የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት @hwgco2012 Channel on Telegram

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

@hwgco2012


የሁልባራግ ወረደ የመንግስት ተራከባት ዡባቦ ክ/ጋር

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት (Amharic)

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በሁልባራግ የሚያስደምርነው ወረዳ ነው። ይህ ወረዳ በአሁኑ በቂ የሚጠቀሙ መንግስታችን ኮሚዩኒኬሽንዎች እና ጉዳዮች ጽ/ቤቶችን ማስገባት ይችላል። ወረዳው ለመመልከት የፕሮጀክት እና መድረስ ተጠቃሚ የሆነ የቴሌግራም እና የኤሌ ሜዳ ቶናል እና አዳዲስ የፕሮጀክት እና መድረስ ጥያቄዎችን በአሁኑ በቂ ያግኙ። ለተጨባን መንግስታዊ ተጠቃሚዎቹ እና ግብረትከላዊ ጉዳዮ ጽ/ቤቶቹ በራሱ ውስጥ እንዲሄድ በማስገባት ማቅረብ እና መርሀዊ እንዲሆን አጋርሟል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Jan, 14:09


በወረዳው ሊካሄዱ የነበሩት የእግር ኳስ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝመዋል❗️

በሁልባረግ ወረዳ ሲካሄድ የነበረው የበጋ ወራት የእግር ኳስ የውስጥ ለውስጥ ውድድር ለነገ ረቡዕና ሀሙስ ተይዘው የነበሩ የጥሎ ማለፍ ጫወታወች ለዞናል ውድድር ዝግጅት (ትሬኒንግ) ሲባል ለሌላ ጊዜ መተላለፋቸውን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ከታላቅ ይቅርታ ጋር ያሳውቃል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Jan, 12:52


የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የ2017 የግማሽ አመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አካሄደ።

ታህሳስ 29/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የ2017 የግማሽ አመት የፓርቲ ስራዎች አፈፃፀም እና የኢንስፔክሽንና ሱፐርቪዥን ግብረ-መልስ እንዲሁም በፓርቲው አደረጃጀትና አሰራር መመሪያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙላጎ ከይረዲን በመድረኩ ባደረጉት ንግግር በቀጣይ አመራሩና አባሉ በፓርቲው የአሠራር መመሪያና ደንቦች ላይ በቂ ግንዛቤ ይዞ መሰራት፣ አዳዲስ አባላትን ማፍራት፣ በየደረጃዉ ያሉ አደረጃጀቶች የዉይይት እና የሪፖርት ልዉዉጥ ስራዎችን በማጠናከር ፓርቲን የመትከል ስራዉ ሰፊ ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኑረዲን መሀመድ የፓርቲውን የአደረጃጀት መመሪያ የያዘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድና የፓርቲውን የ6 ወር አፈፃፀም ለውይይት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። 

በመድረኩም የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች፣ የቀበሌ ፓርታ ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ የመሠረታዊ ድርጅት አመራሮች፣ የወጣቶችና የሴቶች ሊግ አደረጃጀቶና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

06 Jan, 17:13


ታህሳስ 28/2017 
የሁልባራግ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ከወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

በእውቀት ስራ አመራር ዐላማ እና አስፈላጊነት፣ በሰው ሀብት ህጎች፣ በካይዘን ፍልስፍና አተገባበር፣ በአፈፃፀም ስራ አመራር እና የመልካም አስተዳደር መርሆዎች ዙሪያ ለአጠቃላይ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

06 Jan, 16:22


በጤና ጣቢያዎች ለህብረተ-ሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና አክሞ ማዳን የሚያስችል ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ ነው -አቶ ሽፋ ሀምዳላ

ታህሳስ 28/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያውን ሩብ አመት የጤና ጣቢያዎችን አገልግሎት አሰጣጥና የመድኃኒት አቅርቦት ሌሎች ተግባራትን በተመለከተ በጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ሪፖርት በቦርድ አባላት ተገምግሟል።

መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ሽፋ ሀምዳላ እንዳሉት በጤና ጣቢያዎች ለህብረተ-ሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋና አክሞ ማዳን የሚያስችል ለማድረግ የቦርድ አባላት ድጋፍና ክትትል ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በጤና ተቋማት የውስጥ ገቢን በሚያሳድጉ ተግባራት እና በጤና ተቋማት የሚከናወኑ ሙያዊ ሥራዎችን ለተገልጋይ ምቹ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በወይይቱ በተገልጋይ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በፍጥነት ምላሽ በመስጠት እና  የበሽታ መከላከል ሥራን አጠናክሮ ከመስራት ጎን ለጎን ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም ቦርዱ ለጤና ጣቢያዎች የመድሀኒት ግዢ 1.5 ሚሊየን ብር ተጨማሪ እንዲገባላቸው እንዲሁም ተሽከርካሪ በጥገና እንዲጠቀሙ በመወሰን የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የቦርድ አባል ሴክተር መስሪያ ቤት ሀላፊዎች፣ የጤና ፅ/ቤት አመራሮችና የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም የሁሉም ጤና ጣቢያ ስራ-አስኪያጆች በመድረኩ ተሳትፈዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

