ኢትዮጵያ ትቅደም @ethiopianfirst22 Channel on Telegram

ኢትዮጵያ ትቅደም

@ethiopianfirst22


ታላላቅ የኢትዮጵያ ታሪኮች የምናገኝበት ቻናል

ኢትዮጵያ ትቅደም (Amharic)

አንድ ቴሌግራም አገልግሎት የኢትዮጵያ ትቅደም ለምንድን ነው? የእስር ቤትን መጠቀም እባክዎ ወደ 'ኢትዮጵያ ትቅደም' ቴሌግራም አገልግሎት በመገለጽ ተመልከቱ! ይህ ቴሌግራም አገልግሎት ተጨማሪ የኢትዮጵያ ታሪኮችን መረጃ ለመስራት ወጣ። ይህ ቴሌግራም አገልግሎት ስነ-ስረኝነትን ለማረጋገጥ ወይፈኛዎቹን ወይዶቢና የዜማ ልዩ ቦታ ብቻ ለመስራት ይሆናል። ምን ያህል እንደሆነ ለመጠቀም እባክዎ ከአሽከርከር እርምጃ በመጠቀም ትቅደም አድርጎ ይጠቀሙ።

ኢትዮጵያ ትቅደም

11 Jun, 08:34


👆Join

ኢትዮጵያ ትቅደም

11 Jun, 08:34


https://t.me/Ethiopianfirst21

ኢትዮጵያ ትቅደም

30 Dec, 06:28


🇪🇹 ጥር እና ቱሪዝም በአማራ ክልል!

#Ethiopia  | ጥር  ወር በአማራ ክልል ውብ እና አጓጊ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ሁነቶች ይስተናገዱበታል።

በወሩ ዋዜማ ማለትም  ታህሳስ 29 እና በአራት ዓመት አንዴ ታህሳስ 28 የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚከበር ሲሆን በልዩ ሁኔታ ከቤዛ ኩሉ ስነ ስርዓት ጋር በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ይከበራል።

በጥር ወደ አማራ ክልል ሲዘልቁ ደግሞ በእጅጉ የተለዬ ወር ነው። የወሩ ቀናት ኹሉ እንደ ክብረ በዓል የሚናፈቁም ናቸው። ጥር ወር በአማራ ክልል እንኳንስ በዓላት ኖረው ይቅርና በሥራ ብዛት የተነፋፈቀው ዘመድ አዝማድ በክቱ ውብ የባሕል ልብስ ተውቦ ለመጠያየቅ ወደ አደባባይ የሚወጣበት፤ የሚጠያየቅበት፣ የሳቅና የጨዋታ ወር በመኾኑ ቱሪዝሙ ድምቅትን የሚላበስበት ነው። በመላው የአማራ ክልል አካባቢ ይሔንን ኹነት ማየት የተለመደ ነው።

ከመጀመሪያዋ ቀን ጀምሮ 30ዎቹም ቀናት ልዩና አጓጊ ድባብ አላቸው። 

🌴ጥርን በባሕር ዳር

በውቡ ጣና ሐይቅ ላይ በልዩ የታንኳ ቀዘፋ እና ጀልባ ውድድር ትዕይንት አይረሴ ትዝታዎች፣ በደብረማርያም ገዳም እና ሰባሩ ጊዮርጊስ ክብረ በዓል፣ የጣና ላይ ጥምቀት እና ልዩ የንግሥ አከባበሮች የምትደምቅባቸው ውብ የቱሪዝም ሀብቶች ናቸው። በውብ ዘንባባዎች ስር የሚደረጉ ደማቅ የጎዳና ትእይንቶች የቱሪዝም ድምቀት ናቸው። ለጥምቀት በዓል የሚደረጉ ዝግጅቶች ከወሩ መግቢያ ጀምሮ በሽርጉድ የተሞሉ ናቸው። 

✍️ ጥምቀትን በጎንደር 

ጎንደርም በጥር ወር የምትደምቅበት ነው። በሰንደቁ ተሞሽራ፣ በጃኖ አጊጣ እዩኝ እዩኝ እያለች የምትጋብዝበት ፍቅር የምታስይዝ ከተማ ናት- ጎንደር። ለጥምቀት በዓል በእንግድነት ወደከተማዋ የሚገቡትን ጨምሮ ከሕጻን እስከ አዋቂ በውብ የባሕል አልባሳት ይዋባሉ። መንፈሳዊ እና ባሕላዊ ክዋኔዎችም ልዩ ናቸው። ከዓመት ዓመትም ጥምቀትን ጠብቀው በከተማዋ ለመታደም የሚናፍቁት በርካቶች ናቸው።  

