Vital Nutritional Therapy @vitalnutritionaltherapy Channel on Telegram

Vital Nutritional Therapy

@vitalnutritionaltherapy


Nutritional Therapy and Health consultancy center

Vital Nutritional Therapy (English)

Welcome to Vital Nutritional Therapy, your ultimate destination for all things related to nutritional therapy and health consultancy. As the name suggests, our channel focuses on providing valuable insights, tips, and guidance on how to improve your overall well-being through proper nutrition. Whether you're looking to lose weight, manage a chronic condition, or simply adopt a healthier lifestyle, our team of experienced professionals is here to help you every step of the way

Who are we? We are a dedicated group of nutritionists, dietitians, and health consultants who are passionate about empowering individuals to take control of their health through proper nutrition. Our goal is to provide you with the knowledge and resources you need to make informed decisions about your diet and lifestyle. Whether you're looking for personalized meal plans, nutritional supplements, or simply guidance on how to make healthier food choices, we've got you covered

What is Vital Nutritional Therapy? It is a channel where you can find a wealth of information on nutrition, health, and wellness. From the latest research on superfoods to tips for improving gut health, we cover a wide range of topics to help you achieve your health goals. Our channel is not just about providing information; it's about creating a community of like-minded individuals who are all on a journey to better health. Here, you can connect with others, share your experiences, and learn from experts in the field

So, why should you join Vital Nutritional Therapy? Because we offer more than just information – we offer support, guidance, and motivation to help you live your healthiest life. If you're tired of fad diets, conflicting nutrition advice, and feeling overwhelmed by all the information out there, then this is the place for you. Let us be your partner in health and wellness, and together, we can achieve a happier, healthier you. Join us today and take the first step towards a better tomorrow!

Vital Nutritional Therapy

02 Dec, 08:59


https://youtu.be/l195oFBGBKY?si=yno9OyhKCL6sKd1W

Vital Nutritional Therapy

19 Oct, 07:00


የምንጠቀመው ምግብ አጠቃላይ ጤንነታችንን በተለይም የልባችንን ጤንነት በመወሰን ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ሳይንሳዊ እና የተመጣጠነ የአመጋገብ እቅድ መከተል እንዲሁም በቂ የአካል ብቃት እንቅስቅሴ በማድረግ የልብ እና የደም ሥር በሽታ ተጋላጭነትን መቀነስ ይቻላል።

🥗 ኑ በምግብ ይታከሙ!
👉ለበለጠ መረጃ:- በ0934454647 0921202298 ይደውሉ።
💻 በአካል መምጣት ለማትችሉ online አንሰራለን።
📌አድራሻ:- ጉርድ ሾላ፣ ሴንቼሪ ሞል አጠገብ G&B ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
#vital #nutritional #therapy

Vital Nutritional Therapy

18 Oct, 11:56


👉ደም ግፊት ከተከሰተ በኋላ መቆጣጠር የሚቻልባቸው መድሃኒቶች ያሉት ሲሆን፤ በአንፃሩ ደግሞ በሽታውን ያለምንም መድሃኒት ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚከተሉትን መንገዶች መጠቀም ይመከራል።
👉የተመጣጠነ ምግብ፦ ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና ቅባት ያልበዛባቸውን የወተት ተዋጽኦ ምግቦች እንዲሁም ስብ እና ኮሌስትሮል ያልበዛባቸውን ምግቦች መመገብ የደም ግፊትን ይቀንሳል።
ጨው መቀነስ፦ ጨው ያልበዛበትን ምግብ መመገብ ከደም ግፊት በተጨማሪ የልብ ህመም እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡
፠የደም ግፊት ላለባቸው ሰዎች በቀን 2 ሺህ 300 ሚሊ ግራም እና ከዛ በታች የሆነ የጨው መጠን (ሶድየም) መጠቀም በቂ ነው፡፡
አልኮል መቀነስ፦ የአልኮል መጠጥ የደም ግፊትን ከሚያባብሱ ነገሮች አንደኛው ነውና ከዛ ይራቁ።
ሲጋራ አለማጨስ፦ ሲጋራም ልክ እንደ አልኮል መጠጥ ለደም ግፊት ተጋላጭነት በመዳረግም ሆነ በሽታውን ስለሚያባብስ አለማጨስ ይመከራል።
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፦ ቢያንስ በየቀኑ ለ30 ደቂቃ በቋሚነት እንደ ሶምሶማ፣ እርምጃ፣ ውሃ ዋና፣ ዳንስ እና መሰል ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ደም ግፊትን የማስተካከል እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
🥗 ኑ በምግብ ይታከሙ!
👉ለበለጠ መረጃ:- በ0934454647 0921202298 ይደውሉ።
💻 በአካል መምጣት ለማትችሉ online አንሰራለን
📌አድራሻ:- ጉርድ ሾላ፣ ሴንቼሪ ሞል አጠገብ G&B ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
#vital #nutritional #therapy