06 Jan, 11:36


በሁልባራግ ወረዳ የገጠር መንገድን ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ የሚገኘው ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የመሰረተ ልማቶች ሁሉ ቁንጮ የሆነው የመንገድ ስራ ከየትኛው የህብረተ-ሰብ ክፍል በላይ ለአርሶ አደራችን ተደራሽ ማድረጉ ወሳኝ ተግባር በመሆኑ በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል።

በቢለዋንጃ ቀበሌ ባቢሶ ልማት ቡድን በህብረተ-ሰብ ተሳትፎ እየተሰራ የሚገኝ 4ኪሎ ሜትር የመንገድ ጠረጋ ስራ በከፊሉ...

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

06 Jan, 08:39


ታህሳስ 28/2017
የሁልባራግ ወረዳ ፕላን፣ መንግስት ኮሙኒኬሽን እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በጋራ በሴክተር የሪፎርም ተግባራት ዙሪያ ለባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጡ።

ሴክተር መስሪያ ቤቶቹ ዛሬ በጋራ ተቀናጅተው በሴክተር የሪፎርም ተግባራት፥ በሰውሃብት ልማት መመሪያ፣ በካይዘንና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ ከሶስቱም ለአጠቃላይ ለባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናውንም የፅ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተው ያስጀመሩ ሲሆን የፕላን ፅ/ቤት ባለሙያ አቶ አበራ ደርጮና የፐብሊክ ሰርቪስ ፅ/ቤት የሪፎርም ስራዎች ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ያየህራድ አሻግሬ አማኻኝነት የስልጠና ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

05 Jan, 14:40


በስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ የተመራ ልዑክ በሁልባራግ ወረዳ ሻማ ከተማ የወተት ሀብት ልማት ስራ እና በግብርና ፅ/ቤት ግቢ በመስኖ እየለማ የሚገኘውን ልማት ምልከታ አደረጉ።

ታህሳስ 27/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ነይማ ሙኒር በሁልባራግ ወረዳ ሻማ ከተማ በኢንቨስተር ሀጂ ካሚል እየለማ የሚገኘውን የወተት ሀብት ልማት ስራ እና በወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ በመስኖ እየለማ የሚገኘውን ልማት ምልከታ አድርገዋል።

አቶ ዘይኔ በምልከታቸውም በኢንቨስትመንት ዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች የህብረተ-ሰቡን ተጠቃሚነት ሊያረጋግጥ የሚችል ጠንካራ ስራ መስራት እንዳለባቸው በማንሳት፤ የሀጂ ካሚል ጅምር የሚበረታታ እና ከሌሎች ተሞክሮ በመውሰድ የተሻለ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም በግብርና ፅ/ቤት ቅጥር ግቢ የለማው ልማት ለከተማው ነዋሪና በዞኑ በሁሉም ወረዳ ለሚገኙ የግብርና ተቋማት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ስራ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በምልከታው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሀምዳላና ሌሎች የወረዳ አስተባባሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

02 Jan, 15:34


በአመራር እና በፖሊስ መካከል ሲካሄድ የነበረው የመረብ ኳስ ጫወታ በአመራር 3 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ

በዛሬው እለት በወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የመረብ ኳስ ጫወታ የወረዳ አመርሮችን ከወረዳው የፖሊስ አባላት ጋር ያገናኘ ሲሆን ጫጨታው በአመራሮች ሶስት ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጫወታው ብርቱ ፉክክር የነበረበት ሲሆን የፖሊስ አባላት ቡድን ምንም እንኳን በተጋጣሚያቸው በወረዳ አመራር ቡድን ሶስት ለባዶ ቢሸነፉም ተፎካካሪያቸውን ለማሸነፍ ብርቱ ፉክክር ሲያደርጉ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ ሁለቱም ቡድኖች ቀደም ብለው በቂ ትሬይኒንግ ባያደርጉም ጫወታው ሞቅ ደመቅ ብሎ የእርስ በርስ ፉክክር የታየበትና በሁለቱም ቡድኖች ለቀጣይ ለወረዳው ተስፋ የሚሰጡ ተጫዋቾች እንደነበሩበት ማየት ችልናል።

በወረዳ አመራሮች ቡድን በኩል በነበረው የነባር ተጫዋቾች ጥረትና የቡድኑ እርስ በእርስ መናበብ የተነሳ ጫወታውን ሶስት ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል።

ጫወታውን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አወልን ጨምሮ የወረዳ አስተባባሪዎችና የወረዳ አመራሮች፣ የፖሊስ አዛዥና የፖሊስ አባላት እና ሌሎች ደጋፊዎችም በቦታው ተገኝተው ድጋፋቸውን እየሰጡ መመልከት ችለዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

