EthioTimes @ethiotimesmedia Channel on Telegram

EthioTimes

@ethiotimesmedia


EthioTimes media

EthioTimes media (English)

Are you looking for a reliable source of information about Ethiopia? Look no further than EthioTimes media! This Telegram channel is dedicated to providing the latest news, updates, and stories from Ethiopia, covering a wide range of topics including politics, culture, sports, and more. Whether you are a local resident or an international observer interested in Ethiopia, EthioTimes media has got you covered. With an experienced team of journalists and contributors, this channel ensures that you stay informed and up-to-date on all things related to Ethiopia. Join EthioTimes media today and be a part of a vibrant community of individuals who share a passion for Ethiopian news and culture.

EthioTimes

13 Jan, 13:24


https://youtu.be/YtRCwUjIvgM?si=MTtwQRHtzlvM4MDx

EthioTimes

13 Jan, 08:57


#ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ካሉ ከሶስቱ መጻሕፍተ መነኮሳት የመጨረሻው አረጋወ መንፈሳዊ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ የጻፈው ታላቁ ገዳማዊ ጻድቅ አባት አረጋዊ መንፈሳዊ ወይም ዮሐንስ ሳባ ነው፡፡ ይህ ታላቅ አባት እየቀደሰ እያለ በተገለጸለት ታላቅ ምስጢረ ምክንያት ነበር ዓለምን ትቶ የመነነው፡፡ እግዚአብሔር በዓለም ሆኜ ይህን ካሳየኝ ከዓለም ብሸሽ የበለጠ ለእርሱ እቀርባለሁ ብሎ፡፡

ገዳማውያን አባቶቻችን እንዲህ ናቸው ወደ ፈጣሪያቸው ለመቅረብ ዓለማዊ ክፋት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መገለጥም ምክንያት ይሆናቸዋል፡፡ ገዳማትን ስንደግፍም የእነዚህን አባቶች በረከት ነው የምናገኘው፡፡

ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ፣ ታዲያ አረጋዊ መንፈሳዊ በየጊዜው በዓለም ላለው ለታናሽ ወንድሙ መንፈሳዊ ደብዳቤ ይጽፍለት ነበር፡፡ ዓለምን እንዲተው ስላስወሰነው ምስጢር፣ ስለነበረበት፣ ስላለበት፣ በአጠቃላይም ስለ ገዳማዊ ሕይወት ነበር የሚጽፍለት፡፡

እነዚህን #”ከዱር አውሬ የተላከ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ የሚጻፉ ደብዳቤዎች እኔ ሳልሞት ለማንም እንዳታሳይ ብሎ ቢያዘውም ወንድሙ ግን በመጽሐፍ መልክ ለማጻፍ ደብዳቤዎቹን ለጸሐፊ ሊሰጣቸው ሲል አጣቸው፡፡ ከአስራ ስንት ዓመታት በኋላ ግን ደብዳቤዎቹን መጀመሪያ ያስቀመጣቸው ቦታ አገኛቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ወንድሜ ሞቷል ብሎ አለቀሰ፡፡ በረከቱ ይደርብንና ይህን ታላቅ ጸጋ የታደለው አባት ነው እንግዲህ ራሱን በትሕትና የዱር አውሬ ብሎ የሚጠራው፡፡

ገዳማውያን አባቶች መሻታቸው አንድ ብቻ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብና ለሀገርና ለሕዝብ መጸለይ፡፡ ታዲያ ገዳማቸውን እናጽና፣ ድጋፍ እናድርግ ስንል በሌላ አባባል በረከት እንፈስ እያልን ነው፡፡



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

EthioTimes

12 Jan, 19:05


ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን አሸነፈ  

በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ 3ኛ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኢምሬትስ ስታዲየም የተገናኙት አርሰናልና ዩናይትድ መደበኛ የጨዋታ ጊዜውን 1 ለ 1 አጠናቅቀዋል፡፡

ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ተጨማሪ ሰዓት ያመሩ ሲሆን ፥በዚህም ግብ ሳይቆጠር ቀርቷል።

አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የፍጹም ቅጣት ምትም ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን 5 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።

EthioTimes

12 Jan, 11:39


ኦሮማይ መጽሃፍ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ታተመ

የበዓሉ ግርማ የመጨረሻ መጽሃፍ የሆነው “ኦሮማይ” ወደእንግሊዝኛ ቋንቋ መተርጎሙን ዘ ጋርዲያን ዘገበ።

ዘጋርዲያን ሰሞኑን ይዞ በመወጣው መረጃ እንዳመለከተው መጽሃፉ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉሞ የቀረበው በእንግሊዝ ሀገር ነው።

መፅሀፉን ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የተረጎሙት ዴቪድ ደ ጉስታ የተባለ እንግሊዛዊና መስፍን ፈለቀ ይርጉ መሆናቸው ታውቋል።

መቼቱን በቀይ ኮከብ ዘመቻ ላይ በማድረግ የተጻፈውና ለደራሲው ህልፈት ዋነኛ መንስኤ እንደሆነ የሚነገረው ኦሮማይ መጽሃፍ፤ በአጻጻፍ ቴክኒኩና አቀራረቡ የተዋጣለትና የአንባቢን ቀልብ የሚገዛ ስለመሆኑ ብዙዎች አንባቢዎችና ሀያሲያን የመሰከሩለት መጽሃፍ ነው።

ደራሲ በዓሉ ግርማ በዚሁ መጽሃፍ የተነሳ ከስራው ከታገደ በኋላ አንድ ቀን ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ቀርቷል።

የዚህ አንጋፋ ደራሲ ህልፈትም ሚስጢር ሆኖ ላለፉት አራት አስርት አመታት ቆይቷል።

EthioTimes

09 Jan, 17:51


አሜሪካ Los Angeles

EthioTimes

09 Jan, 15:03


#ሰማያዊ አክሊል የተቀዳጀው የይቅርታ መምህር

ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ጳውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ አባቱ ስምዖን እናቱ ማርያም የሚባሉ በብዙዎች ዘንድም ፍጹም እስራኤላዊ የሚባል በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፤ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፡፡

ቅዱስ እስጢፋኖስ የነበረበት ወቅት አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበርና መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀት እየሰበከ ሲመጣ ነገሩን መረመረ፤ ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው ደቀ መዝሙሩ ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ሲጠይቀው "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ልኮት ከጌታ ዘንድ ሔዶ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፤ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው፡፡ 

EthioTimes

09 Jan, 15:03


ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅድስናን፣ ጵጵስናን የተሾመ ነው፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፣ በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ “መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት እንደሆነ በሐዋ. 6፣5 ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ “ሊቀ ዲያቆናት” ሲባል እንደ ዘመናችን ሳይሆን እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው፡፡ ለ አንድ ዓመት ያህል 8ሺውን ማኅበር እየመራ፣ ወንጌል እየሰበከ ሲጋደል ኦሪት “እጠፋ እጠፋ”፣ ወንጌል ደግሞ “እሰፋ እሰፋ” ብትል አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸው አንድም በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ ጥር አንድ ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡

አስገራሚው ነገር ጥር አንድ ቀን የልደቱ ቀንም መሆኑ ነው፡፡ እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: ለሚወግሩት ሰዎች እንደ አምላኩ “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” በማለት ይቅርታ መጠየቁ ነው፡፡ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶ እያለቀሱ ቀበሩት፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ዓለምን የናቁ ገዳማውያንም ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሁሉን ትተው መንነዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ያደርጋል፡፡ ገዳማቸውን በመደገፍ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

EthioTimes

08 Jan, 16:34


እሳተ ገሞራ
ሰሞኑን በኢትዮጵያ እየተከሰተና ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰ በመጣው  ያልተቋረጠ የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በአፋር ክልል ዶፋን ተራራ ላይ አዲስ የፈነዳው እሳተ ገሞራ ይህን ይመስላል።

Source: አዩዘሀበሻ

EthioTimes

08 Jan, 14:41


ኢትዮ-ሸማች የተሰኘው ችግር ፈቺ የመሰረታዊ ሸቀጦች (ስኳርና ዘይት) ስርጭት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ በሁሉም ክፍለ-ከተሞች መተግበር ሊጀምር ነው!

በወጣት የቴክኖሎጂ ተመራማሪዎች በልፅጎ የቀረበውና የሸማቹን ማህበረሰብ ችግር በዘላቂነት የሚቀርፈው ኢትዮ-ሸማች የተሰኘው የቁጥጥር መተግበሪያ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኩል በአራዳ ክፍለከተማ ንግድ ፅ/ቤት ስር በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች መተግበር ጀምሯል። ስኳርና ዘይት መከዘን፣እያለ የለም ማለት፣ ጥቁር ገበያ፣ ሰው-ሰራሽ የዋጋ ውድነት... ወ.ዘ.ተ ሲስተሙ የሚገታቸው ሲሆኑ ለማህበረሰቡም የላቀ እፎይታን የሚያመጣ ይሆናል።

ኢትዮ-ሸማች በሀገራችን ከሚገኙ አያሌ ዲጂታል የክፍያ አማራጮች መካከል ዋነኛ ከሆነው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር MoU በመፈረም የተሟላ System Integration ሰርቶ ያቀረበ ሲሆን፤ 6 ወራት በወሰደ የሙከራ ትግበራው የዲጂታል ግብይቱን ውጤታማነት ማረጋገጥ ተችሏል። የቁጥጥር ሲስተሙ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ ሲሆን ሸማች ህብረት ስራ ማህበራትም ሆኑ የDelivery ተቋማት የሚያካሂዷቸውን የግብዓት ስርጭቶች በፍትሃዊነትና በገለልተኝነት ለመቆጣጠር  ያስችላል።

መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገባቸውን መሰረታዊ ሸቀጦች ግብዓቱ ለታለመላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በስርዓቱ እንዲደርስ፣ ሰው-ሰራሽ እጥረት እንዳይኖር ብሎም የገበያ መረጋጋት እንዲኖር ለማድረግ አቅዶ እየሰራ የሚገኘው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር (MOTRI), በቀጣይ ሲስተሙን ለማሳደግና  ሀገር አቀፍ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል ተገቢውን ስራ መስራት ጀምሯል።

ለፓይለት ትግበራው መሳካት ማህበረሰቡና የአራዳ ክ/ከ ንግድ ፅ/ቤት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።በቀጣይም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማዎች እንዲሁም በሌሎች ከተሞችና በሀገር አቀፍ ደረጃ ትግበራው የሚቀጥል ይሆናል።

መንግስት የተለመውን ዲጂታላይዜሽን ከማሳካት አንፃር ይህ የቁጥጥር ቴክኖሎጂ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል። የሀገራችን የእድገት ሞተር የሆነው ንግድ ባንክም የዳሬ ቴክኖሎጂ ሁነኛ አጋር በመሆን የዲጂታል ትራንዛክሽኑን በሰፊው ያሳልጣል።

መንግስት ለወጣት ስራ ፈጣሪዎችና ስታርትአፕ በፖሊሲ ደረጃ የሚያደርገውን ሙሉ ድጋፍ በሚመለከት ይህ ፕሮጀክት አይነኛ ምሳሌ ሆኖ መቅረብ የሚችል ነው።

EthioTimes

08 Jan, 09:38


አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ ‼️
*******
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በደባርቅ ወረዳ ቤተክህነት ስር በአደጋት ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የምዕራፈ ቅዱሳን አፅሐራራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም በእናታችን ቅድስት አመተ ክርስቶስ በ14ኛዉ ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ታላቅ እና ታምራዊ ገዳም ሲሆን በጊዜ ብዛት የድሮው ቤተክርስቲያን ፈርሶብናል። ጣራዉን ለማደስ አስቸኳይ ነዉና በውጭም ያላችሁ ወገኖቻችን በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የአቅማችሁን በማገዝ ከበረከቱ እንድትሳተፉ እንለምናችዋለን‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000331624334
☎️ 0934654964 ወይም 0918532706
ለብዙዎች እንዲዳረስ እባካችሁ ሼር አድርጉት‼️