Vital Nutritional Therapy

04 Oct, 10:43


💃🌹🌷💐🥀🌺🌻

Vital Nutritional Therapy

04 Oct, 10:43


ውጥረት ውፍረትን ያስከትላል? #asham_tv | #አሻም_ቲቪ
https://youtube.com/watch?v=LhL7DzemVA4&si=Y30mhzISItaM-ViP

Vital Nutritional Therapy

28 Sep, 16:54


እርጎ የሚከተሉትን በርካታ የጤና ጥቅሞችን ይሰጣል።
1. ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ስላለው፡- እርጎ ፕሮቲን ስላለው ለጡንቻ መጠገኛ፣ የረሃብ ስሜት እንዳይኖር እና ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።
2. በፕሮባዮቲክስ የበለፀገ ስለሆነ፡ በፕሮቲዮቲክስ የበለፀገ ሲሆን ይህም ጨጓራ እና አንጀት ጤንነት ጠቃሚ ነው። እነዚህ ህይወት ያላቸው ባክቴሪያዎች የምግብ መፈጨትን ለማሻሻል እና የሰውነትን በሽታ የመከላከል ስርዓትን ሊያሻሽሉ ይችላሉ፡፡
3. ዝቅተኛ የስኳር መጠን ስላለው፡ እርጎ ዝቅተኛ ስኳር አለው፣ ይህም የስኳር አወሳሰዳቸውን ለሚከታተሉት ጤናማ አማራጭ ያደርገዋል።
4. ከፍተኛ ካልሲየም ስላለው ፡ ጥሩ የካልሲየም ምንጭ ሲሆን ለአጥንት ጤንነት አስፈላጊ እና ኦስቲዮፖሮሲስን ለመከላከል ይረዳል።
5. በጠቃሚ ቫይታሚኖች እና ማዕድናት የታጨቀ ስለሆነ፡ በውስጡ ጠቃሚ ቪታሚኖች (ቢ) እና ማዕድናት (ፖታሲየም እና ማግኒዚየም) ስለያዘ ለአጠቃላይ ጤናችን ወሳኝ ነው።

እርጎን በአመጋገብዎ ውስጥ ማካተት ለአካላዊ እና አእምሯዊ ጤና አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ቫይታል ኒውትሪሽናል ቴራፒ

Vital Nutritional Therapy

11 Sep, 13:20


🌻እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

ዘመኑ የሰላም የፍቅር  እና የጤና ይሁንልን።

ቫይታል ኒውትሪሽናል ቴራፒ///

Vital Nutritional Therapy

16 Aug, 15:37


ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከሳንባ እና ሌሎችም ጋር የተያያዙ ህመሞች ከተፈጥሮ ውጭ ያሉ ለልብ ህመም አጋላጭ መንስኤዎች ናቸዉ።

ዉፍርት  ለመቀነስ፣ ጣፋጭ ነገሮችን መቀነስ፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት የሚያመጡ ምግቦችን አለመመገብ።

በተጨማሪ ወደ ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና እና የጤና ማመከር አገልግሎት በመሄድ በአጭር ጊዜ የሚፈለገውን ዉጤት ማምጣት ይችላሉ።

🥗 ኑ በምግብ ይታከሙ!

