ልብ-ወለድ እና ትረካ @lib_weled_ena_tireka Channel on Telegram

ልብ-ወለድ እና ትረካ

@lib_weled_ena_tireka


ይህ ቻናል አስገራሚ አጫጭር ልቦለዶችን አዳዲስ ትረካዎችን ያቀርባል

እንዲሁም
፦ አለም አቀፍ እውነታዎች
፦ ግጥሞችን
፦ እንዲሁም ተረኮችን

ለ አስተያየቶች
@Amalay22
ላይ አናግሩኝ

ልብ-ወለድ እና ትረካ (Amharic)

ይህ ቻናል አስገራሚ አጫጭር ልቦለዶችን አዳዲስ ትረካዎችን ያቀርባል! አምላክ22 ለ አስተያየቶች እና ተስከፍሎች ስንት ሲሆን ተለይቶ ከመላክ እና አምላኩ መሀከል አድርገው አናዓቃ። በማንኛውም ቆንጆ ስለ እርምጃ እና ስለ መረጃ እንቀርባለን። ስለፍቅርና ስለአባቶች ለመስራት ይህ ቻናል እና ትረካ በእኛ ላይ እንገናኛለን። አኪባሪነት እና ፈንክሽን እስከ ትንሳኤ ድረስ የምንገናኘን በሆነው በስሜሮች ቤተሰብ ስለ ማስረጃ የምንድን እና አስተያየቶችን በተጨነቁበት ቀን አድራገም እንደሚሆን በልብ-ወለድ እና ትረካ ቀጣይ ወሬ እንሆናለን።

ልብ-ወለድ እና ትረካ

07 Jul, 02:20


🎈Welcome to Tele Birr Bot
➣ ቴሌ ብር Botን ሲጠቀሙ

📋 ሲመዘገቡ 15.00 ብር Bonus

🎁 በየ 48:00 ሰሀት(2 ቀን) 3.00 ብር ጉርሻ

🔗 ጓደኛ በመጋበዝ 5.00 ብር ያገኛሉ።

TeleBirr Botን ይቀላቀሉ

🔗 https://t.me/TeleBirrProBot?start=Bot6128474

ልብ-ወለድ እና ትረካ

07 Jul, 02:20


ስለጠፋሁ በጣም በጣም ይቅርታ 🙏🙏🙏 ይሄን ነገር ሞክሩት እና የካርድ ወጪያችሁን ቀንሱ

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 05:45


​​ከጭኔ ገብቶ የሚወዘውዘኝ ሰው ነው በጣም
ተርቤያለው "አለችው ።ታረቀኝ በምን ያህል በፍጥነት ልብሱን እንዳወላለቀ
አላወቀም ባዶ እራቁቱን ሆኖ ዘሎ ወጣባት ስሜቱ አልጋ ጋር እስኪደርሱ ጊዜ
አልሰጠውም መሬቱ ላይ ተያይዘው ወደቁ ጭኖቿን በሀይል ከፈተው ለምንም
እድል አልሰጠም ጭኗ ወስጥ ገባ።
" ምነው ገና በቁምህ ጨርሰሀል እንዴ?" አለችው።
ምሽቱ እንዲህ አልፎ ነው የነጋው።
" ምን ፈልገህ መጣህ ?" አለችው ማክዳ በጥላቻ እያየቺው
" ማለት አልገባኝም " አላት ግራ በገባው ሁኔታ ኬብሮን። ለረዥም ደቂቃዎች
ሲተያዩ ቆይተው።
" ማታ አብረሀት እየተዝናናህ አብራህ ካደረቺው ጋር እዛው አትሆንም እኔ ድሀዋ
ምንም የሌለኝ ጋር ምን አመጣህ?" አለች ኬብሮን ገርሞት እየሳቀ።
" የሆነ ማድረግ የነበረብኝ ነገር ነበር አደረኩ ከዛ ግን አብሬ አላደርኩም ለሊት
ትቼያት ወጣሁ " አላት
" እሱን እኮ ነው ያልኩሁ .... እኔ የአንተ አለመፈለግ እንጂ እኔ ከልክዬሀለው እቢ
ብዬህ ነበር ?.... ውጣልኝ እንደውም " አለች በጩሀት እያለቀሰች።
" ማኪ አንቺ እንዳሰብሺው አይደለም ምንም አለረኳትም እምልልሻለው " አላትና
አጠገቧ ሄዶ አልጋ ላይ ተቀምጦ አቅፎ ሊስማት ሲል በንዴት ከተኛችበት ተነስታ
በጥፊ ጉንጩን አቅልታው እንዲወጣላት ነገረቺው በዚህ ጊዜ ተናደደ
አመነጫጨቀችው።
" እረ ቆይ ቢሆንስ ባደርግስ አንቺ ምኔ ነሽ የምፀፀተው የማዝነው ካደረኩም በቃ
እንኳን አደረኩ አያገበሻም " አላትና ወጥቶ ሄደ እሷም እሱም በየቤታቸው
ማልቀስ ጀመሩ ።
ሰላም ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ለረዥም ጊዜ ፍቅረኛዋ የሆነውን ጓደኛዋን ከትላንት
ጀምሮ እንዳላገኘችው እናም አንድ ሰው ሚስቴን ገሏል እገለዋለው እያለ
እንደነበርና ለእሷም መጥቶ እንደዛተ ተናግራ የተጠርጣሪው ስም ስዩም የሚባል
እንደሆነ አመልክታ በሄደች በጥቂት ሰአታት ውስጥ የአድማሱ አስክሬን
እንደተገኘ እሷንም ጠርተው ሲያሳያት እሱ እንደሆነና ገዳዩም ስዩም እንደሚሆን
ተናግራ ሄደች። ወዲያው የስዩም ፎቶ ተበትኖ በሀገሪቱ ተፈልጎ እንዲያዝ ትዕዛዝ
ተላለፈ........

ይቀጥላል...

@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ብቸኝነቴን...... መልሺልኝ😘

ክፍል ሀያ ስምንት (28)
.
.

.
.
.
ሚካኤሌ ልጁን ስጦታ እቅፍ አርጎ የሚስማት ቦታ እስኪያጣ ድረስ እሷም
በተመሳሳይ አቅፋው አጠገቡ ቁጭ ብላለች አይን አይኑን ታየዋለች።
" ቆይ በዚህ ምሽት ከየት መጣሽ የአዳሩ ትምህርትሽስ ?" አላት ሚካኤሌ ።
" በቃ ስትናፍቀኝ ድንገት ልምጣ ብዬ አድማሱን ደውዬ ጠራሁትና ውሰደኝ
ስለው እንቢ ብሎኝ በስንት ጭቅጭቅ ነው እዚህ አድርሶኝ የተመለሰው።"
አለቺው ሁሉም በግርምት እያያት ነው።
" እንዴ እናትሽንም ሳታያት ነው ወደ እዚህ ቀጥታ የመጣሺው ?" አላት ሚካኤሌ
በፍቅር እያያት
" አባ ለእኔ አንተ ነህ እናቴም አባቴም ከአንተ ውጪ ማንንም አላውቅም እሺ"
አለች ስጦታ።
" የኔ ፍቅር እንዲህማ አይባልም ውዴ የምናውቀውና የተነጋገርነው እሱ እንዳለ
ሀቅ ነው እሺ" አላት እየሳማት ።
" ታስገድደኛለህ አንተ እኔን አትፈልገኝም አትወደኝም እኔ የምፈልገው ጥሩ
እናትና አባት አለሽ እንድባል እንጂ መጥፎ እራስ ወዳድ እናትና አባት አሉሽ
እንድባል አልፈልግም "
" የኔ ልጅ እርግጠኛ ሁኚ በዚህ ከፈጣሪ በታች ህይወቱን የሚሰጥልሽ ሰው
ቢኖር እኔ ነኝ ግን...." አላት ሳይጨርስ
" በቃ እሱን አውቃለው ለእኔ አንተ በቂ ነህ ..... ሌላ ምንንም አልፈልግም
ሁለቱንም አልወዳቸውም በጣም በጣም ያስጠሉኛል አዳሪ ት/ቤት የገባሁትም
ከእነሱ ጋር ላለመኖር እኮ ነው ከአንተ መራቅ ፈልጌ አይደለም " አለችው
እያለቀሰች
" እናቴ አታልቅሺብኝ እኔ እኮ....." ሚጣ አላስጨረሰቺውም በመሀል ገባችና ።
" እንዴ መብቷ እኮ ነው ..... ለምን ታጨናንቃታለህ ከፈለገቺው ጋር ትኑር እኔም
ብሆን ምርጫዬ እንደ እሷ ነው ደግሞ እኔም ቆንጅዬ እህት አገኘሁ ማለት ነው።
" ስትል ስጦታን ጨምሮ ሁሉም በድንጋጤ ሲያያት ሰርካለም ግን ተናደደች።
ኬቡ ከወገቡ በላይ እራቁቱን ሆኖ በሁለት እጆቹ ወደ ኋላ ተደግፎ አልጋ ላይ
ቁጭ ብሎ ከፓንት ውጪ ምንም ያላረገቺው ሰላምን ያያታል እሷ ሙዚቃ ከፍታ
እየደነሰችለት በእጇ ውስኪ ይዛ የጠጣች እየመሰለች ከግራና ከቀኝ በከፈሮቿ
ጥግ እና ጥግ እየፈሰሰ ወደ ጡቶቿ ከዛ ቁልቁል ወደ እንብርቷ ከዛም እየፈሰሰ
ከዛም ...... ከዛም..... ወደ ታች ወረደ እሷም በእርጋታ ወደ እሱ ተጠጋች ወደ
ኋላ በጀርባው አንጋለለቺው ከወደ እንብርቱ መሳም ጀመራ ወደ ላይ ወጣች
ጡቶቸን አገጩን ስማው ከንፈሩን ልትስመው ስትል አሸሸባት መሳም
ከጀመረችበት ጀምሮ ፎቶ እያነሳቺው ነው ከንፈሩን ማሸሹ ምንም አልመሰላትም
ወደ ጆሮው ሄዳ ትንሽ ከሳመቺው በኋላ ወደ ከንፈሩ ሄዳ ጫፍ ላይ ስትደርስ
ኬብሮን አስቆማትና ከሰላዩ ላይ ገፋ እያደረጋት ።
" እፕፕፕፕ ምንድን ነው የሚሸተው በጣም የሚሸት አለ " አላት እንደ በፊቱ
የስካሩ ሙድ የለቀቀው በሚመስል።
" እኔ ምንም አልሸተተኝም .... ምን ይሸታል ?" አለች ግራ በማጋባት ስሜት
እያየቺው።
" የሚሸት ነገርማ አለ እእእእ .... ነው ከኋላ አስተነፈሽ እንዴ"
" ሄይ ... መቀለድህ ነው ቀልድ አያምርብክም " አለች ፈገግ ብላ እያየቺው እሱ
ግን ከላዩ ላይ ገፍትሮ አስነሳትና እሱ ቆሞ እሷ በጀርባዋ እንደተኛች ።
" እውነቱን ልንገርሽ ሽታ ሳይሆን ግማት ነው በጣም የሚገማ የሳንባ ምች
የሚያሲዝ ግማት ነው ያለው " አላት በመጠየፍ ስሜት።
" አንተ የምርህን ነው እንዴ ? " አለችው ከተኛችበት ብድግ በማለት ተቀምጣ
ቀንዴትና በቁጣ።
" ከምሬ ነው አንቺ ነሽ የምትሸቺው ቤቱን ሙሉ ነው ያገማሺው ከአሁን አሁን
ይለቃል ብዬ ነበር ግን ጭራሽ እየባሰ መተንፈስ አቃተኝ እጅግ እጅግ አንቺ
ትገሚያለሽ መቼ ነው የታጠብሺው ውሀ ቤትሽ የለም ውይይይይ .... አንድ ወር
በቦቲ ጫማ ሳይታጠብ የተደረገ ካልሲ እንኳን እንደ አንቺ አይሸትም " አላት
ሰላም በንዴት ጨሳ እና በግና ከአልጋው ተፈናጥራ ሄዳ በጥፊ ልታጮለው
ስትል እጇን ያዘውና በጥላቻ እና በንቀት እያያት።
" ትገሚያለሽ እያልኩሽ ወደ እኔ ትመጪያለሽ እንዴ? ስታስጠይ .............በዚህ
ግማት እንዴት ነው ሰው ፊት የምትቀርቢው በብርሽ ስለፈሩሽ ይሆናል መቼም
ዝም ያሉሽ" አላት ። እውነት ንዴቷን መቋቋም አልቻለች ።
" አንተ ውሻ እኔን ትገሚያለሽ ትላለህ " አለችና ግራ እጇን ሰደደች ለጥፊ
እሱንም ያዘውና ፊት ለፊት እየተያዩ።
" እንደምትገሚ ደጋግሜ ነግሬሻለው ውሻ ላልሺው በሴስኝነቱ ከሆነ አንቺ ነሽ
ውሻዋ በታማኝነቱ ከሆነ ልክ ነሽ እኔ ነኝ ሰለ ሚኪ ሰልልኝ ብለሽ የምትሰጪኝ
ብር ሰልዬልሽ አላውቅም ለሚኪ እውነቱን ነግሬው እየተጠቀምንብሽ ነበር እሺ
ጨርሰናል እውነቱን እወቂ አልሰከርኩም ነበር የአንቺን ጨዋታ ለመጫወት ነው
ደራሲ ነኝ ብር የማይገዛው እውቀት አለኝ እሺ አንድ ነገር ልበል የቆዳ የገላ
ግማት እና ሽታ በውሀ ይጠራል የውስጥ ግማት ግን ንሰሀ ካልገባሽ በምንም
አይፀዳም እንደገማሽ ትኖሪያለሽ " አለና እጇን ወርውሮ ወጥቶ ሊሄድ ሲል ከፊቱ
አድማሱ በንዴት ቆሞ እያያቸው አየውና ደንግጦ ቆመ።
ሚካኤሌ ስጦታ እና የሰርካለም ቤተሰቦች ተሰብስበው ተቀምጠው ሳለ ሚጣ
ወደ ሚኪ በመሄድ ስጦታን ይዛ እሱ ቤት እንድትሄድ ጠየቀቺው ሚኪም
የሚፈለገው ነገር ስለነበር ፈቀደላት ቁልፍ ተቀብላ ከስጦታ ጋር ተያይዘው
ሲወጡ እነሱን ተመለከተና።
" ምን ያህል አውሬ እና ጨካኝ እናት ብትሆን ነው በልጅ እንደዚህ የምትጠላው
ከዚህ በኋላ አሪፍ ጨዋታ እጫወትባታለው ጥሩነቴን አይታለች መጥፎነቴን
ደግሞ በትንሹ ላሳየት ለልጄ ብዬ ነበር እስከአሁንም ለልጄ ስል ነበር ...." እያለ
እያወራ አክስትየውን አየ ። ወዲያው ግን ሞባይሉ መልዕክት እንደገባ ድምፅ
አሰማ ከኪሱ ሲያወጣ።
" ሚኪ ቆይ እኔ ልይልህ " አለቺውና ማክዳ አጠገቡ ተቀምጣ ከፈተቺው አየቺው
ሰላም ነበረች የላከቺው ከኬብሮን ጋር ስትስመው የተነሳውን ፎቶ እያየቺው
በድንጋጤ አይኗ ፈጠጠ እንባዋ እረገፈ።.........


