ፍቅሬን በግጥም 💞 @getemi Channel on Telegram

ፍቅሬን በግጥም 💞

@getemi


✍️ለምን ወደድኩህ/ሽ?
እንጃ።🤷‍♀️
✍️ምንህ /ምንሽ ተመቸኝ ?
እንጃ🤷‍♀️
✍️እንዴት ማረከኝ/ሺኝ?
እንጃ🤷‍♀️

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟

👉comet ena malt yemet felguti ngr kal
@Erazatube_bot

ፍቅሬን በግጥም 💞 (Amharic)

ልዩ ሰውየውን ለፍቅሬ በውስጥ መጠን የሚሰራባቸው የወንድሜ ጉዳይ የታወቀ በሽታ ተመኑ፡፡ እንዲህም መጽሀፍት በእኔ ደስታ፤ ምኞት በእኔ መበከል፤ ማየት በእኔ ደስታ፡፡ በቻይ ወይም በነፍህ የፈጠረበትን ፍቅር መስጠት፡፡ የሚገኘው የታጠቁ ቆይታዎችን አግኝቶ መድረስ እና ማጣሪያዎችን ማስተማር፡፡ ይህ ይህንን ፍቅሬ በግጥም ማለት፤ ከድህረ ሲንዲንቲ፤ እና ማህበራዊ መገኛ በሚሰራው ሌላ መደላላታ አማጻን ውስጥ ተመኑ፡፡

ፍቅሬን በግጥም 💞

16 Dec, 12:04


🤍💞  ይቆጨኝ ነበረ  💞🤍


ከፍቅርክ ከፍታ ላፍቃሪ ከራቀው
ኩራት ከውበት ጋር ከተደባለቀው
ከሚታየው ርቆ የዝናህ ቅርንጫፍ
ከጥላቻህ አናት ከመፈቀርህ ጫፍ
              አላፈቅርም ብለህ
             አልወድሽም ብለህ
       እንኩዋን ገፈተርከው
         እንኩዋን መሬት ጣልከው
እንኩዋንም ባንተ እጅ ልቤ ተሰበረ
ባላፈቅርህ ኑሮ ይቆጨኝ ነበረ💕

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

16 Dec, 12:04


💔ተዉከኝ ብዬ አላዝንም😄😄
        ⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️


እየወደድኩ ተውከኝ ብዬ
ስላፈቀርኩ ካድከኝ ብዬ
እኔ አሎቅስክም አመሰግናለው
አንተ በመሄድ ልቤን የከፈትከው
አሁን ስለራከኝ ደስታዬን ሞላከው
:
    ምወደው ሲተወኝ እኔን ንቆ ሲያልፈኝ
    የሚወደኝ መጣ ፍቅሩን ሊገልጽልኝ
    እኔ የምወደው የኮራብኝ መስሎት
    ሚወደኝ ወሰደኝ መንገዱን ከፍቶለት
      :
ለዚ ነው ማሎቅስክ እኔን ስለተውከኝ
ካንተ የተሻለ አዳለ አሳየከኝ
ላመስግንክ እንጂ ለምን ወቅስካለው
አንተ ባትተወኝ መች የሱ ሆናለው

     አሁንም አሁንም አሁንም ልድገመው
     ውለታክ አለብኝ አንድ ቀን ከፍላለው
     
ማፍቅረውን ትቼ ከሚያፈቅረኝ ጋር ነኝ
እኔ ማለት ለሱ እንደ ብርጭቆ ነኝ
እንደ እንቁላል ነው የሚከባከበኝ
:
    ታዲያ ከዚ በላይ ውለታ ምን አለ
    እንዳለ አሳየከኝ ካንተ የተሻለ። ። ።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

