አላሁ ሱሃሁ ወተዓላ አደምን ዐ ሰ ለመፍጠር በፈለገ ግዜ
ጂብሪልን ወደ መሬት ወርዶ አፈር ዘግኖ እንዲያመጣ ላከው።
ጅብሪልም ወደ መሬት ከወረደ በኋላ ከመሬት አፈር ሊዘግን ሲል
መሬት፦"እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው።
ጅብሪልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ
ተመለሰ።
አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ እጠበቃለሁ ስትለኝ
ተመለስኩ" አለው።
ከዚያም አላህ ሚካኢልን ላከው።ሚካኢልም ትእዛዙን ሊፈፅም ወደ
ምድር ሲወርድ መሬት፦" እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ"
አለችው።
ሚካኢልም በአላህ እጠበቃለሁ ስትለው ምንም ሳይነካት ትቶ
ተመለሰ። አላህም ዘንድ መጣ'ና ፦"ጌታዬ ምድር ባንተ
እጠበቃለሁ ስትለኝ ተመለስኩ" አለው።
በመጨረሻም አላህ አዝራኢልን ላከው አዝራኢልም ተልዕኮውን
ሊፈፅም ምድር ላይ ወረደ'ና አፈር ሊዘግን ሲል ምድር፦"
እንዳትቀንሰኝ በአላህ እጠበቃለሁ" አለችው።
አዝራኢልም፦"እኔ እራሴ የአላህን ትዕዛዝ ሳልፈፅም ከመመለስ
በአላህ እጠበቃለሁ" ብሏት አፈር ከተለያየ ቦታ መዘጋገን ጀመረ።
ከጥቁሩም፣ከነጩም፣ከቀዩም ዘገነ።ለዝያም ነው የሰው ልጆች
መልክም የተለያየው። ከዚያም አዝራኤል አፈሩን ይዞ አላህ ዘንድ
ሲቀርብ አላህም፦"አፈሩን አንተ እንዳመጣህ ሁላ ነፍሳቸውንም
እንድታወጣ አንተን ወክዬሃለሁ" አለው።
ከዚያም ከምድር የመጣው አፈር ረጥቦ ጭቃ በሆነ ግዜ አላህ
ለመላዕክቶቹ፦"እኔ ከጭቃ ሰውን ልፈጥር ነው። ፍጥረቱንም
ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ
ውደቁ።" ብሎ መልዕክት አስተላለፈላቸው።
ከዚያም አላህም ኢብሊስ እንዳይኩራራ አደምን በእጁ
ፈጠረው።ከዚያም ለ40 አመት ያህል ጭቃው ቅርፅ ብቻ ሁኖ
ከረመ። መላዕክትም በዝያ በኩል ሲያልፉ አደምን ሲያዩት በጣም
ይፈሩ ነበረ፤ ነፍስም አልገባለትም ነበር።
ከሁሉም በላይ እሚፈራው ኢብሊስ ሁሌ ከአደም ጭቃ አጠገብ
ሲያልፍ በእግሩ መታ አድርጎት ነበር ሚያልፈው። ያን ግዜ ሸክላ
ሲመታ እሚወጣው ድምፅ ይሰማ ነበር።
ከዚያም ኢብሊስ ከአደም ጭቃ ጎን ላይ ቁሞ፦"አንተማ ለሆነ ነገር
ነው የተፈጠርከው" እያለ በአፉ እየገባ በመቀመጫው ይወጣ
ጀመር።
ለመላዕክትም፦"እኔ በዚህ ላይ ከተሾምኩ አጠፋዋለሁ። እሱም እኔ
ላይ ከተሸመ አምጸዋለሁ" በማለት ይዝት ጀመር።
አላህም በአደም ገላ ላይ ነፍስ መንፋት በፈለገ ግዜ
መላዕክትን፦"ልክ ሩሁን/ነፍሱን እንደነፋሁለት ሰጋጆች ሆናችሁ
አጎብድዱ" ብሎ አዘዛቸው።
መላዕክትም ዝግጁ ሁነው መጠባበቅ በጀመሩ ግዜ አላህ በአደም
ሩሁን/ነፍሱን መንፋት ሲጀምር ገና ነፍሱ በአደም ጭንቅላት በኩል
ስትገባ አደም አስነጠሰው።
መላዕክትም፦"አልሀምዱሊላህ በል" አሉት።
አደምም፦"አልሀምዱሊላህ" ሲል...
አላህ ደግሞ፦"ጌታህ ይማርህ" ብሎ መለሰለት።
ከዚያም ነፍሱ አይኑ ጋ ስትደርስ የጀነት ውስጥ ፍራፍሬዎችን
ተመለከተ አንገቱ ላይ ስትደርስ ደግሞ ፍራፍሬዎችን መብላት
አሰኘው'ና ገና ነፍሱ እግሩ ላይ ሳትደርስ ሄዶ ለመብላት ተጣደፈ።
ነፍሱ መላ ሰውነቱ ላይ ስትሰራጭ ከመላዕክት ሁሉ ቀድሞ
ሱጁድ ያደረገለት ኢስራፊል ነበር። ከዚያም አላህ ለአደም፦"ሂድ
እነዛን ሰላም በላቸው'ና ምን ብለው እንደሚመልሱልህ አድምጥ"
ብሎ ላከው።
ሄዶ ሰላም ሲላቸውም መላዕክትም፦"ወዐለይኩሙሰላም
ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ" ብለው መለሱለት። አላህም
ለአደም፦"አደም ሆይ! ካሁን በኋላ ይህ ያንተ እና የዝርዮችህ
ሰላምታ ሆኖ ይዘልቃል" አለው።
አደምም፦"ጌታዬ ዝርዮቼ እነ ማን ናቸው?" ብሎ ጠየቀው።
አላህም፦"ከሁለቱ እጆቼ ምርጥ" አለው።
አደምም፦"ቀኝህን መርጫለሁ ሁለቱም እጆችህ ቀኝ ናቸው" ብሎ
ሲል...
