ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ @ethio_tksa_tks Channel on Telegram

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

@ethio_tksa_tks


#𝑞𝑢𝑜𝑡𝑒
#𝑚𝑜𝑡𝑖𝑣𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛
#𝑖𝑛𝑠𝑝𝑖𝑟𝑎𝑡𝑖𝑜𝑛

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ (Amharic)

የኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ ቻናል አሁን በተገኘ በመገኘትና በመረጠው ችግር ከሆነ ከተለያዩ አይነቶችን ሳንካዋን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ለውጭ ተወዳጅ ስለሆነ ብዙ ተከታታይ ውይይቶችን መጠን ይመልከቱ። ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ በተጨማሪም ማለት ነው የሚቆይና የምግብ እና ሌሎችን ሊስት እያልኩ ይታወቃሉ። ይህን በእርስዎ ተከታታይ እና ታዳጊ የተዘጋጀ ተከታታይ ውይይት በበጎ በጠበቁ ቦታዎችን ይገኛል።

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Feb, 03:44


ከእንቅልፍህ ስትነቃ ፈጣሪህን ማመስገንን አትርሳ #ምክንያቱም እርሱ አንተን ማንቃትን አልረሳምና

አንዴ ልመርቃችሁ አሜን በሉኝ እንደ እናት ፈገግታ ያማረቀን ይሁንላችሁ 👋

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Feb, 03:18


Everything you need 🔥🔥🔥

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

06 Feb, 11:59


ልብ የሚነካ ታሪክ💔

በአንድ ወቅት በጃፓን የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቀዝቀዝ ካለ በኋላ የነብስ አድን ሰራተኞች በአንድ ፍርስራሽ ቤት ሲገቡ የአንዲት ሴትን እሬሳ ተመለከቱ።
ሴትየዋ በጉልበቷ  ተንበርክካለች፤ ሰውነቷ ወደ ፊት ዘንበል ብሎ ነበር፣  ሁለቱ እጆቿ በአንድ ነገር ተደግፎ ነበረ። የፈራረሰው ቤት ጀርባዋ እና ጭንቅላቷ ላይ ወድቋል።
የነፍስ አድን ቡድን መሪው እጁን ወደ ሴቲቱ አካል ለመድረስ በግድግዳው ላይ ባለው ጠባብ ክፍተት ውስጥ እጁን ሴትየዋ ላይ አደረገው።
ሴትየዋ አሁንም በሕይወት ልትኖር እንደምትችል ተስፋ አድርጎ ነበር። ይሁን እንጂ ቀዝቃዛው እና ግትር ሰውነቷ በእርግጠኝነት እንደሞተች ነገረው💔
እሱና የተቀሩት የቡድኑ አባላት ከሴትየዋ ቤት ወጥተው ቀጣዩን የፈራረሰውን ሕንፃ ለመፈተሽ ሄዱ።
የቡድን መሪው ግን የሆነ ነገር ተጠራጠረና ወደ
......

ከ20♥️ like በኋላ ይቀጥላል

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

06 Feb, 06:09


እንደ ንስር ሁኑ!

ንስርን የሚደፍር ሁነኛ ወፍ ቁራ ነዉ። ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥ እና አንገቱን ይነክሰዋል።ንስሩ ምላሽ አይሰጥም፤ ከቁራ  ጋር አይጣላም፤በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበት አያጠፋም፤ ይልቁንም ክንፉን ከፍቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር  ይጀምራል።
በረራዉ ከፍ ባለ መጠን ቁራዉ ለመተንፈስ ይቸገራል እና በመጨረሻም ቁራዉ በኦክስጂን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።
ዝቅ ብላችሁ ስላገኟችሁ፤ ጀርባችሁ ላይ እየወጡ ፣ ሥራችሁን እንዳትሰሩ የሚነቋቁሯችሁ ፣ ሠላም የሚነሷችሁ በዙሪያችሁ ቢኖሩም መፍትሄው መጣላት ፣ ማማረር፣ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን  ከፍ ብላችሁ መብረር,ነዉ!!
ራሳችሁን በእዉቀት አጠንክሩ፤ በሥራችሁም የበለጠ ታታሪ ፣ ጠንካራና ዉጤታማ ሁኑ!

በቅንነት share & react  እያደረጋችሁ

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

05 Feb, 17:47


የፍቅር ጥግ!

አባትነት በልጅነቴ አይገባኝም ነበር።
በጠዋት የሚወጣ ኮስተር ያለ ሰውዬ ማታ ይመጣል።
አጥና ይላል , ሳጠፋ ይመክራል, ግዛልኝ ያልኩትን አይነት ጫማ እና ልብስ አይገዛም።

እንደሚወደኝ ነግሮኝ አያውቅም።
እንዳይቆጣኝ እርቄ አልሄድም ቤት ውስጥ ቁጭ ካለ እንደልቤ አልነጫነጭም። ካጠፋሁ , ላጠፋ ስል የሱን ስም እየጠሩ ያስፈራሩኛል።

አደኩኝ።
ሳድግ አባቴን አየሁት። ጨዋ ነው , ታታሪ ነው , ለፍቶ አዳሪ ነው። ሀላፊነቱን ይወጣል እንደሱ ደሀ እንዳልሆን ነበር የሚታገለው። ባለጌ እንዳልሆን ነው የሚመክረኝ። ከሱ የተሻለ እንድሆን ነው የታተረው። ፋብሪካ ሰርቶ እየዋለ ነው ደከመኝ ብሎ የማያውቀው። መዝናናት እያማረው ፍላጎቱን ቸል ብሎ ነው የቻለውን ሁሉ ለሚስቱ , ለልጆቹ , ለጎጆው የሚያሟላው።

ስሜቱን ስለሚቆጣጠር ነው የሚሰማውን ሁሉ የማይናገረው። ሲያመው አመመመኝ የማይለው እንዳንጨነቅ ነበር። ሲያመኝ የሆነውን, የምፈልገውን ለማሟላት የሄደበት መንገድ የፍቅሩን መገለጫዎች ሳያቸው መውደዴ ከማዘን ጋር ተጣበቀብኝ።

በቅንነት share & react  እያደረጋችሁ
@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

01 Feb, 05:02


መጀመሪያ አንተ ተቀየር!

ለሰዎች መምከርማ እንችልበታለን! ምን ቢያደርጉ እንደሚሻል ከነሱ በላይ እኛ እናውቃለን፤ ችግሩ እሱ አይደለም "ለራሴስ እንዴት ልወቅበት?" ነው ጨዋታው።

አንድ የማከብረው ሰው "አገሬን እቀይራለው ብዬ ተነሳው ብዙም ሳልቆይ እንደማይሆን ገባኝ፣ አይ መቀየር ያለብኝ ከተማዬን ነው አልኩ እሱም እንደማይሳካ ሲገባኝ ሰፈሬን አልኩ፣ ከዛ ቤተሰቦቼን አልኩ....በመጨረሻ የገባኝ ነገር መጀመሪያ ራሴን መቀየር እንዳለብኝ ነው" ይለናል።

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

31 Jan, 19:31


እንግሊዝኛ ምን በአለም ቢነገር፣ ምን ቢሊዮኖች ቢመኙት .. እዚያው ከቻይና ብር ይበደሩበት እንጂ፤ ፊልም ይስሩበት እንጂ፤ እንደ እኔ ላለው መች እንደ አማርኛ የልብ ያደርሳል?

✔️እስቲ አሁን "አይዞህ"ን በእንግሊዝኛ ልበልህ ብለው እንዴት ይገለጻል?
እንግሊዘኛ እንደ ቋንቋ መተሳሰብን መች ይደግፋል? እስቲ አሁን እንግሊዝኛ "እኔን እኔን" ብሎ ነገር የት አባቱ ያውቃል? እሱን ተውት "የት አባቱ!" ማለትንስ የት አባቱ አውቆት? ሰው እንቅፋት ሲመታው "እኔን" በሚለው መተሳሰብ ፋንታ "ዋች አውት! አር ዩ ኦኬ? የት ያደርሳል? "ዋች አውት" አጠጋግተን ስንተረጉመው "ምን አባሽ ያደናብርሻል?" አይደለምን?

©ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚያብሄር

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Jan, 11:54


ማጂድ ካቮሲፋር፡ ዝርዝር ታሪክ

  ስለ ማጂድ ካቮሲፋር የልጅነት እና የወጣትነት ህይወት ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም። በ20ዎቹ መጀመሪያ አመት የእድሜ ክልል ውስጥ እንደነበረ የሚገመት ሲሆን፣ ያደገው እና የኖረው በኢራን መሆኑ ይታወቃል። ከቤተሰቡ ጋር የነበረው ግንኙነት ምን እንደሚመስል በግልፅ አይታወቅም።

  በማጂድ እና አጎቱ በሆሴን ካቮሲፋር የተፈፀመው የአቃቤ ህግ ማሶድ ሞላሳልታኒ ግድያ ዋና ምክንያት በይፋ የሚተታወቅ አይደለም። ሆኖም ብዙዎች ይህ ግድያ በፖለቲካዊ ወይም በግለሰባዊ በደል የተፈፀመ ነው ብለው ያምናሉ። አንዳንድ ወሬዎች ደግሞ ግድያው በሌሎች ወንጀሎች ውስጥ ከመሳተፋቸው ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ይናገራሉ። ነገር ግን በምንም መልኩ እውነቱ በግልጽ አልታወቀም።

  ማጂድ እና ሆሴን አቃቤ ህጉን የገደሉት በጥይት በመተኮስ እንደሆነ ታውቋል። ቦታውም በኢራን ዋና ከተማ በቴህራን መሃል ላይ ነበር። ግድያው በጠራራ ፀሀይ የተፈጸመ ሲሆን ይህም በወቅቱ ብዙ ሰዎችን አስደንግጦ ነበር።

  ከግድያው በኋላ ሁለቱ ወንድማማቾች በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ። በፍርድ ቤት ክስ ቀርቦባቸው ሁለቱም በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ተፈርዶባቸዋል። በወቅቱ በኢራን የነበረው የፍርድ ስርዓት ለግድያ ወንጀል የሚሰጠው ቅጣት ሞት ነበር። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ ሁለቱንም ወንድማማቾች በሞት እንዲቀጡ ወሰነ።
 