16 Dec, 12:04


#ልበ_ዱሪቆን


አለሜ......
በአፍላነት እድሜ ገና በልጅነት
የደወርነው ፍቅር ደርሰው ያልፈተሉት
የትዝታ መንጋ ልባችን ያዘለው
ማደግ ያልዘነጋው
አርያም ባይሰማው ይህን አይነት ፍቅር
ህቡዕ ነው ልንገርሽ የኔና አንቺስ ነገር
እዚህ ከኛ ልብ ውስጥ ንዴት አሸልቧል
ያልወለድነው ፍቅር ልባችን አርግዟል
የኔም የአንቺ አንደበት ዝምታውን መርጧል
ይሁን ይሁን ልቀበለው
ያ ልባችን አማን አለው
.
ትዝ ይልሻል
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ
.
ያ ልብሽ ደጋ ነው በማፍቀር የናኘ
የኔ ልብ ቆላ ነው አንቺን የተመኘ
ምክኒያቱ ይህ ነው የልበ ዱሪቆን
ልባችን ተማምኖ አንደበት ቢከዳን
በቃ ተፈጥረን ነው እሳት ውሃ ሆነን
.
ደግሞ ጊዜው ቢተም
ምሽት ደርሶ ቢጨላልም
ከውብ አይንሽ ቅሬታሽን አነባለው
ክንድሽ ሲያቅፈኝ ጭንቀትሽን እረዳለው
.
በሌላ ቀን ተነፋፍቀን ስንገናኝ
ትንፋሽሽ ነው ማፍቀርሽን የሚያወጋኝ
እርግብ ሆነሽ እኔ ቁራ
ተራርቀን ባንድ ጣራ
እሳት ስሆን አንቺ ውሃ
ያልታደልኩሽ የኔ አምሃ
.
ዱሪቆን ነው በቃ እንቅር
እኔና አንቺ አንናገር
በሀሳብ መንገድ እንሳፈር
በልባችን እንፋቀር
አርግዚኝ በተስፋ ልብሽ ከኔ አይሽሽ
ልታገስሽ እኔም በተስፋ ላርግዝሽ
.
በማሪያም ዕለት ከንግስ መልስ
ከሜዳው ላይ ከአፀዱ ስር ምሽት ሳይደርስ
ተቀምጠን ተጠጋግተን በፍንደቃ ስናወጋ
ተሰምቶኛል አንዳች እውነት ከሙቀትሽ የላብ ቀጋ
-------------//----------

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

16 Dec, 12:04


😔😔   #መልስህን ንገረኝ  😔😔

ድሮስ የወደደውን መች ሰው ይፈልጋል
የማይፈልገውን ሄዶ ይለምናል።

    እኔም ከነዛ ውስጥ አንዷ ነሽ ብለዋል
    አንተ የኔ እንደሆንክ ማን በቅጡ ያቃል።

እኔ ስፈልግህ አንተስ እርቀሀል
እንዴት የኔ ላርግህ ሌላ ሰው ይዘሀል።

      የኔን ልብ ስሰጥህ መች አንተ ይገባሀል
       ለኔ ያለህን ስሜት ማወቅ ተስኖኛል።

እኔ አንተን ስፈልግ አንተ ስትል ሌላ
የኔ ልብ በስቃይ በሀዘን ተሞላ።

       አሁን የማሳይህ ላይገባህ ይችላል
       ስታቀው ሲገባህ እግርህ ይመልስሀል።

ተስፋ እንዳትቆርጥ ልቤ ይቀበልሀል
ጥላቻንም ገፍቶ ፍቅርን ያለብስሀል።

        በርግጥ አልዋሽህም ልቤ ይፈልግሀል
        በአፍ ባልነግርህም አይኔ አሳይቶሀል።

አልገባኝም ማለት አውቃለው እንደምችል
ግን ጥቅም የለውም አይገባኝም ብትል።

         አውቃለው እንደሌለህ የኔ እምትላት
         እኔ እኮ የለኝም የቅናት ስሜት።

ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እባክህ
ልሂድልህ በቃ ሙሉ ከሆነ ልብህ።

         ልቤ መውደድ ይበቃሀል
         ለእሱ እኔ አለሁ ለኔ ማን ያስብልብኛል።

የሰማዩ ጌታ የኔ ሁን ካላለው
ለኔ የፃፈውን እስኪ ልፈልገው።

         ካንተ ጋር መሆኑን ልቤ ይመኘዋል
          ያላንተ መኖሩን እንዴት ይችለዋል።

አንድ ቀን አስበህው ይገባህ ይሆናል
የሰው ልብ እንዲ ነው በተራው ይመጣል።

          ፈላጊ ነኝ እንጂ ማን ይፈልገኛል
          የሚፈልገኝስ መቼ ፍቅር ያውቃል
          እስኪጠግበኝ ብቻ ከጎኔ ይቆያል።