EthioTimes

07 Jan, 15:26


ቤንዚን ከ 100 ብር በላይ እንዲሸጥ ተወሰነ

👉🏼በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን  የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ ተደረገ

የሚኒስትሮች ም/ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታ የአፈጻጸም ውሳኔ መሠረት፤ ከዛሬ ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለዉ እንዲሸጥ በመንግስት መወሰኑ አሳዉቋል።                        
በዚህም መሰረት  በአዲስ አበባ የችርቻሮ የመሽጫ ዋጋ

ቤንዚን  በ101.47 ብር/ሊትር

ናፍጣ   በ98.98 ብር/ሊትር

ኬሮሲን  በ98.98 ብር/ሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ በ109.56 ብር/ሊትር

የከባድ ጥቁር ናፍጣ  በ105.97 ብር/ሊትር

የቀላል ጥቁር ናፍጣ   በ108.30 ብር/ሊትር በመሆን ከዛሬ ታህሳስ 29/2017 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ አበባ እንዲሸጥ ተወስኗል።

EthioTimes

06 Jan, 06:15


ጉምቱዉ ፖለቲከኛ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
ነፍስ ይማር‼️

EthioTimes

05 Jan, 14:15


በዛሬዉ የማንቸስተር ዩናይትድና ሊቨርፑል ጨዋታ ማን ያሸንፋል? ስንት ለስንትስ ያልቃል? ግምታችሁን አስቀምጡ።
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👇👇
EthioTimes media
https://t.me/ethiotimesmedia

EthioTimes

04 Jan, 16:51


ዛሬም ታህሳስ 26, 2017 ከምሽቱ 1:38 ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ አዲስ አበባ ላይ ተከስቷል። ጀሞ፣ጣፎ አካባቢም ንዝረቱ ተሰምቷል።

EthioTimes

04 Jan, 16:12


የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በመላው ሀገሪቱ  ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ፈተና እየሰጠ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች የአቪዬሽን ዘርፉን እንዲቀላቀሉ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ አመልካቾች የጽሁፍ ፈተና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።

የመግቢያ ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በአዳማ ፣ አምቦ ፣ አርባ ምንጭ ፣ አሶሳ ፣ ባህር ዳር ፣ ደሴ ፣ ድሬዳዋ ፣ ጋምቤላ ፣ ጎንደር ፣ ሀዋሳ ፣ ጂግጂጋ ፣ ጅማ ፣ መቀለ ፣ ነቀምት ፣ ሮቤ ፣ ሰመራ ፣ ወልቂጤና አዲስ አበባ በሚገ ዩኒቨስርቲዎችና የፈተና ጣቢያዎች መሆኑን ነው አየር መንገዱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት አመቺ ትራንስፖርት በሌለባቸው ቦታዎችም ጭምር በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራዎቹ በመጓዝ በሁሉም ማዕዘናት ያሉ ወጣቶች ብሔራዊ ሀብት የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀላቅለው ራሳቸውን፣ አየር መንገዱን እና ሀገርን እንዲጠቅሙ ለማስልቻል ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

EthioTimes

31 Dec, 19:38


#Earthquake : ዛሬ ምሽትም 4:17 ላይ ጠንከር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።
ከጋርመንት፣ ጀሞ፣ አራብሳ፣ አያት ፣ ጎተራ፣ አያት 49 ጣፎ ... ሌሎችም አካባቢዎች ንዝረት ተሰምቷል።

EthioTimes

31 Dec, 03:01


አስደንጋጩ የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
#Earthquake

ለሊት 7:13 ላይ በሬክተር ስኬል 4.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተከሰተ የጀርመኑ ጂኦ ሳይንስ እና የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመላክታል።

የመሬት መንቀጥቀጡ የተመዘገበው ከአቦምሳ 39 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው።

ይህ ባለፉት ሰዓታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.0 ፣ 4.5 ፣ 4.6 ፣ 4.7 ... የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጦች ቀን፣ ምሽት እና ለሊቱን በተከታታይ ተመዝግበዋል።

የነዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቶች አዲስ አበባ እና የተለያዩ የክልል ከተሞች ጠንክረው ተሰምተዋል።

በተለይ በህጻዎች ላይ ያሉ ሰዎች ጠንከር ያለ ንዝረት ተሰምቷቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በከሰም ቀበና ቤቶች እና ንብረት ላይ ወድመት መድረሱን ነዋሪዎች ጥቆማቸውን በፎቶ አስደግፈው ልከዋል።
Via- Tikvah ethiopia

EthioTimes

30 Dec, 18:24


በአዋሽ ፈንታሌ የመሬት መንቀጥቀጡ ወደ ቮልካኖ አመራ።
ትኩረት‼️

EthioTimes

30 Dec, 13:33


ምስኪኗ እናት ተገኝታለች

የባንክ አካውንቷም ተስተካክሏል

የአራት ልጆች እናትና በፅኑ ታማሚ ናት። ልጆቿ ከህመሙ ተርፈውላታል። ባለቤቷና የልጇቿ አባት ጥሏት ጠፍቶ የት እንዳለ አይታወቅም። አሁን የምትኖረው መብራትም ውሃም በሌለው መጠለያ ነው። ከጤናዋ ጋር እየታገለች ልጆቿን ማሳደግ ቢከብዳት ይዛቸው እየዞረች ትለምናለች።

ሁላችንም ብንተባበር ከዚህ መከራ ውስጥ ልጆቹን ማውጣትና ይህቺን አሳዛኝ እናት ማሳረፍ እንችላለንና ከዚህ በታች በተቀመጠው የንግድ ባንክ አካውንት የአቅማችሁን ታደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንለምናለን።


1000099602205
CBE

ፀሃይ ተሻለ ዘሪሁን

ስልክ 0923149392

ቅዳሜ ተለጥፎ የነበረው አካውንቷ ለሞባይል ባንኪንግ Active ባለመደረጉ መርዳት ፈልገው ላልቻሉ ብዙዎች ይደርስ ዘንድ share በማድረግ እንድታዳርሱልን በፈጣሪ ስም እንማፀናለን 🙏

EthioTimes

29 Dec, 16:49


አሳዛኝ የመኪና አደጋ ተከስቷል

ዛሬ ታህሳስ 20/2017 ዓ.ም በሲዳማ ከልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው  አደጋ ከ60 በላይሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።

አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና ከ60+ የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ተብሎአል።

የሟቾች ቁጥር ከዚያም ሊበልጥ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/ethiotimesmedia

EthioTimes

29 Dec, 16:03


“በመካከላቹ አድር ዘንድ መቅደሴን ስሩልኝ” ዘፀ 25-8

👉በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የሚገኘው የባዚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን እርዳታ ይፈልጋል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በአምባሰል ወረዳ የባዚ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በ1587 ዓ.ም የተመሠረተ ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከግሸን ደብረ ከርቤ ቅ/ማርያም ገዳም በምሥራቅ አቅጣጫ 20 ኪሎ ሜትር ላይ ወይም በደልባ አምሣለ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ በታች ከቆላው ላይ ይገኛል፡፡
ለመስራት የታሰበው ዋናዉን ቤተክርስቲያን ለማሰራት፣ቤተልሔሙን ለማሰራት፣እቃ ቤቱን ለማሰራት፣አዳራሽ ለማሰራት እና ለካህናት መተዳደሪያ ማዘጋጀት የታሰበ ሲሆን ለዚህም ወጪ በጠቅላላ አሁን ባለው የገቢያ ሁኔታ 7,801,860 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ አንድ ሺ ስምንት መቶ ስልሳ ብር) እንደሚያስፈልግ የተገመተ ሲሆን ለዚህ ለተቀደሰ ዓላማ በመሽቀዳደም ከፃዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፀጋና በረከት እናገኝ ዘንድ ጥሪ ቀርቧል።

ስለዚህ አቅማችሁ የፈቀደውን ያህል እንድትረዱ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በፃዲቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም እየጠየቅን የባንክ አካውንታችን የባዚ ተክለ ሃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ሂሳብ ቁጥር 1000502246287 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መሆኑን በታላቅ ትህትና እንገልጻለን፡፡

ስልክ ቁጥር ፡- 0911551512
0913400914
0913586114
0925317689

EthioTimes

29 Dec, 12:40


አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ‼️
_____
"እህታችን ቤተልሔም ሽመልስ መንግስቱ ከአዲስአበባ ወደ ዳንግላ በመምጣት ላይ እያለች መንገድ ላይ በታጣቂዎች ታግታብናለች። አጋቾቹም ለማስለቀቂያ አንድ ሚሊዮን ብር ጠይቀዉናል። የተቻላችሁን ታግዙን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን።"
ቤተሰቦቿ
☎️ 0960808027
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ- 1000138985826

EthioTimes

29 Dec, 05:57


አሳዛኝ ክስተት!

በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የ179 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከታይላንድ ወደ ደቡብ ኮሪያ እየበረረ እያለ #ሙዓን ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ነው የተከሰከሰው። በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩ 181 ሰዎች ውስጥ ሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ በህይወት ተርፈዋል።

ከሁለት ቀን በፊት የአዘርባጃን አውሮፕላን በሩሲያ ሚሳኤል ተመትቶ 38 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።

EthioTimes

29 Dec, 05:56


በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

ዛሬ ታህሣስ 20/2017 ዓ.ም ከሰአታት በፊት ረዘም ላሉ ሰከንዶች የቆየውና አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዋሽ ፈንታሌ ከማለዳው 12:58 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ ተመዝግቧል 10km ጥልቀትም እንዳለው መረጃዎች ያሳያሉ።

ሰሞኑን ተከታታይ ቀናት እየተከሰተ እንደሚገኝ ይታወቃል።

EthioTimes

28 Dec, 15:20


ፎቶ ፦ የታኅሣሥ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በሰላም በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በበዓሉ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተገኝተው ነበር።

በክብረ በዓሉ ላይ ቅዱስነታቸው ቃለ ምዕዳን እና ቡራኬ ሰጥተዋል።

በቁልቢ የቅዱስ ገብርኤል ንግሥ በዓል ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን ተገኝቶ ነበር።

ዓመታዊው የታሥሣ 19 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አህጉረ ስብከቶችም ተከብሮ ውሏል።

የፎቶ ባለቤት ፦  የኢ/ኦ/ተ/ዋ/ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

EthioTimes

25 Dec, 10:56


ከጠቅላይ ሚንስተር ቢሮ!

የኮዲንግ ሥልጠና ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወጣቶች!

በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎች የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ ይመዝገቡ፡፡

የኦንላይን ስልጠናውን በተሰጡት 8 ሳምንታት ለሚያጠናቅቁ ብቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ይበረከትላቸዋል፡፡

ተሰጥዎን በማውጣት፤ ነገን እንለውጥ!!!