👉ለበለጠ መረጃ:- በ0934454647 0921202298 ይደውሉ።

📌አድራሻ:- ጉርድ ሾላ፣ ሴንቼሪ ሞል አጠገብ G&B ሕንፃ 3ኛ ፎቅ

Vital Nutritional Therapy

03 Aug, 19:56


ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከሳንባ እና ሌሎችም ጋር የተያያዙ ህመሞች ከተፈጥሮ ውጭ ያሉ ለልብ ህመም አጋላጭ መንስኤዎች ናቸዉ።

ዉፍርት ለመቀነስ፣ ጣፋጭ ነገሮችን መቀነስ፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት የሚያመጡ ምግቦችን አለመመገብ።

በተጨማሪ ወደ ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና እና የጤና ማመከር አገልግሎት በመሄድ በአጭር ጊዜ የሚፈለገውን ዉጤት ማምጣት ይችላሉ።

🥗 ኑ በምግብ ይታከሙ!

👉ለበለጠ መረጃ:- በ0934454647 0921202298 ይደውሉ።

📌አድራሻ:- ጉርድ ሾላ፣ ሴንቼሪ ሞል አጠገብ G&B ሕንፃ 3ኛ ፎቅ

Vital Nutritional Therapy

27 Jul, 09:56


ምግብ መድሃኒት ነው እድሜችንን ይወስናል።

Vital Nutritional Therapy

06 Jun, 19:59


🥑የአቮካዶ አስገራሚ ጥቅሞች

አቮካዶ በተለያዩ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የተሞላ ነው።  እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ ጤናማ የሞኖንሳቹሬትድ ስብ፣ እንዲሁም ቫይታሚን ሲ፣ ኢ፣ ኬ እና ቢ-6፣ ሪቦፍላቪን፣ ኒያሲን፣ ፎሌት እና ፓንታቶኒክ አሲድ ምንጭ ነው። በተጨማሪም እንደ አይረንማግኒዥየም፣ ፖታሲየም፣ ኮፐር እና ማንጋኒዝ ያሉ ማዕድናት ይይዛል።

🥑የልብ ጤናን ያበረታታል።

ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት ጤናማ ቅባቶች (ኦሜጋ 3 ቅባት) እና አንቲኦክሲዳንት የኮሌስትሮል መጠንን እና የደም ግፊትን በመቀነስ ለልብ ህመም ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል።

🥑የስኳር በሽታን ይከላከላል።

አቮካዶ በፋይበር የበለፀገ በመሆኑ በደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ይረዳል።  ጥናቶች በው የኢንሱሊን መመረትን ለማሻሻል እንደሚረዱ ይጠቁማሉ።

🥑ክብደትን ለመቀነስ ያግዛል

ምንም እንኳን ከፍተኛ የስብ ይዘት ቢኖረውም አቮካዶ ክብደትን ለመቀነስ ወይም ለጥገና ሊረዳ ይችላል።  ጤናማ ስብ እና ፋይበር የረሃብ ስሜትን በመቀነስ ክብደትን ይቀንሳል።

🥑የፀረ-ኢንፍላማቶሪ ባህሪያት

በአቮካዶ ውስጥ የሚገኙት አንቲኦክሲደንትስ እና ጤናማ ቅባቶች በሰውነት ውስጥ ፀረ-ብግነት ስሜት እንዳላቸው ተረጋግጧል ይህም ከእብጠት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ይረዳል።

🥑 ለዓይናችን ጤና ጥሩ ነው።

በውስጡ የሚገኘው ካሮቲኖይድ ሉቲን ዓይኖቻችንን ከእድሜ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ለመከላከል ይረዳል።

🥑 የስትሮክ እድልን ይቀንሳል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአቮካዶ ውስጥ የሚገኘው ከፍተኛ መጠን ያለው ፎሌት ለስትሮክ ተጋላጭነትን ይቀንሳል።

