Jobs @awashmart Channel on Telegram

Jobs

@awashmart


ሀገሬ Gebeya

Jobs (English)

Are you tired of endlessly scrolling through job boards and classifieds in search of the perfect job opportunity? Look no further! Welcome to 'Jobs' - the Telegram channel created by 'awashmart' to bring you the latest and most relevant job listings in various industries. Whether you are a fresh graduate looking to kickstart your career or a seasoned professional searching for a new challenge, this channel is your one-stop destination for all job-related updates. 'Jobs' is dedicated to connecting job seekers with reputable companies and organizations that are actively hiring. With daily updates and curated job postings, you can stay ahead of the competition and land your dream job in no time. Join 'Jobs' today and take the first step towards a rewarding career!

Jobs

21 Oct, 11:17


ልምድ ያለው አካውንታት ይፈለጋል። የስራ ቦታ ገርጂ:: ደሞዝ 18,000 ብር ልምድ ያለው ብቻ (በ ቫት ሪፓርት እና ሂሳብ አያያዝ text to @Addis_j

Jobs

21 Oct, 11:00


ሴት ፀሃፊ ይፈለጋል አድራሻ ቃሊቲ ውሃ ልማት። ደሞዝ 10,000 ብር text to. @Addis_j

Jobs

22 Aug, 09:34


@bolejobs
አውቶ ካድ መጠቀም የሚችል የ ዲዛይን ክህሎት ያልው ፣ የሽያጭ ባለሙያ ይፈልጋል፥
የአርት ሜታል የዲዛይን ስራ ላይ የሰራ ይበረታታል
ደሞዝ በስምምነት
@bolejobs

Jobs

05 Feb, 10:27


🦺 የዩኒቨርሲቲ/የኮሌጅ መምህር ይፈለጋል 🦺

የማስተማር ልምድ ያለው ፣ የስራ ልምድ እና የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- በ ኢንጂነሪግ
- በ ሳይንስ
-በአካውንቲንግ
-በማናጂመንት
-በኮምፒውተር ሳይንስ ወይም
- በጤና የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ። የስራ ሁኔታ Part-time
ደሞዝ በስምምነት
የትምህርት እና የስራ ልምዳችሁን በ ቴሌግራም አድራሻችን 👉 @bolejobs
በመላክ ማመልከት ትችላላችሁ

Jobs

27 Oct, 10:42


የኦሮምኛ  መምህር ይፈለጋል::
ደሞዝ 18,000 ብር
በኦፋን ኦሮሞ የተመረቀ የትምህርት ማስረጃውን በ @bolejobs ልኮ መመዝገብ ይችላል

Jobs

19 Oct, 13:21


ቫት ሪፖርት ላይ፣ ታክስ ፣ የሂሳብ አያያዝ ላይ የረጂም ጊዜ ልምድ ያለው ሰው ይፈለጋል፥፥
ደሞዝ በስምምነት
የቅጥር ሁኔታ በቁዋሚነት
ቦታ : ቃሊቲ  & ገርጂ

👉 @bolejobs

Jobs

08 Oct, 06:34


ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
👆🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺👆

3 በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ የተመረቀ
2 በኮምፒውተር ሳይንስ የተመረቀ
2 በ አካውንቲንግ የተመረቀ
2 በማናጂመንት የተመረቀ ይፈለጋል
ደሞዝ በስምምነት
የስራ ቦታ ቦሌ፣ አዲስ አበባ
ሲቪ እና የትምህርት ማስረጃችሁን @bolejobs እየላካችሁ መመዝገብ ትችላላቹ

Jobs

24 Jul, 16:36


የ CNC (የብረት ፕላዝማ) ባለሙያ ይፈለጋል

ደሞዝ 8,500 እና ኮሚሽን በስራ መጠን

@bolejobs ያናግሩን

አስቸኩዋይ

Jobs

09 Jul, 14:42


ስራ Jobs
📮📮📮

⛔️ቪዲዮ ኤዲተር ይፈለጋል⛔️

👉 ብዛት 3

⛔️ የካርቶ አኒሜሽን ችሎታ ያለው ይፈለጋል⛔️

ብዛት 1



👉 በትርፍ ሰዓት(Part time) የሚሰራ

🎯 ክፍያ በቪዲዮ

@bolejobs ላይ ያናግሩን

ለጀማሪዎች ቦታ አለን!

