Abu hatim Abduselam Assalefiy @abuhatimaselefiy Channel on Telegram

Abu hatim Abduselam Assalefiy

@abuhatimaselefiy


ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች ንግግር የሚሰራጭበት ቻናል ነው።

Abu hatim Abduselam Assalefiy (English)

Abu hatim Abduselam Assalefiy is a Telegram channel that provides valuable insights and teachings on Islamic faith and practices. Led by the knowledgeable and respected individual, Abu hatim Abduselam Assalefiy, this channel is a great resource for those looking to deepen their understanding of Islam. With a focus on promoting peace, love, and unity through the teachings of the Quran and the Prophet Muhammad, this channel offers daily reminders, lectures, and discussions on various topics related to Islam. Whether you are a seasoned Muslim seeking further knowledge or someone new to the faith wanting to learn more, Abu hatim Abduselam Assalefiy is the perfect channel for you. Join the community today and embark on a journey of spiritual growth and enlightenment.

Abu hatim Abduselam Assalefiy

20 Nov, 07:12


ኒቃቢስት ከሆነች ተሸነፍላት
👌👌👌👌

ከሸይኽ አብዱልሃሚድ ጋር ፈገግ ይበሉ!ከፈገግታው ጀርባ ግን ታላቅ ቁም ነገር ትማሩበታላችሁ አስተውሉ!❵

~> ሶስቱንም ጥይት አስተኮሰችው! አሉ ሸይኽ

➧ አንድ ሰው ነበር አላህ ሶስት ዱዓወችን ሊቀበለው ወስኖለታል። ሚስቱ ቆንጆ እንዲሆን ዱዓ አድርግልኝ አለችው [ሴቶችኮ የቁንጅናቸው ነገር...]
➧ እሱም ሴት የላከው ሞት ❨ጅብ❩ አይፈራም ነውና ዱዓ አደረገላት ከዛም ከበኒ ኢስራል ሴቶች ሁሉ ቆንጆ ሆነች! ግን ናቀችው ❮ጉድኮ ነው❯
➧ በድርጊቷ ተናዶ እንዲህ አለ «ጌታዬ ሆይ የምትጮህ ውሻ አድርጋት» አለ ሆነችም።

➧ ልጆቹ የውሻ ልጅ እንባላለን ሲሉት ወደነበረችበት እንዲመልሳት ዱዓ አደረገና ተመለሰች

↪️ ሶስቱንም ዱዓዎቹን አጠናቀቀ!!!

👌 ቁም ነገሩ ለሴቶች ቁንጅና አትንበረከክም ለእምነቷ መስተካከል ትኩረት አድርግ። ያቺን አደበኛ የጌታዋን ትዕዛዝ አክባሪ ሌሎች በተገላለጡበት መገላለጡንም ስልጣኔ ብለው በሰየሙት ዘመን በኒቃብ ለተዋበችው እንቁ ትኩረት ስጥ!!!

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy
https://t.me/AbuImranAselefy

Abu hatim Abduselam Assalefiy

20 Nov, 06:17


📌 ታላቅ የኮርስና የዳዕ ፕሮግራም በስልጢ ወረዳ ለአሳኖ ቀበሌ እና አከባቢዋ ሰለፊዮች በሙሉ
       🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴

       የፊታችን ዓርብ ጥቅምት 8/ 2/2017 ከአስር ሰላት ጀምሮ እስከ ቅዳሜ 10:00 ሰዐት ድረስ በስልጢ ወረዳ በአሳኖ ቀበሌ በፈትሕ መስጅድ ላይ ታላቅ የዳዕዋና ኮርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል።