02 Jan, 08:04


''ኬራቴን ለነዋሪዎቿ ፅዱ እናደርጋለን'' በሚል የተጀመረው ሳምንታዊ የከተማ የፅዳት ዘመቻ የመንግስት ሰራተኞች፣ የከተማ ነዋሪዎችና ወጣቶች በተገኙበት ዛሬም ተካሂዷል።

ታህሳስ 24/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

01 Jan, 17:08


ነገ ሐሙስ ነው❗️
''ኬራቴን ለነዋሪዎቿ ፅዱ እናደርጋለን'' በሚል የተጀመረው ሳምንታዊ የከተማ የፅዳት ዘመቻ ነገም ይቀጥላል።

ስለዚህ ነገ ከጧቱ 2:00 ጀምሮ ሁላችሁም ኢክራም የጀበና ቡና ፊትለፊት በመገኘት እንድትሳተፉ የወረዳው ወጣቶችና ስፖርትና የኬራቴ ማዘጋጃ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ።

ታህሳስ 24/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

01 Jan, 16:09


በወረዳችን የሚገኘው አመራር ኮሙኒኬሽንና ሚዲያን ቁልፍ የተልዕኮ ማስፈጸሚያ መሣሪያው አድርጎ ሊጠቀም ይገባል፦ አቶ ሽፋ ሀምዳላ

ታህሳስ 24/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ለሚገኙ አጠቃላይ የወረዳ አመራሮች በኮሙኒኬሽንና በሚዲያ አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል።

አመራሩ ኮሙዩኒኬሽን እና ሚዲያን ቁልፍ የተልዕኮ ማስፈጸሚያ መሣሪያው አድርጎ ሊጠቀም እንደሚገባ የሁልባራግ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሀምዳላ ገልፀዋል።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙላጎ ከይረዲን በበኩላቸው የፓርቲንም ሆነ የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም የልማት ስራዎቻችንን በአግባቡ ለማስፈጸም ሚዲያ ወሳኝ በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀም ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም በአመራሩ የሚዲያ አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን በዝርዝር በማንሳት በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በመወያየት መድረኩ ተጠናቋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Dec, 14:56


የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን በተሻሻለው የኮሚሽን መመሪያ ዙሪያ ለወረዳ እና ለቀበሌ እንዲሁም ለመሰረታዊ ድርጅት ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ስልጠና ሰጠ

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Dec, 14:56


የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የብልፅግና ፓርቲ ቀይ መስመር የሆነውን ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ከውስጥ ሆኖ ማረም የሚችል ብቻም ሳይሆን ፓርቲውን ጠንካራ ፓርቲ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና ይጫወታል- የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሙላጎ ከይረድን

ህዳር 28/2017 ዓ.ም ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን - ኬራቴ

የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የብልፅግና ፓርቲ ቀይ መስመር የሆነውን ሌብነትና ብልሹ አሰራሮችን ከውስጥ ሆኖ ማረም የሚችል ብቻም ሳይሆን ፓርቲውን ጠንካራ ፓርቲ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የጎላ ሚና ይጫወታል- የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሙላጎ ከይረድን፥ ይህንን ያሉት በዛሬው እለት የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ለወረዳና ለቀበሌ አመረሮችና የኮሚሽን አመራሮች የተሰጠውን ስልጠና ባጠቃለሉበት ወቅት ነው።

የሁልባራግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተሻሻለው የኮሚሽን አደረጃጀትና አሰራር መመሪያና በሌሎች ተያያዥ የኮሚሽን መመሪያዎች ላይ ለወረዳ፣ ለቀበሌ እና ለመሰረታዊ ድርጅት ኮሚሽን አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ አመራሮች የስልጠናውን ሰነድ ተከፋፍለው በማቅረብ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን በብልጽግና ፓርቲ የአመራርና አባላት የዲሲፕሊን መመሪያና የአቤቱታ አቀራረብና አፈታት መመሪያ ላይ የኮሚሽኑ ሰብሳቢ አቶ አክመል ጁሃር፣ በተሻሻለው የኮሚሽን አደረጃጀትና አሰራር መመሪያና የግምገማና ምዘና መመሪያ ላይ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጃ ከሊል እንዲሁም በኢንስፔክሽንና ቁጥጥር መመሪያ ላይ የኮሚሽኑ ፃሃፊ ወ/ሮ ነጃት ሳዲቅ ስልጠናውን ሰጥተዋል።

የስልጠናውን መድረክ የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪና የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላጎ ከይረድን፣ የወረዳው የመንግስት ረዳት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኑረድን መሀመድ እና የኮሚሽኑ ሰብሳቢ አቶ አክመል ጁሃር የመሩት ሲሆን በስልጠናው የወረዳ አመራሮችና የኮሚሽን አመራሮች፣ የቀበሌ ዋና አስተዳዳሪና ስራ-አስኪያጆች እንዲሁም ከመሰረታዊ ድርጅት የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢንስፔክሽንና ስነምግባር ኮሚሽንን እንደ ተቋዋሚ ፓርቲ የሚታይበትን የተሳሳተ የግንዛቤ ችግር በማረም የፓርቲውን ክፍተት እየሞላ የሚሄድና ችግሮችን ቀደም ብሎ እያረመ የሚሄድ ዘርፍ መሆኑን የገለፁት የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሙላጎ ከይረድን፥ ዘርፉን የሚመሩ ሰዎች ጠንካራ የሆኑ ብቻም ሳይሆን የፓርቲውን ድክመቶችና ክፍተቶችን ቀድሞ ከውስጥ ማረም የሚችሉና ፓርቲውን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና የሚጫወቱ ነው ብለዋል።

የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽንን በማጠናከር በየደረጃው ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኑረድን መሀመድ፥ ታች ላይ ያሉ የግንዛቤ ችግሮችን በመቅረፍ ኮሚሽኑን ፓርቲውን በሚያጠናክር መልኩ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።

ስልጠናው ከሰልጣኞች በኩል በሀሳብ አስተያየት ዳብሮና ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ ምላሽ በመስጠት መግባባት የተፈጠረ ሲሆን በመጨረሻም ከመድረክ መሪዎች የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ የዘርፉን አመታዊ እቅድ የግብ ስምምነት ከታችኛው መዋቅር የዘርፍ ኃላፊዎች ጋር በመፈራረም የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Dec, 14:13


ህዳር 28/2017
የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የተሻለ አፈጻጻመም ላስመዘገቡ አካላት ማበረታቻ ዕውቅና ሰጠ።

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ዛሬ ባካሄደው የ2016 በጀት ዓመት የሴክተር ጉባኤ አና የ2017 የህብረተሰብ ተሳትፎ መንገድ ንቅናቄ መድረክ ላይየተሻለ አፈጻጻመም ላስመዘገቡ አካላት ማበረታቻ ዕውቅና ሰጥቷል።

በዚህም መሠረት፦
ከቀበሌዎች በመንገድ ስራ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ
1ኛ/ ብርሃን ክትክታ፣
2ኛ/ አምበርቾ ጊምባ ቀበሌዎች ሲሆኑ

ከትራፊክ አደጋ በመንገድ አጠቃቀም ግንዛቤ በማስጨበጥ
ኬራቴ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ሁልባራግ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና ወራበት ሻማ ትምህርት ቤቶች ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የመንግስት ተቋም፣ የግል ድርጅቶች፣ ግለሰቦች በመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ ጉልህ አሰተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን ከዚህም የሁልባራግ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት እና በኬራቴ ከተማ የዛጎል ማደያ ባለቤት አቶ ካሚል ናስር፤ ሸምሱ ነስሬ፣ ሁልፈሞ ረዲ፣ በህሬ መሀመድ፣ ያሲን ሀጂ ከማል፣ አብዱል አዚዝና በህሬ ተማም ይጠቅሳሉ።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

03 Dec, 15:02


ኢንተንጎት/ህዳር 24፤ 2017
የአመሰበይ የላቶዋ ፈየ መቲንዳደሬ ክሼ ላትሪግጦት ቡሊሚ ጉለንተ ጎትተኜ ጃድ አሶት ኢትጌባነኮ ተጬቀመ።

ዩልባራግ ወባጀ ጋር የ4ለኜ ውርት የ46ለኜ ሴረኜ ቡልሻን አውጄ ተረሻን።

ወባጀ ጋሪ የ2017 የ1ለኜ ቂንጥ አይዶ የመቲንዳደሬ ውጥን ከውን ሪፓርት በቡር አቲንዳዳሪ የሐምዳላይ ሽፋ የቀረበይ ሪፓርተ ባጥናቦት አዞፋኒ አሰበታን።

የወባጀ ጋርሚ ወሻሾ፥ የአመሰበይ የላቶዋ ፈየ መቲንዳደሬ ክሼ ላትሪግጦት ቡሊሚ ጉለንተ ጎትተኜ ጃድ አሶት ያትኬሻን በበሎት ወረዳይ የመስኖ ቆት ላለይኤት በመስኖ ብል ጃድ ባሶት ፈየክ አትላቶት ኢትጌባነኮዋ ታራሺ ወባጀ ባሶትም የጥቃቀለ ዲነት ግዞት ኢነብርብያን ባሎን።

ተደነብ ደቺ ተትቅራቀሮት፣ በቀፈት መንግስት የቴንዜ የፋን-1 የመይ ፕሮጀክት ተክታተላት በሶት ተፈጃኒ በብል ደር ኢውላነኮ አሶት ኢትጌባነክ፣ ተብሌቶዋ የኦዲት ሩክቤ ታትግሪግቦት አዘር፣ ተከተመ አቁምስነ በቲንዛዘ ዩንገ ጨረ አቅኖት የከተመ ጡሃረ ቂሮትዋ ግርግቦ ምኖት ያትኬሻነምኮ አዋለኮን።

ሂንኩምገ በአሽር ደረሳይ ውጣታንቾ ሊዮን በጌም ሆነ በከተማ ቆማሬ ጃድ አሶት ኢድጌባነም ቲሉዋ ገነ ገናም ግዝቸ ወሻሾይ ነቀሎኒ በቡር አቲንዳዳሪይ መፍታቼ ታበብያን።