━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

07 Dec, 17:37


ሳልችል ቀርቼአለሁ😔

ልረሳሽ እልና ሁሉን አውጠንጥኜ
አውጥቼ አውርጄ ቀንሼ መጥኜ
ከልቤ ከአፌ ላወጣሽ ወስኜ☹️
ስላንቺ ላለማሰብ ድጋሜ እምላለሁ
አንቺኑ ለመርሳት ቃልም እገባለሁ🤚
  ግን ሱሴ ያን ሁሉ አውርቼ
   መሀላዬን ቃሌን ሁሉን እረስቼ🫢
አሁንም ስላንቺ መልሼ አስባለሁ🙈
እረስቼሻለሁ እንደው ቃልም ገብቻለሁ
አንቺን ላለማሰብ ጠላሁሽ ብያለሁ💔
  ስላንቺ ላለማውራት ከሰው ርቂያለሁ
አንቺን ላለማየት መንገድ ቀይሬለሁ😔
አንቺኑ ለመርሳት ሁሉን አድርጊያለሁ
ግንማ ድንጋይ ላይ ውሀ እንደማፍሰስ
    በዚ ጆሮ ሰምቶ በዛ እንደመደምሰስ
ካልኩሌተር ይዞ ከ 0 ላይ 0 እንደመቀናነስ
ሳልችል ቀርቼአለሁ አይሆንም ብያለሁ❤️‍🔥
   ልረሳሽ ያልኩ ለት በፍቅርሽ ወድቄያለው


#እራዛ

#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

07 Dec, 17:36


ኡፍፍፍፍ ሲከብድ

ልባችን ሲያቃስት መቋቋም ሲከብደው
አጥብቆ ሲፈልግ ደጋግሞ አንድን ሰው
መሸከም ተስኖት ፍቅርና ናፍቆትን
ጨካኝ ነሽ ቢላት ጨክኖ ህይወቱን

መጠጣት መብላቱን እርግፍ አርጎ ቢተው
እንቅልፍ ካይኑ ቢርቅ እንባ እንየሸፈነው
መተንፈስ ቢሳነው ሁሉ ቢለው ጭልም
የምር እረዳለው እኔ በሱ አልፈርድም


ከባድ ነው ትዝታ እጅጉን አድካሚ
በታሰበ ጊዜ የፍቅር ልብን አድሚ
አንዴ በፈገግታ አንዴ ደሞ ለቅሶ
ሁሌም ይታጀባል መልሶ መላልሶ

ብቻ ግን ከባድ ነው መቋቋም ይከብዳል
የደረሰበት ሰው ሁሏንም ያቃታል🥹


#እራዛ

#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

07 Dec, 17:36


🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
                 ይሏታል...........

ይሏታል መልከ መልካም ጸባየ ሰናይ🤗
ከምድር ያልሆነች የመጣች ከሰማይ🌎
ይሏታል ቆንጂት የኣይኖች ማረፊያ
የውበት ሁሉ ምሳሌ መታያ🥀
ይሏታል ከብርሃን የፈካች 💙
ከጨረቃ ከኮከብ የደመቀች🌜
ይሏታል እንደ እርግብ የዋ ውስጧ ገራገር💗
 ውበቷ ሀይል ኣለው ኣንዳች ሚስጥር
ይሏታል ሁሉን የረታች ጀግና❤️‍🩹
ከሁሉ ስም በላይ ስመ ገናና
ይሏታል ኩሩ ልበ ደንዳና❤️‍🩹
እሷን ያልፈራ ማን ኣለና❤️‍🔥
ለኔ ግን ሁሌም ምንም ናት
ያልሆነች እንደ ተባለላት🤎
ከማንም በምንም የማላሳንሳት
ሰው ስለሆነች እንደ ሰዉ ያየዋት
እዳዉም ለኔ ተቃራኒ ነች
እራሷን በሰዉ የደበቀች🖤
ማንነቷን በጥሪት የሸጠች
ክብሯን ጥላ የረከሰች 🩶
ማንነቷን ረስታ ለብር የኖረች
ሳትተኛ ተቀምጣ ያንቀላፋች
ኣዎ ለኔ በቁም የሞተች ነች🥹