ይቀጥላል..


😘ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ😘

ክፍል ሀያ ዘጠኝ (29)
.
.
.
" የእኔ ስም ሚስጥር ነው የአንቺን ግን አላወኩትም" አለች ሚስጥረ ከሚጣ ጋር
በሚካኤሌ ቤት ሶፋ ላይ እግራቸውንም ሶፋ ላይ አድርገው እጥፍ ጥፍ ብለው
ተቀምጠው።
" የእኔ ሚጣ ነው ..... ወይኔ ግን ሚስጥር እድለኛ ነሽ ሚኪን የመሰለ አባት
ከየትም ማንም አያገኝም " አለቻት ሚጣ መንፈሳዊ ቅናት እያደረባት ።
" እውነቱ ምን አለበት ጥቂት እንኳን የሚኪ ደም ባለብኝ እላለው ደስ የሚለኝ
ደግሞ አይኔን ስገልጥ ጀምሮ አጠገቤ ሆኖ መልካምነትን ፍቅርን እየሰበከ
ያሳደገኝ እሱ ነው ... እናቴን አልወዳትም ጭካኔ አረመኔነት እራስ ወዳድነትን
ነበር የምትሰብከኝ በቃ በጣም ነው የምታስጠላኝ ከእሷ ምንም ነገር መውረስ
አልፈልግም መኖርም ጭምር " አለች ለሰላም እጅግ የበዛ ጥላቻ እንዳላት
በሚያስታውቅ የምሬት ድምፅ ለእውነትም የልጆች በሀሪ የአካባቢና የቤተሰብ
ድምር ውጤት ነው ። ብዙ ጊዜ በጥሩ ቤተሰብ የኑሮ ደረጃ ላይ ያደጉ ልጆች
ከቤተሰብ ብዙውን በሀሪ ይወስዳሉ ። እናትም አባትም መጥፎ ከሆኑ ብዙውን
ጊዜ ልጆቹም መጥፎ ሆነው ያድጋሉ ነገር ግን እንደ ሰላምና ሚካኤሌ አይነት
በሀሪ

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


​​😍ብቸኝነቴን ......መልሺልኝ😍

🔥ክፍል ሀያ ሰባት (27)
.

.

.
ሰላም ዛሬ ብርሀን ሆኖ እንደዋለው ቀን ምሽቷን ብርሀን ለማድረግ አስባ
ለኬብሮን ብዙ ብር አውጥታ ገላውን ፍልውሀ ገብቶ በንድብ እንዲታጠብ
አድርጋ ልብስ ገዝታለን እጅግ ውብ አድርጋው ለሚካኤሌ የደወለቺው እሱ ግን
ጭራሽ ስቆ እሷን አናደዳት በህይወቷ እንደ እሱ አይነት ወንድ አልገጠማትም
የእሱን ንዴት ለማየት ስትደክም እረ እሱ ምን በወጣው ጭራሽ እሷን ያናድዳታል
በዚህ ካልተናደደ ችግር የለም ሁለተኛውን ጥይቴን እተኩሳለው።
" ምነው ሳክ ደስ አለህ እንዴ " አለችው ሰላም።
"በጣም እንጂ ካረገ ከመቆየቱ የተነሳ ቦታ ሁሉ ሳይጠፋው አይቀርም አንቺ
ደግሞ እንደምታስደስቺው ቦታውን እንደምታሳይው አምናለው መልካም አዳር "
አላት እየሳቀ
" ቆይ እንዳትዘጋው ...... ምን እያልክ ነው" አለች ተናዳ።
" ገብቶሻል ምነው ተገረምሽ ..... መልካም ምኞቴን ነው የገለፅኩልሽ እሺ "
አላት ሰላም አለመናደዱ ጭስስ እርር ድብን ነው ያረጋት እውነቱ ግን ለእሷ
ያልተናደደ ይምሰል እንጂ ከእሷ በበለጠ እርሱ ውስጥ አንጀቱ ከስሏል ግን ምን
ማረግ ይችላል እሷ ሰውን ለማሳበድ ለማናደድ ስትጥር ተናዶ እሷን ከማስደሰት
የሆድን በሆድ ይዞ ለሰው ያሰበችውን ለእሷ ማድረግ ይሄ ነው ምርጡ ሀሳብ
ቀድሞ የተዘጋጀበት።
" አንድ አንዴ ሳስበው እብድ ትመስለኛለህ የድሮ ባለቤቴ " አለች ሰላም ዳግም
ስሜቱን ለመረዳት።
" አይይ የድሮ ሚስቴ ምን አንድ አንዴ ነው ሁሌም ነው እንጂ ምን ታረጊዋለሽ
አብዳ የምታሳብድ ሚስት ለጥቂት ጊዜ አግብቼ ነበር ለዛ ነው " አላት እና ከት
ብሎ ደጋግሞ ሳቀ ሰላም አናቷ የነደደ መሰላት ፀጉሮቿ ቀጥ ብለው እንደ ስልክ
እንጨት ቆሙ።
" ቆይ አንተ ምንድን ነው የሚያስገለፍጥህ ግልፍጥ ...." አለችው በጣም ተናዳ
እሱ እንደገና ሳቀ ንግግሯን ቀጠለች።
" ..... የጓደኛህ የቶማስ ሚስት ቃልኪዳን መሞቷን እእ መገደሏን ሰማህ?..."
አለችው ሚኪ ሳቁን አቆመ ክው ብሎ ቀረ ዝምምም ጭጭጭጭ ለደቂቃዎች
አይምሮው የተናጋ መሰለው አይኑ ፈዞ በአንድ ቦታ ተተክሎ ቀረ።
" የት ሄድክ አሀን በደንብ ደነገጥክ አይደል " አለችው ሰላም በእርካታ በደስታ
ተውጣ።
" አዎ ደንገጬያለው ሰላም ..... የደነገጥኩት ለአንቺ ነው ቶማስ በሚስቱ
ሚስቱም በእሱ የመጣባቸውን ሰው አይምሩም ይገልሻል እውነቴን ነው አትሞኚ
ፍቅር እና ትዳር ለአንቺ ነው ጥቅም ለአንቺ ነው እቃቃ ጨዋታ ለአንቺ ነው
ሴሰኝነት ለእንደ ዕነ ቶማስ አይነቱ ዓለም ነው ህይወት ነው ፀጋና በረከት
የሞላበት ነው ተጠንቀቂ ይገልሻል" አላት የደነገጠው ግን ለእሷ አልነበረም
ለቃልኪዳን ለቶማስም ነው የነገራትም ነገር ይገልሻል ያላት እውነት ነው። እሷ
ከት ብላ ስትስቅ እሱ ልክ እሷ ስልኩን ስትዘጋው እሱ በጣም ተናዶ በሀይል
ጮሆ ስልኩን ከኮሪደሩ ጋር ፈጠፈጠው በጩሀቱ ሁሉም ሰምተውት ነበረና ከቤት
ከሰርካለም ውጪ ሁሉም እየሮጡ ወጡ ሲያይት መሬት ላይ ተንበርክኮ ሲያለቅስ
ተመለከቱት ሚጣ እየሮጠች ሄደችና አቀፈቺውና ምን እንደሆነ ጠየቀቺው እሷም
እያለቀሰች ወደቤት ይዘውት ገቡ።
ኬብሮን ፅድት ብሎ በጣም ሰክሮ ሶፋ ወንበር ተቀምጦ እየጠጣ ሲጋራ እየሳበ
ቆየ የሚያጨሰውን ሲጋራ ልክ እንዳጠፋው ሰላም በነጭ የለሊት ልብስ
(በቢጃማ ) ካለ ጡት ማስያዣ ያለውን ጡቷን እና ፓንቷን እያሳየች መጣች
ኬብሮን ልክ እንዳያት አይኑ ፈጠጠ እና አፍን ከፈተ።
" አሁን የትኛውን እንቀጥል መጠጡ ወይስ ይሄ ውብ ሰውነት" አለችው ሰላም
ፈገግ ብላ ውብ ሰውነቷን ገልፃ እያሳየቺው እሱም ፈገግ ብሎ እየተገዳገደ
በመሄድ ጉንጯን ሳማትና ።
" በሾህ የታጠረው ፅጌሬዳ አበባ አይሻለኝም " አላት ፈገግ ብለው ወደ መኝታ
ክፍል ገቡ።
" በጣም የምወደው ልጅ ነው ታማኝ ባልና ሚስት ናቸው ግን ምን ያደርጋል
በመሀል ሴጣን ገባ አልሳካ ሲለው ገደላት የምታሳዝን ታማኝ አፍቃሪ ትዳሯን
ባሏን አክባሪ ነበረች " እያለ ሚኪ አለቀሰ ሚጣ አጠገቡ ሆና አቅፋው
እያፅናናችው።
" ሴጣን ይመጣል እንዴ ?" አለችው ሁሉም አያት ።
" አዎ ሚጣዬ የድሮ ሚስቴ ሴጣን ነች እሷ ነች የገደለቻት ... አሁን ግን ባሏ
ይገላታል ከገደላት ደግሞ ሁለት ልጆቹን ጥሎ እስር ቤት ይገባል ከዛ ልጆቹ ......
ሄጄ ላስቆመው ይገባል አዎ ልሂድና ላስቁመው " ብሎ ወደ በሩ ከሚጣ ጋር
ሲሄድ ሰርካለም አየችውና ጠራችው ቆም ሲል ።
" ሚኪ እኔንም እንደዚህ ያረገችኝ እሷ ናት " አለችው ሁሉም ደንግጠው ወደ
ሰርካለም ሲመለከቱ በሩ ተንኳኳ ሚጣ እሮጣ ሄዳ ከፈተች አንዲት ቆንጅዬ
የእሷ እድሜ እኩያ በር ላይ ቆማለች ተያዩ።
" ይቅርታ እዚህ ቤት የሚኖረው የት ሄዶ ነው?" አለች ወደ ዕነ ሚኪ ቤት እያሳየች
በዚህ ወቅት ውስጥ ስታየው "....የኔ አባት ናፍቀሀኝ ነበር " ብላ እሮጣ
አቀፈቺው እሱም እቅፍ አረጋትና።
" ልጄ ወዴ ፍቅሬ በዚህ ምሽት ከየት ተገኘሺልኝ " አላት አቅፎ በፍቅር እየሳማት
ሰርካለም በቅናት አንጀቷ ሲያር ሚጣ ተደሰተች አክስቷ እና ማክዳ በድንጋጤ
እንቆቅልሽ ሆኖባቸው ያያሉ......

ይቀጥላል...