የሁልባራግ ወረዳ ቡር አቲንዳዳሪ የሁርሚ የሐምዳላይ ሽፋ ለነቁ ሱልቸዋ ባላሎ ኪምባየ ቲዮቡ የባሉኮ፥ በወባጀ ጋሪ የነቁ ግዝቸ በውሰዶትት ሌገሬ ያጥቃቅሌነኮ ኤወዶኒ አመሰበይ በላቶ ብልቸ፣ በየፈ መቲንዳደሬ ተፈያጅ ላሶትዋ ቡሊሚ ዙረ አቶታንቾ ለሁኖት ተገነይ ወክት በጠቀለ ሀለት ጎትተኜ ጃድ በትረሶት ደር ኢትረከባን ቲሉ አትፈሀምን።

ዩልባራግ ወባጀ ጋር ቡር አፈ ቡልሻን የፍቃዱይ እንዳለ በፊለኒሙ ወባጃ ጋርቸዋ ወሻሾ ታት ቀበሌ ጃንጎ ቆምሮት አለቢሙ ባሎን።

በቀበላሎ በአንጋሞ፣ በቶዴ፣ በአምበርቾ ጊምበዋ በገናሚ ተአሽር፣ ተፈይነት፣ ተገነ ገነም ያሉ ምካትቸ በወባጀ ጋር ወሻሾ የነቁ ሱር በሱትከ ቲንዞኒ ቢዬድበይማን አትኬዋኚ ቃምቸ አጥሮኒ ፍቶት ኢነብርቢይማነምኮ ኤወዶን።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

03 Dec, 13:48


ማስታወቂያ❗️
በሁልባራግ ወረዳ ኬራቴ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት መሬት በሊዝ ጨረታ የወሰዳችሁ አመታዊ ውዝፍ ግብር እንዲሁም መደበኛ የአፈር ግብር ያለባችሁ የመሬት ባለይዞታዎች ከህዳር 24/2017 እስከ ታህሳስ 11/2017 ባለው አጠናቃችሁ እንድትከፍሉ ማዘጋጃ ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል።

ህዳር 24/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

03 Dec, 13:43


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተዘጋጀው የሴት ምክር ቤት ተመራጮች ኮከስ ረቂቅ መመሪያ ላይ የወረዳው ምክር ቤት አባላት ውይይት አደረጉ።

ህዳር 24/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ ምክር ቤት በ4ተኛ ዙር 46ተኛ መደበኛ ጉባኤው የሴት ምክር ቤት ተመራጮች ኮከስ አባላት የሴቶች ሁለንተናዊ ተሣታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያትት ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

መድረኩን የወረዳው ምክትል አፈ-ጉባኤ አቶ ሸምሱ ጉልታና የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ወ/ሮ በቱላ ላለምዳ የመሩት ሲሆን በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች ላይ ውጤት ለማስመዝገብና ሴቷን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም አጠቃላይ ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅትና በመደጋገፍ መስራት ከሁሉም አካላት ይጠበቃል ብለዋል።

በቀረበው ሰነድ ላይም ተሣታፊዎች አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሴቶችን ለማብቃት ብሎም ወደ ውሳኔ ሰጭነት ለማምጣት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ተጋፍጠን ለማሳካት ትግል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ በማዋቀር መድረኩ ተጠናቋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

03 Dec, 11:59


ዩልባራግ ወረዳ ወባጀ ጋር ባውጄይ አያም የጠቀለ ብለ ላሱ ክትበት ጋርቸ የማንሻሸጬ ሹልም ያቦትዋ የታርቶ አትገባት ቲዬድበይማን ቃምቸ አሼ።

ኢንተንጎት/ህዳር 24፤ 2017 ወባጃ ጋሪ አውጄ በባለፈይ ዘማን በሼሽቲሚ ዙራሮ በመቲንዳደሬ፣ በኢኮኖመኜዋ አመኜ ዙረ ቢትረከቦን ክትበት ጋርቸ በሉላሌ ግዝቸ የጠቀለ ብል ባሶት የማንሻሸጬ ሹልም ያበ ቲዮን የታርቶ አትገባትም ተመቲንዳደሬዋ ተፐብሊክ ሰርቢስ ክ/ጋር አሶት አቀተለን።