አላህም እጁን ሲከፍትለት አደም እስከቂያማ ድረስ ያሉ ልጆቹን
ሁሉ ተመለከተ።በዚያም መሀል አንድ ብርሀናማ ሰው
ተመለከተ'ና፦"ያ አላህ ይህ ማን ነው?" ሲል ጠየቀ።
አላህም፦"እሱ ልጅህ ዳዉድ ነው"ብሎ መለሰለት።
አደምም፦"ጌታዬ ለዚህ ልጄ እድሜውን ስንት ነው ያደረግክለት?"
ብሎ ሲጠይቅ...
አላህም፦"60 ነው" አለው።
አደምም፦"ጌታዬ ከኔ እድሜ 40 ቀንስ'ና ለሱ ጨምረህ መቶ
ሙላለት" አለው።(ለአደም የተመደበለት እድሜ 1000 ነበር)
አላህም እሺ ብሎ ሞላለት'ና ምስካሪ መላዕክቶችንም አደረገ።
ከዝያም አላህ ዳግም ለአደም ልጆቹን ሁሉ ሲያሳየው አንዱ ጤነኛ
ነው፣አንዱ እግር የለውም፣አንዱ መስማት የተሳነው ነው፣አንዱ
ማየት የተሳነው ነው።
ይህን ሁሉ ሲመለከት፦"ምንው ጌታዬ ሁሉን እኩል ብትፈጥር ምን
አለበት" ሲለው
አላህም፦"አንተ አደም ሆይ! እኔ እንድመሰገን እፈልጋለሁ" ብሎ
መለሰለት፡፡
ከዚያም አላህ የአደምን ጀርባውን አንድ ግዜ አብሶ የሰው ልጆችን
ሁሉ አወጣ።
ከዚያም ሰበሰባቸው'ና፦"ጌታችሁ አይደለሁምን?" ብሎ
ሲጠይቃቸው፦"አዎ ጌታችን ነህ እንመሰክራለን" አሉ።
ከዚያም አላህም፦"እኔ ሰባት ሰማያትን እና ሰባት
ምድርን፣መላዕክቶችንም፣አባታችሁ አደምንም እናንተ ላይ ምስክር
አድርጊያለሁ።
የቂያማ ቀን ስጠይቃችሁ አላወቅንም ነበር ብላችሁ እንዳትክዱ
አሁንም እወቁ!!!
ከኔ ሌላ አምላክ የለም ከኔ ሌላም ጌታ የለም።በኔም ምንንም
አካል እንዳታጋሩ።
እኔ ወደ እናንተ መልዕክተኞቼን/ነቢያቶችን ቃል ኪዳኔን እና ዛቻዬን
የሚነግሯችሁ ሲሆኑ እልክላችኋላሁ። መፅሀፎቼንም
አወርድላችኋለሁ" አላቸው።
የአደም ዝርያዎችም፦"ካንተ ሌላ ጌታ እንደሌለ እንመሰክራለን ፤
ካንተ ሌላ አምላክ እንደሌለም እንመሰክራለን" ብለው ቃል ኪዳን
ገቡ።
አሁን ወደ ኢብሊስ ልመልሳችሁ፡፡
ቅድም ከመላዕክት ሁሉ ቀድሞ ለአደም ሱጁድ ያደረገው
ኢስራፊል ነው ብለናል ። እስራፊልን ተከትለው ሁሉም መላዕክት
ሱጁድ አድርገው ነበር ግና ኢብሊስ ሁሉም ሱጁድ ሲወርድ እሱ
በኩራት ቆመ።
አላህም፦" ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት
ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ)
ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?" ብሎ ኮነነው፡፡
ኢብሊስም፦" እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ አደምን
ደሞ ከጭቃ ፈጠርከው" አለ።
አላህም፦" ከጀነት ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና ፤ እርግማኔም
እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን" አለው።
ኢብሊስም፦" ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት (የቂያማ) ቀን
ድረስ አቆየኝ" አለው።
አላህም ጥያቄውን ተቀብሎት እስከቂያማ ድረስ ኢብሊስን
ሊያቆየው ቃል ገባለት።
ከዚያም ኢብሊስ፦"ጌታየ በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ የአደምን ልጆች
ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ በመላ
አሳስታቸዋለሁ፡፡" ሲል ዛተ።
አላህም፦"አንተን እና ከአደም ልጆች የተከተሉህን ሁሉ ጀሀነም
እንደምሞላችሁ ቃል እገባለሁ" አለ።
ከዚያም አላህ ኢብሊስን ከጀነት አውጥቶ አደምን ጀነት
አስቀመጠው።
አደምም እማያውቀው ቦታ ላይ አንድ አጫዋች በሌለበት ቁጭ
ብሎ የድብርት ስሜት ተሰማው።
ከዝያም እዝያው ጋደም አለ፡፡ ድንገት እንቅልፍ ሸለብ አደረገውም።
ልክ ከእንቅልፉ ሲነቃ እራስጌው ላይ አንዲት ሴት ተመለከት
ከአይኖቿ ፍቅር እና እዝነት ይነበብባታል።
አደም፦"ከመተኛቴ በፊት እዚህ አልነበርሽም"