🥑 ካንሰርን ይከላከላል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት አቮካዶ የሚበሉ ሴቶች ለጡት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው አነስተኛ ሲሆን ወንዶችም ከፕሮስቴት ካንሰር የመከላከል እድላቸው ከፍተኛ ነው።

🥑 መጥፎ የአፍ ጠረንን ይከላከላል።

አቮካዶ ለመጥፎ የአፍ ጠረን ከሚሰጡ ተፈጥሯዊ መፍትሄዎች አንዱ ነው።

🥑 ለቆዳችን ጥቅም

የአቮካዶ ዘይት በብዙ የውበት ምርቶች ውስጥ የተካተተ እና ለቆዳ ጠቃሚ እና ጤናማ የሆነ ፍራፍሬ ነው።

በአጠቃላይ አቮካዶን ወደ ጤናማ እና ሚዛናዊ አመጋገብ ማካተት የተለያዩ ጠቃሚ የጤና ጥቅሞችን ያስገኛል።

ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና

Vital Nutritional Therapy

05 May, 02:22


ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች፣
እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የደስታ እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
መልካም በዓል!!!

ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና፣ 2016 ዓ. ም

Vital Nutritional Therapy

18 Mar, 21:15


በኢትዮጵያ 52 በመቶ በላይ የሚሆነው ሞት የሚከሰተው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መሆኑ ተገለጸ‼️
በኢትዮጵያ 52 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ህይወታቸውን የሚያጡት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መሆኑን የጤና ሚኒሰቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ተላላፊ በሆኑ በሽታዎች ስኬቶችን ብታስመዘገብም አሁንም ችግሩ ቀጥሏል ሲሉ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በአዲስ አበባ ከመጋቢት 8 እስከ 10 ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው 35ኛው የኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።  

በአዲስ አበባ ከተማ አልጋ ይዘው ከሚታከሙት መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች (ስኳር፣ ግፊት፣ ኩላሊት፣ ካንሰር፣ የአዕምሮ ጤና መታወክ እና ሌሎች በሽታዎች) ተጠቂዎች መሆናቸውም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ወቅት ከሟቾች መካከል 52 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ ያሉት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መሆናቸውን የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ወደፊት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋልም ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው መናገራቸውን ዘገባው አመላክቷል።

Vital Nutritional Therapy

21 Feb, 16:01


አቴሮስክለሮሲስ (የደም ቧንቧዎችን የሚያጠብ በሸታ)

አቴሮስክለሮሲስ ምን ማለት ነው?

አተሮስክለሮሲስ  በደም ሥር ግድግዳዎች የሚከሰት ትክክለኛ ያልሆነ  የስብ መከማቸት ሲሆን በረጀም ጊዜ ሂደት የስብ ንጣፎች ሳይስተዋሉ በደም ስር ግድገዳ ስር ይሰራሉ። ይህም ደም ስሮች እንዲጠቡ  (stenosis) አልፎ ተርፎም የተጎዱትን የደም ሥሮች መዘጋት ሊያስከትል ይችላል።

ደም ስሮች መጥበብ  (stenosis)  ለተጎዱት የአካል ክፍሎች የኦክስጂን አቅርቦትን ያስተጓጉላል። ከዚያም ወደ ምልክቶች ያመራል።
በአቴሮስስክሌሮሲስ የሚጠቁ የተለመዱ ቦታዎች የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች፣ዋናው የደም ወሳጅ ቧንቧ (aorta)፣የዳሌ እና የእግር ደም  ቧንቧዎች እና የካሮቲድ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች ናቸው።

የአቴሮስክለሮሲስ በሽታ ማንን በበዛት ሊይጠቃ ይችላል?ምን አጋላጭ ሁኔታዎች አሉ?