  በኢራን የሞት ፍርድ በተለያዩ መንገዶች ይፈፀማል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ በአደባባይ ላይ በመስቀል ነው። የማጂድ እና የሆሴን የሞት ቅጣት የተፈፀመውም በዚሁ መንገድ ነበር። ከመገደላቸው በፊት በሰንሰለት ታስረው እና የሞት ገመድ አንገታቸው ላይ ተጠምጥሞ፣ በአደባባይ ታይተዋል። ይህ በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ትዝብት እና ሀዘን ፈጥሯል።

  ከሁሉም በላይ የሚያነጋግረው የማጂድ ካቮሲፋር ፎቶግራፍ፣ በሞት ፍርድ ከመገደሉ በፊት ሲስቅ የሚያሳይ ነው። የዚህ ፈገግታ ትርጉም እስካሁን ድረስ ግልፅ ባይሆንም፣ ብዙ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተውበታል።

  •  ድፍረት እና ተቃውሞ፡ አንዳንዶች ማጂድ በሞት ፊት እንኳን ሳይንበረከክ ድፍረቱን ለማሳየት ፈገግ ብሏል ይላሉ። ለፍርድ ቤቱ እና ለስርዓቱ ተቃውሞውን የገለፀበት መንገድ እንደሆነ ያምናሉ።
  •  መጨረሻ ሰላምታ: ሌሎች ደግሞ የማጂድ ፈገግታ፣ ከዚህ ዓለም ለመሰናበት መዘጋጀቱን እና በመጨረሻም ሰላም ማግኘቱን ያሳያል ይላሉ።
  •  በጣም የተወሳሰበ ስሜት: አንዳንዶች ደግሞ ፈገግታው በጣም የተወሳሰበ ስሜት ሲሆን፣ ድብልቅልቅ ያለ ፍርሃት፣ ተስፋ መቁረጥና ተስፋ ማድረጉን ያሳያል ይላሉ።

 
ብቻ የምሆነ ይህ ማጂድ ካቮሲፋር በ2007 የተገደለ አንድ ኢራናዊ ወንጀለኛ ሲሆን ፈገግታው ግን ሁሉም ልብ ውስጥ ቀርቷል

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Jan, 03:56


"What’s more unbelievable: Words that move mountains, facts that defy logic, or images that seem unreal?"

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

29 Jan, 16:13


ንጉሱ ግጥም አነበበና እንዴት ነኝ¿ ብሎ ነስሩዲንን ጠየቀዉ

"ምንም አትችልም። ልክ እንደ ህፃን ነህ።"

ንጉሱ ተናደደና 3 ቀን አሳሰረው።

በአራተኛው ቀን አሶጣውና አነበበለት...ከዛም እ አሁንስ እንዴት ነኝ? አለው።

ነስሩዲን ዝም ብሎ ሄደ። ንጉሱ ተናዶ ወዴት እየሄድክ ነው? ሲለው

ነስሩዲን፦ "ወደ እስር ቤት.."😐

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

29 Jan, 13:34


✅️ በአንድ ወቅት ጋዜጣ በመሸጥ ደሃ ቤተሰቦቹን ለመርዳት ይታትር የነበረ አንድ የ ሰምንት አመት ልጅ፣ቀኑን ሙሉ ምግብ ሳይቀምስ  በከተማዋ መንገዶች እየተዟዟረ ጋዜጣ ሲሸጥ ይዉላል።

ይሁን እንጂ ያገኘዉ ገንዘብ ምግብ ገዝቶ ለመብላት የሚበቃ አልነበረም ፣ከረሃቡ በላይ የዉሃ ጥሙ ቢበረታበት፣ በአካባቢው ከነበሩ ቤቶች ወደ አንዱ በመሄድ....

✅️  "የምጠጣው ዉሃ ስጡኝ??"ሲል ይለምናል።የቤቱ ባለቤት መልካም ሴት ስለነበረች፣ምንም እንኳን ህፃኑ የጠየቀዉ ዉሃ ቢሆንም በዉሃዉ ምትክ ወተት ትሰጠዋለች።

ህፃኑም በዝግታ ወተቱን ጠጥቶ ከጨረሰ በኋላ፣ወደ መልኳሟ ሴት እየተመለከተ "ስንት ብር ነዉ የምከፍለዉ?"ሲል ይጠይቃል።

✅️ "አይ ምንም አትከፍልም!!ለመልካም ስራ ክፍያ እንዳልቀበል ያስተማረችኝ እናቴ ነች።"በማለት ህፃኑን ወደ ቤቱ ትሸኘዋለች።

ከአመታቶች በኋላ ይህ ህፃን በአሜሪካ ታዋቂ በሆነዉ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል እጅግ ከሚከበሩ ዶክተሮች መሃል አንዱ በመሆን እያገለገለ በነበረበት ወቅት፤አንድ በጠና የተመመች ሴት ወደ ሆስፒታሉ ትመጣለች።

በጠና የታመመችዉ ሴት፣ዉሃ ጠይቆ ወተት የሰጠችዉ ያች መልካም ሴት እነደሆነች ለማወቅ አስታዋሽ አላስፈለገዉም ነበር።

ቀንና ለሊት ሳይሰለች ከህመሟ እንድታገግም እርዳታ ያደርግላታል።ምንም እንኳ እሷ ባታስታዉሰዉም ለሰጣት እንክብካቤ አጅግ ታመሰግነዋለች።

ለህክምና ወጪ የምትከፍለዉ ገንዘብ አልነበራትምና  የገንዘብ መክፈያ ደረሰኙን ሲሰጧት በፍርሃት ነበር የከፈተችዉ፣በደረሰኙ ግርጌ በጉልህ የተፃፈ አንድ ፅሁፍን ተመለከተች፤ፅሁፉም እንዲህ የሚል ነበር.....

        "በአንድ ብርጭቆ ወተት፣ሙሉ በሙሉ ተከፍሏል። "

         "Paid in full with a glass of milk."

የዚህ እዉነተኛ ታሪክ ባለቤት የአሜሪካዉ ጆን ሆፕኪንስ ሆስፒታል መስራችና አሜሪካ ካፈራቻቸዉ ድንቅ ዶክተሮች መሃል አንዱ የሆነዉ የዶክተር ሃዋርድ ኬሊ ነዉ።

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

29 Jan, 13:20


For profile picture

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

29 Jan, 10:21


የህይወትን ምንነት የሚያጠቃልል አጭር ታሪክ ይህ ነው።

ልጅ አባቷን ጠየቀችው፦“ምርጥና ደግ ሰዎች ለምንድነው ቶሎ የሚሞቱት?”

አባትም ጥያቄዋን በጥያቄ መለሰ፦“የአትክልት ስፍራ ውስጥ ብትሆኚ የትኛውን አበባ ነበር የምትመርጪው?”

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

28 Jan, 18:28


ይህ አሜሪካዊ ሰው ስሙ ኢሳያስ ማትዮስ ይባላል።

አሜሪካን አይዶል ላይ ቀርቦ አንዲህ አለ . . .
"ልጅ እያለሁ እንደማንኛውም ልጅ ምኞትና ተስፋ ነበረኝ። አድጌ፣ ተመርቄ፣ ስራ ይዤ፣ ሚስት አግብቼ፣ ልጆች ወልጄ፣ በቤተክርስቲያን ዘማሪነት እያገለገልኩ በደስታና በስኬት የመኖር ትልቅ ህልምና ተስፋ ነበረኝ። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ አንዱም አልተሳካልኝም። ምክንያቱም 18 ዓመት ሲሆነኝ በአንድ በተረገመች እለት ምንም በማላውቀው🤷‍♂ ጉዳይ ፖሊሶች በዘረፋ ተጠርጥረሀል አሉኝና ያዙኝ። ኧረ ንፁህ ነኝ ብልም የሚሰማኝ👂ጠፋና ተዘርፈዋል የተባሉ ሰዎችም ሌባውን ይመስላል ስላሉ ብቻ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደብኝ። ያለ ጠያቂ ለ54 ዓመት በአንድ ክፍል ውስጥ ተቆለፈብኝ። መጀመሪያ አከባቢ ተስፋ ቆረጥኩ። ቆየት ብዬ ግን ይሄ ነገር የእግዚአብሔር አላም ሊሆን ይችላል ብዬ በፀጋ መቀበል ጀመርኩ። ከዚያ ያለ አጃቢ ባንድ፣ ያለ ሙዚቃ መሳሪያ🎹 በባዶ ክፍል ውስጥ በየቀኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር ማመስገን ጀመርኩ። ብዙ አመታት ያለምን ለውጥ ነጎዱ . . .
ከ54 አመታት በኃላ መዝገቤን በአጋጣሚ ሲያየው አላግባብ እንደተፈረደብኝ የተገነዘበ አንድ ወጣት የህግ ባለሙያ ወደ እኔ መጣና ጉዳዬ እንደገና እንዲታይ(judicial review) ሊደረግ እንደሆነ ነገረኝ። ተስፋ ባላደርግም ይቅናህ አልኩት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ጉዳዩን እንደገና አሳይቶ በ72 አመቴ በነፃ እንድለቀቅ አደረገኝ። ስወጣ ግን ምንም ነገር አላገኘሁም። ቢሆንም እግዚአብሔር ይመስገን እዚያ እያለው በነፃነት በመኖራቸው እቀናባቸው የነበሩት ብዙዎቹ በህይወት የሉም። እኔ ግን ዛሬ ላይ ንፁህ አየር እየተነፈስኩ🌬️ የማለዳ ፀሀይ በነፃነት እሞቅኩ በህይወት አለው። በህይወት መኖር ብቻ ሳይሆን አንድ ቀን በህዝብ ፊት እዘምራለሁ ብዬ ስመኘው የኖሩኩት ምኞቴ እውን ሆኖ ይሄው በእናንተ ፊት ቆሜ እግዘብሔርን ላመሰግን ደስተኛ ነኝ" አለና በለስላሳ ድምፁ . . .
"በሀሰት በከሰሱኝ ጊዜ፣ የሚሰማኝ አጥቼ በተፈረደብኝ ጊዜ፣ ከ50 ዓመት በላይ ያለ በቂ ምግብ እና ልብስ፣ ያለ ጠያቂ ወገን በአንድ ክፍል ውስጥ በተዘጋብኝ ጊዜ፣ አለም ሁሉ በረሳኝ ጊዜ፣ አበቃልኝ ብዬ ቀኑም ለሊቱም በጨለመብኝ ጊዜ ከጎኔ ያልተለየኸኝ አባቴና አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ከልቤ አመሰግናለሁ!" እያለ በእንባ ታጅቦ መዝሙሩን ያንቆረቁረው ጀመር።
ይሄኔ ከአወዳዳሪዎች እስከመድረክ አስተባባሪዎች፣ ከታዳሚዎች እስከ ጥበቃዎች አዳራሹ በሙሉ በለቅሶ ተናጋ።