            I miss you, more than I show
                I love you, more than you know 💞

#እራዛ

#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

07 Dec, 17:36


#ፍቅርን

#ፍቅርን :_በቃላት ሁሌም መግለፅ አስፈላጊ ቢሆንም በተግባር ግን ወሳኝ ነው።
የምታፈቅራት ከሆነ በተግባር አሳያት እንጂ በምላስህ አትደልላት የኔ ማር፣ የኔ ፍቅር፣ ህይወቴ፣ እናት፣ ቆንጆ ነሽ፣ ልዩ ነሽ፣ አይንሽ፣ ወ.ዘ.ተ እያልክ የቃላት ጋጋታ ከምትደረድርላት በተግባር አሳያት ያኔ እስትንፋስዋን ትሰጥሀለች።
ከቃላት ድርደራ ይልቅ አድርጎ ማሳየት አንተ ለሷ ምን አይነት ቦታ እንዳለህ ይነግራታል።
#እውነተኛ ፍቅር በምላስ ሳይሆን በተግባር ትገልፃለች እና አንተ ትንሽ ብለህ በተግባር ያሳየሀት ነገር ለሷ ትልቅ ነገር ነው።
ፍቅር ምላስን ሳይሆን በተግባር ትፈልጋለችና
#እውነተኛ ፍቅር የሚመነጨው ከልብ እንጂ ከቃላት ጋጋታ ብቻ አይደለም፤ ልብ ያስባል አንተ ትተግብርዋለህ።
ፈጣሪ እውነተኛ ፍቅር ይስጠን አሜን

Love is when the other person’s
happiness is more important
than your own.

#እራዛ

#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Nov, 11:47


🌹።።።።።🌹የፍቅር ጅማሮ🌹።።።።🌹


አዳምና ሄዋን ፍቅራቸው ሲጀመር
ታሪኩ እንዲህ ነበር

ሄዋን ፍቅር ይዟት ተጨንቃ ተጠባ
ስትል ፈራ ተባ
ቆይታ ቆይታ
እንደዚ አለችው አዳምን ተጣርታ

"ምን ብዬ ልንገርህ
አዳም የኔ ፍቅር
ፍቅርህን እሻለሁ
በጣም እወድሃለሁ
መልሥህን ንገረኝ እባክህ በሞቴ
ፍቅሬን ተቀበለኝ አዳም አካላቴ"

በማለት ጠይቃው ልቧ ሲንሠፈሠፍ
"ምን አማራጭ አለኝ!" አላትና እርፍ

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ምን በፍቅር ብታልቅ
ከሡ ይምጣ እንጂ እሷ ጠይቃ አታውቅ!

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Nov, 11:47


😍 ከአቅም በላይ ስለወደድኩሽ
      🙏 ይቅር በይኝ!
💞ከማንም በላይ ከአንቺጋ መሆን በመፈለጌ
      🙏 ይቅር በይኝ!
❤️በህይወትሽ ውስጥ ትልቅ ቦታ እንድትሰጪኝ በመጠየቄ
      🙏 ይቅር በይኝ!
💘መካድ እስከማልችል ድረስ ስላፈቀርኩሽ
     🙏 ይቅር በይኝ!
💔መውደዴ ስላልገባሽና በእኔ ውስጥ ያለሽን ቦታ ስላላወቅሽ
    🙏ይቅር እልሻለሁ!

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Nov, 11:47


​​​​        
   💔
#ተወደሻል_አንቺ_ልጅ💓

                   
💁‍♂
#እንዳንቺ አይነት ሌባ አይቼ አላቅም💕
ሰው ገንዘብ እንጂ ልብ እኮ አይሰርቅም
💗ፍቅሬ ህይወቴ የልቤ ትርታ
ወድጄሻለሁኝ ባንድ ቀን እይታ
ተወደሻል ቆንጅት ተወደሻል በቃ ላጣሽ አልፈልግም🙅‍♂ ለአንድ ደቂቃ!
👩የቆንጆዎች ቆንጆ የውበት ጭማቂ
ማትሰለቺ ነሽ ሁሌም ተናፋቃ
የ-አለም🌍 ውብ🦋 ነገሮች ሁሉም ይገቡሻል
💝የቁንጅና ሚለው ቃል በጣም ያንስብሻል💘
ሳልደብቅ ልንገርሽ ቆንጂት
ተወደሻል💖
💛ከልብሽ አስገቢኝ ከልቤ ገብተሻል የምር ስልሽ በኔ ተወደሻል🌹💞💔
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​  ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
🤍
━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Nov, 11:47


#እውነትን ከውሸት
ትወጂኝ እንደሆን እያልኩ ሳሰላስል
ሆኖብኝ ተቸገርኩ ፍቅርሽ የጅብ ችኩል
የጅብማ ችኩል ቀንድ ይነክሳል አሉኝ
ፍቅር ጣቴን ብሰጥ ነክሰሽ አቆሰልሽኝ
ትቀበዪኝ ብዬ ፍቅር ልቤን ብሰጥ
አልቀበል ብለሽ አንቺን ስለማመጥ
ሰከሬ ወደኩኝ በጭካኔሽ መጠጥ
አደነጋገርሽኝ ግራም አጋባሽኝ
ምን ልበል ጨነቀኝ የማወራው ጠፋኝ
እንደስደተኛ መሄጃ አጣሁኝ
ሀገሬ ውስጥ ሆኜ ሰው ሀገር መሰለኝ
በአይኔስ አያለሁ አሳወርሽው ልቤን
አካሌስ እዚሁ ነው ገደል ከተትኩ ፍቅሬን
ለምን?አትበዪኝ ልቤ ከታወረ በምኔ አያለሁ
ሁሉ ጨልሞብኝ ሰው ያለህ እላለሁ
ሰውም ጨካኝ አይደል ሚደርስልኝ አጣሁ
መስጠት እየቻልሽ ድምቅ ያለ ብርሀን
ጭካኔን ጨክነሽ አጨለምሽው ልቤን
ያንቺስ አጃኢብ ነው እንዲያው ትገርሚያለሽ
እውነተኛ ፍቅሬን ውሸታም ትያለሽ መልሰሽ
እየደባለቅሽ እውነትን ከውሸት ውሸትን ከእውነት
አመቱን ወር አልሽው ወሩን ደግሞ አመት
አሁን ግን ከበደኝ መለመን አልችልም
ሂጂ ሸኝሻለሁ ፍቅር በልመና ፈፅሞ አይሆንም

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

18 Sep, 16:48


ስልኬ አለው ግን ለስሙ ደውሎ አያውቅም👩🏾‍🦯👩🏾‍🦯 ቱ (ወይ ተነቀሰው😭💀)

ፍቅሬን በግጥም 💞

18 Sep, 16:47


“እንዲህ አይነት ፎቶ ግን አትላኪ። የሚወድሽ ወንድ እኮ እንዲህ አይነት ፎቶ እንድትልኪ አይጠይቅሽም" ብያት "በእዉነት አንተ በጣም ጥሩ ሰዉ ነህ። ከማዉቃቸዉ ወንዶች ሁሉ ትለያለህ" ብላ ለኔ መላኩን ትታ ለጓደኛዬ መላክ ጀመረች 😂😁😂

ቱ! እኔን ብሎ መካሪ!! 😢😄

በሉ እንግዲህ
ፏ ቧ ጓ ያለች ምሽት ተመኘሁላችሁ!!

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

18 Sep, 16:47


🧡ሰነፍ ሴት መባልን ፍራቻ የተሰሙሽን ስሜቶች መደበቅና ማፈን አይጠበቅብሽም የአንድ ሰሞን ማዘን እና መሰበርሽ ገፅታሽ ላይ መታየቱን እንደ ድክመትሽ ልትቆጥሪዉ አይገባም ይህ እኮ ሰዉኛ ባህሪ ነዉ አንቺ ላይ ብቻ አይደለም የታየዉ።

ይልቅ ከመሰበር ቡዃላ ያለችዋን አንችነትሽን አጠንክሪያት.....የማንንም ክንድ ለድጋፍ አትጠይቂ እንባሽን ማበሻ መዳፍ አትፈልጊ አንቺ ላንቺ በቂ ነሽ።

