ፍቅሬን በ 4 መስመር: @fkren_be_4_mesmr Channel on Telegram

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

@fkren_be_4_mesmr


╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
ይቅርታዎን ፍቅሮን ሚስጥሮንና ፍላጎቶን እኛን በመቀላቀል በምናጋራቹ 4 መስመር ግጥሞች ሙሉ ስሜቶን ይግለጹ

️╯▅╰╱▔▔▔▔▔▔▔╲╯☼
▕▕╱╱╱╱╱╱╱╱┛▂╲╲
╱▂▂▂▂▂▂╱╱┏▕╋▏╲╲
▔▏▂┗┓▂▕▔┛▂┏▔▂▕▔
▕▕╋▏▕╋▏▏▕┏▏▕╋▏|



#Just ዘና ፈታ

ፍቅሬን በ 4 መስመር: (Amharic)

ፍቅሬን በ 4 መስመር: የፍቅሮን ሚስጥሮንና ፍላጎቶን እናቴና በመቀላቀል በምናጋራቹ 4 መስመር ግጥም ሙሉ ስሜቶን ለማግኘት ይግለጹ! እንኳን ደህና መጡ ዘና ፍቅሮን ሚስጥሮንና ፍላጎቶን በዚህ መስመር ለማከናወን ምንም አንባቢዎች እና ሳኒሺዎች ብሎን እንቀበልን! የሚያበረታቹትን ግጥሞች ስሜቶናል እና አስፋፋና በሰላም ወዳላከነናቸው። ለበለጠ ጉዞ ለአስፋፋና ለሃሳብ የሚለዋወጡትን ቅድሚያን ይቀበሉ፡፡ #Just ዘና ፈታ

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

13 Nov, 18:35


አንተ ለኔ አድርጎህ ልቤ ካልደረጀ
እንዳሰብኩት ሆኖ ኑሮዬ ካልበጀ
የጸለይኩት ጸሎት አንተን ካላመጣህ
እስኪ ልሳል ደሞ ከልቤ እንዲያሶጣህ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

13 Nov, 18:34


በገና ለገና ይሆን ይሁን እያልኩ
አንተን እንዳላጣ አይኖቼን ከጨፈንኩ
እንቅልፌን አጥቼ ሳልተኛ አድራለው
ካራራቀን ብዬ ህልሜን እፈራለው
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

13 Nov, 18:34


ካንተ ጋር እያለው የምትሞቀኝ ጸሀይ
ላይኔ ጥሩ ሆኖ የሚታየኝ ሰማይ
አንተ ሳትኖር ጎኔ ላንተ እየወገኑ
ሁሉም ባዶ ይሆናል ከኔ ጋ ላይሆኑ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

06 Oct, 07:14


ትላንት አጥቼ ዛሬ አጊንቻለው
ብዙ ሰው እረስቶኝ እኔም ረስቻለው
እኔን የቸገረኝ የሆነኝ አበሳ
ያጣሁት መዳኒት አንቺን የሚያሥረሳ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

26 Sep, 18:01


ለልቤ መድሀኒት ያንተን ልብ ስሻ
ላኖርህ ሳልሽርህ እስከ መጨረሻ
ዳንኩ ስል ተነሳው አገገምኩኝ ካምና
ያንተም ጦር ሰበቀኝ ቆሰልኩ እንደገና
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

24 Sep, 11:39


ሳልፈራ እንደ ልቤ በረርኩኝ በረርኩኝ
አንዱን እየለቀኩ አንዱን እየያዝኩኝ
አወይ የኔ ነገር የኔ መጨረሻ
ከኔው ቢጤ እንዳይሆን ልቡ ከማይረጋ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

24 Sep, 11:39


አካሌ እንዳልዛለ መስሎት እየኖረ
ልቤ እያዘነ ከፍቶት እያደረ
እየሳቀ ጥርሴ ባያስረሳኝ ኖሮ
አይሆንም ነበረ አይገፋም ኑሮ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

