Dehna Sew

@dehna_sew


My Aim To Upload Videos To Educate And Motivate People. This Channel Is Purely For Inspiration, Motivation And Raise Your Awareness Into Higher Level Of Consciousness If You Like The Channel Make Sure You SUBSCRIBED Or If You Didn't Go And Press The Red

Dehna Sew

13 Sep, 07:36


#ይህን_ሁሌ_ተግባራዊ_አድርግ!

ያለፀሎት አትውጣ ያለ ተስፋ አትኑር
ያለ አላማ አትጓዝ!!

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

11 Sep, 03:21


መልካም አዲስ አመት 2017
የሰላም ፣ የደስታ ፣ የጤና፣ የስኬት አንዲሁም በበለጠ የምንማማርበት ይሁን።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

10 Sep, 11:04


#ራሰህን_እይበት!

ከባድ ጊዜያት የጥንካሬ ቁልፎች ናቸው ፤ ስራህ ሲበላሽብህ የፍቅር ግንኙነትህ ላይ ችግር ሲያጋጥምህ የተለያዩ ነገሮች ወደአንተ ሲመጡ ያንን ጊዜ በሚገባ ተጠቀምበት ነገህን የተሻለ ለማድረግ የሚረዳህ ትልቁ ቁልፍህ ነው እና ራሰህን እይበት !

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

05 Sep, 08:10


#7ቱ_ሕይወትህን_በኃያልነት_የምትመራባቸው_ሕጎች

4️⃣8️⃣ Laws of POWER የተሰኘው አነጋጋሪ መጽሐፍ #የኃያልነት_ሕጎች ፡፡ ከመጽሐፉ በርካታ ትምህርቶች መካከል ሕይወታችንን በኃያልነት የምንመራባቸውን ሰባት ሕጎች ለቅምሻ እነሆ ብለናል፡-

🔹#አንድ
በወዳጆችህ ብዙ አትታመን፣ ጠላቶችህን መጠቀም ተማር፤ ወዳጆችህን ቅርብ፣ ጠላቶችህን ግን የበለጠ ቅርብ አድርግ፡፡ 

🔹 #ሁለት
ሁልጊዜ ከሚያስፈልገው ያነሰ ተናገር፤ ትንሽ ብቻ በመናገር ሌሎች ችሎታህን አሳንሰው እንዲያዩት አድርግ፡፡  

🔹 #ሶስት
ብዙ ነገር በመልካም ስም ላይ የተመሰረተ ነው፤ ስምህ ሁሉ ነገር ነው፤ ስለዚህ የትኛውንም ዋጋ ከፍለህ ልትጠብቀው ይገባል፡፡ 

🔹 #አራት
በምንም መንገድ ይሁን ትኩረት አግኝ፤ ሌሎችን ለማሳመን ውዳሴና ግርማ ሞገስ ተጠቀም፡፡ 

🔹 #አምስት
ሌሎች ለአንተ እንዲሰሩልህ በማድረግ ሁልጊዜ ምስጋናውን አንተ ውሰድ፤ የሌሎችን ጥረት ለአንተ መጠቀሚያ አድርግ፡፡  

🔹 #ስድስት
በክርክር ሳይሆን በድርጊቶችህ አሸንፍ፤ ከቃላትህ ይልቅ ድርጊቶችህ ይናገሩ፡፡  

🔹 #ሰባት
ፍጹም ወይም እንከን የለሽ ሆነህ አትታይ፤ ይህ በሌሎች ውስጥ ቂምና ቅናት ይፈጥራል፡፡

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

03 Sep, 06:36


#በሰዎች_ምላሽ

መከራ ተሸክሞ ሲኖር ያላዩትን
ትከሻ ኮት ሲለብስ ያጨበጭቡለታል::
ካልተለወጥክ ሰው መቼም አያዝንልህም ሊያዝኑልህ እና ሊረዱህ የሚችሉ ሰዎችም እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው አፈር ዲሜ በልተህ ራስህን ቀይር በሰዎች ምላሽ ምክንያት አታለቃቅ በርታ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

01 Sep, 05:25


#ትኩረታችሁን

አውጥታችሁ አልተናገራችሁም እንጂ ብዞቻችሁ ከፍቶአችዋል ስሙኝ ከልቤ ልምከራችሁ መፍትሄን እንጂ ጥፋትን የሚፈልግ ሰነፍ ሰው በፍፁም አትሁኑ ከጨለማው ይልቅ ትናንሽ እና ጥቃቅን ኮከቦች ላይ ትኩረታችሁን አድርጉ።


ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

29 Aug, 05:25


#ማንም_አይጠላም!

