Adoni Gospel channel @adonigospel Channel on Telegram

Adoni Gospel channel

@adonigospel


የእግዚአብሄርን ፍቅር፣ ምህረትና ይቅርታ በተገለጠው የወንጌሉ ቃል መሰረት የምንማማርበት ቻናል ነው። ትምህርቶቹን በሚያመቻችሁ የሶሻል ሚድያ በኩል ለመጠቀም ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ።

Telegram ፦ @adonigospel

WhatsApp ፦ https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel (Amharic)

የAdoni Gospel channel ቻናል እንዴት እንደሚሰራው በትዕግስት እንዲሽየው አማራኛ በፊት ለሁሉም የምንትን አመራር እንደሚቃረም አውቃለች። ይህ ቻናል በውስጡ የእግዚአብሄርን ፍቅር፣ ምህረትና ይቅርታ መሰረት የምንማማርበት ነው። የቃል ኪዳንሱ ሰዎች የአገልግሎትን መሠረት ሲቆይ ሌላ መሠረትን የሚሰጥ እና መምህሩን ለማግኘት ሌላ ስልጠና ቻናል ነው። በቻናሉም ያሉት ትምህርትን በሚያግዝና ሌሎች እቃዎች በአንዴት ይጠናቁ። ማንኛውም በትክክለኛ ዋጋ እና ፈልገው ለመሰረታዌና ለመከላከያ ቻናል ደግሞ ይመልከቱ። እባኮትን በTelegram የተለያዩ ቻናል መሰረታዊ መረጃዎች እና ምሳሌ ለመረዳ ደግሞ @adonigospel ይጠቀሙ።

Adoni Gospel channel

13 Feb, 22:34


የመጽናናት አምላክ እግዚአብሔር እንደኔ የረዳኸው የለም። እንደኔ የወደድከውም የለም። ለኔ ያደረከውን ለማንም አላደረክም ተመስገን። ስለበዛልኝ ባርኮትህ፣ ስለበዛልኝ በረከትህ ስምህ ቡሩክ ይሁን! አሜን

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

13 Feb, 04:10


የዘላለም አባት እግዚአብሔር ሆይ ስለዚህ ማለዳ ስምህ ቡሩክ ይሁን

አቤቱ ከቀኑ ክፋት ጠብቀን። መንገዳችን ሁሉ አንተ የቀደምክበት፣ በውሏችን ሁሉ አንተ የምትውልበት ቀን አድርገው። ተመስገን! አሜን

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

11 Feb, 03:49


  ( ሳነብ ካገኘሁት የወደድኩትን ላካፍላችሁ)


‹‹የባሰ አታምጣ…››

ተጣብቀው የተወለዱ ወንድማማቾች አብረው አደጉ፡፡
ታዲያ እነዛ ወንድማማቾች ምን በአካል ቢጣበቁ አመለካካታቸው እና አስተሳሰባቸው ተራራቀ ኖሮ ሁሌም ይጨቃጨቃሉ፡፡
‹‹እግዜር ግን ምን በደልነው?›› ይላል አንዱ፡፡
‹‹ተው አሱ አይጠየቅም ‹ተመስገን› ነው የሚባለው››ይመልሳል ሌላው፡፡
‹‹ተመስገን? ምን አድርጎልኝ? ካላጣው ጭቃ ፤ ካልጎደለው ጥበብ እንዲህ አጣብቆን መፍጠሩ ምን ያስመሰግነዋል? ወይስ ተሳስቶ ይሆን?
ስንቱን ሲያቆነጅ፤ በፈቃዱ ያሻውን እንዲያደርግ ሲፈቅድ፤ ቆዳህን እና ቆዳዬን አንድ ላይ ስለሰፋው? ለምኑ ላመስግነው? ንገረኛ…
በህሊናዬ ብቻ ሳይሆን በህሊናህም እንዳስብ ሲያስገድደኝ ምኑን ላመስግነው ? እስር ቤት እኮ ነው ያለሁት፡፡ በእገረ ሙቅ ስላልታሰርን ነው? ያው የስጋ እስር ነው፡፡ ሰው ሲያየን እንዴት እንደሚደነግጥ አታይም? ሁሉ እያማተበ በህልሙ እንዳንመጣ ፊቱን እያዞረ ይሸሸናል፡፡ ጓደኛም የለንም፡፡ ሲኦል እኮ ነው ያለነው፡፡ ሲኦል፡፡ ምኑ አስደስቶህ እንደምታመሰግነው እኔን አይገባኝም… ›› ምሬቱን ያዠጎደጉደዋል፡፡

‹‹በቃ ተወው ካሁን በኋላ አንተ የምትፈልገውን ብቻ እናደርጋለን፡፡ ወደምትፈልግበት ብቻ እንሄዳለን እኔን እንደሌለሁ ቁጠረኝ ፡፡ ማድረግ የምትፈልገውን ብቻ ነገረኝ፡፡ ያቅሜን ያህል አሟላልሃለሁ፡፡›› እያለ ያፅናናዋል፡፡
‹‹ካንተ ጋር እየተጓተቱ መሄዱ አይደል እንዴ ነፍሴን ያስመረራት? ‹ያቅሜን ያህል ›ይላል ደግሞ!! ምን አቅም አለህና? የኔ ቢጤ እስረኛ፡፡ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ፡፡ በቃ ብቻዬን !!! ነፃነቴን!! መጸዳጃ እንኳ ሰይቀር ካተው ጋር ነኝ፡፡ ከዚህ ኑሮስ ምናለ ሞቼ ባረፍኩት›› እያለ ይነዘንዘዋል፡፡

‹‹አንተ ሰው አንደበትህን አርም፡፡ ‹የባሰ አታምጣ› ነው የሚባለው›› ይለዋል ሌላኛው በትህትና፡፡
ያሉበት ሁኔታ አንድ አይነት ሆኖ ያኛው ያለማቋረጥ ያማርራል ይሄኛው ያለማቋረጥ ያመሰግናል፡፡
‹‹የባሰ?ከዚህ የባሰ? ምን አለ? ከኛ ኑሮ የባሰ ነገር እኮ የለም!!! እንደ ልቤ ሳልራመድ ፤ሳልሮጥ ፤ሳልቀመጥ እና ሳልተኛ ለተመልካች ሰቀቀን ሆኜ እየኖርኩ፡፡ ለሰው ከዚህ የባሰ ምን ይመጣበታል? ንገረኛ ምንድነው የባሰ?››
‹‹ወንድሜ ሆይ ሁሌም የባሰ አለ፡፡ ወዳንተ እንዳይመጣ ብቻ ፀልይ፡፡ ላለህበትም አመስግን ፡፡ጥረህ ግረህ መለወጥ የማትችለውን ነገር ተቀብለኸው ኑር፡፡ እንጂ አታማርረው፡፡ ›› እያለ መምከሩንም አላቋረጠም፡፡

በአንድ አካል ሁለት ነፍስ ይዘው እንዲህ ሲኖሩ ሲኖሩ ታዲያ ሞት አይቀርምና… ማን ቀድሞ ሞተ?
አመስጋኙ!!!
ኗሪው  ብቸኝቱ ሳያንሰው፤ ሀዘኑ ሳያንው ፤ የሚያዋራው ማጣቱ ሳያንሰው…ቀሪ ዘመኑን የወንድሙን  አስከሬን ተሸክሞ መኖር ሆነ ዕጣው፡፡
‹‹ የባሰ አታምጣ…›› እያለ፡፡


     ወዳጆቼ ማመስገን የመጣውን መከራ ያቀልልናል ያልመጣውን መከራ አርቆ ያጥርልናል። እግዚአብሔር ችግር መከራ የሌለው ሕይወት እንድንመራ አያደርገንም። በመከራውና በችግሩ ውስጥ አብሮን ሆኖ ብርታትና ጥንካሬን ይሰጠናል። ተወዳጆች እናመስግን! ሳንጠይቅ ስላደረገልን ውድ ነገሮች እናመስግን።

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

10 Feb, 11:53


   " ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤
ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።" ( መዝ 121:1-2)

               የኔ ከፍታ ተራራ አይደለም የኔ ትልቁ ነገር አንተ ነህ። ዓይኖቼን ወዳንተ አነሳለሁ አንተም የተበላሸውን ለመስራት ታያለህ፣ የሞተውን ለማስነሳት ትመለከታለህ። ረዳት ፍለጋ በምድር አልኳትንም አንተ ቀኝህን ትዘረጋልኛለህ፣ አንተ አደግድገህ ስራዬን ትሰራልኛለህ።

        አንተ ብቻ የልቤን ጓዳ፣ የሃሳቤን አስኳል፣ የጭንቄን ምስጢር፣ የትካዜዬን ምክንያት ታውቃለህ ቸል አትበለኝ መልስህን ላክልኝ፣ ዝም አትበለኝ በረከትህን ስደድልኝ፣ እንዳትረሳኝ ዘንበል በልልኝ። አንተ ጥሜን የምታረካ ምንጬ ነህ እንደ ቀንበር ተጭኖ ያጎበጠኝን አንገት ያስደፋኝን ነገር ሁሉ በስምህ ጉልበት አንከባልልኝ። የነገሩህን የማትረሳ የለመኑህን የማትነሳ ረድዔቴ ሆይ ክበርልኝ።

           ረዳት ፍለጋ የሰው ደጅ አልጠናም አንተ ለምኑኝ ብለሃል በፍፁም ትህትና ራሴን አዋርጄ እለምንሃለው ።

          አትዘግይብኝ በቀንህ ድረስልኝ። ባቃተኝ ነገር ላይ ሙሉ አቅም ያለህ አንተ ነህና ድረስልኝ። በምትወደው ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመንኩህ አንተም ስለሰማኸኝ ተመስገን!!

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

09 Feb, 10:49


       ንካን

       ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ከነካችሁ ለህይወት ዘመናችሁ ሁሉ መፍትሄ ይሆናል። እርሱ አንድ ጊዜ ይንካችሁ ዘመናት ያስቆጠረ ችግራችሁ ይቆማል። እርሱ አንድ ጊዜ ይንካችሁ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ችግራችሁ እልባት ያገኛል።

        ጌታ ሆይ ዛሬም በቆሰሉት እጆችህ ንካን። የአገራችን መከራ ይቁም። የህዝቤ ሰቆቃ ይቁም። አንተ ንካን መቆም ያለበት ነገር ሁሉ ይቆማል። ንካን ክፉ ልቦች መልካም ይሆናሉ፤ ያዘኑ ጽኑ መጽናናት ያገኛሉ። ተስፋ አጥተው የደረቁ ይለመልማሉ።

      ንካን እጅህ ላይ ደስታ አለ፤ ንካን እጅህ ላይ መድኃኒት አለ፤ ንካን እጅህ ላይ ሰላም አለ። ንካን ንካን ደጋግመህ ንካን አዲስ አድርገን አሮጌ ሕይወታችንን አስጥለን። ንካን እንዳልበደሉ አድርገህ አቁመን።

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

06 Feb, 18:53


ጸሎት

አቤቱ ሰማይን ያለምሰሶ ምድርንም ያለመሰረት በቃልህ ያፀናህ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለው። ማደሪያህ ይባረክ ስምህ ይባረክ። በአንተ አይን መታየቴ በአንተ ህሊና መታሰቤ ተዓምር ነውና ያዩኝ አይኖችህ ያሰበኝ ልቡናህ የተባረከ ይሁን። አንድያ ልጅህን ሙትለት ብለህ የሰደድክልኝ ቃል በማይገልፀው ፍቅር የወደድከኝ ሙት ሆኜ ያልረሳኸኝ አንተን አመሰግንሃለው።

አቤቱ ጌታዬ ክርስቶስ ሆይ የሆነብኝን፣ የደረሰብኝን ሁሉ አስብ። አንተ ስታየኝ መከራዬ ይቀላል ያስጨነቀኝ ይራገፋልና የስስት አይኖችህ ይረፉብኝ።

ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሞትን ልደት ታደርጋለህና አከተመ ያልኩትን ጉዳዬን ቀስቅስልኝ፣ ተፈፀመ ያልኩትን በእንባ የዘጋሁትን ከመጨረሻው መጀመር የምትችለው አንተ ነገሬን ስራልኝ። አቤቱ ልቤን እንደ ባላ ከወጠራት ሃሳብና ስጋት ሁሉ በስምህ ስልጣን አሳርፋት።

ግዑዙ የሚገዛልህ፣ ጆሮ የሌለው ድንጋዩ የሚያደምጥህ አንተ የኔ ልዑል ማዕበሌን ገስፀው ወጀቤን ዳርቻ አበጅለት የመከራ ቀናቶች አይርዘሙ በቃ በላቸው። እባክህ በአንተ ደስ አሰኘኝ። በተወደደው በክርስቶስ ስምህ በፈሰሰው ደምህ ለመንኩህ። አሜን!!!!

  በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

06 Feb, 06:21


እልፍ እልፍ በሉ


የሰው ልጅ አመል እጅግ አስቸጋሪ ነው። ፍቅር እንደ አባጨጓሬ የሚኮሰኩሰው ነው። ስታቅፉት አንገላታችሁኝ፣ ስትስሙት ነከሳችሁኝ፣ ስታስቡለት አሴራችሁብኝ ይላችኋል። እንደዚህ ያለን ሰው በሕይወታችን ውስጥ ይዘን መቀጠል ይከብደናል። ከሕይወታችን ገንጥለን ለማውጣት እንሞክርና አዝነን የእንደገና እድል ልንሰጣቸው እንሞክራለን። ከእናንተ ሳይሆን ከእነርሱ ጎድሎ ነውና ህመም ይፈጥሩባችኋል። ደግ በሰራሁ፣ ፍቅር በሰጠሁ፣ አለውልህ ብዬ ከጎኑ በቆምኩ ለምን ይህ ተመለሰልኝ ትላላችሁ። የምትችሉት መውደድ፣ ፍቅርን መስጠት፣ ደግ መሆን ነው እንጂ ያ ሰው እንዲወዳችሁ እንዲያፈቅራችሁ ማድረግ አትችሉም። ልቡ ላይ ደግነትና ፍቅርን መዝራት ትችላላችሁ ተንከባክቦ ማብቀል ግን የሰውዬው ድርሻ ነው።

ክርስቶስ ወደ ገዛ ወገኖቹ መጣ ፍቅርን ሰጣቸው፣ ምህረትን አደረገላቸው፣ መልካምነቱን በልባቸውም በቤታቸውም ናኘላቸው፣ ጉድለቶቻቸውን ቀረፈላቸው እነርሱ ግን አልተቀበሉትም። እልፍ ብሎ ወገኖቹ ወዳልሆኑት አህዛብ ሄደ። ወዳጆቼ አለመቀበል፣ አለመፈለግ ወዳጅ ጓደኛ ካረጋችሁት ይቅርና ወገኔና ቤተሰቤ ከምትሉትም ሊገጥማችሁ ይችላል።

ዮሴፍ ወንድሞቹ ሲሸጡት የማያውቁት ናቸው የገዙት፣ ከተወለደበት አገር ሲገፉት ያልተወለደበት አገር ላይ ነው የተሾመው፣ የስጋ ክፋዮቹ ጠሉት በስጋ ያልተዛመዱት ወደዱት። ስለዚህ የግድ ሲጠሏችሁ ለመወደድ አትጣሩ፣ ሲገፏችሁ ላለመውደቅ እንጂ ላለመለየት ግትር አትበሉ። እልፍ ማለትን ልመዱ! ሕይወት ከሰውም ከእግዚአብሔርም ጋር የምንጓዛት መስካችን ናት። ስለዚህ ከሰው ጋር ያለንን ግንኙነት በፍቅር እናድርገው። አንድነታችሁ ብቻ ሳይሆን ከሰው ጋር ስትለያዩም በሰላም አድርጉት።