EthioTimes

24 Dec, 15:09


ዩኒቨርሲቲው  ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም…….  በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።


ታኀሣሥ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

EthioTimes

23 Dec, 20:02


መረጃ❗️
አሁን ከደቂቃወች በፊት 4:40 ሲል የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል ንዝረቱ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ተሰምቷል።

EthioTimes

22 Dec, 16:21


አርቲስት ዳናዊት መክብብ ወንድሟ ዘማሪ አቤል መክብብ አዲስ ላሳተመው የመዝሙር አዲስ አልበም ሕትመት ማገዣ ይውል ዘንድ 200,ዐዐዐ ብር መስጠቷ ከኢንተርኮንቲኔንታል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

EthioTimes

21 Dec, 16:10


በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ዛሬ ከቀኑ 5 ሠዓት ከ20 ላይ በፈንታሌ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

ከአሁን ቀደም የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰትበት በነበረው ፈንታሌ አካባቢ ዛሬም ክስተቱ መስተዋሉን በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስ እና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) ገልጸዋል፡፡

በሬክተር ስኬልም 4 ነጥብ 3 መመዝገቡን አረጋግጠዋል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ ያደረሰው ጉዳት መኖሩ ወይም አለመኖሩ በቀጣይ እንደሚገለጽም መናገራቸው ፋና ዘግቧል፡፡

EthioTimes

21 Dec, 15:15


Update

ኢትዮጵያ ገቡ

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከደቂቃዎች በፊት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

ማክሮን አዲስ አበባ ከመምጣታቸው በፊት በጎረቤት ሀገር ጅቡቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

EthioTimes

21 Dec, 14:13


አፍሪካችን‼️
በናይጄሪያ አቡጃ ከተማ በአንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለገና መዋያ በሚል አነስተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን ለመደገፍ የምግብ እህል እየተሰራጨ በነበረበት ሰዓት በተከሰተ ግጭት እና ግርግር በትንሹ የ10 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል። ከሟቾቹ ውስጥ አራቱ ህፃናት ሲሆኑ ሌሎች ስምንት ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
አዩዘሀበሻ

EthioTimes

20 Dec, 16:14


update

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ  በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተውን የአመጋገብ ችግር በቅርብ ጊዜ እየተከታተለ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

EthioTimes

16 Dec, 03:38


ሚስት ባሏን ደሀ ነህ ብላ በፈታች በማግስቱ የሚሊዮን ዶላሮች ሎተሪ ያሸነፈ ባል፡፡

ሰውዬው ለተወሰነ ጊዜ ሥራ አጥ ነበር እና ሚስቱ በሂደቱ ላይ እምነት መጣል ትዕግስት ስለሌላት ወደ ፊት ለመቀጠል ወሰነች።

ሆኖም የፍቺ ሰነዶችን ከፈረመ ከአንድ ቀን በኋላ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የሚለዉጥለትን ሎተሪ ሊያሸንፍ ችሏል።

EthioTimes

13 Dec, 13:44


ከአል-አሳድ ውድቀት በኃላ በሶርያ መዲና ደማስቆ የመጀመሪያዉ የጁማ ጸሎት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተገኙበት በአደባባይ ተካሄደ🙏

EthioTimes

12 Dec, 11:01


የባሽር አላሳድ ተቃዋሚዎችን በአንበሳ በማስበላት የሚታወቀው ጨካኙ ወታደር ህዝብ ፊት ተገደለ

በሶሪያ በጣም ከሚፈሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው እና በራሱ ለማዳ አንበሳ እስረኞችን በማስበላት የሚታወቀው ወታደር በሞት ተቀጥቷል። በአንድ ወቅት የ25ኛው የሶሪያ ጦር ልሂቃን ክፍል አባል የነበረው ታላል ዴካክ የበሽር አል-አሳድ አገዛዝ ከወደቀ በኋላ በአማፂያኑ በአደባባይ ተገድሏል።

ዴካክ ጨካኝ አንበሳ ይዞ የሚዞር በመሆኑ በብዙዎች ዘንው የተፈራ በሶሪያ ውስጥ በጣም ታዋቂ  ሰው ነበር። በ2005 አንበሳውን ከእንስሳት መካነ አራዊት ሰርቆ በማስወጣት አደገኛ እና ገዳይ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ጀምሮበታል። በድርጊቱ ይደሰት እንደነበር ይናገራል። ለባልንጀሮቹ “የአሸባሪዎችን” አስከሬን ለቤት እንስሳው እንደሚመግብ በኩራት ይናገር ነበር።

የሶሪያ ታዛቢ ቡድን በግለሰቡ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት ከፍተኛ ወታደራዊ አባል በነበረበት ጊዜ የሰው አካልን በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ነዳጅ በማዘዋወር እንዲሁም ምግብ፣ ያልተመዘገቡ ተሽከርካሪዎች እና አደንዛዥ እጾች ንግድ ይሳተፍ ነበር ብሏል። ዴካክ በጣም የሚፈራው የሶሪያ ጦር ክፍል አባል ከመሆኑ በፊት የታክሲ ሹፌር ነበር። በሠራዊቱ ውስጥ ከነበረው ሚና በኋላም ነጋዴ ሆኗል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ ከሀብታም ቤተሰብ የመጡ ሶርያውያንን እያሰረ ገንዘብ ይወስድ ነበር። ዳካህ ሀገሪቱን ከአል አሳድ የጭቆና አገዛዝ ነፃ ባወጣችበት ወቅት በታጣቂ አማፂ ሃይሎች ተይዟል ተብሎ ይታመናል።

EthioTimes

08 Dec, 04:39


#BREAKING🚨

የበሽር አላሳድ አገዛዝ ተገረሰሰ።

የሶሪያው ፕሬዜዳንት በሽር አላሳድ አገዛዝ ወደቀ። እሳቸውም ሀገር ለቀው ጠፍተዋል።

የታጠቁ የሶሪያ ተዋጊዎች የፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድን የ24 ዓመት አገዛዝ ለመደምሰስ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄዱ ነበር። በመጨረሻም ተዋጊዎች አሸንፈዉ ስልጣኑን ተቆጣጥረዉታል።

EthioTimes

07 Dec, 16:11


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

EthioTimes

05 Dec, 15:48


ተዋናይት ማስተዋል ወንደሰን የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆና ተመረጠች

👉አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ አቃቤ ነዋይ ሆነው ተመርጠዋል

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

ጉባኤው ኢንጅነር ሀይለእየሱስ ፍስሀን ፕሬዘዳትነት  አድርጎ ሲመርጥ አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን ም/ፕሬዘዳትነት  እና አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ አቃቤ ነዋይ ሆነው ተመርጠዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤው ዛሬ ያካሄደ ሲሆን የስራ አሰፈፃሚ ኪሚቴን ምርጫን ጨምሮ በአራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቆል።

ጉባኤው ኢንጅነር ሀይለ እየሱስ ፍስሀን በአብላጫ ድምፅ የፌዴሬሽኑ ፕሬዘዳንት አድርጎ ሲመርጥ  አርቲስት ማስተዋል  ወንደሰን እና አርቲስት ሀረገወይን አሰፋን ም/ፕሬዘዳንት እና አቃቢ ነዋይ በመሆን ተመርጠዋል።

ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት  አመታት በስራ አስፈፃሚነት የሚመሩ ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ 9 ስራ አስፈፃሚዎች በጉባኤተኛው የተመረጡ ሲሆን የአርማ እርክክብም ከቀድሞው የስራ አስፈፃሚዎች አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆነው የተመረጡት ኢንጅነር ሀይለእየሱስ ፍስሀ በቀጣይ ለከተማዋ ሁለንተናዊ የእግር ኳስ እድገት ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው በ2015ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ፣ በ2016 በጀት አመት የእቅድ አፈፃፀም፣በ2016 የኦዲት ሪፖርት፣ በ2017 በጀት  እቅድ ላይ ከተወያየ በሆላ አብላጫ ድምፅ አፅድቆል።

Via Dagu Journal

EthioTimes

05 Dec, 09:54


ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ 100 ሺህ ዶላር ተመነዘረ።

ቢትኮይን የተሰኘው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ (ክሪፕቶ ከረንሲ) በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

በዚህም የአንድ ቢትኮይን ዋጋ በ100 ሺህ ዶላር በመመንዘር ላይ ሲሆን ይህም በዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ ታሪክ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

የቢትኮይን ዋጋ እንዲህ ሊጨምር የቻለው፤ ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክሪፕቶ ከረንሲን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን እንደሚቀበሉ በማሳወቃቸው መሆኑ ተገልጿል።

ትራምፕ የቀድሞን የአሜሪካ የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽነር ፖል አትኪንስ የሃገሪቱ የስቶክ ገበያ የሆነውን ዎል ስትሪት እንዲመሩ ማጨታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ የቢትኮይን ዋጋ እንዲጨምር ምክንያት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ሚስተር አትኪንስ አሁን ካሉት የሴኪውሪቲስ እና ኤክስቼንጅ ኮሚሽን ኃላፊ ጋሪ ጌንስለር የበለጠ የክሪፕቶ ከረንሲ ደጋፊ ስለመሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የዲጂታል መገበያያ ገንዘቡ 100 ሺህ ዶላር መግባቱን ተከትሎ በዓለም ዙሪያ ያሉ የቢትኮይን ተጠቃሚዎች እና ደንበኞች ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑን የዘገበው ቢቢሲ ነው።

EthioTimes

04 Dec, 12:03


የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር በሆኑት ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመራ የሠራዊቱ አመራሮች የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎበኙ።

EthioTimes

04 Dec, 12:01


ቻይና በዩኒቨርስቲ እና ኮሌጆች ውስጥ የፍቅር ትምህርት እንዲሰጥ ወሰኔ አሳለፈች፡፡

ዜጎች በትዳር፣ በፍቅር ግንኙነት እና ቤተሰብ ላይ አዎንታዊ አመለካከቶችን እንዲያዳብሩ ነው ቤጂንግ ውሳኔው ላይ መድረሷ የተሰማው፡፡

ቻይና በ2023 ለሁለተኛ ተከታታይ አመት የህዝብ ቁጥር መቀነስ ካስመዘገበች በኋላ ልጅ መውለድን ለወጣት ጥንዶች ይበልጥ ማራኪ ለማድረግ የተለያዩ የማበረታቻ እርምጃዎችን ስትወስድ ቆይታለች።

ሀገሪቱ ምንም እንኳን በ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ህዝብ በአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ብትገኝም፤ የውልደት ምጣኔዋ ሲቀንስ በአንጻሩ በእርጅና ላይ የሚገኙ ዜጎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡

በዚህ የተነሳ የስነህዝብ ፖሊሲ ቀውስ ሊያጋጥማት እንደሚችል በስጋት ላይ የምትገኘው ቤጂንግ ቀውሱ በኢኮኖሚው እና በአጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ተንብያለች፡፡

የሀገሪቱን የውልደት ምጣኔ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው የሚጠበቁት የኮሌጅ ተማሪዎች በትዳር እና በፍቅር ላይ ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡

ይህን ለመቀየር ቻይና ከአንድ ልጅ ፖሊሲ ወጥታ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የትዳር እና የፍቅር ትምህርቶችን በመስጠት ወጣቶች በመዋለድ እና ቤተሰብ በመመስረት ዙርያ ያላቸውን ዝቅተኛ ተነሳሽነት ለመቀየር ወጥናለች፡፡

የፍቅር ትምህርቶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ለታዳጊ የኮሌጅ ተማሪዎች ስለ ህዝብ ብዛት እና ሀገራዊ ሁኔታ፣ ስለ አዲስ ጋብቻ እና ልጅ መውለድ ጽንሰ ሀሳቦች በማስተማር ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ፡፡

EthioTimes

03 Dec, 17:11


ለቸኮለ! ማክሰኞ ኅዳር 24/2017 ዓ፣ም የዋዜማ ዕለታዊ ዜና

1፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን፣ ሸዋቤንች ወረዳ ስር የሚገኙ የስድስት ጤና ጣቢያዎች ሰራተኞች የሁለት ወራት ደምወዝ አልተከፈለንም ሲሉ ለዋዜማ ተናግረዋል። ለሠራተኞች ደምወዝ ያልተከፈለባቸው በወረዳው ስር ያሉት የጤና ጣቢያዎች፣ ኩላጋቻ፣ ጥቅምት እሸት፣ ማዝ፣ ጃጅ፣ መስከረም ፍሬ እንዲኹም ከሽታ ጤና ጣቢያዎች ሲኾኑ፣ የጤና ሠራተኞች ደመወዛቸው እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው እንደነበርና ኾኖም እስካኹን ምንም መፍትሄ እንዳላገኙ ለዋዜማ አስረድተዋል። በሌላ በኩል ጤና ጣቢያዎቹ ያሏቸው አምቡላንሶች ለወላድ ሴቶች እና ለታማሚዎች አገልግሎት ከመስጠት ይልቅ፣ የወረዳውን የፖለቲካ አመራሮች በማመላለስ ሥራ ተጠምደው እንደሚውሉና ታማሚዎችን ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሆስፒታሎች ለመላክ አምቡላንሶች አይገኙም ብለዋል። አምቡላንሶቹ ለታለመላቸው ዓለማ ብቻ እንዲውሉ ከክልሉ የተሰጠው መመሪያ ሥራ ላይ አለመዋሉን የሚገልጹት ምንጮች፣ ይልቁንም አምቡላንሶቹ ጉዳት ሲደርስባቸውና ጥገና ሲፈልጉ ከእያንዳንዱ ሠራተኛ ደምወዝ ላይ ተቆራጭ ተደርጎ ጥገና እንደሚደረግላቸው ጠቁመዋል።

