✞ኬብሮን @kebbron Channel on Telegram

✞ኬብሮን

@kebbron


👉በዚህ ቻናል

📖የተመረጡ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ተከታታይ ታሪኮች
ወግ
ብሂላተ አበው
የኢትዮጵያ ጥንታዊ ታሪክ
ከተለያዩ መፃህፍት እና ንግግሮች የተመረጡ ፅሁፎችን

" ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤"
(1ኛቆሮ 8:2)



💚💛❤️ማንኛውምንም ጠቃሚና አስተማሪ ፅሁፍ ካሎት @Teshubotላይ ይላኩልን*

✞ኬብሮን (Amharic)

ይህ ቻናል ለዘላለም በመመለስ ትምህርትን እንደሚወስደን ሰላም እና ፊት ለዋጋችን ያበረርኩናል። "ኬብሮን" በዚህ ቻናል የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማክሰኞት እና ሎሚኒትን ለመታለል የሚያሰብስበት የድምፅ ቋንቋ ነው። በእንግዲህ በተመሳሳይ ጽሁፎችና ወግ እና ብሂላተ አበው ወይም የኢትዮጵያ አበባዊ ታሪክ ለመስጠት ነው። በተለያዩ መፃህፍት እና ንግግሮች የተመረጡ ፅሁፎችን ይከታተላል። ምንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤ (1ኛቆሮ 8:2) ማንኛውምንም ጠቃሚና አስተማሪ ፅሁፍ ካሎት @Teshubotላይ ይላኩልን።

✞ኬብሮን

18 Jul, 10:28


Great app to earn FREE gift cards, PayPal cash, or mobile recharge. Enter code KN2ME1 to receive 500 coins instantly!
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.gettocash.app

✞ኬብሮን

01 Jun, 18:03


😲 የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 
➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋር ያገኛሉ


📍 አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
      📱  Tel.  0995975237
                     
                     

.

✞ኬብሮን

23 May, 17:49


😲 የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 
➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋር ያገኛሉ


📍 አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
      📱  Tel.  0995975237
                     
                     

.

✞ኬብሮን

20 May, 20:46


😲 የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 
➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋር ያገኛሉ


📍 አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
      📱  Tel.  0995975237
                     
                     

.

✞ኬብሮን

17 May, 05:03


😲 የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
የ ምስራች ለ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ!

መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች መማር ይፈልጋሉ ?

 
እምቢልታ መንፈሳዊ የዜማ መሳርያዎች  ማሰልጠኛ  ተቋም 
➜  በገ ና
➜  ክራር
➜ መሰንቆ
➜ ዋሽንት

   በሚፈልጉት ቀን እና ሰዓት  እንዲሁም በግል ቤት ለቤት  እናስተምራለን ! በተጭማሪ  ጥራት ያላቸው  የበገና , የክራር , መሰንቆ እንሸጣለን እናከፋፍላለን የክራር የበገና የመሰንቆ ቦርሳ እኛ ጋር ያገኛሉ


📍 አድራሻችን  -  ጀሞ 1 ሩት የገበያ ማዕከል
                            
      📱  Tel.  0995975237
                     
                     

.

✞ኬብሮን

08 May, 04:04


🤱💍 ከበዓል በኃላ ለሰርጎ , ለልጆቾ ክርስትና የዲኮር ስራ ማሰራት ይፈልጋሉ ?



🎈 ለ ሰርግ                            🎈 ለ ክርስትና
🎈 ለ ልደት                            🎈 ለ ቀለበት
🎈 ለ ገዓት                             🎈 ለ ሽምግልና
🎈 ለ ተማሪዎች ምረቃ           🎈 ለ ልጆች ልደት
🎈 ለ ቤት ምርቃት                  🎈 ለ ሆቴል ምረቃ
🎈 ለ ስብሰባ አዳራሾች          🎈 ለ ቤተሰብ ኘሮግራሞች
🎈 ለ ሰርግ ለመኪና ዲኮር
🎈በ ቤተክርስቲያን ስርዓት ለሚፈፀሙ ሰርጎች እና ኘሮግራሞች

💎🌹 ለተለያዮ ዝግጅቶችም ጭምር የተለያዮ የዲኮሪሽን ስራዎችን እንሰራለን እንዲሁም የተለያዮ የዲኮር እቃዎችን እናቀርባለን !
       

      👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇 👇👇
              ይህን ይጫኑት  ...  ይህን ይጫኑት

█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░         ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻      ▒▓█
█▓▒░        ►𝗢𝗽𝗲𝗻◄░►𝗢𝗽𝗲𝗻       ▒▓█


📞 Tel .   +251961064953
                 +251703504953
.

✞ኬብሮን

30 Apr, 12:50


ከዚህ በፊት እንደ ነገርኋችሁ ልጆቻቸውን በምግባር በሃይማኖት እንዲያድጉ የማያደርጉ ወላጆች የልጆቻቸው ገዳዮች ናቸው፡፡ እስኪ ንገሩኝ! ለዔሊ ልጆች መሞት ተጠያቂው ማን ነው? እርሱ ራሱ አይደለምን? እርግጥ ነው የጠላት ጦር ልጆቹን ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡ የአባታቸው የዔሊ ደንታቢስነት ግን ጦሩ ልጆቹን አነጣጥሮ እንዲወጋቸው አድርጎታል፡፡ ረድኤተ እግዚአብሔር ስለ ራቃቸው በፍልስጥኤማውያን ጦር ፊት እንዲቆሙ አደረጋቸው፡፡ በዚህም አባታቸው ራሱንም ልጆቹንም ገደለ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ይህንን ዕለት ዕለት በዓይናችን ፊት እያየነው ነው፡፡ የማይታዘዙትንና ሥርዐት የለሽ ልጆቻቸውን በአግባቡ መቅጣት የማይፈልጉ ወላጆች ስፍር ቊጥር የላቸውም! ልጆቻቸውን ጠንከር አድርገው መገሠጽን ይፈራሉ፡፡ የወላጆቹ እንደዚህ መኾንስ የሚያመጣው ውጤት ምንድን ነው? የልጆቹ ሥርዐት አልበኝነት ይጨምራል፡፡ አለመቀጣታቸው ወደ ዓመፃ ወንጀል ያመራቸዋል፡፡ ወደ ወኅኒ ይወሰዳሉ፡፡ ከዚህ እጅግ ከከፋም በሞት ይቀጣሉ፡፡ ወዮ! የራሳቸውንና የተፈቀደላቸውን የመቅጣት መብት ችላ በማለታቸው፥ ልጆቻቸውን ለከፋ ቅጣት አሳልፈው ይሰጣሉ፤ ሕዝባዊ ሕጉም ለራሱ የተፈቀደለትን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ እነርሱ (ወላጆቹ) እያዩአቸው በቀላል ቅጣት ሊያስተካክሏቸው ሲገባቸው፥ ይኸው ማንም አጠገባቸው በሌለበት አሰቃቂ ቅጣት ይፈጸምባቸዋል፡፡

© ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 162

✞ኬብሮን

02 Mar, 04:16


✞ኬብሮን:
#ያቺ_ሰአት

።እጅግ ወኔ የተሞላው እና የሚነሽጥ ለሊት ነበር ንጉሱ ባስነገሩት አዋጅ መሠረት ማንም ከቀየው የቀረ ያለ አይመስልም የወራት የመንገዱ ጉዞ ሣይበግራቸው ሁሉም ቦታቦታውን ይዞል:ካህናቱ በተተከለው ድንኳን ውስጥ ጽላቱን ይዘው ማህሌቱን ተያይዘውታል በሌላ ወገንም ቅኔው እንደጉድ ይዘረፋል:: ህዝቡም ቢሆን "በእውነት ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላል" የሚለውን ቅዱስ ቃል በመቀበል ሀገራቸውን ሊበትን ሀይማኖትን ሊያጠፍ የመጣውን ጠላት ለመመከት በንቃት ቆመዋል::
አንዳንዱ እንደመነሸጥ ሲያደርገው ከወደ ጥግ ወደ መሀል እየመጣ "ጦርሜዳ ላይ ጀርባዬን ተመትቼ ካገኘህኝ አንስተህ እንዳትቀብረኝ አሞራ ይብላኝ ፈርቼ ስሸሽ ነው እና ለፈሪ ሚገባው ይሄ ነው,: ግንባሬን ተመትቼ ካገኘህኝ ግን በክብር ቅበረኝ " ይላል
* ሰአቱ አልደርስያላቸውም ይቁጠነጠናሉ ግማሹ ጎራዴውን ይሞርዳል ግማሹ ጦሩን ይቀጠቅጣል ፈረሶቹም ቢሆን የበኩላቸውን ለመወጣት የቸኮሉ በሚመስል ሁኔታ ጭራቸውን እያወዛወዙ አለውልህ ይሉታል ጌታቸውን ባለፈረሱም ወገባቸውን መታመታ እያደረገ እንግዴ ፈረሴ አደራህን እንደ ይሁዳ በመጨረሻው ሰአት እንዳከዳኝ ባይሆን እንደ ሠማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጩፈረስ በርትተህ አበርታኝ ብሎ እንደወዳጁ ግንባሩን ሣም ያደርገዋል::
ፉከራው እና ሸለልቶው ደርቶል
+መሣርያውን ታጠቅ ሁሉም ይሠናዳ(2)
+ልክ ማስገባት ነው ይሄን ወራዳ አረጎራው አረጎራው
ስትል አንዶ
ባለገር አይዞሽ እያለች ገብታ
በሚሸንጥ ቅላጼ
+ በለው በለው እና አሣጣው መድረሻ (2)
+የሠውልክ አያቅም ባለጌ እና ውሻ ሀሀሀሀሀ
!ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
!ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
!አባሮ ገዳይ
አይዞህ
!ቆንጥር ለቆንጥር
ዘራፍ
!በሀገር ለመጣ
ዘራፍ
የማይበገር በለው አስኪ አንተዬ አረ በለው እያለች አንዶም ትገባና
+ያሣደግነው ጥጃ ለምለም ሣር አስግጠን(2)
+ፈርገጥ ፈርገጥ አለ እኛኑ ሊረግጠን.........አረጎራው አረጎራው

ሀገሬን ሀገሬን ሀገሬን እላለው
ኢትየጵያን ለጠላት እንዴት እሰጣለው
,

አረስጡኝ እማ ዝናር ጥይቴን(2)
ገፍቶ ለመጣ ሰው መመከቻዬን,,,አረጎራው አረጎራው

አሁን ወሣኞ ሠአት ደርሳለች ሠማዩላይ ያለው ጭለማ ባታውን ለብርሀን ለመስጠጥ እየተንጎራደደ ነው አብዛኛው ጦረኛ ዳዊቱን ገልጦ የመጨረሻውን ፀሎት እያደረገ ነው ካህናቱም ወደ ቅዳሴ ለመግባት መዘጋጀት ጀምረዋል ያለውን ድባብ ግን ተውት ያቺ ነጫጭባ በእግሮ ፈርጥጣ ሮም ካልገባች ምን አለ በሉኝ በዚ መሀል ወደ አስር ሰአት ገደማ የጠለት ጦር መንቀሳቀሱን የሠሙት አጼውና ንግስቲቱ እንዲሁም መኳንቱ ሰራዊቱን ማንቀሳቀስ ጀመሩ እንግዴ የተናቀው አቢሲኒያው ህዝብ ማንነቱን ለማሳየት ከፈጣሪው ጋር መጋዝ ጀመር ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,