            
ተጋባዥ ዱዓቶች

1– ታላቁ ሸይኽ አብዱል ሐሚድ ኢብን ያሲን አስ–ሰለፊይ ሐፊዘሁሏህ

2— ኡስታዝ ኑራዲስ ስራጅ ( አቡልበያን) ከቡታጅራ

3 – ኡስታዝ ስራጅ ከወራቤ

4 – ኡስታዝ ዘይኑ ከመነከሪያ

👌 በዚህ ፕሮግራም ላይ ጠቅላላ ሙስሊም ማህበረሰብ የተጋበዘ ሲሆን በተለይም ደግሞ አጎራባች ቀበሌዎች፣ አልከሶ ሰለፊያ ጀመዓ፣መነከሪያ ከተና፣ ወራቤ ጀመዓ፣ ገርቢበር ጀመዓ፣ ቡተጅራ ጀመዓ፣ ስልጢ ቅበትን ጨምሮ ሌሎች በዙርያ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰቦች ተጋብዛቹሀል።

ልብ በሉ የኮርስ ኪታብ በቦታው ስለተዘጋኛ እዛው ስለምተወስዱና በተጨማሪም ምግብ እና ማደሪያ በጀመዓው በኩል የተዘገጀ ስለሆነ እናንተው ለወገኖቻቹው በማሰማት በደዕዋው ለመጠቀምና ግልፅ ያልሆኑለቹሁን ጉዳዩች ፈትዋዎችን በመጠየቅ መረዳት ትችለለችሁ።

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘገጅቷል።

አድረሻ:— ከቡተጅራ ወደ ወራቤ በሚወስደው ጥቁር አስፐልት አጠገብ አሳኖ ቀበሌ በተለምዶ አስፓልት ዳር ከቲቲ ጎራ ት/ቤት ከፍ ብሎ አጠገብ 5 ሜትር ገባ ብለችሁ መስጅዱ ነው።

📞ለመደወል📞
ኡስታዝ አብዱረዛቅ  0954047289
አቡ አብዱል ወዱድ
0921892212

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናለችንን ጆይን ይበሉ:—
https://t.me/TawheedandSunnahPromoter/2344

Abu hatim Abduselam Assalefiy

17 Nov, 17:11


Live stream finished (1 hour)

Abu hatim Abduselam Assalefiy

17 Nov, 15:41


Live stream started

Abu hatim Abduselam Assalefiy

17 Nov, 15:40


ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ
ገባ
       ገባ
                በሉ
https://t.me/abuhatimaselefiy

Abu hatim Abduselam Assalefiy

16 Nov, 18:46


👉 ለሞተ ሰው ሶደቃ ማድረግ

ለሞተ ሰው ሶደቃ ማድረግ የሚቻል ለመሆኑ በሙስሊሞች መካከል ኺላፍ የለም ። በተቃራኒው ደግሞ የሟች ቤተሰብ የሞተባቸው ቀን ሙስሊሞች ሰርተው ሊያበሉዋቸው ነው ሸሪዓችን ያዘዘው ። እንደዚሁ ሶስተኛ ቀን ፣ ሰባተኛ ቀን ፣ አርባኛ ቀን ብሎ ማረድ የተከለከለ ነው ። ወደ ሞተ ሰው ለመቃረብ ብሎ ማረድ ወይም ቀብር ጋር ወስዶ ማረድም አይፈቀድም ። እነዚህ ተግባራት በቀጥታ ሽርክ አሊያም ወደ ሽርክ መዳረሻ ይሆናሉ ። ከዚህ ውጪ በማንኛውም ቀን የሞተውን ሰው አላህ እንዲምረው ነይቶ አርዶ ቢያበላ ለሟቹም ሆነ ለሶደቃ አድራጊው የሚጠቅም ለመሆኑ ዑለሞች ያረጋገጡት ነው ። ይህን አስመልክቶ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ : –

سؤال : إن أنا تصدقت عن والدي، فهل يصيبني نفس الأجر، حيث أن والدي متوفى، وأرجو بيان الأوجه التي يمكن الإنفاق فيها عن الميت، وهل الدعاء أفضل من هذا كله

الجواب :

