Sidama Region Health Bureau @sidamarhb Channel on Telegram

Sidama Region Health Bureau

@sidamarhb


Sidama Region Health Bureau (English)

Welcome to the official Telegram channel of the Sidama Region Health Bureau, also known as @sidamarhb! This channel is dedicated to providing the community with important updates, resources, and information related to health services in the Sidama region. Whether you are a resident looking for healthcare facilities, a healthcare provider seeking the latest guidelines, or simply interested in staying informed about health initiatives in the region, this channel is for you. The Sidama Region Health Bureau works tirelessly to promote and protect the health of all individuals living in the Sidama region, through various programs and services. By joining this channel, you will have access to a wealth of information on health promotion, disease prevention, and healthcare services available in the region. Stay connected and informed by subscribing to @sidamarhb today!

Sidama Region Health Bureau

30 Jan, 17:49


https://www.facebook.com/share/1D9FR9rzaA/

Sidama Region Health Bureau

29 Jan, 18:19


የግሎባል ሄልዝ ኢኒሽዬቲቭ ልኡካን ቡድን በሲዳማ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማትን ጎበኙ
__

የጤና ሚኒስቴር የልማት አጋር ድርጅቶች ጥምረት የሆነው የግሎባል ሄልዝ ኢኒሺዬቲቭ ልኡካን ቡድን አባላት በሲዳማ ክልል የሚገኙትን የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ሀዌላ ቱላ ጤና ጣቢያ፣ ቁልባ ጤና ኬላ እና የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ሃዋሳ ቅርንጫፍን ጎብኝተዋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ለልኡካን ቡድኑ የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ስርአት ትግበራ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል፡፡ የክልሉ ጤና ቢሮ እየተገበራቸው የሚገኛቸው ኢኒሽዬቲቮችን ማጠናከር፣ የህክምና እና የመድሃኒት አቅርቦትን ማሳደግ፣ የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ስራዎችን ማስቀጠል፣ እና የጤና ፋይናንስን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ከልኡካን ቡድኑ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አካሄደዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር አጋር ድርጅቶች በሲዳማ ክልል በመገኘት የጤና ተቋማትን መጎብኘታቸው ለኢትዮጵያ የጤና ስርአት መጠናከር የሚያደርጉት ድጋፍ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ በአካል እንዲያዩ ያስቻለ መሆኑን የገለጹት በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶ/ር መብራቱ ማሴቦ፤ ጉብኝቱ አጋር ድርጅቶች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ መተማመኛ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች የህብረተሰቡን ጤና በማሻሻል በኢትዮጵያ ጠንካራ የጤና ስርአት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ መመልካታቸውን የልኡካን ቡድኑ አባላት የተናገሩ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሃዋሳ ቅርንጫፍ ዲጂታላይዝድ የሆነ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት መቻሉን አድንቀዋል፡፡

Sidama Region Health Bureau

12 Jan, 18:16


ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በይርጋዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የተገነባውን የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ
መርቀው ከፈቱ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጥር 04/2017 ዓ.ም

በይርጋዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የተገነባውን የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የኦክሲጂን ማምረቻ ፋብሪካው ግንባታ መንግሥት ለጤና አገልግሎት መሻሻል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያሳይ ገልፀዉ፥ ይህም የጤና አገልግሎት ጥራትን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው እንደገለፁት የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካው የኦክስጅን ምርቱ በሆስፒታሎች የሚታየውን የኦክስጅን እጥረት ከመቅረፍ ባሻገር በጤና ችግሮች ምክንያት ሊከሰት የሚችል ህመም እና ሞት የሚቀንስ መሆኑን ገልጸዋል ።

የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው በህክምናው ረገድ ከመተንፈሻ አካላት ህመም፣ ከቀዶ ህክምና እና ከሌሎች ከባድ ህመሞች ጀርባ የኦክስጅን አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

በዚህ ረገድ 86 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካው በቀን 192 ባለ 50 ሊትር ሲሊንደር ጥራት ያለው ኦክስጂን የማምረት አቅም ያለው መሆኑን ትልቅ ዕምርታ መሆኑን ክብርት ሚኒስሯ በንግግራቸው አመላክተዋል ።

ፋብሪካው ከሆስፒታሉ ባሻገር በአከባቢው ለሚገኙ ለሌሎች አስር የጤና ተቋማትም ኦክስጅን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፍፍት እንደሚረዳ ተብራርቷል ።

የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካው ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃት ለአካባቢዉ ማህበረሰብ፣ አጎራባች አካባቢዎች እንዲሁም አንደ ሀገር አቀፍም የሚኖረዉ አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ተናግረዋል ።

የኦክስጂኑ መመረት ህብረተሰቡ የሚፈልገውን አማራጭ ህክምና እውን ከማድረግ ባሻገር፣ የህብረተሰቡን የጤና ችግር ሳይወሳሰብ መፍትሄ ለመስጠትና ካልተጠበቀ ጊዜና ጉልበት ወጪ ለመታደግ ያግዛል ብለዋል ዶ/ር ሰላማዊት አክለውም የኦክስጅን ማምረቻ ፋብርካው ከሆስፒታሉ ፍጆታ በላይ 3/4ኛውን ወይም ሶስት አይሱዙ ኦክስጅን በየቀኑ ለሌሎች አሥር ሆስፒታሎች ሳይቋረጥ እያመረተ ሊያቀርብ የሚችል ዐቅም እንዳለው ገልጸዋል ።

በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ርዕሰ መስተዳድሩንና ሚኒስትሯን ጨምሮ ፣ የክልሉ አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ ፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ፣ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የክልሉ ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የሆስፒታሉ ሰራተኞችና አስተዳደር አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣የሆስፒታሉ ቦርድ አባላት ፣ የአገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸው ታውቋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ

Sidama Region Health Bureau

08 Jan, 10:10


https://www.facebook.com/share/1EZY8GgoRM/

Sidama Region Health Bureau

02 Dec, 18:43


በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የሚመራ የተቀናጀ ድጋፍዊ ክትትል ቡድን ወደ ሲዳማ ክልል ገቡ ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ሕዳር 22/2017ዓ.ም

በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በክብርት ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ የሚመራ የተቀናጀ ድጋፍዊ ክትትል ቡድን ከቢሮው ማኔጅመንት እና ከተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የተቀናጀ ድጋፍዊ ክትትል የሚያደርገው የጤና ሚኒስቴር ቡድን በሲዳማ ክልል ሥር የሚገኙ በአራት ዞኖች ፣ ስምንት ወረዳዎች ፣ አራት ሆስፒታሎችን ፣ ስምንት ጤና ጣቢያዎችን እና ስምንት ጤና ኬላዎችን እንዲሁም እስከ ነዋሪው 40 አባወራ/እማወራዎችን (ህብረተሰብ ድረስ ) ያለውን በክልሉ በበጀት አመቱ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን ምልከታ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ በመስክ ምልከታው የወባ መከላከልና ቁጥጥር ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ የሥራ ሁኔታ፣ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎች አቅርቦትና አያያዝ እንዲሁም የነዋሪው ህብረተሰብ ስለ ጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አተገባበርና የነበራቸው ግንዛቤ በምን ደረጃ እንደሚገኝ
ተዘዋውሮ እንደሚመለከቱ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ገልጸዋል ።

ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለውም ከጤና ሚኒስቴርና ከተጠር ተቋማት በቅንጅት በክልሉ በተመረጡ ጤና ተቋማት የመድኃኒት አስተዳደር ሥርዓቱን በሚመለከት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ክትትልና ቁጥጥር ሲያደርግ የነበረ ቡድንም በዚሁ መድረክ ገብረ-መልስ እንደሚያቀርብ እና ሌላው በወባ እና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድ ስራ እንቅስቃሴን የሚደግፍና የሚከታተለው ቡድን ይዞ የሚወርደውንም ቼክ ሊስት እንደሚቀርብ ጠቁመው ፤ በእነዚህ በሁለቱ ቡድኖች የመስክ ምልከታ ሪፖርት እና በአዲስ መልክ ከዛሬ ጀምሮ የሚወርደው ቡድን ቼክ ሊስት ቀርበዋል።

በዚሁ መሠረት ቀደም ስል ክትትል ሲያደርግ የነበረው ቡድን ከመድኃኒት አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ የታዩ ጠንካራ ጎኖቹ ይበልጥ እንዲጎለብቱ እና በጉድለት የተለዩ ችግሮችን ስለሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ ጠንከር ያለ ውይይት ተደርጓል።

ከዚህም ባሻገር ከጤና አገልግሎት አሠጣጥ አኳያ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና እንደ አገር እየጨመረ የመጣው የወባ በሽታ በህብረተሰቡ ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመከላከልና ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎችን በሚመለከት ከዛሬ ጀምሮ ወደ ታች የሚወርደው ቡድንም ድጋፍና ክትትሉን እንደጨረሰ በተገኘው ግብዓት መነሻነት በክቡራን እንግዶቹ የቀጣይ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ ብለዋል ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ፍሬህይወት ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው ቡድኑን እንኳን ደህና መጣችሁ የሚል መልዕክት ባስተላለፉበት ንግግራቸው የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች በክልላችን በየጊዜው እየተገኙ የሚያደርጉልን ድጋፍና ክትትል የሚደነቅና እንደክልል ውጤታማ የሆነ ስራ እንዲሰራ በእጅጉ የሚያግዝ ነው ብለዋል ። አያይዘውም በመጀመሪያው በመድኃኒትና ህክምና መገልገያዎች አስተዳደር ላይ በቡድኑ የተለዩ ቁልፍ መሻሻል የሚገባቸው ችግሮች ላይ የተሻለ ስራ ተሠርቶ እንዲሻሻሉ ይደረጋልም ብለዋል። ይህን ለማድረግ እንደክልል የተቀረጸው ''ለላቀ ውጤትና ጥራት እንስራ'' ኢንሼቲቪ እንዳለ ጠቁመው የየደረጃው የዚሁ ኢንሼቲቪ ተዋናዮች አጀንዳ እንዲሆን በማድረግ ችግሮቹን መቅረፍ እንደሚቻልም የቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ሕዳር 23/2017 ዓ.ም

Sidama Region Health Bureau

21 Oct, 09:20


በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት የወባ ሳምንት ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም

በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ በዛሬው ዕለት '' ወባን ማጥፋት ከእኔ ይጀምራል ! '' በሚል መሪ ቃል በሀገር እና በክልል ደረጃ ለ6ኛ ጊዜ የወባ ሳምንት የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ባጥሶ ዌድሶ ፣ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ ከፍተኛ የወባ በሽታ ጫና ያለባቸው ዞኖች/ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና ስምንት ወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በጫፌ ኮትጃዌሳ ቀበሌ ለወባ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ መንደሮች ላይ የመስክ ምልከታ ተደርጎ የተጀመረው የወባ ሳምንቱ ንቅናቄው በአሁኑ ጊዜ Cluster intervention Review & Next Plan በሚል የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም