Neueste Beiträge von ግዕዝ ለኵሉ (@geezzlekulu) auf Telegram

ግዕዝ ለኵሉ Telegram-Beiträge

ግዕዝ ለኵሉ
Dieser Telegram-Kanal ist privat.
ዝንቱ ማኅበር ዘተርኅወ ለአፍቃርያነ ግእዝ !!!

ይህ ቻናል ለግእዝ ወዳጆች የተከፈተ ነው!!!

ንዑ ንኩን ጠቢበ !

ኑ ጠቢብን እንሁን !

https:/geeZzlekulu

የመነጋገርያና የመወያያ ግሩፕ

https:/geeZzlekulu
6,840 Abonnenten
117 Fotos
15 Videos
Zuletzt aktualisiert 06.03.2025 20:26

Der neueste Inhalt, der von ግዕዝ ለኵሉ auf Telegram geteilt wurde.

ግዕዝ ለኵሉ

31 Jan, 14:41

881

🔴🔴🟢ዘኢነገሩከ ኢትስማዕ
ዘኢወሀቡከ ኢትትወከፍ
ዘኢጠየቁከ ኢታውሥእ 🟢🔴🔴

🔵🔴ያልነገሩህን አትስማ፣
ያልሰጡህን አትቀበል።
ያልጠየቁህን አትመልስ።🔴🔵

🔵 ኅሩይ ወ/ሥላሴ [ብላቴን ጌታ]


✈️https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

31 Jan, 05:27

1,191

ጥበብ የራሶቿን አገልጋዮች በትልቅ ስብከት እብድ የሆነ ከእኔ ይራቅ እያለች ላከች ። ማስተዋል የጎደላቸውንም  ምግቤን አንሱ ብሉም ወይኔንም ጠጡ ፤ እብደትንም ተዉ ሕይወትንም አግኙ እያለች ጠራች ። ጥበብስ ሥጋውን በመስጠት ያተቤዤን ደሙንም በመርጨት የገዛን ለመንግሥቱም የመረጠን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።



🔸ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
🔹በመጋቤ ሐዲስ ለይኩን ብርሃኑ


✈️ https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

31 Jan, 04:52

1,103

✔️ ጋራ📌 ለሚል አማርኛ ፍቺ ✔️ምስለ 📌 መጠቀም እንችላለን ።

✔️ምስለ መንፈስከ
✔️ከመንፈስህ ጋራ
✔️ምስለ እምየ
✔️ከእናቴ ጋራ
✔️ምስለ አቡየ
✔️ከአባቴ ጋራ
✔️ምስለ ኵሎሙ
✔️ከሁሉም ጋራ
✔️ምስሌከ
✔️ከአንተ ጋራ
✔️ምስሌኪ
✔️ከአንቺ ጋራ
✔️ምስሌየ
✔️ከእኔ ጋራ
✔️ምስሌነ
✔️ከእኛ ጋራ
✔️ምስሌክሙ
✔️ከእናንተ ጋራ
✔️ምስሌሆሙ
✔️ከእነርሱ ጋራ

✈️ https://t.me/geeZzlekulu ✈️
ግዕዝ ለኵሉ

30 Jan, 16:24

1,192

🔤ሀገርከ ደጋ ወስምከ ወርቄ🔤

ከልክ የተረፈውን ባለቅኔ አለቃ ዘመደ ብርሃንን ጎጃም ደጋማ ክፍል ይኖሩ የነበሩ አንድ ቅኔ የማያውቁና ቄስ ወርቁ የተባሉ ካህን በደንገት ያገኙትና ለሰው ሁሉ ቅኔ ስትዘርፍ ለእኔም ምናለ ብትዘርፍልኝ ይሉታል።ዘመደ ብርሃንም በዚያው ቅጽበት
🔻ሀገርከ ደጋ ወስምከ ወርቄ፣
በጊዜ ማኅሌት በግዕ ወበጊዜ መብልዕ አንቄ። ብሎ ዘረፈባቸው።

🔵ትርጉም:-ሀገርህ ደጋ ፣ስምህ ወርቄ የምትባል ቄስ በማኅሌት ጊዜ በድን ቃል የማትተነፍስ፣ዜማ የማታውቅ፣በመሐራ ጊዜ ደግሞ ጭልፊት ፣አሞራ ነህ ብሎ በጓደኞቻቸው ፣ካህናት መካከል ተቀኘባቸው ይባላል።

😄የቅኔውን ምሥጢር ስለማይሰሙትና ያመሰገናቸው ስለመሰላቸው በጣም ደስ ብሏቸው አንድ ጠገራ ብር ሸለሙት።



ብሂል ቅኔ እንማር🤓
ግዕዝ ለኵሉ

30 Jan, 15:09

1,273

https://t.me/geazlekuluu
ግዕዝ ለኵሉ

30 Jan, 14:05

1,211

◼️ ነጽር ላዕሌየ ወተሣሀለኒ እስመ ባሕታዊ ወነዳይ አነ ወብዙኅ ኃዘኑ ለልብየ አድኅነኒ እምንዳቤየ ◼️

🔺እኔ ብቸኛ እና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም ። የልቤም ችግር ብዙ ነውና ከጭንቀቴ አውጣኝ 🔺

🔻 መዝ ፲፮

https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

30 Jan, 09:25

1,305

ቅድመ ጸልዮትከ - እመን
ከመጸለይህ በፊት - እመን።

ቅድመ ተናብቦትከ - አጽምዕ
ከመናገርህ በፊት - አዳምጥ።

ቅድመ አማስኖትከ- ርከብ
ከማጥፋትህ በፊት - አግኝ። [ገንዘብ]

