FDRE Education and Training Authority @fdre_eta Channel on Telegram

FDRE Education and Training Authority

@fdre_eta


በኢፌድሪ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን
http://www.eta.et/

9799 "በኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ነጻ የስልክ ጥሪ ማዕከል"

FDRE Education and Training Authority (Amharic)

መሰረት FDRE ትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን ቦታ፣ እና ትራንስፎርሜሽን (ETA) እንዴት እንደሚያስችል አስተዋጽኖ ለመሆኑ ይህን ማዕከል እዚህ በመሆኑ አላባረክነትና በባለአገልግሎት ከበከበው ነው። ከሚያሰክርና ለማኅበርም ያስፈፃሚ አመልካች በአፍኖም ከእንግሊዝ ተለይተውስ የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣንን እንዲሆን የሚጠቀሙ በተሳሱበት በሁላችሁም ምግብ ባለሥጋችሁ ዓለም እና ውጤታማ ፕሮግራም እርምጃዎችን መዝጊያ ሊሆኑ ይችላል ፡፡ በኢፌዱሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንነት ምክንያት እንዴት ተገንቦ እንደሚሆንባችሁ እንምዟችሁ።

FDRE Education and Training Authority

20 Nov, 07:31


ህዳር 10፣2017

አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡

አህመድ አብተው(ዶ/ር) የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸውን ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ሰምተናል።

ዶክተር አህመድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ከትናንት ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ነው ተብሏል፡፡

ይህንን ለሸገር ራዲዮ የነገሩት በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የህዝብ ግኑኝነት እና ኮሙኒኬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርታ አድማሱ ናቸው።

ቀድሞ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣንን በዋና ደይሬክተርነት ሲመሩ የነበሩት አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል፡፡

ማንያዘዋል ጌታሁን

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q

📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g

📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s

📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il

FDRE Education and Training Authority

20 Nov, 07:17


የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሾመለት
***** ***** ***** ***** ***** *****
አህመድ አብተው(ዶ/ር) ከህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ምጀምሮ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ ተሾመዋል፡፡
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡፡ የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ

FDRE Education and Training Authority

19 Nov, 12:29


የባለሥልጣኑ አመራሮች እና ሠራተኞች የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል ርዕስ ላይ ተወያዩ
============= ========== =========
የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮች እና ሠራተኞች ብልፅግና ፓርቲ የተመሠረተበት አምስተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ "የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም በባለሥልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ሰነዱ በሀገር ደረጃ እንዲከናወኑ በእቅድ የተያዙ ስራዎችን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ ግንዛቤ በመያዝ በዘርፉ እንዲሁም በሀገር ደረጃ የሚጠበቀውን እድገት ለማስመዝገብ በትጋት መስራት አለበት ብለዋል፡፡
የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡት በባለሥልጣኑ የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ ሲሆኑ በውይይቱ የብልፅግና ፓርቲ አመሠራረት፤ ተግዳሮቶችና ትሩፋቶች እንዲሁም ቀጣይ ጉዳይ አመላካች፣ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠርና የሀገረ መንግስት ቅቡልነትን ለማሳደግ የሀገራዊ ፓርቲ አስፈላጊነት፣ የጋራ ህልምን መረዳትና ማሳካት እና የመንግስት ሠራተኛውን ሚና በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ድንኳና ንጉሳ ፤ የተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና የጥራት ኦዲት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ እና የተቋማት ቁጥጥር፣ኢንስፔክሽን እና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ኤሮ የውይይት ሰነድ መሠረት በማድረግ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢፊዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን
ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ፤አዲስ አበባ
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