▪️ ለሸይኽ ዐብዱለጢፍ እስካሁን የተሰበሰበው ብር 499,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሽ) ብር ነው። አጠቃላይ የሚፈለገው $8500 (ስምንት ሽ አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር ) ነው። ይህ ማለት 1,037,000 (አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ሰባት ሽህ) የኢትዮጲያ ብር ገደማ ነው። ከዚህ ላይ ግማሹን እንኳን መሰብሰብ አልተቻለም!!
▪️ ሸይኻችን ከእስር ቤት ሲወጡ በስጦታ የተበረከተላቸው መኪና ይሸጥ ቢሉም እያሰባሰቡ ያሉ ሽማግሌዎች በጭራሽ እኛ ሙስሊሙን ይዘን አሰባስበን እንከፍላለን እንጅ መኪናው አይሸጥም በማለት የህዝቡን ትብብር እየጠበቁ ነው!
▪️ ጉዳዩ እንዲህ ነው ፦ ህመሙ ወደ ካንሰር የመለወጥ እድል የነበረው እጢ በመሆኑ እናሳክማችሁ ብለው ወደ ቱርክ የወሰዷቸው ወንድምና እህቶች ከህዝቡ ሰብስበን እንከፍላለን በሚል መተማመን ከሰዎች በብድር አንስተው ነበር የከፈሉት።
▪️ መጀመሪያ $4000 የተገመተ ህክምና ኋላ ላይ $7500 ተጨማሪ ተጠየቀበት። ይህ ሁሉ ሲሆን ሸይኻችን አያውቁም ነበር። ከዚያ የተወሰኑ ቅርብ ሰዎች ጉዳዩን ሲነግሯቸው ነበር «መኪናዬ ይሸጥ» የሚል ሀሳብ ያመጡት ።
ይህም ጠቅላላ ህክምናው $11,500 ዶላር ሲሆን $2500ው በወንድሞች ስለተከፈለ ለህዝብ የተጠየቀው $8500ው ብቻ ነው። የአንድ መርፌ ዋጋ $300 (36,600 ብር ) ሆኖ ህክምናው እንደቀጠለ ነው። መርፌውም የሚቆም ሳይሆን በየ3ወሩ የሚቀጥል ነው።
▪️ ወደርሳቸው አካውንት ገቢ እንዳይደረግ የተደረገውም በዚሁ ምክንያት ብቻ ነው። ከአካውንትህ አውጣና ዱቤ ክፈል እንዴት ይባላል? ለሸይኽ አይደለም ለተርታ ሰውስ ነውር አይደለም? ስለሆነም በኮሚቴ አካውንት እንዲሰበሰብ ተወሰነ።
▪️ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ በእምነታቸው ድፍን የሰንበቴ ከተማ ነዋሪ የሚመስክርላቸው ዓሊሞችና ሽማግሌዎች እንዲሁም የሸይኹ የቅርብ ጓደኞች ናቸው።
ስለሆነም ሙስሊሙ ኡማ ይህንን ተገንዝቦ «ሀብታሞች ገቢ ያደርጋሉ» ብለን ሳንዘናጋ ትንሽም ብትሆን ሁሉም የራሱን ገቢ እያደረገ ሸይኻችንን እናሳክም!
የከሸፍን ትውልዶች ሆነን እንጅ ወላሂ በዚህ መልክ ለሸይኻችን ስፅፍ ክብራቸውን ዝቅ ያደረግኩ እየመሰለኝ ነው!
የንግድ ባንክ አካውንት ፦
1000392652788
የአካውንት ስም ፦
YEJILE TIMUGA W/COMMUNITY SUPPORT
(የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ኮሚዩኒቲ ሰፖርት)
አሰባሳቢ ኮሚቴዎች ፦
1) ሸኽ ጡሃ ሸኽ መሀመድ
2) ሸኽ ሁሴን ሀሰን ሱሩር
3) ሸኽ አህመድ አሊ ሃሰን
ሼር ማድረግም ትብብር መሆኑ አይዘንጋ!