الصدقة عن الميت مشروعة ومفيدة ونافعة للميت، وقد ثبت في الصحيحين عن النبي ﷺ أنه سئل عن ذلك قال له رجل: «يا رسول الله! إن أمي ماتت أفلها أجر إن تصدقت عنها، قال: نعم فالصدقة تنفع الميت، ويرجى للمتصدق مثل الأجر الذي يحصل للميت؛ لأنه محسن متبرع، فيرجى له مثل ما بذل، كما قال عليه الصلاة والسلام: من دل على خير فله مثل أجر فاعله.
فالمؤمن إذا دعا إلى خير، أو فعل خيرًا في غيره يرجى له مثل أجره، فإذا تصدق عن أبيه، أو عن أمه، أو ما أشبه ذلك، فللمتصدق عنه أجر وللباذل أجر، وهكذا إذا حج عن أبيه أو عن أمه فله أجر ولأبيه وأمه أجر، ويرجى أن يكون مثلهم أو أكثر؛ لفعله الطيب وصلته الرحم وبره لوالديه، وهكذا أمثال ذلك فضل الله واسع.
وقاعدة الشرع في مثل هذا أن المحسن إلى غيره له أجر عظيم، وأنه إذا فعل معروفًا عن غيره يرجى له مثل الأجر الذي يحصل لمن فعل له ذلك المعروف، وقد قال عليه الصلاة والسلام: إذا مات ابن آدم انقطع عمله إلا من ثلاث: صدقة جارية، أو علم ينتفع به، أو ولد صالح يدعو له.
فأنت -يا عبد الله- في صدقتك عن والديك، وفي إحسانك إلى عباد الله بما تفعله من المعروف لك فيه أجر عظيم، ولمن أحسنت إليهم بأن علمتهم وقبلوا منك، وأرشدتهم وقبلوا منك، ودللتهم على الخير وقبلوا منك لهم أجر أيضًا ولك مثلهم. نعم.

نور على الدرب

በኡለሞች መካከል ኺላፍ ያለው አንድ ሰው ለሞተ ሰው ሶደቃ አድርጎ ሰዋቡን ለእገሌ ይሁን ማለት ይችላል ወይስ አይችልም በሚለው ነው ። ነገር ግን ጁሙሁሮቹ ዑለሞች እንደ ሐንበሊዮች ፣ ሐነፊዮች ፣ ማሊኪዮችና ከፊል ሻፊዒዮች ይቻላል ይላሉ ። ቀጥለን የተወሰኑትን የዑለሞች ንግግር እናያለን : –
 
قال الإمام أحمد :
" الميت يصل إليه كل شيء من الخير للنصوص الواردة فيه، ولأن المسلمين يجتمعون في كل مصر، ويقرءون، ويهدون لموتاهم من غير نكير، فكان إجماعاً، وكالدعاء والاستغفار".
المبدع في شرح المقنع (2/281)

وقال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله تعالى – : 
" وقد صح عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه أمر بالصدقة على الميت، وأمر أن يصام عنه الصوم، فالصدقة عن الموتى من الأعمال الصالحة، وكذلك ما جاءت به السنة في الصوم عنهم، وبهذا وغيره احتج من قال من العلماء،………… " انتهى من الفتاوى

وقال ابن قدامة رحمه الله :
" وَأَيُّ قُرْبَةٍ فَعَلَهَا , وَجَعَلَ ثَوَابَهَا لِلْمَيِّتِ الْمُسْلِمِ , نَفَعَهُ ذَلِكَ , إنْ شَاءَ اللَّهُ " انتهى
من المغني (2/226) .

ሰዋቡን ለእገሌ ማለት አይቻልም የሚሉ ዑለሞች ያሉ ሲሆን ከመረጃ አንፃር ተመዛኝ ነው ። ሀገራችን ላይ በተለይ በሰሜኑ ክፍል ሰው ሲሞት በሶደቃ ስም ከሽርክና ቢዳዓ ጋር የተገናኘ ተግባር በብዛት የሚፈፀም ሲሆን በሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች ከዚህ ጋር በተገናኘ ሙኻለፋዎች አሉ ። ይሁን እንጂ እነዚህን ሙኻለፋዎች ለይቶ ማውገዝና ማስተማር ሲገባ በጥቅሉ ለሞተ ሰው ሶደቃ የለም የሚሉ እንደውም የሱና ኡስታዞች ከሚባሉትም ጭምር መኖራቸውን እየሰማን ነው ። ከዚህም አልፎ ከላይ ከተጠቀሱት ሙኻለፋዎች በፀዳ መልኩ አርዶ በማብላት ሶደቃ ያደረገን ሰው ከሱና እስከማስወጣት ይደርሳሉ እየተባለ ነው ። ለእነዚህና ለሌሎችም ወንድሞች ይጠቅም ዘንድ የዑለሞችን ንግግር መሰረት ባደረገ መልኩ ይህችን ማስታወሻ ጀባ ብያለሁ አላህ የምትጠቅም ያድርጋት ።

https://t.me/bahruteka

Abu hatim Abduselam Assalefiy

16 Nov, 17:06


Live stream finished (1 hour)