እንበለው እና ጉልበት ጉልበቱን
እያፎቀቀ ይውጣው ዳገቱን

በሉ እንግዴ ብእሬን ከትቼ ከአባቶቼጋ በመንፈስ ወደ ፍልሚያው ልግባ።


"አድዋ የሁላችንም ታሪክ"


ተጻፈ የካቲት 2012

@kebbron
@kebbron

✞ኬብሮን

27 Feb, 03:55


ፆም ገባ ይሉኛል

ቀኑን ሙሉ ብፆም እስኪደርቅ አንጀቴ
ቅቤና ሥጋውን ባርቀው ከፊቴ
ዘውትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
ብቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዙም ባወድስ በሚጣፍጥ ዜማ
ድርሳናት ብተርክ ሚስጥር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ግዕዝን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴf
ሀሜትና አድመኝነት ካልጠፋ ከቤቴ
እኔን ብሎ ጿሚ ከንቱ ነው ፀሎቴ
ፈጣሪ ያዝንብኛል ፍቅር በማጣቴ


ምንጭfb

✞ኬብሮን

07 Jan, 04:45


"ኦ ለዝንቱ መንክር ልዑል ላዕለ ኩሉ ሕሊናት ብእሲት ምድራዊት ወለደቶ ለእግዚአብሔር ቃል ዘኮነ ሰብአ፡፡ ድንግል ወለደቶ ለገባሪሃ ወለሊሁ ፈጠረ ወላዲቶ ወእምኔሃ ነስአ ሥጋነ ዘውእቱ ፈጣሪ"
"ከሕሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ምስጢር አንክሮ ይገባል ምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ ከርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ"
(ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም)
እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

✞ኬብሮን

05 Dec, 17:52


" ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:4)

✞ኬብሮን

02 Nov, 00:55


✞ኬብሮን

“ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ - እስመ ወለድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን | ወስትየ ሕይወት ዘበአማን +++ ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሽለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን | እውነተኛ የጽድቅ መብልን እና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና
ሊቁ አባ ሕርያቆስ ( ቅዳሴ ማርያም )

@kebbron
@kebbron

✞ኬብሮን

26 Oct, 17:03


✞ኬብሮን



ወንድሜ ሆይ በዝናብ ጊዜ ከሚሞላው ሐይቅ ተማር።ዝናቡ በጣለና ውኃው ሐይቁን በሚሞላበት ጊዜ መጀመሪያ ላይ ውኃው ይደፈርሳል።ነገር ግን የዝናቡ ጊዜ ሲያልፍ በቆይታ ሐይቁ መጠኑ ከመጨመሩ በላይ እንደ መስታወት ጥርት ብሎ በውስጡ የሚመላለሱት ዐሣትን ያሳየናል።ስለዚህ ተወዳጆች ሆይ በመከራ ምክንያት ልባችሁ አይዛል።ጸጋ ሊሰጣችሁ ሲል መከራ ይመጣባኝኋልና መከራ ካለፈ በኋላ በጸጋው ይሞላችኋል፤ጽድቃችሁም በሰው ሁሉ ፊት የተገለጠ ይሆናል....



@kebbron
@kebbron

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

✞ኬብሮን

16 Oct, 17:35


ኬብሮን


ንስሐ ፦ ነስሐ ተፀፀተ ካለው የተገኘ ሲሆን ፤ ንስሐ ማለት በሠሩት ኃጢአት መፀፀት ፣ ማዘን ፣ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ መወሰን ማለት ነው። ንስሐ ከዘለዓለማዊ ፍርድ የሚያድን ፤ ዘማዊውን እንደ ድንግል ፤ ሌባውን መጽዋች የሚያደርግ በፊት ከተሠራው ኃጢአት ንጹህ አድርጎ ፤ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ የሚያደርግ ምሥጢር ነው ።

