ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም @loret_tsegaye Channel on Telegram

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

@loret_tsegaye


📓• ድርሰት ህይወት ነው ።

•|➮ የህይወት ትርጉም ያለው ማንበብ ውስጥ ነው።
•|➮ ማንበብ ውስጥ ራስን ማግኘት አለ
•|➮ ራስን ማግኘት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት አለ
•|➮ ቤተሰብ ውስጥ ሀገር
•|➮ ሀገር ውስጥ ፍቅርን
•|➮ ከሀገር ከቤተሰብ ከፍቅር ከፈጣሪ ከነዚህ በላይ ደሞ ምንም የለም !!

•══════════

📚•|For any promotion • Contact Admin @eyosiii

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም (Amharic)

የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም ቡድን ምንድን ነው? ስለሆነ የቡድን እና መረጃ እንዴት ነኝ? በዚህ ቡድን እንዴት እንደዚህ ላይ እንደሚታወቅ አገልግሎታችሁ ተዝናምና እንደሚመረጡ አስተካክሎ ለእኛ ተመንምኖዋል።nnቡድንሽ ውስጥ የሆነውን ህይወት ስለሚያሳውቅ ያለ መረጃዎችን በቡድን ያግዳል። ቡድንሽ ራስን ማግኘት አለና የራስን ማግኘት አራስን ማግኘትም ይሆናል። በሰጠሽ ቡድን የሚታይ ወንድም ውስጥ ሀገርን ማድረግና የሚሰማ ሀገርን ምንም ላይ ችግሮችን ሲሰማ ሀገርን ባግኝላት እና የአንድ ብሔር ሀገር ሲወለዱ። በምንም የለም!
ምንም አይነታዎችችን ለማግኘት ከሆነሽ ላይ ማንበብ ባለንበት የሚሳሩ ሰዎችን እና የህይወት ስነ-ምግባር ማድረግ በሚለው አስተካካዮ ሀገር ከትግሉ በፊት የማይሇን ሰዎችን ተመልከትለታለሽ። ለማንበብ ስለሚያሳውቅ መረጃዎች ተከታታይ የሚሆኑ ወንድሞቹን ለማንበብ ብለው የሚመልሱን መረጃዎችን እንቀሳቃሽ።nnበቡድን ብሔር ህይወታቸውን የማውቅ ሰዎች ለሆኑ እና በልባቸው ለሚደረግ ለማንበብ ስለሚሆኑ መረጃዎች ያግዳል በዚህ ቡድን በሁሉም የስራ ማህበረሰብን ማስተካከልና በማካተት የሆነውን ልምድ እንጠቀማለን።

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

01 Nov, 13:27


https://vm.tiktok.com/ZMhCYnVfF/

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

25 Aug, 12:52


የፍቅር ቀጠሮ

ጠበቅኩሽ እኔማ እዚያው ሥፍራ ቆሜ
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
እግሮቼን ተክዬ ቀኔን አስረዝሜ
በሔድሽበት መንገድ ልቤ እንደነጎደ
ስንት ነገር መጣ ስንት ነገር ሄደ
ስንት ጊዜስ ነጋ ስንቴ ጎህ ቀደደ
ስንቴ ዝናብ ጣለ ስንት ጊዜ አባራ
ትመጫለሽ ብዬ በቆምኩበት ሥፍራ
ስንቴ አድማሱን ማተርኩ ስንትና ስንት ዓመት
አንገቴን አስግጌ በራስ ዳሽን ቁመት
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
በቀጠርሽኝ ሥፍራ ስጠብቅሽ ቆሜ
ስንት ሳቅ አለፈ ስንትና ስንት ዕንባ
ስንቴስ ክረምት ሆነ ስንቴ ፀደይ ጠባ
ስንቱ ተገናኘ ስንቱ ሰው ተጋባ
ሽል ስንቴ ልጅ ሆነ ስንትስ ጊዜ አረጀ
ስንት ኮት ጨረሰ ስንት እንጀራ ፈጀ
ስንት ዓይነት ሞት አየሁ ስንት ዓይነት ፍፃሜ
በአክሱም ቁመና በላሊበላ ዕድሜ
በቆምኩበት ሥፍራ ስጠብቅሽ ቆሜ?
ስንት ውበት አለፈ ስንት ውበት ነጎደ
ስንት ትውልድ መጣ ስንት ትውልድ ሄደ
ስንት ዕውነት ከፍ አለ ስንት ዕውነት ወረደ
ስንት ዓለም ተሻረ ስንት ዓለም ነገሠ
ስንት ሀገር ተሰራ ስንት አገር ፈረሠ
ስንት ሺህ ዓመት ሸኘሁ ስንት ሺህ ተቀበልኩ
እዚያች ሥፍራ ቆሜ አንችን እየጠበቅኩ
እግሬን አስረዝሜ ቆየሁ ቆየሁና
በላሊበላ ዕድሜ በአክሱም ቁመና
ሳትመጪ ወደኔ ሳላገኝሽ ገና
ብዙ ነገር መጥቶ ብዙ ነገር ያልፋል
የራስ ዳሽን ራስ አንገቱን ይደፋል
አክሱምም ተንዶ እንደጨው ይረግፋል
ላሊበላም ወርዶ ቁልቁል ይነጠፋል
ሰማይና ምድርም ያልፋሉ ታያለሽ
እኔ ግን እዛው ነኝ አንች እስክትመለሽ…