@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


ሲሆን ልጆች አንደኛውን መርጠው ለሌላኛው ለሌኛው ብዙ ስሜት
ላይኖራቸው ይችላሉ እንደ ስጦታ።
" ስለ ሁሉም ነገር እኮ ሚኪ እንደ ትልቅ ሰው ቁጭ አርጎ ነግሮኛል .....
የሚያሳዝነኝ ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ በዚህ ወቅት ምግብ በላስቲክ ገዝቶ
መጥቶ ሲበላ አያሳዝንም " አለቻት ሚጣ ስጦትን እያየቻት ።
" በጣም እንጂ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ እርኩሷ እናቴ ነች አሁን ግን እኔ አለሁለት
በደንብ እከባከበዋለው አዳሪ ት/ቤት አልሄድም ማንም ቢጠራኝ ከእሱ ውጪ
የትም አልቀሳቀስም" አለች ስጦት የሚጣ ፍላጎት ይሄ አልነበረም በአይሆንም
እራሷን ነቀነቀችና ።
" አንቺ ተማሪ ነሽ አባትሽን ትከባከቢያለሽ ወይስ ትምህርት ትማሪያለሽ እሱም
እሺ አይልሽም እኔ ግን ሌላ ሀሳብ አለኝ"
" ምን " አለች ሰጦታ በጉጉት።
" እኔ አሁን ብቸኛ ነኝ አንቺም ብቸኛ ነሽ አይደል ? እኔ እህት ብትኖረኝ ደስ
ይለኛል አንቺስ ደስ ይልሻል ? " አለቻት በጉጉት መልሷን እየጠበቀች ።
" እንዴ በጣም ነው ደስ የሚለኝ ሁሌም እህትና ወንድም ወንድማማቾች ወይም
እህታማቾች ሳይ እኔ መቼ ይሆን የሚኖረኝ እላለው " አለቻት በሰመመን በህልም
ዓለም እየዋኘች እየበረች እየተሳፈፈች።
" የእኔ እናት እኮ እንደ ሚኪ ባይሆንም ጥሩ እና ውስጧ ምንም የሌላት ምስኪን
ነች ደግሞ አንቺን ሳይሽ እህቴ በሆነች ብዬ ተመኘሁ ሚኪ እና ሰርኬን
እናጋባቸው " አለች
" አውቄ ብሻለው ባክሽ ዳር ዳር ስትይኝ ...... እኔም ወድጄሻለው .......
ለአባቴም አስባለው .....ከዛሬ ጀምሮ ወደ ማጣበስ ስራችን እንሂድ .." በደስታ
ተጨባበጡ ተሳሳሙ።
አድማሱና ኬብሮን ቆመው ለትንሽ ተያዩ ፍጥጥ ተባብለው ሲተያዩ ቆዩና
አድማሱ እራቁቷን ያለቺውን ሰላምን አያት በጣም ተናዷል ሰላም ዝም ብላ
ታወራለች።
" አንተ አህያ ሚስቴ እኮ ነች " አለው ተቆጥቶ
" እኔ የምታልብህ ነች መቼ አልኩ " አለው ፈገግ ካለ በኋላ
" እንዴት ሚስቴን ታወጣታለህ?" አለው ወደ እሱ እየተጠጋ በጩሀት ።
" ታሾፋለህ እኔ እሷን ላወጣት .... በምን አቅሜ ስታየኝ እሷን እችላታለው ....
ትረማለህ እሷ ልታወጣኝ ስትል ለምን ለባልሽ ታማኝ ሁኚ ስላት እሱ ልክስክስ
ግማታም ነው በጣም ይሸታል ካልሲው ብብቱማ ለብቻው የሞተ ይመስለኛል
በጣም ይሸታል አፍ አይጥ የሞተበት ይመስላል ከእሱ ጋር የምተኛው እንደ ውሻ
አድርግ ያልኩቱን ስለሚያረግልኝ ነው እንጂ አንድ ደቂቃ ከእሱ ጋር አይተኛም
ስትለኝ ለባልሽ ታማኝ ሁኚለት ብያት ልሄድ ስል ያገኘሁሁ " አለው የውሸቱን
" እሷ ነች ይህን ያለችህ " አለውና ጫማውን አውልቆ አሸተተው ወደ ኬብሮን
አፍንጫ ሲወስደው ኬቡ እንዲተው ነገረው ቀጠለና ብብቱን.......
" አድሜ ውሸቱን ነው እውነት አላልኩትም " አለች እያለቀሰች
" አንቺ ቆይ በጨረፍታ እኮ ስለመግባት ስታወሩ ሰምቼያለው አንተ ሂድ እኔና እሷ
እንጨርሳለን " አለው ኬቡም ሀሳብ ሳይቀይርበት አመስግኖት ሲወጣ እየጮሀ
እየሰደባት ወደ እሷ ተጠጋና በቦክስ መታት ወደቀች በአፏ ደም እየፈሰሰ።
" አድማሱ በቃ አለቀልህ አንተም ኬብሮንም ትሞታላቹሁ " አለች እየሳቀች ።
እሱም እሱ እንደሚገላት ተናግሮ ዘወር ሲል ግንባሩ ላይ ሽጉጥ ተደቀነና ተተኮሰ
ግንባሩን በሳው ፈገግ አለች።
በንጋታው ጠዋት ለሊቱ ለሊት ሲይመስላት አዳሯን በለቅሶ ነው ያደረቺው
የኬብሮን ከሰላም ጋር መሆኑ አናዶታል ከልቧ ነበር የምታፈቅረው ማታ ሚካኤሌ
ሊያፅናናት ሊያግባባት ምን እንዳላደረገ ሊያሳምናት ሞክሯል ግን አልሆነለትም
ከዚህ በኋላ በትገለው ኬብሮንን በወደደች አይኑን እንኳን ማየት አትፈልግም ።
በዚህ ወቅት የመኝታ ቤት በር ተንኳኳ ከዚህ ቀደም ሳሎን ውስጥ ፍራሽ አጥንፋ
ከሚጣ ጋር ነበር የምትተኛው አሁን ሳሎን ሶፋ ላይ ሰርካለም ስለተኛች
በሰርካለም መኝታ ቤት ከሚጣጋ ነበር የተኛቺው እሷ ከእንቅልፋ ተነስታ ወጥታ
ሄዳለች ኮደሚኒየሙም በለ አንድ መኝታ ክፍል ነው። የተንኳኳው በር ተከፍቶ
ኬብሮን ገባ ዘወር ብላ በጥላቻ አየቺው እሱ በፈገግታ ..........
~~~~ ይቀጥላል ~~~~


😘ብቸኝነቴን .... መልሺልኝ😘

ክፍል ሰላሳ (30)
.
.
.
" እስከ አሁን ምን አስቆየህ ቶሎ ና አይደል ያልኩል " አለች ሰላም ከፊቷ
ጭንቅላቱ በጥይት ተበስቶ የሞተውን አድማሱን እና ገዳዩን በእጁ ሽጉጥ ይዞ
የቆመውን ታረቀኝን እየተመለከተች።
ታረቀኝ ማለት የዛሬ ወዳጇ አይደለም የቆየ ነው እረዥም ጊዜ በእሷ ፍቅር
የሚሰቃይ ወጣት ነው እሷ ግን በጣም ስለምትጠላው ገና ስታየው እብድ
እንዳየች ትሸሸዋለች ። ከእሱ ጋር ሰው ፊት መቅረብ አይቻልም መልኩ የሰው
አይመስልም የጎማሬ እንጂ ትላለች ነገር አለባበሱ እና በጣም እራሱን መጠበቁ
የናጠጠ ሀብታም ያስመስለዋል ብራድ እና ውድ ልብሶች ነው የሚለብሰው እሱ
በአንድ የውጭ የእርዳታ ድርጅት ሹፌር እንደሆነ ነግሯታል ስታስበው ደመወዙን
ለዚህ ጉዳይ ለልብሱ ነው የሚጨርሰው ብላ ታስባለች የማያምረውንም
መልኩን በውድ ልብሶቹ ነው የሚሸፍነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሰራተኞቹ
ሲሸሿት ድርጅቱንም መምራት ሲከብዳት ለአድማሱ ማስታወቂያ ለጥፍና ሰራተኛ
ቅጠር ስትለው እሱ መጥቶ ተወዳድሮ ነበር ያቀረበው መረጃ ደግሞ በአንድ
የግል ድርጅት ብቃት ያለው ስራ አስኪያጅ እንደ ነበረ የሚያሳይ ነው ። ስለዚህ
ም/ስራ አስኪያጅ አድርጋው ሙሉ ለሙሉ ስራውን ለእሱ ትታዋለች። ወደ ቢሮ
በሄደች ቁጥር እያያት አይኑ እንደሚከራተት ከቀሚሷ እና ከፓንቷ ስር በሀሳብ
እየገባ እራሱን እንደሚያዝናና ስለተረዳቺው አንድ ቀን እንደሚጠቅማት ስታስብ
ነበር ይሀው ዛሬ ጠቀማት ። ለሚካኤሌ ፎቶውን በላከቺበት ቅፅፈት ለእሱም
መልእክት "ልሞትልህ ነው ና ቶሎ ድረስልኝ " ብላ ፅፋለት ነው የመጣው
" እንዴ ይሄ እኮ ባልሽ ነው ገደልኩት " አላት በድንጋጤ
" ሁሌም ለአንቺ ህይወቴን እሰጣለው ትለኝ አልነበር " አለች
" አሁንም እሰጣለው መቼም ቢሆን " አላት
" አየህ ይሄ ሆዳምና የገንዘብ ሰው ነው የድሮ ፍቅረኛውን ከፎቅ ወርውሮ ገሏት
ነው የመጣው አሁን እኔንም ገሎ ሀብትና ንብረቴን ሊወርስ ነበር አንተ
ባትደርስልኝ " ብላ ከተቀመጠችበት በመነሳት ወደ እሷ ሄዳ አቀፈቺው እናም
አለቀሰች ። እሱ አሁን የተረዳው ነገር ከፓንት ውጪ ምንም እንዳላደረገች ትዝ
ሲለው ሰውነቱ ነዘረው አቀፋት ቀጥሎ አፅናናት እና ሁሌም ከእሷ ጋር መሆኑን
ነገራት እሷ ግን ከጀርባው ሆና እያላገጠችበት ነበር ። ከእቅፍ ወጣችና ወደ
ጀርባው ሄደች እሱ ደግሞ የአድማሱን አስከሬን እያየ ቁጢጥ አለና ።
" አሁን ሶልዬ ይሄን ምን እናርገው " አላት ወደ አስክሬኑ እያየ
" እኔ የምልህ የትኛው ይሻልሀል " አለችው ዞሮ አላያትም።
" አስክሬኑን ቅድሚያ ከማንሳትና ወይም ከዚህ..." አለችው። ቀስ ብሎ ዘወር
በማለት ተመለከታት አሁን ፓንቷም ወልቋል አይኑ ፈጠጠ አፍን ከፈተ
የሚከድነው ደጋግሞ እየመጣበት ያለውን ምራቅ ለመዋጥ ነው ከተቀመጠበት
ተነስቶ ቆመ እንጆሪ የመሰሉ ከንፈሮቿን ቀጠለ የጠነከሩ የመሰሉ ጡቶቿን
ቀጥሎ እንብርቷን ሲያይ አለጋ በመሰሉት የእጆቿ ጣቶች እየተራመደች ወደ ታች
ስትወረድ ተመለከተና ከጣቷ ቀድሞ ያንን ተመለከተ የሚያምሩት ጭኖቿን
እግሮቿን አየና የመጨረሻውን ምራቅ ውጦ ።
".......እእ ..... እእ ..... ማ ..... ለቴ .... ምን እናረገው ....... " አላት ውብ ገላዋ
እና የወሲብ ጥማቱ አንደበቱን ቆልፈውት። እሷ ደግሞ ቁልቁል ወደ ሱሪው
ተመለከተች ድንኳን የሰራውን የሱሪውን ዚፕ አካባቢ አየችና።
" እኔን ያሳሰበኝ እሱ ሳይሆን

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


​​😘ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ ስድስት (26)


በአንድ ሰው በሞላው መጠጥ ቤት ሰላምና ኬብሮን ቁጭ ብለው ይጨቃጨቃሉ
እሷ መጠጥ እንዲጠጣ ት ፈልጋለች እሱ እንደማይጠጣ ይነግራታል።
" አንተ ግንብ እራስ ዝም ብለህ ጠጣ አንተ እኮ አይደለህም የምትከፍለው እኔ
ነኝ እሺ " አለችው ሰላም።
" ክፈልስ ብትይኝ ከየት አምጥቼ እከፍላለው ቆዳዬ ተገሽልጦ ብር አይሆን
....ትሰሚያለሽ እኔ መጠጥ አልወድም ከጠጣው እንኳን ጤነኛ አልሆንም
እራሴንም የማረገውንም አላውቅም ስለዚህ መጠጥና እኔ አይጥና ድመት ነን
እሺ" አላት የማስንጠቀቅ አይነት ንግግር ተናግረ።
" ዝም ብለህ ጠጣ ከማን ጋር ያለህ መሰለህ እኔ እኮ ነኝ ... እኔ ሰላም ....
ሰላም ሽቡሩ እሺ " አለች በመተማመን።
" ልክ ነሽ ሰላም ሽብሩ ነሽ ... እኔ መቼ አልጋነሽ ሽብሩ ነሽ አልኩሽ ? " አላት
ፈገግ ብሎ እሷ ተናዳ።
" አ .... አ .. አልጋነሽ .. ስትል አልገባኝም?" መረር ባለ ቁጣ
" እንዴ ምን አስቆጣሽ ?..... አልጋነሽ ስም እኮ ነው " አላት
" አ አ ስም እማ ስም ነው ..... ያልገባኝ አሽሙሩ ነው ... ልትል የፈለከው የአልጋ
ላይ ሽብርተኛ ነው አይደል" አለችው ኬብሮን የሆነ ነገር እንደገማው ፈገግ አለና

" አሀ ሀሀሀ .... አልጋነሽ ሽብሩ አይገርምሽም እኔ ተናግሬው አንቺ ሲገባሽ እኔን
ገባኝ ..... ምን አለበት ....... አይይደል የሚባለው " አለና ከት ብሎ ሳቀ ።
" እንደውም ልክነህ ..... አልጋ ላይ ሽብርተኛ ነኝ ተስማማን አሁን ....... ትንሽ
ጠጥተህ ትሄድና ይሄ ዝናብ የመታው ፍየል ፍየል የሚሸተውን ጠረንህን
ታጥበሀው ትመጣለህ " አለች ሰላም በመጠየፍ። ኬብሮን ዝም ብሎ በፈገግታ
አየትና።
" እኔ የምልሽ ሶል ..... ፍየል ዝናብ ሲመታው መጥፎ ጠረን እንዳለው እንዴት
አወቅሽ ነው ....... አብረሻቸው አድረሻል ?" አላት ኬቡ የሰላም ፊት በንዴት
ተለዋወጠ ።
በጣም በፍጥነት እጅግ እየበረረ በትላክስ አካባቢውን እየበጠበጠ ቶማስ
እየበረረ በመምጣት የሆስፒታሉን ቅጥር ግቢ በር አቁም እየተባለ ዝም ብሎ
ገባ መኪናውን አግባብ ባለው ቦታ አላቆመውም ። ከመኪናው ዘሎ በመውረድ
ወደ ውስጥ ገባ ፊቱ እና አይኑ ቀልቷል በደንብ እንዳለቀሰ ያስታውቃል ቀጥታ