ከንስሐ በፊት

መፀፀት
አንድ ክርስቲያን በድፍረትም ይሁን በስህተት “የሠራው በደል” መጻሕፍት በማንበብ ፣ ከመምህራን ተምሮ ፣ የስብከት ካሴት አዳምጦ ፤ ህሊናው ወቅሶት ፣ ወይም በሌላ በአንድ ምክንያት ስህተት መሆኑን ከተረዳ በኋላ ተፀፅቶ ከእግዚ አብሔር ለመታረቅ (በደሉን ለማስተስረይ) የሚያደርገው ጉዞ ንስሐ ይባላል ። በሠራው በደል ሳይፀፀት ፤ ለጊዜው ህሊናውን ስለረበሸው ብቻ ንስሐ የሚገባ ሰው ፤ ከስሐውን በኋላ ወደ ቀደመ ሕይወቱ ሊመለስ ይችላል ። ምክንያቱም ፡ ንስሐ የገባው ፡ በሠራው በደል ከልቡ ተፀፅቶ ሳይሆን ፤ በስሜት ተነሳስቶ ነውና ፤

ኃጢአትን መጥላት
በበደላችን ከተፀፅትን በኋላ የሰራነውን በደል መጥላትና ወደፊትም መሥራት እንደሌለብን ራሳችንን ማሳመንና ከኃጢዓት መንገድ መራቅ ማለት ነው ።

❖ከንስሐ በኋላ ስላለው ሕይወት መወሰን
አንድ ምዕመን ንስሐ ከመግባቱ በፊት ለወደፊቱ የሚኖረውን ሕይወት አስቀ ድሞ መመርመርና መወሰን ይገባዋል የእግዚአብሔን ቃል ስንሰማ ለጊዜው ልባችን ሊነካ ፣ ምን እናድርግ ልንል እንችላለን ። የሐ ሥ 2 ፥ 37 ። ነገር ግን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ዓለሙን ወደመምሰል እንደማንመለስ አስቀድመን ራሳችንን መመርመር አለብን ። ብዙዎቹ በስሜት ወደ ክርስትና ከገቡ በኋላ ፤ በጊዜያዊ ነገር ተታለው በድንገት ከሃይማኖት መንገድ ወጥተዋልና ።

@kebbron
@kebbron

✞ኬብሮን

13 Oct, 19:42


✞ኬብሮን

ብሂላተ አበው


🙏እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ ›› አባ እንጦንስ

🙏ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል›› ቅዱስ አትናቴዎስ

🙏ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስን ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢአተኞች የሚገቡበት የገሃነም እሳት ግን ለዘላለም እንዲሁ ይኖራል፡፡›› ቅዱስ ሚናስ

🙏በማንም ላይ ክፋትን አትሥሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና›› ታላቁ አባ መቃርስ

🙏ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናለሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም›› ቅዱስ አርሳንዮስ

🙏ቤተክርስቲያን መጠሪያችን ነች ፤ ቤተ ክርስቲያን የኖኅ መርከብ ነች ፤ በውስጧ እንጠለላለን ከውጪው ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል›› ቅዱስ እንድርያስ

??🙏ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው›› ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ
??
🙏ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከሆነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስ ቅዱስ የተሞላን እንሆናለን ›› አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን

🙏የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተ ክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› ብፁዑ አቡነ ጎርጎሪዮ ካልዕ

🙏ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊትን በሙሉ ስትጸልይ እደር›› ቅዱስ ይስሐቅ ሶሪያዊ



🙏እራ?ራስህን በሐሰት አትውቀስ፤ ራስን መክሰስ ትህትና አይደልም ታላቁ ትህትና ሰዎች ሲወቅሱህ መታገስ ነው›› ቅዱስ ስራፕዋን

🙏አንደበቱን ከቧልት ፣ ከሐሜት፣ ያየውንም ምሥጢር ከመናገር የሚከለከል ሰው ልቦናውን ከሃልዮ ኃጢአት ያርቀዋል፡፡›› አርጋዊ መንፈሳዊ



?‹🙏ጸጋ ሲሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እንዳታጣ›› ማር ይስሐቅ

@kebbron
.