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

02 Feb, 18:00


ተመስገን

ኑር ብለህ እድሜ ስለጨመርክልኝ። ኑር ብለህ ልታኖረኝ ታማኝ ስለሆንክልኝ፣ ሳትሰስት ከፍቅር ጓዳህ የእድሜን ጸጋ ስለቸርከኝ አመሰግንሃለው።

መኖር ብርቅ በሆነበት በዚህ ዘመን መኖሪያዬ ሆነህ ከክፉ ሸሽገህ ቀን ስላወጣህልኝ ተመስገን።

እግዚአብሔር ሆይ እንዳንተ ደግ እንዳንተ ቸር አላየሁም። የጨመርክልኝን ዘመን በክንድህ ቀዝፌ፣ በደምህ ተጋርጄ መኖር ይሁንልኝ።

መልካም ልደት ለእኔና በዚህ ቀን ለተወለዳችሁ ሁሉ ይሁንልኝ። ተባረኩ

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

31 Jan, 05:11


የንስሐ ሕይወት ይኑረን


" አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌም ፈፅሞ እጠበኝ፣ ከኃጢአቴም አንፃኝ፣ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና "
መዝ 50(51)


ዳዊት ስህተቱን የሚያምን፣ በደለኛነቱን የሚቀበል፣ ኃጢአቱን የሚናዘዝ ሰው ነው። በሽታውን የሚደብቅ መድኃኒቱ አይገኝለትም እንደሚባል ሊያድነው፣ ሊፈውሰው በሚችለው እግዚአብሔር ፊት ሆኖ እጠበኝ ቆሽሻለሁ፣ አንፃኝ በድያለሁ እያለ ራሱን ያራቁታል።

ከእግዚአብሔር ዘንድ መንፃትን ለማግኘት ኃጢአትን ማመንና መናዘዝ የመጀመሪያው ተግባር ነው። በሰራነው ኃጢአት ካላፈርንበት በበደላችን ካልተፀፀትንበት ቀጣዩ እርምጃችን አይቀናም። ስለዚህ በሰራነው በደልና ኃጢአት እውነተኛ ጸጸት መፀፀትና የንስሐ መንገድን መጀመር አለብን። ይህን ስናደርግ ወደ እግዚአብሔር የጀመርነው ጉዞ የመፅናናትና የዕረፍት ይሆንልናል። ትንሿን ኃጢአት ንቀን አንተዋት ቶሎ እንናዘዛት። ትናንሾቹን ቀበሮዎች አጥምደን ካልያዝናቸው ነገ የሚውጡን አዞዎች ይሆናሉ።

እግዚአብሔር የሚያነፃን በእርሱ እጅ ለመታጠብ ስንፈቅድ ነው። ለንስሐ የሚያስፈልገው ጸጸት የትናንቱን ሕይወት እየረገሙ ለመኖር ብቻ ሳይሆን ነገን በተሻለ መሰረት ላይ ጥሎ ከጌታ ጋር ለመኖር የሚያስችል መሆን አለበት። ንስሐ ያለፈውን የኃጢአት ክንብንብ ማውለቂያና ወደ ኃጢአት የሚያመሩ ምዕራፎችን ሁሉ መዝጊያ ነው። ምክንያቱም ንስሐ አንድ ያላዋጣን ኮንትራት መዝጋትና ሌላን ደግሞ እንደመሞከር ያለ ሳይሆን ያለውን ሁሉ ጥሎ አዲስ ሕይወት መጀመር ነው። ከኃጢአት ጋር የተገናኘ የትኛውም ውል ከሕይወታችን የምናፈርሰው በንስሐ ነው።

ለጸሎት የሰነፉ እጆቻችንን እናንሳ፣ ለንስሐ የማይንበረከኩ ጉልበቶቻችንን እናድስ። አንዳንድ በሽታዎቻችን፣ ሀኪም አላውቅልን ያሉ ህመሞቻችን በንስሐም ጭምር የሚድኑ ናቸው። የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ህይወታችን እንዲታደስ ያደርገዋል። የክርስቶስ ኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ሊያነፃን ዛሬም በፊታችን አለ። በንስሐ እንመለስ በደሙ እንታጠብ።


አቤቱ መድኃኔዓለም ሆይ እጠበን ቆሽሸናል፣ አንሳን ወድቀናል፣ አበርታን ደክመናል። ከአንተ እጅ በቀር የሚታደገን የለምና ለሠጠመው ጴጥሮስ የተዘረጋው እጅህ በኃጢአት በበደል ለሰጠምነው ልጆችህ ፈጥኖ ይዘርጋልን። አሜንን

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

29 Jan, 06:11


ቸርነትህ ነው
       
መጽሐፍ ቅዱሳችን በእግዚአብሔርን ቸርነት የተመላ ነው። ምድር የከደናት የእግዚአብሔር ቸርነት ነው። ይህ ሁሉ ሰው በልቶ ማደሩ የቸርነቱ ማሳያ፣ ይህ ሁሉ ሰው ተኝቶ መንቃቱ የቸርነቱ መገለጫ፣ ይህ ሁሉ ሰው በሕይወት መቆሙ የቸርነቱ ውጤት ነው። እግዚአብሔር ቸር ባይሆንልን ኖሮ አንድ ደቂቃ መኖር የዘላለም ያህል ረጅምና ጭንቅ ነው። ነገር ግን በሕይወት ውጣ ውረድ ውስጥ አንዳንድ ፈታኝ ሁኔታዎች ሲገጥሙን ይህንን የእግዚአብሔር ቸርነት የምንዘነጋበት ሁኔታ ብዙ ነው።

        ኑኃሚን እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ታምናለች።  ለምራቶቿ እንዲህ አለቻቸው።
    " ኑኃሚንም ምራቶችዋን፡— ሂዱ፥ ወደ እናቶቻችሁም ቤት ተመለሱ፤ በእኔና በሞቱት እንዳደረጋችሁ፥ እግዚአብሔር ቸርነት ያድርግላችሁ።" (ሩት 1:8)

         ነኃሚን በደረሰባት አስከፊ የሕይወት ምዕራፍ ውስጥ የምታውቀውን የእግዚአብሔርን ቸርነት ዘነጋች። የእግዚአብሔር ቸርነት ያለቀባት መሰላት። የእግዚአብሔር ቸርነት ለእኔ ባያልቅ ኖሮ የባሌንና የልጆቼን መቃብር ብቻ ባልታቀፍኩ በሰው አገር ሌጣዬን ባልቀረሁ ሕይወቴ የምሬት ሆነ ብላ አዘነች።
         
      "እርስዋም፡— ሁሉን የሚችል አምላክ አስመርሮኛልና ማራ በሉኝ እንጂ ኑኃሚን አትበሉኝ። በሙላት ወጣሁ፥ እግዚአብሔርም ወደ ቤቴ ባዶዬን መለሰኝ፤ እግዚአብሔር አዋርዶኛልና፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኛልና ኑኃሚን ለምን ትሉኛላችሁ? አለቻቸው።" (ሩት 1:20-21)

           ሰው ነን። ሰው ከሆንን ሰው የሚሰማው ስሜት ይሰማናል። የማይከፋው ሀብታም፣ የማያዝን ባለጠጋ፣ የማይጎድልበት ሞጃ የለም። ሀዘንና ብስጭት ለእግዚአብሔር ያለንን አመለካከት አዛብተውብን ያውቃሉ። ለዚህ እኔ ምስክር እሆናለሁ። ለምን አንተ እያለህ ይህ ሁሉ ደረሰብኝ ለምን ይህ ሁሉ መከራ መጣብኝ ብዬ አውቃለሁ። እርሱ እንዲህ እንድሰቃይ አይፈቅድም ብዬ ተሟግቻለሁ። እንዲህ መሆኔን እርሱ ፈቅዷል ስለዚህ ረስቶኛል ብዬ አጉረምርሜበታለሁ።
ጊዜያዊ ነገሮች የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ጥበብ እንዳንረዳ እንቅፋት ይሆኑብናል።

      ሩት ቃርሚያ ቃርማ ወደቤቷ ስትመለስ ስለ ቦዔዝ ለኑኃሚን ስትነግራት የመነመነው የኑኃሚን ተስፋ ነፍስ ዘራ ተስፋዋ ከቆመበት ቀጠለ።
         " ኑኃሚንም ምራትዋን፡— ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት።" (ሩት 2:20)

     እግዚአብሔር ወርዶ አይሰራም። ሰው በማጣት፣ ያገኘነውን በማጣት፣ ያተረፍነውን በመክሰር፣ የሰራነው በመፍረስ፣ ከማረፊያችን በመሰደድ፣ በተወለዱበት ባይተዋር በመሆናችን ማራ በሉኝ ሕይወቴ መረረብኝ እያልን ይሆናል። እግዚአብሔር ግን ቸር ነው። ሁሉ ሲጨልም ወደማታ ይመጣል። ቦዔዝን ይልክልናል። ሁሉ ሙሉ ነውና ጉድለታችንን ይሞላልናል፣ የጣልነውን ተስፋችንን ይመልስልናል፣ ሞታችንን ስንጠብቅ አዲስ ህይወት ሰጥቶ ያለመልመናል።

       ቦዔዛችን ክርስቶስ ዛሬም ከእኛ ጋር ነው። አናልፋቸውም ያልናቸውን ሁኔታዎች፣ ጊዜዎች ያሳልፈናል። እርሱ ቸር ነው። ማንም በሕይወታችን ላይ ይልሰራውን ድንቅ ስራ ይሰራልናል። ቦዔዛችን ይመጣል። ክብር ለእርሱ ይሁን!


       አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እናመሰግንሃለን። ዛሬ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ህይወታችን በእጅህ ነው ነፍሳችን በመዳፋችን ናት አንተ የወደድከው ብቻ በእኛ ላይ ህከናወናልና እናመሰግንሃለን። ቢርበን አጉራሻችን፣ ቢጠማን የህይወት ምንጫ ሆነህ የምታረካን አንተ ነህና ተመስገን። በቤታችን ሁሉ ሞልቶ አንተ አትጉደልብን፣ በሰው ዘንድ ባለጠጋ ተብለን ውስጣዊ ሰላምና እርካታን አትንፈገን። ስትሰጠን ሁሉን ከአንተ ጋር ስጠን። ቦዔዛችን ክርስቶስ ተመስገን።

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

26 Jan, 19:23


    "በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።" (መዝ 4:8)

ስለሁሉም እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን።

Adoni Gospel channel

26 Jan, 14:59


እግዚአብሔር ትልቅ ነው! ሊደርስባችሁ ያለውን ሞት በሕመም፣ ትልቅ ችግር እንቅፋት በምታክል ነገር፣ አደጋን በትምህርት ይቀይርላችኋል። ይገርማል ስራው ግሩም ነው።

እግዚአብሔር ይመስገን ልትሞቱ ነበር እግዚአብሔር ግን ንብረታችሁን አጥታችሁ እናንተ እንድትተርፉ አድርጓችኋል።

ተመስገን ተመስገን

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

21 Jan, 02:15


ወዳጆች ሆይ

        በባንክ ያስቀመጥከው ገንዘብህ ቁጥሩ እያሽቆለቆለ ይሆናል፤ ያተርፈኛል ብለህ የጀመርከው ስራ ትርፉ ቀርቶ ዋናውንም አልመልስ ብሎ ይሆናል፤ ደመወዝህ ሳያድግ የቤት ኪራይህ እየጨመረ ይሆናል.......ይሄንን ሁሉ ቁጭ ብለህ ስታስበው ደም ግፊትህም ስኳርህም አብሮ ሊጨምር ይችላል። ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል በሚለው ፈሊጥ ኑሮን አትግፋ እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ካንተ ጋር እንደሆነ አስብ። የከበደህን ቀለል ሊያደርግልህ፣ ካንገዳገደህ ነገር ሊደግፍህ፣ ባዛለህ ነገር ላይ ብርታት ሊሆንህ ሰው የሆነልህ ክርስቶስ ካንተ ጋር ነው። እህቴ ገንዘብ ቢኖርሽ መልካም ነው ስለሌለሽ ግን ምንም አትጨነቂ። ላንቺ የተፈጠሩት ፍጥረታት ሳይጨነቁ እየኖሩ አንቺ ለምን ትጨነቂያለሽ። የሳሎንሽ ውሻ የምትበላው ነገር ከየት እንደሚሸመት ስጋት ገብቷት አያውቅም። አንቺ የሚመግብሽ አምላክሽ እያለ ያበጀሽ የሰራሽ ፈጣሪሽ እያለ ለምን ትጨነቂያለሽ።

         ካዝና ያጣበበ ገንዘብ ቢኖራችሁ ደስተኛ እንደምትሆኑ ታስቡ ይሆናል። ዛሬ የጎደላችሁ ነገር ቢሟላላችሁ ዘና ብላችሁ የምትኖሩ ይመስላችኋል ግን አይደለም። ገንዘብና ደስታ ወንድምና እህት አይደሉም። ደስታ በገንዘብ የሚገዛም የሚለወጥ አይደለም። ድምፃዊ ቦብ ማርሊ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦" ገንዘብ ቁጥር ነው። ቁጥር ደግሞ መጨረሻ የለውም። ደስታን በገንዘብ በኩል የምትፈልግ ከሆነ ፍለጋህ ማለቂያ አይኖረውም።"

     አዎ ወዳጆቼ ገንዘብን ስናሳድድ ኪሳችን እያበጠ ሲመጣ ሆዳችን እየሰፋ፣ ምኞታችን እያደገ፣ ደስታችን እያነሰ፣ እርካታችን እየተሟጠጠ፣ የመኖር ውሉ ትርጉሙ እየጠፋ ይመጣል። ህይወት ክርስቶስ ሲደመር የሆነ ነገር፣ ክርስቶስ እና ገንዘብ የሚል ህግ የላትም። ክርስቶስ ብቻውን የምንከተለው የምንገዛለት ስለ እርሱ ሁሉን የምንተውለት ጌታ ነው። እርሱን ከያዛችሁ እንደ አየሩ ጠባይ አትሆኑም፣ እርሱን ከመረጣችሁ አለምና ፍላጎቷ አያምሯችሁም። ሁሉን ትተው እንደተከተሉት ሁሉን ትተን ልንከተለው ይገባል። በእግዚአብሔር መንግስት ሁሉ ሙሉ ነው። እግዚአብሔር ያለው ሰው አይጎድልም ይልቅ ሙሉ ነው። ተባረኩ

                           በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

19 Jan, 12:28


ለካ.........