ወደ ዶክተሩ ቢሮ በመሄድ ሳያንኳኳ ገባ።
" አቤት " አሉት ዶክተሩ በእድሜ ፀና ያሉ ሽበታም ወፍራም።
" ዶክተር ከፎቅ ላይ ወድቃ የመጣችው የቃል ኪዳን ባለቤቷ ነኝ እንዴት ነች
ዶከተር " አለ ቶማስ እያለከለከ።
ዶክተሩ በትህትና እንዲቀመጥ ካደረጉት በኋላ ለደቂቃ እራሱን እንዲያረጋጋና ከዛ
በኋላ ያለውን ነገር እንደሚነግሩት አሁን ግን ስሜቱ የሚረጋጋ ከሆነ ደህና
መሆኗን ነገሩት በእርግጥም ለቶማስ ይሄ ንግግር አረጋጋው።
ወደ እራሱ እንዲመለስ ካደረጉት በኋላ አሁን ያለውን የቃል ኪዳንን ውጤት
ነገሩት። በእርግጥም ቃል ኪዳን አሁን ባለው የህክምና ውጤት ወገቧ ላይ
ዪለው እስፓይናል ኮርድ በመሰበሩ የተነሳ ከዚህ በኋላ መራመድ አይደለም
መቀመጥም የምትችል እንደማይመስላቸው ሙሉ ለሙሉ ያለውን ውጤት
ደግሞ በተጨማሪ ከሚደረግላት ምርመራ እንደሚያሳውቁ ነገሩት። ቶማስ
በየንግግራቸው መሀል እያለቀሰ እንደ አይምሮ በሽተኛ ለሀጭ ንፍጡን
መቆጣጠር ተስኖት እየተዝረከረከ ነበር የሚሰማው በመጨረሻ ከቢሮው
በፍጥነት ወጥቶ ሄደ የት እንደሚሄድ እርግጠኛ ነበር።
" እማ ያ ሳቂታ ተጨዋች የነበረው ሚኪ ለምን ሳቁ ጠፍቶ ጭምተኛ የሆነበትን
ችግር አሁን ደረስኩበት እኮ ፍቅር ፍቅር ይዞት እኮ ነው " አለች ሚጣ ከሆስፒታል
ወጥተው ሰርካለም ከረጅሙ ሶፋ ላይ ጋደም ብላ እነሱ ባለ አንድ አንድ ሶፋ ላይ
ተቀምጠው። ሚኪ ደንግጦ ።
" እረ እንደሱ አይደለም ሚጣ ምን ሆነሽ ነው" አላት እያፈረ።
" ሚኪዬ እኔ ልጅህ እኮ ቅመም እኮ ነኝ የፍቅር ቫይረስ ሲይዝ የህመሙን
ምልክት እኔ አውቀዋለው እንደ አንተ ነው የሚያረገው እሺ " ስትል በሩ ተንኳኳ
ሚጣ ለመክፈት እየሮጠች ሄደች ከፍታ ከአክስቷ ጋር ተመልሳ መጣች ሰርካለም
እንዳየቻት።
" አክስቴ ምነው ከመሸ ከየት ነው ?" አለቻት
" ሄይ አንድ boy frend ቀጥሬ ሲጋበዘኝ አምሽቶ እንደር አላለኝም አይገርምም
በአንደ ቀን 300 ብር አውጥተህ የ3000 ( የሶስት ሺህ ) ብር ስትፈልግ
አይደብርም ብዬው ትቼው መጣኋ ....... " አለችና ሚኪን ተቀምጦ ስታየው
ዳበስ እያረገቺው በፈገግታ "....ዋው ይሄ ቆንጆ እዚህ ነው እንዴ ዛሬ...... ዋው
በጣም ነው የሚያምረው" ስትል ሚጣ አይኗን በቀጥታ ወደ እናቷ ወረወረቺው
ሰርካለም መናደዷን አየች።
" በይ አክስቴ ከእሱ ጋር እንኳን አቁሚ እና ነይ ቁጭ በይ " አለች ያልተናደደች
በመምሰል ።
" እማ እንዴ ምን አናደደሽ ..ምን ችግር አለው " አለቻት ሚጣ
" እረ ተይ አንቺ ልጅ " አለች ሰርካለም በምሬት በዚህ ሰአት የሚካኤሌ ስልክ
ጮሀ ስልኩን ይዞ እንደተለመደው በዱላው እየተመራ ከቤት ሊወጣ ሲል ማክዳ
ጋር ተገናኝተው ሰላም ተባባሉ እና እሷ ስትገባ እሱ ወጣ ግን ስልኩ ተዘግቶ
ስለነበር ዳግም እስኪደወል ጠበቀ። ተደወለ ሰላም ነበረች በምሽት መደወሏ
ገርሞታል አነሳውና ወደ ጆሮው ወሰደው።
" አንተ ብርሀን አልባ ዛሬ ማን ሲያስደስተኝ እንደሚያድር ልንገርህ ኬቡ ነው ....."
አለችና ለኬብሮን ስልኩን ሰጠችው "ሀይ ወዳጄ ወንድሜ ዛሬ አዳሬ ይቅርታ
እዚህ ነው ....." አለው የሚኪ ፊት ወዲያው ተቀያየረ ።
" ያው እንዳታስብ ብዬ ነው የነገርኩሁ እሺ ከፈለክ በኋላ በፎቶ እልክልሀለው
ለማረጋገጥ " አለችው ሚኪ የምን ሳቅ እንደሆነ ያላወቀው ሳቅ ከት ብሎ ሳቀ..

ይቀጥላል....

@lib_wele_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ ሁለት (22)
.
.
.
ከጥቂት ዓመታት በፊት የሚካኤሌ ሀሳብ
ምን መወሰን ምን ማረግ እንዳለበት ግራ ተጋብቶ በዱላው እየተመራ ወደ ሳሎን
ሄደ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ ምን ማረግ እንዳለበት እንቅልፍን ሳይተኛ ሲያስብ አደረ
። አማራጩ በዚሁ አይነ ስውር መስሎ መቀጠል እንዳለበት ህሊናውን አሳመነ።
የሚካኤሌ አይን እንደፈጠጠ ሰማይም ቦገግ ብላ ፈካች በዚህ ሰዓት የሰመመን
እንቅልፍ ወስዶት ነበር ። ውስጥ ሲጎዳጎዱ ብንን አለ ግን አልተነሳም እዛው
አይኑን ጨፈነ ። እነሱ ወደ ስራ ለመሄድ ዝግጅታቸውን ጨረሰው ወደ ሳሎን
መጡና እያዩት ተጠቃቀሱና ።
" ጨርሰናል አልጋውን ከፈለከው ጠረኔ አለልህ አንሶላውን ያረጠብንበት እሱን
በአፍጫክ እየማክ ተኛ።" አለችውና ሳቀች ዝም ብሎ ሰማት አይኑን በአንድ ቦታ
ተክሎ ከሰማት በኋላ።
" አይበቃኝም ሰላም ቤቴን ድርጅቴን ሀብት ንብረቴን ለቀሺልኝ ትሄጂ መካፈል
ያለብሽን ወጭ ሆነሽ ተከራከሪ " አላት ሰላምና አድማሱ እየተያዩ ከት ብለው
ሳቁበትና ።
" የምን ሀብት ንብረት ሁሉም በሚሊየን የሚቆጠር ብር ተበድረሀኝ መክፈል
ስላልቻልክ ሀብት ንብረቴን ለእኔ እንደሰጠህ የሚያረጋግጥ አሻራህም
ፊርማህም ያለበት ማስረጃ እጄ ላይ ነው ከዕነ ምስክሮቹ " አለችው ሚካኤሌ
አልደነገጠም ያኔ ዓይነ ስውር እያለ እንደሚስት አምኗት ፈረመላት ከፈረመ በኋላ
በጣም ትልቅ ስህተት እንደሰራ ገብቶታል የሆነ አንድ ነገር ጎትቶ እንደሚመጣ
ታውቆት ነበር ይሀው ሆነ ዝምታን መረጠ ። ሰላም ንግግሯን በመቀጠል "...ያው
እኔ ክፍ ስላልሆንኩ ቤት ተከራይቼልሀለው ከዛሬ ጀምሮ እዚህ ቤት እንዳላገኝህ
ንብረቴን ቀማቺኝ የምትል ከሆነ ፍ/ቤት ክሰሰኝ ከዚህ በኋላ እዚህ ቤት
ድርጅትም ዝር እንዳትል እኔ ባለትዳር ነኝ እሺ " አለችው
" እሺ ..... ግን ማን ነው የሚወስደኝ ወደ ተከራየሺው ቤት " አላት ፍፁም
ትህትና በተላበሰበትና በፈገግታ ።
" ሹፌር እልክልሀለው እሱ ይዞህ ይሄዳል እስከምችለው የቤት ክራይህንና
ምግብህን እችልሀለው ለፈጣሪ ስል ልጁ እስከሚመጣ እቃህን አዘጋጅ ይህን
ስል ልብሶችህንና የምታነባቸውን መፅሀፎች ብቻ ነው ይዘህ የምትወጣው "
ብላው ፈገግ እያለ ዱላውን አንስቶ እየተመራ እየሄደ
" ሄጄ ላዘጋጃ አይመስላቹሁም " አላት በመሳቁ መልስ ሳትሰጠው እየሄደች
ለአድማሱ የምትናደድበት ሰው መናደድ ሲኖርበት የእሱ መሳቅ ነው እናም
እያላገጠባት ይመስላል።
ከለሳብ መልስ አሁን ላይ
የሚጣ ፊት ሀይለኛ ዝናብ የዘነበበት መሬት መስሏል አይኖቿ በለቅሶ
ሞጭሙጨዋል የሰካራም አይን ይመስል ደፍርሷል ። ሚካኤሌ በሀሳብ
ከሄደበት ሲመለስ የእሱም ዓይን እንባ አዝሎ ነበር ጭምቅ አርጎት እንባዎቹን
ከመሬት ፈጠፈጣቸው።
" ጋሼ እሷን ስናስባት ሴጣን የዋህ ነው እንበል " አለቺው እና እሱ ፈገግ ብሎ
ዝም ሲላት ።" .... ጋሼ እረ ቆይ ለምንድን ነው እንዲህ ክፍ የሆነቺው? " አለቺው
" ሚጣዬ እሱን እንኳን እኔ እሷስ ታውቀዋለች " አላት በዚሀ ሰዓት ሰርካለም
የተኛችበት መኝታ ክፍል ተከፍቶ ዶክተሩ በመውጣት ወደ እነሱ በመምጣት።
" የተደረገላት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተፈፅሟል አሁን ልታያት ትችላላቹ
በቅድሚያ ግን እንኳን ደስ አላቹሁ አለና ጨበጣቸው ሁለቱም በደስታ እየሮጡ
መኝታ ክፍሉን ከፍተው ሲገቡ ሰርካለም ሚካኤሌን እንዳየቺው በጩሀት
እንዲወጣላት አባረቀችበት ሚጣም እሱም ደንግጠው በቆሙበት ደርቀው ቀሩ።
ኬብሮን ሚስት ሳይሆን ያገባው ፌዴራል እስር ቤት ነው ያለው ብላ በዱላ ጫት
ቃም በዱላ ተኛና ወሲብ አርገኝ በዱላ ሆኖበት ምርር ብሎታል ፊቱ ቆስሏል ።
አሁንም ቁጭ ብሎ እየቃመ እሷ ቡና እያፈላች ነበር ። እናም መፀዳጃ ቤት ደርሼ
ልምጣ በማለት አስፈቅዶ ወደ መፀዳጃ ቤት አስፈቅዶ በመሄድ ሽንቱን እየሸና
ሳለ ሞባይሉ ጮሀ ከኪሱ አውጡቶ ደዋያን ሲመለከት ሰላም ነበረች ማናገር
ጀመረች።
" አንተ ምን አባህ ልሁን ብለህ ነው ብሬን በልተህ የጠፋሀው" አለችው ሰላም
" እረ በመድሀኒያለም ፣ በማርያም ፣በሚካኤል ፣ በገብርኤል እባካቹሁ ሴቶች
ተውኝ በቃ ..... ቆይ ማን ነው በእኔ ላይ ያዘመታቹሁ እኔ የኢትዮጵያ ጠቅላይ
ሚኒስትር አልነበርኩ ማን አቃጥላቹሁ ድፍት ብሏቹሁ ነው?" አለ በምሬት
" አንተ ደግሞ ሰው ሆነህ አንተን ለመግደል ሰው ይላካል ውርጋጥ አሁን ስለ
ሚኪ ንገረኝ አለበለዚያ አስደፋሀለው " አለች ሰላም በዚህ ወቅት መዓዛ መቆየቱ
አናዷት ስትመጣ ከሴት ጋር እያወራ ነው በንዴት አየቺው ።
" ምንም የለኝም ....እሱማ ግልግል ነው ላኪብኝና አድርጊው በጣም ይሻለኛል"
እያለ ዘወር ሲል አያት በድንጋጤ አይኑ ፈጠጠ እሷም ያን ቡጢዋን አቅምሳው
ከሽንት ቤቱ ሲንክ ላይ አጋደመቺውና።
" እኔን ተደብቀህ ትጀናጀናለህ አንተ አህያ እገልሀለው እሷንም እገላታለው"
አለቺው እና በወደቀበት ምራቋን ተፋቺበት።
ኬብሮን ጠዋት የተነሳው የቤቱ በር በለይል ሲንኳኳ ነበር ።ተነስቶ ቤቱን ተዟዙሮ
ሲያይ የለችም መዓዛ ፊቱ ላይ ብልዝና ፕላስተር ሞልቷል በሀይል ወደ ሚንኳኳው
በር ሄዶ ሲከፍት የታጠቁ ፖሊሶች እና ሲቢል የለበሰ በዕድሜው ፀና ያለ
አስቀያሚ ሰውዬ ቆሟል ስሙን ጠርተውት እሱ መሆኑን አረጋገጡ መዓዛ
እንዳለች ጠየኩት አለመኖሯን ተናገረ ሲቢል የለበሰው ሰው በጥላቻ እና በንዴት
እያየው።
" ነፍሰ ጡሯን ሚስቴን በፍቅር አጃጅለህ ብሬን እየዘረፈች እንድትሰጥህ ከደረክ
አስኮብልለህ አብረሀት ትኖራለህ ያዙልኝ ይሄን ወንጀለኛ " አለ ሰውዬው
ፖሊሶቹም ልብስ እስኪለብስ አልጠበቁትም እያዳፍት ወሰዱት።.........

ይቀጥላል ....

@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


​​😘ብቸኝነቴን ...... መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ አራት (24 )
.
.
.
በፖሊስ ጣቢያው የምርመራ ቢሮ ውስጥ ኬብሮንን እየመረመረች ያለችው
ፖሊስ ሌሎቹን ተመለከተች እሱም ለጥያቄው መልስ እንድትሰጠው
በአይኖቿቸው ነገሯት።
" አሁን ዝም ብለህ ወንጀልህን እመን " አለች መርማሪ
" ምንም ወንጀል አልሰራሁም " አላት በድፍረት በኬብሮን
" ዝም በል እራሰህም ከተናገርከው ......"
" እኔ ከተናገርኩት እ ምን ወንጀል ሰራሁ አስገደደቺኝ እንጂ " አላት ኬብሮን
በግርምት አየቺው።
በዚህ ወቅት ሰላም መኪናዋን እያሽከረከረች ፖሊስ ጣቢያ ግቢውስጥ አቁማ
ልትወርድ ስትል ስልኳ ጮሀ የደዋዩን ማንነት አየቺው አድማሱ ነበር ከመኪናዋ
እየወረደች ማናገር ጀመረች ። አድማሱ ቃልኪዳንን አዲስ የምታሰራው ባለ አንድ
ፎቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ያላለቀውን ህንፃ ብቻዋን እየጎበኘች እንደሆነና ምን