✍️✍️ታገል ሰይፉ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

21 Aug, 17:45


"ህልሜን አላቀልጥም"

ወታደርም ቢባል
ያው በቀቀናም ነው፣
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
አሸናፊም ብትል
ይፈራል ነገውን
ፍርሃት አለው ነውጡ፣
ንጉሠ ነገሥትም
ፍርሃት አለ ቆጡ፣
አንበሳ ደቦሉም
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
ማንኛውም ብትል
ጠልፎ የሚጥል ሰው
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
"ብተወውስ" ብሎ
ይፈራል ታንቲራ፤
እኔ ግን የምልህ
ህልምህን አትፍራ፣
ድፈረው፣ ድፈረው
ወንጀለኛ አይልህም ፍርድ ቤቱ ደፍሮ
አቃቤ ህግ አይከስ፣
እንዲያውም ይፈራል-ይፈራል ወጥሮ
ህልምህን የምተው...
ወመኔ 'ሚዘራው
ገንዘብ ስላጣህ ነው?
ተስፋ ስላጣህ ነው?
ያዘው ግፋ ብሎ
ተስፋን የሚመግብ
ቤተሰብ ነው ያጣህ?
ወይስ ነው ከጀርባህ
ኦና ሆኖ ታየህ?
እኔ ግን የምልህ
እኔ የምመክርህ፣
እንዳትመለስ ነው
ከተስፋ ከእድልህ
እኔ የሚታየኝ
እኔ እንደሚሰማኝ፣
ችግርም ብትፈጥር
በራስህ ላይ ወጥር
ለውጥ አምጣ
ለውጥ አምጣ
ቀን አውጣ
ቀን አውጣ
ችግርና ፍዳህ የመኖርህ ትርጉም
ላብ ነህ ለዚህ ምድር
ወዝ ነህ ለዚህ ዓለም፡፡
ወዝና ጊዜየን በቁሜ ብቀማም
እንደ አሸን ተራግፈው
ጓደኞቼን ባጣም
ወደሁዋላ ስዞር
አንድም ሰው ባይመጣም
ተስፋዬን አልሸጥም
ህልሜን አላቀልጥም፡፡


✍️✍️ ይስማዕከ ወርቁ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

11 Aug, 17:17


https://vm.tiktok.com/ZMrgjKWnn/

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

10 Aug, 18:54


ሞት አያምም

እኖር ብዬ ብታረድም
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡

የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

✍️✍️ በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

06 Aug, 16:10


ፈተሽ እንጋባ

የሰርጌ ቀን መሃላ፣ ሃጥያት ገለመሌ
ኩነኔ ነው ይሄ፣ አመልህ አመሌ
ጡር አለው ምናምን፣ እንዲያ አትበይኝ
ይልቅ ከወደድሽኝ፣ ፈተሽ ተከተይኝ።
"
ደሞ መሃላ ላልሽው
ሳትፈሪ መልሽው
በውነት' ለማገልገል'፣ ለአንዲት አላማ
ምሎ ተገዝቶ፣ በሃገር ፓርላማ
የአምስት መቶ ሰው፣ ማላ ተርከፍክፎ
ሃገር ከተሸጠ፣ ከተሰጠ ታልፎ
ስለ መሃላ ፈርተሽ፣ ለምን መክሰራችን
ሃገር በሸጠ ፊት፣ ፅድቅ ነው ስራችን
ሁሉም በየዘርፉ፣ በመሃላ ከታጨ
ኩነኔ ደርሶበት፣ ፂም እንኳን ካላጨ
የዚህ ሁሉ ምዑር፣ መሃላ ከጠፋ
የምን ኩነኔ ነው፣ ነይ ፈተሽ እንጥፋ።