ስሙኝ እማ ያደገና ያማረበትን ማንም ሰው አይጠላም ሁል ጊዜ እራሳችሁ ላይ መስራታችሁን አታቅዋርጡ እንዳትዘነጉ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

28 Aug, 15:03


🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Sorry for the recent break in posts, everyone. Life got a bit hectic, but I'm back and excited to share more with you. Thanks for your patience and continued support!
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

Dehna Sew

28 Aug, 14:59


#በርቱ!

ወደ ኋላ መለስ ብዬ ሳስበው እነዚያ ያጋጠሙኝ አስቸጋሪ ጊዜያት በጣም ከባድ ጊዜያት ነበሩ። ግን ደግሞ የዛሬውን መልካም ማንነቴን እንድሆን ቀርፀውኛል የበለጠም ጠንካራ፣ ጥበበኛ እና ብርቱ አድርገውኛል። አንዳንድ ጊዜ, በጣም አስቸጋሪ መንገዶች ወደ በጣም ቆንጆ እና መልካም መድረሻዎች ይመራሉ ስለዚ በርቱ ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

05 Apr, 06:43


#የማያምኑ፣

Cheat ሳደርግባት ተለየችኝ ጥላኝ ሄደች ለካ ለመለያየት ምክንያት ነበር ስትፈልግ የነበረው አለ አሉ ስንቶቻችሁ ናችሁ በሕይወታችሁ ጥፋታቸውን የማያምኑ የማይቀበሉ ለሁሉም ነገር እናንተን እና ሌሎችን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሰዎች ያጋጠምዋችሁ እናንተም ካላመናችሁ ብላችሁ ሙጥኝ ያላችዋቸው አንድ ነገር አድምጡኝ ሁሌም ቢሆን ልክ ከመሆን ይልቅ ሰላማችሁን ምረጡ ግርግዳ አትግፉ ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

19 Feb, 09:57


#መፍራት_የለም!

በህይወት አስጨናቂ ወቅቶች የሚመጡት ለአጭር ጊዜ ነው ግን የዘላለም ያህል ይረዝማሉ፤ ያንተ ማንነት ነጥሮ የሚወጣው በዚህ ከባድ ወቅት ነው፤

ጀግና ታላቅነቱ የሚታየው ከብርቱ ጠላት ጋር ሲፋለም ነው!

የገጠመህ ከባድ ችግር ከኋላው የፈጣሪን ስጦታ የያዘ ሊሆን ይችላል፤ አንተ አላየኸውም ማለት ደግሞ የለም ማለት አይደለም!

ፈርተህ የትም አትደርስም የምትችለውን እያረክ መጋፈጥ አለብህ!

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

14 Feb, 12:17


የጠፋውት ለYouTube ዝግጅት ሳደር ስቀዳ ነው ከሰኞ ጀምሮ በሰፉው በYouTube እመጣለው በዚያ እንገናኛለን በተጨማሪም ስራዬን ለምትወዱ በሀሳብ በበተለያዮ ለYouTube በሚረዱ እቃዎች መደገፍ እምትፈልጉ በ#0919242505 ይደውሉ በውጭ አገር እምትገኙ Telegram @biruk_zk username እኔን ማግኘት ይችላሉ።

በመንገዳቹ እንቅፋቶች ሲገጥማቹ እንዴት መሻገር አለባቹ አስተማሪ ታሪክ
https://youtu.be/F_O-SWBDoXY

Dehna Sew

14 Feb, 12:07


#ገንዘብ_ላይኖርህ_ይችላል!