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

18 Sep, 16:47


ኪያዬ

ከዚ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ❤️

ፍቅሬን በግጥም 💞

18 Sep, 16:46


♡ህይወትን የሚያስውቡ ውብ ሰዎች አሉ።
ሳትፅፍ ያነቡሀል።
ሳትናገር ይረዱሀል።
ውለታን ሳይሹ መልካም ይውሉልሀል።
በእነዚህ ሰዎች ውስጥ መኖር ህይወትህን ውብ💞 ያደርገዋል።

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

14 Sep, 18:23


እዚህ ቻናል ውስጥ የቱ ይበዛል?


1.ተጀማሪ አፍቃሪ🥰
2.የተጎዳ አፍቃሪ💔
3.በፍቅር ውስጥ ያለ❤️
4.ሲንግል😜
5.ፍቅሩን ያልገለጸ🙈
6.ፍቅር አይዘኝም😱
7.sigma boy🙅‍♂
8.sigma girl 🙅‍♀

1🥰2💔34😜5🙈6😱7🙅‍♂8🙅‍♀
@public_Groupppp
@public_Groupppp

ፍቅሬን በግጥም 💞

14 Sep, 17:06


https://www.tiktok.com/@eraza_fil

ፍቅሬን በግጥም 💞

14 Sep, 17:06


https://www.tiktok.com/@eraza_fil

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:59


🌹ያችን ሴት ሁኚ🌹....
🍃

ማንም ስለፈለገ የማያገኛት🍃
በብልጭልጭ የማትታለለው
በቃ ለራሷ ክብር ያላትን🥀

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:59


💖💖...ስወድህ

ያለ ተቀናቃኝ ያለ ፉክክር😍
ቦታ አለህ በልቤ በፍቅሬ መንደር😘
አላወዳድርም አቻስ መች አለህ💓
እኔ አይሰለቸኝም ብኖር ስወድህ❤️
......
ስወድህ ስወድህ ስወድህ ኣ ኣ ኣ
Lyrics.....

እኔው ልጋፈጠው አንተ ተው አትልፋ 😔
የዘመኑን ጋሪ ችለህ ላትገፋ😌
ፍቅርህ እንደሆነ ርቆኛል አድቅቆ😭
መኖር ያውቅበታል የተነሳ ወድቆ😔
ኣ ኣ ኣ ኣ........

አይኔ ሌላ አያይም 🙈
❤️ አይሻ ሌላ
ካንተ ውጭ ቢኖር😮
ቆንጆ ወንድ ቢሞላ💓💓💓💓

ስወድህ ስወድህ
ስወድህ ስወድህ

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:59


ወንድነት ማለት
ሁሉም ሴት ስለወደዱህ
ሳይሆን ለ1ሴት ንፁህ ሆነህ
በንፁህ ልብህ አፍቅረሀት
ከሁሉም ሴቶች አስበልጠህ
ንግስት ማድረግ ማለት ነዉ።
ለሁላችሁም ይህን ያድላችሁ

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:58


ስላንቺ ማሰብ ለማቆም ሁሌም ለራሴ ቃል እገባለሁ፣ ከዛ ስልክ ቁጥርሽን እና ከሁሉንም የኢንተርኔት ገፆቼ አጠፋሻለሁ ፣ የሚያናድደዉ ይሄንን አድርጌ በደቂቃዎች መሃል እፀፀታለሁ፣
ከዚያ ቶሎ ስልክሽን ማፈላለግ እጀምራለሁ፣ ፎቶዎችሽን በማጥፋቴ ፀፀት ይሰማኛል ፣ከዚያ የበለጠ ትናፍቂኛለሽ የማልችለዉን በመሞከሬ ብዙ እቀጣለሁ፣
መቼም ልተዉሽ አልችልም የኔ ፍቅር!