18 Sep, 14:56


ደና ነኝ እላለው መድከም የት አባቱ
ገደልኝ አልልም ሰበረኝ ናፍቆቱ
ልክ እንደ ጀግነ ሲዋሽልኝ አፌ
ደና ነኝ እላለው ፎቶህን ታቅፌ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

12 Sep, 18:54


ለሰው ማይወራ ሚስጥር እንዳልለው
እሷ እንዳታቅብኝ ከሷ እንዳልደብቀው
እንደተረታሁኝ ልቤ እንደ ደከመ
አይኔ ይናገራል ካፌ እየቀደመ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

10 Sep, 18:32


ናፍቆት ህመም ሆኖ አመመኝ በብርቱ
መከፋት ማዘኑ የቱ ይወራ ስንቱ
ህመም ማስያገሻ መዳኒት የሌለው
አወይ ናፍቆት ሞኙ ገድሎኝ እንዳያርፈው
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

10 Sep, 18:32


የኔ ያልኩትን ሰው በፍቅር ያየሽው
እንደምን ብለሽ ሞትን ተመኘሽው
ማርያምን ብያለው ደግሜ አልምልም
እሱንማ ደፍረው ካዩብኝ አልምርም
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

09 Sep, 17:28


ካደኝ ልቤ አንተን አንተን ይላል
ጉዴ ፈላ መልክህ ያታልላል
አታላዩን ውበት አጎናጽፎ
ስንቱን ጣለ ልቡናውን አልፎ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

09 Sep, 17:27


ማዶ ማዶ እያየ አይኔ ሊያይሽ ሳሳ
እንደራብሽኝ ዋልሽ ምነው ቀረሽሳ
ናፍቆት አንገብግቦ ካላዋለኝ ደጇ
የዛሬውስ አጀብ ማደሬንም እንጃ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

03 Sep, 11:25


ሆዴ ተረበሸ ፍቅርህ ትዝ እያለኝ
አይ ኑሮ ተስማማህ ወይ እስኪ ጠይቁልኝ
ጨነቀኝ ጠበበኝ ለማን ሰው ላዋየው
ሰው ካልደረሰበት እንደራሱ አያየው
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

28 Aug, 20:02


ያሻው ቢያምር ቢጎላ መልኩ
አንቺ ነሽ ለኔ የልቤ ልኩ
ሚዛን የደፋሽ ለኩል ሚዛኔ
ሌላ እኔ አላይም አንቺ ነሽ የኔ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

28 Aug, 20:01


ስንቱን ነገር ቻልኩት ሲመጣ ካንቺማ
አይቼ እንዳላየው ሰምቼ እንዳልሰማ
ስታጠፊ በጀ አወይ የወደደ
ፍቅርሽ እያነጣኝ ሆዴ እየነደደ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

19 Aug, 05:49


ልብህ እንዳይመታ ሌላ ሄዋን ስታይ
እኔ ወድሀለው ከሚወዱህ በላይ
ከተመኙህ በላይ ካሉት አፈቀርንህ
የለም አትፈልግ እንደኔ ሚወድህ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

10 Aug, 05:34


የፍቅር ዳር ድረስ ልያዝህ አድርሰኝ
እስከድሜዬ ማምሻ ላፍታ ሳትለቀኝ
እስካሸልብ ድረስ ከማልነቃው እንቅልፍ
ያኑረኝ በፍቅር ዘላለም ካንተ እቅፍ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

10 Aug, 05:34


ለናፈቀ ደሞ አይንሽን ለሚሻ
ከሰመመን ሊድን ለመም ማስታገሻ
ቅርብ አደል አዳርሽ ቅርብ አደል ወይ ውሎ
ሳትነጠል ነፍሴ ድረሺልኝ ቶሎ
@fkren_be_4_mesmr

ፍቅሬን በ 4 መስመር:

20 Jul, 20:13


ልቤ ወዳጄ ሚስጥሬ ነበረ
ዛሬ እንዲ ሊከዳኝ አንተን ባፈቀረ
አንድ ያለኝ ወዳጅ ካሳጣከኝ አይቀር
ላፈቀረህ ልቤ አንተ ሁነው ሚስጥር
@fkren_be_4_mesmr