ የሰጡትን ምላሽ ያድምጡ።

«ሙስሊም ሆኖ ኢሬቻን ማክበር አይቻልም የሰይጣን ስራ ነው። የሙስሊም ባህሉ ሃይማኖቱ ነው። ኢሬቻ ነፃ ያወጣኛል የሚል ሙስሊም እምነቱ አደጋ ላይ ነው።»
[ሸይኽ አደም ቱላ ከተናገሩት]

Namni muslima tahe Ayyaana Irreechaa akka hin dhayne.

𝙺𝚎𝚠𝚜𝚎𝚛 |ᴩᴏꜱᴛꜱ

06 Oct, 04:02


﴿قُلْ أَرَأَيْتُمْ إِنْ أَتَاكُمْ عَذَابُهُ بَيَاتًا أَوْ نَهَارًا مَّاذَا يَسْتَعْجِلُ مِنْهُ الْمُجْرِمُونَ • أَثُمَّ إِذَا مَا وَقَعَ آمَنتُم بِهِ آلْآنَ وَقَدْ كُنتُم بِهِ تَسْتَعْجِلُونَ • ثُمَّ قِيلَ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذُوقُوا عَذَابَ الْخُلْدِ هَلْ تُجْزَوْنَ إِلَّا بِمَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ • وَيَسْتَنبِئُونَكَ أَحَقٌّ هُوَ قُلْ إِي وَرَبِّي إِنَّهُ لَحَقٌّ وَمَا أَنتُم بِمُعْجِزِينَ﴾.

«اللَّهُمَّ زَيِّنَّا بِزِينَةِ الإيمَانِ ، وَكَرِّهْ إلَيْنَا الكُفْرَ وَالفُسُوقَ وَالعِصْيَانَ ، وَاجْعَلْنَا مِنَ الرَّاشِدِينَ .. نَسْألُكَ يَا رَبَّنَا أنْ نَكُونَ هُدَاةً مَهْدِيِّينَ ، غَيْرَ ضَالِّينَ وَلَا مُضِلِّينَ ، سِلْمًا لِأوْلِيَائِكَ ، وَحَرْبًا عَلَى أعْدَائِكَ .. تَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ ، وَأحْيِنَا مُسْلِمِينَ ، وَألْحِقْنَا بِالصَّالِحِينَ ، غَيْرَ خَزَايَا وَلَا مَفْتُونِينَ».