Jobs

07 Jul, 20:00


የቅጥር ማስታዎቂያ ⭕️
             👉👆👆👆

ተፈላጊ: - የሜታል አርት (Metal art) ስራዎች የሽያጭ ባለሙያ

መስፈረት : ተግባቢና የሽያጭ ልምድ ያለው

በሜታል አርት ስራ ላይ ልምድ ላለዉ ቅደሚያ እንሰጣለን

ፆታ : ወንድ

ደሞዝ 6500  ብር  እና ኮሚሽን

አድራሻ ጎሮ አዲስ አበባ

ብዛት 1

@bolejobs ላይ ያናግሩን

Jobs

19 Sep, 17:26


የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ሊሰረዝ ነው⬇️

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊያደርገው የታቀደው ኮንሰርት #ሊሰረዝ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹልኝ ብሏል።

እንደ ዘ-ሀበሻ ምንጮች ዘገባ #ቴዲ ለአዘጋጆቹ "በዚህ የሃዘን ወቅት መድረክ ላይ ወጥቼ የመዝፈን አቅም የለኝም - አልችልምም" ብሏቸዋል ተብሏል።

ድምጻዊው ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ሊያደርገው የነበረው ኮንሰርት በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሊደረግ የነበረ ሲሆን ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ፊታችን #ቅዳሜ ተዘዋውሮ ነበር።

ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይኸው ኮንሰርት የፊታችን ቅዳሜ የማይካሄድ ሲሆን መቼ እንደሚደረግ እንደማይታወቅ ታውቋል።

ሰው እየሞተ መዝፈን አልችልም ያለው ቴዲ አፍሮ በነገው ዕለት ጠዋት በመድሃኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት በቡራዩና በአካባቢው የተፈናቀሉ ወገኖችን እንደሚጎበኝ በተጨማሪም የገንዘብ እርዳታ እንደሚያደርግ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ነግረውኛል ብሏል።

Jobs

19 Sep, 14:40


ወሎ ዩኒቨርሲቲ⬆️የ2011 ዓ.ም. የመደበኛ የጤና ተማሪዎች ምዝገባ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

Jobs

17 Sep, 05:34


#update የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ሊቀመንበር #ኦባንግ_ሜቶ ከ16 ዐመታት በኋላ ዛሬ ወደ ጋምቤላ ተጉዟል።

Jobs

13 Sep, 08:48


ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም – የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ። (አቶ ታዬ ደንዳዓ ከጠቅላይ አቃቢ ሕግ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር)

አሁንም ጥንቃቄ
ከዝህ በፊት ብያለሁ። አሁንም ደግሜ እላለሁ! ከትናንሽ አጀንዳዎች እንዉጣ። ስለ ምልክት ሳይሆን ስለሀገር ከልብ እናስብ! ሀገር ካለች ባንዲራ መስቀል እና ሀዉልት መገንባት አይከብድም! ሀገር ከሌለ ግን ባንዲራ ብቻዉን ትርጉም የለዉም! አሁን ሊቢያ ወይም የመን ላይ ባንዲራ መያዝ ወይም ሀዉልት መትከል ምን ያደርጋል? ችግራችን በባንዲራ ወይም በሀዉልት አይፈታም።የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ።
ጆሮ ያለዉ ይስማ


Ammas of eeggannoo
Kanaan duras jedheera. Ammas irran deebi’a! Ajandaa xixinnoo keessaa haa baanu. Waan mallattoo dhiifnee waan biyyaa onnee irraa haa yaannu! Biyyi yoo jiraatte alaabaa fannisuu fi siidaa dhaabuun hin dhibu. Yoo biyyi hin jirre garuu alaabaan qophaatti hiika hin qabu! Amma Liibiyaa ykn Yemen keessatti alaabaaqabatuun ykn siidaa dhaabuun maal godha? Rakkoon keenya alaabaa ykn siidaan hin hiikkatu! Shira diinaa haa fashalsinu!
Dubbii kana qalbisaa! (Taye Dendea)

Jobs

10 Sep, 16:49


በሰኔ 16 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ በመወርውር በማቀበል የተጠረጠሩ ጥላሁን ጌታቸውና ብርሃኑ ጃፋር ላይ ፍርድ ቤቱ የመጨረሻ የክስ መመስረቻ ጊዜ ሰጠ፡፡