2፤ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ አምስት ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ካገኙ ሰባት ዐመት እንዳለፋቸው ዋዜማ ካሰባሰበችው መረጃ ተረድታለች። የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የጀነሬተር ወጪ ስለከበዳቸው፣ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን በእጅ ጽሑፍ እንደሚሰጡ ታውቋል። ዳምቤ፣ ምዥጋ እና ዛይ የተባሉ ወረዳዎች የኔትወርክ አገልግሎት ባለማግኘታቸው፣ በተለይ የዛይ ወረዳ ነዋሪዎች ስልክ ለመደወል 72 ኪሎ ሜትር መጓዝ ግዴታ ኾኖባቸዋል። ወረዳዎቹ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙ የነበረው፣ ከኦሮሚያ ክልል በተዘረጋ ማስተላለፊያ ነው። በመተከል ዞን የሚገኙት ድባጤ፣ ቡለን እና ወንበራ ወረዳዎችም ኤሌክትሪክ ኃይል ካገኙ ኹለት ዓመት አልፏቸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የድባጤ ወረዳ አመራሮች ግን የተበላሹ መንገዶች በቅርቡ እንደሚጠገኑና በሦስት ወራት ውስጥ በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች ላይ ጥገና ተደርጎ ሦስቱም ወረዳዎች ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለዋዜማ ተናግረዋል።

3፤ በመቀሌና ዕዳጋ ሀሙስ የተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከላት ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ 640 የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎች ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀላቸውን የመንግሥት ዜና ምንጮች ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽንን በመጥቀስ ዘግበዋል። ባኹኑ ወቅት በሁሉቱ የሥልጠና ማዕከላት፣ 1 ሺሕ 360 የቀድሞ ተዋጊዎች ሥልጠና እየወሰዱ መኾኑን ኮሚሽኑ መናገሩን ዘገባዎቹ ገልጸዋል። ኮሚሽኑ በመጀመሪያው ዙር ትጥቅ የማስፈታት፣ የመበተንና ከኅብረተሰቡ ጋር የማቀላቀል መርሃ ግብር፣ 75 ሺሕ የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ተሃድሶ ማሠልጠኛ ማዕከላት ውስጥ አስገብቶ በማሠልጠን ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ዕቅድ ይዟል።

4፤ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት በሦስት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ የጣሉትን እገዳ ባስቸኳይ እንዲያነሱና በሲቪል ማኅበራት ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት እንዲያቆሙ አዲስ ባወጣው ሪፖርት ጠይቋል። ድርጅቱ፣ መንግሥት በሲቪል ማኅበራት ላይ የሚወስዳቸውን ርምጃዎች ዓለማቀፍ አጋሮች እንዲያወግዙም ጥሪ አድርጓል። ሦስቱ ድርጅቶች የታገዱት፣ መንግሥት በቅርቡ ባዘጋጀው ረቂቅ የመገናኛ ብዙኀን አዋጅ ላይ በርካታ ድርጅቶች በደብዳቤ ያቀረቡትን ትችት ከተቀላቀሉ ከጥቂት ቀናት በኋላ እንደሆነ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠቅሷል። ድርጅቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ጥብቅ ክትትል እንዲያደርግና ሪፖርት እንዲያወጣም ሂውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል።

5፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር፣ በመላ አገሪቱ 283 የሚጠጉ ሕገወጥ ኬላዎች ከሚንስቴር መስሪያ ቤቱ አቅም በላይ መኾናቸውን ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል። ሚንስቴሩ፣ ኬላዎቹ በሸቀጦች ዝውውር ላይ እክል መፍጠራቸውንና ለኑሮ ውድነቱ ዋነኛ ምክንያት መኾናቸውንም ገልጧል። የክልል መንግሥታት ገቢያቸውን ለማሳደግ ሲሉ በጫት ምርት ላይ የሚጥሉት ከፍተኛ ቀረጥ፣ በጫት ላኪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረና አገሪቱ ከጫት የወጪ ንግድ ማግኘት የሚገባትን ገቢ ማግኘት እንዳልቻለችም ሚንስቴሩ ጠቅሷል። ሚንስቴሩ፣ ባለፉት አምስት ወራት ከ105 ሺሕ በላይ በሚኾኑ ያላግባብ ዋጋ በጨመሩ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ እንደተወሰደና 1 ሺሕ ያህል ነጋዴዎች ደሞ በእስራት እንደተቀጡም በሪፖርቱ አመልክቷል።

6፤ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ13ቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል አስሩ ወደ ‘’ልዩ የኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸውን ለኮርፖሬሽኑ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡ ኢንደስትሪ ፓርኮቹ ወደ "ልዩ ኢኮኖሚ ዞን’’ ያደጉት፣ የምርታማነት እንቅስቃሴያቸው ተገምግመሞና አስፍላጊውን መስፈርት አሟልተው በመገኘታቸው እንደኾነ ኮሚሽኑ ገልጧል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ወደ ‘’ልዩ ኢኮኖሚ ዞን’’ ማደጋቸው፣ የግል ዘርፉ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በአገልግሎትና ሌሎች ልማታዊ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲሳተፍ ለማበረታታት፣ የአገሪቱን የውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የመሳብ እንቅስቃሴ ለማጠናከር፣ ምርቶችን ወደ ውጭ የመላክ አቅምን እንዲኹም ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ሸቀጦችን በአገር ውስጥ ምርቶች የመተካት አቅምን ለማሳደግና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል በደብዳቤው ላይ ተጠቅሷል፡፡ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የአዳማ፣ የባሕርዳር ፣ የቦሌ ለሚ፣ የደብረ ብርሃን፣ የሀዋሳ፣ የጅማ፣ የቂሊንጦ፣ የኮምቦልቻ፣ የመቀሌ እና የሠመራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ናቸው ተብሏል፡፡

7፤ ኢሰመኮ፣ የሽግግር ፍትሕ ተቋማትን የማቋቋም ሂደት ተጎጂዎችን ያማከለ እንዲኾን አሳስቧል። ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር በሽግግር ፍትሕ ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ አሳስቧል። ልዩ ችሎቱን ጨምሮ የሽግግር ፍትሕ ተቋማቱ ያለፉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ብቻ ሳይኾን ወደፊትም ጥሰቶች እንዳይፈጸሙ ጠንካራና ነጻ ተቋማትን ለመፍጠር መሠረት ይጥላል ብሏል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምኅረት በበኩላቸው፣ የችሎቱ ማቋቋሚያ አዋጅ ችሎቱ የገለልተኛነት ነጻነት መርኾዎችን መሠረት ያደረገና ዓለማቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ እንዲኾን አሳስበዋል። አርቃቂው ቡድን፣ ተቋማዊ የቅንጅት ማዕቀፍ መፍጠርና በፌደራልና በክልል ማዕቀፎች መካከል ቅንጅታዊ ሥርዓት እንዲኖር ክልላዊ ማዕቀፍ መዘርጋት እንደሚቀር ገልጧል። [ዋዜማ]

EthioTimes

03 Dec, 16:10


ኢትዮጵያ በበጀት ዕጥረት እራሷን ከውድድሩ አገለለች !

የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አዘጋጅነት ከሚካሄደው የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር በበጀት እጥረት ምክንያት ራሷን ማግለሏን እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

EthioTimes

02 Dec, 17:53


ሴት በመምሰል የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች  ጋር በመሆን እየዘረፈ  ሲሰወር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር  ስር ዋለ

በደብረ ማርቆስ ከተማ መኳንት ናጋ የተባለው የ18 ዓመት ወጣት  የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች ጋር በመመሳሰል ሲዘርፍ በቁጥጥር  ስር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ ቀበሌ 08 በአብማ አካባቢ ሴት በመምስል ማታ የወሲብ ንግድ  ከሚሰሩ ሴቶች ጋር አብሮ በመሆን ገንዘብ በመቀበል ከአካባቢው በመጥፍት በተደጋጋሚ   የወንጀል  ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር  ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

EthioTimes

02 Dec, 15:17


ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ከተማ ሲ.ኤም.ሲ ሚካኤል አካባቢ ዛሬ ከረፋዱ 5:30 ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት አልፏል።

አደጋው የሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ከሞተር ሳይክል ጋር በመጋጨቱ በተከሰተ ሲሆን፤ በግጭቱ ምክንያት ሞተር ሳይክል የሚያሽከረክረው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱ ማለፉን አሐዱ በቦታው ተገኝቶ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

በአካባቢው የተገኙት የትራፊክ ፖሊስ እና የጸጥታ አካላት ጉዳዩን እያጣሩት መሆኑን ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡

ጉዳቱን ያደረሰው አሽከርካሪም እጁን ለጸጥታ አካላት መስጠቱን አረጋግጠናል።

@አሐዱ ሬዲዮ

EthioTimes

02 Dec, 10:02


አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ ‼️
*******
በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በደባርቅ ወረዳ ቤተክህነት ስር በአደጋት ቀበሌ ውስጥ የሚገኘው የምራዕፈ ቅዱሳን አፅሐራራ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድነት ገዳም በእናታችን ቅድስት አመተ ክርስቶስ በ14ኛዉ ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ታላቅ እና ታምራዊ ገዳም ነው በጊዜ ብዛት የድሮው ቤተክርስቲያን ፈርሶ አሁን በዚህ በምስሉ እንደምታዮት ሊያልቅ የቆርቆሮ ,የመስኮት እና የበር እጥረት ያጋጠመው ስለሆነ በውስጥም በውጭም ያላችሁ ወገኖቻችን በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የአቅማችሁን በማገዝ ከበረከቱ እንድትሳተፉ እንለምናችዋለን‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000331624334
☎️ 0934654964 ወይም 0918532706
ለብዙዎች እንዲዳረስ ሼር አድርጉት‼️

EthioTimes

02 Dec, 07:57


"በእንጦጦዋ ኪዳነ ምህረት በእግሬ ቆሜ መራመድ ቻልኩኝ። ዶክተሮቹ 6 ወር እድሜ ብቻ እንዳለኝ ነገሩኝ ከዛ ሀገሬ ሄጄ ልሙት ብዬ መጣው ።"‼️

"ከመጣሁ 6 ቀኔ ነው የእንጦጦዋን ኪዳነምሕረት ፀበል እየጠጣው ይህው አሁን በእግሬ ቆሜ ለመራመድ በቅቻለሁኝ። መጀመሪያ እንዲህ ጉልበት አልነበረኝም፤ አሁን ግን ተመልከት"

"አሜሪካን ሀገር ሁለት ጊዜ የመኪና አደጋ አጋጠመኝ፤ ስመረመር ዶክተሮች የጀርባ አጥንት ካንሰር ይዞሃል እሱም ወደ ጉበትህ ሄዷል እንዲሁም የጉበትም ካንሰር አለብህ አሉኝ። ብዙም እንደማልቆይ ነገሩኝ። እኔ ግን እግዚአብሔር ያሸንፋል አልኩ። እነሱም በጣም ገረማቸው"