✍️✍️እንግዳዬሁ ዘሪቱ

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

20 Jul, 15:00


ስርቆሽ

አልመለስ ያለ ትውልድ
አዳኝ መርከቧን ንቆ
በጥፋት ውሃ ሰጠመ
በዝሙት ሃጥያት ወድቆ
ኀላም ውሃው እንደጠፈፈ
ምድርን 'ሀ' ብሎ ሲያቀና
ኖህ በኩራት እንደቆመ
ፍጥረቱን ሰበሰበና
በቅደም ተከተላቸው
በጥምረት እንዳሳፈረ
ከመርከቡ ሊያወርዳቸው
አንድ በአንድ እየቆጠረ
አጋር የሌለው ፍጥረት
መጀመሪያ ያልነበረ
አንድ እንስሳ ትርፍ ቀረ
ለካስ የዝሙት መንፈስ
ከአህያ ጋር ተሳፍሮ
ሚስቱን እየደበቀ
ከፈረስ ፍቅር ጀምሮ
ከማይሆን ተኝቶ ኖሮ
ከመርከቡ እንደወረደ
መሃን በቅሎን ወለደ!

እንግዲህ ከኖህ ጀምሮ
ዘመን ዘመንን አያደሰ
የጥፋት ውሃም የለ
ዝሙትም እዚህ ደረሰ፡፡

✍️✍️ ሜሮን ጌትነት

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

17 Jul, 06:12


https://t.me/BlumCryptoBot/app?startapp=ref_AQuzbg9SD6

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

03 Apr, 16:25


ነግሬሽ ነበረ

ውበት ደም ግባትሽ ፣ ሁሉን ያስደምማል
ከንፈርሽ አየር ነው ፣ በሁሉም ይሳማል
ነግሬሽ ነበረ፡፡
ሰማይ ሚያህል ጭንሽ ፣ ከጭንቅላት ያንሳል
ምን ተራራ ቢያህል...
ጡትሽ አቅመ ቢስ ነው ፣ ሲነኩት ይፈርሳል፡፡
ነግሬሽ ነበረ
ክብረ ቢስ ህይወቶች ፣ ጣፍጠው አይቀጥሉም
የወለዱ ሁሉ ፣ እናቶች አይደሉም፡፡
ነግሬሽ ነበረ
የናትነት ስሟ ፣
ከክብሯ ነው እንጂ ፣ከልጇ እንዳልመጣ
ወልዳም ምንም ነች ፣ ሴት ክብሯን ስታጣ፡፡
ነግሬሽ ነበረ
አትስደበኝ እያልሽ ፣ የነገርኩሽ ሁሉ
ልክ ነሽ አንዳንዴ
እውነቶች ውሸት ፊት ፣ ስድብ ይመስላሉ፡፡

✍️✍️በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

23 Mar, 18:16


ዓለምና ጊዜ

አንዱ ሥፍራ ሲለቅ አንዱ እየተተካ፤
ሁሉም ርስቴ ነች እያለ ሲመካ፤
ሞኝነት አድሮብን ሳናስበው እኛ፤
ዓለም ሰፈር ሆና ህዝቡ መንገደኛ፤
ትውልድ ፈሳሽ ውሃ, መሬቷም ጅረት፤
መሆኑን ዘንግቶ ይህ ሁሉ ፍጥረት፤
ስትመለከቱት በሰልፍ ተጉዞ . . .
ሁሉም በየተራው ያልፋል ተያይዞ።

✍️✍️ከበደ ማካኤል

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

21 Mar, 19:22


ትናንትና ማታ

ላሟሟሽ ሲገባኝ፣እንዳሞሌ አጥቤሽ
በመጨረስ ፋንታ
ለነገ ቆጥቤሽ
አስተርፌሽ ለሰው
የጸጸት ሱናሚ ፤ዓለሜን አመሰው፡፡
ምነው ቢቻል ኖሮ
ፈገግታሽን ቋጥሮ
ሙዳይ ውስጥ መደበቅ
ጃንደረባ ቀጥሮ
ጭንሽን ማስጠበቅ
ክፍት ልቤን ይዤ፤ ዝግ ደጅሽን ጠናሁ
በሰበብ ወድጄሽ ፤ያለሰበብ ቀናሁ፡፡
ፍቅር በተባለ፤ ግራ- ገቢ ነገር
ከጨመተው አገር
ከሰከነው ቀየ
መናፍቅ ይመስል፤ ባዋጅ ተነጥየ
እንደካፖርቴ ቁልፍ፤ ልቤን የትም ጥየ
የትም ስከተልሽ
የትም ሆኖ እድልሽ፤
ሁሉ ያንች ወዳጅ
ሁሉ ባላንጣየ
መፈቀር ሆኖ ጣሽ፤ መቅናት ሆኖ ጣየ
ላንቺ ብስል ፍሬ፤ ለኔ ገለባ ግርድ
ላንቺ እቅፍ አበባ፤ ለኔ እቅፍ ሙሉ ብርድ
ማነው የበየነው ፣ይህን ግፈኛ ፍርድ፡፡