       አንዳንድ ጊዜ ጭንቀት የዕለት ምግባችን የምንመገበው ፣ መከራ እንደ ውሃ የምንጨልጠው ፣ ፈተና እንደ አየር የምንስበው ቅርባችን ይሆንብንና ሕይወት መራር ትሆናለች። ጨለማው ላይ ብቻ ስናተኩር በጨለማው መኃል የወጡትን ኮከቦች ማየት ይሳነናል። ለካ በምናልፍበት የመከራና የችግር ጊዜዎች ውስጥ የእግዚአብሔር አብሮነት እንደ ኮከቦቹ የበዛ ነው። ለካ አይኖቹ በእኛ ላይ ናቸው። ለካ እጆቹ ሊረዱን ተዘርግተውልናል።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

13 Jan, 10:12


      (መዝሙር 91)

   " በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
    
    እግዚአብሔርን፡— አንተ መታመኛዬ ነህ፡ እለዋለሁ፤ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ።

    እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።

      በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ በክንፎቹም በታች ትተማመናለህ፤ እውነት እንደ ጋሻ ይከብብሃል።

      ከሌሊት ግርማ፥ በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር፥ ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም።

     በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም።

      በዓይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ብድራት ታያለህ።

       አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
  
       ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
 
       በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤

      እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል።

      በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።

      በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።

       ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።

      ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።


           አባት እግዚአብሔር ሆይ መጠጊያ መታመኛ የሁሉም ተስፋ ነህ። በዚህ በሰጠኸን አዲስ ቀን ብርሃንህን እንቀበላለን መለኮታዊ ምሪትህን እንከተላለን ጥበቃህ ከኛ አይለየን።

       በፍቅር ክንዶችህ ከበህ ያዘን። በመንገዳችን የሚመጣብንን ማንኛውንም ፈተና በድፍረት በጸጋህ ብርታት እንድናልፈው እርዳን።  በምሪትህ በፍቃድህ ታምነናል በራሳችን ግንዛቤ ከቶ አንደገፍምና አቅም ጉልበት ሁነን።

      አንተ ከሚያቆስለውም ከሚገድለውም ማዳን ትችላለህ። ችግሮችን በጸጋህ ጉልበት መቋቋም እንድንችል፣ በመከራ የሚማሩ እንጂ የሚሰበሩ እንዳንሆን ቀኝህ ትያዘን። በዙሪያችን ላሉ ሰዎች የተስፋና የመጽናኛ ምክንያት እንሆን ዘንድ ብርሃንህን በእኛ ላይ አብራ። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!!


አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

13 Jan, 04:40


      " ሃሳቤን ከሩቅ ታውቃለህ"
            (መዝ 139:2)

        እኛ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት የምናድግ ፍጡር ነን። ሁለቱም እድገቶች አስፈላጊ ናቸው። በእግዚአብሔር ፊት በቃሉ፣ በጸጋው፣ በመንፈሱ ልጁ ክርስቶስን ወደመምሰል ማደግ ሲኖርብን በእግዚአብሔር ፊት እየጎረመስን እንሄዳለን። እግዚአብሔር ያሳድገናል እንጂ አያጎረምሰንም። እኛ የዘላለም የእግዚአብሔር ጥገኞች ነን። አደግን ብለን ስናስብ የመጀመሪያው ድርጊታችን በራሳችን ሁኔታዎችን ለማቋቋም ጥበበኞች እንደሆንን እናስባለን። ስለዚህ በትንሿ ጭንቀታችን ውስጥ እግዚአብሔርን ወደጎን አድርገን በራሴ እወጣዋለው እንላለን። እግዚአብሔርን በትናንሿ ጭንቀታችን ውስጥ አላስጨንቀውም ብለን በማሰብ ከእርሱ ጋር ስላለንበት ሁኔታ ስለሚሰማን ስሜት ምን ማድረግ እንዳለብን መጸለይም የልብን ማውራትም እናቆማለን። ምክንያቱም እኛ ራሳችንን መቆጣጠር እንችላለን ብለን ስላሰብን። በዚህ ጊዜ የጠብታ ያህል የቆጠርናት ጭንቀት ባህር ሆና ታሰጥመናለች ያቃለልናት ትወርሰናለች። እግዚአብሔርን ማዕከል ያላደረግንበት እርምጃችንም ሕይወታችንም አይሰምርም። በዚህ ውስጥ ማስመሰል እንጂ እውነት የለም።

     እግዚአብሔር እድሜህ ረዝሞ ሽበት አውጥተህ ምርኩዝ ጨብጠህ እንኳን ያስፈልግሃል። ያለ እኔ ምንም ልታደርግ አትችልም ይልሃል። ትንሿንም ትልቋንም ጭንቀትህን ንገረው፣ አማክረው፣ አሳልፈህም ስጠው። ደህና ካልሆንክ በእግዚአብሔር ፊት ደህና መስሎ መታየቱን አቁም። እርሱ ወደራሱ እየጋበዘህ ነውና አንተ ከምትፍጨረጨር እርሱ በውበት ቢሰራው መልካም ነው። ምን ላድርግ ካልክ ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አያስፈልግህም ራስህን በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጥ። ስሜትህን በፊቱ አፍስስ። እርሱ ብቻ ልብህን ይፈልጋል። አዲስ ያደርገዋል። (ምሳሌ 23:26)

      ማስመሰልን ከህይወትህ አስወግደህ በእውነት መራመድ ጀምር።

የእግዚአብሔር ቀኙ ትደግፋችሁ

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

12 Jan, 12:53


አንተ ትችላለህ

     በሕይወታችን ውስጥ የሚሆነውን የሚፈጠረውን ነገር በእኛ ዓይን ስንመለከተው ሀዘን፣ ጭንቀት፣ ፍርሀትን ያመጣል። ነገር ግን እግዚአብሔር ነገሮችን ከሚሰራበት አቅጣጫ ሆነን ሕይወታችንን በመመልከት ከእርሱ ጋር እንስማማ።

      ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ ሊለወጥ በማይችለው ነገር ላይ የመቀበል እርጋታን፤ ሊቀየር የሚችለውን የመቀየር ብርታትን ሲያልፍም ፈቃድህን ፈቃድህ ካልሆነው የመለየትን ጥበብህን አድለን።

               በቸር አውለን


አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

12 Jan, 06:06


በመላው አሜሪካ የምትኖሩ ወዳጆቼ ሁላችሁ አይዟችሁ! ከእሳት የሚነጥቅ እሳቱን መናፈሻ የሚያደርግ፣ ከክፉ አደጋ የሚታደግ እናንተንም መላ ቤተሰባችሁን ሁሉ እግዚአብሔር አምላኬ ይታደጋችሁ። ነፋሱን ውሽንፍሩን ይገስፅላችሁ በረዶ ዝናቡንም ጸጥ ያድርግላችሁ። ፍፁም መጠበቅን ይጠብቃችሁ። በነገር ሁሉ ይራራላችሁ ልባችሁን በልቡ ደግፎ ይያዝላችሁ። ለምስጋና እንጂ ለክፉ ተላልፋችሁ መሰጠት አይሁንላችሁ። እግዚአብሔር በያላችሁበት የእሳት ቅጥር ሆኖ ይጠብቃችሁ።

Adoni Gospel channel

07 Jan, 04:38


እንኳን አደረሳችሁ!


በረት ሳይንቅ፣ ቤተልሄምን ሳይጠየፍ፣ ናዝሬትን ጀርባ ሳይሰጥ የተወለደው የናዝሬቱ ኢየሱስ ሕይወታችንን ሳንጠየፍ በፍቅር ይወለድበት።

የዓለምን ታሪክ ለሁለት የከፈለ የምህረት ዓመትን ያወጀ ጌታ በሕይወታችን ውስጥ የምስራች የሆነውን ምህረቱን ያውጅበት።

ሊኖር ሳይሆን ሊሞት ተወልዷልና ለእርሱ ኖረን የምናልፍበትን ጸጋና አቅም ይስጠን።

ለዓለም ሰላምን ሊሰጥ እንደመጣ ዛሬ በቤታችሁ አዕምሮን የሚያልፈውን ሰላሙን ይስጣችሁ፣ የማይነጥፍ ፍቅሩን ያድላችሁ።

በመወለዱ የምስራች እንደሰማን ምስራችን ስሙ። ልባችሁን ደስ ያሰኛችሁ። መልካም በዓል። እወዳችኃለሁ።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

05 Jan, 18:15


ከድካሜ አልፈህ የምትሰራ፤
ስብራቴን ጠግነህ ምታቆመኝ፤

የልቤን ትካዜ በፍቅርህ ዘይት የምትሽር፤
አበቃ ስል አዲስ ምዕራፍ የምትሰጠኝ፤
በፍቅርህ ከበህ የያዝከኝ፤
በጨነቀኝ ቀኖች በከፉብኝ ጊዜ ምርኩዝ የሆንከኝ፤

የአብ ልጅ ክርስቶስ ዛሬም ያረጀው በረት የሆነውን ልቤን ሳትንቀው ተወለድበት፤ አዲስ ታሪክ ፃፍበት።


አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

16 Dec, 16:10


እግዚአብሔር መልካም ነው በመከራ ቀንም መሸሸጊያ ነው።

አቤቱ አንተ ከክፉ መሸሸግ፣ ከጠላት መሸሸግ፣ ከራሳችንም መሸሸግ፣ ከማናየውም ከምናየውም ሁሉ መሸሸግ ትችላለህና ሸሽገን።

በእውነት በተስፋ መቁረጥ እንዳንዋጥ በተስፋህ ብርሃንህ ውስጥ ሸሽገን።

ከብቸኝነት ዓለም ውስጥ አውጥተህ ባንተ ፍቅር ውስጥ ሸሽገን።

ከሚፈታተነን እንደ ሰንሰለት ከረዘመብን መከራ ሁሉ አንተ ለይተህ ሸሽገን።


ረድዔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይህ ዘመን ያንተን እቅፍ የሚያስመኝ፣ ያንተን ክንድ የሚያስመኝ፣ ያንተን የምህረት መዳፍ የሚያስናፍቅ ነውና ልትሸሽገን ናልን!

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

13 Dec, 03:23


ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ


እስትንፋሴን ቀጥለው

ሊያቆመኝ የመጣውን አቁመው ሊጥለኝ የመጣውን ጣለው ሊያጠፋኝ የመጣውን ከፊቴ ጠርገህ አስወግደው

ነገን ማስፈራቱን ግፈፈው ምርኮ አድርገህ ስጠኝ

ወጀብ ማዕበሉን ሁሉ በስምህ ጸጥ አርገው

በእንባ የጨቀዩ ዓይኖቼን ዳብሳቸው

ሰላምህ በአዕምሮዬ፣ በልቤ፣ በቤቴ ደግሞም በዙሪያዬ ይንፈስ

በምንም አላርፍም አንተ ግን እፎይታዬ ሁን


እንዳልሰከነ ውኃ የታመሰችውን ነፍሴን አርጋት ድፍርሱን ሁሉ አንተ አጥራው

ያሰብኩትን አስጥለህ ያሰብክልኝን አስጨብጠኝ፣ የጨበጥኩትን አስለቅቀህ አንተን ልያዝህ፣ የጀመርኩትን መንገድ ሳልጨርሰው መንገድህን ምራኝ


የጠላት ምክር ሀሳብ ሁሉ በስምህ ሀይል ይበተን

በምገባበት በምደርስበት ሁሉ ያንተ ሞገስ ይቅደምልኝ አንተ ታይልኝ

ሀሌሉያ

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

09 Dec, 11:57


    " አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወደ ባሪያህ ጸሎትና ልመና ተመልከት፥ ዛሬም ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎትና ጥሪውን ስማ" (1ኛ ነገ 8:28 )

       አቤቱ ጌታዬ እግዚአብሔር ሆይ የእኔንም የህዝቦችህንም ጸሎት ስማ!

               ወዳጆቼ ጸልዩልኝ!

Adoni Gospel channel

29 Nov, 09:01


ሕይወታችሁ ከገባችበት አጣብቂኝ ቅርቃር ውስጥ የእግዚአብሔር መለኮታዊ ኃይል ያውጣችሁ።

Adoni Gospel channel

28 Nov, 13:10


ኢየሱስ ወንጌላችን

ጠፋሁ በስራ ተጠምጄ፣ ጠፋሁ በትምህርት ተጠምጄ እንላለን። የተጠመድነው በእግረመንገድና በጊዜያዊ ኑሮ ነው። ሊያጠምደንም ልንጠመድም የሚገባው በወንጌል ነው። ወንጌል የምስራች ነው የምስራቹም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ለሰዎች ክርስቶስን ከመስበካችን በፊት በየቀኑ ክርስቶስን ለራሳችን እንስበከው። ለሌሎች ክርስቶስን ከማቅረባችን በፊት እኛ በክርስቶስ ፊት እንቅረብ። ለሌሎች ክርስቶስን ከመንገራችን በፊት እኛ ራሳችንን በክርስቶስ እንጥመደው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይሰለች ሱስ፣ የማይጠገብ ሕይወት፣ የማይታበል እውነት፣ የማይገፋ ፍቅር ነው።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

28 Nov, 08:38


"በማለዳ ምሕረትህን አሰማኝ፤"
        (መዝ 146:8)


          ሰውን የሚያቆመው የተጫማው ጫማ፣ የቆመባት መሬት፣ የበላው ምግብ ሳይሆን የእግዚአብሔር ምህረት ነው። ዛሬን የቆምኩት በራሴ ነው የሚል ደፋር አይጠፋም ነገር ግን እግዚአብሔር እግዚአብሔር ስለሆነለት ነው ዛሬን የቆመው። ብዙዎች ማለፋችንን ሲመኙ፣ ብዙዎች መጥፋታችንን ሲመኙ፣ ብዙዎች ሊጥሉን ሲሸርቡ፣ ብዙዎች ሊገድሉን ሲያደቡ ይሄን ሁሉ ሸሽጎ በህይወት ያቆየን ምህረትህ ነው።

       ነፍሳችንን ያረጋጋት፣ እንቆቅልሻችንን የፈታው፣ ጥያቄያችንን የመለሰው ምህረትህ ነው። እኛ ለሰው በጎ የምንሆነው እስከታዘዙን ድረስ፣ እሺ ብለው እስከተገዙልን ድረስ ነው ያጠፉ ቀን፣ የተሳሳቱ ቀን በጎነታችንን እናቆማለን። ምህረት የለሾች እንሆናለን ጨክነን ጀርባ እንሰጣቸዋለን። እግዚአብሔር ግን እየበደልነው ምህረቱን ያበዛልናል፣ እያጠፋን ምህረቱን ያበዛልናል። በጥፋታችን በበደላችን ውስጥ ሆነን እንኳ ምህረቱን የሚያበዛልን ከበደላችን ከጥፋታችን ጋር ስለተስማማ አይደለም የእኛን ጠንካራ ልብ በምህረቱ ለማለስለስ፣ በምህረቱ ለማከም ስለሚፈልግ ነው። ምህረቱ ለኃጢአት መስሪያ ልዩ ፍቃድ አይደለም። ስህተታችንን የምናርምበት የእንደገና እድላችን ነው።

       ገቢዬ አይቀንስ እንጂ፣ ስራዬ ሁሌም ያትርፍ እንጂ፣ እውቀቴ ውሎ ይግባ እንጂ፣ ጉልበቴ አይዛል እንጂ እኖራሉሁ አትበሉ። እነዚህ ነገሮች ለእኛ የተፈጠሩ ናቸው። ለእኛ የተፈጠሩ ነገሮች መኖሪያችን ሊሆኑ አይችሉም ይልቅ የእግዚአብሔር ምህረት ይብዛልን። እርሱ በሕይወት ያኖረናል።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

25 Nov, 04:45


ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፦

          አንተ የድሀ ጌጥ ነህ፣ የምናሳየው የምንለብሰው የምድርም የሰማይም መዋቢያችን አንተ ነህ።

     አንተ የማትቆሽሽ ልብሳችን፣ የማትዝግ ዝርግፍ ጌጣችን፣ ከአልማዝና ከከበሩት ማዕናት ሁሉ ለኛ የከበርክ የልባችን ውበት ነህ።

      ሀብታም ብቻ የማያገኝህ ለድሆች ቅርብ የሆንህ፣ ለልባችንም የተጠጋጋህ፣ አትመጥኑኝም ብለህ የማትፀየፈን፣ የተቸገራችሁ ናችሁ ብለህ ጀርባ የማትሰጠን አንተ ብቻ ነህ።

     እንዳንተ ያለ የለም። እንዳንተ ያለ አይኖርም። እንዳንተ ያለ ብቸኛ ወዳጅ አናገኝም። የተረሳውን አስታዋሽ፣ የተጠሉትን አፍቃሪ፣ የሌጣዎች ሀብት፣ የጎስቋሎች አለኝታ እንዳንተ የለም።

      እንወድኃለን ስለወደድከን፣ እናከብርሃለን ስላከበርከን፣ እንቀድስሃለን ስለቀደስከን፣ እንኖርልሃለን ስለሞትክልን ስምህ ቡሩክ ይሁን።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

23 Nov, 04:12


" እርስ በርሳችሁ በኃጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች።" ያዕ 5፥16


አንዳችን ለአንዳችን ስንጸልይ እግዚአብሔር የደከሙትን ያበረታል፣ የዛሉትን ያፀናል፣ የወደቁትን ያነሳል፣ ተስፋ የቆረጡትን ያስቀጥላል። ስለዚህ ቅዱሳን ሁላችሁ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት ስትሆኑ አስቡኝ። እግዚአብሔር በመልካም ያስባችሁ!!!!