ቀደም ሲል አቃቢ ህግ በሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ በቦምብ ጉዳት የደረሰባቸው ተጨማሪ ቃል ለመቀበልና የስልክ ልውውጥ ማስረጃን እንዲሟላ ለመርማሪ ፖሊስ መዝገቡን መመለሱንና ማስረጃዎችንም ለሟሟላት ጊዜ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት መርማሪ ፖሊስ ለፌደራል የመጀመሪ ደረጃ አንደኛ ተረኛ ወንጀል ችሎት ተጨማሪ ማስረጃውን አሟልቶ አጠናቆ ለአቃቢ ህግ መመለሱን አስረድቷል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ በበኩሉ የምርመራ መዝገቡን መቀበሉን በመግለጽ ይህንን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ፍርድ በቱን ጠይቋል፡፡

እስከዚያውም አቃቤ ህግ ተጠርጠሪዎቹ በእስር እንዲቆዩ በማለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

ተጠርጣሪ ጥላሁን ጌታቸውም ጨለማ ቤት እንደሚገኝ እንዲሁም በቦምብ አደጋ የደረሰብኝ በመሆኑ ህክምና እያገኘሁ አይደለም ሲል በዋስ ልወጣ ይገባል በማለት ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

መርማሪ ፖሊስም በባለሙያ እየተደገፈ አቤት ሆስፒታል ህክምና እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ ለዚህም የተያዘ ቃለጉባዔ መኖሩንም ገልጿል፡፡

ጨለማ ቤት የተባለውም ጉዳይ ሐሰት መሆኑንና በአሁኑ ወቅት ጨለማ ቤት የሚባል እስር ቤት እንደሌለ ፖሊስ ለችሎት አስረድቷል፡፡

ተጠርጣሪ ብርሃኑ ጃፋር በበኩሉ እኔ ከተያዝኩ ብዙ ቀናትን ያስቆጠርኩ በመሆኑ እንዲሁም በተደጋጋሚ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀብኝ ሲሆን አሁን የጊዜ ቀጠሮ ሊሰጥ አይገባም በማለት የዋስትና ይፈቀድልኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡

አቃቢ ህግም ተጠርጣሪዎቹ የፈጸሙት ወንጀል ከባድና ውስብስብ እንዲሁም በርካታ ዜጎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ለሁለት ሰዎች ህልፈት ምክንያት በመሆኑ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም በማለት ጥያቄያቸውን ተቃውሟል፡፡

የሁለቱን ክርክር ያደመጠው ፍርድ ቤትም የዋስትና ጥያቄያቸው በማለፍ ጥላሁን ጌታቸው ላይ እስከ መስከረም 10 ባለው ጊዜ ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ብርሃኑ ጃፋር ላይ ደግሞ እስከ መስከረም ዘጠኝ ቀን የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

#FBC

Jobs

08 Sep, 17:45


#update የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። ኮሚቴው ከሁለት ሳምንት በፊት አካሂዶት በነበረበው መደበኛ ስብሰባ ወቅት ከተወያየባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ መታየት ሲኖርባቸው በጊዜ እጥረት ምክንያት ባልተዳሰሱ ድርጅታዊና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ይመክራል። በተጨማሪም በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በሚቀርበው የድርጅቱ ሪፖርት ላይ የሚወያይ ሲሆን አጠቃላይ የጉባኤ ዝግጅቱ ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የቀሪ ሥራዎች አፈፃፀም አቅጣጫን ያስቀምጣል፡፡

©etv

Jobs

05 Sep, 14:26


ፎቶ⬆️ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2 ቀን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ኤርትራ ይገኛሉ።

ፎቶ፦ አቶ የማነ ገብረመስቀል (የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር)

