(ጉለሌ ኮሙኒኬሽን 13/5/17)
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለ1ኛና ለ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሂሳብና እንግሊዘኛ እስትራቴጅ አፈጻጸም የ6ወር ሪፖርት የጋራ ግምገማ የተደረገ ሲሆን የንብረት አያያዝና አስተዳደር ኦረንቴሽን መስጠት፣የፈተና አዘገጃጀትና በተማሪዎች ውጤት ትንተና ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል።
ሁሉም የ1ኛና 2ተኛ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ርዕሰ መምህራን፣ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮች ፣በዘርፉ የሚገኙ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የአይሲቲና የመረጃ ማዕከል ባለሙያዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል።
በመድረኩ ክትትልና ድጋፍ የተደረገበት ዋና ዋና ግቦችና ዝርዝር ተግባራት በማየት በክፍተት የታየባቸውንና በጥንካሬ የተከናወኑትን ተግባራት እንደ ተቋሙ ነባራዊ ሁኔታዎች በማመላከት ፣የንብረት አያያዝና የመረጃ አደረጃጀትና በተለይም በሂሳብና በእንግሊዘኛ የ6ወር እስትራቲጂ አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ከትምህርት አመራሩ ጋር የጋራ ውይይት ተደርጓል።