✍️ ጥምቀትን በኢራንቡቲ 

የጥምቀት በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው  ኢራንቡቲ፡፡ በበዓለ ጥምቀቱ 44 ታቦታት በአንድላይ ሆነው ነው የሚከበረው፡፡ በምንጃር ሸንኮራ ኢራንቡቲ 'ዳግማዊ ዮርዳኖስ' በዓለ ጥምቀት በተለየ ሃይማኖታዊና ባህላዊ  ሥነ ሥርዓት በድምቀት ይከበራል፡፡  በሸዋ ውብ የባሕል አልባሳት የሚዋቡ ወጣቶች የበዓሉ ድምቀት፤ የቱሪዝም ውበት ናቸው።

✍️ ግዮንን በግዮን 

የዓባይ ወንዝ መነሻዋ ሰከላ የምትደምቀው በጥር ወር ነው። የግዮን በዓል በየዓመቱ ጥር 13 በዓባይ ወንዝ መነሻ በልዩ ድምቀት ይከበራል፡፡ ግዮንን በግዮን ወደፊት የአፍሪካዊያን እና የግዮናዊያን (በግዮን ተፋሰስ የሚኖሩ ሕዝቦች) ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ ክብረ በዓል እንደሚኾን አያጠራጥርም። ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ክዋኔዎች ልዩ የበዓሉ ድምቀት ናቸው። 

✍️ አስተርዮን በመርጡለ ማርያም  እና በደረስጌ ማርያም

በኦሪት ዘመን መስዋእት ከሚሠዋባቸው 4ቱ እጅግ ጥንታዊ ገዳማት አንዷ መርጡለማርያም ገዳም ናት። በ333 ዓ.ም በሕገ ኦሪት ፀንታ የዘለቀች፣ ውብ እና ምስጢራዊ ምልክቶችን የያዘ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ባለ ዐሻራ የኾነች፣ የበርካታ ሰማእታት፣ ነገሥታት እና ታዋቂ ሰዎች የክብር ልብሶችና ጌጣጌጦች፣ ቅርሶች ባለቤት የኾነችው ይች ገዳም ጥር 21 ልዩ ክብረ በዓሏ ነው።

በተለይ በንግሥ ቱሪዝም ትልቅ እድገት ያላት በመኾኑ በየዓመቱ  ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ እንግዶች ወደከተማዋ ያቀናሉ። አስተርዮን በመርጡለማርያም ታቦተ ሕጉ ሊቀ ጳጳሳት እና ምዕመናን ታጅቦ የሚከበር በመሆኑ፣ የቅርስ ጉብኝቶች እና ባሕላዊ ክዋኔዎች አጓጊ በመኾናቸው በዓሉን ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲኾን አድርጎታል። 

✍️ አስተርዮን - በግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም 

ግሸን ደብረ ከርቤ ማሪያም ገዳም በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ከቀደምት ገዳማት ውስጥ አንዱ ነው።  ከአምባሰል ከፍተኛ ተራሮች ውስጥ በአንዱ የሚገኘው ግሸን ደብረ ከርቤ የተራራው አናት (አምባ) መስቀለኛ ቅርጽ ያለው ነው። ይህ ቦታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል የሚገኝበት ነው። 

ግሸን ደብረ ከርቤ ማሪያም ገዳም በዓመት ሁለት ጊዜ መስከረም 21 እና ጥር 21 በሚከበሩት በዓላቶቿ በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይታደማል። 

✍️ የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በእንጅባራ

ጥበብ፣ ውበት እና ታሪክ በአንድ መድረክ የሚቀርቡበት ልዩ ትዕይንት ነው። የፈረሰኞች ጥበብ በእጅጉ ያስደምማል። ፈረስ ለአዊ ሕዝብ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡ የጥበብ ማሳያውም ኾኖ የሚታይበት በዓል መኾኑ ተመስክሮበታል። የአዊ ሕዝብ ባሕል በውብ አለባበስና አጨፋፈር የሚደምቅበት ቀንም ነው።

ክብረ በዓሉ የታሪኩ መነሻም የአገውን ሕዝብ ጀግንነት የሚያወሳ በመሆኑ ድባቡን የተለየ ያደርገዋል። የበዓሉ ታሚዎች ክብረ በዓል አይረሴ እና ድንቅ ትውስታዎችን የሚጎናፀፉበት በመኾኑ የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል ወደፊት ትልቅ የቱሪዝም መዳረሻ የሚኾን ነው። ዘንድሮውም 84ኛው የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በጉጉት ይጠበቃል፡፡ 