በመርህ ደረጃ  ማንኛውም ሰው ሊጎዳ ይችላል። ምንም እንኳን እድሉ በእድሜ እየጨመረ ቢሄድም በተለይ አጫሾች፣ የስኳር ህመምተኞች፣ የደም ግፊት ህመምተኞች፣ የኩላሊት ህመምተኞች እና ከመጠን በላይ ወፍራም የሆኑና የደም የስብ(የኮልስትሮል) መጠናቸው ከፍ ያሉ ሰዎች በተለየ ተጋላጭ ናቸው። የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ሰዎችም የመጋለጥ እድላቸው ይጨምራል።

የአቴሮስክለሮሲስ በሽታ ምልክቶች

መጀመሪያ ላይ በሽታው ብዙውን ጊዜ ሳይስተዋል ይቀራል። የደም ቧንቧው ጥበት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረስ ከሆነ ወይም በስብ ክምችቶች ክፍተት መሃል የደም መርጋት ከተፈጠረ እነዚህ  የተለመዱ ምልክቶች ይከሰታሉ፦

የልብ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች አካባቢ ከሆነ(Coronary arteries)፡
•   የደረት መጨናነቅ(ጭብጥ አድርጎ መያዝ)፣ የደረት ህመም እና የትንፋሽ ማጠር
የዳሌ ወይም የእግር ደም መላሽ ቧንቧዎች( Pelvic or leg veins) ፡-

•  Intermittent Claudication( እንደ መራመድ ባሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ወቅት የሚከሰት የሚከሰት    የእግር ህመም  እና እረፍት በምናደርግበት ጊዜ የሚጠፋ የእግር ፣ የጭን እና/ወይም የመቀመጫ ህመም)፣
•   በእረፍት ጊዜ  ላይ የሚኖር ህመም (ለምሳሌ እግራችንን ከፍ ስናደርግ)፣
•  በቶሎ  የማይድኑ  ቁስሎች መኖር
ካሮቲድ ደም ወሳጅ ቧንቧዎች፡-
•  ስትሮክ፣ ማዞር፣ ግራ መጋባት እና ሌሎች ምልክቶች።

ምርመራው እንዴት ይደረጋል?

በመጀመሪያ ደረጃ የልብ ምት (ክንድ፣ አንገት፣ወዘተ) ምርመራ መውሰድን ጨምሮ የአካል ምርመራ ይካሄዳል ።
በተጨማሪም የደም ግፊት መለኪያዎች በእጆቹ እና በታችኛው እግሮች ላይ ይከናወናሉ
ያልተለመዱ ነገሮች ካሉ  የአልትራሳውንድ ምርመራ ይካሄዳል
መጥበብ ወይም መዘጋቶች ብዙውን ጊዜ አልትራሳውንድ በመጠቀም በቀላሉ ሊገመገሙ ይችላሉ። ሌሎች ሂደቶች ኮምፕዩትድ ወይም ማግኔቲክ ሬዞናንስ ቲሞግራፊ እና በኤክስ ሬይ ስክሪን (angiography) ያሉ  ምርመራዎችን ሊያካትት ይችላል።
ግልጽ ባልሆኑ ግኝቶች ላይ የትሬድሚል፣የብስክሌት ወይም ሌሎችሙከራዎችን በመጠቀም የተለያዩ የተግባር ምርመራዎችም ሊሰጡ ይችላሉ።

ምን ዓይነት የሕክምና አማራጮች አሉ?

ሕክምናው ብዙውን ጊዜ የሚከናወነው በመድኃኒት ነው። መድሃኒቶች የደም መርጋትን ለመግታት እና የደምስብ መጠንን ለመቆጣጠር ያገለግላሉ። የሕክምናው አስፈላጊ አካል አጋላጭ መንስኤዎችን (ለምሳሌ የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ) መቆጣጠር ነው።እንዳስፈላጊነቱ ሚኒማሊ ኢንቬሴቭ የሆኑ ህክምናዎችና  የቀዶ ህክምና አማራጮች ሊወሰዱ ይችላሉ።