በርግጥ አንኳን እነሱ እኔም ሳየው አልቅሻለሁ

ጎበዝ እምነት ማለት ሲደላን የምናጠነክረው የምንጠብቀው ስንጣል ደግሞ የምንጥለው አይደለም🙅‍♂‼️ ፈጣሪን በመሸ በነጋ እንደ ኢሳያስ ከልብ ለማመስገን ምንም ባይኖር በእስር ቤትም ቢሆን ያለምንም ነገር መኖር ብቻ በቂ ነው።


አንድ ሰው ያስተምራል ካላቹ Please ➥Share

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

28 Jan, 15:48


🦅ንስርን ለመምታት የሚደፍር ብቸኛው ወፍ ቁራ ነው። በንስር ጀርባ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በመንቁሩ ይነክሰዋል። ሆኖም ንስር ምላሽ አይሰጥም ወይም ቁራውን አይዋጋም። ንስር ከቁራ ጋር በመዋጋት ጊዜና ጉልበት አያባክንም። ንስር ክንፉን ከፍቶ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ መብረር ይጀምራል። በረራው ከፍ ባለ ቁጥር ለቁራ መተንፈስ አስቸጋሪ ይሆናል እና በመጨረሻም ቁራ በኦክስጂን እጥረት ይወድቃል። ለዚያም ነው አንዳንድ ጊዜ ለሁሉም ጦርነቶች ምላሽ መስጠት አያስፈልግም።ለሰዎች ክርክር ወይም ትችት ምላሽ መስጠት አያስፈልግም። ስብዕናዎን ብቻ ያሳድጉ።

🗣 ኦሾ

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

28 Jan, 09:37


ለፈገግታ

አንድ በእድሜ ብዛት የጫጨ አዛውንት አልጋ ላይ ሊሞት እያጣጣረ ነው።

✔️አምስት የቤተሰቡ አባላት ቆንጅዬ ሚስቱና አራት ልጆችሁ ከአልጋው አጠገብ ቆመው የማይቀረውን ሞት እየጠበቁ ነበር።

✔️ ከልጆቹ መካከል ሦስቱ ታላላቆች ረጃጅሞች፣ ቆንጆዎች እና አትሌቲክስ ነበሩ፤ ነገር ግን አራተኛውና የመጨረሻው ልጅ የቤተሰቡ አስቀያሚ ነገር እንደነበር ጥርጥር የለውም።

ባልየው በሹክሹክታ "ውድ ሚስቴ ትንሹ ልጅ በእውነት የእኔ መሆኑን አረጋግጭልኝ። ከመሞቴ በፊት እውነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ ሃቅ ከነገርሽኝ ይቅር እልሻለሁ" ሚስትየው በእርጋታ አቋረጠችውና "አዎ የኔ ውድ በፍፁም ምንም ጥያቄ የለውም በእናቴ መቃብር ላይ እምላለሁ አባቱ አንተ ነህ" አለችው። ሰውየው በመጨረሻ ለብዙ አመታት ያስጨነቀውን ጥያቄ በመጠየቁ ደስተኛ ሆኖ ሞተ።

ውድ ባል ትንፋሹ ፀጥ ካለ በኋላ ሚስትየው ቁና ቁና እየተነፈሰች "ፈጣሪ ይመስገን ስለ ሶስት ታላላቆች አልጠየቀኝም" 🤦🏼‍♀

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

28 Jan, 05:05


Relax!!!

•  ያመለጣችሁን “እድል” ስታሰላስሉ፣ በፊታችሁ ያለውን ድንቅ ነገር እንዳታባክኑት!

•  ትተዋችሁ ስለሄዱት ሰዎች ስታወጡና ስታወርዱ፣ አጠገባችሁ ያሉትን አስገራሚ ሰዎች እንዳታቷቸው!

•  ገና ለገና ይሆንብኛል ብላችሁ ስለምትሰጉት ነገር ስትጨነቁ፣ ለሚመሆንላችሁ ድንቅ ነገር ሳትዘጋጁ ጊዜ እንዳያልፍባችሁ!

•  ሰዎች ሊያዝኑባችሁ ስለሚችሉት ነገር በማሰብ እነሱን ለማስደሰት ስትታገሉ ራሳችሁን እንዳታጡት!


እስቲ ትንሽ ፈታ፣ ዘና በሉ!

መልካም ቀን

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

27 Jan, 18:29


ከዚህ ታሪክ ምን ተማራችሁ ሃሳባችሁን ግለጹልን

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

27 Jan, 16:42


ስህተትህን ....

ቶማስ ኤዲሰን ብዙ ተሳስቶ አምፖልን ፈጠረ። ስለስህተቶቹ ሲያወራ ግን እንዲህ ይላል 'እኔ ብዙ ስለሞከርኩ ደስተኛ ነኝ ምክንያቱም ሁሌም ስሞክር ወይ ልክ ነኝ ወይ ደግሞ ተምሬበታለው' ይለናል።

ያለፉ ስህተቶቻችንን ለከፍታችን መጠቀም አለብን፤ ሰሞኑን ካጋጠመኝ ችግር ምን ተማርኩበት እንበል። ሁለቴ መውደቅ የሚፈልግ የለም መቼም...አሸናፊ ማለት የማይወድቅ አይደለም፤ ቢወድቅም መልሶ የሚነሳ ነው። የሆነ ነገር አልሳካ ሲለን እስኪ ምንድነው ያጎደልኩት ብለን ጊዜ ወስደን ማሰብ አለብን።

ከስህተት በላይ ምን አስተማሪ ነገር አለ? እንደውም ምርጥ አድርጌ ደግሜ እንድሰራው እድል ተሰቶኛል ማለት አለብን።

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

27 Jan, 14:37


የአንገት ጌጡ

አንድ ውብ ወጣት ሴት ነበረች። ነገር ግን ከድሀ ወገን ስለነበረች አንድ ተራ ፀሀፊ አገባች።በህይወቷ ደስተኛ አልነበረችም።

*ታዲያ ባሏ የትምህርት ሚኒስትሩ ከሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ተጠራ።ዜናው ያስደስታታል ብሎ ሮጦ መጥቶ ቢነግራት እንደጠበቀው አልተደሰተችም።**

"ምነው?" ቢላት
"ምን ለብሼ እሄዳለሁ?" አለችው።

ትንሽ አሰበና ለአስፈላጊ ጊዜ ይሆናል ብሎ አስቀምጦት ከነበረ ብር ላይ 300 ፍራንክ ቀንሶ ሰጣት
ደስ እያላት ሄዳ አዲስ ቀሚስ አሰፋች።

ቀሚሱ ካለቀ በኋላ ደግሞ ለካ ስታስበው ምንም የሚረባ ጌጣ ጌጥ የለት።ባሏ ግን አንድ ሀሳብ አቀረበላት።አንድ ሀብታም ጓደኛ ነበረቻት።

"እና ለምን ከሷ አትዋሺም?" አላት።

በማግስቱ ጓደኛዋ ጋር ሄደች።
መረጠችና በጣም የተዋበ የአንገት ሉል ተዋሰች
አሁን ሁሉም ሙሉ ሆነ።ወደ ግብዣው ሄደች።ሰዎች ምን ያህል ውብ እንደሆነች አዩ።ሁሉም ሰው ከሷ ጋር መደነስ ፈለገ።ሚኒስትሩ ሳይቀሩ አነጋገሯት።በህይወቷ በጣም የተደሰተችበት ቀን ሆነ።

ግብዣው አልቆ ከባሏ ጋር በሰረገላ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ሄደች።ቤት ስትደርስ ሉሉን ከአንገቷ ላይ ብትፈልገው አጣችው።በጣም ደነገጠች።ከባሏ ጋር ሆነው በመጡበት መንገድ ተመልሰው ሌሊቱን ሁሉ ሲፈልጉት አደሩ።ሊያገኙት አልቻሉም።በማግስቱም በብርሀን ፈለጉት። ምንም ፍንጭ ጠፋ። ተስፋ ቆረጡ።

በመጨረሻ ጌጣ ጌጥ ሰሪ ቤት ሄደው ተመሳሳዩን ለመግዛት ጠየቁ።17000 ፍራንክ ተባሉ።ድሀ ቤተሰብ ናቸው!እድሜ ልካቸውን ከፍለው የማይጨርሱት የአራጣ ብድር ተበድረው ሉሉን ገዝተው ለባለቤቷ መለሱ።ከዚያ ያንን ብድር ለመክፈል ሁለቱም ከአቅማቸው በላይ ሶስት አራት ስራ እየሰሩ በ10 አመት ብድሩን ከፍለው ጨረሱ። በድካሟ መሀልም፣ ያን ሌሊት ያ ጌጥ ባይጠፋ ፣ ህይወቷ ምን ሊመስል ይችል እንደነበር ታልማለች።

ታዲያ ያች ውብ ወጣት ሴት በስራ ብዛት ምክንያት ያለእድሜዋ ገርጅፋ ወዟ መልኳ ጠፍቶ አስቀያሚ አሮጊት መስላለች።አንድ ቀን መንገድ ላይ ያች ሀብሉን ያዋሰቻትን ሴት ታገኛታለች።

አሁን ያለፈ ስለሆነ ስለ ሉሉ ወይም ስለ ጌጡ መጥፋት ልንገራት ትልና ሰላምታ ትሰጣታለች።ሀብታሟ ሴት ግን ልታውቃት አልቻለችም፦

"እኔ ማቲልዳ ነኝ"
"ውይ ምነው አረጀሽ?"
"ባንቺ ምክንያት ነው!"
"በኔ? እንዴት?"
"ታስታውሻለሽ ውድ ጌጥ አውሰሽኝ ነበር"
"አዎ"
"እና ጠፋብኝ"
"እንዴ መልሰሽልኛል እኮ"
"አዎ!ግን በምትኩ ሌላ በ17000 ፍራንክ ገዝቼ ነው የመለስኩልሽ"
ጓደኛዋ በጣም አዘነች።
"እኔ ያዋስኩሽ እኮ አርቴ ነበር,,,ዋጋውም 500 ፍራንክ አይሞላም!!!"😐

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

27 Jan, 07:39


አንድ Caps NFT በ 71 TON እየተሸጠ ነው ያለው የሚፈጠረው አይታወቅም 6ቀን ነው የቀረው

መጀመር የምትፈልጉ ➜
https://t.me/DurovCapsBot/caps?startapp=7682786416

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Jan, 14:38


መክብብ እንዳለው «ከእውቀትም ብዛት ትካዜ ይበዛል!» በዓለም የቱንም ያህል ከእውቀት እውቀትን ብጨምር "እውነትን" ግን አላክላትም። ምክንያቱም ፈጣሪዬን የሚያስክደኝ ጥበብ የመውደቂያዬ ከፍታ ነው!።

ስለመጣውም ስለሄደውም፣ ስለ መከራና ደስታ፣ ስለምኖረው ህይወት ብሎም ስለምሞተው ሞት ሁሉ አንደበቴ ፈጣሪዬን ታመሰግናለች።

ፈጣሪ ይመስገን 🙏🏼


SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Jan, 08:33


💎ከክፉ ትናንትህ ፊትህን አዙር!!
Let it go the past!

💡ሰው በዓለም እያለ በፈተና መኖሩ የታየና የተረጋገጠ እውነታ ነው፡፡ ማንም በሕይወት መንገዱ ላይ እንቅፋት አያጣውም፡፡ የሰው ልጅ በእድሜ መሰላል ወደ ላይ ሲወጣ፤ ወይ መጀመሪያው ላይ፣ ወይ መጨረሻው አካባቢ፤ አልያም ደግም መካከሉ የዕድሜ ዘመን ላይ አንሸራትቶት የሚፈጠፍጠው አዳላጭ አይጠፋውም፡፡ ድሃ ይሁን ሐብታም፤ ተራ ይሁን ባለስልጣን፤ ሊቅ ይሁን ደቂቅ፣ ብቸኛ ይሁን ባለብዙ ዘመድ ሕይወቱ የሚፈተንበት፣ ኑሮው የሚደናቀፍበት እክል አያጣም፡፡ ሰው ነዋ!

💡አንዳንዱ በማጣት ይፈተናል፤ አንዳንዱ በማግኘት ይፈተናል፤አንዳንዱ በጥጋብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በረሃብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በገንዘብ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በዕውቀቱ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በውበቱ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በሀዘን ይፈተናል፤ አንዳንዱ በደስታ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በጤናው ይፈተናል፤ አንዳንዱ በፍቅሩ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በዓመሉ ይፈተናል፤ አንዳንዱ በገዛ ልጁ ይፈተናል፡፡ ሰው ይፈተንበት ዘንድ የተሰጠው ፈተና ሺ ነው፡፡ እስትንፋሱ እስካለች ድረስ ፈተናው አያልቅም፡፡ ተረጋጋሁ ሲል የሚረበሽ፤ አረፍኩ ሲል እንከን የማያጣው ጥቂት አይደለም፡፡ ኑሮዬ ተስተካከለ፤ ሕይወት ሰመረልኝ፤ ጎጆዬ ሞቀ፤ ሁሉ ነገር አማረልኝ ሲል የሚበላሽበት፣ በብዙ የሚጎድል፤ ደስታውን ሳይጨርስ ሐዘን የሚገባው ዕድለቢስ ብዙ ነው፡፡ ሰው ነዋ!

ፕሮፌሰሩ ለተማሪዎቻቸው ምሳሌ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ አዘጋጁ፡፡ ብርጭቆውን አንስተው፡-‹‹የዚህ ብርጭቆ ውሃ ክብደቱ ምን ያሕል ነው?›› ብለው ጠየቁ፡፡ ተማሪዎቹም የራሳቸውን ግምት መመለስ ጀመሩ፡፡ አንዱ 8 ኦዝ ነው፤ ሌላኛው 12 ነው፤ ሌሎቹ 16፣ 10፣ 8፣ ወዘተ አሉ፡፡

🕯ፕሮፌሰሩ የመላሾቹን ተማሪዎች እጆች እየጨበጡ ለሁሉም አድናቆታቸውን ገለፁ፡፡ ጥያቄው ስለፊዚክስ አይደለም፡፡ ጥያቄው ክብደቱን የማወቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጥያቄው ዋናው ትኩረቱ ስለብርጭቆው ውሃ አልነበረም፡፡ ፕሮፌሰሩ የጥያቄውን ዋና ቁምነገር ማብራራት ጀመሩ፡-

‹‹ትክክለኛው የብርጭቆው ክብደት ትርጉም አያመጣም፡፡ ቁምነገሩ ያለው ብርጭቆውን ለምን ያህል ጊዜ ይዘነዋል የሚለው ላይ ነው››

በማለት የፍሬ ነገሩን ጭብጥ ተናገሩ፡፡

💎‹‹ለምሳሌ ይሄን ብርጭቆ ለጥቂት ደቂቃ ብቻ ብይዘው ክብደቱ ያን ያህል አይደለም፤ ነገር ግን ለሰዓታት ብይዘው ግን ክንዴ ይዝላል፤ እጆቼም ይደክማሉ፡፡ ለቀናት ብይዘው ደግሞ ክንዴ ሽባ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የብርጭቆው ውሃ ክብደት ባይለወጥም የምይዝበት ጊዜ ግን ብርጭቆውን ከባድም ሆነ ቀላል ያደርገዋል፡፡›› ሲሉ አስረዱ፡፡

ተማሪዎቹም በሃሳባቸው መስማማታቸውን ጭንቅላታቸውን በማወዘወዝ ገለፁ፡፡ ፕሮፌሰሩ ስለብርጭቆው ሚስጥር ገለፃቸውን ቀጠሉ፡፡

🔑‹‹ጭንቀትም ልክ እንደብርጭቆው ውሃ ነው፡፡ ጭንቀታችንን ለትንሽ ጊዜ ብቻ ከያዝነው ብዙ ችግር አይፈጥርም፡፡ የምንጨነቅበት ሰዓት እየረዘመ ሲመጣ ግን ጉዳት ያስከትላል፡፡ ጭንቀታችን ለቀናት፣ ለወራት አልፎ ተርፎ ለዓመታት ሲሆን ደግሞ በጣም ይጎዳናል፡፡ በጤናችን ላይ፣ በኑራችን ላይ፣ በአስተሳሰባችን ላይ ችግር ያመጣል፡፡ የማሰብ አቅማችን ሽባ ያደርጋል፡፡ አዲስ ሕይወት ለመጀመር የሚያስችል ብቃት እናጣለን፡፡ በአጠቃላይ አቅመ ቢስ እንሆናለን›› በማለት የብርጭቆውን ምሳሌ አብራሩ፡፡

በመጨረሻም ፕሮፌሰሩ የያዙትን ብርጭቆ ጠረጴዛቸው ላይ እያስቀመጡ፡-

‹‹ሁልጊዜም ቢሆን ብርጭቆውን ከመያዝ ይልቅ ማስቀመጣችሁን አትርሱ›› ... በማለት የዕለቱ ትምህርታቸውን ጨረሱ፡፡

💎እውነት ነው! ብዙዎቻችን በትናንት እየተብከነከንን፣ ባለፈው እየቆሰልን ዛሬን እንገድላለን፤ ነጋችንንም እናጨልማለን፡፡ አንዳንድ ክፉ ቀንን ‹‹ይሁን እንግዲህ ካመጣው›› ብሎ ማሳለፍ መልካም ነው፡፡ የመጣው ሊያስተምረን እንደሆነ ራሳችንን በማሳመን እንደመጣው ሁሉ እንዲሄድ ልንፈቅድለት ይገባል፡፡ አባቶቻችን ‹‹መተው ነገሬን ከተተው!›› የሚሉት ልንለውጥጠው የማንችለውን ነገር መተው ጭንቀትን ጠቅልሎ እንደመጣል ነው ማለታቸው ነው፡፡ ፈረንጆቹም ቢሆን የመጣባቸውን የህይወት ሳንካ የሚያሸንፉት ከችግሩ ጋር በመቋሰል ሳይሆን ‹‹Let it go›› በማለት ነው፡፡

💡ወዳጄ ሆይ... በራስህም ይሁን በሌላ ምክንያት የመጣብህን ፈተና ከቻልክ ለውጠው፡፡ ልትለውጠው ካልቻልክ ደግሞ ተቀበለውና ትምህርት ውሰድበት፡፡ የሆነውን መቀየር ባትችልም አንተ ግን ተለወጥ፡፡ ከክፉ ትናንትህ ፊትህን አዙር!! ያለፈውን ቁስልህን እየነካካህ ራስህን አታሳምም፡፡ ከትናንትህ ነፃ ውጣ፡፡ ይዘኸው የቆየኸውን የዘመን ሸክም ከጫንቃህ አውርድና ትከሻህን አሳርፍ፤ ራስህን ፍታ! ጭንቀትህን ጣልና የአዕምሮ ሠላምህን ተጎናፀፍ!!

የትናንትህን ጣጣ አስቀምጠህ ቆልፍበት እንጂ ተሸክመኸው አትዙር! (Always remember: put the glass down)

ነፃ ማንነት! አዲስ ሰውነት!