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_ @getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:58


       ❤️🩵❤️🩵❤️🩵
          ማነው የተረዳኝ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።

━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

13 Sep, 16:58


ቅጣት

ውዴ ሳታስፈቅጂ በህይወቴ ገብተሽ
ባላስብኩት መንገድ እወድሀለው ብለሽ
ምንም አይቼ የማላቀውን ፍቅር አሳይተሽኝ
እኔም ድንገት ስላንቺ ማሰብ ጀመርኩኝ
ሀያሉ ፍቅር ነውና እኔም ሳይዘኝ አይቀረም
እንዲህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያቅም
ግንለምን ተለየሽኝ ይመስለኝ ነበርበጣምየምትወጅኝ
ቅጣት መሆኑ ነው እኔ እየወደድኩሽ አንቺ ምትለይኝ

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

10 Sep, 23:16


አዲስ አመት
.
.
ያ...ጠቢብ ሰለሞን..........
ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤
ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?

ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤
ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።

ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤
ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤
አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።

የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤
ጸሎቷን ለማድረስእጇን ለዘረጋች፤
ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤
ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።

የእምነትሽን ጥግ የቀሚስሽ ልኩን፤
በመጠበብ አየ ሰው ሰው መሽተትሽን።

ኢትዮጵያ የሚል ስም ገና ሳትነግሪዉ፤
ባንቺነሽ ክታብ ተቀልሞ ቢያየዉ፤
ሐበሻ ይሆን ዘንድ ዘሩን ቀላቀለዉ።

ዛሬም ለሀገሬ........
መከራ እንደ ሀምሌ ፀንቶ ላጨገጋት፤
ዉሽንፍር መባርቅት አብሮ ለሚንጣት፤

ቀለበትሽን አዉሻትና........
መከራዋ ያብቃ ነጭ ልብስ ትልበስ፤
ተስፋዋ ይለምልም በፍቅር ትታደስ፤
እንባዋ ታብሶ ብርሃን ይታያት፤
በዚ በአዲስ አመት ደግ ቀን ይዉጣላት።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

10 Sep, 23:16


አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?

ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን

አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት

"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው

"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ  ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና  የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ

እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?

"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"

ሆሆሆሆ!

አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!

ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?

አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው

ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ

እኔ ምስኪኑ

ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው  የማይቆጠር

እህት አበባ  ፡ እህት አበባ
እህት አበባ  ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው  የጨለመብኝ።

ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦

እንኩ አትበዪን፡

ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

05 Sep, 16:16


❤️💙💕💕❤️💛

አፍቅሬሽ ከልቤ ያኔ ስጠይቅሽ
አሻፈረኝ ያልሽው ብር የለህም ብለሽ
እድሜ ላንቺ ውዴ አሁን ብር ይዣለው
አሁን ስንት ገባሽ ይሀው ልገዛሽ ነው..

💘💘❤️‍🔥❤️‍🔥💝💝❣️❤️‍🩹🤍

-------------------------------------------
@getemi
@getemi
@getemi
♡ ㅤ  ❍ㅤ    ⎙ㅤ  ⌲            
ˡᶦᵏᵉ  ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ  ˢᵃᵛᵉ  ˢʰᵃʳᵉ
----------------------------------------