✍️✍️በእውቀቱ ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

20 Mar, 17:10


ጨለማህን አጥፋ

ቁራጭ ሻማ ይዘህ ፣ ካጣህ ክብሪት መግዣ
ወደቤትህ ጠርተህ ፣ ጨለማን በግብዣ
‹‹መሽቶብኛል›› አትበል!
ከፅልመት ይገዝፋል ፣ ሽንፈትን ማባበል
ከእጦት ይከፋል ፣ ጨለማን መቀበል፡፡

ይልቅ….
በፅልመት ከምትኖር ፣ በይነጋል ተስፋ
ከኑሮህ እሳት ላይ፣
ሻማህን ለኩሰህ ፣ ጨለማህን አጥፋ፡፡

✍️ ታገል ሰይፉ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

15 Mar, 06:42


🔔#አዲስ_የሚሸጥ_ቻናል!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📱 39.000 & 31.000 active የሆኑ channel መግዛት የምትፈልጉ
📌 ዋጋ :- በስምምነት
😀 የቻናል አይነት ወደ ፈለጋችሁት👌 መቀየር ትችላላችሁ።

🆘ፈጥናችሁ ኑ!! እንዳያመልጣችሁ!!

➡️@MIKIYAS_WAVE
➡️@MIKIYAS_WAVE

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

07 Mar, 04:35


የወፍ ምክር ሰማሁ

ሌሊቱ ተሽሮ፤  ጀንበር ዳግም ነግሳ
ያንሶላ መግነዜን፥ በጥሼ ስነሳ
አንዲት የንጋት ወፍ ፥ መስኮቴ ላይ ቆማ
እንዲህ ትለኛለች ፤ በሚያስገርም  ዜማ፥
“ እንባህን ቆጥበው ፥ በየጥጉ አትዝራው
መከረኛው እንጂ፤ አያልቅም መከራው”

እድሜ ሲገሰግስ
አብሬው ገስግሼ
ከዚህ ዓለም  ድግስ
ከፍዳው ጠግቤ፥  ከተድላው ቀምሼ
ለኑሮ እጅ ሰጠሁ፤ ከጣየ ተስማማሁ፥
ጠቢባንን ትቼ፤ የወፍ ምክር ሰማሁ፤
እንባየን ቆጥቤ፤ ሳቄን ላበረክት
ወደ ጌጥ ቀየርሁት፤ የቁስሌን ምልክት::

✍️✍️ በእውቀቱ ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

21 Feb, 18:51


ፍቅር_ፈራን

"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን...።
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን

✍️ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

31 Mar, 19:46


ላፕቶፕ ለመግዛት አሰበዋል?

የተለያዩ አይነት ላፕቶፖችን ይዘን እንጠብቆታለን

💻2021/2022 Model new laptops
💻Gaming laptops
💻Slightly and Dubai used laptops

ከ1 አመት አስተማማኝ ዋስትና ጋር

የቴሌግራማችን ቻናላችንን በመቀላቀል የሚፈልጉትን ይመረጡ

https://t.me/joinchat/byKVUnPiXhowN2U0


ይደውሉ
📲 0907 270775
0912 690379

👉አድራሻ:- መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 326

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

31 Mar, 19:25


የፍቅር ቃጠሎ

ጕንጭሽ ፅጌሬዳ
ሞቆት የፈነዳ
ዐይንሽ የጠዋት ጨረር
የበራ ማለዳ።
የማትጠገቢ የስንዴ ራስ ዛላ አገዳ ጥንቅሽ
ጠብ አትይ አንጀቴ ባኝክ ብመጥሽ
ቆንጆ ነሽ አንቺዬ
እሳት ነበልባል ነሽ ንዳድ በአካላቴ
ሆነሻል ሙቀቴ፤ ሆነሻል ሕይወቴ።
የጋለው ትንፋሽሽ
የሞቀው ምላስሽ
ማርኮኝ በከንፈርሽ
እጄን ሰጥቻለሁ።
እስረኛ ሆኛለሁ።
ያንቀጠቅጠኛል ወባ ቅናት ገብቶ
ልቤን አስፈራርቶ ፣ ትኩሳት አምጥቶ።
ፍቅርሽ አቃጠለኝ በመልክሽ ልተክዝ
እቀፊኝ ለቀዝቅዝ ፣ ንከሽኝ ልደንዝዝ።