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Jan, 06:45


ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦

‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..›› ❤‍🩹

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Jan, 05:41


🐎 እንደ ፈረስ እሩጥ (Run like a horse🐴)

🪽 አንድ አትሌት በልምምድ ሰዓት በተደጋጋሚ ይደክመውና ሩጫውን ማጠናቀቂያው ጋር ሳይደርስ ያቆማል።

🪽 ከዛ ሚስቱ አንድ ምክር ሰጠቸው "እንደ ፈረስ 🐎 እሩጥ!"ስትል፤

🪽 "ምን ማለት ነው እንደ ፈረስ እሩጥ?" ስለመጨረሻው አታስብ አሁን ላይ ሆነህ (present) እሩጥ። ፈረስ ሲሮጥ የመጨረሻውን መዳረሻ እያሰበ አይደለም፤ የቻለውን ያህል ይጋልብ ይጋልብ እና ከአቅሙ በላይ ሲሆንና ሲደክመው ያቆማል።

🪽 አንተም እንደ ፈረሱ መጨረሻ ላይ መድረስ ሪከርዱን መበጠስ ሚለውን ትተህ አሁን ላይ አንድ እርምጃዋን ውሰድ ከዛም ሌላኛውን..

🪽 ይህ ምክር ለአትሌቶች ብቻ አይደለም፤ ለእኛም ይሆናል ብዙ ጊዜ ግባችን ላይ እናተኩርና ትልቅ ሆኖ ከባድ ሆኖ ሲታየን ተስፉ እንቆርጣለን፣ እናቆማለን።

🪽 ግን ትልቁ ግብ ላይ ማተኮር ትተን ወደ ግባችን ሚያደርሰንን ትንሹን ስራ ብንሰራ ግባችን ጋር መድረሳችን አይቀርም።🐴

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Jan, 03:11


Which Unlocks The World Secrets?¿😐

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

13 Jan, 17:01


ስኬትህ የሚወሰነው በሌላው ሳይሆን በአንተ አመለካከት ነው።

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

13 Jan, 14:48


⚠️ ማሳሰቢያ !!  ይድረስ ለቻናሉ አባላት በሙሉ

በአዲሱ የቴሌግራም ፖሊሲ መሠረት ይህን  ከታች unmute ሚለው ላይ የሚያደርጉ አባላት ቻናሉ ላይ እንደሌሉ ይቆጠራሉ ፡፡ ይህንን ማድረግ የሚፖሰቱትን መረጃዎች #VIEW ይቀንሰዋል።

ምንም እንኳን የምንፖስተውን እየተመለከቱ ቢሆንም ቻናሉ ላይ እንዳሉም አይቆጠርም ፤ ስለዚህ...

ከታች #MUTE የሚለው ላይ ከሆነ ምንም አይንኩት ነገር ግን

#UNMUTE ላይ ከሆነ 1 ግዜ በመንካት MUTE የሚለው ላይ አድርጉት

🙏 ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን 🙏

✌️ Share & React 🤞❤️

sʜᴀʀᴇ @ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

13 Jan, 06:59


=>ስህተትን ከተረዱ በኃላ መመለስ
ተሳስቼ ነበር ለማለትም አለመግደርደር

=>በችግር ግዜ ተስፋ አለመቁረጥ
በሀዘንም ግዜ አለመደንገጥና
እራስን መቆጣጠር

=>የተጣሉትን ወዳጅ ሚስጥር አለማባከን
መልካም ውለታውንም አለመርሳት

=>ሳይመች ተለማማጭ ሲመች ተሳዳቢ አለመሆን ነው!

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

13 Jan, 04:31


Bruce lee የተባለው ታዋቂው የሆሊውድ አክተር በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር..

"የምትጓዝበት መንገድ ወደ ጥሩ አሊያም ወደ መጥፎ የሚመራው አንተን እንጂ ተመልካችህን አይደለም...
የምትለብሠው ልብስ የሚያሞቀውም ሆነ የሚያበርደው አንተኑ እንጂ የሚያይህን አይደለም...
የምትበላው ምግብ የሚጣፍጠው ወይም የሚመረው አንተን እንጂ ሌላውን አይደለም።

እናም አንድን ነገር ለታይታ ማድረግ ሞኞች የፈለሠፉት የመከበር ሙከራ መሆኑን ተረድተህ" በቀጥተኛው መንገድ ለመጓዝ ሞክር...

እንማር

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

11 Jan, 15:56


አሳ አጥማጆች ሁልጊዜ ላይቀናቸው ይችላል አይደል?

👇🏾

አሳ አጥማጆች ማእበል ሲያስቸግራቸው: አሳዎች የሚፈልግ ቦታ ላይ ሳይመጡላቸው: ንፋስ ሆኖ በቂ የሆነ ቀዘፋ ማድረግ ሳይችሉ ሌሎች ተግባራቶች አሏቸው

ከማእበል እና ንፋስ ጋር ታግለው ለማጥመድ አይጋጋጡም
.
ሁኔታውን እያወቁት "አሳ ካልያዝኩኝ ሞቼ እገኛለሁ" ብለው መረባቸውን አይጥሉም
.
አሳ መያዝ አልቻልኩም ብለው አይቆዝሙም

👇🏾

ባህሩ እስኪሰክን እና ንፋሱ ገለል እስኪል ድረስ ሌሎች ስራዎችን ይከውናሉ

መረባቸውን ያጠናክራሉ: ይጠግናሉ: ይሰፋሉ
.
ጀልባቸውን ያጠባብቃሉ: ቀዳዳዎችን ይደፍናሉ
.
ማእበሉ ሲበርድ እና አሳዎች ሲገኙ ለማጥመድ ይዘጋጃሉ

……………….

አንዳንድ ጊዜ አለ አይደል?🤔

👇🏾

ቁጭ ማለት የሚገባን: ነገሮች የማይሆኑበት
.
ያሰብነው የማይሳካበት: ብንታገልም ድካም የሆነበት

አሳ አጥማጁን መሆን !!!

❤️🙌🏼

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Jan, 18:38


ታሪካችሁ ሲነገር እንዲህ እንዲባል አድርጉ እንዳቃታቸው እንዳልተሳካላቸው እንደወደቁ እንዳለቀሱ ሰዎች እንደተሳለቁባችው አልቀሩም ሁሉንም በድል አሸንፈዋል!💪👏👏👏

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Jan, 15:53


በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው

አህያው ዛፍ ስር ታስሮ ነበር። በአጋጣሚ ሰይጣን መጣና አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ለቀቀው። አህያውም ወደ ማሳው እየሮጠ ገብቶ ሰብሉን ማውደም ጀመረ።

ይህን ያየችው የገበሬው ሚስት አህያውን በጥይት መታችው። የአህያው ባልተቤት ተበሳጨና የገበሬውን ሚስት ገደላት። ገበሬው መጣና ሲያይ ሚስቱ ሙታለች። ወዲያው አጸፋውን መለሰና የአህያው*ን ባለቤት ተኩሶ ገደለ*ው።

የአህያው ባልተቤት ሚስት ልጆቿን ጠራችና የገበሬውን ቤት እንዲያቃጥሉ አዘዘቻቸው። ልጆቹም አመሻሹ ላይ እናታቸው ያዘዘቻቸውን ለመፈጸም ገበሬውም በውስጥ ሲቃጠል እያሰቡ በደስታ ሄዱ። ወዲያውም ቤቱን አቃጥለው ተመለሱ። እንዳጋጣሚ በሚያሳዝን ሁኔታ ገበሬው እቤት አልነበረምና ተመልሶ መጥቶ የአህያ*ውን ባልተቤት ሚስትና ልጆቹን ገድሎ ተመለሰ።

ሲመለስ ግን ሰይጣንን መንገድ ላይ ያገኘዋል። ገበሬው ትንሺ ሰከን ሲል የሆነውን አስታውሶ ነበርና ሰይጣንን ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቀዋል? ሰይጣንም እንዲህ አለ፦ እኔ ምንም አልሰራሁም። አህያው*ን ብቻ ነው የፈታሁት። ግን ሁላችሁም የውስጣችሁን ሰይጣን ፈታችሁት። ሁሉንም ነገር ያደረጋችሁት እራሳችሁ ናችሁ።

ሌላ ጊዜ ለምንም ነገር ምላሺ ከመስጠታችን ፣ ውሳኔወችን ከማሳለፋችን በፊት ለአፍታ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል። ብዙጊዜ ሰይጣን የሚያደርገው ውስጣችን ያለውን አህያ መልቀቅ ነው። "በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው!"


SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Jan, 08:27


“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
  — ሉቃስ 2፥11


እንኳን ለጌታችን እና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሰላም አደረሰን

🙏በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን🙏

መልካም በዓል❤️

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Dec, 09:12


አንድ የቤተክርስቲያን ሰባኪ ለረዥም ሰዓት በመንበርከክ ወደ ፈጣሪ ሲፀልይ ከቆየ በኋላ ፈጣሪውን በድንገት እንዲህ ሲል ጠየቀው፡- "አምላክ ሆይ! በእንተ ዘንድ አንድ ሚሊዮን ዓመት ስንት ይሆን?"
ፈጣሪም መለሰ "አንድ ሴኮንድ፡፡"
በቀጣዩ ቀን ይህ ሰባኪ በተመሳሳይ እየፀለየ አሁንም ፈጣሪውን ሌላ ጥያቄ ጠየቀው፡·
"አምላክ ሆይ! በአንተ ዘንድ አስር ሚሊዮን ዶላር ስንት ይሆን?"
ፈጣሪም መለሰ "አንድ ሳንቲም።"
በዚህ ጊዜ ሰባኪው "እንግዲያውስ አምላክ ሆይ አንዲት ሳንቲም ብቻ ልትስጠኝ ትችላለህ?"
ፈጣሪም መለሰ፡- "አንዲት ሴኮንድ ብቻ ታገሰኝ!"