በመቲንዳሬ አዘር የጠቀለ በከውኖት ሹልም የታበይሙ ክትበት ጋርቸ፦

1ኛ/ አድል ክትበት ጋር 2ኛ/ ፍርድ ጋር 3ኛ/ መቲንዳደርሬ ክ/ጋር

በኢኮኖመኜ ዙረ የጠቀለ ብለ ባሶት የሸለሙይሙ ክትበት ጋርቸ፦

1ኛ/ ገቤ ክ/ጋር 2ኛ/ ትራንስፖርትዋ ኡንገ መትግራገቤ 3ኛ/ ፋይናንስ

በአመኜ ዙረ የጠቀ ብለ ባሶት የሸለሙይሙ ክትበት ጋርቸ፦

1ኛ/ ኢንፎርሜሽንዋ ሳይንስ ቴክሎጂ ክ/ጋር
2ኛ/ ፐብሊክ ሰርቢስ 3ኛ/ ፈይነት ክ/ጋር

በሉልነት ሹልም የታበይ ክ/ጋር ዩልባራግ ወረደ አሽር ክትበት ጋርን

በማስበቼም የሁልባራግ ወረደ ቡር አፈ ቡልሻን የፍቃዱይ እንዳለ ተወረዳይ ቡር አቲንዳዳሪ የሐምዳላይ ሽፋዋ ተፐብሊክ ሰርቢስ ክ/ጋር ወሻይብ ተሆኑይ ተጁሃሪ አክመል የተርቶ አትጋቦት ባሶት መስኒጃይ ተከመላን።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

30 Nov, 19:10


የሁልባራግ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት በባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ቀበሌዎች ማትጊያ አካሄደ።

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ዛሬ ባካሄደው 19ኛ ዙር ጉባኤ በ2016 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ቀበሌዎች ማትጊያ አካሂዷል።

በዚህም መሠረት ከተማሪ ውጤት በማሻሻል፣ ለሀይራንዚ በማሳለፍና በሌሎችም ተግባራት ተሸላሚ ትምህርት ቤቶች፦

1ኛ/ አዘር መረቦ 2ኛ/ ኬራቴ 3ኛ/ ደመቄ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ

ከርዕሰ- መምህራን፦ 1ኛ/ በህረዲን ሸሬ 2ኛ/ሙባሪክ ጀማል፣ 3ኛ/ ኢታላ ደርሞሎ ናቸው። ከመምህራን ደግሞ
1ኛ/ አ/ካፍ ያሲን ከመረቦ ት/ት ቤት 2ኛ/ መሐመድ ሳኒ ከደመቄ ት/ት ቤት 3ኛ/ ወጋየሁ ቅጣው ከኬራቴ ት/ት ቤት ተሸላሚ ሆነዋል።

ተሸላሚ ቀበሌዎች በዋናነት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ፣ ቅድመ መደበኛ ገንብቶ ከማስመረቅ፣ ለመጽሐፍ ሀብት ከማሰባሰብ፣ ከውስጥ ገቢ፣ ከምዝገባ ጋር ተያይዞ፦

1ኛ/ብርሃን ክትክታ 2ኛ/ አምበርቾ ጊምባ 3ኛ/ አምበርቾ አጫሞ ቀበሌዎች ሲሆኑ ከቀበሌ አስተዳዳሪዎች፦

1ኛ/ ዋበለ ሰኪን 2ኛ/ከማል ከድር 3ኛ/ ነስሮ ከድር ናቸው።

ከታማሪዎች በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ያመጡና የተሸለሙ፥
1ኛ/ አብዱልመጂድ በድሩ (ኬራቴ) ውጤት 85.59
2ኛ/ አቡዘር ጀማል (ደመቄ) ውጤት 85
3ኛ/ ሀናን አወል ኢብሮ (ኬራቴ) ውጤት 79.52 ሲሆን

ከ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ፥
1ኛ/ሪድዋን ራመቶ ሁልባራግ 2ኛ ደረጃ በተፈጥሮ ሳይንስ ውጤት 416
2ኛ/ ነቢል ዴተሞ አ/ዬዴ 2ኛ ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ውጤት 356
3ኛ/ ሀምደግባ ሁሴን ሁልባራግ 2ኛ ደረጃ በተፈጥሮ ሳይንስ ውጤት 347 እና
4ኛ/ አብዲቄሲም ከሁልባራግ 2ኛ ደረጃ በተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ዩኒቨርሲቲ አልፈው የተሸለሙ ተማሪዎች ናቸው።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

30 Nov, 16:22


ህዳር 21/2017
በትምህርት ያጋጠማንን ህመም ለመሻገር በባለድርሻ አካላት ባለቤት ሆኖ በተነሳሽነትና በቅንነት መስራት ያስፈልጋል- የሁልባራግ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሐምዳላ

በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት በዛሬው ዕለት 19ኛ ዙር የትምህርት ጉባኤ በተካሄደበት ወቅት በትምህርት ያጋጠማንን ህመም ለመሻገር በባለድርሻ አካላት ባለቤት ሆኖ በተነሳሽነት፣ በቅንነትና ራስን በመስጠት ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የሁልባራግ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሐምዳላ ገለጹ!