አዶኒ

Adoni Gospel channel

21 Nov, 07:09


አቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ።

ባህሩን ረግጠህ የምትረማመድበት ዛሬም የብዙውን ሰው መከራና ችግር ጭንቀትና ውጥረት ተረማመድበት ሰላምህን አስፍንበት። በዚህ ሰዓት በሀሳብ ማዕበል ለሚናጡ፣ ልባቸው የታወከባቸውን ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን በሚለው አሳራፊ ቃልህ ተገለጥላቸው። የሚያነቡትን እንባ አባሽ፣ የተሰበሩትን ጠጋኝ፣ የወደቁትን አንሺ፣ የታሰሩትን ፈቺ፣ የታመሙትን ፈዋሽ የሆንክ ጌታ ሁሉ ይፈልጉሃልና ለሁሉ መፍትሔ ሆነህ ና። የነገሩህን የማትረሳ፣ የጠየቁህን የማትነሳ አንተ ረድዔታችን ሆይ ዛሬ ታስፈልገናለህ። ሁሉ ለጨለመበት፣ በር ሁሉ ለተዘጋበት፣ የሚሰማው ላጣ የሚጎበኘው ለቸገረው ሁሉ የአንተ ታዳጊ እጅ ትዘርጋ። ባወራው የሚረዳኝ ብናገረው ንግግሬ የሚገባው የለም ብሎ በዝምታ ተሸብቦ ለተቀመጠው ሁሉ የሚገላግለውን ብርሃንህን ፈንጥቅለት። አንገት የደፋውን ሁሉ በስምህ ቀና አርገው። ዋይታና ሀዘን በሰው ሁሉ ቤት ገብቷል አንተ ለሁሉ ዘንበል በል። አንተ አልፋውም ኦሜጋውም መፍትሔ ነህ፣ አንተ ፊተኛውም ኋለኛውም መድኃኒት ነህ ቅረበን። የመኖር ውሉ የጠፋባቸውን ነግቶ አልመሽ፣ መሽቶ አልነጋ ያላቸውን፣ በነፍሳቸው የቆሰሉትን፣ ልባቸው በውስጣቸው የፈሰሰችባቸውን ከአንተ ውጪ ታዳጊ የሌላቸውን ሁሉ ዛሬ ተገናኛቸው። ለእነዚህ ሁሉ ልጆችህ እንደ ሳንራዊቷ ሴት ወዳለችበት እንደሄድህ ዛሬም ወደነዚህ ልጆችህ በፍቅርህ፣ በምህረትህ፣ በቸርነትህ ሂድላቸው። አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ተመስገን። አሜን!!!

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

15 Nov, 19:07


"እምነታችሁ የት ነው?"
    (ሉቃ 8፥25)



       የለበስነው ስጋ የሚታይ መደገፊያ፣ የሚዳሰስ መታመኛ ይፈልጋል። ለዚህ ነው በእግዚአብሔር ከመታመናችን ይበልጥ በሚገጥሙን ማዕበልና ወጀቦች የምንፈራው። ሰው መሆን የአሁንን ብቻ እንድንመለከት ያደርገናል እምነት ግን ከዛሬ አሻግረን እንድናይ ያደርገናል።

      እምነት ማጣት ዛሬ ላይ እንድዘገይ ትላንት በሕይወታችን ያየነውን የእግዚአብሔርን እጅ ያስረሳናል። ሐዋርያቱ በጀልባቸው ላይ በገጠማቸው ማዕበል ምክንያት ትላንት ያዩትን የጌታን ተዓምር ዘነጉት።
ይህ ታሪክ ዛሬ ለእኛ ትልቅ ጠቀሜታ አለው.  ኢየሱስ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የነበረው ሰላም ደቀ መዛሙርቱ ካጋጠሟቸው ፍፁም ብጥብጥ ጋር ሲነፃፀሩ ማየት የሚያስደንቅ ነው።  ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ስለ እምነት ማነስ ስለገሰጻቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የሆነውን ያውቅ ነበር።  በዚያን ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ በእግዚአብሔር ከመታመናቸው የበለጠ ማዕበሉን ፈሩ። 

        ጊዜ ጥሩ ሲሆን እግዚአብሔርን መታመን ይቀላል።  ነገር ግን ጊዜዎች አስቸጋሪ ሲሆኑ በእግዚአብሔር መታመን የበለጠ አስፈላጊ መሆኑን ማስታወስ አለብን።  ስንፈራ ወይም ስንጨነቅ በኢየሱስ ላይ ያለን እምነት ምን ያህል ደካማ እንደሆነ ራሳችንን እያጋለጥን ነው። 

        ሕይወትን መተንበይ አይቻልም። በመንገዳችን ላይ አውሎ ነፋሶች ይኖራሉ፤ ነገር ግን ነገሮች ያልተረጋጉ እና እርግጠኛ ያልሆኑ ሲመስለን የእግዚአብሔር የማይለወጥ ባህሪ ጠንካራ መሰረት ይሰጠናልና በእርሱ ልንደገፍ ይገባል።  ጌታችን ኢየሱስ በመንፈሱ በውስጣችን አለ እስከ አለም መጨረሻም ከእኛ ጋር ይኖራል።
 

        አቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እያለፍንበት ያለው ማዕበል፣ እያንገላታን ያለው ወጀብ ከብዶናልና ይህንን ጊዜ የምናልፍበትን ጥንካሬ እንድትሰጠን እንለምንሃለን። ማዕበሉን ፀጥ የሚያደርገው ቃልህን በማዕበላችን ላይ አውጅበት። ከመጣብን መከራ ይታስተምረን ያሰብከውን ቁምነገር አስጨብጠን ካንተ ጋር መተላለፍ አይሁንብን። በመከራ ውስጥም በፍቅር ስለምትጠብቀን ተመስገን።

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

14 Nov, 18:06


"ማርታ ግን አገልግሎት ስለ በዛባት ባከነች፤ ቀርባም። ጌታ ሆይ፥ እኔ እንድሠራ እኅቴ ብቻዬን ስትተወኝ አይገድህምን? እንኪያስ እንድታግዘኝ ንገራት አለችው።" ( ሉቃ 10:40)

ሁልጊዜ ማስተዋል ያለብን ጥሩ በልክ ይመዘናል እንጂ ልክ በጥሩ አይመዘንም። ማርታ የምታደርገው ነገር ጥሩ ነው የማርያም ተግባር ግን ልክ ነው። ጌታ ኢየሱስ ማርታ የምታደርገውን ተግባር አልነቀፈም ማርያም ግን የተሻለውን እያደረገች ነው። ማርያም ከእግሩ ስር ሆና ቃሉን መስማት፣ እርሱን መውደድና ማምለክ ጀምራለች። ከጌታ ጋር መሆን እርሱን የማወቅና በእርሱ የመተማመን ምስጢር ነው።

      እንደ ማርታ በስራ ተጠምዳችሁ ይሆን? ቢዚ ናችሁ? ሰዎች፣ ሁኔታዎች ከጌታ ፊት እንድትርቁ ግፊት እያረጉባችሁ ነው? ጌታ ከእኛ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ይፈልጋል። ሊመክረን፣ ሊገስጸን፣ የልቡን ሊነግረን ይፈልጋል። እኛ ግን እንደ ማርታ በጓዳ ነን። እኛ በጊዜያዊ ነገር ተጠምደናል። እንደ ማርያም ፊቱን ልንፈልግ የልቡን ሃሳብ ልናደምጥ ጊዜ ልንመድብለት ይሻል። ጊዜ የለኝም ያላለንን ጌታ ጊዜ አንንፈገው።  በሰላም እደሩ


🙏አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

13 Nov, 18:10


  
የናፍቆት ስፍራችን እግርህ ስር ነው

       ዛሬ ዓለማችን ላይ ሕይወትን ቀላል ለማድረግ ብዙ ባለሙያዎች በየምርምር ጣቢያው በራቸውን ዘግተው ቀመር ሲቀምሩ ደረስንበት የሚሉትን ሲሞክሩ ይውላሉ። ለክርስቲያን ሕይወት ቀላል የሚሆነው ከአገር አገር እየዞረ መስራቱ ስጋውን በምቾት ማደላደሉ ላይ ሳይሆን ከእግዚአብሔር እግር ስር ቁጭ ማለቱ ነው።

በእግዚአብሔር እግር ስር ቁጭ ስትሉ በዓለም ያለው ርኩሰት፣ ክፋት ያመልጣችኋል። የእግዚአብሔር እግር ስር የሚፈስ የቃሉ ጅረት አለ።

ቃሉ እናንተ የማትደርሱበትን የሕይወታችሁን ክፍል እንኳ ዘልቆ ይደርሳል። ርካታን ይሰጣችኋል።

እግሩ ስር ትልቅ በረከት አለ። ሩት ቦዔዝ እግር ስር ተኝታ የቦዔዝን መቤዠት እንዳገኘች ሁሉ ጌታ እግር ስር ቁጭ ብለን የቃሉን ፍሪዳ በልተን ልባችን ተማርኳል ዘላለማዊ ሕይወትን አጭደናል።

እግሩ ስር ትቢያ ሳይሆን በረከት አለ። ራሳችንን በፍቅር አዋርደን ከእግሩ ስር መዋልና ማደር ስንጀምር እግዚአብሔር በጊዜው ከፍ ከፍ ያደርገናል።

  "እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ"
(1ኛ ጴጥ 5፥6 )

      አቤቱ ጌታ ሆይ ከእግርህ ስር ኑሯችንን ደስታችንን አርግልን። ማርያም የማይቀሟት በጎ እድልን ያገኘችው እግርህ ስር ቁጭ ብላ ነው። የማንቀማው በጎ እድላችን እግርህ ስር ነውና አታሳጣን። የቃልህ ድርቅ አያግኘን በእግርህ ስር መረስረስ ይሁንልን። አቤቱ በምትወደው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለመንኩህ! አሜን


🙏አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

12 Nov, 14:45


ላረጀው ጥያቄያችሁ
እግዚአብሔር አዲስ መልስ ነው!

ለሞተው ነገራችሁ
ክርስቶስ ትንሳኤያችሁ ነው!

ተመስገን

Adoni Gospel channel

09 Nov, 11:44


“ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤”
— መዝሙር 51፥2

አባት እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ፊት የተራቆትነው በፊትህ የተገለጥነው ልጆችህ ፊትህን ሽተን መጥተናል ዘንበል በልልን ዓይኖችህን በእኛ ላይ አድርጋቸው ልብህን ክፈትልን።

አቤቱ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ በተለያዩ ርኩሰቶች፣ በደሎች፣ የኃጢአት ልምምዶች ረክሰናል የአንተን ፈቃድ ትተን ለፍቃዳችን የተገዛን በስጋና ደም ሀሳብ የተዋጥን ሆነናል እባክህ ይቅር በለን ቀድሰን ጸጋህን አብዛልን።

ከምንጓዝበት የኃጢአት መንገድ እንድትመልሰን ከዚህ የኃጢአት ልምምድ በቃ ብለህ እንድመልሰን እጃችንን ይዘህ እንድታወጣን እንናፀንሃለን።

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ሀሳባችን በውስጣችን ረክሷል፣ አንደበታችን በፊትህ ረክሷል፣ ድርጊታችን አንተን የሚያሳዝን ሆኗል በፊትህ መልካም ነገር የለንምና እባክህ ልባችንን ቀድሰው ልባችንን እንድታጥበው እንማፀንሃለን።

በሕይወታችን ስፍራ ነስተንሃል ቅድሚያ ስፍራውን ሁሉ ለሰው፣ ለገንዘብ፣ ለቁስ፣ ለኃጢአት ሰጥተናል እባክህ ጌታ ሆይ ይቅር በለን። አንተን ብቻ በደልኹ እንዳለ አንተን ብቻ በድለናል አንተን ብቻ አሳዝነናል እባክህ እንደልቤ እንዳልካቸው አገልጋዮችህ እንደልብህ እንድንሆንልህ በቅድስና እንድንመላለስ አንተን በሕይወታችን ማክበር እንዲሆንልን እባክህ በነገር ሁሉ አግዘን እርዳን።

የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛን ጥለነው ወደመጣነው የጨለማ ህይወት እንዳንመለስ ልባችን በዓለም እንዳይሸፍትብን ጸጋህን አብዛልን። አቤቱ የጀመርነውን የሞት መንገድ ሳንጨርሰው እንደ ጳውሎስ መሀል ገብተህ አጨናግፈው አዲስ ሕይወትን ከአንተ ጋር አስጀምረን አሸንክታባችንን አስጥለን።

ከማንፈልገው ግን ካጠመደን እስራት ልባችንን ዓይኖቻችንን ለርኩሰት አሳልፎ የሰጠ ይህንን መንፈስ ከወንድና ከሴት ልጆችህ ሁሉ አንሳ የቅድስናን መንፈስ አፍስስብን። አንተን አንተን ማለትን አብዛልን። ከበረዶ ይልቅ ነጭ የምታደርግ፣ ነፍስን ማንፃት የምትችል እግዚአብሔር ሆይ አንተ ብቻ ነህና ከኃጢአት ከበደላችን በልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለየን። ሁሉ ሲሆን ለአንተ ክብር ይሁን!