ፍቅሬን በግጥም 💞

05 Sep, 16:15


🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

😍😍😍ደስ ትይኛለሽ😀😀😀
""""""""'"''"'""""
ያቺ የመጀመሪያ ቀን ገና ሳይሽ ውዴ፣
ሳላስበው መተሽ ስትቆሚ ከፊቴ፣
ደስ ብለሽኛል ልንገርሽ በሞቴ፣
........
አይኖችሽ ተኩለው ልብ ይሰርቃሉ፣
አፍንጫሽ ቀጥ ብሎ ሌላ ያስንቃሉ ፣
ውበት ሰጥተውሻል ጥርስሽ መደርደሩ፣
ፈገግ ስትይ ዲንፕልሽ ማማሩ፣
ይሄ ሁሉ ነገር አሁን የማደንቀው፣
እውነቱን ስነግርሽ ደስ ስላልሽኝ ነው፣
ፀጉርሽን ስትለቂው እጅግ ያምርብሻል፣
አጠር ያለም ቢሆን ሌላው ቀንቶብሻል፣
አተኩሬ ሳየው የአንገትሽን ውበት፣
ጌጣጌጡ ይበልጥ ሆነውሻል ድምቀት፣
ውዴ ስለውበትሽ ብዙ ነገር ምለው፣
ደስ ትይኛለሽ ምክንያቱ ይሄ ነው፣
........ .
ወገብሽ መቅጠኑ ቀሚስ ሳመሩ፣
የዳሌሽ ስፋቱ አቤት ማስገረሙ፣
ቁመትሽ ሎጋ ነው ሰንደቅ ያሰቅላል፣
ይሄ ሁሉ ውበት ምን ይሰራልሻል፣
ሁለት ብትሆኚ ይበልጥ ያምርብሻል፣
እኔ ግን እውነቱን ስነግርሽ፣
የእግዜርን ጥበብ ማድነቄ ነው ስልሽ እመኚኝ እባክሽ፣
...........
ውበትሽ ልዮ ነው እርከን የሌለበት፣
ደም ግባትሽ ይስባል ምንም አይወጣለት፣
ይበልጥ ለግሶሻል ውበት ላንቺ አብልጦ፣
አብዝቶ ሰቶሻል እግዜር ላንቺ አድልቶ፣
ግን እኔ.................
ይሄ ሁሉ ነገር አሁን የምነግርሽ፣
ደስ ስላልሽኝ ነው ፍቅር እንዳይመስልሽ፤
😜😜👍አለቀ😆😆👌

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

05 Sep, 16:15


አትሂድብኝ

አንተን ሳገኝ . . .

ከሠማዩ ጥጋት ይመስለኛል የቆምኩ
ከሁሉ በልጬ ዓለምን የጨበጥኩ፤
እኔ ፀሐይ ሆኜ አንተ ውብ ጨረቃ
ሌት ከቀን ስንቦርቅ ህይወታችን ደምቃ፤
ከዛም ይሰማኛል በልቤ ደስታ
በሐሴት መሞላት የፍቅር እርካታ፤

አንተን ሳጣ . . .

ከባህር ጠለል ስር ልክ እንደተጣልኩኝ
መኖር ያቅተኛል ሁሉም ጨላልሞብኝ፤
እንባዬ ገንፍሎ በዝቶብኝ ትካዜ
እሸበራለሁኝ በናፍቆት አባዜ፤
ወዘናዬ ጠፍቶ ውበቴ ተገፎ
በአጥንቴ እቀራለሁ ስጋዬ ተራግፎ      

━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ

ፍቅሬን በግጥም 💞

05 Sep, 16:15


💔 ልቤ ምን አጠፋ💔

እኔስ መስሎኝ ነበር  ካንጀት ያፍርከኝ
ልቤን አብከንክነህ ምነው ጉድ አረከኝ
መውደዴን ነግሮህ  የሆዴን አውጥቼ
መዋል ማድር አልችል  ካንተ ተለይቼ
ሃሳቤ ጭንቀቴ ቢገባህ ምን አለ
ሌላ ብትቀይር ምን የተለዬ አለ?


ልቤን ብቻ ይዘህ ለምን ትዞራለህ
ተመልሰህ ጨርስ ነፈሴነው የቀረህ
ያንተው ህመምተኛ  ባይተዋር ሆኛለሁ
ህመምተኛ አደርኸኝ ለማን እሆናለሁ


እንግዲህ  ኑሮዬ በዱር በገደል ነው
ከሰው መኖር አልችል  ልቤ ካንተ ጋር ነው
አልበላም  አልጠጣም  ልድረቅ ልሁን እንጨት
የልቤን ከተማ ብቻ አንተ ኑርበት፣



አላስገድድህም ና ተመለስ ብዬ፣
ሁለተኛ ብትሄድ ምን ዋስትና ጥዬ
ያሁኑም ስራህ ምን ይታወቅሃል
የጊዜው  ይርዘም እንጂ ልቤ ይፈርዳል
ጊዜው ይርዘም እንጂ እንባዬ  ይፈርዳል 💔


━━━━━━━━✦✦━━━━━━━━
━━━━⸙ ፍቅሬን በግጥም⸙━━━━
#ሼር
♥️
   ♥️
♥️
▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️
━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━

    🪴🌹ከወደዱት አጋሩ🌹

        ✦_
@getemi _✦
      ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲            
      ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