The Throne Of Grace Church @grace_a_lone23 Channel on Telegram

The Throne Of Grace Church

@grace_a_lone23


Grace alone

The Throne Of Grace Church (English)

Welcome to The Throne Of Grace Church Telegram channel, where grace abounds! Our channel, with the username @grace_a_lone23, is dedicated to spreading the message of grace and love to all. We believe in the power of grace alone to transform lives and bring hope to the world. The Throne Of Grace Church is a welcoming community where people from all walks of life can come together to worship, learn, and grow in their faith. Our channel provides daily inspiration, devotions, and messages of encouragement to help you in your spiritual journey. Who are we? We are a group of passionate believers who are dedicated to sharing the message of God's grace with the world. We believe that grace is a gift that is freely given to all, regardless of their past or present circumstances. Our goal is to create a space where people can come as they are and experience the transforming power of grace. What is The Throne Of Grace Church? It is a place where you can find support, community, and most importantly, grace. Our channel offers a variety of content, including Bible studies, prayer requests, and uplifting messages from our pastors and members. Whether you are looking for spiritual guidance, a sense of community, or simply a place to belong, The Throne Of Grace Church is here for you. Join us on this journey of grace and love. Follow @grace_a_lone23 on Telegram to stay connected with our church community and receive daily doses of inspiration. Together, we can experience the amazing power of grace alone to transform our lives and bring hope to the world. Welcome to The Throne Of Grace Church, where grace abounds!

The Throne Of Grace Church

10 Nov, 09:01


#የድል_ድምፅ
#ዛሬ_በቀን_30_02_2016_ዓ.ም የተደረገ የወንጌል ሥርጭት።
#አዲስ_23, #ንሰሐ_13, ተስፋ =3 #በድምሩ_36 ነፍሳት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ተጨምረዋል።
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ሉቃ 10_² አላቸውም፦ መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ለመከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት። ³ ሂዱ፤ እነሆ፥ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።

The Throne Of Grace Church

08 Nov, 13:42


"ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ::"

ሚልክያ 4:2

The Throne Of Grace Church

04 Nov, 11:41


ከጥያቄዎች

ሰላም ወንድም ዘላለም። አንድ ጥያቄ ነበረኝ። አሁን ግብ& ረሰዶ* ማው ያን እዚህ አገር እንደበዙ ይታወቃል። በየቢሮዎቻቾን ያሉትን እንዴት ነው አብረናቸው የምንውለው? አንደኛዋ ቸርች የተባለ አጥብቃ ትጠላለች፣ ብዙ judge ተደርጌአለሁ ትላለች። በዚህ ሳቢያ እግዚአብሔርንና ቸርችን ጠላሁ አለችኝ። ምላሼ ምን መሆን አለበት። እኔ ክርስቲያን መሆኔን ታውቃለች። (T. A.)
. . .
ሰላም T. A. ቁጥራቸው የተጋነነ ቢሆንም መብዛታቸው እውነት ነው። ቁጥራቸው የተጋነነ እንዲሆን ነው ዓይነታቸውን ያበዙት። ጥንት አንድ ወይ ሁለት ዓይነት ብቻ ነበሩ። ዛሬ ዓይነታቸው ከ40 በላይ ሆኖአል። አናሳ ቢሆኑም ትልቅ ከበሬታ እየተቀዳጁ ናቸው። አንዳንድ ቦታ ተገለልን ወይም መድልዎ ተደረገብን ብለው እንዳይከስሱ የተለየ ክብካቤም ይደረግላቸዋል። ለምሳሌ በአንዳንድ የሕክምና ተቋማት ለብቻቸው ክፍል ይሰጣቸዋል። በነፃነት ስም በየተቋማት የነሱ ክበቦች የተፈቀዱ ናቸው፤ ያንን መቃወም ደግሞ ኋላ ቀርነትና ጠባብነት፥ ከጥላቻ የሚመደብ ኢ-ታጋሽነትም ተደርጎ ይታያል። በግልጽ እነሱን ተቃውሞ መጻፍ የጥላቻ ንግግር ተብሎ ይፈረጃል። በአንዳንድ ማኅበራዊ ሚድያ ስማቸው ሲጻፍ እንኳ እንዲህ ግብ& ረሰዶ* ማው ያን በማለት እንጂ በቀጥታ ከተጻፈ ገጹ ለጊዜ ወይም ለዘለቄታ ሊታገድ ሁላ ይችላል።