🙏አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

05 Nov, 06:20


ሠላማችን ሆይ


             አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ላይ የሚከሰቱት ሁከቶች ምንጫቸው ምን እንደሆነ ግራ ይገባናል። ሁሉ አለን ስንል ምንም እንደሌለን ይሰማናል።  ጥሩ ቤት አለኝ፣ ጥሩ ገቢ አለኝ፣ የተሟላና ጤና አለኝ፣ የሚያስመሰግን ሙያ አለኝ፣ መኪና እየቀያየርኩ እነዳለሁ፣ ጥሩ መዝናኛ ቦታዎች አሳልፋለሁ፣ ብዙ ትምህርቶችን ከሀገር ውጪ የተማርኩ፣ በውበት ቢባል ቁንጅናን የተላበስኩ በጠቅላላው በሚታየው ነገር ጎደለኝ የምለው ምንም ነገር የለም። ይሄ ሁሉ አለኝ  ነገር ግን ሰላም የለኝም የሚሉ ሰዎች በርካታ ናቸው። በጥሩ ስጋዊ ምቾት ውስጥ ሰላም እንደ አየር ያጠራቸው፣ ከቅኝት እንደወጣ ሙዚቃና እንደተዘበራረቀ ኖታ ሰላም በማጣት ሕይወታቸው የታወከባቸው ብዙ ናቸው።

          ይህ ሁሉ ምቾት የአንዱን የሰላም ቦታ ሊተካ አይችልም። ሰላም የሌለው ሰው ቀለሙን በጨረሰ ብዕር የመፃፍ ያህል ውስጡ ባዶ ይሆናል። ሰላም ከሕይወታችን ሲሟጠጥ ነፍሳችን በውስጣችን ትሟሟለች፣ መንፈሳችን ይደርቃል። ለዚህ መፍትሄው ሰላምን የማግኛ አምስት ዘዴዎች የሚሉ የዓለም ማስታገሻዎችን ማግበስበስ አይደለም።

          ጌታችን “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) ብሎናል። ወዳጆች ዓለም ሰላም አላት ነገር ግን ሰላሟ ኦርጂናል ሳይሆን ፎርጂድ ነው። የዓለም ሰላም የሚሄድ ግን የማይከርም፤ የሚያረግርግ ነገር ግን የማይፀና ነው። አልፎ አልፎ የሚመጡ ሰላሞች አገኘን ስንል እናጣቸዋለን፤ ደረስን ስንል እንርቃቸዋለን፤ ጨበጥን ስንል እንበትናቸዋለን።
ሰላምን ማንም አይሰጣችሁም ሰላም የግል ንብረቱ የሆነለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

      ሕይወታችን ወደዛም ወደዚህም ማማተር የለባትም ሰላሟ የሞተላት የቀራንዮ ሙሽራ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰላማችሁን የትኛውም ነገር ላይ አትመስርቱ። ሰላሜ ልጄ ነው ስትሉ ልጃችሁ ሲታመም ሰላማችሁን ታጣላችሁ፤ ሰላሜ ስራዬ ነው ስትሉ ከስራችሁ ሲዘጋ ወይም ስትባረሩ ሰላማችሁ ይከስማል፤ ሰላሜ ገንዘቤ ነው ካላችሁ ገንዘብ የምትጠብቁት እንጂ የሚጠብቃችሁ ስላልሆነ ሰላም አይሰጣችሁም፤ ሰላሜ እገሊትና እገሌ ናቸው ካላችሁ እነርሱ ሲለይዋችሁ ሰላማችሁ አብሮ ይለያችኋል።

         ወዳጆቼ ሰላምን በጦርነት አታመጧትም፣ በጠረጴዛ ላይ የሃሳብ መንሸራሸር ሰላምን አትጨብጧትም፣ ጥሩ የሰላም ዜማ በማቀንቀንም አታገኟትም። ሰላምን የትም አትገዟትም ነገር ግን ሰላማችን የእጁ ስጦታ ሳይሆን እርሱ ራሱ ነው።  “እርሱ (ክርስቶስ ኢየሱስ) ሰላማችን ነው" (ኤፌሶን 2፥14-15) ብሏልና። ሰላማችን ክርስቶስ ነው። ከራሳችን ጋር ያስታረቀን፣ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ያስታረቀን፣ ከተፈጠርንበት ዓላማ ጋር ያስታረቀን ብቸኛ ሰላም መድኃኔዓለም ነው። ዋጋ ብንከፍል የማንከስርበት ውድ ሕይወታችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
         
        አቤቱ የሰላም አለቃ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በዚህ ሰዓት ሰላም ላጡ ሁሉ ሰላም ሁንላቸው።
                         

አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
              

Adoni Gospel channel

03 Nov, 18:04


ጸሎት

የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እግዚአብሔር የሚያነባ እንባችሁን ይመልከትላችሁ፤ የልባችሁን ጩኸት ይስማላችሁ፤ የከበዳችሁን አንዳች ሸክም ያቅልላችሁ።

     አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እኛ የማናየውን የሰዎችን የችግር ጓዳ ታያለህ፤ ለኛ የማይታየንን በሰዎች ልብ ውስጥ ያለውን እንቆቅልሽ ታውቃለህ፤ የእንባቸውን ምክንያት ታስተውላለህ እባክህ ፈዋሽ አይኖችህ ፊትህን በሚሹት ላይ ሁሉ ትረፍ።

    አቤቱ በመከራ የሚያልፉትን፣ በማጣት የሚያልፉትን፣ በጉድለት የሚያልፉትን፣ በጭንቀት የሚያልፉትን፣ በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ የሚያልፉትን፣ በመንፈሳዊ የህይወት መዛል የሚያልፉትን፣ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ የሚያልፉትን፣ በመንፈሳዊ ህይወታቸው ቀና ቀና ማለት የከበዳቸውን ሁሉ ረድዔትህ ትድረስላቸው፤ በሚያበረታው መንፈስህ ጎብኛቸው። በምትወደው ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተማጸንኩህ።

                  አዶኒ

Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X
               @adonigospel

Adoni Gospel channel

03 Nov, 06:53


    አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? መዝ 39:7


        ብዙ የባከኑ ዘመኖችን አሳልፈናል። ተስፋዬ ብለን የያዝናቸው ነገሮች እንኳን ለእኛ ለራሳቸውም ተስፋ የማይሆኑትን ነው። ዲቪን ተስፋ አድርገን ኖረናል፣ ከብታሙን ዘመዳችንን ተስፋ አድርገን ኖረናል፣ ስልጣናችንን ተስፋ አድርገን ኖረናል፣ ውበቴ የእንጀራዬ ምንጭ ነው ብለን ተስፋ አድርገን ኖረናል፣ ጉልበቴ ውሎ ይግባ ብለን ጉልበታችንን ተስፋ አድርገን ኖረናል፣ እውቀታችንን ተስፋ አድርገን ኖረናል። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ በራሳቸው የቆሙ አይደሉም። እነዚህ ሁለ ከእኛ በፊት የነበሩ ከእኛም በኋላ መኖር የሚችሉ አይደሉም። ሁሉም ይጨነግፋሉ። ነገሮች ተስፋ ቢስ እንደሆኑ ስንወስን በሩን በእግዚአብሔር ፊት ዘጋነው ማለት ነው።
 
        ወዳጆቼ ችግሮቻችሁን፣ ምኞቶቻችሁን፣ እቅዳችሁን ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ውሰዱ። በሕይወታችሁ ተስፋ እንደሌላችሁ ወደሚሰማችሁ ደረጃ ከደረሳችሁ እምነታችሁን በግልጽ ችላ ብላችኋል ወይም በእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ያልሆነ ነገር ተስፋ ስታደርጉ ነበር ማለት ነው። ስለዚህ አሁንስ ተስፋዬ ማነው? ለምትሉ ተስፋችሁ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

        እግዚአብሔር ለእናንተም ከእናንተም በኋላ ለሚኖረው ትውልዳችሁ እንኳን ተስፋ ይሆናል። በግርግም ውስጥ በመጠቅለያ የተጠቀለለ ሕፃን የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ ምልክት አድርጎ የሰው ልጆችን እጣ ፈንታችንን ለወጠው።

        ተስፋ አድርገናቸው የነበሩ ነገሮች አሁን አንዳቸውም የሉም። እግዚአብሔር ግን አለ። ልባችሁን ከፈለጋችሁት በእግዚአብሔር ላይ ጣሉት።


አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

01 Nov, 15:28


          እኔ አሳርፋችኋለሁ

“እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።” — ማቴዎስ 11፥28


     ብዙዎችን ስለት ይዘን፣ ጥይት ተኩሰን፣ በድንጋይ ወግረን አልገደልን ይሆናል፤ ነገር ግን ጆሮ በመስጠት ከችግራቸው ሊወጡ የሚችሉትን ሰዎች ጆሮ በመንፈግ ገለናቸዋል። እንባቸውና ንግግራቸው ሕይወታችንን ይረብሸናል ብለን ጆሯችንን ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ አድርገንባቸዋል። እኛም ያልሞትነው እኛም የተረፍነው የምንተነፍስበት ስፍራ ቦኪም የሆነ ጌታ ስላገኘን ነው። ወዳጆቼ ለሰዎች የምናወራው ማበርቻ ቃል ባይኖረን እንኳ ችግራቸውን የሚሰማ ጆሮ ልንነፍጋቸው አይገባም።

         ከፍጥረት ውስጥ በቃል የሚበረታ፣ በቃል የሚፅናና፣ በቃል የቆመ ከሰው ውጪ የለም። እግዚአብሔር በቃሉ ከሚያጽናናው ፍጥረት ውስጥ የሰው ልጅ ብቸኛው ነው። ቃል ይጠግናል ቃል ያቆማል።

         ዛሬም በደጃችን የሚያደምጣቸውን የሚሹ በርካታ ወገኖች አሉ። የተበደሉ መንግስት እንዲሰማቸው፣ የታመሙ ሀኪም እንዲሰማቸው፣ የተቸገሩ ወዳጅ እንዲሰማቸው ይፈልጋሉ። ማረፊያ ያጣች ነፍስ ብዙ ናት።

         ሰውነታችን በእጅጉ ሲደክመን የጤና ባለሙያዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ዘይቤን መከተል፣ በቂ እረፍት ማድረግ አለባችሁ፣ በቀን ውስጥ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት መተኛት አለባችሁ  ብለው ይመክሩናል። ይህ ጥሩና ተገቢ ምክር ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ በእንቅልፍ፣ በእንቅስቃሴና በአመጋገብ የማይፈታ ጉድለት አለበት።

        መንፈሳዊው የሕይወት ክፍላችን በጤና ባለሙያ ሳይሆን በክርስቶስ ብቻ ይታከማል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም በፊዚካል ጤና ባለሙያዎች የማታውቀውን መንፈሳዊ ዕረፍት የሚሰጥ ብቸኛ መድኃኒት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈጣሪያችን እንደመሆኑ መጠን ያውቀናል። ድክመታችንን፣ ስብራታችንን፣ ትግላችንን ያውቃል። የሚያስፈልገን እረፍት ጎናችንን አልጋ ላይ በማሳረፍ የሚቀረፍ ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ በመቅረብ የሚፈታ ድክመት ነው ያለን።

       ወደ ነፍሳችን ጥልቀት የሚደርስ እረፍት መስጠት የሚችለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። ወደ ክርስቶስ ስንጠጋ የእረፍት ፕሮግራም አውጥቶ አይሰጠንም እርሱ ራሱ ሌላ የማያስመኝ እረፍት ይሆነናል። ሰው ሻይ ቡና ሊጋብዛችሁ ከዛም ከፍ ሲል ምሳ ሊጋብዛችሁ ይችላል ጌታ ኢየሱስ ብቻ ወደ ራሱ ይጋብዛችኋል።

      ጌታችን ኢየሱስ በከተማው የተከበሩትን፣ በስልጣናቸው ስመ ጥር የሆኑትን፣ በሀብታቸው የታወቁትን ሳይሆን በሕይወታቸው የደከሙትን፣ በዚህ ዓለም የቆሰሉትን፣ በሰው የተገለሉትን፣ አለም አይጠቅሙም ብላ ጡረታ ያወጣቻቸውን ወደ እርሱ እንዲመጡ ጋበዛቸው።

       ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የዋህ በልቡም ትሁት ነውና እንድንከተለው ራሳችንን በእትሱ ላይ እንድንመሰርት ሕይወታችንን በእርሱ ላይ እንድናንፅ ይፈልጋል። ዛሬም ወዳጅ የምትፈልጉ ኑ ወደ ክርስቶስ፣ ማረፊያ ያጣችሁ አዕምሯችሁ የባከነ ሃሳባችሁ አልጨበጥ የምትኖሩለት ዓላማ ጥፍት ያላችሁ፣ ሁሉ የጉም ዝግን የሆነባችሁ ኑ ወደ ክርስቶስ እርሱ ብቻ እውነተኛ አሳራፊያችሁ ነው።

      አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

01 Nov, 04:23


አንተ ክርስቶስ ሆይ

የማናውቀውን ስላወክልን፤

የተረሳነውን ያስታወስከን፤

የማናየውን ያየህልን፤
የምንረግጠውን ቀድመህ የረገጥክልን፣ እሾህ አሜኬላውን ያስወገድክልን፤


የሞትነውን ሕይወት የዘራህብን፤

ከጠፋንበት ፈልገህ ያገኘኸን፤

ከጠላት መንጋጋ ፈልቅቀህ ያወጣኸን፤

ለክፉ መደበቂያ ዋሻችን፣ ለእኛ መሰማሪያ ለምለማችን ነህ፤

ተመስገን! ክብር ሁሉ ለአንተ ይሁን!


አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

31 Oct, 07:11


“አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ።”
  — ዘዳግም 6፥5


      እግዚአብሔር የምናመልከው ብቻ ሳይሆን የምንወደው አምላክ ነው። ሰዎችን ከአንገት በላይ በሆነ መውደድ፣ በጊዜያዊ ፍቅር፣ በጥቅም ፍቅር፣ ስሜታዊ በሆነ ፍቅር ልንወዳቸው እንችላለን። እግዚአብሔርን ግን በእነዚህ መውደድ ልንወደው አንችልም። እግዚአብሔርን ፍፁም ነውና ፍፁም በሆነ ልብ፣ ፍፁም በሆነ ነፍስ፣ ፍፁም በሆነ ኃይል ልንወደው ይገባል።

        እግዚአብሔርን በፍፁም ኃይል መውደድ ማለት  ከፍተኛ መጠን ያለው ኃይላችንን ለመንግስቱ ዓላማ ማዋል ማለት ነው። ደምና ላብ ከእንባ ጋር እስኪቀላቀል ማገልገልና መውደድ አለብን። እግዚአብሔር እኛን የወደደን የልጁን ደም አፍስሶ ነው። ደም ላፈሰሰልን ጌታ በሳምንት አንድ ቀን የምንሰጠው ጊዜ አይበቃውም ደማችን እስኪፈስ አጥንታችን እስኪከሰከስ ድረስ ልናገለግለው ልንወደው ይገባል።
       ክርስትና ስም ሳይሆን ተግባር ነው። በመስዋዕት የተጀመረ ሕይወት እንደመሆኑ መጠን የሚቀጥለውም በመስዋዕትነት ነው። አንድ ሰው ትርፍ ለሌለው ነገር ገልበቱን አያፈስም ጉልበቱን የሚያፈስለት ላቡን የሚያዘራለት ነገር ቅድሚያ የሚሰጠው ነገር መሆኑን ያሳያል። ጉልበታችንን ከእግዚአብሔር በላይ አፍስሰን የምንወደው ነገር ሊኖር አይገባም። ለእግዚአብሔር መንግስት እንደመትጋትና ካሎሪን እንደማቃጠል አስደሳች ነገር የለም።

         የክት ልብስ በዓል ሲደርስ ወይም አንዳንድ ፕሮግራሞች ሲኖሩን አውጥተን የምንለብሰው ልብስ ነው። እግዚአብሔር እንደ ክት ልብስ ለአንዳንድ ቀን ሳይሆን ዕለት ዕለት የምንለብሰው የምናጌጥበት የምንኖረው ነጩ ሸማችን ነው።

         እግዚአብሔርን በየቀኑ ውደዱት። መውደዳችሁን ቃሉን በመስማት ደሞም በመታዘዝ ግለፁት። እግዚአብሔርን በፍፁም ኃይሉ ወድዶ ልቡ የተሰበረ፣ ተስፋው የጨለመ፣ ወድዶ የተከዳ የለም። ዕለት ዕለት ራሳችንን በእርሱ እናስደግፈው እርሱን መውደድን እንለማመደው።

          እግዚአብሔርን በጨከነ ፍቅር የመውደድ ቀን ይሁንላችሁ!!!