እንዲያደርጋት ጠየቃት እሷም አደጋ አስመስለህ እንዲገድላት ነገረቺው እና
በቀጥታ ኬብሮን ወደ የሚመረመርበት እየመጣች ሳለ በር ላይ ተቀምጣ
የነበረቺው ማክዳ አይታት ተደበቀች ሰላምም እንደደረሰች በሩን አንኳኩታ ከፍታ
ገባችና ።
" አንቺ እውነት ለህግ ከቆምሽ የእሱን ፊት የቦክስ መለማመጃ አድርጋው
ቀጥቅጣው ፊቱ እንዲህ ሲበላሽ የት ነበርሽ " አለቻትና አገጩን ይዛ አሳየቻት።
" አንቺ ልጅ ምንድን ነው የምታወሪው እስቲ ቀስ ብለሽ እደጊ ...... አሁን ተይኝ
እኔ እራሴ አሞኛል " አለቻት
" አይ እማ እኔ ብተውሽ እሱ ልብሽ ውስጥ ያለው ፍቅር እሺ ብሎ ይተውሻል እ እ
እናቴ..." በፈገግታ አያየቻት
" አንቺ ምን አይነት ልጅ ነሽ ገና ህፃን ልጅ እኮ ነሽ"
" ማን እኔ ነኝ ህፃን ......." ስትል በሩ ተንኳኳ እና ተከፍቶ ሚካኤል ገባ እና
በፍራቻ ሁለት እጆቹን ወደ ፊት አጣምሮ ቆመና አይን አይኗን ሲያይ ። ሚጣ
አየቺውና።
" እማ ህፃን ልጅ እሱ ነው ....... እይው እንዴት እንደፈራ አያስቅም እማ በጣም
ያስቃል?" አለችው ። ሚኪ በድንጋጤ ኮስተር ብሎ ሚጣን አያት እና ሰርካለምን
አያት።
" ቆይ አትመጣብኝ ብዬህ አልነበር ለምን መጣህ?" አለችው
" እኔ እኮ ግርምምም የምትይኝ እማ የሌለብሽን በሀሪ አጉል ቁጡ ሴት ተናጋሪ
መጥፎ ሴት ለመምሰል የምትሞክሪው ነገር አይገባኝም የዋህ ምስኪን አንጀት
ለማንም ስፍስፍ እንደሚል አውቃለው....." እያለች ሚጣ ስታወራ ሰርካለም
አፍራ በቁጣ ።
" አንቺ ልጅ ምነው ዝም ብትይ ሚጥሚጣ ሆንሽብኝ እኮ "
" እማ ለምን እውነቱ ሲነግርሽ የምትቆጪው ለሰው ሁሉ አንጀትሽ ይሰፈሰፋል
ለምንድን ነው ሚኪ ላይ ከመሬት ተነስተሽ ዘራፍ የምትይበት ይሄ ፍቅር
አይደል?"ስትላት
" አንቺ ልጅ ሂጂ ውጪልኝ ምን የተረገመች ነች " አለች ሰርኬ
" አልወጣም እኔም በሽተኛ ነኝ አልጋ እኮ ይዤያለው አንቺ ዶክተር ነሽ እንዴ እኔን
ማስወጣት አትችይም " አለች በማላገጥ እያሾፈች ሰርካለም ተናዳ ልትናገር
ስትል ሚካኤሌ በመሀል በመግባት።
" ችግር የለም ሰርኬ እኔ እወጣለው በልጅና በእናት መሀል አልገባም ግን አንድ
ጥያቄ መጠየቅ ፈልጌ ነው።"
" እረ ሚኪዬ አባቴ በመሀል አልገባህብንም እሺ ጠይቅ ችግር የለም በአግባቡ
የማይመለስ ጥያቄ የለም"አለች ሚጣ ሁለቱንም አከታትላ እያየች። ሰርካለም
አየሩን በንዴት በሀይል ወደ ውስጧ ሳበችውና መልሳ አወጣቺው።
" ውይ..... ውይ..... በጣም ወሬ አብዝተሻል ልጄ "አለች ሰርካለም ሚጣ
በአዎንታ ፈገግ ብላ ጭንቅላቷን እየነቀነቀች
" ይቅርታ ሰርኬ የመጣሁት ማን እንዳናደደሽ እንድትነግሪኝ ነበር ፍቃደኛ
ከሆንሽ ?" አላት አሁንም በፍራቻ እጁን ወደ ፊት አድርጎ አጣምሮት። ሰርኬ
አየቺው እና።
" ምን አገባህ ማን ስለሆንክ በምን ተናደሽ ነው የምትለኝ " አለች በቁጣ
ሰርካለም። ሚካኤሌ ደንግጦ ቅልስልስ እያለ።
" ማንም አይደለሁም ምንም ፈልጌም አይደለም " አላት
" ስለዚህ ካላገባህ በሽተኛ ነኝ ለምን አትወጣለኝም " አለችው ቀዝቀዝ ብላ።
ሚካኤሌም በእሺታ ጭንቅላቱን ነቅንቆ በአይነ ሱውሩ የሚመራበት ወደ መሬት
ወርውሮ በመዘርጋት ሊወጣ ሲል ሚጣ እጁን ይዛ አስቆመቺውና።
" እንዴ አንተ ወንድ ልጅ አይደለህም ? ... ምንድን ነው እንደ ቄጤማ
ልምጥምጥ የሚያረግህ ቆፍጠን ኮስተር በል የወንድ ወንድነቱ የሚታወቀው
ሴትም የምትወደው እንደዛ ሰትሆን ነው ወጣ እሺ ግባ እሺ ስትል አፍቃሪዋ
ሳይሆን የምትመስለው የበሯ ጠባቂ ነው ........ ለማንኛውም አንዴ እናቴን
ላናግራት እና እጠራሀለው ጠብቀኝ " ብላው እስከ በር ስትሸኘው የነገራትን
ልተነግራት መስሎት ያዝ ሲያረጋት እንዳልሆነ በአይኗ ነገረቺው እና አስወጥታው
በሩን ዘግታ ወደ እናቷ ስትዞር እናቷም አየቻትና ።
" ልጄ በሽተኛ እኮ ነኝ ልትደፊኝ ነው እንዴ?"አለች ሰርኬ
" እማ በሽታውን ለግልሽ ያሺው እኮ እኔም በሽተኛ እኮ ነኝ አንቺስ አቃጥለሽ
ልትደፊኝ ነው "አለች ወደ እሷ እየተጠጋች።
ቃል ኪዳን በአዲስ ገና እየተሰራ ፎቅ ላይ ሁኔታውን እየተዟዟረች ትመለከታለች
አድማሱ ተደብቆ ይከታተላታል ወደ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ወጣች ዙሪያውን ዘወር
ዘወር ብላ ስትመለከት አድማሱ ከኋላ ይከተላት ነበር ። አንድ ጫፍ ላይ ተደብቆ
ጠበቃት ከትንሽ ቆይታ በኋላ እሷ ለማየት ስትመጣ ተደብቆ አያትና ተደርድሮ ሄዶ
ገፈተራት ከሁለተኛ ፎቅ ተወርውራ መሬት ላይ በተከመረ አሸዋ እና ድንጋይ ላይ
እየጮሀች ወደቀች ጩሀቷን ሰምተው ጥበቃው እየሮጡ መጡ አያትና
ደንግጠው ጮሁ። ..........

ይቀጥላል...

@lib_wele_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ከዳንሰኛው ወንድሜ ድርሰቴ ላይ የተቀነጨበ...😘

በሶፊ👤
<------------------------------------------>
( )
( @lib_weled_ena_tireka )
( )
<------------------------------------------>
4 any comment
@amudye_bot

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


​​😘ብቸኝነቴን ..... መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ አምስት (25)


በፖሊስ ጣቢያው የምርመራ ቢሮ ውስጥ ኬብሮንን በዋስ መልቀቅና
አለመልቀቅ መርማሪዎቹን ጨምሮ ከተነጋገሩበት በኋላ ኬብሮን የመዓዛ ባል
ጠፋ ያለውን ብር አይደለም ምንም አይነት የባንክ አካውንቱ እንኳን የሌለው
በሆነ ጊዜ አንድ ቀን ከምትልክለት አነስተኛ ብር ውጪ ሌላ አለማወቁን እና
የተለያየ ነገሮችን አይተው በዋስ ሊፈቱትና በሚፈለግበት ጊዜ መምጣት
እንዲችል ነግረውት ከሰላም ጋር ሊወጣ ሲል መርመሪዋ ጠራችው ዘወር ብሎ
አያት ።
" ከዚህ በኋላ እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ እንዳትገባ "
" እንዴት አይነት ነገር " አላት ኮስተር ብሎ
" እንደዚህ የሰው ሚስትን አጭበርብሮ ገንዘብ መቀበል አቁም ለአንተም ጥሩ
አይደለም " አለችው መርማሪው
" ይሀውልሽ ሄጄ አላስገድዳት አልቀማት አልዝረፋት ወዳ ፈቅዳ ከሰጠችኝ አንቺ
እንቢ ትይ አይደል እሺ እኔም እላለው ትቀልጂያለሽ እንደውም አጠናክሬው ነው
የምቀጥለው " ብሏት ከሰላም ጋር ወጥተው ሊሄዱ የበሩን እጀታ ሊይዙ እና
ሊከፍቱ ሲሉ የመዓዛ ባል ከፍቶ ኬብሮንና ሰላምን አያቸውና ገፍትሮዋቸው ሲገባ
ኬብሮን ወደ ውጭ ሲወጣ ሰላም ሰውዬውን በቆመችበት ሆና በአይኗ
ተከተለቺው።
" ልጁ የት እየሄደ ነው እየፈታቹሁት ነው እንዴ?" አለ ሰውዬው በመገረም ሰላም
ለመውጣት ብላ ቆመች።
ውጭ ደግሞ ኬብሮን ማክዳን ከተደበቀችበት ጠራትና ከዚህ ማንም ሳያያት
አሁኑኑ እንድትሄድ ከታየች ግን ጥሩ እንዳልሆነ ነገሯት ቶሎ እንድትሄድ አስረዳት
ትንሽ ካገራገረች በኋላ በእሺታ ተለያዩ።
" አዎ ተለቋል እሺ " አለች በምርመራ ክፍል ወስጥ የተቀመጠችው ሴቷ
መርማሪ አለችው ሰውዬው በጣም ተናዶ መርማሪዋን ሌላ ጊዜ ሰላምንና ወደ
ወደ በሩ ሲመለከት ኬብሮን መጥቶ በሩ ላይ ቆመ ያየዋል ።
" እንዴት ተብሎ ነው እዝች ሀገር ጋር የሚኖረው እየተዘረፍን እየተቀማን
ወንጀለኞች የሚለቀቁባት እቺ ሀገር ነች " አለ
" እኔ የምልህ ጌታው ከሚስትህ ጋር በአንድ ወር ውስጥ ከሚስትህ ጋር ስንቴ
ትተኛላቹሁ ?" ሰላም ጠየቀቺው ሰውዬው በግርምት እሷንም ፖሊሶቹንም አየና።
" እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ትጠይቃለሽ እኔ እኮ የቢዝነስ ሰው ነኝ ከወር
በላይም አብረን ሳንተኛ ልናሳልፍ እንችላለን ይሄ ምን ችግር አለው ሚስቴ እኮ
ነች" አለ በግርምት።
" አዬ አንተ ሰውዬ ትሰማለህ ሚስት ወንጀለኛ አይደለችም ኬቡብ አይደለም
መርማሪ ትልቁ ወንጀለኛ እና መያዝ ያለበት መታሰር የሚኖርበት እሱ ነው" አለች
ወደ ሰውዬው እያሳየች ሰላም ። ሰውዬው በአሽሙር ፈገጌ ብሎ።
" እረ ስሙልኝ በተዘረፍኩ ሚሰቴን በተቀማሁ እኔ ነኝ ወንጀለኛ የተባልኩት
እንዲህ ነች እቺ ሀገር" ሁሉንም እያየ።
" ሰውዬ ሚስትህ የትራስጌህ አሻጉሊት ወይም የምትጎበኝ ቅርስ አይደለችም
የምታስቀምጣት ለምን ትዳር ያስክ እዚህስ መጣ እ እ እቺ ልጅ አያምራትም
አያስፈልጋትም እና አንተ ካልነካሀት ስሜቷን የምታረካበት ወንድ መፈለግ አለባት
እሺ ሰውን ከመክሰስ እራስህን ክሰስ " አለቺው በንዴት
" እረ ተይ እንጂ ክሱን አቁሜ የጭን ውሽማሽን ከእስር እንዳድነው ፈልገሽ ነው "
አላት ሰላም ፈገግ ብላ ወደ እሱ ቀረበችና በጠቋሚ ጣቷ አይምሮው ላይ
እየነካካች።
" በዚህ አይምሮ ቢዝነስ እንዴት እንደምታተርፍ ብቻ ሳይሆን ሚስትህንም እንዴት
መያዝ እንዳለብህ ጠይቀው አሁን ክስህን ተውና ወደ ቤትህ ሄደህ ሚስትህን
እደርባት ይህን ነገር ቀጥልበት እሺ ያኔ የአንተ ትሆናለች።" አለችውና መልስ
ሳትጠብቅ ኬብሮንን ይዛ ሄደች።
በሆስፒታል መኝታ ክፍል ውስጥ ሚጣ ለእናቷ የሆነ ንግግር እየነገረቻት
ሰርካለም በድንጋጤ ትሠማታለች አልፎ አልፎ ሚጣን ትጠይቃታለች
ስትመልስላት ይገርማታል በመጨረሻ በአንድ ነገር ተስማሙ።
" እማ ታዲያ አንቺ ምንም እንደማታውቂ ሁኚ እሺ " አለቻት ተስማሙ
ተጨባበጡ እና ወደ በር ሚጣ በመሄድ ከፈተችና ሚኪን እንዲገባ ነገረቺው
እንደተለመደው ምርኩዙን ዘርግቶ ወደ ውስጥ ሲገባ ሚጣም እጁን ያዘችና
ይዛው ገባች እና የፈለገውን ነገር እንዲጠይቅ ነገረችው ለደቂቃ ዝም ብለው
ሳለ ዶክተር በመግባት ሰርካለምን ደህንነቷን ከጠየቀ በኋላ ወደ ሚካኤሌ
በመዞር አሁን እንደተሻላት እና ውጭ ሆና መከታተል ስለምትችል ተናግረው ዛሬ
ወደ ቤት ውሰዷት አሉ።
የቃልኪዳን ባል ቶማስ በሚያምረው ቢሮ ውስጥ በስራ ተወጥሯል በዚህ ወቅት
ሞባይሉ የጥሪ ድምፅ አሰማ ስራውን እየሰራ ሳያየው አነሳው ።
" ሄሎ የኔ ቆንጆ " አለች ሰላም ሙልቅቅ ብላ ። ቶማስ ደነገጠ እና ሞባይሉን
ከጆሮ አንስቶ ቁጥሩን ተመለከተ።
" ምን ፈልገሽ ደወልሽ ?" አላት ስራውን አቁሞ ለጠጥ እያለ
" ምንም ቶሚ የሆነ ወሬ ሰምቼ ልጠይቅህ ነበር" አለች
" የምን ወሬ ..... እኔ አሁን ስራ ላይ ነኝ ስልኩን ልዘጋው ነው"