በትምህርቱ ዘርፍ ላይ ከተማሪ ውጤትና ጥራት ከማረጋገጥ ጋር በተያያዘ ባጋጠመን ስብራት ታማናል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው የዚህ ህክምናውም በዚህ ጉባኤ ላይ የተሳተፍን ባለድርሻ አካላት ሁሉ ትውልድ ለመቅረጽ በፍላጎትና በመሰጠት የህልና ስራ መስራት አለብን ብለዋል።

በትምህርት ላይ ያለው ስብራት በዚሁ ከቀጠለ የአንድ ጊዜ ትውልድ ሊያጠፋብን ይችላል ያሉት አቶ ሽፋ ሁላችንም የጋራ ውድቀት ነው በሚል በቁጭትና በባለቤትነት መንፈስ ተቀራርበን እና ተቀናጅተን ርብርብ በማድረግ በቀጣይ በውጤት መገናኘት ይኖርብናል ሲሉም ተደምጠዋል።

አክለውም በዚህ ዓመት በትምህርት ቤቶች የምገባ፣ ቅድመ አንደኛ ማጠናከርና የተማሪ ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰው ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለዩ ትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃግብር እንደሚጀመር አንስተዋል።

የሁልባራግ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሪድዋን ያሲን እንደተናገሩት ትምህርት በተሰራበት ያህል ከየትኛውም ዘርፎች በተለየ መልኩ ውጤት የሚታይበት ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

በትምህርት ላይ የተማሪ ውጤትና ሌሎችም ያጋጣሙ ተግዳራቶችን ለመሻገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት የራሳቸው ሚና ቢኖራቸውም አንዳንድ ርዕሰ መምህራን ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት በተጨባጭ አበረታች ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል።

ስለሆነም በሪፎርም አዲስ የገባችሁ ርዕሰ መምህራን በያላችሁበት ቦታ ማርሽ ቀይራችሁ ለውጥ የማምጣት ትልቅ ኃላፍትና የተጣለባችሁ መሆኑን አውቃችሁ በንቃት ይህን መወጣት አለባችሁ ሲሉም ኃላፊው አሳስበዋል።

ለውይይት መነሻ በተማሪ ምገባ ዙሪያ ገለጻ ያደረጉት አቶ ሪድዋን በ11 ት/ት ቤቶች 1 ሺህ 322 ተማሪዎች ለምገባ ልየታ በማድረግ ከ1.4 ሚሊየን ብር በላይ ወይም 163 ኩንታል ዕህል ወጪ እንደሚያስፈልግ ተናግረው ይኼንንም በበጎ አድራጎትና በማህበረሰቡ ተሳትፎ ስኬታማ ለማድረግ መታቀዱን አብራርተዋል።

የተማሪዎች ውጤትን በተመለከተ በባለሙያው በአቶ በህረዲን ሰነድ ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል።

በጉባኤው ተሳታፊዎችም በየትምህት ቤቶቹ ባሉ ተግዳራቶች ዙሪያ በጥልቀት ውይይት በማድረግና በቀጣይ ችግሮችን በቁርጠኝነት በመፍታት ዘርፉን ስኬታማ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ጉባኤው ማትጊያ ተደርጎ ተጠናቋል።

በጉባኤው የወረዳ አመራሮች፣ የቀበሌ አመራሮች፣ ርዕሰ-መመህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

18 Nov, 14:31


የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና ፕላን ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በበጀት ግልፀኝነት እና በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጡ

ህዳር 09/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን - ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና ፕላን ጽ/ቤት በጋራ በመሆን በበጀት ግልፀኝነት እና በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ሰጡ።

የስልጠና ሰነድ በሁለቱም ጽ/ቤት ልማት እቅድ ማለሙያዎች በአቶ አበራ ዶርጮ እና በአቶ ከማል ነስሬ አማካኝነት በዝርዝር ግልፅ በሆነ መልኩ ቀርቦ ከሻይ እረፍት መልስ ስልጠናውን በውይይት ለማዳበር መድረኩ በሁለቱም ጽ/ቤት ዋና ኃላፊዎች ተይዞ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።

የፋይናንስ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ መሀመድኑር አክመል በጀትን ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው የበጀት ጉድለትን በህግ አግባብ የማስመለስ ሂደቱ እንደተጠበቀ ከኦዲት አስመላሽ ኮሚቴ ጋር በመሆን ጉድልት ያለባቸውን ግለሰቦች በመጥራት በድርድር የማስመለስ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።

ዕቅድ የሁሉም ነገር መሰረት ነው ያሉት የፕላን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘይነዲን ረሻድ የፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ለማሻሻል በፕላን ፅ/ቤት ደረጃ ጠንካራ ክትትል እንደሚያደርጉና ለሚያጋጥሙ ችግሮች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሄ እየሰጡ እንደሚሄዱ ገልፀዋል።

በስልጠና መድረኩ የዞን ከፍተኛ ባለሙያዎችን ጨምሮ በወረዳው ከሚገኙ የሴክተር መስሪያ ቤት ልማት እቅድ እና የሰው ሀብቶች እንዲሁም የጤና ጣቢያ ሂሳብ ሰርስተኞች ተሳትፈዋል።

በመጨረሻም መድረኩን የመሩት ሁለቱም ኃላፊዎች ከሰልጣኞች የተነሱ ሀሳብ አስታየቶችን መነሻ ያደረገ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ስልጠናውን አጠቃለዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

16 Nov, 18:05


#እንኳን_ደስ_አላችሁ/አለን!!!

