#DGC ህዳር 12/2017
"ኑ ደም እንለግስ ህይወትን እንታደግ "በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 500 ዩኒት ደም የመለገስ መርሃ-ግብር በወረዳ 02 አስተዳደር ተካሄደ፡፡
የወረዳ 2 አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አቤል ምስራቅ በወቅቱ እንደተናገሩት የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ አመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ከተቋማት፣ከህብረተሰብ፣ከተለያዩ ወረዳዎችና እንዲሁም ተማሪዎች በማቀናጀት በሳቢያን ሜዳ የደም ልገሳ እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ደም ልገሳ በፈጣሪ ዘንድ የበረከት ስራ መሆኑንም ተናገርዋል፡፡
አክለውም ብዙ እናቶች በወሊድ ወቅት ፣በተለያዩ አደጋዎች በደም እጦት ምክንያት ለሞት እንደሚዳረጉ ገልፀው ይህንንም የእናቶችን የዜጓችን ህይወት ለመታደግ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለትም 60 ዩኒት ደም ይለገሳ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናገርው ነገር ግን ካለው የለጋሽ ብዛትና ንቅናቄ አንጻር እስከ 150 ዩኒት ይለገሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንን በጎ ተግባርም ህብረተሰቡ ለወደፊት ከጎናቸው በመቆም አጠናከሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በደም ልገሳ መርሓ ግብሩ ሲሳተፉ ያገኝናቸው አካላትም ሲገልጹ ደም መለገስ በሰብአዊነት የሰውን ልጅ ህይወት ለማዳን የሚሰጥ ስጦታ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ደም በመለገስ የወገንን ህይወት በማትረፍ ወገንተኝነቱን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በማቲያስ እንዳለ
ምስል:- አገኝው ሸዋረጋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.diredawacommunication.org
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/DDGCAB
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/channel/UCQNCC5tcc6Jd9zCKcmzQ-eA
ቴሌግራም፦ https://t.me/DDGCAB
ትዊተር፦ https://twitter.com/DawaOffice
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!