አንዳንድ ሀብታሞች፣ነጋዴዎችና የቤተ መንግሥት ሰዎች በድንጋዩ አጠገብ ሲመጡ በዙሪያው እየተመላለሱ ያማርሩ ነበር።
ብዙ ሰዎች መንገዱን ንጹህ ባለመሆኑ ንጉሡን ወቀሱ።
አንዳቸውም ድንጋዩን ከመንገዱ ለማስወገድ ግን ጥረት አላደረጉም።
ከዚያም አንድ ገበሬ ብዙ አትክልቶችን ተሸክሞ መጣ።ገበሬው ወደ ድንጋዩ ሲቀርብ ሸክሙን አውርዶ ድንጋዩን ከመንገዱ ለመግፋት ሞከረ።
ከብዙ ጥረትና ትግል በኋላ በመጨረሻ ተሳካለትና ድንጋዩን ከመንገድ አስወገደው።
ገበሬው አትክልቱን ሸጦ ወደ ቤቱ ሲመለስ ድንጋዩ በነበረበት ቦታ ላይ አንድ ከረጢት ተቀምጦ ተመለከተ።
በከረጢቱ ውስጥ ብዙ የወርቅ ሳንቲሞችና ከንጉሡ የተላከ ማስታወሻ አገኘ።
ማስታወሻው ድንጋዩን ላስወገደው ሰው እንደሆነ ያስረዳል።
በመንገድህ ሁሉ የሚያጋጥሙን መሰናክሎች ሁሉ እኛነታችንን ለማሻሻል ዕድል ይሰጡናል።
ሰነፎች ቅሬታ ሲያሰሙ፣ ሌሎች ግን በደግነት፣ በልግስና እና ነገሮችን ለማከናወን ፈቃደኛ በሆነ ልባቸው በሕይወታቸው ውስጥ ዕድልን ይፈጥራሉ...
መልካም ቀን!!