  በመቅረዝ አጠቃላይ  ሆስፒታል ውስጥ ያሉ ልዩ ባለሙያተኞችዎ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ የትኛውን አሰራር መጠቀም እንደሚቻል ይወስናሉ የደም ስር  ቀዶ ህክምና ቡድኖች አካል የሆኑት ልዩ ሐኪሞቻችን ከተለያዩ የህክምና ክፍሎች ጋር  ፣ የልብ ሐኪሞች ፣ ራዲዮሎጂስቶች ፣ የነርቭ ሐኪሞች ፣ ወዘተ)  ውይይት በተገኘው ግኝቶች እና በታካሚው ፍላጎት ላይ በመመስረት የትኛው ህክምና በተናጥል እና ለእያንዳንዱ በሽተኛ ተስማሚ እንደሆነ በጋራ ይወስናሉ።


በሽታውን ለመከላከል እና ለህክምና ራሴ ምን ማድረግ እችላለሁ?

የአተሮስስክሌሮሲስ በሽታ እድገትን ለመቀነስ ወይም በሽታው እንዳይከሰት ለመከላከል ብዙ መንገዶች አሉ።
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በተለይ  እነዚህ ሰባት ልዩ ምክሮች  አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖራቸዋል። እነዚህም 7ቱ ቀላል የጤና መንገዶች በመባል ይታወቃሉ፡-

1. የሰውነት ክብደት መረጃ ጠቋሚ (BMI) በ20 እና 25 መካከል ማድረግ
2. መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (በሳምንት ቢያንስ 150 ደቂቃ  አካላዊ እንቅስቃሴ) ማድረግ
3. የተመጣጠነ  ዝቅተኛ-ኃይል እና ዝቅተኛ ቅባት ያለው አመጋገብ መከተል
4. አያጭሱ
5. ምግብ ከመብላታችን በፊት  ያለውን  የደም ስኳር መጠን (fasting blood sugar) ከ 100mg/dl በታች ማድረግ
6. የደም ግፊት መቆጣጠር
7. የኮሌስትሮል መጠንን መቆጣጠር

ጤናማ ምግብ በሽታን የመከላከል ብሎም የመቀልበስ ሀይል አለው።

ምንጭ: መቅረዝ ጠቅላላ ሆስፒታል

Vital Nutritional Therapy

09 Feb, 15:13


በአዲስ አበባ የደም ግፊት በሽታ ስርጭት 22 በመቶ ደረሰ

#Ethiopia | የደም ግፊት በሽታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ የደም ግፊት ስርጭት 16 በመቶ ሲሆን በአዲስ አበባ ደግሞ 22 በመቶ መሆኑን ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የጤና ማጎልበት እና በሽታ መከላከል ዳይሬክተር አቶ ጌቱ ቢሳ በወንዶች 25 በመቶ በሴቶች ደግሞ 18.8 በመቶ ነ ዉ ብለዋል፡፡

ይህም የሚያሳየው ከ5 ሴቶች 1፤ ከ 4 ወንዶች ደግሞ 1 ሰው የደም ግፊት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
የተቀመጠው ቁጥርም ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩትም እድሜቸው ከ30 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ብለዋል፡፡

ለችግሩ መስፋፋት እንደመንስኤ ከሚነሱ ነገሮች ወስጥ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ፣ ከመጠን በላይ ጨው መጠቀም ፣በቂ ያልሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚገኙበት አቶ ጌቱ ተናግረዋል ፡፡

የአዲሰ አበባ ጤና ቢሮ በአጠቃላይ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ላይ ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችም ተጠናክረው እንደቀጠሉ አስታውቀዋል።

Vital Nutritional Therapy

09 Feb, 11:20


ዝምተኛ ገዳይ (silent killer) 👉ደም ግፊት👇
የደም ግፊት በአዲስ አበባ በ22 ፐርሰንት ጨመሯል ተባለ‼️
* ከ 5 ሴቶች በ1 ሴት
* ከ 4 ወንዶች በ1 ወንድ
በአዲስ አበባ የደም ግፊት በሽታ እንዳለባቸው የተነገረ ሲሆን
* በወንዶች ላይ 25 ፐርስንት
* በሴቶች ላይ 18.8 ፐርሰንት ጨምሯል ተብሏል።
ለዚህም ዋና ዋና ነገሮች :-
1. ጤናማ ምግብ አለመብላት
2. ጨው ከመጠን በላይ መጠቀም
3. ስፖርት አለመስራት
ሲሆኑ በዚህ ከቀጠለ ከሴቶች ይልቅ ብዙ ወንዶች የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ ይሆናል ተብሏል::