" አትዝጋው ያቺ በእኔ የተደሰታቹሁባት ምሽት እያስታወስኩ አሁን ተደውሎ ቃል
ኪዳን አዲስ እየሰራሀው ካለው ቤት ላይ ወድቃ ህይወቷ አለፈ ሞተች አሉኝ "
ስትለው ቶማስ በድንጋጤ ከተቀመጠበት ተነሳና ጮሀ።............
ይቀጥላል..

@lib_wele_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ብቸኝነቴን ...... መልሺኝ😘

🔥ክፍል ሀያ ሶስት (23)
.
.
.
በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ከምርመራ ቢሮ በር ላይ ማክዳ ተቀምጣ በር በሩን
ትመለከታለች። ውስጥ ደግሞ ኬብሮን በመርማሪ ፖሊስ በጥያቄ እያፋጠጡት
ነው መርማሪዋ ሴት ነች በጥላቻ ነው የምታየው ኬብሮን ደግሞ በሄደበት ሁሉ
ሴት የሚያጋጥመው ለምን እንደሆነ ግራ ገብቶታል ።
" አንተ የሰውን ነፍሰ ጡር ሚስት ማስኮብለል አይደብርህም አንተ ወንድ
አይደለህም እሷን ብታገባት ለአንተስ ታማኝ ትሆናለች የእኔ አይጥ የሆንክ ልጅ "
አለችው መርማሪዋ
" እረ በፈጠራቹሁ እኔ አላስኮበለልኳትም " አለ በልመና
" እና እኔ ነኝ ያስኮበለልኳት " አለች በቁጣ እያየቺው።
" እሱንማ እኔ ምን አውቃለሁ"
" ማወቂያህ ይደፈን አሁንም... ስለተደፈነ አይደል የሰው ሚስት የቀማሀው አሁን
እውነቱን ብታወራ ይሻልሀል"
" እሷ ነች ያስገደደቺኝ እውነቴን ነው" ሲላቸው እየተያዩ ሳቁበት እና መርማሪዋ
ወደ እሱ ቀረብ ብላ።
" እስቲ ከመጀመሪያ ጀምሮ አንተ አዲስ አበባ እሷ ክ/ሀገር ሆና የት አጊተሀት
እንዴት ለዚህ በቃቹሁ እውነቱን" አለችው በማስጠንቀቅ።
" እሺ ትውውቃችን በፌስ ቡክ ነው ማን የጓደኝነት ጥያቄ እንደጠየቀ አላውቅም
አንድ ቀን ሰላም አለቺኝ መለስኩላት እኔ በተፈጥሮዬ ሴትን ማወራት ደፋር
አይደለሁም f.b ላይ ሴቶቹ ልታናግራቸው ሀይ ስትል " ምን አባህ ፈለክ "
ስለሚሉኝ እነሱ ካላናገሩኝ ደፍሬ እኔ አላናግርም ስራ ስለሌለኝ ሁሌም ቀንም
ለሊት ኦን ላይን ላይ ነኝ ብዙ ጊዜ አነባለው ፊልም አያለው እንጂ ከሰው ጋር
አላወራም....."
" እኔ የአንተን እንቅልፋም ታሪክ አልፈልግም ከእሷ ጋር ስላለህ ግንኙነት እንጂ "
አለች መርማሪ ቆጣ በማለት።
" እሺ .... እናም ሰላም አልቺኝ መለስኩላት የማወራው ጠፋኝ ዝም አልኳት
ሁለቴ ሶስቴ ስታናግረኝ ጨዋታውም መጣልኝ ባለ ትዳር መሆኔን ጠየቀቺኝ
አይደለሁም አልኳት እሷም ስጠይቃት እንዳልሆነች ነገረቺኝ ጎበዝ ነጋዴ
እንደሆነች ነግራኝ እኔን ስትጠይቀኝ ጎበዝ ቦዘኔ በረዳ አዳሪ አይዞህ እንረዳዳለን
ባይሆን ሸገር ስመጣ ታስጎበኘኛለህ አለቺኝ ከዛ በስንተኛው ቀን 10 ሺህ ብር
ልኬልሀለው ሂድና ከባንክ አውጣ እራስህን ቀይር ቤት ተከራይ ስትለኝ
አላመንኩም ስልኩ እንደተዘጋ ወደ ባንክ እሮጥኩ ይህን ያህል ብር ሰው እጅ ላይ
እንኳ አይቼ አላውቅም ደግሞ እንዴት በአካል ለማታውቀው ይሄን ሁሉ ብር
ትልካለች ብዬ አይምሮዬን እያጨናነኩ ስሄድ ብሩ እውነት ነበር ደስ አለኝ"
" ደስ ብሎህ ተቀበልክ አይደል ?" አለቺው መርማሪዋ
" አዎ እንደ እኔ አይነቱ ሾላካ ድሀ አይደለም የትኛውም ሀብታም ቢሆን እንቢ
አይልም ... እረ ቆይ አንቺ እንቢ ትያለሽ መርማሪ እ?" አላት ኬብሮን
መርማሪዋም ዘወር ዘወር ብላ ሌሎች መርማሪ ፖሊሶችን አየችና በቁጣ።
" ዝም ብለህ የተጠየከውን መልስ እኔን አትጠይቅ አለችው "
" ....... ያኔ በጣም አመሰገንኳት ከልቤ ለእኔ አዝና ስለመሰለኝ ከትንሽ ቀን በኋላ
ለሞባይል መግዣ ብላ 6ሺህ ስትልክ በቃ እንጋባለን ስላለቺኝ ታምኜ ተቀምጬ
አገባታለው አልኩ የስልኩን ከላከች በኋላ ፀባያ ተቀየረ በተደጋጋሚ መሳደብ
ጀመረች ጠቅላላ እስከ ዛሬ 60 ሺህ ይሆናል በተለያየ ጊዜ የላከቺው ግን
በእራሷ ፍቃድ ነው ከዛም ከእኔ ውጪ ሌላ ሴት ብትካ አስገድለሀለው ትለኝ
ጀመር በቃ የገባኝ ብሩን የላከቺወ እኔን በገንዘቧ ለመግዛት እንጂ ከልቧ ለእኔ
አዝና እንዳልሆነ ገባኝ......" ሲላት መርማሪዋ በጩሀት
" ዝም በል ..... ደግሞ በህየወቷ ላይ ተጫውተህ ሌላ ወሬ ታወራለህ ባለጌ "
አለችው ንግግሩን አስቁማው
" እሷ ብር ስለላከቺልኝና በገንዘቧ ልትገዛኝ ፈልጋ እንቢ ስላልኩ በህይወቷ
ተጫወትኩባት አይደል.. እሷስ በእኔ ላይ በፍቅር ስትቀልድብኝ የእሷ ምን ሊባል
ነው ዛሬ የደረሰብኝን ተውትና ባለ ትዳር ሆናም አይደለሁም ማለቷ ልጠይቃቹሁ
እስቲ ፍቅር ወይስ ገንዘብ የቱ ነው ህመሙ ከባድ?" አላት ሌሎቹ መርማሪዎች
መልስ ስጪው አይነት አያት።
በሆስፒታል ውስጥ ሚጣ ዕናቷን በንዴት ታናግራታለች ።
" እማ .... አንቺ ብቻሽን መሆን ከፈለግሽ እሺ እኔ ግን ወደ አባቴ ጋር ልሄድ ነው
ተሽሎሻል አይደል ?" አለች ሚጣ
" አባትሽ ከየት መጥቶ ነው የምትሄጂው " አለች ሰርኬ በግርምት ልጇን
በግርምት እያየቻት
" የትኛው ያ ውሸታሙ እሱማ አይደለም አይሆንም የእኔ አባት እያፈቀርሽው
የውሸት በቁጣ የምታባሪው ሚኪ ነው የእኔ እውነተኛ አባቴ " አለቻት ሰርካለም
ደንግጣ ግራ በመጋባት ስታያት ሚጣ በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀች። ....

ይቀጥላል .....

@lib_wele_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ብቸኝነቴን.... መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ አንድ (21)

ከዳኒ
.
.
.
" የምነግርህ ነገር አንተንማ እደፋሀለው ነገሩ ድሮውንም የሞትክ ነክ እኔን እዛ
አስቁመህ አንተ እዚህ ፍቅር ትሰራለህ " አለች መዓዛ የኬብሮንና የማክዳን ሁኔታ
ተመልክታ ኬብሮን አልደነገጠም ዘወር ብሎ ተረጋግቶ አያትና ።
" አዎ ደስ የሚል ፍቅር እየሰራን ነበር አንቺ ባትደርሺብን ምን አለ ትንሽ ቆይተሽ
ብትመጪ እራቁታችንን ሆነን ስታገኚኝ ያኔ ይበርድልሽና እርግፍ አርገሺኝ ጥለሺኝ
ትሄጂያለሽ " አላት ደረቱን ነፍቶ ማክዳ ገርሟት እያፈራረቀች አየቻቸው።
" መስሎህ ነው መቼም አልተውህም ..... ግን እሷ ምንህ ነች እንዲህ እኔን
እንዳታይ አይንህን የጨፈነችብህ " አለች በዛ ግዙፍ ሰውነቷን ሰበር ሰካ
በረገጠችበት በእግሯ ጎን በጎን ከወገቧ ዘንበል እያለች እያለች ቀረበቺው ።
" ንፁሁ የነበረውን ውሀ አንቺ መጥተሽ አደፈረሺው እንጂ እሷማ በጣም
የምወዳት የምሞትላት ፍቅረኛዬ ነበረች " አላት እሷ በንዴት ወደ እሱ ቀርባ
አየቺው እና በግምት 25 ኪሎ የሚሆነውን እጇን ቦክስ ( ቡጢ ) ጨበጠችና
ጎድጉዶ አጥንቱ የወጣበት ጉንጩን ነረተቺው ከቤቱ ቡሎኬት ግድግዳ ጋር
ተጋጭቶ ተመልሶ ሊወድቅ ሲል ያዘችውና።
" እና እኔስ ምንህ ነኝ አንት ቆሻሻ ግማትም " አለቺው ኬብሮን በአፍ የሞላውን
ደም ወደ መሬት ተፍቶት አየትና።
" ሰው ነው ወይስ መብረቅ የመታኝ እእእእ አላወኩም " አለ ኬብሮን ግራ
በመጋባት ።
" እኔ ነኝ የመታሁሁ ...... አይጡ ቆይ ልድገምህ " አለችውና ባልተመታበት
እሷም ባልመታቺው እጇ ደገመቺው አሁን ግን እንዲወድቅ ለቀቀቺው በቀጥታ
መሬት ላይ ወደቀ።
ሚካኤሌና ሚጣ በሆስፒታሉ ኮሪደሩ ላይ ባለ አግዳሚ ላይ ቁጭ ብለው ሚጣ
አይን አይኑን ስታየው ቆይታ ።
" ጋሼ ቅጥልልኝ መጨረሻው ምን ሆነ ለምን አይነ ስውር መሰልክ ? ግን እመነኝ
ለማንም አልናገርብህም " አለችው በጉጉት እያየቺው ።
" የኔ ልጅ እንደማትናገሪ ስለማውቅ ነው የነገርኩሽ ... አይኔን ብቻ አይደለም
ህሊናዬንም አይቶ እንዳለየ እንዲያልፍ አድርጌዋለሁ ስለዚህ በቃ እናም ብዙ
ነገር አይቼ አይኔ እንደማያይ አልፌዋለሁ " አለ በግርምት ፈገግ ብሎ
" ለምሳሌ ምን ምን?" አላችው ዘወር ብሎ ፈገግ ብሎ አያትና ፀጉሯን እያሻሸ
ለእሷ ሳይነግራት እሱ በሀሳብ ሄደ ።
ሀሳብ ነው ወደ ኋላ ከዓመታት በፊት
ሚካኤሌ ሳሎን ውስጥ የአይነ ስውራን መፅሀፍ በጣቶቹ እየነካካ እያነበበ ትንሽ
ደቂቃ ቆየና ።
" የኔ ፍቅር ምነው ሻዩ እስከ አሁን አልፈላም እንዴ?" አላት
" እረ.... ፈልቷል.. ይ.... ይ ...ዤልህ እየ...መጣሁ .. ነ ው " አለችው ቁና ቁና
እየተነፈሰች በተቆራረጠ ቃላቶች ከዛም ብዙም ሳትቆይ እራቁቷን ሆና ሻዩን ወደ
ፊት ይዛ ከኋላዋ አድማሱ እየወሰለታት ሲመጣ ሚካኤሌ አየና ደነገጠ ግን ያለየ
በመምሰል አንገቱን አቀረቀረና።
" ፍቅሬ ከእኔና ከአንቺ ውጪ ሌላ ሰው አለ እንዴ?" አላት
" እረ የለም .... ምነው ?" አለች እየተሳሳቁ ሙድ ያዝንበት አይነት ፈገግታ ፈገግ
እያሉ።
" አይ ተይው በቃ መሬቱ ክብድ ብሎኝ ነው " አላት እሷ እየወሰለተች ሻዩን ይዛ
አጠገቡ መጥታ ጠረጴዛ ላይ አድርጋ እየቀዳችለት ።
" ምነው መሬትን ተሸከምካት እንዴ " አለች እየሳቁ የእነሱ የወሲብ እንቅስቃሴ
ጠረጴዛው ይንቀሳቀሳል እየተቀጠቀጠች ነው የምትቀዳው ። ሚኪ አየሩን
በአፍንጫው ወደ ውስጥ ጎተት ጎተት አረገና ።
" ጥሩ ጠረንም አይሸተኝም " አለ ግን መልስ ሳይሰጡት እነሱ ዝም ብለው
እየባለጉ ሄዱ ሚኪ መነፅሩን አውጥቶ እንባዎቹን ጠረገ ።
በሌላ ቀን ጠዋት ወደ ስራ ሄጃለው ብላው በኮሪደሩ ላይ ጉርድ ቀሚሷን ከፍ
አድርጋ ሸሚዟን ቀዶት ቁልፍን ነቃቅሎት ጡቷ እየታየ አድማሱ ሱሪውን አውልቆ
ያደርጋሉ ይህንን ተመልክቶ ።
እጅግ የከፋውና ሲያስበው ዛሬም ድረስ የሚያስለቅሰው አንድ ቀን ለሊት
አብረው ተኚተው እያለ ግማሽ ለሊት ሆናል የመኝታ ክፍላቸው በር ሲከፈት ሰማ
ገብቶታል እዛው አልጋ ላይ ወሲብ መፈፀም ጀመሩ ለእሷ ጀርባውን ሰጥቶ ነበር
የተኛው እና ሳታየው ሲያለቅስ ቆየና ሁለቱም ሲያቃስቱ አይምሮው መሸከም
አልቻለም እያየ እንዳላየ ሆነላት ግን እየሰማ እንዴት አለመስማት ይችላል
ድንገት ከተኛበት ተነሳና ቁጭ ብሎ ።
" አሁንስ በዛ ሰላም ከማን ጋር ነው ሴክስ የምታደርጊው?" አላት ። ደንግጠው
ሳይላቀቁ አዩትና አድማሱ ከላያ ላይ ሊወርድ ሲል ወገቡን ጭምቅ አርጋ
እንዳያቆም ይዛው ይለይለት ብላ በጣም እየጮሀች ማረጓን ቀጠለች እሱ
ከአልጋው ወርዶ ማስመሰያ ዱላውን ይዞ እያለቀሰ ከመኝታ ክፍሉ ወጣ።..........

ይቀጥላል ....

@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

11 Sep, 04:05


😘ብቸኝነቴን መልሺልኝ😘

🔥ክፍል ሀያ (20)

ከዳኒ
.
.
.
ሚካኤሌ ፍዝዝ ብሎ ሚጣን ሲያያት እሷም ዝም ብላ እያየቺው ቆይታ።