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

07 Dec, 04:40


በአንድ ወቅት አንድ ወጣት ሶቅራጥስን ስኬት ምስጢር ምን እንደሆን እንዲነግረው ጠየቀው ሶቅራጥስ ከወጣቱ ጋር በነጋታው ጠዋት ከወንዙ ዳርቻ ስመገናኘት ቀጠሮ ያዘ በነጋታው ሁለቱም እየተራመዱ ወደ ወንዙ ገቡ።ውሀው አንገታቸው ላይ ሲደርስ በድንገት ሶቅራጥስ ልጁን  ውሀው ውስጥ ደፈቀው።ልጁ ለመውጣት ቢታገልም ጉልበት ከሶቅራጥስ ጋር ሊመጣጠን ስላልቻለ ጥረቱ አልተሳካስትም በመጨረሻ የወጣቱ ፊት ወደ ሰማያዊነት መቀየር ሲጀምር ለቀቀው ልጁ አየር ስቦ ከተረጋጋ በኋላ ሶቅራጥስ ጥያቄውን አቀረበለት። ለመሆኑ ውሀው ውስጥ ሳለህ ከምንም ነገር  በላይ አስፈስጎህ የነበረው ነገር ምንድነው? ልጁም ሳያመነታ አየር ሲል መለሰለት የስኬትም ሚስጢር ይህ ነው። ....የስኬትም ሚስጥር ይህ ነው ልክ አየር የፈለግከውን ያህል ስኬትንም ፈልገውና ታገኘዋለህ።ሌላ ምስጢር የለውም አለው ሶቅራጥስ። ትክክል ብሏል ሌላ ምንም ምስጢር የለውም።
ክልብ መሻት የውጤታማ ጉዞ ዋነኛ መነሻ ነጥብ ነው፡፡ በፍንጣሪ እሳት በቂ ሙቀት ማግኘት እንደማይቻል ሁሉ ደካማ ፍላጐትም ታላቅ ውጤት ሊያስገኝ አይችልም።

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

06 Dec, 18:25


"በህይወትህ የተደረገልህንና የተደረገብህን እንዳትረሳ ሁለቱን የረሳክ ቀን ግን እንደሞትክ ቁጠረው"

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

05 Dec, 18:28


#ልጅ ፡ አባቴ  ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?

#አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ

#ልጅ ፡ እንዴት ?

#አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ  ጊዜ ግን እንዲገኝ  ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤ እንደጨውም ሁን ለሁሉም  ምግብ  ቢፈለግም በቀላሉ  ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ  አይደለምና ፤

ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ  ይመጣል  እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።

#ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው  የለም ?

#አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ  አትሁን
#ልጅ ፡ እንዴት  ?

#አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን  የሌሎች ብዙ ቀዳዳ  እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ  መቋሚያም አትሁን  ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ  ግን መቆም  አይችልምና ፤
...............

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

05 Dec, 08:10


"There is a human organ that can regenerate itself, no matter how much damage it takes." are you curious?
😱😱😱😱
"ምንም ያህል ጉዳት ቢደርስበት ራሱን የሚያድስ የሰውነት አካል አለ።" የማወቅ ጉጉት አሎት?

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

04 Dec, 04:07


ትልቁ ድላችን ምንም ውድቀት ያላጋጠመው ሳይሆን በወደቅን ቁጥር የተነሳንበት ነው ።

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

03 Dec, 04:18


#እንደ_ውኃ_ጠቃሚ_እንደ_ወርቅ_ውድ_እንሁን!

እዚህ ዓለም ላይ እጅግ ጠቃሚው ነገር ውኃ ነው። ርካሹም ግን ውኃ ነው።
ለሰዎች ብዙም የማይጠቅመው ወርቅ ደግሞ ውድ ነው።

ውኃ ርካሽ የሆነው የትም ስለሚገኝ፣ ወርቅ የተወደደው ደግሞ በቀላሉ ስለማይገኝ ነው።

ስለዚህ ወዳጄ ሆይ እንደ ውኃ ጠቃሚ ግን ደግሞ እንደ ወርቅ ውድ እንሁን።

#ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ ❤️

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

02 Dec, 04:03


"ችግሮች የህይወት አካል ናቸው በፈገግታ መታገል ደሞ የሕይወት ጥበብ ነው"

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

01 Dec, 18:35


የአቀባበል ስነ-ስርአቱ ፡ ምን መምሰል እንዳለበት ፡ ጊዜ ወስዶ የመከረው የአሜሪካ መንግስት ዝግጅቱን አጠናቆ
በኦክቶበር 1 - 1963 የሀገረ ኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ፡ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዋሽንግተን ሲደርሱ ፡ በወቅቱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት JF ኬኔዲ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
.....
ከዛም ንጉሱ ከአሜሪካን ፕሬዝደንት ጋር በመሆን በግልፅ መኪና ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ሲጓዙ ፡ በተጓዙበት ጎዳና ላይ ሁሉ ህዝቡ ግራና ቀኝ ግልብጥ ብሎ በመውጣት በዚህ መልኩ እያጨበጨበ ተቀበላቸው ።
....
እና ....
በወቅቱ በአሜሪካን ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የነበረን ክብር ይህን ይመስል እንደነበር ሲታሰብ ያስቆጫል

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Nov, 19:53


ይህን አሳዛኝ የእናትነት መስዋዕትነት ምልክትና ተምሳሌት የሆነውን ፎቶ ያነሳው ደቡብ አፍሪካዊ ፎቶግራፈር ማርክ ደምብልተን ነው።

እናት አንበሳ ልጇን ከአዳኞች እንስሳት ለማዳን ስትል ሞት ቀረሽ ፍልሚያ አድርጋለች ።

ልጇን ለማዳን ባደረገችው ትግል አድና ለመብላት የምትጠቀምበትን አንዱን የፊት ጥርሷን አጥታለች፤ ቤተሰቦን በአደን ለምትመግብ አንበሳ የአንድ የፊት ጥርስን ማጣት ምን ያህል እንደሚጎዳ አስቡት።

እናት አንበሳ ልጇን ለማዳን ስትል ከሌሎች እንስሳት ጋር ከፍተኛ ፍልምያ አድርጋ ጥርሷን አጥታ ፊቷ ደም በደም ሆኖ በድል አድራጊነት ስሜት ልጇን በአፎ ይዛ ትታያለች።

ትንሹ አንበሳ ግን እናቱ እሱን ለማዳን ስትል የከፈለቸውን መስዋዕትነት ያወቀና የተረዳ አይመስልም።

ይህ ሁሉ መሰዋእትነት የተከፈለለት አንበሳ ነገ ሲያድግ መንጋውን በጀግንነት ከጠላት እንደሚመክትና እንደሚጠበቅ ተስፋ ይደረግበታል።

እናት

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Nov, 19:31


ትላንት ነበር አለፈ ... 🙄
ቃል ነበር ታጠፈ ...🫢
ልብ ነበር ተሰበረ ...💔
ሰው ነበር ተቀየረ ...😎

ህይወት ግን ይቀጥላል ወዳጄ ...🧍‍♀🧍🧍‍♂

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Nov, 19:01


ለዘላለም ኑሪልኝ በሏት እናታቹን

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Nov, 06:59


የዩናይትድ ኪንግደም ፡ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት፡ ዊንስተን ቸርችል እንዲህ ብሎ ነበር.

"አንድ ቀን ወደ ቢቢሲ ቢሮ ፡ ለቃለ መጠይቅ ፡ ለመሄድ ታክሲ ያዝኩኝ፤ ቢሮዉ እንደደረስኩ፡  ባለታክሲውን ቃለ- መጠይቁን ጨርሸ ፡ እስክመለስ ለ40 ደቂቃ ያህል እንዲጠብቀኝ ጠየቅኩት።

ባለ ታክሲዉም ይቅርታን በማስቀደም "አልችልም ፡ ምክንያቱም እቤቴ ሂጄ ከደቂቃዎች በኋላ ፡ ዊንስተን ቸርችል የሚያደርገዉን ቃለመጠይቅ መስማት እፈልጋለሁ።"አለኝ

የእኔን ንግግር ለመስማት ይህን ያህል በመጓጓቱ በጣም ተደነቅሁ፤ ኩራት ቢጤም ተሰማኝ።ማንነቴን ሳልገልፅለት ለታክሲ አገልግሎቱ መክፈል ከሚጠበቅብኝ በላይ መልሱ ስላስደሰተኝ 10 ፓዉንድ ሰጠሁት
ባለ ታክሲዉም የሰጠሁት ብር በደስታ አየቆጠረ "ጌታዬ እስከ ምትፈልገዉ ስዓት ድረስ እጠብቅሃለሁ፡ ሲፈልግ ዊንስተን ቸርችል ገደል  መግባት ይችላል!"ብሎኝ አረፈ.፡፡

SHARE|||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

16 Nov, 18:47


ማይክ ታይሰን ለእኔ ቦክሰኛ አይደለም!
(አሌክስ አብርሃም)

ከህይወት ቡጢ ለማምለጥ ሲሮጥ ያቀረቡለት የቦክስ ጓንት ውስጥ የወደቀ ሚስኪን ወፍ ነው። እንደብዙ ጥቁር አሜሪካዊያን ገና በልጅነቱ ብዙ መከራ ተቀብሏል። አባቱን በእርግኝነት አያውቅም ነበር። አንድ ጀማይካዊ የታክሲ ሹፌር ነው ይባላል።ይሁንና እሱ አባቴ ብሎ የሚያስበው /የተነገረው/  ሴቶችን ለሴተኛ አዳሪነት የሚያቀርብ ሰካራምና ዱርየ ሰው ነበር። ያም ሆነ ይህ ከንቱ ነበሩ።  የሆነ ሁኖ የአባት ፍቅርም ይሁን ከለላ ሳይኖረው እናቱ ጋር መጠጥ አደንዛዥ እፅ ፣ወሲብና ወንጀል  በተሞላ በዘግናኝ ሰፈር ውስጥ ለመኖር የተገደደ ሚስኪን ህፃን ነበር። የባሰው አሳዛኝ ነገር እናቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ሴት መሆኗሲሆን  የምታሳድጋቸው  በዚሁ ስራ ነበር። ማይክ እናቱ በመጠጥና ድራግ በናወዙ ሰካራሞች እናቱ ላይ ብዙ ግፍ ሲፈፀም አይቷል።

በቤተሰቤ እንደተሳቀኩ ነው የኖርኩት ይላል በሀዘን።ብዙዎቹ  የተገፉ ህፃናት ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፣ ከሰው ያጡትን ፍቅር ከአሻንጉሊት፣ ከቤት እንስሳት ወይም በሃሳባቸው ከሚፈጥሩት ታሪክ  ለማግኘት ይጥራሉ. . .ማይክ ታይሰን ርግብ ነበረችው የሚወዳት ! አንድ የሰፈር ጉልበተኛ እርግቡን ገደለበት  . . .የማይክ ታይሰን የታፈነ ብሶት ለመጀመሪያ ጊዜ ቡጢ ሁኖ የተገለጠው እዚህ እድለቢስ ወጣት ላይ ነበር ይላሉ ታሪኩን የፃፉ! ከዛማ ምኑ ቅጡ ማይክ ከአንደበቱ ቡጢው የሚፈጥን የለየለት ተደባዳቢ የጎዳና ልጅ ሆነ። እስርቤትና ፖሊስ፣ ክስና መታሰር. . .!