ፈረንጆች ዝምተኛ ገዳይ ወይንም "Silent Killer " እያሉ የሚጠሩት ይህ የደም ግፊት በሽታ

1. ለልብ ህመም
2. ለስትሮክ

የሚያጋልጥ ሲሆን ::

ህብረተሠቡ ራሱን መጠበቅ አለበት ተብሏል::

Vital Nutritional Therapy

01 Feb, 15:09


Vacancy Announcements:-


Organization: Vital Nutritional Therapy & Health Consultancy

Location: Addis Ababa

Positions:-

1. Position: General Practitioner

Education: #Medical_doctor

Minimum Experience: #0_year


2. Position: Receptionist

Education: BSc in #Public_Health Officer, #Nursing, #physiotherapy and any related field

Minimum Experience: #0_year

Position 3: executive secretary

Education: BSc in secretarial management and related field with an excellent interpersonal communication and computer skills

Minimum experience: 2 years




Deadline: February 8 2024

Vacancies Details -> Attached

Vital Nutritional Therapy

29 Jan, 10:46


ሰውነታችን ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ ህመሞችን እነዴት በአመጋገባችን መከላከል እንችላለን?

የሰውነታችን በሽታ መከላከል አቅም በተለያዩ ምክንያቶች ሊቀንስ ይችላል።
እነዚህም፡-
•እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ
• ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት ካለን
• የቫይታሚንና የማዕድናት እጥረት ካለ
• የተለያዩ ህመሞች ካሉ
• ህይወታችን በጭንቀትና ውጥረት የተሞላ ከሆነና እረፍት የሚያሳጣ ከሆነ
እንዲሁም ጤናማ ያልሆነ የአመጋገብ ስርዓትን የምንከተል ከሆነ
በተለያዩ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ በህመም ልንጠቃ እንችላለን።

ምን አይነት አመጋገብ ብንከተል ጥሩ ነው?

ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን ያልለቀቁና የተመጣጠኑ ምግቦችን በመመገብ ሰውነታችን የበሽታ መከላከል አቅሙ እንዲጨምር ማድረግ እንችላለን። በተለይ በየቀኑ ብዙ አትክልትና ፍራፍሬን ማዘውተር፤ አቅማችን በሚፈቅደው መጠን ጤናማ የቅባት አይነቶችን እና የሚያስፈልገንን ፕሮቲን ማግኘት አለብን።

አመጋገባችን ውስጥ ማካተት፤ በተቻለ መጠን በሳምንት ከአንድ እስከ ሁለት ጊዜ ቅባታማ የአሣ ዝርያዎችን መመገብ፤ በቀን ከ4-8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣት፤ እንዲሁም አካላዊ እንቅሰቃሴን ማዘውተር በህመሞች ቶሎ ቶሎ እንዳንጠቃ ይረዳናል።

ማስወገድ ወይም በትንሽ መጠን መጠቀም ያለብን ነገሮች ምን ምን ናቸው?

እንደ ነጭ ዱቄት፣ ፓስታና መኮሮኒ በፋብሪካ የተቀነባበሩ የእህል ዘሮችና ከእነርሱ የተሰሩ ምግቦች (ነጭ ዳቦ፣ ኩኪሶች፣ ኬኮች እና ሌሎች ጣፋጮች) ፣  የተጠባበሱ ምግቦች፤ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦች፤ እንዲሁም በፋብሪካ የተቀነባበሩ የስጋ ውጤቶችን ማስወገድ ህመሞችን ለመከላከል እጅጉን ይረዳናል።

ምግብ መድሃኒትም መር ዝም ነው!

መልካም ጤንነት ለሁሉም....!

ቫይታል የስነ ምግብ ህክምና