✞ኬብሮን

07 Oct, 04:03


✞ኬብሮን

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡

በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ? ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡ በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡ በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡

በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡ በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡ ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡

በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡ በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡

ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ? መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡

መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ጌጥ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡

© አምስቱ የንስሐ መንገዶች



@kebbron
@kebbron

✞ኬብሮን

06 Oct, 03:59


መስከረም 29 በክርስቶስ ስም አንገቷን ለሰይፍ የሰጠችው የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ በቀደምት የኢትዮጵያ ሊቃውንት ❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ ስለ ቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ቀደምት ሊቃውንት መስክረዋል፤ ሥዕሏን ሥለዋል፤ መልክእ ደርሰውላታል፤ የዚኽች ቅድስት ሰማዕት አባቷ ቴዎድሮስ እናቷ አትኖስያና ይባላሉ፤ በብፅዐት ያገኟት ልጅ በመኾናቸው በተወለደች በሦስት ዓመቷ በእመቤታችን ስም በታነጸች ቤተ ክርስቲያን አድጋለች።
እጅግ መልከ መልካም ነበረች። ቅዱስ ጳውሎስ “ያልተጋባች ሴትና ድንግል በሥጋም በነፍስም እንዲቀደሱ የጌታን ነገር ያስባሉ፤ የተጋባች ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንድታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።” (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥34) ያለውን አስባ ራሷንም በድንግልና ሕይወት ለክርስቶስ ለይታ ነበር። ከ284- 305 በሮም የነገሠው ከሓዲው ድዮቅልጥያኖስ መልኳ ውብ የኾነች ድንግል ሊያገባ ፈልጎ ቆንጆ መርጠው ያመጡለት ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው፡፡
❖ እነርሱም በፍለጋቸው በሮሜ አገር ባለች ቤተ ክርስቲያን ቅድስት አርሴማን በማግኘት ሥዕሏን ሥለው ለንጉሡ ላኩለት፡፡ ርሱም በእጅጉ ተደስቶ እንዲያመጧት በማዘዝ ወደ ሰርጉም እንዲመጡ ለመኳንንቱ ላከ፡፡
❖ ርሷና ዐብረዋት የነበሩትም ደናግል ይኽነን በሰሙ ጊዜ በማዘን ጌታችን በወንጌል “በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ” (ማቴዎስ 10፥23) ያለውን አስበው ድንግልናቸውን ይጠብቅላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በመለመን ከሮም ተነሥተው በስዉር የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደነበረችው ወደ አርመን ሸሽተው ኼደዋል፡፡
ቅድስት አርሴማም ወደ አርመንያ ሀገር በገባች ጊዜ ከሓድያኑ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የሚያምኑትን ክርስቲያኖችን ላይ መከራን ሲያጸኑባቸው ተመለከተችና
አምላካችን ክርስቶስ "ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።" (ማቴ 10:32-33) ያለውን በማሰብ “እኔ በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነትን የማምን ክርስቲያን ነኝ” በማለት መሰከረች፡፡
❖ የመልኳን ደም ግባትም በማየት ንጉሥ ድርጣድስም ለራሱ ስለተመኛት አምልኮቷን እንድትተው፣ ክርስቶስን እንድትክድ በብዙ ሽንገላን ሊሸነግሏት ቢሞክሩም አልኾነላቸውም፤ ከዚያም ፈርታ ትክዳለች ብለው በማሰብ ክርስቲያኖች ለአናብስት ወደሚጣሉበት አደባባይ በመውሰድ የተራቡ አናብስትን ሲለቅቋቸው ነቢዩ ዳንኤል እንዳደረገው በጸሎቷ ኀይል አናብስቱ ወደ ንጉሡ ወታደሮች በመወርወር ብዙዎችን ገድለዋል፤ ከዚያም ከሥሯ ተንበርክከው ሰግደውላታል፡፡