" እህ ንገረኝ ለምን አይነ ስውር መሰልክ .... ግድ የለህም ለማንም አልናገርም
..... ነው በእራሴ ልማልልህ " አለችው
" እረ እንዳትምዪ በቃ እነግርሻለው ....." አላትና ለደቂቃ በዝምታ ሲያያት ከቆየ
በኋላ ንግግሩን ቀጠለ ".... ሚጣዬ እኔ ወደ አራት የሚጠጉ የትልልቅ ድርጅት
ባለቤት ነበርኩ አይኔም ያያል እና እናትና አባቴ እንዲሁም ታናሽ እህቴ በመኪና
አደጋ ሞተው ነበር የቤተሰቤ አነስተኛ እና አንድ ብቻ የነበረውን ድርጅት ጠንክሬ
ቀን ከለሊት ለፍቼ ሰርቼ ትርፋማ አድርጌ አራት ወጤታማ እና በጣም ትርፍ
የሚያስገኙ ድርጅት አረኳቸው በዚህ ሰአት ብቸኝነቴን የምትጋራኝ ሚስት አገባሁ
። እሷ ለካ ወዳኝ አልነበርም ሀብቴን ንብረቴን ፈልጋ ነበር አንዲት የምታምር ልክ
እንደ አንቺ ልጅ ወለደችልኝ ደስ አለኝ እንዴት እንደምወዳት ልጄን ልነግርሽ
አልችልም በጣም ነው የምወዳት።
የሆነ ጊዜ ጠዋት መኪናዬን አስነስቼ ወደ ስራ ስሄድ ፍሬኑ ተበላሽቶ ነበረና ከሲኖ
ትራክ ትልቁ መኪና ጋር ፍሬዬኑ እንቢ ብሎኝ ተጋጨው የመኪናው የፊት
መስታወት ተሰብሮ አይኔ ውስጥ ገብቶ አይኔን አጠፋኝ።
ሆስፒታል ገብቼ ለረዥም ቀናት ታከምኩ አይኔን እዚህ ማዳን ስለማይችል ውጪ
ሄጄ እንድታከም ታዘዝኩ እና ከሆስፒታል ወጣሁ ። እናም ወደ ውጭ ልሄድ ስል
ድርጅቱን ሀብትና ንብረቱን በውክልና እኔ ላስተዳድረው ብላኝ ሚስቴ
አስፈረመችኝ ከዛ ውጭ ሄጄ ታክሜ አይኔም አይቶ ሰፕራይዝ ላደርጋት ሚስቴን
ስመጣ ወንድሜ ነው ትለኝ ከነበረቺው ልጅ ጋር በቤቴ ፍቅር ላይ ነች ልጄ ብዬ
ያሳደኳትም የእኔ ሳትሆን የእሱ ልጅ መሆኗን ሰማሁ....... ከሀብት ንብረቴ በላይ
የጎዳኝ ልጄን ማጣቴ የእኔ አለመሆኗን ማወቄ ነበር" አለና እንባ በጉንጮቹ
በአራት አቅጣጫ ይፈሱ ጀመር ሚጣም እያየቺው አለቀሰች ወደ እሱ ሄዳ
አቀፈቺው አቀፋት ።
" ጋሼ ከዚህ በኋላ አትዘን እኔ ልጅህ አለው እሺ አታልቅስ ከዚህ በኋላ አባዬ
እልሀለው የአባቴንም ስም የአንተን ነው የምፈልገው ለእማ እነግራታለው "
አለቺው እሱ እቅፍ አርጎ ሳማት ተቃቅፈው ተላቀሱ።
ህይወት መከራ ሴቶች የጋለ ብረት ምጣድ የሆኑበት ኬብሮን መኖርን ጠልቶ
እራሱን ቢያጠፋ በወደደ ነበር ግን ከፈጣሪ ጋር ጠብ ነው እራስን ማጥፋት ብሎ
እቺ ግፍ እየሰራችብት ያለችን የህይወት መንገድ እና ሴቶችን ሳይወድ በግዱ
መጋፈጥን አምኖ ተቀብሏል።
መዓዛ አሁን የመጣቺው ከእሱ ጋር ለመሆን መሆኑን ነግራው ቤት ተከራይተው
አንድ ላይ እንኑር ብላው አልፈልግም ቢልም ሚካኤልን እንደ ምክንያት
ቢያቀርብም እንቢ ብላው እሷ ኮደሚኒየም ተከራይታ ዕቃህውን ሄደን እናምጣ
ብላው ተያይዘው ኮንትራት ታክሲ ይዘው ሄዱ።
በኬብሮን አውቆ እንድትጠላው ሲጋራ በእሷ ፊት በተደጋጋሚ ያጨሳል እሱ
ካልቃመ ለሲጋራ ብዙም አይደለም እረ ሲቅምም ብዙ አያጨስም ግን በቃ አሁን
እሷ በጣም አጫሽና ቃሚ ነው ብላ እንድትጠላው ነበር አልተሳካለትም እሷ
ታየውና።
" ኬቡ ሁሌ እንደዚህ ነው የምታጨሰው ?" አለችው
" ማ እኔ አንቺን አፍሬ እንጂ የዚህን ሁለት እጥፍ ነው የማጨሰው " አላት
የደበራት መስሎት በደስታ።
" አይገርምም እንደዚህ የምታጨስ አልመሰለኝም ነበር ... ማጨሱን አጭስ ግን
እራስህን እንዳትጎዳ " አለቺው በንዴት አያትና።
" አንቺስ?" አላት የእሱ አባባል ጥለሺኝ ትሄጃለሽ ወይ ለማለት ነበር እሷ ግን
ፈገግ ብላ አየቺውና።
" እኔ ምን ላጭስልህ እ ወይ ዘድሮ " ብላው ስትስቅ እሱ በሀሳቡ ።" እኔን
እያጨሺኝ ምን ታጨሺያለሽ " አለ እሷ ንግግሯን በመቀጠል " ኬቡዬ ስትቅም
ግን ደስ ይለኛል .... ለምን መሰለህ ማታ ሴክስ እናደርግ ጀግና ትሆናለህ " ብላ
አፏን ከፍታ ስትስቅ በንዴት እና በጥላቻ አያት የታክሲ ሹፌሩ በንግግራቸው
በግርምት ፈገግ አለና ታክሲውን አቁሞ መድረሳቸውን ነገራቸው ። መዓዛ እዛው
ተቀምጣ እሱ ቶሎ ደርሶ እንዲመጣ ነገረችው እና እሱ ከታክሲው ወርዶ ወደ
ቤት በመሄድ ደረጃውን ወጥቶ በኮሪደሩ ላይ መራመድ ሲጀምር ማክዳ ልትወጣ
አለችና እሱ ሲመጣ አይታው መልሳ ስትገባ እየጠራት በፍጥነት በመሄድ
ልትዘጋው የነበረውን በር ያዘባትና ሰላም ሲላት እንዲወጣ ተናግራው ወደ
ውስጥ ስትገባ ተከትሏት ገባና ምን አርጓት እንደሆነ ደጋግሞ ቢጠይቃትም
መልስ አልሰጠቺውም ለምን እንደሚለምናት አልገባውም ግን እንድታናግረው
ወደ እሷ ተጠግቶ ይለምናታል እሷ ጀርባዋን ሰጥታው ዝም ካለቺው በኋላ
በመጨረሻ በንዴትና በጩሀት እንዲወጣላት ተናግራ ፊቷን ወደ እሱ አዙራ
በጥፊ አጮለቺው ደንግጦ ጉንጩን ይዞ ምን እንደሆነች ሲጠይቃት ተመልሳ
በጥፊ ልትደግመው ስትል እጇን ያዛትና ወደ እሱ አስጠግቶ ከንፈሯን ግጥም
አድርጎ ሳማትና ለቀቃት እሷ አፍጣ ስታየው።
" እመቤቴን ማኪ አውቄ አይደለም " አለ ደንግጦ። መዓዛም ተጠራጥራ
ስትከተለው ነበረና በሩ ላይ ቆማ በንዴት ታየው ነበር እነሱ አላያትም።...........

ይቀጥላል....

@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

03 Sep, 16:38


አጫጭር ታሪኮች

https://telegra.ph/ወንድሜ-08-19

ልብ-ወለድ እና ትረካ

03 Sep, 10:47


😘ብቸኝነቴን መልሺልኝ😘

🔥ክፍል 19

ከዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
ሚጣ በግርምት ፍዝዝ ብላ ሚካኤሌን አየቺው ምን እንደሆነ ያላወቀችው
የግርምት ይሁን የደስታ ፊቷ እየፈካና እየበራ ሄዷል እሱ ደግሞ በድንጋጤ አይኑ
ፈጦ ተመለከታት። ሚጣ በንገረኛ ፊቷን ነቀነቀች ።
" ሚጣዬ አንቺ እኮ የሰማሽውን ያየሺውን ቆልፈሽ በሚስጥር ማስቀመጥ
አትችይም " አላት ፈገግ እያለ።
" ጋሽዬ ስለ መልካም ስራህ አንተ ማሳወቅ ባትፈልግም እኔ ግን ከፈጣሪ በታች
ህይወት የሰጠኝን ሰው የአለም ህዝብ ሁሉ ቢያውቅልኝ እደሰታለው ለእኔ
ህይወት ለእናቴ እና አስቴ ሰላምን ሰጠህልኝ እና ማሰወቄ ስህተት የለውም ጋሼ
" አለች የሆነ ደስ በሚል ፍንክንክ ብላ ለመግለፅ በሚያዳግት....
" የእኔ ቅመም ..... የሆንሽ ... ፍቅር የሆንሽ ልጅ ነሽ አንቺ አለመውደድ በእራሱ
ይቅርታ የሌለው ሀጢያት ነው " አለና ወደ እሷ ሄዶ እቅፍ አርጎ ጉንጯን ሳማት።
" ጋሽዬ የምን ቅመም የወጥ ነው....... ልትሸውደኝማ አትሞክር ንገረኝ ......
አሁን አይኔ አያይም ብለህ ለእኔ እንደምታይ ብትነግረኝ የደበክበት ምክንያት
ስላለህ እኔ ልሙት ለማንም አልናገር " ስትለው ኮስተር ብሎ ሚኪ አያትና ።
" ከዚህ በኋላ ሚጣ እኔ ልሙት ብለሽ ስትምዪ እንዳልሰማሽ እሺ እኔ ክፍት
ይለኛል እሺ እና .... እኔ አያለው እሺ
" እኔ አላምንም ...... ወይኔ ታዲዬ ...... እኔ እኮጰአሁን ወደ እኔ ጋ ስትመጣ
ጠርጥሬያለው ..." አለችና በደስታ እየጮሀች ስታቀፈው አፏን ያዘና እናቷን
አሳያት ከዛም ዝም አለች ሳመቺውና።
" ጋሼ እማ ለምን እንደምትቆጣህ ታውቃለህ...... አታውቅም አይደል እኔ ግን
አውቃለው" አለችው ደነገጠ ሚኪ አያት
" .... እእእእእ ለምንድን ነው? " አላት በግርምት እያያት
" እኔ ነኛ እንደምታፈቅራት ነግሬያት " አለች እሱ ደነገጠ ገረመው ፈገግ ብሎ
አያት ።
" በምን አወቅሽ ወይስ ማን ነገረሽ ?" አላት ሚኪ
" የአንተ ሁኔታን ዝም ብዬ ጠረጠርኩና ለምን አላጣብሳቸውም ብዬ ዘይት
ሳላበዛ ምጣድ ላይ አርጌ ለመጣበስ ሞከርኩ ሳስበው እሷም ጠበሳው
የተስማማት መሰለኝ " አለች ሚኪ ግራ ገብቶት በዝምታ አያት።
ልባቸው ሊፈነዳ የደረሰ ይመስላል ቁና ቁና ይተነፍሳሉ። መርፌ እና ክር ከሆኑበት
ተላቀው በጀርባቸው ከአልጋው ላይ ተንጋለሉ።
" አንተ.....እራስህን ገለህ እኔንም ልትገለኝ ነው እረ በቃ .... አልጋዬንም
ልትሰብረው እኮ ነው" አለች ሰላም በተደጋጋሚ በስሜት ከጨፈረባት በኋላ
ደክሟት በተቆራረጠ ትንፋሽ።
" ቆራጥ እንዳልሆን ያረገኝ ይሄ አማላይ ገላሽ አይደል ክፍያዬን የማውቀው እሱን
በደንብ አድርጌ ስደበድበው ነው"
" አንተ የተረገምክ ነህ ባክህ " አለችው
" ከአንቺ የበለጠ የተረገመ ሰው አለ እንዴ ? ..... የሚገርመኝ ይሄ ከፈጣሪ በላይ
የምትመኪበትን ገላ ብታጪ ምን ልትሆኚ እንደምትቺዪ ሳስብ ይገርመኛል" አላት
ሰላም ከምር ተናደች።
" ትሰማለህ በውበቴና በገላዬ ማንም ሲመጣብኝ አልወድም ከዚህ በኋላ
እንዲህ እንድትለኝ አልፈልግም እሺ" አለች
" እረ ቀስ ..... እረ ቀስ...በቃ ይቅርታ እና ግን ለምን ነበር የፈለግሺኝ ዋናው
ቁም ነገሩ እሱ ነው አይደል?" አላት
" ነበር ቃልኪንን ከዕነ ባሏ መግደል ወይም አካለ ስንኩል ማረግ ግን አሁን
ሳስበው ከእነሱ በፊት አንተ የእነሱ እጣ ሊደርስህ ይገባል" አለችው ሰላም
እውነቷን ነበር በውበቷ በመተማመኗ ማንም ክፍ መናገር አይደለም እራሷ
ለእራሷ ክፍ ማሰብ አትፈልግም ።
በሆስፒታል ኮሪደር ላይ መዓዛ ተቀምጣ ኬብሮን ከግራ ወደ ቀኝ ይዟዟራል ።
በሀሳቡ " ቆይ ማን ነው የተረገመው እኔ ወይስ እቃዬ አልገባኝም ...... ምን
አለበት ሽንት የምሸናበት ተከፍቶ ከሴት ጋር የምገናኝበትን በደፈነው ..." ሲል
ቆየና ፊት ለፊቷ ቆሞ መዓዛን አያት ። መዓዛ ከእሱ ዕድሜ ቢያን 7 አመት
ትበልጠዋለች ታላቅ እህቱ እንጂ ሚስቱ አትመስልም አያት አትኩሮ ።
" ይቅርታ መዓዚ አንዴ ሽንት ቤት ሽንቴን ሸንቼ ልምጣ " ብሏት ወደ መፀዳጃ ቤቱ
ሊሄድ ሲል ።
" የት አባህ ነው የምትሄደው ስንቴ ነው ሽንትህ የሚመጣው በ5 ደቂቃ ሀያ ጊዜ
እንዴት ሽንትህ ይመጣል ... ና ቁጭ በል"
" እረ ዛሬ ነው የእኔ መሽናት ያሳሰበሽ ያኔ ስሸና ምነው ተው አትሽና ባልሺኝ ነበር
.... እኔን ለማሳበድ ሴቶች ብቻ ሳትሆኑ የእራሴውም እቃ ተፅኖ ፈጥሮብኛል ....."
አለና ግራ ገብቶት መሄጃ ሲፈልግ የመዓዛን ስም ተጠራና አንዲት ነርስ ወደ እሷ
በመምጣት አጠገቧ ስትቆም ኬብሮንም ለመስማት ጓጉቶ አጠገባቸው ቆመ።
" እንኳን ደስ አለሽ ወሮ መዓዛ ..." ስትል ኬብሮን በፍጥነት እጁን ዘርግቶ
የነርሷን በግድ ይዞ ጨበጣትና።
" እንኳን አብሮ ደስ አለን ..... እርጉዝ አይደለችም አይደል " አለ ይህንን ነበር
የፈለገው።
" አይ አይደለም ነፍሰ ጡር ነች ... የወንድ ልጅ እናትና አባት ልትሆኑ ነው ደስ
ይላል " አለች በፈገግታ
" እረ ኡኡኡኡኡኡ ..... እንኳን ደስ አላቹሁ ወይስ እንኳን ተረገማቹሁ " አለና