አርቲስት አሳዬ ዘገየ ሰይፉ ሾዉ ላይ ቀርቦ ከተናገረው የተወሰደ።
እግዚአብሔር ጨርሶ ይማርህ🙏

EthioTimes

01 Dec, 15:47


በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ቼልሲ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ከ30 በስታምፎርድ ብሪጅ አስቶንቪላን ያስተናገደው ቼልሲ በኒኮላስ ጃክሰን፣ ኤንዞ ፈርናንዴዜ እና ኮል ፓልመር ጎሎች 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ሌላ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ፤ ጆሽዋ ዚርኬዜ (ሁለት) እና ማርከስ ራሽፎርድ (ሁለት) ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የመጀመሪያ የፕሪሚየርሊጉ ድላቸውን አስመዝግበዋል፡፡

በቶትንሃም ስታዲየም በተደረገ ሌላው የቶተንሃም እና ፉልሃም ጨዋታ አንድ አቻ ሲለያዩ፤ ቤርናን ጆንሰን የቶተንሃምን ቶማስ ካርኔይ ደግሞ የፉልሃምን ጎል አስቆጥረዋል፡፡

የ13ኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብሮች ሲቀጥሉ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከማንቼስተር ሲቲ በአንፊልድ የመሚያደርጉት የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

EthioTimes

01 Dec, 15:36


https://youtu.be/Ak2HsG3CjpE?si=2JQE99l0tGDaFLJ8

EthioTimes

01 Dec, 11:05


አትሌት መገርቱ አለሙ የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ሆነች

#Ethiopia | ዛሬ ረፋዱን በተካሄደው የቫሌንሲያ ማራቶን ውድድር የአሸናፊነት ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረችው አትሌት መገርቱ አለሙ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌቷ የውድድሩን ርቀት ለማጠናቀቅ 2ሰዓት ከ16 ደቂቃ፤49 ሴኮንድ ፈጅቶባታል።

ሌላዋ በውድደር የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩዬ መስፍን ሶስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

ዩጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንድ ደግሞ የሁለተኝነቱን ደረጃ ወስዳለች።

ባለፈው አመት በተካሄደው የቫሌንሲያ ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት ማጠናቀቃቸው አይዘነጋም።

በወቅቱ አትሌት ወርቅሽ ደገፋ በቀዳሚነት ስትገባ ሌላኛዋ የኢትዮጵያ አትሌት አልማዝ አያና ሁለተኛ አትሌት ህይወት ገብረኪዳን ሶስተኛ በመግባት አሸንፈዋል።

የቫሌንሲያ ማራቶን የሴቶች ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት አማኔ በሪሶ ስትሆን ከሁለት አመት በፊት በተካሄደው ውድድር ርቀቱን በ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባ ማሸነፏ ይታወሳል።

አትሌቷ በዘንድሮው የቫሌንሲያ ማራቶን ላይ በጉዳት ምክንያት እንደማትሳተፍ ተገልጿል።

EthioTimes

28 Nov, 12:44


ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል  የሚያስችል አዲስ መድሃኒት በስኬታማ ሁኔታ ተሞከረ

በየሳምንቱ  በጤና ጉዳይ ላይ የሚዘግበው "ኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜዲስን" ይፋ እንዳደረገው፤ ሌናካፓቪር (Lenacapavir) የተባለ መድሃኒት በየስድስት ወራት መከተብ በ ኤችአይቪ ተህዋሲ መያዝን በተሳካ ሁኔታ ይከላከላል።

በአሁኑ ጊዜ ኤች አይ ቪን ለመከላከል በተህዋሲው የተያዙ ሰዎች በየቀኑ መድሃኒት መወሰድ ግድ ይላቸዋል።

ይሁንና አዲሱ የሌናካፓቪር  ሕክምና በዓመት በሰው 42,000 ዶላር ያህል ወጪ ስለሚያስወጣ እጅጉን ውድ ነው ተብሎለታል።

እንደ ተባበሩት መንግስታት የኤድስ ፕሮግራም UNAIDS ባለፈው የጎርጎሮሲያውያን ዓመት 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኤች አይ ቪ ተህዋሲ ተይዘዋል።

630 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ የኤድስ ታማሚዎችን ይበልጥ በሚያጠቁ በሽታዎች ሞተዋል።

EthioTimes

28 Nov, 12:08


ካህኑ አሮን ትልቅ ጭንቅ ውስጥ ገባ፡፡ እምቢ ቢላቸው እስራኤል ቁጡዎች ናቸውና እንደሚገድሉት ያውቃል፡፡ እናም ለገንዘብ ባለቸው ከፍተኛ ፍቅር ምክንያት እምቢ ይሉኛል ብሎ “ከግብጽ ያወጣችሁትን ወርቅና ብራችሁን አምጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ሰይጣን አነሳስቷቸዋልና እንዋል እንደር ሳይሉ ወዲያው ሰጡት፡፡ ያንን አቅልጦ ጣኦት ሰራላቸው፡፡ ለጣኦቱ እየሰገዱ ሲበሉ ሲጠጡ ሲዘፍኑ ቢያይ እግዚአብሔር አዘነና ለሙሴ “ሕዝብህ እስራኤል ከዱኝ፣ እነርሱን ላጥፋቸውና አንተን በሌላ ታላቅ ሕዝብ ላይ ልሹምህ” አለው፡፡

ሙሴ ግን “አቤቱ እነርሱን ከምታጠፋቸው እኔን ከጻፍከኝ ከሕይወት መጽሐፍና ከቅድስቲቱ ከተማ ሰርዘኝ” ሲል ራሱን ለሕዝቡ ቤዛ አድርጓል፡፡ ከሲና ከወረደ በኋላም ፍቅረ ጣኦት ያደረባቸውን ሰዎች በሞት ቀጥቷል፡፡

መንፈሳውያን አባቶችና ገዳማውያን መነኮሳት ለሰራነው በደልና ኃጢአት የሚያመጣብንን መከራ ይመልሰው ዘንድ፣ ብሎም በእኛ ጥፋት ምክንያት የመጣው መከራ እነርሱን ያገኛቸው ዘንድ ሌት ተቀን ይጸልያሉ፡፡ ስለ ኃጢአታችን ስርየት የሚጸልዩበት ገዳማቸው ምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌለውና እነርሱም ለችግር የተጋለጡ ሲሆኑ ማገዝ ደግሞ እኛን የበረከቱ ተሳታፊ ያደርገናል፡፡   

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሣ  ማር  ቅዱስ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444

ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444

EthioTimes

28 Nov, 12:08


🙏🙏🙏

#እኔን ከጻፍከኝ ከሕይወት መጽሐፍና ከቅድስቲቱ ከተማ ሰርዘኝ

በረከቱ ይደርብንና ነቢየ እግዚአብሔር፣ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት መርቶ ካወጣ በኋላ በደብረ ሲና ሕግ ሲሰራለት ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ 40 ቀንና 40 ሌሊት ይቆያል፡፡ በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ወደ ወንድሙ አሮን ሔደው “ሙሴ ደብረ ሲና ሄዶ የሆነውን አናውቅምና አማልክት የሚሆነን ጣኦት ስራልን” አሉት፡፡ ከ400 ዓመታት በላይ ከነበሩበት ባርነት ያወጣቸውን እግዚአብሔር ረሱት፡፡

በጨነቀን ጊዜ፣ ያመነው የተመካንበት ሁሉ በከዳን ጊዜ፣ አብቅቶልናል ባልንበት አጋጣሚ የደረሰልንን የእግዚአብሔርን ውለታ የረሳን ስንቶች ነን፡፡ ባጣን በነጣን ጊዜ ጠይቀነው አትረፈርፎ የሰጠን እግዚአብሔር ያደረገልንን ረስተን፤ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት ሲቸገሩ እያየን ሞልቶ ከፈሰሰው ሃብታችን ላለመስጠት ዝም የምንል ስንቶቻችን ነን፡፡
 

EthioTimes

27 Nov, 10:16


“ሙዚቃው በአሁን ሰዓት ዳግም እንዲለቀቅ መደረጉ ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

ከ40 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰተውን የ1977 ዓ.ም ድርቅ ለዓለም ድምጽ ለመሆን እና ገቢ ለማሰባሰብ በማሰብ የሰሩት ዘፈን አሁን ለመታሰቢያነት ዳግም እንዲለቀቅ መደረጉ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልጸዋል።

"የሀገራችን ጥንታዊ ታሪክ፣ ባህል፣ ልዩነትና ውበት ወደ ጥፋትና ድቅድቅ ጨለማ ሲገባ ማየት ተስፋ አስቆራጭ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዘታይምስ መጽሄት ጋር ባደረጉት ቆይታ ይህን የተናገሩ ሲሆን አሁን ላይ ኢትዮጵያ ሙዚቃው ላይ እንደተገለጸችው ሳትሆን በፈጣን እድገት ውስጥ የምትገኝ መሆኗን ገልጸዋል።

ሙዚቀኞቹ በወቅቱ የሰሩት ሥራ የሚያስመሰግናቸው ቢሆንም ሙዚቃው ዛሬ ላይ ከጊዜው ጋር አብሮ አለመሄዱ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊያመዝን እንደሚችል ጠቁመዋል።

የሙዚቃው ርዕስ “የገና በዓል መሆኑን ያውቁ ይሆን “ መባሉ እንደሚረብሻቸው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  ኢትዮጵያ የኢየሱስን ክርስቶስን ልደት ከዓለም በፊት ያከበረች ሃገር እንደሆነች አስታውሰዋል።

አንዳንድ የሬዲዮ ጣቢያዎች ስለ አፍሪካ ጊዜ ያለፈባቸውን ጽንሰ ሐሳቦች የሚያጠናክር ታሪኮችን ወይም ዘፈኖች የመጫወት ወይም የማስተዋወቅ አዝማሚያ እንዳላቸው ጠቁመው ይኼንን የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ አስመልክቶ የባንድ ኤድ ጥንቅር ዛሬ ላይ ከግንዛቤ ማስጨበጥ ይልቅ ኢትዮጵያ በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት ሀገሮች መካከል መሆኗ ቢታወቅ ይሻል ነበር ብለዋል።

"ዘፈኑ ለሚያስፈልገን ኢንቨስትመንት ድምፅ አይደለም፤ ረሃብ እንደ ሀገር ወይም አህጉር ማን መሆናችንን አይገልፅም እንግሊዝ እንኳን በታሪኳ የረሀብ ዘመን አጋጥሞት ነበር" ብለዋል፡፡

EthioTimes

25 Nov, 12:56


ፒያሳ የእሳት አደጋ ተከስቷል

በተለምዶ ፒያሳ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው የእሳት አደጋው የተከሰተው።

የእሳት አደጋው የተከሰተበት ስፍራ ላይ ቻይኖች ሲሚንቶ እና ኮንክሪት የሚያዘጋጁበት ስፍራ ነው

በስፍራው ሲሚንቶና ኮንክሪት ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ ኬሜካሎች እንዳሉ ነው የተነገረው።

እንደዚሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅም በዚሁ ስፍራ እንዳለ ነው የተነገረው።

ለተለያዩ አገልግሎት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎችም አደጋው በደረሰበት ቦታ መኖሩን ተመልክተናል።

እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው እርብርብ እያደረጉ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስም ባካባቢው ደርሶ ጥበቃ እያደረገ ነው የሚገኘው።

EthioTimes

25 Nov, 11:55


ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ 15 ሺህ የአሜሪካ ጦር አባል ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ተገለጸ‼️

ከአንድ ወር በፊት 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት ዶናልድ ትራምፕ ጥር አጋማሽ ላይ ስልጣን የሚይዙ ሲሆንካቢኔያቸውን ከወዲሁ እያዋቀሩ ነው።

የፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጁ ፔቴ ሄግሴትን የመከላከያ ሚንስትር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