❖ ንጉሡ በዚኽ ባይኾንለት በግድ ለጣዖታቱ እንድትሰግድ አሳስሮ አማልክቱ ወዳሉበት ቤተ ጣዖት ሲወስዳት፤ በመስቀል ምልክት ብታማትብ በጣዖታቱ ላይ ዐድረው ሰዎችን የሚያስቱ አጋንንት እየጮኹ ሲወጡ ጣዖታቱ በመላ እየተሰባበሩ ወድቀዋል፤ ከዚያም በረኀብ ለመቅጣት ወደ እስር ቤት ቢያኖሯት መልአኩ ኅብስትን እንደ ኤልያስ መግቧታል፡፡
❖ ከዚያም ንጉሡ ወዳለበት እየጐተቱ ወሰዷት፤ “ወተንሥአ ንጉሥ እማዕከለ ዐውድ ወአኀዛ ከመ ያብኣ ውስተ ጽርሑ ለአርሴማ ድንግል ወሶቤሃ ኀደረ ኀይለ እግዚአብሔር ላዕለ አርሴማ ቅድስት ወገደፈቶ ውስተ ምድር” ይላል፤ ንጉሡ ይዞ ወደ እልፍኙ ሊያስገባት ከአደባባይ ተነሥቶ ድንግል አርሴማን በያዛት ጊዜ፤ ዳዊት ጎልያድን በእግዚአብሔር ኃይል እእንዳሸነፈ ቅድስት አርሴማም እላይዋ ላይ ባደረው የእግዚአብሔር ኀይል በምድር ላይ ጣለችው፤ ያን ጊዜ በዐፍረት ኾኖ ራሷ ይቈረጥ ዘንድ አዘዘ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን? ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው።" (ሮሜ 8:35-36) እንዳለ ያደረሱባት መከራ ሁሉ ከክርስቶስ ፍቅር ሊለያት አልቻለም።
ከዚያም የክብር ባለቤት ጌታችን እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስከትሎ ተገለጸላት። በቅዱስ መጽሐፍ ላይ “አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ፤” (ዘዳግም 7፥9) እንደሚል
ስሟን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ምሕረትን እንደሚያደርግ ቃል ኪዳንን ከገባላት በኋላ መስከረም 29 በ290 ዓ.ም. አንገቷን ተቈርጣ የሰማዕታትን አክሊል ተቀዳጅታለች።
አስቀድሞ በኢሳይያስ ዐድሮ "እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።" (ኢሳ 56:4-5) ብሎ እንደተናገረ በስሟም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ታኅሣሥ 6 ቅዳሴ ቤቷ ሲከበር፤ የከበረ ሰውነቷ ዛሬ ድረስ በአርመን አለ፡፡
❖ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በስሟ እየታነጹ ከክርስቶስ አምላኳ በተቀበለችው አማናዊ ቃል ኪዳንም ብዙ ሕሙማን እየተፈወሱ በረከቷን እያገኘን እንገኛለን፡፡ ታቦቷ ካለባቸው እጅግ ብዙ በረከት ካላቸው የሰማዕቷን ገድል ከተረጎምኩባቸው ቦታዎች መኻከል በደቡብ አፍሪካ በረስተንበርግ፤ በዱባይ እና በአውሮፓ ስኮትላንድ ግላስኮ ይገኛሉ፨
❖ ካመሰገኗት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀደምት ሊቃውንት ውስጥ ሊቁ አርከ ሥሉስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሚጠቀሱ ሲኾኑ፦
❖ ሊቁ አርከ ሥሉስም ይኽነን የቅድስት አርሴማ ተጋድሎ ሲመሰክር፡-
“በጾታ ኅሩያን ዕደው እንዘ ተኀብሪ ጾታ
እንበለ ትፍርሂ ምንተ ብልኀተ ኲያንው ወሰይፍ ልሳነ መንታ
ዘፈጸምኪ ስምዐ በእንተ ኢየሱስ ንጉሠ ኤፍራታ
ሰላም ለኪ አርሴማ ምስለ እምኪ አጋታ
ወለደናግል ሰላም ምስሌኪ ዘሞታ”
(በተመረጡ ወንዶች ወገንነት ተባብረሽ ኹለት አፍ ያለው ሰይፍንና የጦሮችን ስለትን ምንም ሳትፈሪ የኤፍራታ ንጉሥ ስለሚኾን ስለ ኢየሱስ ምስክርነት የፈጸምሽ አርሴማ ከእናትሽ ከአጋታ ጋር ሰላምታ ላንቺ ይገባል፤ ካንቺ ጋር የሞቱ ለኾኑ ደናግል ሰላምታ ይገባል) በማለት በኅብረት አመስግኗቸዋል፡፡
❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በተአምኆ ቅዱሳን ታላቅ መጽሐፉ ላይ፦
“ሰላም ለአርሴማ ቅድስት ከመ በቀልት ዘይመስል ቆማ
ወዘከለላ ዘመንፈስ ግርማ
ዘፈጸመት ገድላ በጻማ
ወበመንግሥተ ሰማይ ዐቢይ ስማ”፡፡
(ገድሏን በሥቃይ የፈጸመች፤ የመንፈስ ግርማ የጋረዳትና ቊመቷ እንደ ዘንባባ የሚመስል ለምትኾን ለቅድስት አርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ በመንግሥተ ሰማይም ስሟ ታላቅ ነው) በማለት ያወድሳታል፨
❖ እኔም በዚኽ ጽሑፌ ላይ ሊቁ አርከ ሥሉስ ለቅድስት ጣጡስ ሰማዕት በሰጣት ምስጋና ለሰማዕቷ አርሴማ በመስጠት አመስግኜያት ጽሑፌን አበቃለሁ፨
❖ “ሰላም ለአርሴማ ሥርጉተ አፍኣ ወውስጥ
በምግባር ፍጹም ወበሃይማኖት ስሉጥ
አመ ኮነት ሰማዕተ እንበለ ተምያጥ
አሕምሞ ሥጋሃ ኢክህሉ አስዋጥ
ወጸበለ እግራ ለሐሱ አናብስት መሠጥ”
(በፍጹም ምግባርና በፍጹም ሃይማኖት በውስጥና በውጪ ያጌጠች ለኾነች ለአርሴማ ሰላምታ ይገባል፤ ወደ ኋላ ባለመመለስ ሰማዕትን በኾነች ጊዜ ዐለንጎች (መግረፊያዎች) ሥጋዋን ማሳመም አልቻሉም፤ ነጣቂዎች አናብስትም የእግሯን ዐቧራ ላሱ) ይላል።
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