Jobs

04 Sep, 19:26


# እውነተኛ_ታሪክ መንትዬቹ ክፍል 4 በቃ እነሱን ለማለያየት ተንኮል
ማውጠንጠን ጀመርኩ
እንደሷ ፀጉሬን ሹሩባ መሰራት
ጀመርኩ የዩኒፎርም ሸሚዜን እንደሷ ረዥም መልበስ
ጀመርኩ። አንድ ሁሌም ከትምህርት
ስንመለስ መንገድ ላይ ተራ በተራ እየያዘ የሚያቸግረንን
ልጅ ትህትና ነኝ ብዬ ተዋወኩትና
ቀረብኩት ከዛም ከጊዜ በኃላ አልፈልግህም ጓደኛ አለኝ
ብዬ ተውኩት እሄን ያደረኩት
ያለምክንያት አልነበረም። ያሰብኩት ተንኮል እንዲሳካልኝ
ነበር። ከዛም እንደበፊቱ ስታይሌ
ተመለስኩ ሹሩባ መሰራት ተውኩ ሸሚዜንም ቀየርኩ ልጁ
ያኔ ትህትና እየተከተለ እንዴት
ያለምክንያት ፍቅር አስጀምረሽ አልፈልግም ትይኛለሽ እያለ
መውጫ መግቢያ አሳጣት እሷ
ምንም የምታውቀው ነገር ስላልነበረ እባክህ ተወኝ
ብትልም ልጁ ጭራሽ መዛት
ማስፈራራት ጀመረ። እኔ ምንም እንዳላወቀ ሰው ሄጄ
እህቴን ምን አርጊ ነው የምትላት
አልኩት እሱም
ፍቅር አስጀምራኝ አልፈልግህም አለችኝ አለኝ እኔም
<<አዎ እሷ በጣም የምትወደው ጓደኛ አላት ኤርሚያስ
ይባላል ከፈለክ አድራሻውን
እነግርሃለው እሱን ሄደህ አናግረው እህቴን ግን ለቀቅ
አድርጋት ብዬው የኤርሚን ሰፈር
ነግሬው መጣው ልጁ እንዳልኩትም እነኤርሚ ሰፈር ሄዶ
ዱላ ቀረሽ ፀብ ፈጥሮ መጣ
ኤርሚም ትህትና ከሱ በፊት ፍቅረኛ እንደነበራትና
ደብቃው እንደሆነ ስለገመተ በንጋታው
ትምህርት ቤት ስንሄድ ተጣሉ በጣም ደስ አለኝ ሆኖም
ደስታዬ ብዙም አልቆየም ኤርሚና
ትሁት ከልባቸው ይዋደዱ ነበርና ከ3 ቀን በላይ ተኳርፈው
መቆየት አልቻሉም እራሱ
ኤርሚያስ እቤት ድረስ እየተመላለሰ ይቅርታ ጠየቃት
ታረቁ። እኔ ግን ሰላም ልሰጣቸው
አልቻልኩም እቤት ስንገባ ትህትናን እንዴት በፈለገው ሰዓት
እየተጣላሽ ሲታረቅሽ እሺ
ትይዋለሽ ለምን እራስሽን አታስከብሪም እያልኩ
መወትወት ጀመርኩ። አልተሳካልኝም ከራሷ
በላይ ትወደዋለች። እንዲህ መዋደዳቸውን እንኳን እያየሁ
ልቤ ሊራራ አልቻለም። ይባስ
እንደውም አውሬ ሆንኩኝ በቃ ሁሉም ነገር አስጠላኝ
እናታችንን እንኳን በተናገርችኝ ቁጥር
ማመነጫጨቅ መቆጣት ማኩረፍ ጀመርኩ 11ኛ ክፍልን
አጠናቀን ወደ 12 ተሸጋገርን
አሁን ደግሞ ጭራሽ እኔና ኤርሚያስ አንድ ክፍል ሆንን
ትህትና ለብቻዋ ሌላ ክፍል ደረሳት
ከኤርሚጋር አንድ ክፍል መግባታችን ለጊዜው ደስ
ቢለኝም ግን እየዋል እያደር እሱን እሱን
እያየሁ ስፈዝ በትምህርቴ እየሰነፍኩ መጣሁ እሱ ግን
አይን ጥሎት እንኳን ዞር ብሎ
አያየኝም ክፍሉ ውስጥ ትኩረቱ ትምህርቱ ላይ ብቻ ነው
በእረፍት ደሞ ወደ ፍቅረኛው
ይሮጣል። በቃ እኔ ያፈቀርኩት ኤርሚያስ እሄ ነው