ሰዎች ተፈጥሯዊ ጾታዎችን መቀየር የለባቸውም ብለው የሚያምኑት ዶናልድ ትራምፕ ጾታቸውን የቀየሩ እና የሀገሪቱ ጦር አባላት የሆኑ ወታደሮችን ከስራ እንደሚያግዱ ታይምስን ዋቢ አል አይን አስነብቧል።

እንደዘገባው ከሆነ ዶናልድ ትራምፕ 15 ሺህ ጾታቸውን የቀየሩ ወታደሮችን የማባረር እቅድ አላቸው።

ከዚህ በተጨማሪም ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ አሜሪካዊያን የሀገሪቱን ጦር መቀላቀል እንዳይችሉ እገዳ እንደሚጥሉም ተገልጿል።

ዶኔልድ ትራምፕ በከ2016-2020 ድረስ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ዓመታት ውስጥ ተፈጥሯዊ ጾታቸውን የቀየሩ ዜጎች የአሜሪካ ጦርን እንዳይቀላቀሉ እገዳ ጥለው የነበረ ቢሆንም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ይህንን እገዳ አንስተውት ነበር።

EthioTimes

25 Nov, 10:41


በግዙፉ የመገበያያ ስፍራ ' መርካቶ ' ያለው የንግድ እንቅስቃሴ።
📷 Tikvah Ethiopia

EthioTimes

25 Nov, 09:57


ለአክሱም ፅዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንደሚገኙ ይጠበቃል ተባለ፡፡

የአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ለዓመታዊው የአክሱም ጽዮን ማርያም ክብረ በዓል 1 ሚሊዮን የሚጠጉ እንግዶች እንዲሚጠበቁ ገልጿል።

የቱሪዝም ፅ/ ቤቱ ሀላፊ አቶ ገብረመድህን ፍፁምብርሀን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት÷ ህዳር 21 በሚከበረው የንግስ በአል ላይ 5 ሚሊዮን ብር ገቢ ይገኛል የሚል ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል።

ቢሮው የከተማውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ከሚደግፉ ነገሮች አንዱ የአክሱም ፂዮን የንግስ በአል እንደሆነ ገልፆ፤ በዚህም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ አንስቷል።

ከሰሜኑ ጦርነት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረውን የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ለመመለስ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውም ሃላፊው ተናግረዋል።

ለበአሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል የከተማ አስተዳደሩ ከከተማው ህዝብ ጋር በመሆን የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ እንደሚገኙም ሰምተናል።

EthioTimes

24 Nov, 15:24


ብሪታኒያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር መንደር የታዩት ባለቤት አልባ ድሮኖች

ብሪታኒያ በሚገኙ ሶስት የዩናይትድ ስቴትስ የጦር መንደሮች አካባቢ ባለቤትነታቸው ያልታወቁ ድሮኖች እንደታዩ የአሜሪካ አየር ኃይል አስታወቀ።

ከረቡዕ እስከ አርብ ባሉት ቀናት “አነስተኛ ሰው አልባ በራሪዎች” ሰፎክ፣ ፌልትዌል እና ኖርፎክ በተባሉ የጦር መንደሮች አካባቢ መታየታቸውን አየር ኃይሉ ገልጿል።

አየር ኃይሉ በሶስቱ የአሜሪካ ጦር መንደሮች የታዩት ድሮኖች ጥቃት ለማድረስ የመጡ ስለመሆናቸው እስካሁን የሚታወቅ ነገር የለም ብሏል።

የአሜሪካ አየር ኃይል ድሮኖቹን ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ ይኖር እንደሁ ከመለግፅ የተቆጠበ ቢሆንም “ራስን ለመከላከል” የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎች ማድረጉን አስታውቋል።

በአውሮፓ የዩናይትድ ስቴትስ አየር ኃይል ቃል አቀባይ “አነስተኛ ሰው አልባ በራሪዎች ብሪታኒያ በሚገኙ ሶስት የአሜሪካ አየር ኃይል ጣቢያዎች መታየታቸውን አረጋግጠናል” ብለዋል።

“ወታደራዊ ደኅንነታችን ለመጠበቅ ሲባል ምን ዓይነት እርምጃ እንደወሰድን አንገልፅም፤ ነገር ግን ራሳችንን ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ እንደምናደርግ እንሳውቃለን” ብለዋል ቃል አቀባዩ።

EthioTimes

24 Nov, 08:32


#ያዩ አይኖቻችሁ፣ የሰሙ ጆሮቻችሁ ብጹዓን ናቸው

በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ምስጢር በሚከናወንበት ስርዓተ ቅዳሴ ወቅት ቅዱስ ወንጌል ከመነበቡ በፊት ዲያቆናቱ ለምስባክ ሲወጡ ሰራኢው ካህን ጌታችን ለቅዱሳን ሐዋርያት የተናገረውን  "ብዙ ነቢያት ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ፈለጉ አላዩም፣ ዛሬ እናንተ የምትሰሙትን ሊሰሙ ወደዱ አልሰሙም፤ የእናንተ ግን ይህን ያዩ አይኖቻችሁ፣ የሰሙ ጆሮቻችሁ ብፁዓን ናቸው።  (ማቴ.13፥16) ይላሉ።

ብዙ ነቢያት ጻድቃን ለማየት ፈልገው ያላዩት፣ ሊሰሙ ፈልገው ያለሰሙት ምን ነበር? ከዐበይት እስከ ደቂቀ ነቢያት የጌታችንን ሰው መሆንና ማዳን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኘተው፣ በትንቢት መነጽር ተመልክተው ቢናገሩም ማዳኑን በዘመናቸው አላዩም፣  ይህ ድንቅ ምስጢር ፈጥኖ እንዲገለጥ አቤቱ ጌታችን ሆይ ውረድ፤ ተወለድ፤ አድነን›› እያሉ ይጾሙ ይጸልዩ ነበር። ቅዱሳን ሐዋርያት ግን ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዋለበት እየዋሉ ባደረበት እያደሩ በቃልና በተግባር ሲማሩ ኖረው፣ ማዳኑን አይተው ለአባቶቻችን፣ አባቶቻችንም ለእኛ ገለጡት።

እኛም የቅዱሳን ሐዋርያትን ዓይን፣ ዓይን አድርገን አየነው ዳሰስነው፣ ከእርሱም ጋራ በላን ጠጣን እንዲል አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም፣ የጌታችንን ማዳን አምነን ተቀብለን ስጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን ልጅነትን እናገኛለን፣ መንግሥቱንም እንወርሳለን።
ታዲያ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳን ነቢያትን ጾም ከሰባቱ አጽዋማት እንዱ እድርጋ ከህዳር 15 እስከ ታህሳስ 29 እንደንጾም ለምን ታደርጋለች? ነቢያት የተናገሩለት፣ የማዳን ሥራ ተፈጸመልን፣ ወርዶ ተወልዶ አዳነን ስንል እንጾማለን። ላመነውም ማዳኑን ያዩ አይኖቻችን፣ የሰሙ ጆሮቻችንም ብጹዓን ናቸው።

EthioTimes

24 Nov, 08:32


ጾም በስጋም ብነፍስም በርካታ በረከት እንድናገኝ የሚረዳ ትልቅ መሳሪያ ነው። በነፍሳችን መንግስተ ሰማያት የምንወርስበት፣ የጠላትን ኃይል የምንደመስስበት፣ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት፣ ንስሐችንን የምንፈጽምበት ኃጢአታችን የሚሰረይበት ነው። በስጋችንም የጾም በረከት እጅግ በርካታ ነው። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የደምና የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ፣ የስብ ክምችትን ለመቀነስ፣ የአንጎላችንን እንቅስቃሴ ለማቀላጠፍ፣ የካንሰር ሕዋሳትን እድገት ለመከላከል፣ ወቅት የመከላከል አቅም እንዲዳብርና፣ ለቆዳ ጥራት ጭምር ትልቅ እገዛ አለው።

ጾም የቃሉ ትርጉም መከልከል ማለት ነውና በጾም ወቅት አእምሯችንንና ሰውነታችንን ከስጋ ስራ ማቀብ በነፍስ መንገድ መመላለስ ይገባል። የተራቡ የተጠሙ ወገኖችን መዘከር፣ በጸሎት መትጋት፣ ቅዱሳን መካናትንና ገዳማውያን አባቶችን ማሰብ ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ትልቅ ተግባር ነው። ወደ ቅዱሳን መካናት ስንሔድ፣ ገዳማውያኑን ስናግዝ ልዩ በሆነው ጸሎትና ቡራኬያቸው እንቀደሳለን።

እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ።

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

EthioTimes

23 Nov, 16:34


መረጃ ‼️

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ የሚያደርግ መኾኑን ዛሬ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።

ባንኩ የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ የሚያደርገው፣ ለደንበኞቹ በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል እንዲኹም ዓለማቀፍ የባንክ አገልግሎቶች እንደኾነ ገልጧል።

EthioTimes

21 Nov, 17:08


መደበኛ ሎተሪ 1725ኛ ዕጣ ዛሬ  ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ  አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮችም ከዚህ ጋር ተያይዟል።

EthioTimes

20 Nov, 06:08


ለፖሊስ የቤት ስራ የሆኑት የታይላንድ ጦጣዎች

Via : fidel

EthioTimes

19 Nov, 15:53


https://www.youtube.com/watch?v=ibYARYn7qzE&t=31s

EthioTimes

17 Nov, 09:58


በመርካቶ ቃጠሎ ተከስቷል

በመርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ ድንች በረንዳ ዛሬ ህዳር 8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 የእሳት አደጋ ተከስቷል።

EthioTimes

16 Nov, 15:53


የዲኤንኤን ምርመራ በኢትዮጵያ ተጀመረ

የዲኤንኤን ምርመራ በኢትዮጵያ መጀመሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ "ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ የፎሬንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን መርቀናል" በማለት ገልፀዋል።

የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ ከነበረበት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥማት በራሷ መስራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም መገንባቱንም ተናግረዋል።

EthioTimes

16 Nov, 09:08


በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ተሳታፊዎች ፣ አምባሳደሮች ፣ ተጋባዥ አትሌቶች የሚታደሙበት መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የሩጫ ውድድር ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር የውድድሩ ተሳታፊዎች ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ ገልፆ  የወድድሩ ተሳታፊዎች  በሚያልፉት አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አዲስ አበባ ፖሊስ  ጥሪውን እያስተላለፈ  ውድድሩ የከተማችንን ዋና ዋና መንገዶች የሚያካልል በመሆኑ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ ውድድሩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት  አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው  ስራ መጀመራቸውን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል። ከውድድሩ ዓላማ ውጪ ህገ-ወጥ ተግባራትንና መልእክቶችን ማስተላለፍ የውድድሩን መንፈስ የሚረብሽ ስለሆነ አዘጋጅ ተቋሙ እና ተሳታፊዎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደለባቸው እያሳሰበ ውድድሩ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፡-

-ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
-  ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
-   ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
-ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
-  ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
  ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
-  ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
-  ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
-  ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
-  ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
-  ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
-  ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት  (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
-  ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
-  ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
-   ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
-  ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
-  ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት  አደባባይ)
-  ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
-  ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
-  ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
-  ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን  (ጥቁር አንበሳ ሼል)
-  ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
-  ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

EthioTimes

16 Nov, 09:08


ለ24ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

EthioTimes

16 Nov, 02:30


የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል!