                  አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

25 Oct, 02:52


የክርስቶስ ኢየሱስ የቆሰሉት እጆቹ ይዳብሷችሁ። አሜን

Adoni Gospel channel

24 Oct, 05:58


“እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
  — 1ኛ ጴጥሮስ 5፥5

      " ትሕትና ክፋት ከሞላባቸው ዓይኖች የምትከልል ጋሻ ናት።"

        ትህትና ልብን የሚያስውብ ልብስ ነው። ትህትናን የለበሰ በሁሉ ፊት ሞገስ ያለውና ያጌጠ ነው። ትሁት ሰው ምስጋናም ሆነ ትችት፣ ማግኘትም ይሁን ማጣት በህይወቱ ውስጥ ምንም ዓይነት ትርምስ አይፈጥርበትም። ለእርሱ ሰማይም ምድርም፣ ከፍታም ዝቅታም፣ መጥገብም መራብም ሁለቱም አንድ ናቸው።

  ትሁት ሰው ራሱን ከሰው በላይ የሚያደርግ ሳይሆን ከእኔ አንተ ከእኔ አንቺ የተሻልሽ ነሽ የሚል ነው። በእውቀቱ የማይታበይ፣ በሐብቱ የማይኮራ፣ በውበቱ ትዕቢት የማይዘው ነው።

     አፈር ፍሬያማ የሚሆነው የምድር ውዳቂዎች ሲጣሉበት ነው። በትህትና ራሱን ዝቅ ያደረገ ሰው ዝቅተኛ ቦታን ስለተቀበለ ማንም ሊጎዳውና ሊያዋርደው አይችልም። ይበልጥ ዝቅ ባልን ቁጥር ፍሬያማና ደስተኛ እንሆናለን።

     ትህትና ከእግዚአብሔር የቁጣ ቀን የምትሰውረን ዋሻ ናት። እግዚአብሔር ትሁታንን ይወዳል። ጸጋን የሚያበዛልን እግዚአብሔርን ወደኛ ዘንበል የሚያደርግልን ትሁት ልብን ስንይዝ ነው።

      አቤቱ ትሁቱ ጌታ ክርስቶስ ሆይ ትህትናን አልብሰን።

አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

21 Oct, 05:36


‘“የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸው”— ሐዋርያት 5፥19

        እግዚአብሔር የደስታ ቀን ወዳጅ ብቻ ሳይሆን የክፉ ቀንም ነው። ሰው የታሰረን ለመጠየቅ ጊዜ አጣሁ ሲል ጌታ ግን አስቸኳይ ስራዬ ወዳጄን መጠየቅ ነው ብሎ ከተፍ ይላል። ሰው ለታሰረ ሰው ዋስ መሆን ሲያቅተው ጌታ ግን እስረኛውን ሊፈታ ይመጣል።
   
       ሕይወት ጀርባ ስትሰጠን መልኳ ሲወይብብን በሚያስፈራ ጨለማ ውስጥ ስትከተን ወዳጅ ያልናቸው ሁሉ ከጨለማው ጋር ያብራሉ እግዚአብሔር ግን በጣም ጨለማ በሆነ ጊዜ ውስጥ ስንገኝ እንኳ ሊያድነን ጨለማችንን አልፎ ይመጣል።

      ሰው ማፅናኛ ቃል ሲነሳን እግዚአብሔር የእጃችንን ሰንሰለት ያወልቃል፣ ብረቱን ይሰብራል፣ ተስፋ መቁረጣችንን ይቆርጣል።

      ከግዞት ነፃ ያወጣናል፣ ከተተበተብንበት ፈትቶ ወደ ሕይወት እቅድ ሊያንቀሳቅሰን ይፈልጋል።

      አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ተአምር የምትሰራ አምላክ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። መውጪያ መንገድ ማየት በማንችልበት ጊዜ እንኳን እንዴት ሁኔታውን እንደምትለውጥ ታውቃለህና ስለዚህ ጥበብህ አመሰግንሃለሁ። በአንተ በታላቅ ኃይልህ በአስደናቂው ስምህ በጌታችን በኢየሱስ እንታመናለን ክብር ለአንተ ይሁን።

                         አዶኒ


Telegram👉 @adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

18 Oct, 12:46


በቤታችሁ

     እግዚአብሔር የከበደውን ያቅልላችሁ።
     እግዚአብሔር የጠፋውን ሰላም ይመልስላችሁ።
     እግዚአብሔር የታመመውን ይፈውስላችሁ።
     እግዚአብሔር የራቀውን ያቅርብላችሁ።
     እግዚአብሔር የቀረበውን ክፉ ያርቅላችሁ።
     እግዚአብሔር ፍቅርን ያብዛላችሁ።
     እግዚአብሔር የደስታን ጸጋ ያፍስስላችሁ።
     እግዚአብሔር ክርስቶስን ይግለጥላችሁ።
     እግዚአብሔር እንደልቡ ይስጣችሁ።
     እግዚአብሔር እንግዳ ሆኖ ይጎብኛችሁ።
     እግዚአብሔር ማረፊያ ይሁናችሁ።
       
                   አሜን!


በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

17 Oct, 05:44


የምንጠብቀው ተስፋችን
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ


ክብሩን ትቶ ለመሞት መጣ ዳግመኛ ሙታንን ሊያስነሳ እኛንም ሊወስደን ይመጣል።

በስጋ ሲመጣ ንግስናውን ተጠራጠሩ ንጉስ መሆኑንም ጠየቁ፤ ዳግም ሲመጣ ዓለም ሁለ እርሱ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ መሆኑን ያውቃል።

የእሾህ አኪልልን ደፋ፤ ዳግመኛ ሲመጣ የክብር አክሊልን ይደፋል።

የባሪያን መልክ ይዞ በድህነት መጣ፤ ዳግመኛ በስልጣን ይመጣል።

የዋህ ሆኖ በኃጢአተኞች መሀል ለመገኘት መጣ፤ ዳግመኛ በክብር ይመጣል።

ማራናታ
አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ቶሎ ና!

በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

15 Oct, 04:42


በድጋሚ የተለጠፈ

             " አራት ቀን ለመኖር
        አምስት ቀን አትጨነቅ "

መዲናችን አዲስ አበባ ላይ ታክሲ በመጋፋት የሚደርስብንን መንገላታት ታክሲው ውስጥ ስንገባ በታክሲው ጣሪያ ላይ የተለጠፉት ጥቅሶች መንገላታታችንን ያስረሱናል። ከምወዳቸው ጥቅሶች መሐል " አራት ቀን ለመኖር አምስት ቀን አትጨነቅ" የሚል ነው።

      እውነት ነው ከምንኖርበት የምንጨነቅበት ይበልጣል። ከቻላችሁ ቀን ተበድራችሁ ኑሩ እንጂ ቀን ተበድራችሁ አትጨነቁ። ስትኖሩ ማድረግ የምትችሉት ነገር እንዳለ ሁሉ ማድረግ የማትችሉት ነገር አለ። ማድረግ የምትችሉትን በእውቀታችሁ በጥበባችሁ ትከውኑታላችሁ፤ ማድረግ የማትችሉትን ብርቱ ክንድ ላለው ጌታ ትተውታላችሁ። መፀለይ እየቻላችሁ አትታገሉ።

          የስራ ባልደረባችሁን ዛሬ አልመጣም ሸፍንልኝ (ተክተኸኝ ስራልኝ) ትሉታላችሁ። መፀለይ እግዚአብሔር በናንተ ፋንታ ባቃታችሁ ጉዳይ ላይ ጣልቃ ገብቶ እንዲሰራላችሁ መጠየቅ ነው። ስለዚህ ፀልዩ ጉዳያችሁን ይስራላችሁ።

       በህይወታችሁ የሚያስጨንቅ ነገር አለ ግን ደግሞ እግዚአብሔርም አለ፤ በኑሯችሁ ብዙ ሸለቆ አለ ግን ደግሞ እግዚአብሔርም አለ፤ በቤታችሁ ብዙ ችግር አለ ግን ደግሞ እግዚአብሔርም አለ። እግዚአብሔር ተአምረኛ አምላክ ነው። እርሱ ውሃን ሰንጥቆ መንገድ የሚያበጅ አምላክ ነው። የተደፈነውን አላንቀሳቅስ የሚለውን ጉዳያችሁን ተረማምዳችሁ የምታልፉበት ድልድይን ያበጅላችኋል። እግዚአብሔር ድንጋዮችን ማዘለል የሚችል ጌታ ነው። እንደተራራ ከፊትህ የተጋረጠውን ጉዳይህን እንደዳማ ጠጠር አዘልሎ ያሳልፍሀል።

       እግዚአብሔር የታመመውን ብቻ አይደለም የሞተውንም የሚያስነሳ መለኮት ነው። ችግርህ ታሞ ቢሆን ያድንልሃል። ጠፋ፣ አከተመ፣ ከሰረ የምትለውን እንኳ ህይወት ዘርቶ ሊያቆምልህ ይችላል። እግዚአብሔር በእጁ መዳፍ ተዓምር የጨበጠ አባት ነው።

       እግዚአብሔር የመርዶክዮስን ፀሎት ለመመለስ፣ የመርዶክዮስን ጉዳይ ለመከወን ንጉሱን እንቅልፍ ነስቶ አሳደረው። ሲነጋ ታሪክ ገልብጦ ሟቹን ሙሽራ፣ ተራውን ሰው ባለ ማዕረግ አደረገው። ያንተንም ያንቺንም ጉዳይ እግዚአብሔር የሚከውንልህን ሰው እንቅልፍ ነስቶ ያስፈፅምልሀል። ያስጨነቀህን ጉዳይ ገልብጦ ያልጠበከውን ከፍታ ይሰጥሀል። ልብህን ከወደቀችበት አንስቶ በሰገነት ያኖራታል። ወፎቹ ስለ ቀጣዩ ምግባቸው አይጨነቁም። እኛም ስለማንኛውም ነገር መጨነቅ የለብንም። አትጨነቁ እግዚአብሔር ምቹ ነው።

“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።” — ማቴዎስ 6፥34

በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

09 Oct, 10:04


ተመስገን

“አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ። አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ሰምተኸኛልና፥ መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።”
  — መዝሙር 118፥28

        አንደበቴን አንተ ፈጥረሃል፤ እስትንፋስህንም አንተ ሰተኸኛል። ስለዚህም በሰጠኸኝ አንደበት፣ በፈጠርከው እስትንፋስ አንተን ብቻ አመሰግንሃለሁ። አንተን ብቻ እባርክሃለሁ፣ አንተን ብቻ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።

        አንተ አምላክ ስትሆን በስጋ ተዛመድከን፣ አንተ ትልቅ ስትሆን በእኛ ልክ ወደእኛ መጣህ፣ አንተ ጌታ ስትሆን የባሪያን መልክ ያዝህ፣ አንተ ሰማይና ምድርን በመዳፍህ ጨብጠህ የያዝህ ስትሆን በክፉዎች እጅ ተያዝህ፣ ዓለምን ሁሉ በሰከንድ ውስጥ አቅልጠህ ማጥፋት ስትችል በትህትና ዝቅ አልህ እንደ ወንበዴም ተቆጠርህ ይህ ለኔ ልዩ ፍቅር ነውና አመሰግንሃለሁ።

        አቁሳይ በሆነች አለም መድኃኒት የሆንከኝ፣ ክፉ በሆነች አለም ላይ ደግ የሆንክልኝ፣ ሲርበኝ አጉራሽ፣ ሲበርደኝ አቄፊዬ፣ ሲጠማኝ እርካታዬ፣ ስቸገር ሀብቴ የሆንክልኝ አንተን የናዝሬቱ ኢየሱስን አመሰግንሃለሁ።

        ጥቂት ለመንኩህ አብዝተህ ሰጠኸኝ፣ ትንሽ አንኳኳው ብዙ ደጅ ከፈትክልኝ ስለማይቆጠር ስጦታህ ስለማይከፈል ውለታህ አመሰግንሃለው።

       ብዙ ዘመን አሳዘንኩህ፣ ብዙ ዘመን በደልኩህ አንተ ግን ብዙ ዘመን ራራህልኝ፣ ብዙ ዘመን ይቅር አልከኝ፣ ሁሉን ይቅር ብለህ ተሸከምከኝ። ዛሬም ጽኑ ታማኝ፣ ቋሚ ወዳጅ፣ እውነተኛ አፍቃሪ ሆነህ ከእኔ ጋር ስላለህ አመሰግንሃለሁ።

       በቸር አውለኝ፣ ቅጥር ሰርተህ ጠብቀኝ፣ በደምህ ጋርደኝ። አሜን
      
በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

05 Oct, 03:49


     ይማርከን

  “የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥”
  — 2ኛ ቆሮ 10፥5

           የሰው ልጅ ሞተሩ ሆዱ ሳይሆን አዕምሮው ነው። አዕምሯችን ድል ወይንም ሽንፈት የሚወሰንበት የጦር ሜዳ ነው። አዕምሮ ለመልካም ወይንም ለመጥፎ ነገር ሊማረክ ይችላል። ሰው ምርጫ አለው ሃሳቡ እንዲመራው ይፈቅዳል ወይም ሃሳቡን ይመራል። ሃሳቡ ይማርከዋል አልያም ሃሳቡን ይማርካል።

       ይህ ሃሳብ ከየት ይመጣል ካላችሁ ከየአቅጣጫው ይመጣል። ከሰይጣን ይመጣል፣ ከስጋ ይመጣል፣ ከእግዚአብሔር ይመጣል። በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር ጥሩ ጊዜ በጸሎትና ቅዱሳት መጻህፍትን በማንበብ የምናሳልፍ ከሆነ ሃሳባችንን እግዚአብሔር ይመራዋል።
ይህን ማድረግ ካልቻልን ሃሳባችን በዙሪያችን ባለው ዓለም መመራት ይጀምራል። ወደ አዕምሯችን የሚመጣው እያንዳንዱን ሃሳብ መቀበል የለብንም እንደ እግዚአብሔር ቃል ፈትሸን ልናስተናግደው ይገባል።

      አንዳንድ ሰዎች ስሜታችሁን ሊጎዳ የሚችል ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ በዚህ ጊዜ ሰይጣን መራራ ዘርን በውስጣችሁ ይዘራና ልትበሳጩ እናንተም ቅስም የሚሰብር ንግግር ልትናገሩ ትችላላችሁ። ይህን ከማድረጋችሁ በፊት ብትችሉ ወደ አዕምሯችሁ የሚመጡትን አሉታዊ አስተሳሰቦች ውድቅ ማድረግና ሰላምና ደስታችሁን እንዳያሳጣችሁ ከቦታውም ከጉዳዩም ዘወር በሉ። ስለዚህ የተሳሳተ ሃሳብን ለማሸነፍ ምርጡ መንገድ በትክክለኛው ሃሳብ መተካት ነው።

       በየቀኑ በእግዚአብሔር ቃል አዕምሯችንን ስናድስ አስተሳሰባችን ይለወጣል። ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ስንውል አመላችን ይቀየራል። በዚህ ጊዜ በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ቁርኝት ይጠነክራል። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ለእኛም ሰላማዊ ህይወትን እንድንመራ ይረዳናል።

በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

28 Sep, 06:50


የኛ እግዚአብሔር


      እግዚአብሔር አንተን አጀንዳ አድርጎ ከጠላት ጋር ውርርድ ውስጥ የሚገባው ቁማር እየተጫወተ ገንዘብ መድቦ ሊያተርፍብህ አይደለም። አስተማሪ አስተምሮ ይፈትንሀል የሚፈትንህ ሊጥልህ ብቻ ሳይሆን ምን ያህል እውቀት እንደጨበጥህ ራስህንም እንድትፈትን ነው። እግዚአብሔርም ብዙ ዘመናትን አስተምሮህ ፍቅሩን ታማኝነቱን ምህረቱን አቅምሶህ ምን ያህል እንደተደገፍከው ምን ያህል እምነትህ ስር እንደሰደደ ለማወቅ በአንዳንድ ፈተናዎች መሀል ያሳልፍሀል።

       ኢዮብን አስታውሱ፦ ሰይጣን በእግዚአብሔር ፊት ቀርቦ ኢዮብ የሚያመልክህ የሚወድህ ህይወቱ ሁሉ የምቾት የስኬት ስለሆነ እንጂ ያለውን ብትወስድበት ይክድሀል ብሎ ከሰሰው እግዚአብሔርም ኢዮብ አይክደኝም ብሎ ተወራረደበት።

      ኢዮብ ባለጠጋ፣ ስኬታማ፣ ብዙ ልጆች ያሉት ጤነኛ ሰው ነበር። ነገር ግን በአንድ ቀን ጀንበር አደጋ ጣዮች ንብረቱን አወደሙ፣ ልጆቹን ገደሉ ሁሉም በዜሮ ተባዛ። ከዚህም አልፎ የገዛ ገላው በቁስል ተመትቶ ይመግልና እያሳከከው ይሰቃይ ነበር። ይህ ሁሉ ነገር ሲከሰት ኢዮብ ለምን እንዲህ እንደሆነ አላወቀም እግዚአብሔርንም አልበደለም። ኢዮብ 1:22

     ወዳጆቼ አንዳንድ ጊዜ ነገሮች ባልጠበቃችሁት ባላሰባችሁት ሰዓት እንዳልነበሩ ይሆናሉ። ህይወታችሁ ምስቅልቅል ይላል፤ የያዛችሁት ይተናል፤ የሰበሰባችሁት ይበተናል የኔ ያላችሁት የሌላ ይሆናል። ግራ ትጋባላችሁ ምን አጥፍቼ ምን በድዬ ነው ትላላችሁ። እናንተ ግን የበደላችሁት ያጠፋችሁት ነገር ላይኖር ይችላል እግዚአብሔር ግን በእናንተ ተወራርዶባችሁ ቢሆንስ?

       እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሁሉ አልነገረውም። እኛም ለምን ይሄ ሆነብኝ እያልን እግዚአብሔርን ልንጠይቀው አይገባም። እግዚአብሔር በኛ የወደደውን ሲሰራ ለምን አይባልም።

    በእኔ ላይ እየሆነ ያለው አልገባኝም አንተ ግን እየሆነ ያለውን ታያለህ ደግሞም ትቆጣጠራለህና እንደወደድክ አድርገው ብለን እምነታችንን ልናጠነክር ይገባል።

እግዚአብሔርን የምናመልከው ጎተራችን ሲሞላ ብቻ ሳይሆን ሲጎድልም ነውና። አለኝ ያልነውን ከኛ ዞር አድርጎት ያለን እርሱ ብቻ እንደሆነ ሲያሳየን ተመስገን እንበለው።

      በእግዚአብሔር ታምኖ የከሰረ የለም። ኢዮብ ያለውን ሁሉ አጥቶ ራሱን ማጥፋትን ምርጫው አላደረገም። እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ አለ። ኢዮብ 1:21

እግዚአብሔር ግን እምነቱን አይቶ ዝም አላለም የወሰደውን በእጥፍ መለሰለት። ወዳጄ ያንተም እንዲሁ ነው እግዚአብሔር የወሰደውን በትኖብህ አይቀርም በእጥፍ ይመልስልሀል።

   "ኢዮብም ስለ ወዳጆቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ምርኮውን መለሰለት፤ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ፋንታ ሁለት እጥፍ አድርጎ ለኢዮብ ሰጠው። "
ኢዮብ 42 : 10

                በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

25 Sep, 18:29


ታውቀናለህ


  “ አንተም፦ በስምህ አወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ።” (ዘጸአት 33፥12)

          
         ጆሯችን ሊሰማቸው የሚናፍቃቸው ድምፆች እንዳሉ ሁሉ ሊሰማቸው የማይፈልጋቸው መራራ ድምፆች አሉ። በሰው አለመረሳትና መታወስ ልባችንን በደስታ ሲያስቦርቅ፤ እንኳን በህይወት ቆመን ቀርቶ ሞተን እንኳ መረሳት የምንወደውን ሰዎች ማን ነበርክ? አላስታወስኩህም! ኸረ አላውቅህም! የሚሉ ድምፆች ስንሰማ የሚስቀውን ፊታችንን ይኮማተራል ልባችን በውስጣችን ይፈሳል።

          ሰው የሚያውቀን በሚያሸማቅቀው በማይነገረው ማንነታችን ይሆናል። ሰው የረሳን የሰጠነውን ፍቅር የቸርነውን መልካምነት ደፍጥጦ ይሆናል። ይህ ከሚያስገርመን በላይ ላይረሳ ያወቀን፣ ላይክድ የተዛመደን መኖሩን ስናስብ እጅግ ደስ ይለናል። በሰው ተረስቶ በማይረሳ አምላክ መታወቅ ምንኛ መታደል ነው።

          እግዚአብሔር ከዋክብትን አንድ ሁለት ብሎ የሚቆጥር ነው፤ በባህሩ ዳርቻ ያለውን አሸዋ በቁጥር የሚያውቀው ነው፤ ተራሮችን በመዳፉ የያዘ ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ ይህ ልዑል ሁሉን ያውቃል።

          ሰው ስለረሳችሁ ሰማይ የተደፋባችሁ ያህል የተሰማችሁ፤ ሰው ስለከዳችሁ ገደል የወረወራችሁ ያህል የተሰማችሁ አይዟችሁ እናንተን በስም የሚያውቃችሁ፣ እያንዳንዱ እርምጃው በዓይኑ ፊት የሆነ ጌታ፣ የምታለቅሱትን የዕንባ ዘለላ ሁሉ የሚመለከት ደግሞም የሚያብስ ጌታ ከናንተ ጋር ነው።

          ሰው አነጣጥሮ ተኩሶባችሁ ይሆናል የእግዚአብሔር ዓይን አነጣጥራ በናንተ ላይ በምህረት ታርፋለች፤ ሰው ለመጉዳት ይቀርባችኋል እግዚአብሔር ለማንሳት ክንዳችሁን ይዟል፣ ሰው ለመደበሪያ ይጠቀምባችሁ ይሆናል እግዚአብሔር ጉዳይ ኖሮት አብሯችሁ ይውላል፤ ሰው ትርፍ ናችሁ ይላችኋል እግዚአብሔር ልጄን የሰጠሁላቸው ዋናዬ ናቸው ይላል፤ ሰው አይረቡም አይችሉም ከንቱ ናቸው ይላል እግዚአብሔር በናንተ ላይ ዓላማዬ ብዙ ነው በዱልድሙም መስራት እችላለሁ ቀኛችሁን ስጡኝ ቀኝ ልሁናችሁ ይላል።

           ወዳጆቼ በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳላችሁ አላውቅም ግን በምንም ዓይነት ጓዳጎድጓዳ ውስጥ ብትሆኑም እግዚአብሔር ያላችሁበትን ሁኔታ ሳይጠየፍ ቦታው አይመጥነኝም ብሎ ሳይንቅ አብሯችሁ ይሆናል። ሕመሙ ሲበዛባችሁ፣ የቀን ብርሃን እንዳታዩ ዓይናችሁን ቢጋርዳችሁ አይዟችሁ በስም የሚያውቃችሁ እጁን ለማቀፍ የዘረጋላችሁ ጌታ ከናንተ ጋር ነው።

               በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

24 Sep, 09:09


👁


የእግዚአብሔር ዓይኖች በእኛ ላይ ናቸው። ሰጎን እንቁላሏን ለመፈልፈል ለብዙ ቀናት ዓይኗን ከእንቁላሉ ላይ አታነሳም አይኗን ዞር ያደረገች ቀን እንቁላሉ ይበሰብሳል። ልክ እንደሰጎኗ የእግዚአብሔር ዓይኖች በእኛ ላይ ናቸው።

ያልታደሉ "ከራስ በላይ ንፋስ" ይላሉ። እኛ ግን ከራስ በላይ ንፋስ የሚለውን ስንፍና አንዋስም። ምክንያቱም ከራስ በላይ ንፋስ ሳይሆን ከራስ በላይ የእግዚአብሔር ዓይኖች አሉ። ዓይኖቹ ሕይወታችን ናቸው ዞር ያሉ ቀን በሕይወት አንኖርም።

ጤናማነታችን በአመጋገባችን የመጣ አይደለም ጥንቁቅ የሆኑት ዓይኖቹ ስላረፉብን ነው። መወደዳችን ደመ ግቡ ሆነን አይደለም የዓይኑ ነጸብራቅ አርፎብን እንጂ!

ዓይኖቹ ለመታዘብ አያዩንም ጉድለታችንን ለመሙላት ይመለከቱናል። ዓይኖቹ በፌዝ አያዩንም ከጠላት ሊጋርዱን ያዩናል። አባቱ የሚያየው ልጅ በፊቱ ይቦርቃል በአንዳችም አይሰጋም። የእግዚአብሔር ዓይን አርፎብናል መውጪያ መግቢያችን በዓይኑ ቁጥጥር ስር ነው አንዳች አያስፈራንም።

የዓይንህ ማረፊያ ስላደረከን ተመስገን!


በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

22 Sep, 14:53


          ፍቅር

   “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤”
  — 1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4

      ፍቅር አካል የለውም ግን ተገልጦ ይታያል፤ ፍቅር አይዳሰሰም ግን ብዙዎችን ይዳስሳል፤ ፍቅር ኪሎው ስንት ነው አይባልም ከልክ ያለፈ ነው። ፍቅር በሰውነታችን ውስጥ እንደ ኩላሊት፣ እንደ ልብ፣ እንደ ጨጓራ አንድ ስፍራ ይዞ እዚህ ጋር ነው የተቀመጠው አይባልለትም በመላ ማንነታችን ውስጥ የፈሰሰና የተሰራጨ ነው። ፍቅር በዓይኖቻችን ሆኖ ሰው የረሳቸውን ይመለከታል፤ ፍቅር በእጃችን ሆኖ የወደቁትን ያነሳል፤ ፍቅር በእግራችን ሆኖ ወዳጅ ወደሌላቸው ሰዎች ይገሰግሳል፤ ፍቅር በልባችን ሆኖ ሰውን ሁሉ ያፈቅራል።

      ፍቅር ስሜት አይደለም እውነት ነው። ስሜት ተለዋዋጭ ነው ፍቅር ግን የጸና ነው። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ፍቅርን ከስሜት ጋር ብቻ
አያይዞ የማይጠቅሰው። ፍቅር ሰፊ የትዕግስት ትከሻ አለው፤ ፍቅር ለሌሎች የሚተርፍ ቸርነት አለው፤ ፍቅር በሰዎች ደስ ይሰኛል እንጂ አይቀናም፤ ፍቅር ዝቅ ብሎ የሚያከብር እንጂ ከፍ ብሎ የሚያዋርድ አይደለም።

      ወዳጆቼ እኛ ፍቅር የምንለው አለመተዋወቅን ነው። ይህ ማለት አንድን ሰው ያወቅነው መስሎን በጣም መልካም፣ ደግ፣ ጨዋ፣ ሩህሩህ ነው ብለን እንወደዋለን። ልክ አንድ የማንጠብቀውን ነገር ሲያደርግ ስናይ እንዲህ አይነት ሰው መሆኑን አላውቅም ነበር፣ እንዲህ አይነት መልኩን በፍፁም አላስተዋልኩም ብለን ስናውቀው እንጠላዋለን። ፍቅር ግን እንዲህ አይደለም። እውነተኛ ፍቅር የሚመጣው ስለ አንድ ሰው ጥንካሬና ድክመት በሚገባ ስናውቅ ነው።
እውነተኛ ፍቅር የያዘው ሰው እነዚህን ነገሮች
የሚያደርገው ጭፍን ስለሆነ ወይም ስለሚወደው ሰው ምንም ስለማያውቅ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ስለ ግለሰቡ ማንነት የተሟላ እውቀት ስላለው ነው።

      የፍቅር ሚዛኑ ካፍቴርያ ውስጥ መሳሳቅ መቻል አይደለም ትዕግስትን የሚፈታተኑ ድክመቶቹን ሳይሰለቹ በልበ ሰፊነት እያረቁ በትዕግስት መሸከም ሲቻል ነው። በቸገረው ሰዓት፣ እጁ ባዶ በሆነበት ሰዓት እኔን ላንተ እግዚአብሔር የሰጠኝ ባዶ በሆንክበት ጊዜ ድክመትህን ሸፍኜ መቆም እንድችል ነው ብሎ ቸርነትን ማድረግ ነው።

    ሀበሻ በሰው ማጣት ይደሰታል በሰው መሳካት ግን ይከፋል። ክርስቲያን ግን የሰውን ስኬት ሲመለከት ከልቡ የእውነት መደሰት መቻል አለበት። ከደስታው ባለፈ በቻለው መጠን ለስኬቱ አስተዋጽዖ ማድረግ ይኖርበታል። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ የልብ ወዳጅ ሳይሆን የጥርስ ብቻ ወዳጅ ስለሆንን እንስቃለን ልባችን ግን ጥላቻን ያመረቅዛል። ይህ ማንነታችን ብዙ አጠገባችን ያሉ ለብዙ ነገር መትረፍ የሚችል ራዕይ ተሸክመው ቁጭ ያሉ ሰዎችን በድካማቸው ገብቶ የሚረዳቸው የሚደግፋቸው ሰው ባለመኖሩ ከነራዕያቸው ያረጃሉ ያልፋሉ ።

     ወዳጆቼ አጠገባችሁ ያለውን የምታውቁትን፣ ወዳጄ የምትሉትን ሰው ራዕይህ ምንድነው? በቀጣይ ምን ለማድረግ አስበሃል? በአንተ ራዕይ ውስጥ የኔ ተሳትፎ ምን መሆን ይችላል? ብላችሁ ጠይቋቸው። የምትችሉትን ያህል ተዘርጉላቸው እናንተም እነርሱም ደስተኛ ትሆናላችሁ። እግዚአብሔር ፍቅርን ያብዛላችሁ።

                 በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

20 Sep, 03:57


      መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ እንዳለው መፅሀፍ ፦ ቀኑን ላንተ አደራ ሰጠን በብርሃን የማናየውን መሰናክል አሳለፍከን፤ ብዙ ጭንቅ ያለበትን ለሊቱን ላንተ አደራ ሰጠን ራሳችንን በማናውቅበት የእንቅልፍ ጊዜ እንኳን ነቅተህ ጠበከን፤ እንዴት እናልፈው ይሆን ያልነውን የምጥ ቀን ከጠላታችን ጋር ሳትወግን ጋሻ ሆነህ አሳለፍከን።

ዛሬ ያለንበት ከፍታ የእውቀታችን፣ የጥበባችን፣ የበጎነታችን ውጤት አይደለም ነፍሳችንን በመዳፍህ አሰማርተህልን፣ እስትንፋስህ ሳይቋረጥብን፣ አይኖችህ ሳይነቀሉብን፣ ያደከመንን ተራራ እጅህ ደልድሎልን፣ ያሰጋንን ሸለቆ ክንድህ ሞልቶልን ነው።

ህይወታችን ባንተ ላይ ጥያቄ የላትም፣ ነፍሣችን ባንተ ላይ እንቆቅልሽ የላትም አደራችንን በልተህ አታውቅም። እንኳን የሰጠንህን ይቅርና ሰይጣን የዋጠብንን አስተፍተህ ይዘህልናል።

እኔ እንጂ አንተስ ቃልህን አጥፈህ አታውቅም፣ እኔ እንጂ አንተስ ዋሽተህ አታውቅም፣ እኔ እንጂ አንተስ አደራ በልተህ አታውቅም። መልከመልካሙ ጌታ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክብር ለስምህ ይሁን!
                        