የሁልጊዜም ተግባሩ እሄ ብቻ ነው። እኔ
ግን ለሱ በሱ ምክንያት የምወዳት ብቸኛዋን መንትያ
እህቴን ለአይኔ ጠልቻታለሁ እንደዛ
የምወደው ትምህርቴን ረስቻለው እራሴን ረስቻለሁ
ህይወቴ ተመሰቃቅሏል በሱ ምክንያት
ለምንድነው ግን የማይፈልገን ሰው ላይ ተተክለን
የምንቀረው?
መልሱን ለናንተ ትቼ እኔ ታሪኬን ልቀጥል..........
ጊዜያቶች ነጎዱ ኤርሚና ትህትና ፍቅር ከጀመሩ አንድ
አመት ሆናቸው ድምቅ ባለ መልኩ
አከበሩት እሷም እናታችንን አስተዋወቀችው እሱም
ቤተሰቦቹን ሁሉ አስተዋወቃት።
ፍቅራቸው በየቀኑ እየጨመረ ይበልጥ እያማረ ሄደ የኔ
ልብ ውስጥም ለኤርሚ ያለኝ ፍቅርና
ለእህቴ ያለኝ ጥላቻ እየጨመረ ሰውነቴ ደግሞ
እየተጎሳቆለ የልጅነት መልኬ እየጠፋ ሄደ።
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የ12ኛ ክፍል ሁለቱ
ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባቸውን
ከፍተኛ ነጥብ አምጥተው ሲያልፉ እኔ ዝቅተኛ ውጤት
አምጥቼ ወደኩ። በቃ አሁን የባሰ
እንዳይስተካከል ሆኖ ህይወቴ ተመሰቃቀለ ዝብርቅርቁ
ወጣ እህቴን ለምን እቤት ውስጥ
አየሁሽ እያልኩ ላንቃት እነሳለሁ ያቺ ንፁዋ እህቴ ግን እኔ
ነጥብ ስላልመጣልኝ በሱ
የምበሳጭ ስለሚመስላት እኔን ለማፅናናት ከስሬ አልጠፋ
አለች እኔ እንዲህ የምሆንበትን
ምክንያት የምታውቀው እናታችን ደግሞ ሰላም የነበረው
ደም ግፊቷ በኔ እንዲህ መሆን
እየተነሳባት አልጋ ስትይዝ ስትነሳ አልጋ ስቲዝ ስትነሳ ጤና
አጣች። ብትመክረኝ ብትዘክረኝ
የምመለስ አልነበርኩም ጭራሽ አንቺ ነሽ ተይ ብለሽ
አስጥለሽኝ ለልጅሽ አድልተሽ ፍቅሬን
የቀማሽኝ እያልኩ እናቴን በበሽታዋ ላይ በሽታ ሆንኩባት።
አሁን ሁሉ ሲያልፍ እንዲህ
ሊቆጨኝ ያኔ ግን ምንም አይመስለኝም ነበር።
እህቴ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ኤርሚ ደግሞ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
ደረሳቸው ሆኖም ተለያይተው
መማር ስላልፈለጉ ኤርሚ በገንዘብ ወደ ሀዋሳ አስቀይሮ
አንድ ላይ ተጓዙ እኔም እናቴ ቤት
ውስጥ ቀረሁ የግል ኮሌጅ እንድማር እናቴ ብትለምነኝም
ፍቃደኛ አልነበርኩም። ቁጭ ብዬ
ነገር ማውጠንጠን ተንኮል መሸረቤን ተያያዝኩት። እኔ
በህይወት ቆሜ እነሱ ተጋብተው
ልጆች ወልደው እንደማይኖሩ እራሴን አሳመንኩ..
|______________ይቀጥላል__________________|
|_________አስተያየታችሁን አይቼ ይቀጥላል_______
ታሪኩን ከወደዱት part 5 ብለው comment ላይ
ይጻፉልን