✍️✍️ገ/ክርስቶስ ደስታ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

26 Mar, 09:40


ናፍቆቴ

ፍቅሬ ብሶ ብሶ መላ ቅጥ ቢያሳጣኝ
ድንገት ለጊዜያት ከጎንሽ ቢያርቀኝ
ናፍቆቴ...
ናፍቆቴ ልበልሽ
ማፍቀሬ ተሰማኝ ላንድ ቀን ብርቅሽ
ሱስ ሆነሽብኛል
አዎ ሱስ ሆነሽብኛል.....
ልቤ ከአንቺ ውጪ ሌላ መች ይመኛል
መረብ ሆኖ ፍቅርሽ አሳስሮ ይዞኛል
ባንቺ እንዴት ልጨክን ሆነሽ የኔ አካል
ናፍቆቴ አልኩሻ
መባዬ አልኩሻ
አይኔ ካንቺ ውጪ ማንንም አይሻ
ያንቺ ሳቂታነት በልቤ ተስሎ
ጀግና የነበረው ፊቴ ከሰል መስሎ
ሸሸ ተደበቀ ኸጥግ ላይ ቆመ ራሱን ከልሎ
በናፍቆትሽ ምክንያት
ንጉስ የነበርኩት ባንቺ የተነሳ አገልጋይ ቢያረጉኝ
....ጀብደኛ የነበርኩት ባሪያ እንኳን ቢያረጉኝ
አንቺን እስካገኘው ሃብታም ቢሉኝ ደሀ ጌታ ቢሉኝ ሎሌ ምንም አይሰማኝ
ናፍቆቴ.....
ናፍቆቴ ሳገኝሽ
ደስታዬን አልችልም እጅሽን ብስምሽ

✍️✍️በ𝐻𝑒𝑛𝑎

#From our subscribers

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

20 Mar, 16:54


ብታውቂ

ስትስቂ!
ጠፈርን እንደምታደምቂ
መንፈስን ካ'ዚም እስራት
እንደምታላቅቂ
ብታውቂ!
ስትስሚ!
አጥንት እንደምታለመልሚ
ታማሚ ልብ እንደምታክሚ
ብታውቂ!
ስታወሪ!
ዱዳ እንደምታናግሪ
መነኩሴውን ከሱባኤ፣
ፈላስፋውን ከጉባኤ
እንደምትጠሪ
ብታውቂ!
እንኳንስ በ'ኔ ልትስቂ
ከራስሽ ጋር ፍቅር ይዞሽ
አይሽ ነበር ስትማቅቂ።

✍️በእውቀቱ ስዩም

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

07 Mar, 04:28


የእያደር ሀገር ህዝቦች

እያደር ይፋጃል፣የጉድ ሀገር ገንፎ
እያደር ውድ ነው፣የጉድ ሀገር ክትፎ
እያደር ይበላል፣የጉድ ሀገር ቴሌ
የጉድ ሀገር ተስፋ፣ይነጋል ነው ሁሌ
ጉድ አንድ ሰሞን ነው፣የጉድ ሀገር ተረት
ለአንዲት ቀን እንኳን፣ጉድ አልቻለም መቅረት
እያደር እንቧ ነው፣የጉድ ሀገር በረት

የጉድ ሀገር ወሬ፣እያደር ሰቀቀን
የጉድ ሀገር ንጋት፣እያደር አንድ ቀን
እያደር እያደር
አድሮ ቃሪያ መሆን፣ወይም ከርሞ ጥጃ
የጉድ ሀገር ምላሽ፣እያደር እኔንጃ
የጉድ ሀገር ፍርሀት፣እያደር ጠብመንጃ

✍️✍️በላይ በቀለ ወያ

@loret_tsegaye
@loret_tsegaye

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን እና ሌሎችም

08 Feb, 05:18


ባለ አንካሳ ልብ ሯጭ

ቅልጥም ለማደንደን ቅቤ ከምትጠጡ
ጋሬጣን ለማምለጥ ጫማ ከምትመርጡ
የልብ ወጌሻ አምጡ
አንካሳ ልብ ያለዉ ምን እግሩ ቢሮጥም
ቢያባርር አይዝም ቢሸሽ አያመልጥም

✍️በእውቀቱ ስዩም


@loret_tsegaye
@loret_tsegaye