በመሰረቱ ይሄ ባህሪው በዛ መንደር መሞቻው ነበር! ግን አንድ ጣሊያናዊ የቡጢ አሰልጣኝ ዓይን አረፈበት! የማይክን የጎዳና ቡጢ ከሞት ወደህይዎት፣ ከእስር ቤት ወደቦክስ ሪንግ አመጣው! እነዛን ቁጡና በብሶት የተሞረዱ የማይክን ሰንጢ ጥፍሮች በጓንት ሸፍኖ ስፖርት አደረጋቸው። ደም ሳይሆን ዝናና ገንዘብ አፈሰሱ። የምታዩት ማይክ ታይሰን ተፈጠረ። ስሙ በዓለም ናኘ። ግን ምን ዋጋ አለው ገና በ20 ዓመቱ የአለምን የከባድ ሚዛን የቦክስ ሻንፒየን የተቆጣጠረው ማይክ የገንዘብ ጎርፍ አጥለቀለቀው፣ የልጅነቱን ስነልቦናዊ ህመም ፣ብቸኝነትና የውስጡን ረብሻ  የማያክም ገንዘብ። በ16 አመቱ በካንሰር ለሞተች እናቱ ያልደረሰ ገንዘብ ። እንደጉድ ብሩን ረጨው፣ ባለፈ ባገደመበት ሴት ነው፣ መጠጥ ነው፣ ድራግ ነው። ውድ መኪና ቅንጡ ቤት ... ከተራ ሰው እስከፖሊስ በውሃ ቀጠነ እየደበደበ ቅጣት ነው። ባዶውን ቀረ።

ይታያችሁ ፎርብስ አንድ ጊዜ የማይክን ሃብት 685 ሚሊየን ዶላር ገምቶት ነበር።  ዛሬስ? ከየኪሱ የቀሩትን ሳንቲሞች ጭምር ቆጣጥሮ የቀረው ሀብት 10 ሚሊየን ብር ቢሆን ነው።  ተራ በሚባሉ ፊልሞች ሳይቀር ተራ ገፀ ባህሪ ወክሎ  አሰሩኝ እያለ እስከመለመን ደርሶ ነበር። ማይክ ታይሰን ብዙዎች እንደሚያስቡት የሚንጎማለል አንበሳ ፣ ከአለት የጠነከረ የቡጢ ንጉስ አይደለም። ቤተሰብ እና ማህበረሰብ እንዲሁም ዘረኝነት የፈጠረው ጠባሳ ለዚህ ያበቃው የቦክስ ጓንት ውስጥ ጎጆውን የሰራ ሚስኪን ወፍ ነው። የልጅነት አዕምሮ ላይ የቆመ ጠባሳ በተጠቂው ቡጢ አይጣልም። ልጆች ላይ የሚሰነዘርን የህይወትን ቡጢ፣ የስነልቦና ፍላፃ  ይከላከል ዘንድ የተፈጠረ ጋሻ  ወላጅ ይባላል። ወላጅ ናችሁ? እንግዲያውስ ለልጆቻችሁ ህያው አጥር ሁኑ
!

ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

16 Nov, 17:28


ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር እንዲኖርህ ከፈለክ......


SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Nov, 17:44


እንዴት አመሻችሁ የኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ ቤተሰብ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ በዚህ ቻናል ዙሪያ

በዚህ ቻናል ላይ ምን ቢጨመር ምን ቢቀነስ መልካም ነው ብለው ያሰቡትን ሀሳብ በ comment ስር ይግለጹልን🙏 የእናንተ ሀሳብ ለኛ እጅጉን ስለሚጠቅመን ሃሳባችሁን በቅንነት እንድትገልፁልን በትህትና እንጠይቃለን

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

14 Nov, 03:43


እንኳን በሕይወት ነቃችሁ!

በሰላም ስላደራችሁ ደስ ይበላችሁ!

በዓለም ላይ በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ አይሮፕላኖች እየተነሱ በሰላም ያሰቡበት በመድረስ ያርፋሉ፡፡ ከእነዚህ በረራዎች መካከል ግን የአንዱም እንኳን በሰላም መግባት በዜናዎች ላይ ሲነገር አንሰማም፡፡ ሆኖም፣ አንድ በረራ ላይ አደጋ ከደረሰ ግን ትኩረት ይስባል፣ ዜናውን ይሞላዋል፣ ወሬው ይሸጣል፡፡  

የአንድ ጤናማ ሰው ልብም ቢሆን በቀን ወደ አንድ መቶ ሺህ (100 ሺህ) አካባቢ ይመታል፡፡ ይህንን ያህል ጠንክሮ የሚሰራው አካላችን ግን በቀን ውስጥ ትዝም አይለን፡፡ የምናስታውሰው መምታት ለማቆም ሲዳዳውና የምቱ ድግግሞሽ ሲለይብን ነው፡፡ ለምን? መልካሙ ነገር ተለምዷል፡፡ የምስራች የሆነው ነገር ትዝም አይለን፡፡ 

ዛሬ መልካም መልካሙን ላስታውሳችሁ፡፡ ዛሬ የምስራቹ ትዝ ይበላችሁ፡፡ በሰላም የመንቃታችሁ ጉዳይ፣ በሌሎች ላይ የደረሰ እናንተ ላይ ያለመድረሱ ጉዳይ፣ የደረሰባችሁ ነገር ከዚህ የከፋ ያለመሆኑ ጉዳይ . . . ትዝ ይበላችሁ፡፡

ከደረሰብን ክፉ ነገር የሆነልን መልካም ነገር ይበዛልና ደስ ይበላችሁ፡፡

ፈጣሪን አመስግኑ! ቤተሰቦቻችሁን፣ ጓደኞቻችሁንና በሕይወታችሁ ላይ መልካም ተጽእኖ ያደረጉ ሰዎችን አድንቁ!

መልካም ቀን!

ከወደዱት ይህን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ ይላኩ።

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

13 Nov, 04:29


🤔እረስቼዋለሁ

#አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።

ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....

"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!

ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡

እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።

ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።

አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡

ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።

ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።

አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።

አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤

"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...

"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...

"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡

እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!

እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!

ሰው እንጂ ፈጣሪ ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።

ፈጣሪ ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!

ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪ እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!

 "ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!🙏


#LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት


ውብ ቀን ተመኘሁ🙏

SHARE @ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

10 Nov, 19:40


እነዚህ መድሀኒቶች የተከፈለባቸው ናቸው: መድሃኒት የሆኑ ሰዎች ቅን ልቦና ከፍለውባቸዋል

👇🏾

መድሃኒት ቤቱ የሚገኘው ሳር ቤት ነው

የመድሃኒት ቤቱ ስም ሃልተን ፋርማሲ ይባላል

እነዚህ የምታይዋቸው ደረሰኞች የተከፈለባቸው ናቸው: ቅን ልቦና ያላቸው ሰዎች የከፈሉት

መድኃኒት ለመግዛት አቅም ያነሳችው ሰዎች እዚህ ፋርማሲ ሄደው እነዚህን የተከፈለባቸው ደረሰኞችን በመጠቀም መድሃኒት መውሰድ ይችላሉ

👇🏾

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው
!!!

❤️🙌🏼

SHARE||¶@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

31 Oct, 16:03


ህይወት እንደ....

@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

31 Oct, 08:06


ቀጣዮ DOGS የሆነውን PAWS ያልጀመራቹ እና ጀምራቹ ደሞ በ MULTI ማሰሩ ሰዎች ምን ሆናቹ ነው ?

PAWS ለመጀመር  ግዜ የላችሁም ቶሎ ነው ሚጠናቀቀው እየተባለ ነው እናም በባይናስ ሊስት መደረጉ ማይቀር ነው👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=YZ2gibPg

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Oct, 17:00


ቀጣዮ DOGS የሆነውን PAWS ያልጀመራቹ እና ጀምራቹ ደሞ በ MULTI ማሰሩ ሰዎች ምን ሆናቹ ነው ?

PAWS ለመጀመር  ግዜ የላችሁም ቶሎ ነው ሚጠናቀቀው እየተባለ ነው እናም በባይናስ ሊስት መደረጉ ማይቀር ነው👇

https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=TG8iM8WH

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

30 Oct, 16:14


እንዴት ማዳመጥ እንዳለብህ.....


SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

29 Oct, 04:29


ሊጠናቀቅ 1 ቀን ነው የቀረው ያልጀመራችሁ task በመስራት eligible መሆን ትችላላችሁ አሁኑኑ ጀምሩት ብዙ ሰው ስላልሰራው ደህና ይከፍላል።

https://t.me/csprfans_bot/csprfans?startapp=668431847

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

27 Oct, 18:41


የስኬት ቀመር ልሰጥህ አልችልም ነገር ግን የውድቀት ቀመር ልሰጥህ እችላለሁ፡ ማለትም፡ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት ሞክር።

© Herbert Swope

SHARE||@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

25 Oct, 19:20


በምስሉ ላይ የምትመለከቱት Ricky Jackson ይባላል። Cleveland, Ohio ነዋሪ ሲሆን ገና በ18 አመቱ በለጋ እድሜው ባልሰራው ወንጀል የሞት ፍርድ ተፈርዶበት 39 አመት ከታሰረ በኋላ (አብዛኛውን ግዜ የሞት ፍርድ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር ካላፀደቁት ወደ እድሜ ልክ ይለወጣል)፣  ትክክለኛው ወንጀል ፈጻሚ በመገኘቱ ዳጎስ ያለ ካሳ ተከፍሎት በነፃ የተለቀቀ ሰው ነው።

እናም ልክ  ከእስር ቤት ተለቆ ሲወጣ ያሳሰረውን ሰው አገኘውና  ... «ይቅር ብዬሃለው» .... ብሎ አቀፈው።

ቃለ መጠይቅ ላደረጉለት ጋዜጠኞች ደግሞ እንዲ ሲል ተናገረ :-

....«እስር ቤት ውስጥ ነህ ማለት እስረኛ ነህ ማለት አይደለም»....