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ  ከቀኑ  8:00   ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

Via EEP

EthioTimes

15 Nov, 16:46


የህፃን ሀሴት ደፋሪ ካስትሮ ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል::


በህፃን ሀሴት አድማሱ ላይ የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመው ተከሳሽ በ13 አመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ተገለፀ

በሠላም በር ከተማ አስተዳደር ዳምባዬ  የሆኑት የ11 ዓመት ህፃን ሀሴት አድማሱን በግምቱ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ለልጅቷ አባት የቅርብ ጓደኛ መሆኑን በማሳበብ   የልጅቷ አባትና እንጀራ እናቷ ሥራ ቦታ መኖራቸውንና በመኖሪያ ቤታቸው ማንም አለመኖሩን በማረጋገጥ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በማቅናት በሩን በማንኳኳት ካስትሮ ነኝ በሩን ክፈቺ በማለት ወደ ቤት እንደገባ ብቻዋን ያለችውን

ህፃን ጎሮሮዋን አንቆ በመያዝ ራሷን እንዳትከላከል በማድረግ የኢፌዲሪ ወንጀል አንቀጽ 627(1) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ መተላለፋን አቃቤ ህግ ለሰላምበር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ችሎት ያቀረበው ክስ አመላክቷል።

በዚህ መሠረት ተከሳሽ አቶ ካስትሮ ካባሎ ካብሮ በተከሰሰበት በህፃናት ልጆች ላይ በሚፈጸም የግብረስጋ ድፍረት በደል በማድረስ ወንጀል ዐቃቤ ህግ ለፍርድ ቤቱ  ባቀረበው በሰውና በሰነድ ማስረጃ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

የሠላምበር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሽ ከዚህ በፊት ግለሰቡ የወንጀል  ሪከርድ የለኝም ልጅና ምስት በክራይ ቤት የጉልበት ሥራ ሠርቼ አስተዳድራለሁ በማለት ያቀረበውን ሁለት የውሳኔ ማቅለያ ፍርድ ቤቱ በመገንዘብ

ከነበረበት የወንጀል እርከን 34 ወደ እርከን 32 ዝቅ በማድረግ ፍርድ ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ተከሳሽን ያርማል ሌላውንም መሰል ወንጀል አድራጊዎችን ያስተምራል በማለት

ከግራና ከቀኝ የተነሱ የቅጣት አስተያየት በመውሰድ ዛሬ በዋለው ችሎት ተከሳሽ እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ መነሻ ቅጣት በኢፌዲሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 627/1  በመተላለፍ ወንጀል በ13 አመት ጽኑ እስራት እንድቀጣ የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።

EthioTimes

14 Nov, 18:08


https://youtu.be/hbG21yREfSE?si=Z0yIMCcH88ITcn8T

EthioTimes

14 Nov, 18:07


የአንድ ቀን ህፃን ልጅ ተጥላ ተገኘች‼️

እንሴኖ፣ህዳር 5/2017 ዓ.ም በእንሴኖ ከተማ አስተዳደር ጫፍ እንሴኖ ኡስሜ ቀበሌ መውጫ ለሊት ላይ በአንድ መኖሪያ ቤት ከግቢ አጥር ውጪ አጠገብ የአንድ ቀን ህፃን ተጥላ ተገኝታለች።

በዚህም የቤተሰቡ አባላት ጠዋት ከመኖሪያ ቤታቸው ግቢ ውጭ ያገኟትን ህፃን ለከተማው ፖሊስ ፅ/ቤት አስረክበዋል።

የፖሊስ አባላቱ ከመንገድ ትራንስፖርትና መንገድ ደህንነት ጋር በመሆን ለህፃኗ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በማሟላት እንዲሁም የተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንድታገኝ ያደረጉላት ሲሆን

በአንዲት አጥቢ የፖሊስ አባላት አማካኝነት ለህፃኗ ጡት እንድትጠባና እና እንክብካቤ እየተደረገላት መሆኑን ከፖሊስ ፅ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

EthioTimes

13 Nov, 19:43


#FactCheck "የድሮ ፎቶ" እንዲመስል በቅንብር የተሰራ ምስል

'አበበ ቶላ ፈይሳ' የተባለ ፌስቡክ ላይ ከ158 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ግለሰብ "የድሮ ፎቶ እያወጣህ እንደ አዲስ የምትለጥፍ ከሆነ..." በሚል ያሰራጨው ምስል እንዳለ ተመልክተናል።

ግለሰቡ በዚህ ልጥፉ ላይ ከትናንት ጀምሮ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ሲንሸራሸር የነበረው የፋኖ ሀይሎች አመራር የሆነው የዘመነ ካሴ ምስል "ዓመት የሞላው" መሆኑን ገልጿል። 

ይህን ያሳያሉ ያላቸውን እና የፋኖ አመራሩን ፎቶ አምና፣ ማለትም እአአ በ2023 የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች አጋርተውት ነበር ያላቸውን ምስሎች አያይዟል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ማጣራት እንዲያደርግ ጥያቄ የቀረበለት ሲሆን እኛም በዚህ ዙርያ ፍተሻ አርገናል።

በዚህ ዙርያ ባደረግነው ማጣራት ምስሎቹ የድሮ እንዲመስሉ '2023' የሚል ዓመት በፎቶሾፕ ቅንብር እንደገባባቸው ተመልክተናል። ቅንብሩ ሲሰራም የፌስቡክን ዲዛይን በማይመስል መልኩ ተጣሞ እና ከዲዛይን ውጪ ክፍተት ኖሮበት ሆኖ እንደተሰራ መመልከት ይቻላል።

ከዚህም በተጨማሪ መረጃውን አጋርተዋል ወደተባሉት የፌስቡክ ገፆች እና አካውንቶች በመሄድ ምርመራ ያደረግን ሲሆን "የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት" ከሚለው ፅሁፍ ጋር ተጋርቶ የነበረው ሌላ የፋኖ አመራሩ ምስል መሆኑን ለማየት ችለናል።

በዚህም ምክንያት 'አበበ ቶላ ፈይሳ' በተባለው ግለሰብ የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና በቅንብር የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል።

ከአውድ ውጪ ከሚቀርቡ፣ በቅንብር ከሚሰሩ እና ተጋነው ከሚሰራጩ መረጃዎች ራሳችንን በማራቅ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን እንከላከል።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck

EthioTimes

13 Nov, 04:13


https://youtu.be/nLd0yqOx_Lw?si=BnTGdgZp1SfKHmz4

EthioTimes

11 Nov, 17:54


አቃቤ ህግም የወንጀል መዝገቡን መርምሮ በህገወጥ መንገድ ሰዉን በማገት እና ያልተገባ ገንዘብ በመጠየቅ ህግ 586 እና 590 ንዑስ አንቀፅ 1ን በመጥቀስ ክስ የመሰረተበት መሆኑ ተገልጿል ።

ክሱን ሲመለከት የነበረዉ የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥቅምት 14/2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ዘላለም ስማቸዉ በፈፀመዉ የሰዉ ማገት ወንጀል ጥፉተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ11 አመት እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከአምቦ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ያገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

EthioTimes

11 Nov, 17:54


የ 10 አመት ታዳጊን በማገት 3 መቶ ሺህ ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ወረዳ ሰንቀሌ ፋሪስ የተባለ አከባቢ የ 10 አመት ታዳጊን አግቶ በመዉሰድ ከወላጆቹ 3 መቶ ሺህ ብር የጠየቀዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የአምቦ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፀ።

እንደ አምቦ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፃ ዘላለም ስማቸዉ የተባለዉ ግለሰብ ህፃኑን አግቶ በመዉሰድ ወላጆቹ ጋር በመደወል በላከላቸዉ አካውንት 3 መቶ ሺህ ብር ካላስገቡ ልጃችዉን በህይወት እንደማያገኙት ሲያስፈራራቸዉ እንደነበረ መግለጫው ጠቅሳል።

ግለሰቡ ወላጆቹ ጋር በተደጋጋሚ በመደወል ህፃኑን በመደብደብ እያስለቅሰ ሲያሰማቸዉ እንደነበረ እና የተጠየቁትን ብር በአስቸካይ በተለከላቸዉ አካዉንት ካላስገቡ የልጃቸዉ በህይወት የመኖር ዕጣ በእጅ ላይ እንደሆነ እና ቤታቸዉንም በእሳት እንደሚያጋየዉ በማስፈራራት ወላጆችን ሲያስጨንቅ እንደነበርም ተገልጿል ።

ወላጆችም ከተጠየቁት የገንዘብ መጠን ዉስጥ 60 ሺህ ብር በተላከላቸዉ አካዉንት አስገብተዉ ልጃቸዉን በማስለቀቅ ድርጊቱን ለፖሊስ አሳዉቀዋል። ፖሊስ ባደረገዉ ክትትል ተከሳሹን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አዉሎታል።ተካሳሹም በሰጠዉ ቃል ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ መሆኑን በማመኑ የምርመራ መዝገቡ በሰዉ ማስረጃ እና በተላከዉ የባንክ አካዉንት ማስረጃነት በማጠናቀር ለአቃቤ ህግ መላኩ ተገልጿል።

EthioTimes

26 Oct, 13:11


የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከሰተ‼️
በአፋር ክልል አዋሽ ከደቂቃዎች በፊት 8:16  እና 8:51 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ንዝረት ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተሰምቷል።
አዲስ አበባ ሰሚት፣አያት እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር፣ልዩአምባ በዚህ ሰዓት(9:25) በሌሎች ቦታዎችም ንዝረቱ ተሰምቷል።
የዛሬው ንዝረት ከባለፈው ከበድ ያለ እንደሆነም ነዉ የተገለጸው።

EthioTimes

25 Oct, 17:55


በኢትዮጵያ እግርኳስ ስማቸው በወርቅ ቀለም በደማቅ ታሪካቸው ከተፃፈላቸው የእግርኳስ ሰዎች መካከል አንዱ የነበረው አሰልጣኝ አስራት ኃይሌ (ጎራዴው) በመጨረሻም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ነፍስ ይማር!

EthioTimes

25 Oct, 11:16


5. አቶ ፈንታሁን ስጦታው ፈለቀ  - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ግብርና ጥራትና ደህንነት ባለስልጣን ኃላፊ

6. አቶ ደምስ እንድሪስ ይማም - የአብክመ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

7. አቶ ጥላሁን ፈንታው ተሾመ -  የአብክመ ፕላን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

8. ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ አማረ -  የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ሙሉነህ ዘበነ ሳህሌ - የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

10. ወ/ሮ አትክልት አሳቤ ታምሩ - የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ዘላለም አረጋ መኮነን - የአብክመ ወጣትና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

12. ወ/ሮ ሃናን ይመር አሊ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ሴ/ህ/ማ/ጉ ቢሮ ረዳት አማካሪ

13. አቶ አባይነህ ጌጡ ያሬድ  - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ

14. አቶ አታላይ ክብረት ማሩ - በኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የክልል ተቋማት ክትትል አማካሪ

15. አቶ ይርጋ አላምነህ ወርቅነህ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርዕሰ መስተዳደር ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ረዳት አማካሪ

16. ወ/ሮ ውዴ እውነቱ አዳምነው - በምክትል ኤጀንሲ ኃላፊ ደረጃ የካቢኔ ሴክረታሪያት ኃላፊ

17. አቶ ዳዊት አቡ አለሙ -  የጣና ሐይቅና ሌሎች ውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ኃላፊ

18. አቶ ወርቁ ኃ/ማርያም ጌጡ - የአብክመ በየነ መንግስታት ግንኙነት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

19. አቶ ዮናስ ይትባረክ አበበ - በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአማራ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ልማትና ማስፋፊያ ድርጅት ስራ አስኪያጅ

20. አቶ ፋሲል ሰንደቁ አደመ - በም/አስተዳዳሪ ማዕረግ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት እና  አደረጃጀት ዋና አማካሪ

21. አቶ ሙሉጌታ ንጋቱ ለገሰ  -  የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ዉሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ

22.አቶ ስጦታው ሰጤ ነጋሽ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ

23. ወ/ሮ ካሳየ ስመኝ ዋሴ - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ደንና አካባቢ ጥበቃ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ

24. አቶ ሙሉጌታ አለም አድገህ   - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ

25. አቶ አግማስ  አንተነህ ውቤ - የምዕ/ጎጃም ዞን አስተዳደር  ምክትል አስተዳዳሪና ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ

26. አቶ  መንግስቱ  አየለ ደምለዉ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር  መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ

27. አቶ  ስጦታው መርሻ አጆነህ - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር  ማዕድን መምሪያ ኃላፊ