"ወጣት ስትሆን ገንዘብ ላይኖርህ ይችላል፤ ግን ቢያንስ በእርጅና ጊዜህ ደሀ መሆን የለብህም" የሚል ፅሁፍ አንብቤ ነበር፤ እውነት ነው አሁን ብትቸገር ከሰው ብታንስ ምንም አይደል፤ ችግሩ ታሪክህን ለመቀየር ምንም ካለደረክ ነው።

ወዳጄ ነገ በጤናውም፣ በደስታውም፣ በገንዘቡም፣ በመንፈሳዊ ህይወቱም፣ በቤተሰብ ግንኙነቱም ሀብታም መሆን አለብህ! መሆን ከፈለክ ደግሞ ካሁኑ ትስፋ ባለመቁረጥ ማሰብ መስራት ጀምር!

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

22 Jan, 10:27


#ችግር_የለውም_ችግር_አለው!

አይንህን ገልጠህ ተጠባበቅ። እናም አንድ ትንሽ ችግር ሲገጥምህ ወዲያውኑ ጠግነው። አይ ችግር የለውም አትበል።

ነገሮች መስመራቸውን በሳቱበት ቅጽበት ለማስተካከል ሞክር።

ህይወት በእጅጉ ከባድ፣ አንዳንዴ ለመቋቋም እስኪያቅትህ ድረስ አስቸጋሪ ናት። እናም ይህን ስታውቅና ለስቃይህ ምክንያት የሆኑ ነገሮች ስትለይ መፍትሄን ማምጣት ትችላለህ።

ስቃይህ እንዲያዳክምህ ከሰውነት ተራ እንዲያወጣህ አትፍቀድለት።

ደጋጋመህ ስታማርር ነገሮችን ታብሳቸዋለህ እንጂ አታስተካክላቸውም። ለገጠመህ ችግር መፍትሄ የምትፈልግበት መንገድ እንጂ ስቃዩን የምታባብልበት ሁኔታ አይኑር።
በሙሉ እምነትም ወደፊት መጓዝና መጋፈጥ ስትጀምር ብቻ ታሸንፋለህ።

ችግር የለውም እያልክ ችግር አታከማች እሺ!

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

19 Jan, 10:21


#ሶስቱ_የንስር_መርሆች

#መርህ_1

ንስሮች በከፍተኛ ከፍታ ብቻቸውን ይበርራሉ። ከሌሎች ትናንሽ ወፎች ጋር ዝቅ ብለው አይታዩም።

🤌ከትናንሽ ወፎች እና ቁራዎች ራቅ። ንስሮች ከንስሮች ጋር ነው የሚበሩት።

#መርህ_2

ንስሮች ጠንካራ እይታ አላቸው።

እስከ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ያለ ነገር ላይ ማተኮር ይችላሉ።

ንስር ሲያድን፣ ትኩረቱን ታዳኙ ላይ ይተክላል፤ ምንም ቢፈጠር ታዳኙን በእጁ እስኪያስገባ ድረስ ትኩረቱን ከታዳኙ ላይ አይነቅለውም።

🤌ግብ ይኑርህ፤ ሙሉ ትኩረትህንም ግብህ ላይ አድርግ፤ እስክታሳካውም ድረስ አይንህን ከእሱ ላይ አትንቀል።

#መርህ_3_የሞተ_ነገር_አትመገብ

ንስሮች እንደ አሞራዎች የሞተ ነገር አይመገቡም። እነሱ የሚመገቡት አድነው ትኩሱን ብቻ ነው።

🤌በፊልሞች እና በቲቪ ላይ አይኖችህን እና ጆሮዎችህን የምትመግበውን ነገር ተጠንቀቅ። ያለፉ እና የቆዩ መረጃዎችን አስወግድ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

17 Jan, 08:15


#ላንቺ_አንቺ!