✞ኬብሮን

06 Oct, 03:59


#ይነበብ

ወርኃ ጽጌ -
(ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን (ዘመነ ጽጌን) ታከብራለች፡፡ ይህ 40 ቀን የእመቤታችንና የጌታ ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ (በዘመነ ጽጌ) የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ (የፈቃድ) የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ7ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ (ሉቃ. 7፡47) እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" (ማቴ. 6፥16) የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡
_________

✞ኬብሮን

01 Oct, 06:36


✞ኬብሮን

⨳የታመሙ ባንቺ ይፈወሳሉ፣የቆሰሉም ባንቺ ይድናሉ።


⨳እመቤቴ ማርያም ሆይ፥ጌጤ ሽልማቴ ሆይ፥ክብሬ ገናንቴ ለችግሬ ሀብት ባለፀግነት ለልምሾነቴም ብርታት ነሽ።

፦አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ


@kebbron
@kebbron

✞ኬብሮን

28 Sep, 08:08


✞ኬብሮን

ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ወጋገን
ፈርቼ እንዳልባክን ሲርቀኝ የሀይልሽ ወጋገን
አንቺ ካጠገቤ አትራቂ በርታ በይኝ እመብርሐን
ቃልኪዳኔን እንዳልረሳት እንዳልዘነጋት ኢትዮጲያዬን

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድን



@kebbron
@kebbron