ቅድመ አቂሞትከ - ትጋህ
ከማቆምህ በፊት - ትጋ ።

ቅድመ መዊቶትከ - ሀሉ
ከመሞትህ በፊት - ኑር።


📱 https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

29 Jan, 19:29

1,464

🔸🔸እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላይ ህየኒ ሀሎከ ወእመኒ ነሣእኩ ክንፈ ከመ ንስር ወሠረርኩ እስከ ማሕለቅተ ባሕር ህየኒ እዴከ ትመርሐኒ ወታነብረኒ የማንከ 🔹🔺

🔸🔸ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ ነህ ወደ ሲኦልም ብወርድ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር በዚያ እጅህ ትመራኛለች ቀኝህም ትይዘኛለች 🔹🔺

🔹🔹 መዝ ፻፴፱፥፰

📱 https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

29 Jan, 13:27

1,479

🔴🟢አኮ ዐብድ ዘኀጥአ አእምሮሁ እምዝንቱ ዐብድሰ ዘኀጥአ ኵሎ እንበለ አእምሮሁ🟢🔴

🟡🔵ጭንቅላቱን ያጣ እብድ አይደለም፤ ይልቅስ እብድ ከአዕምሮው በስተቀር ሁሉን ያጣ ሰው ነው ! 🟡🔵

              🔸Jacques Lacan


📱 https://t.me/geeZzlekulu
ግዕዝ ለኵሉ

29 Jan, 07:19

1,626

የአምላክ እናት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያምን ተስፋችን ፣ ደስታችን ፣ ክብራችን ፣ የትምክህታችን አክሊል፣ የድኅነታችን መመክያ ፣ የንጽሕናችን መሰረት እንላታለን ። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አንዳንድ መነፍቃን ከላይ ያሉትን ነገሮች እንዴት ለድንግል ማርያም እንናገራለን ? እሷ ሰው አይደለችምን ? በማለት ይጠይቃሉ ። እናንተ ልቡናችሁ የታወረ ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች ምን እንዳላቸው አላነበባችሁምን ? ቅዱስ ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ሰዎች ምን አላቸው ? " ተስፋችን ወይስ ደስታችን ወይስ የትምክሕታችን አክሊል ማን ነው ? በጌታችን በኢየሱስ ፊት በመምጣቱ እናንተ አይደላችሁምን ? " ዳግመኛም "እናንተ ክብራችን ደስታችንም ናችሁና።" በማለት ደጋግሞ ይነግራቸዋል ። ( 1 ኛ ተሰ 2፥19)

ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ክቡራን እና ልዑላን ቃላት ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጠቀመው በተሰሎንቄ የሚገኙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል ስላልተቀበሉ ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ማኅበርተኛ በመሆናቸው ምክንያት በአገራቸው ሰዎች ብዙ መከራዎችን እና ሥቃዮችን ስለተቀበሉ ነው ። በዚህም ምክንያት ቅዱስ ጳውሎስ እነሱን ለማየት ናፍቆ እንደነበረ እና ሰይጣን እንዳዘገያቸው " እኛ ግን ወንድሞች ሆይ በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ ዐጥተናችሁ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን ወደ እናንተ ልንመጣ ወደን ነበርና እኔ ጳውሎስም አንድና ኹለት ጊዜ ሰይጣን ግን አዘገየን" (1 ኛ ተሰ 2፥17) በማለት ተናግሯል ።

የተሰሎንቄ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል እንደ እግዚአብሔር ቃል በመልእክት ስለተቀበሉ ደስታችን ፣ ተስፋችን ፣ የትምክህታችን አክሊል ናችሁ ከተባሉ ቅድስት ድንግልማ ከእነሱ በምን ያህል ትበልጥ ይሆን ? ክብሯስ በምን ያህል ከፍ ከፍ ያለ ይሆን ? ከዚህ በፊት ተሰምቶ የማይታወቅ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤልን ቃል " እንደ ቃልህ ይሁንልኝ እኔ ለእግዚአብሔር ባርያው ነኝ " በማለት ተቀብላለችና ።


የተሰሎንቄ ሰዎች እሷ ስለወለደችው ስለ ክርስቶስ ብለው መከራና ሥቃይ ተቀብለው ተስፋችን ፣ ደስታችን ፣ የትምህክታችን አክሊል ፣ ክብራችን ናችሁ ከተባሉ ቅድስት ድንግልማ ምን ያህል ከእነሱ የላቀ የማይነገር እጥፍ ድርብ ክብር ይገባት ይሆን ? ምክንያቱም እነሱ መከራ የተቀበሉለትን ፣ ስለ እሱ ብለው የተሠቃዩለትን ክርስቶስን የወለደችላቸው እሷ ናትና ይልቁንም እነሱ መከራ ሥቃይ የተቀበሉለትን ክርስቶስን በጀርባዋ አዝላ በረሓ ለበረሓ ጥምና ረኃቡን ታግሳ ወደ ምድረ ግብጽ ተሰዳለችና ። የአምላክ እናት ላይ እንዲህ አይነት ንግግርን መናገር ምን ያህል እብደት ነው ? ምን አይነት አለማስተዋልስ ነው ?

ይልቁንም ከእንዲህ አይነት ስንፍና ርቀን ከሊቁ ከቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጋር ሆነን እሱም በውዳሴ ማርያም ምስጋናው የተናገረው ነው " የትምክህታችን አክሊል ፣ የድኅነታችን መጀመርያ፣ የንጽሕናችን መሰረት በማርያም ድንግል ሆነልን " በማለት እንናገር እናመስግን ።

እመቤታችንን ለማየት እንናፍቃለን !

📱 https://t.me/geeZzlekulu