ነጻነት ያለው ያላችሁበት ስፍራ ላይ ሳይሆን አይምሯቹ ውስጥ ነው። የቂምና የጥላቻ እስረኛ እንዳትሆኑ ይቅር በሉ!!
ይቅር በሉ፣ መራመድ አታቁሙ ፣ ጉዳታችሁ ላይ አትቆዩ! ህይወት ሰፊና ፣ ብዙ ደርዝ ያላት የጉዞ ሃዲድ ናት!!

ይቅርታ ለራስ የሚሰጥ ድንቅ ስጦታ ነው ሰው ይቅር ማለት ሲጀምር ህይወት ይጀምራል።

የበደለንን ይቅር ማለት መሸነፍ ሣይሆን ፍቅርን ማስተማር ፣ ቀንነትን መዝራት ፣ ህይወትን ማደስ ነው።

SHARE"@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

22 Oct, 18:51


#ሁሉም_ለበጎ_ነው !

አንድ ሰው ባህር ላይ ብቻውን እየተጓዘ እያለ፤ በማዕበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩ ውሰጥ ይሰምጣል። ሰውዬው እንደምንም ራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፋል። ከዛም ደሴቷ ላይ ጎጆ ነገር ይሰራና ለብቻው ዓሳ እያጠመደና እየተመገበ ብዙ ቆየ።

አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ ሲሄድ፤ በመሀል ጭስ ይሸተዋል። ዞር ብሎ ሲመለከት፤ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነበር። እየሮጠ ቢመለስም ጎጆውን ሊያድናት አልቻለም። ለካስ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ኖሮ ጎጆውን አንድዶታል። ሰውየውም:- "እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለከኝና ከቤተሰቦቼ ነጥለክኝ ስታበቃ፤ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ?!" ብሎ ፈጣሪውን አማረረ!

ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምጽ ሲሰማ፤ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ ሲያይ ተደሰተ። የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት። ከዚያም ለሰዎቹም:- "እዚህ አካባቢ (ባህር) ላይ ማንም አይመጣም። እናንተ እንዴት አገኛችሁኝ?" ብሎ ጠየቃቸው። መርከበኞቹም:- "እኛ እየተጓዝን ነበር። ጭስ ስናይ ሰው ይኖራል ብለን ስንመጣ፤ አንተን አገኘንክ!" አሉት። "አቤት ጌታዬ! ለካ ከዚህ ስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ኖሯል፤ ትንሿን ጎጆዬን አፍርሰክ ወደ ትልቁ ቤቴ የወሰድከኝ!" አለ።

አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ (ሲበላሽብን)፤ ፈጣሪንም፣ ሰውንም እናማርራለን። ነገርግን ካጣነውና ከጎደለብን ነገር ጀርባ፤ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን። በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን ጌታችንን እንረሳለን። ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን። ጌታችን! አዕምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን!

መልእክቱ  አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌𝙡𝙞𝙠𝙚 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 እያደረጋችሁ አበረታቱን።    

          SHARE @ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

20 Oct, 03:59


🌗የሁላችንም ጥንካሬ ያለው በተመቻቸው ስፍራ ሳይሆን ሁኔታዎች ፈር ሲለቁ ጨለማ ሲከበንና ሕይወት መውጫ የሌላት መስላ ስታስጨንቀን በምንወስነው ውሳኔ ውስጥ ነው።

የማንነታችን ትርጉም የሚለካው ነን ብለን የምናስበው ማንነታችን ፈተና ሲገጥመው በምንወስደው እርምጃ ነው። እራሳችንን የፍቅር ጥግ አርገን የምናይ ከሆነ የፍቅር ጥግ መሆናችንን የሚረጋገጠው ጥላቻ ግድ የሚሆንበት ቦታ ላይ የፍቅርን ፀዳል መልቀቅ ስንችል ነው።


የይቅርታ ሰው መሆናችን የሚታወቀው ይቅርታ ለማድረግ በሚያስቸግርበት ሁኔታ ላይ ይቅር ማለት ስንችል ነው።

                       ~ ኦሾ

@ethio_tksa_tks
ቻናላችንን ሼር በማድረግ ይተባበሩን..!😊

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

19 Oct, 16:27


°•3 የህይወት ደረጃዎች;

   #የጉርምስና ዕድሜ;
         ጊዜ + ጉልበት .... ግን ገንዘብ የለም.
   #የስራ ዘመን፡-
          ገንዘብ + ጉልበት ... ግን ጊዜ የለም.
   #የዕድሜ መግፋት:
      ጊዜ + ገንዘብ ... ግን ጉልበት የለም.

ህይወት ማለት ምን ማለት እችላለሁ ...... °
          @ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

19 Oct, 10:32


ይህ ከጀርመን ጎዳናዎች አንዱ ነው

👇🏾

ሰዎች ለድሆች እና በልተው ማደር ላቃታቸው ችግረኞች ምግብ በፌስታል አምጥተው ያንጠለጥላሉ

ቦታው ላይ ምንም አይነት ይህንን የሚገልጽ ማስታወቂያ የለም: ካሜራም አልተገጠመም: ምግቡን ሲያስቀምጡ እና ችግረኞችም ምግቡን ሲወስዱ አብረን ፎቶ ካልተነሳን የሚላቸው የለም: ሲመገቡ ቪዲዮ እየቀረፀ የሚያጎርሳቸው የለም

ምግቡ: ፌስታሉ እና ችግረኞቹ ብቻ ነው የሚተዋወቁት

👇🏾

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው!!

❤️🙌🏼


@ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

18 Oct, 18:55


#የእንጨት_ቆራጩ_ታሪክ
በአንድ ወቅት በጣም ጠንካራ እንጨት ቆራጭ ወደ አንድ  እንጨት ነጋዴ በመሄድ ስራ እንዲሰጠው ጠየቀ ነጋዴውም ፈቀደለት ። ክፍያውም የስራ ሁኔታውም ጥሩ ስለነበረ እንጨት ቆራጩም ያገኘውን እድል ላለማጣት የተቻለውን ሁሉ ለማረግ በርትቶ ለመስራት ወሰነ ...

አለቃውም መጥረቢያውንና የሚሰራበትን ቦታ አሳየው።
እንጨት ቆራጩ በመጀመሪያው ቀን 18 ዛፎችን አመጣ...አለቃውም ተደስቶ እንኳን ደስ አለህ አለው አክሎም በዚሁ መንገድ ቀጥል አለው ..በአለቃው ቃላት እጅጉን ተነሳስቶ በቀጣዩ ቀን የበለጠ ለማምጣት ሞከረ ግን 15 ዛፎች  ብቻ ማምጣት ቻለ ...በሶስተኛው ቀን የበለጠ ሞከረ ሆኖም ከ 10 ዛፎች በላይ ማምጣት አልቻለም ከቀን ወደቀን ቁጥሩ እየቀነሰ መጣ....
እንጨት ቆራጩም እያሰበ እራሱን ጠየቀ እኔ ጥንካሬዬን እያጣሁ መሆን አለበት ..? አለቃው ፊት መቅረብ እየፈራ ለአለቃውም እንዲ ሲል አስረዳ ምን እየሆነ እንደሆነ አላውቅም ብሎ  ይቅርታ ጠየቀ...አለቃውም መልሶ ...#ለመጨረሻ ግዜ መጥረቢያህን ያሳልከው  መቼ ነው ሲል ጠየቀው እሱም ..ብዙ ዛፎችን በመቁረጥ ሀሳብ ስለተጠመድኩ መጥረቢያዬን ለመሳል  ግዜ አልነበረኝም ሲል መለሰ ...
የኛም የእለት ተእለት ህይወታችን እንዲሁ ነው  በሌላ ስራ ተጠምደን መጥረቢያውን ለመሳል ግዜ አንሰጥም ...አሁን ባለንበት ዘመናዊ በሚባለው አለም ሁላችንም ከመቼውም በበለጠ በብዙ ተወጥረናል busy ነን ግን ያነሰ ደስታ ነው ያለን።

ለምን ይሆን?
ሁላችንም ለመዝናናት ፣ ለማሰብ ለማሰላሰል ፣ ለመማር እና ለማደግ ጊዜ ያስፈልገናል። “#መጥረቢያውን” ለመሳል ጊዜ ካልወሰድን አሰልቺ የሆነ የኑሮ ድግግሞሽና ውጤታማነታችንን በግዜ ሂደት እያጣንው እንሄዳለን ።


𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 @ethio_tksa_tks

ኢትዮ ጥቅሳ ጥቅስ

17 Oct, 17:47


ይሄ Project  እስከ December 4  ወይም ለ1 ወር 18 ቀን ብቻ ነው ሚቆየው የ 5 sec ስራ ስለሆነ ሁላችሁም ተሳተፊ ለመሆን ሞክሩ!!!

በዚህ Link ግቡ :
https://play.google.com/store/apps/details?id=io.doctorx.app

➨ Play store ሚለውን በመምረጥ ከ play store አፑን አውርዱት

➨ ክፈቱትና email በማስገባት ወደ Email የሚላክላቹን 3 digit code አስገቡ

➨ next step ሚለውን በመንካት  ስማቹን አስገቡለት

➨ Refferal Code ከተጠየቃቹ ይሄን አስገቡ
  👉 @y1056

complete ሚለውን ንኩት

➨ Telegram ቻናላቸውን Join አድርጋችሁ Verify አድርጉ

➨ በ 24 አንዴ ገብታችሁ ከ 3-5 Sec የ X ምልክቷን ጫን ብላችሁ በመያዝ Mine አድርጉ