በአዶኒ
   
Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

18 Sep, 07:53


           ይቅር በለኝ

" ዕርቃኑን በነጠላ የሸፈነ አንድ ጎበዝ ይከተለው ነበር፥ጎበዛዝቱም ያዙት፤ እርሱ ግን ነጠላውን ትቶ ዕራቁቱን ሸሸ። የማርቆስ ወንጌል 14 : 52

     በደጉ ዘመን ከብቤህ ነበር አንዳች አልጎደለኝ፤ ከእጅህ እበላለው አልተራብኩም፣ በእጅህ እፈወሳለው አልታመምኩም፣ በእጅህ እደገፋለው አልወደቅሁም፣ አይኔ እልፈዘዘም መልክህን እያየሁ እደሰታለው፣ ጆሮዎቼ አልተራቡም ህይወት ባለው ቃልህ እረክተዋል፣ ፀጉሬን ስታሻሸኝ እናትና አባቴን ረስቼ ጉያህ ውስጥ እገባለው፣ እግሮቼን ስታጥበኝ እየኮረኮርክ ስታስቀኝ ፍቅርህን ስታሳያኝ ልቤን በደስታ ታዘልልብኝ ነበር፣ ቃልህን ስሰማ ስታቆላምጠኝ ነፍሴ ውስጤ ትፈስብኝ ነበር ።

አይ ሀሙስ ማታ! ይሄን ሁሉ ነበር አስባለችኝ። የደስታ ቀን እንጂ የክፉ ቀን ወዳጅ አልሆንኩም። ሁሉን ትተህ ተከተለኝ ስትለኝ ሁሉን ትቼ ተከተልኩ ዛሬ ቃልኪዳኔን አፍርሼ ሁሉን ትቼ እርቃኔን ሸሸውህ። መጠጊያዬ ብዬ ሳመሰግንህ ኖሬ ዛሬ ግን መጠለያ ዋርካዬ ፈረሰብኝ ብዬ ሌላ መጠለያ ፍለጋ ያገለደምኩትን ነጠላዬን ጥዬ ጠፋው። የኔ መውደድ እዚህ ድረስ ነው።

ዛሬም እኮ እዛው ላይ ነኝ። ጎበዛዝቱ ተከተሉኝ እንዴ ብዬ ስርቻ ስር ተወትፌ እያጮለኩ ነው። ላንተ ጀርባ ሰጥቼ አለምን ለማሳደድ ዛሬም ሩጫዬን አልገታሁም። ትቼው የመጣሁትን የአለምን ግሳንግስ ዛሬ እያግበሰበስኩ ነው። ካንተ እንደተለየሁ ተራቆትኩ የሰው ማሟሻ አዳም አንተን እንደተለየ መራቆቱን አወቀ እርቃኑን ሊሸፍን ቅጠል ቢሰፋም አልታደገውም ነፋስ ይገልብበታል እኔም ካንተ ተለይቼ እርቃኔን ነኝ በዝና አልሸፈን፣ በስልጣን አልከልለው፣ በሀብት አልጋርደው ሁሉም ይገጣል ገበናዬን ሸፋኝ አንተ ብቻ ነህ።

ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ አትዘንብኝ! አስተካክለኝ ተንሸራታች ነኝ፣ አፅናኝ ወላዋይ ነኝ፣ ልቤን ደግፈኝ ወደሞቀበት ነኝ፣ ፅኑ ፍቅር የለኝም በፍቅርህ ያዘኝ፣ እንደገና ስራኝ የምፈርስ ነኝ፣ ክህደቴን ክጄ ፀንቼ ልመንህ፣ ፍርሀቴን ክጄ አለቴን ልያዝህ እባክህን ሀሙስንም ቅዳሜንም አሻግረህ እሁድን አሳየኝ።

                  በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

18 Sep, 05:54


Channel photo updated

Adoni Gospel channel

16 Sep, 09:12


Channel photo updated

Adoni Gospel channel

13 Sep, 15:50


የእስራኤል ቅዱስ ተመስገን


ጨረቃዋን ከለሊቱ ድምቀት ላይ አንስተህ ቀኑን ከብሩህ ጠል ጋር የለገስከን ዘላለማዊ ጌታ እግዚአብሄር በሰጠኸን አንደበት እናመሰግንሀለን።

በመዓትህ ውስጥ ምህረት ፣በቁጣህ ውስጥ ትዕግስት ፣በቅጣትህ ውስጥ ፍቅር ፣በፍርድህ ውስጥ ይቅርታ ያለህ ጌታችን አምላካችን ሆይ እናመሰግንሀለን።

ሰዎች የሚዋጋ አምላክ ይፈልጋሉ፣ የሚገድል ጌታ ስላላቸው ይደሰታሉ። አንተ ግን ከአማልክት ልዩ ነህና የተወጋህልን ፣ የሞትክልን አምላካችን ስለሆንህ እናመሰግንሀለን።

ሰዓቱ የመሸ፣ ቀትሩ የደመነ፣ ወራቱ የጨለመ፣ ዓመቱ የከበደ ቢመስልም፣ ለምሽት ንጋት፣ ለደመና ፍካት ፣ ለጨለማ ብርሃን ለአስጨናቂው ቅለት በምትሰጥ ጌታችን እናምናለን።

          እኛን የሚመስሉ ብዙ ሰዎች አሉ። ድካማቸው ድካማችን ነው ፣ አንተን የሚመስል አምላክ የለምና ተመስገን። እኛን ለማየት ጨለማው አይከለክልህም፣ ደመናው አይጋርድህም፣ ምሽቱ አይጨልምብህም፣ ማንነታችን አያርቅህምና ድንቁ ጌታችን ዛሬም ተመስገን።

    በዘመናት የሸመገልክ ግን ያላረጀኸው ጌታ ክብር ላንተ ይሁን። አሜንን!!

    ቻናላችንን ይቀላቀሉ
                       
             በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

13 Sep, 07:03


   
“አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።”
  — መዝሙር 119፥11

     
       የሰው ልጅ አጠገቡ ያለውን ባልንጀራውን ብቻ ሳይሆን አምላኩ የሆነውንም እግዚአብሔርን የሚበድል ፍጡር ነው። ሁልጊዜም ቢሆን አኗኗራችንን ስንመለከት ራሳችንን አልያም ሰዎችን ለማስደሰት እንጂ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት አንኖርም። ኃጢአትም ስንሰራ ሰው አየኝ አላየኝ ብለን እንጂ እግዚአብሔር ያየኛል ብለን አንቆጠብም። ተኝተንም ተነስተንም በሃሳብም በተግባርም እግዚአብሔርን በድለናል።

        ታዲያ እግዚአብሔርን እንዳንበድል ምን እናድርግ? ስንል የመንፈስን ሰይፍ እንታጠቅ። ጌታችን ኢየሱስ በምድር ቆይታው የመንፈስ ሰይፍን ታጥቆ ነበር። ሰይጣን ሊፈትነው በቀረበ ሰዓት ኢየሱስ ስጋው ደክሞ ተርቧል፣ በውኃ ጥም ውስጡ ተቃጥሏል፣ ምቾት በማጣት ዝሏል። ዙሪያውን ደግሞ ሀብት፣ ምቾት የሚያገኝበት ተጽዕኖ የሚያሳድርበት የምርጫ ፈተና ነበር። ጌታ ኢየሱስ ግን ምንም ቢዝል ቢደክምም  መንፈሳዊ ትጥቁ የተሟላ ነበር። እያንዳንዱን ፈተና ከተፅፏል በማለት ድል ይነሳው ነበር።

       የእግዚአብሔር ቃል መቀመጫ ማህደሩ የሰው ልብ ነው። ቃሉ ምን እንደሚል ካላወቅን በመንገዳችን የሚመጡ ፈተናዎችን እንዴት ማለፍ እንደምንችል አናውቅም። ምክንያቱም ቃሉ የስህተትና የትክክል መለኪያ ሚዛኑ ነው። ንጉሱ ዳዊት ኃጢአትን ለማስወገድ የእግዚአብሔር ቃል በልቡ መካተት እንዳለበት ተረድቶ ቃሉን በልቡ መዝገብ ያስቀምጥ ነበር። ፈተና ሲመጣም ቃሉን መመከቻ አድርጎ ያሸንፋል።

         መንገድ ላይ እየተጓዝን ከፊታችን በኃይለኛ ንፋስ የተነሳ አቧራ ሲመጣ በቅጽበት አይናችንን እንሸፍናለን። ልክ እንዲሁ ሁሉ ቃሉ በልባችን ሲኖር አንድ ፈተና ሲገጥመን ያንን ፈተና የምናመልጥበትን ቃል ያቀብለናል። በልባችን የሰወርነው የእግዚአብሔር ቃል የፈተና ቀን መውጫ፣ የክፉ ቀን መሻገሪያ፣ የጠላትን ወጥመድ መዝለያ ነው። ሰይጣን ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ የሚወረወርበትን የትኛውንም ጦርና ጥይት አይፈራም። የእግዚአብሔር ቃል የተገለጠውንም የተሸሸገውንም የጠላት ፈተና ድል ይነሳል።

  
         የልባችን አምላክ በሰማይ የምትኖረው አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ማለዳ በፊትህ የሰራነውን በደልና ኃጢአት ሁሉ በስምህ ኃይል ደምስስልን። ይቅርም በለን። ያቃተንን የልምድ ኃጢአት አንተ በጣጥስልን። አዲሱን አመት ቃልህን በልባችን በመሰወር ያንተን የቃል ጉልበት ድል ነሺነትን እንድንለማመድ እርዳን። በምትወደው ልጅህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!

  በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

11 Sep, 06:33


🌻🌻🌻🌻እንኳን አደረሳችሁ🌻🌻🌻🌻

ፍቅርህ እንደ ወንዝ ፈስሶ ያጥለቀለቀን፣ ሰላምህ እንደ አየር በውስጣችንም በዙሪያችንም የከበበን አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ስለሰጠኸን ስለዚህ አዲስ አመት እናመሰግንሃለን።

     ወዳጆቼ እግዚአብሔር በርህራሄ በታማኝነት የተመላ የተባረከ አዲስ አመት ያድርግላችሁ።
የጌታ በረከት በእናንተ ላይ ይውረድ። በህይወት ጉዞ ጥንካሬን ተስፋ ማድረግን ይስጣችሁ። ልባችሁ በአንዳች ነገር እንዳይወድቅ ይጠብቅላችሁ። ጅማሬያችሁ ፍፃሜ ውጥናችሁ ከግብ የሚደርስበት የፍሬ ዘመን ያድርግላችሁ። በከንቱ ከመድከም በከንቱ ከመልፋት ይታደጋችሁ ማንም የላባችሁን ውጤት አይከልክላችሁ። ፈተናዎችን ድል የሚነሳ የእግዚአብሔር ኃይል ከእናንተ ጋር ይሁንላችሁ። በእግዚአብሔር ቃል ማደግ መሰራት ብሎም ማበብ ይሁንላችሁ። የሰሜን ኮከብ ተጓዦችን እንደሚመራ እንዲሁ እግዚአብሔር በቃሉ ይምራችሁ በመንፈሱ ያሰማራችሁ። ክፉ የማትሰሙበት የምስራችን የምታደምጡበት ዘመን ያድርግላችሁ። እግዚአብሔር ከፊቱ ጋር መጽናናትን መበርታትን ይስጣችሁ ፍቅሩ ልባችሁን ያሙቅ። በጌታ በኢየሱስ ስም ይሁንባችሁ።

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X

Adoni Gospel channel

07 Sep, 18:00


እግዚአብሔር ይመስገን ዘመን ተጨመረልን

    “በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።” — መዝሙር 65፥11

        ወዳጆቼ ያገባደድነው ዓመት ለእናንተ እንዴት ነበር? በመልካም በደስታ የምታስታውሱት ይሆን? ወይስ አመቱን መለስ ብላችሁ ስታስቡት ሃዘን ይወራችሁ ይሆን?

     እኔ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን እንጂ አዲስ ዓመት ማየቴ የማይታሰብ ነበር። በሞትና በእኔ አንድ እርምጃ ቀርቶ እንዳለ ዳዊት በህይወቴና በሞት መሀል አንድ እርምጃ ቀርቶኝ እግዚአብሔር የታደገኝ አመት ነው። በሰፌድ ላይ ያለች ስንዴ ተበጥራ ገለባዋ እንደሚለይ እግዚአብሔር የእኔን መከራ እንደ ሰፌድ ተጠቅሞ እውነተኛ ወዳጅና ገለባ ወዳጄን አበጥሮ የለየልኝ አመት ነው። መስዋዕትነት የሚከፍል ወዳጅነትን ያየሁበት አመት ነው። እግዚአብሔር ይመስገን!

     በዚህ ዓመት በብዙ ሰው ህይወት ውስጥ ብዙ ውጥኖች ፈርሰዋል፣ ብዙ እቅዶች መክነዋል፣ ብዙ የመኖር ተስፋዎች ጨልመዋል፣ ብዙ ደስታዎች በሀዘን ተውጠዋል፣ ብዙዎችን በነበር ቀርተዋል። እኔና እናንተ ከማንም የተለየን ስለሆንን ዛሬን ለማየት አልበቃንም፣ ከማንም በላይ ጥንቃቄያችን ረድቶን እዚህ አላደረሰንም፣ እውቀታችን ክፉውን ቀን አላሻገረንም። እንዲያው ምህረቱ በዝቶልን ከእርሱ የሆነ መልካምነት ስላልጎደለብን፣ የመጨረሻ እድል የሌለው የዘላለም ተሸካሚያችን ኑሩ ብሎን ነው።

        እቅዳችን ገዳይ ነበር ጣልቃ ገባልን እንጂ፣  የጨበጥነው አጥፊ ነበር ጌታ አመከነልን እንጂ፣ የረገጥነው ተንሸራታች ነበር ጌታ አጸናን እንጂ፣ የሳመን የሚሸጠን ነበር ጌታ አስጣለን እንጂ! ከብዙ ክፉዎች አስጣለን፣ ብዙዎችንም ከእኛ ከአመጸኞቹ አስጣላቸው።

     ስለዚህ እግዚአብሔር ብል ያልበላው አዲስ የምስጋና አመትን ጨምሮልናል። እናመሰግነዋለን!!

          አንደበታችን ስምህን ይቀኛል ስናምንህ አንደበታችንን ዳብሰኸዋልና ላንተ ብቻ ቅኔን እናቀርባለን ላንተ ብቻ ጉልበታችን ይንበረከካል ላንተ ብቻ ልባችን ዙፋን ይሆናል ክብር ለአንተ ይሁን። ባሳለፍነው አመት ስላደረክልን መልካም ነገር ሁሉ ተመስገን። ደግ አባት ስለሆንከን ተመስገን። በዘላለም ፍቅር ስለወደድከን ተመስገን። በጤና ስለጠበከን ተመስገን። አጥፊው ስላላጠፋን ገዳዩ ስላልገደለን አንተ ጣልቃ ስለገባህልን ከክፉ ሁሉ ተናጥቀህ ያንተ ስላረከን ተመስገን። ብዙዎች በሚሞቱበት በዚህ ዘመን ኑሩ ብለህ ህይወት ስለሰጠኸን ዘመን ስለጨመርክልን ተመስገን። እንወድሀለን እናከብርሃለን። ዘመንን እንደሰጠኸን ዘመናችንን ሁሉ ለአንተ ተገዝተን መኖር እንድንችል ጸጋህን አድለን አቅም ጉልበት ሁነን። በልጅህ በወዳጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን!!

በአዶኒ

Telegram👉 t.me/adonigospel

   Whatsapp👉 https://chat.whatsapp.com/BnTcBA0mML6E7gakQUIJ8X