28. አቶ ንብረት አበጀ አለሙ  -  የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር  ስራና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ

29. አቶ ዘውዱ  ላቀው  ሞገስ -  በም/አስተዳደሪ ማዕረግ ለሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር አማካሪ

30. ወ/ሮ የሽወርቅ ድረስ ተሰማ  - የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር  ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ

31. ወ/ሮ ፀሐይነሽ ተፈራ በላይነህ -  የሰሜን ጎጃም ዞን አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ መምሪያ ምክትል ኃላፊ 

32. አቶ ዘነበ ሀይሉ ተ/ፃዲቅ  -  የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ህብረት ስራ ማህበራት ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ

33. ወ/ሮ ተዋባች ጌታቸው ዘዉዴ - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ

34. አቶ ዋሲሁን ብርሀኑ ሰብስቤ  - የሰሜን ሽዋ ዞን አስተዳደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ በመሆን መሾማቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

EthioTimes

25 Oct, 11:16


የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፤ ለ34 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦

1. አማኑኤል ፈረደ አያሌው (ዶ.ር)  በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአብክመ ርእሰ መሥተዳደር ልዩ አማካሪ

2. መስፍን አበጀ ተፈራ (ዶ.ር) - በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የርእሰ መሥተዳደሩ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ አማካሪ

3. ወ/ሮ መሰሉ ብርሃኑ ካሳው  -   የአብክመ ቆላና መስኖ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ ደረጀ ማንደፍሮ ዳመነ -  የአብክመ ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ

EthioTimes

24 Oct, 19:20


#Tigray

በትግራይ ክልል የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ

በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት” ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታወቀ።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ላይ ጉዳይ ላይ እስከ አኹን የተባለ ነገር የለም። ኾኖም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች ግን፥ እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር። (VOA)
ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/ethiotimesmedia

EthioTimes

23 Oct, 11:16


አዲስ አበባ የተፈፀመ

ከታች በምስሉ የሚታየው ሰለሞን ሉልሰገድ ይባላል።ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት በአዲተር ክፍል ውሰጥ ሰራተኛ ነበር። ጥቅምት 3 ቀን 2017ዓም አዲስ አበባ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ተገድሎ መገኘቱን ከጓደኞቹ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

የአስክሬኑ ከተመረመረ በኋላ የቀብር ስነ ስርዓቱ በትውልድ አካባቢው አማራ ክልል ወልዲያ ከተማ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ተፈፅሟል።ግድያው በማን እንደተፈፀመ ለመለየት ፓሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።

ለቤተሰቡ ሁሉ መፅናናቱን አብዝቶ ይስጥልን
ምንጭ- ዋሱ መሀመድ

EthioTimes

23 Oct, 08:37


በአደጋ ምክንያት ለዓመታት ራሱን ስቶ የቆየው ሰው የ40 ዓመት ህይወቱን ረስቶ ተነሳ

የ63 ዓመት እድሜ ያለው ይህ ሰው ራሱን የሚያየው እንደ 24 ዓመት ጎረምሳ ነው

የ30 ዓመት እድሜ ልጅ እና የልጅ ልጅ ያለው ይህ ሰው በቴክኖሎጂዎች ፍጥነት በየዕለቱ እንደተገረመ ነው ተብሏል

በአደጋ ምክንያት ለዓመታት ራሱን ስቶ የቆየው ሰው የ40 ዓመት ህይወቱን ረስቶ ተነሳ፡፡

ሉሲያኖ የተባለው ጣልያናዊ አንድ ከአምስት አመት በፊት ነበር በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል የገባው፡፡

የ63 ዓመት እድሜ ያለው ይህ ሰውም ከሰሞኑ ለአምስት ዓመታት ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ ራሱን ሊያውቅ ችሏል፡፡

ይሁንና ይህ ሰው ሚስቱን እና የ30 ዓመት ጎረምሳ ልጁን ጨምሮ ከ1983 ወዲህ ያሉ የሕይወቱን ክስተቶች እንደማያስታውስ ተገልጿል፡፡

ሉሲያኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓመታት ከቆየበት የኮማ ህይወት ሲነቃ ሚስቱ ተጠርታ ስሙን ስትጠራው “ስሜን እንዴት አወቅሽ” ሲል መልሶ ጠይቋታል ተብሏል፡፡

አደጋው በደረሰበት ወቅት ባንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ነበር የተባለ ሲሆን እሱ ግን የሚያስታውሰው ከ20 ዓመታት በፊት በጣልያን ኤርፖርት ውስጥ የቴክኒክ ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ የነበረውን ስራ ብቻ እንደሚያስታውስ ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡

ሉሲያኖ በወጣትነት እድሜው የሚያስታውሳት እናቱን ስም እየጠራ የት ሄደች የሚል ጥያቄ ያቀርባል የተባለ ሲሆን እናቱ ግን ከዓመታት በፊት ህይወታቸው እንዳለፈ በስርዓተ ቀብራቸው ላይ መገኘቱን ሲነገረው ለማመን ይቸገራል ተብሏል፡፡

ይህ ሰው አሁን ዘመኑ 1983 እንጂ 2024 ነው ብሎ ለመቀበል ይቸገራል የተባለ ሲሆን እንደ ጎግል ማፕ፣ ሞባይል ስልክ እና ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎችን ሲያይ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ በማለት እንደሚገረም ተገልጿል፡፡
አል ዓይን

EthioTimes

22 Oct, 09:49


ፎቶ ፦ ' መርካቶ ሸማ ተራ ' ከትላንት ምሽቱ አስከፊና ከባድ የእሳት አደጋ በኃላ ዛሬ ላይ ከላይ በፎቶው የምትመለከቱትን ይመስላል።

ከቆርቆሮ እና ከኮነቴነር ቤቶች አቅራቢያ ወዳለው ' ነባር የገበያ ማዕከል (ህንጻ) ' የተዛመተው እሳት የህንጻውን አንደኛውን ክፍል ክፉኛ አውድሞታል።

እስካሁን ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።

በትላንት ምሽቱ የእሳት አደጋ ምንም እንኳን ይፋዊ የጉዳት መጠን ባይገለጽም የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።

በርካቶች ብዙ የደከሙበት ንብረታቸው በአንድ ምሽት ወደ አመድነት ተቀይሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፥ " በአደጋው የደረሰውን የጉዳት መጠኑን የተመለከተ ዝርዝር ጥናት ተደርጎ ከባለሃብቶች እና ከህብረተሰቡም ጋር በመሆን በፍጥነት መልሶ የማቋቋም ስራ ይሰራል ፤ ቦታውንም ወደ ቀደመው የንግድ ተግባር እንዲመለስ የማድረግ ስራ እንሰራለን "  ብሏል።

@tikvahethiopia

EthioTimes

22 Oct, 09:45


በርካታ ተጠቃሚዎች ደግነቷን ሊከፍላት ይችላል የሚለውን አባባል መቀበል አቅቷቸዋል። በህመሙ ወቅት ከባድ ጊዜን አሳልፌያለሁ በየቀኑ እንዲያገግም እረዳው ነበር፣ ቤተሰቦቼ በየቀኑ ሊረዱኝ ይመጡ ነበር፣ ለልጆቼና ለባለቤቴ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ብቻዬን ሳሟላ ቆይቻለሁ ስትል ተደምጣለች።ሆኖም ኑሩል የቀድሞ ባለቤቷ “ኃላፊነቱን በሚገባ እንደተወጣ” እንደሚሰማት ጠቁማ ሰዎች እሱን እና አዲሷን ሚስቱን ማስጨነቅ እንዲያቆሙ ጠይቃለች ። ሆኖም ደጋፊዎቿ በሀሳቧ አልተስማሙም። አንድ ሰው በሰነዘረው አስተያየት “እንዴት እንዲህ ያለው ምስጋና አልባ ሰው ሊኖር ይችላል?

የቀድሞ ባሏን እና አዲሲቱን ሚስቱን ከብዙሃኑ ትችት ለማዳን ስትል ኑሩል ሲያዝዋኒ በፌስቡክ ላይ የደረሰባትን ያሰፈረችውን ፅሁፏን በማጥፋት ሰዎች ለተፈጠረው ነገር የቀድሞ ባሏን መወንጀል እንዲያቆሙ ደጋፊዎቿን ጠይቃለች።የቀድሞ ባለቤቴን፣ አዲሲቱን ሚስቱን እና ቤተሰቦቻቸውን በፌስ ቡክ  ላይ ባጋራሁት መልዕከት ለደረሰባቸው ትችት ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። የሆነው ሁሉ የእኔ ስህተት ነበር ሲል ኑሩል ጽፋለች።(✍️ስምኦን ደረጄ)

EthioTimes

22 Oct, 09:45


ከእንደዚህ አይነት ፍቅር ይጠብቃችሁ

በማሌዥያ የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባለቤቷን ለስድስት ዓመታት ስታስታምም የነበረችው ግለሰብ ከበሽታው ካገገመ በኋላ ሌላ ትዳር መሰረተ

በደረሰባት የተሽከርካሪ አደጋ ለስድስት አመታት የአልጋ ቁራኛ የሆነውን ባሏን የተንከባከበችው ማሌዥያዊት ሴት ባሏ ከበሽታው ካገገመ በኃላ ሌላ ሴት ማግባቷን በቅርቡ አስታውቃለች።

ለዓመታት ኑሩል ስያዝዋኒ የዕለት ተዕለት ህይወቷ የባለቤቷ ጠባቂ በመሆን የምታሳልፈውን ጊዜ በማህበራዊ ድህረ-ገፆች ላይ በማሳየት ስራ የበዛበት ተግባሯን አጋርተች። ይህም ባለቤቷ ምግብ በእጁ ጎርሶ ስለማይወርድለት በናሶጋስቲክ ቱቦ መመገብ፣ ዳይፐር መቀየር እና እንዲታጠብ መርዳት የእርሷ የእለት ከእለት ስራ ነበር። የኑሩል ባል የመኪና አደጋ ከደረሰበት በኃላ እንደገና ለመራመድ ስድስት አመታት መጠበቅ የግድ ብሎት የነበረ ሲሆን በነዚህ ዓመታት ሁሉ ግን እሷ ከጎኑ ነበረች።

ለባሏ ያሳየችው ትጋት እና ታታሪ አገልግሎት በፌስቡክ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ብዙዎቹ የኑሩል ሲያዝዋኒ ባል ካገገመ በኋላ ፈትቷታል፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ሌላ ሴት ማግባቱን ሲሰሙ ደንግጠዋል። የእብደት ድርጊት ሲሉ በርካቶች የተደመጡ ሲሆን ኑሩል በፌስቡክ ገጿ የቀድሞ ባለቤቷን እና አዲሲቷን ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችሁ ብላለች።ለባለቤቴ እንኳን ደስ አለህ ፤ በመረጥከው ህይወት ደስተኛ እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ። አዲሲቱ ሚስቱ አይፋ አይዛም እባካሽ ልክ እንደ እኔ ተንከባከቢው ፤አሁን  ተራው የአንቺ ነው ስትል ኑሩል መልዕክቷን አጋርታለች። በጥቅምት 4 መጠናቀቁ የተነገረለት የኑሩል የፍቺ ዜና የማሌዢያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ማስደንገጡን ተሰምቷል።

EthioTimes

21 Oct, 21:21


መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
መርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋዉን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በርካታ የሰው ኃይል አሰማርቷል።:

በቀጣይ በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳትና መንስኤዉን በማጣራት ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታዉቋል፡ መሰል አደጋዎች እንዳይከሰቱም ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደረግ ጥሪ ተላልፏል።

EthioTimes

21 Oct, 17:13


#FireAlert 🔥

መርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ተከስቷል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው መድረሳቸውንና እሳቱን ለማጥፋት በጥረት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

EthioTimes

20 Oct, 13:44


https://youtu.be/wRxSKhREKTo?si=tJ-e_ULteDLp9Ql4