✍️ መርቆሬዎስን በደብረታቦር  እና እስቴ መካነየሱስ


ፈረሰኛው ሰማዕት ቅዱስ መርቆሬዎስን ለመዘከር የሚከበረው የንግሥ በዓል ደብረታቦርን ከሚያስናፍቁ በዓላት አንዱ ነው፡፡  በበዓሉ የፈረስ ጉግስ ትርዒት  ክብረ በዓሉን በጉጉት እንዲጠበቅ የሚያደርግ ኹነት ነው። ይህ በየዓመቱ ጥር 25 በድምቀት የሚከበር ክብረ በዓል ሃይማኖታዊ ክንውኖቹ፣ ባሕላዊ ወጉ ሳቢ ኾኖ ከዓመት ዓመት የታዳሚዎቹም ቁጥር እያደገ የመጣ ትልቅ የቱሪዝም ሀብት ነው። 

ጥር በአማራ ክልል በእነዚህ እና በሌሎችም ደማቅ ትዕይንቶች ልዩ ወር እንድትኾን አስችሏታል። በርካታ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎችም በጥር ወር ወደ ክልሉ በመዝለቅ በዓላቱን ይታደማሉ።

ጥር በአማራ ክልል የቱሪዝም ጌጥ የኾነ ደማቅ ወርም ነው። በጥር ወር እነዚህን ክብረ በዓላት ለማሳለፍ ከወዲሁ እቅድ ይያዙ።

👉 ከዋሲሁን ተስፋዬ

ኢትዮጵያ ትቅደም

27 Nov, 17:54


መገናኛ በ1940 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ትቅደም

13 Apr, 10:18


#ፀሎተ_ሐሙስና_ጉልባን

👉ጉልባን እና ታሪካዊ ዳራው በቤተክርስቲያን

👉ጉልባን ከባቄላ ክክ፣ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ ጋር አንድ ላይ ተቀቅሎ የሚዘጋጅና የጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ነው

👉የጉልባን ትውፊት እስራኤላውያን ከግብፅ ተሰደው በሚወጡበት ጊዜ በችኮላ ስለነበር አቡክተው ጋግረው መብላት ያለመቻላቸውን ሁኔታ ያመለክታል

👉ያን ጊዜ ያልቦካውን ሊጥ እየጋገሩ ቂጣ መብላት ንፍሮም ቀቅለው ስንቅ መያዝ ተግባራቸው ነበር

👉ይህን ለማሰብ በሰሙነ ሕማማት ቂጣና ጉልባን በማዘጋጀት በዓሉ ይታሰባል በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል፡

👉ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሳል ይህ ትውፊታዊ ሥርዓት ከእስራኤላውያን የመጣ ሲሆን በኢትዮጵያም አብዛኛዎቹ የትውፊት ክንዋኔዎች የብሉይ
ኪዳን መነሻ ስላላቸው ሥርዓቱ ዛሬም ይከበራል

👉ለፀሎተ ሐሙስ እንኳን አደረሰን
@Ethiopianfirst21

ኢትዮጵያ ትቅደም

14 Mar, 13:32


የደንቀዝ ቤተ መንግስት
🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹
ደንቀዝ ቤተ መንግስት በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ከማክሰኝት ከተማ በደጎማ መስመር 28 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ታሪካዊ ቤተ መንግስት ነው፡፡ ቤተ መንግስቱ በ1620ቹ የመጀመሪያ ዓመታት በአጼ ሱስንዮስ የተሰራ ሲሆን አካባቢውን ለመቃኘት ከሚያስችልና በወይራ ዛፍ በተከበበ ማራኪ አምባ ላይ ይገኛል፡፡

አጼ ሱስንዮስ ጎመንጌ አፋፍ ደንቀዝ ላይ ቤተ መንግስት ማሰራታቸው ከአጼ ሰርፀ ድንግል ጀምሮ ሲነገር የነበረውን “ጎ ትነግስ” ንግርት ለመፈጸም እንደነበር ይነገራል፡፡ “ጎ ትነግስ” በ “ጎ” ፊደል በሚጀመር ቦታ ቤተ መንግስቱን የተከለ ንጉሥ መንግስቱ ይረጋል ተብሎ ሲነገር የነበረ አፈ-ታሪክ ነው፡፡

አጼ ሱስንዮስ በደንቀዝ ሁለት የተለያዩ ህንጻዎችን ነበር ያስገነቡት፡፡ የመጀመሪያው ባለሁለት ፎቅ እና ምድር ቤት የነበረው የቤተ መንግስቱ ህንጻ ሲሆን የተለያ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች ነበሩት፡፡ ዛሬም የቤተ መንግስቱ ፍርስራሽ በቦታው ይገኛል፡፡ ሁለተኛው ከቤተ መንግስቱ በግምት 250 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ በመስቀል ቅርጽ የተሰራ ቤተ ክርስቲያን እንደነበር የሚታመን ህንጻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ በውስጡ የሚገኙ ልዩ ልዩ ምልክቶችን በማየት ምንአልባትም በወቅቱ ለነበሩ ካቶሊኮች ሲጠቀሙበት የነበረ ሊሆን እንደሚችል የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።