እነዚህን ሰዎች ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ እየሄዱ መሆናቸውን እናውቃለን። ግብ& ረሰዶ* ማዊ ነት ኃጢአት መሆኑ በቃሉ ውስጥ በቀጥታ ተጽፎ ይገኛል፤ በሕጉ ውስጥ እንዲህ ተጽፎአል፤ ከሴትም ጋር እንደምትተኛ ከወንድ ጋር አትተኛ፤ ጸያፍ ነገር ነውና። ዘሌ. 18፥22። ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። ዘሌ. 20፥13። በአዲስ ኪዳንም፥ በሮሜ. 1፥22-28 በግልጽ ተጽፎአል። ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። ቁ. 26-27። ይህ ግልጽ ኃጢአት ነው። አስጠያፊም ነው።

እነዚህን ሰዎች በመጀመሪያ እንደ ሰዎች ሁሉ ነው ማየት ያለብን። የእግዚአብሔር ፍጡር ሁሉ የሆኑ ሰዎች ናቸው። እንደ ሌላው ኃጢአተኛ ሁሉ ናቸው። ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ግብረ ሥጋ መፈጸም በእግዚአብሔር ፊት ከጋብቻ ውጪ ግብረ ሥጋ ከመፈጸም ጋር እኩል ነው። የእነርሱው አስከፊነት ይህኛውን ቀለል ያለና ተቀባይነትን የተቀዳጀ አያደርገውም። ኃጢአት በቅዱሱ እግዚአብሔር ፊት ኃጢአት እንጂ ትልቅና ትንሽ ኃጢአት የለም። ይህ ማለት በሰው ዓይን ፊት ሲታዩ ጉልህና ፈዛዛ፥ ትልቅና ትንሽ የምንላቸው ኃጢአቶች የሉም ማለት አይደለም። የነዚህ ሰዎች ኃጢአት ገዝፎ የወጣው ተቀባይነትን ለማግኘት መንግሥታዊና መያዳዊ (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅታዊ) ጉልበቶችን በመጠቀም የመንግሥትም የሕዝብም አጀንዳ ሆኖ የመቅረቡ ጉዳይ ነው። እነዚህ ሰዎች ሊድኑ ይችላሉ? በትክክል! ከኃጢአታቸውና ከአኗኗር ዘይቤአቸው ሊላቀቁ ይችላሉ? በትክክል! ብዙዎችም ተላቅቀዋል፤ በቅዱሳን ኅብረትም ተቀላቅለዋል።

በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ሰዎች ነበሩ። 1ቆሮ. 6፥9-11 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል።

ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ካለ፥ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ቀድሞ በዚህ የኑሮ ዘዬ ውስጥ ያለፉ ሰዎች ነበሩ ማለት ነው። ኋላ ምን ሆኑ? ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል። ይህ ድንቅ ለውጥ ነው። እንደ ማንም መለወጥ ድንቅ የሆነ ለውጥ ነው። እንዴት ሊለወጡ ቻሉ? ማንም ሰው እንደሚለወጠው ወንጌልን በመስማት። የዘመናችን ግብ& ረሰዶ* ማው ያንስ ሊለወጡ ይችላሉ? እንዴታ! ብዙዎች ተለውጠዋል፤ በጌታ አምነው ድነዋል። አንዳንዶች በቅጽበት፥ አንዳንዶችም በሂደት ከዚህ የወሲብ እስራታቸው ተፈትተዋል። ግብ& ረሰዶ* ማዊ ነት የወሲብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አጋንንታዊ የሰው ልጆች ጥላቻ ወጥመድም ነው። እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ባሕርይ የሚቃረን፥ የሰው ዘር እንዳይቀጥልና እንዲጠፋ የሚፈልግ ርኵሰት ነው።