የነርሷን እጅ እንደያዘ መሬት ላይ ዝርፍጥ ብሎ ቀመጠ ።.............

ይቀጥላል....

@lib_weled_ena_tireka
@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

03 Sep, 10:42


😘ብቸኝነቴን መልሺልኝ😘

🔥ክፍል 18

ከዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
የኬብሮን ጭንቅላት መብረቅ እንደወደቀበት ለሁለት ተከፈለ ከፍራሹ ላይ ቁጭ
አለ መልሶ ተነሳ ተመልሶ ቁጭ አለ እንደገና ተነሳ ማክዳ ልቧ እንደ ክምር በረዶ
በየማይክሮ ሴኮንዱ ሲቀልጥ ይሰማታል አይኗ በሀዘን ተስፋ በመቁረጥ
የቀለጠው ልቧ ሀዘኑን በአይኗ በኩል በእንባ መልክ ያፈሰው ጀመር።
" አታሹፊ እንጂ መዓዛ .... እውነት ነው ከእኔ አረገሽ ?" አላት ግራ ገብቶት
የሚገባበት ጠፍቶት ጭንቅ ጥብብ ብሎት።
" ምን ለማለት ፈልገህ ነው ከሌላ ወንድ ተኛሽ ኤያልከኝ ነው አንተ... አንተ
የማትረባ እእእ" አለችው መዓዛ በንዴት እያየቺው ወደ እሱ ለመቅረብ ጠጋ
ስትል።
" ቆይ መአዚ እዛው ሁኚ..እኔ ሌላ ወንድ ጋር ሄድሽ አላልኩም ግን አንድ ቀን እኮ
ነው አብረን የተኛው እንዴት ሆነ ብዬ"
" አዎ አንድ ቀን ነው አንተ ጨዋ ነህ ዝም ብለህ ነው የተኛሀው...... ሙሉ ለሊት
ዘፈን እንደተከፈተልህ ስትጨፍርብኝ አይደል እንዴ ያደርከው ?" አለችው
በግርምት እያየቺው።
" እናቴ ትሙት እረ እኔ ጭራሽ ጭፈራ አልችልም .... ግን ወሲብ አድርገናል አዎ
ትዝ ይለኛል ግን ጭፈራ ..." ብሎ ሊደግመው ሲል ከት ብላ ስትስቅበት
ንግግሩን አቆመ።
" ታዲያ ጭፈራ ማለቴ ወሲቡን አይደል እንዴ? "አለችው ከሳቀችበት በኋላ
እሱም መዓዛን ካያት በኋላ ዘወር ብሎ ማክዳን ሲያያት እያለቀሰች እሷም
አየቺውና በሩን በመክፈት ወጥታ ስትሄድ እሱም በዕፍረት አንገቱን ደፍቶ።
" ነው ላካ ስደነግጥ ስለምረሳ እንጂ ጭፈራ ገብቶኝ ነበር እኮ " አላት እና ወደ
ሱሪው ዚፕ ተመለከተ ንብረቱን አሰበ።
የሳላም ባል አድማሱ አንድ አንስተኛ መኪና የተጎዳች ወደ 10 ሰዓት ገደማ
እየነዳ ከሰላም ቤት ግቢ በራፍ ላይ ሲደርስ ትላክስ አደረገ ጥበቃው ከፈተለት
ሰላምታ ሰጠውና ወደ ውስጥ አስገባው ወደ ሶስት ከሚጠጉ ዘመናዊና
የሚያምሩ መኪናዎች ጀርባ አሸማቆት የራሱን መኪና አቆመ እና በመውረድ ወደ
ቤቱ ሄደ በመሄድ በሩን በዝግታ ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ ሳሎኑን በአይኑ አማተረ
ማንም የለም ቆሞ በአይኑ ሲማትር ከመኝታ ቤቷ በሌሊት ልብስ ሰላም
በመውጣት ።
" ሀይ ... ና እዚህ ነኝ " አለችውና ወደ መኝታ ክፍሏ ስትገባ እሱም በመሄድ በሩ
ላይ ቆሞ ተመለከታት እሷም ቢጃማዋን ሙሉውን በማውለቅ እንደ አልማዝ
የሚያንፀባርቀውን ገላዋን እንደፍጥርጥሯ ካለ ምንም መሸፈኛ ጨርቅ
አሳየቺው።
" አሀሀሀ ና ብለሽ የደወልሺው ለእዚህ ነበር ያ ማለት ችግር ውስጥ ገብተሻል
ማለት ነው አይደል?" አላት
" እሱን በኋላ እናወራለን አሁን ናልኝ በሩን ዝጋውና ተርቤያለው ሰው ተርቦ እኮ
አያወራም " አለቺው እሱም ይሄን እያየ መመለስ አልፈለገም እንደ ዘዶ
ተወርውሮ ተጠመጠመባት እና ተያይዘው ከአልጋው ወደቁ።
ቁልቁል አቀርቅሮ ወደ ሱሪው እየተመለከተ በንዴት፡
" አንተ የተረገምክ ከ5 ዓመት በላይ አንገትህን ከሽንት ውጪ ምንም ሳትፈልግ
ሳያምርህ አርፈህ ኖረህ ያኔ ምን አባህ ልሁን ብለህ ነው እኔ ነኝ ወንዱ ብለህ
ዘራፍ ብለህ ቀና ያልከው እ..እ ..ተናገር አንተ የተረገምክ ነገሩ መረገምክ ከሱሪ
እና ከፓንት ስር የወሸቀህ አሁንም ከዛው አትወጣ የሰው ታምር ይሰራል የእኔ
ታምር ታሰራብኛለህ...." እያለ የእራሱን ንብረት ሲረግም ።
" አንተ ደደብ ምን አባህ ነው የምትለው እ?" አለችው መዓዛ
" እህ ምን አልኩ ምንሽ ላይ ደረስኩ የአንቺ ጋር አልደረስኩ የእራሴንም መርገም
አልችልም እንዴ ?..... ይሄ ጦሰኛ ምናለ ፈጣሪ ወደ እዛ ቆርጦ ቢጥልልኝ......
ውይ ጌታዬ ይቅር በለኝ ደግሞ በምኔ እሸናለው .... ውይ ... ውይ " አለ በምሬት
" አንተ እውነትም ደደብ ነህ አንተ ባትፈልገው እኔ እፈልገዋለው ከአንተ ልጅ
መደገም እፈልጋለው " ብላ በዛ ጉዙፍ ሰውነቷ ዘላ ተከመረችበት አልቻላትም
ተያይዘው ፍራሹ ላይ ወደቁ።
ሰርካለም በምትታከምበት ሆስፒታል በመኝታ ክፍል ውስጥ ሚጣ ወደ እና
ሚካኤሌ ወደ ቤት አንሄድም ብለው ውሎም አዳራቸውም እዚሁ ከሆነ ቆይቷል
ግን ለሚጣ ጥሩ ሆኗል ሚካኤሌ የሆስፒታሉን ሀላፊ አናግሮ ለእሷም አልጋ
ከእናቷ አጠገብ እንዲሰጣት አድርጎ ለልቧ ክትትል እንዲያደርጉላት አርጓል።
አሁንም ከእናቷ አጠገብ በጉና ተኝታ በጀርባዋ በህክምና መሳሪያ ተከባ
የተኛችውን እናቷን እያየቻት ሳለ በሩ ሲከፈት የተኛች መሰለች አንዲት ነርስ
በእጇ የመዳህኒት ማዘዣ ወረቀት ይዛ ገባች ሁለቱንም አየቻቸውና ወረቁቱን
አልጋው ላይ አርጋ ልትወጣ ስትል ሚካኤሌ ከመፀዳጃ ቤት እየወጣ ::
" ሲስተር እዚህ ነኝ " አላት እሷም መድሀኒት እንዲገዛና ወረቀቱን አልጋ ላይ
ማረጓን ነግራው በሩን ዘግታ ሄደች እሱም ቀጥታ በመሄድ ወረቀቱን አንስቶ
ሲያይ ሚጣ በጨረፍታ በግርምት አየቺውና ተነስታ ቁጭ አለች አልጋው ላይ
እሱም አያትና።
" ተነሳሽ እንዴ ሚጣ " ሲላት ደንግጣ
" ጋሼ ሚኪ ማየት ትችላለህ እንዴ " አለችው እሱም ቀድንጋጤ ዞሮ አያት። .......

ይቀጥላል....

@lib_weled_ena_tireka
@lib_weled_ena_tireka

ልብ-ወለድ እና ትረካ

03 Sep, 10:41


​​😘ብቸኝነቴን መልሺልኝ😘

🔥ክፍል 17

ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
ሚካኤሌ ለትንሽ ደቂቃ በሩ ላይ ቆመና ሲያያቸው ቆየና ሚጣ በመነሳት ሄዳ
እጁን ይዛ ወንበሩ ላይ አስቀመጠችው ለደቂቃ በዝምታ ቆየና ።
" መሽቷል ማክዳና ሚጢ ለምን በኮንትራት ታክሲ አትሄዱም " አላቸው ሚካኤሌ
ግን ሁለቱም ለመሄድ ፍቃደኛ አልነበሩም
" ምን እንደተባለች ለምን አትነግረንም " አለች ማክዳ
" እሺ ምንም በሽታ የለባትም " አለቸው ሚካኤሌ
" እና ምን ሆና ነው " አለችው ማክዳ
" አይምሮዋ ከአቅሟ በላይ ጫና መቋቋም ተስኖት ነው እራሷን የሳተችው ግን
በወደቀችበት የጭንቅላት አጥንቷ እና የጀርባ ተሰብሯል ሌላም የተሰበሩ
አጥንቶች እግር እጇ ላይ የተሰበሩ አሉ " አለ እና አንገቱን ወደ መሬት ደፋ።
" ሚኪ ይሄ እኮ ውድ ሆስፒታል ነው ለሜን የመንግስት አንወስዳትም አሁን እኮ
ለዚህ ህክምና በትንሹ 10 15 ሺህ ይጠይቃሉ ....."
" የመንግስት ሆስፒታል መሄዱ ምን ትሩጉም አለው እነሱ ወደ የሚያክሙበት
የግል ሆስፒታል ይልኳታል ስለዚህ እዛ መሄዷ ትርጉም የለውም " አለ ኬብሮን
ድንገት በመሀል በመግባት ።
" ሚኪ ለአልጋና ለህክምናውን ስንት ጠየቁህ በእናትህ ንገረኝ ለምን
ትደብቀኛለህ " አለች ማክዳ በልመና ።
" እነግርሻለው ማኪ ለምን እደብቅሻለው እዚህ ከ15 እስከ 20ሺህ ለጀርባ
አጥንቷ የቻይና ሆስፒታል አለ እዛ ሄዳ መታከብ አለበት " አላት ሚኪ ማክዳ እንባ
አይኗን ሞላው
" ህክምናውን ባታገኝስ ሚኪ " አለች በሚያሳዝን ቃል።
" ለምን ማኪ ? " አለ ሚኪ
" ከየት እናመጣለን ፈጣሪ በእኛ ላይ ጨክኖብናል የምንበላው ሳይኖረን በሽታ
በበሽታ አድርጎን የምንጠየቀው ብር ደግሞ ከእኛ አቅም በላይ ሆነብን ምን
አይነት ሀጢያት እንደሰራን አላወቅም ግን ጨክኖብናል " አለች እያለቀሰች
" ተይ ማኪ ፈጣሪን ማማረር ጥሩ አይደለም ለሁሉም ነገር ምክንያት አለው እሺ
" አላት ሚካኤል
" ምን ምክንያት አለው ሚጣንም እግዚአብሔር ይስጠውና ዶክተሩ ከፈለልን
አሁን ማን ይከፍለዋል ?" አለች ማክዳ
" እረ ማኪ ዶክተሩ እኮ አይደለም የከፈለልኝ ሚኪ ነው የከፈለው እኮ " አለች
ሚጣ ሁሉም ደንግጠው ተመለከቷት የሚኪ ድንጋጤ እንዴት አወቀች የሚለውና
ማንም እንዲያውቅ ባለመፈለጉ ነው ማክዳ አንዴ ሚጣን ሌላ ጊዜ ሚኪን
አየችና።
" አንቺ እንዴት አወቅሽ ግን " አለቻት ማክዳ ግራ ተጋብታ
" እራሴን ስቼ በነበረ ጊዜ እሰማ ነበር ዶክተር ማን ይከፍላል ሲሉ ሚኪ ደግሞ
እኔ እከፍላለው ግን ማንም እንዳያውቅ ሲል ሰምቼያለው " አለች ሚጣ ማክዳ
በድንጋጤ ሚካኤሌን ስታየው እሱ አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ ነበር።
ቃልኪዳን የሆቴሉን መኝታ ክፍል በር ላይ ቆማ ተመለከተቻቸው ሁለቱም
ከወገባቸው በላይ እራቁታቸውን ነበሩ የሰላምን ፈገግታ አየችና እሷም ፈገግ
ብላ።
" በጣም የምወድህ እና የማምንህ ባሌ መጣሁልህ " አለችው እሱም ፈገግ
ብሎ ሰላምን ለቆ ወደ ሚስቱ በመሄድ ተቃቅፈው ከንፈሯን ሲስም ሰላም ደንግጣ
ስታይ።
" አንቺ አንድ ሺህ ዲያቢሎስ አንቺን ሴራ ቀድሞ ታማኙ ባለቤቴ ነግሮኛል አንቺ
የእኛን ትዳር ለማፍረስ ያሴርሽ መስሎሻል ግን እኛ ነን በአንቺ ያሴርነው ... ነይ
ውጪ ዛሬ ውርደትሽን ትቀምሺያለሽ ... " አለችና ከባሏ ጋር በመሄድ እራቁቷን
እንዳለች ከአልጋ ጎትተው አውረደዋት መሬት ለመሬት እያፏቀቁ ወደ ዋናው
መዝናኛ በርካታ ህዝብ ወደ ተሰበሰበበት ወስደዋት በሁሉም ሰው ፊት እራቁቷን
እንዳለች አቁመዋት ሴራዋን ያደረገችውን ሁሉ ህዝቡ ግማሹ የሚጠጣውን
ሲደፍባት ሌላው በጠርሙስና በጫማ ሊመቷት ሲሉ ከለከሉና ድራፍቱ ሲደፍባት
መሬት ላይ እጥፍጥፍ ብላ በመቀመጥ እንዴት መበቀል እንደምትችል ታሴር
ነበር።
ኬብሮን ከፍራሹ ላይ ተቀምጦ ጫቱን ሲቅም ማክዳ አጠገቡ ቁጭ ብላ
እያየቺው ።
" መቃም እኔም እፈልጋለው" አለች ማክዳ
" እኔን ለማናደድ ነው ወይስ ..." አለና ዝም ብሎ ሲያያት እሷም ሆስፒታል
እንደምታድር ተናግራ ብዙ ቢከራከሩም እንቢ አላት መጨረሻ ላይ የቤቱ በር
ተንኳኳ ማክዳ ሄዳ ከፈተች አታውቃትም ግን መአዛ ነበረች ገፈተረቻትና
በመግባት ከኬብሮን ፊት ስትቆም እሱ ደንግጦ ተነሳ እሷ በንዴት ስታየው
ቆይታ።
" አንተ ብስብስ ወረዳ እቺ ደግሞ ማን ነች ... እኔን አስረግዘህ ከሌላ ሴት ጋር
አሸሼ ገዳሜ....." ስትለው ኬብሮን ብድንጋጤ ከተቀመጠበት ተነስቶ እያያት
" ምን?.... አስረግዘህ ነው ያልሺው " አለ ሰውነቱ እየተቀጠቀጠ.........

ይቀጥላል....

@lib_weled_ena_tireka
@lib_weled_ena_tireka