Jobs

26 Aug, 13:27


# እውነተኛ_ታሪክ መንትዬቹ ክፍል 3
<<ይድረስ ለምወድሽ ትህትና ቲቲዬ እሄን ደብዳቤ
ካነበብሽ በኃላ ምናልባት ልትርቂኝ
ልትቀየሚኝ ትችያለሽ እንዲህ አይነት ነገር ላለማሰብ ብዙ
ሞክሬ ነበር ግን አልቻልኩም።
ትሁት በጣም አፈቅርሻለሁአልፈልግም እንኳን ብትይኝ
ንፁህ ጓደኝነትሽን ስለምፈልግ
እባክሽን እንዳትርቂኝ.................ያንቺው ኤርሚያስ>>
አንብቤ ከጨረስኩ በኃላ ድርቅ ብዬ ነበር የቀረሁት። ቀና
ብዬ እሷን አየዋት ፊቷ በፈገግታ
እንደደመቀ ደብዳቤውን በተመስጦ እያነበበች ነው።
<<ትወጂዋለሽ እንዴ?>> አልኳት አልወደውም እንድትለኝ
እየተመኘው
<<ማንን?>> አለችን ደብዳቤው ላይ እንዳፈጠጠች
<<ኤርሚን ነዋ>> አልኩ ጮክ ብዬ
እንደማፈር ብላ ትንሽ ዝም ካለች በኃላ.....
<<አዎ ....ከተቀራረብን ጀምሮ ወድጄዋለው ግን አንቺንና
እማዬን ስለፈራሁ ሳልነግራቹ
ቀረው እንጂ ኤርሚን በጣም ነው የምወደው>>
የባሰ በተቀመጥኩበት ደንዝዤ ቀረሁ በእጄ ይዤው
የነበረው ወረቀት ወደቀ.... ትኩር ብዬ
አየኃት እህቴ አልመስልሽ አለችኝ እንደምንም እራሴን
አረጋግቼ
<<ለማንኛውም አሁን እማዬ ሁሉንም ነገር ማወቅ
አለባት>> አልኳት ዝምም አለችኝ
ተነስቼ የወደቀውን ወረቀት አንስቼ ወደ ውስጥ ገባሁ
እሷም ተከትላኝ ገባች። እናታችን
ከስራ ገብታ ሶፋ ላይ ጋደም ብላለች የትምርትቤት
ቦርሳዬን ወርውሬ ሁሌም
እንደምናደርገው ሄጄ በተኛችበት ግንባሯን ስሚያት
አጠገቧ ቁጭ አልኩ።
<<ምነው ምን ሆናቹ ተኳርፋቹዋል እንዴ?>> አለች
ሁለታችንንም በየተራ እያየችን ምንም
ሳልናገር ደብዳቤውን ሰጠኃት አነበበችውና ቀና ብላ
አየችን እህቴ እንዳቀረቀረች ከኛ ራቅ
ብላ ተቀምጣለች። እናቴ ከተኛችበት ተነስታ ቁጭ ካለች
በኃላ ወረቀቱን አጣጥፋ
<<ሉሌ ተነሽ ዩኒፎርምሽን ቀይረሽ መክሰስ አቀራርቢ እኔና
ትሁት ብቻችንን ማውራት
አለብን>> አለችኝ እኔም እንደታዘዝኩት ተነስቼ ወደ ውስጥ
ገባሁ። ልብሴን ቀያይሪ ምግብ
ይዤ ስመጣ አውርተው ጨርሰዋል። ከምግብ በኃላ ወደ
ጥናት ገባን መሸ እናቴ መኝታ
ክፍሏ ስትገባ ተከትያት ገብቼ ጠየኳት ትህትና ኤርሚያስን
ስለምትወደው አብራው መሆን
እንደምትፈልግ እንደነገረቻት ነገረችኝ
<<እማ እኔም እኮ ወደዋለሁ?>> አልኳት እምባዬን
እየታገልኩ
<<አውቃለው ልጄ አውቃለው ግን እሄ ልጅ ላንቺ ቢለው
ኖሮ እህትሽን አይወድም ነበር
እህትሽም አቶደውም ነበር ስለዚህ ልጄ እሱ አሁን
የእህትሽ ነው እባክሽን ተያቸው ሁሉን
ነገር ለመርሳት ሞክሪ ያንቺ አዳም ደሞ የሆነ ቦታ ነው
በህይወት መንገድ ላይ አንድ ቀን
ትገናኛላቹ>>
አለችኝ እቅፍ አድርጋ እየሰማችኝ እናቴን ማስጨነቅ
አልፈለኩም እንዳለችኝም ኤርሚን
ለእህቴ ትቼ ለመኖር ወሰንኩኝ ግን አልቻልኩም በተለይ
ትምህርት ተጀምሮ ፍቅራቸውን
በይፋ አደባባይ ሲያወጡት በቅናት ላብድ ደረስኩ እህቴ
እንደዛ የምሳሳላት እህቴ
አልመስልሽ አለችኝ ጠላኃት አጠገቤ ባየኃት ቁጥር
እንቂያት እነቂያት ይለኛል እሷ ግን
አሁንም እንደልጅነታችን በንፁህ ልቧ ትወደኛለች
ከኤርሚጋር ስላሳለፉት ታወራኛለች
በፅሞና ካዳመጥኳት በኃላ ተደብቄ አለቅሳለሁ። በዚህ
ሁኔታ እሷና ኤርሚ ጥሩ ውጤት
በማምጣት እኔም እንደምንም ተንጠልጥዬ ወደ 11ኛ
ክፍል [ፕሪፕ] ገባን አብረው
ባየኃቸው ቁጥር ለእህቴ ያለኝ ጥላቻ እየባሰ መጣ በቃ
እነሱን ለማለያየት ተንኮል
ማውጠንጠን ጀመርኩ.......
|_________ ይቀጥላል_______