"…ጠቅላይ ሚንስትሩ የእናንተ ሰፈር ሚኒሻ አይደለም… 👏👏👏👏👏
"…አንተ ንጉሡን፣ አንተ የጌታን ሰው፣ አንተ በንግርት የተገኘህ ድንቁን መሪ፣ በጌታ ቅባት የተቀባህ መልእክተኛ፣ እንዴት ቢደፍሩህ፣ ቢንቁህስ ነው አንተን እንደ አንድ ተራ የመንደር ሚኒሻ ቆጥረው የሚወቅሱህ…?
"…ማንስ ቢሞት አንተ ምን አገባህ የእኔ አትክልተኛ፣ ኮይሻ፣ ወንጪ፣ ጎርጎራ፣ ሸገር ፓርክ፣ እንጦጦ እያለማህ አይደል…? ለምን አዳሜ አይተራረድም። ምን አገባህ አይደል …? ለጊዜው የሚጠይቅህ ደፋር ሰው፣ ደፋር ወታደር አልተገኘም። የሆነ ቀን ግን ከመጣህ ጀምሮ በፈሰሰው የንፁሐን ደም መጠየቅህ አይቀርም። ጋዳፊም፣ ሳዳም ሁሴንም እንዲሁ እንዳንተ ነበር የሚንጠባረሩት። ህዝባቸውም ላይ የሚጨማለቁት። መጨረሻቸው ግን የውሻ ሞት መሞት ነው የሆነው።
"…ስማኝማ ይሄ 3 ሰዓት ሙሉ ሜካፕ ተለቅልቀህ፣ እንደሴት ተቀንድበህ በአደባባይ ልታይ፣ ልታይ ያልክበት "ኡሙንዱኖኢሹ" ፊትህም አንድ ቀን ሜካፕ ቢያጣ ሊመስል የሚችለውን ታውቃለህ። እንዲያ ሆነህ ለፍርድ ስትቀርብ ማየት የዘወትር ጸሎቴ ነው። አይቀርም ደግሞ የግፍ ጽዋው ሲሞላ አይቀርም። ዕድለኛ ከሆንክ ነው የጋዳፊም የሳዳምንም ዕጣ የምታገኘው።
"…ለማንኛውም አዳሜና ሔዋኔ የተሾመለት የደሰኮረውን አማላይ ዲስኩር ሰምተህ አዚሙ ያደነዘዘህ ሁላ የእጅህን እያፈስክ ነው። ዛሬም ድረስ ዐቢይ፣ ዐቢይ የምትሉ የእነዚህ ንፁሐን ደም ይፋረዳችሁ። ሃዘን በቤታችሁ ይግባ፣ ድንኳኑም አይነቀል። አሜን…!! የፈሰሰው የእነዚህ ምስኪን የጋምቤላ ወጣቶች ደም ይታያችኋል…? አዎ ደማቸው ይፋረዳችሁ።
"…እየታረዳችሁ…!!