በዙሪያችን እንዲህ ያሉ ሰዎች ልናገኝ እንችላለን። ማስተዋል ያለብን እነዚህ ሰዎች የሰይጣንና የሰው ድብልቅ አይደሉም። ዘላለማውያን ሰዎች እና ክርስቶስ የሞተላቸውም መሆናቸውን አንርሳ። ከእግዚአብሔር ጋር መተዋወቃቸው ከራሳቸው ጋርም እንዲተዋወቁ፥ ማለትም እግዚአብሔር ከፈጠራቸው የተፈጥሮ ማንነታቸው ጋር እንዲተዋወቁ ያደርጋቸዋል። ይልቁንም የክርስቶስን የቤዛነት ሥራ ተረድተው መዳንን ይወርሱ እንደሆነ ማን ያውቃል? እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን የሚጠሉበት ምክንያት አንዳንዶቹ በእርግጥም ተኮንነው ሲሆን፥ ብዙዎቹ ግን ለምን በማንነታችን አልተቀበሉንም? ከሚል የመብት ጥያቄ የተነሣ ነው። ቤተ ክርስቲያን እነዚህን ሰዎች ለመቀበል ስትል መለኪያዋን በነሱ ልክ አሳንሳ አትቆርጠውም። ከመዳን ክልል የጠፉና ምንም ዕድል የሌላቸው የተጣሉ አድርጋም ልትቆጥራቸው አይገባትም። ምንም እንኳ እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ቢባልም፥ ከዚህ ቃል በፊት ያለው ሐረግ፥ ‘እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን’ የሚል ነው። እግዚአብሔርን ለማወቅ እንዳልወደዱ የምናውቀው ስለ እግዚአብሔር አውቀው ባይወድዱት ነው። ቢወድዱትስ? ለዚህ ከላይ ያየናቸው የቆሮንቶስ አማኞች ምስክሮች ናቸው።

ስለዚህ፥ ምላሼ ምን መሆን አለበት? ላልሽው፥ እነዚህን ሰዎች ስታዪ ጠፍተው እንደቀሩ ሳይሆን ሊድኑ እንደሚችሉ ኃጢአተኞች መመልከት አለብሽ። እኛ ሁላችንም ከክርስቶስ በፊት የኃጢአታችን ዓይነትና መጠን ይለያይ እንጂ የጠፋን ኃጢአተኞች ነበርን። እኛም፥ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥበናል፥ ተቀድሰናልል፥ ጸድቀናል። ልክ እንደኛው፥ እነሱም ሊሆኑ ይችላሉ።

ዘ. መ.

The Throne Of Grace Church

11 Oct, 22:43


የምናውቀው ነገር ግን የማንኖረው እውነት፤

ስለ ኤፌሶን መልእክት ዋና ጭብጥ ብዙ ተብሏል በእኔ ውስን ጥናት የመልእክቱ እንብርት ጭብጥ አንድ አዲስ ህዝብ መፍጠር የሚል ነው። ይህ ጭብጥ በመደብ መከፋፈል ምክንያት የሰው ልጅ በሁለት መልኩ ይመደብ የነበረበትን ታሪክ የዘጋ ነበር። ይህም በአይሁድና በአህዛብ መካከል የነበረ ልዩነት ነበር። ታዲያ ጌታ በደሙ በሰራው ስራ አንድ ህዝብ ተፈጠረ። መደብ ፈረሰ። ሰላም ሆነ። በምህረትና ርህራሄው በመደብ መካከል የነበረው ጥል ተወገደ። በመሆኑም ወንጌል በራልኝ ብሎ በብሄርተኝነት እሳቤ ተጠምዶ የተገኘበትን መደብ አልቆ በመመልከትና ሌሎችን አሳንሶ በመመልከት ጥልን ዳግም ህያው ሊያረግ የሚታትር እሳቤ ከኤፌሶን መልእክት ጋር የሚጋጭ ፀረ ወንጌል ነው። ለዚህ ነው ክርስቲያን ባለፈ የተበዳይና በዳይ ትርክት ላይ በቆመ የብሄር ፖለቲካ መጠመድ የሌለበት። ይህ የፖለቲካ ስርአት ህጋዊ ስለሆነ መፅሐፍ ቅዱሳዊ ነው ማለት አይደም። የክርስቲያናዊ ኑሮ እሴት ምህረት፣ ይቅርታ፣ ሰላም፣ እርቅ ... እንጂ በደል ቆጣሪነት አይደለም።

The Throne Of Grace Church

07 Aug, 21:16


Channel photo updated

The Throne Of Grace Church

07 Aug, 21:15


Channel photo removed

The Throne Of Grace Church

23 Jul, 09:29


ሮሜ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹-² ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።
³-⁴ ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

The Throne Of Grace Church

26 Jun, 16:06


Channel created