በሁልባራግ ወረዳ በክልሉ መንግስት እየተሰራ ለሚገኘው ፋን-1 የውሃ ፕሮጀክት በ20 ሚሊየን ብር የተገዙ ሁለት ጀነሬተሮች ኬራቴ ደረሱ።

ህዳር 07/2017 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

በሁልበራግ ወረዳ ለዘመናት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ የቆየው ይህ ፕሮጀክት በወረዳው የሚገኙ 05 ቀበሌዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር የሚፈታው ነው።

ከተጀመረ ለብዙ አመታት የቆየው ፋን-1 የውሃ ፕሮጀክት ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተደራጅቶ ከወጣ በኋላ በትኩረት እየተመራ ሲሆን ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮችን በመገምገም ውል በማቋረጥ ቀሪ ስራዎችን ለወላይታ ውሃ ስራዎች በመስጠት እየተሰራ ይገኛል።

ለፕሮጀክቱም መሠረታዊ የሆኑ ሁለት ጀነሬተሮች በ20 ሚሊየን ብር ግዥ በመፈፀም በዛሬው ዕለት ወደ ወረዳችን ማስገባት ችሏል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

07 Nov, 17:53


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በስልጤ ዞን በወራቤ ከተማ በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ድንገተኛ ክትትል አደረጉ!

ጥቅምት 28/2017 ፣ ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን

ክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የተመራ ቡድን በወራቤ ከተማ በተለያዩ ተቋማት እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ስራዎች ላይ ድንገተኛ የመስክ ክትትልና ቁጥጥርን አድርገዋል፡፡

በመስክ ምልከታቸው የወራቤ ጤና ጣቢያ አገልግሎት አሰጣጥ ፣በማቺንግ ፈንድና በዓለም ባንክ በወራቤ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ፣የወራቤ ማዘጋጀ ቤት አገልግሎት አሰጣጥና በስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ እየተገነባ ያለውን የህዝበ መፀዳጃና የገላ መታጠቢያ ቤት ተዘዋውረው ቃኝተዋል፡፡

መረጃው የስልጤ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

25 Oct, 17:17


ለአንበሪቾ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወረዳ አስተዳደር ከ700ሺ ብር በላይ በጀት ተይዞ እየተሰራ ያለውን ፈርኒቸር በሁለተኛ ዙር የመምህራንና የላብራቶሪ ክፍል ወንበር እና ጠረጴዛ ርክክብ ተደረገ

ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን - ኬራቴ

በሁልባራግ ወረዳ ለአንበሪቾ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በወረዳ አስተዳደር ከ700ሺ ብር በላይ በጀት ተይዞ እየተሰራ ያለውን ፈርኒቸር በሁለተኛ ዙር የመምህራንና የላብራቶሪ ክፍል ወንበር እና ጠረጴዛ እስከ ትምህርት ቤቱ ድረስ በመውሰድ ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ዮሴፍ በቀለ ርክክብ ተደርጓል።

ለትምህርት ቤቱ ፈርኒቸር ለማሟላት በወረዳ አስተዳደር ከ700ሺ ብር በላይ በጀት ተይዞ ተሰርቶ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ወንበር የወረዳው አስተዳደር አቶ ሽፋ ሀምዳላ ለትምህርት ቤቱ ኮሚቴዎች ርክክብ ማድረጋቸው ይታወቃል። ይህ የመምህራን እና የላብራቶሪ ወንበር እና ጠረጴዛ በወረዳ አስተዳደር በጀት ተይዞ ከተሰራው ፈርኒቸር የሁለተኛ ዙር መሆኑን ርክክብ ያደረጉት የስርዓተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ወ/ሮ ሮማን ታጁ እና አቶ መርከቡ ዳምጠው ገልፀዋል።

ወንበሩን የተረከቡት የአንበሪቾ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዮሴፍ በቀለ እና ሌሎች የትምህርት ቤቱ መምህራን እንዳሉት በዘንድሮው አመት ትምህርት የጀመረው የአ/2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ እንደሆነና የላብራቶሪ ክፍልን ስራ ለማስጀመር ዛሬ የገባው ወንበርና ጠረጴዛ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

25 Oct, 12:52


ጥቅምት15/2017
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዛሬ በተማሪዎች ጉብኝት ተካሄደ።

የሁልባራግ ሁለተኛ ደረጃ የ10ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች በኮሌጁ በተግባርና በሳይንስ የሚሰጡ ስልጠናዎችን ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ጉብኝት ተካሂዷል።

በጉብኝቱ ተማሪዎች በሁልባራግ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በስድስት የሙያ መስኮች የሚሰጡ ስልጠናዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

የኮሌጂ ምክትል ዲን አቶ ሁሴን በመደበኛ፣ በማታ፣ በሳምንትና በአጫጭር ጊዜ መርሃግብር ኮሌጁ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝና ተማሪዎች የዚህ ዕድል ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።