እሱን ማጣት ምንም የሚፈጥረው አዲስ ነገር የለም ምክንያቱም ያለሱ ብዙ ጊዜ ኖረሽ ነበር ዋናው ነገር እሱን ላለማጣት ስትይ ራስሽን እንዳታጪ።

ልብ በይ እሱ ያስፈልገኛል ብለሽ ከምታስቢው በላይ ላንቺ አንቺ ታስፈልጊያታለሽ።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

16 Jan, 09:05


ተስፋ ማለት ምንም በሌለህ ሰዓት ወደፊት እንደሚኖርህ ማመን ማለት ነው። አንድ ሰው ምንም በሌለው ጊዜ ወደፊት እንደሚኖረው እና አሁን ካለበት የተሻለ ሁኔታ እንደሚመጣ ካመነ ተስፋ አለው ይባላል።

የሰው ልጅ ትልቁ መሰረት ተስፋ ነው። በራስህ ተስፋ ማድረግ አለብህ፤በህልምህ ተስፋ ማድረግ አለብህ። አሁን ያለንበት ሁኔታ በሙሉ ይቀየራል፤ ነገ ሌላ ከዛሬ የተሻለ ቀን ይመጣል። የተሻለውን ለማምጣትም መስራት ይጠበቅብናል።

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘው
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

15 Jan, 11:23


#ነገራችን_ወሬ_ብቻ_እንዳይሆን!

“ስለ አንድ ነገር የምታወሩ ከሆነ ነገሩ ህልም ይባላል፣ ስለነገሩ በሚገባ ማሰብ ስትጀምሩ ነገሩ ወደመቻል ይሸጋገራል ማለት ነው፣ ለነገሩ የጊዜ ሰሌዳ ካዘጋጃችሁለት ግን ነገሩ እውን ወደመሆን ይመጣል” - ANTHONY ROBBINS

•  ቁጭ ብላችሁ ወደማሰብና ስለነገሩ ወደማሰላሰል ያልደረሰ እስካሁን በወሬ ብቻ የቀረውን ነገር እስቲ ለማስታወስ ሞክሩ!

•  ካሰባችሁና ካሰላሰላችሁት በኋላ ወደ እርምጃ እና ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት የጊዜ ገደብና ሰሌዳ ያላስቀመጣችሁለትንም ነገር እስቲ አስቡት!

ነገሮቻችሁ ከወሬ አልፈው ሃሳባችሁን እንዲገዙት፣ ከሃሳብ አልፈው ደግሞ ወደ እውነታ እንዲመጡ ከፈለጋችሁ ይህንን መርህ መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡

ንግግራችን ረገብ፣ ሃሳባችሁን ሰፋ፣ እቅዳችሁ ደግሞ ተግባራዊ በማድረግ ልቃችሁ ተገኙ!

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘው
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

11 Jan, 10:50


#በራስህ_አትቀልድ !

ህይወት እቃቃ ጨዋታ አይደለችም መወሰን ያለብንን በሙሉ መወሰን መቻል አለብን አንድ ዓይን ያለው በዓይን አይቀልድም አንድ ህይወት እያለን እንዴት በእስዋ ይቀለዳል አትቀልድ እኛ ለማደግ የሚገባንን ሁሉ እየለፋን እየባከንን ከስር ከስር
አቅማችንን ፣ ጉልበታችንን የሚወስዱ እና ውጤታችንን ከሚያሳንሱብን ሰዎች ፈፅመን ልንርቅ ይገባናል ካልሆነ ልፋታችን ሁሉ ከንቱ መቅረቱ ነው !

ስለዚህ ዋጋህ ዋጋ ያለው ቦታ ላይ ብቻ አውል !

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።

መልካም ቀን ተመኘው
@dehna_sew
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።

Dehna Sew

10 Jan, 11:02


#አስተውል_ይሄ_እውነታ_ነው

1•| ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትወደቅ ማለት አይደለም ! ወድቀህ መነሳትን ልመድ ማለት እንጂ😘
2•| ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ! ሌሎችን ለመስማትም ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ::
3•| ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም ! በሰዎች ሃቅ ላይ አትለፍ ማለት እንጂ።
4•| ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ! ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ።
5•| ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ! ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ።

            መ. ል. ካ. ም   ቀ. ን

ለማማከር አገልግሎት @dehna_sew1  ይጫኑ።
ሁሉም ቀን ሁለተኛ እድል ነው።