Abu hatim Abduselam Assalefiy

16 Nov, 15:47


Live stream started

Abu hatim Abduselam Assalefiy

16 Nov, 15:45


ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ
ገባ
       ገባ
                በሉ
https://t.me/abuhatimaselefiy

Abu hatim Abduselam Assalefiy

16 Nov, 12:09


🔷 የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው

ክፍል ሰባት

ዳዕዋ ኢለላህ

የተብሊግ ጀማዓ አጠቃላይ እንቅስ ቃሴያቸውን በህይት አንድ ጊዜ አራት ወር ፣ በአመት አርባ ቀን ፣ በወር ሶስት ቀንና በአካባቢ መቃሚና ኢንቲቃሊይ ፣ እንዲሁም በአካባቢ መስጂድ ላይ ተዕሊም በሳምንት ጀውላ በሚል ይከፋፍላሉታል ።
በቁጥር ስድስት ላይ እንዳየነው አንድን ሰው አሳምነው ይዘውት ለሶስት ቀን ካወጡት በኋላ ሰው ፊት ቆመህ አስተምር አላህ ያናግርሀል ይሉታል ። ከላይ ያየናቸው በህይወት ፣ በአመትና በወር የሚሉ ክፍልፍሎች ምንም መረጃ የሌላቸው ሲሆን የዳዕዋ መሻኢኾት ተርቲብ ነው ይላሉ ።
በወር ለሶስት ቀን ሲወጡ በየምደባቸው ከአሚራቸው ጋር ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የ24 ሰአት የስራ ምደባ ያደርጋሉ ። በዚህ ምደባ ኻዲም ይመደባል ፣ ኢዕላን የሚያደርግ ይመደባል ፣ ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በያን ( ሙሓደራ ) የሚያደርግ በመመደብ ይከፋፈላል ። ዐስር ሶላት ላይ ከጀማዐው አንዱ ተነስቶ " ዛሬ በአዱንያ ነገ በአኼራ ፈላሕና ነጃ የምንወጣው የአላህን ትእዛዝ በነብዩ መንገድ በመፈፀም ነው " ይህን በተመለከተ ከሶላት በኋላ በያን ተደርጎልን ጀውላ እናደርጋለን እኛ ሙሀጂሮች እናንተ አንሷሮች ሆነን በጋራ እንሰራለን ለአካባቢው እውሮች ስለሆንን የማይሰግዱና የታመሙ ሰዎች ቤትና እንዲሁም የአዛውንትና ዑለሞች ቤት የሚያዘይረን እንፈልጋለን ይላል ። ከሶላት በኋላ ለጀውላ ( አጃባቢ ላይ ለመዞር) ሰው ይመደባል ።
ጀማዓው በሶስት ወይም በአራት ተከፍሎ አሚር ፣ ደሊል ( ቤት የሚያሳይ)ና ሙተከሊም ( ተናጋሪ ) ተብሎ ይሄዳል ። ለዚህ ለወጣው ጀማዓ ኢስቲጝፋርና ዱዓእ የሚያደርግ አንድ ሰው ተመድቦ መስጂድ እንዲቀመጥ ይደረጋል ። ይህ የተቀመጠው ሰው ለወጣው ጀማዓ እንደ ዲናሞ ( አንቀሳቃሽ ) ነው የሚል እምነት አለ ። በዚህ ሰውና በወጣው ጀማዓ መካከል ተዋሱል ( በውስጥ መገናኘት) አለ ይላሉ ። የወጣው ጀማዓ የሆነ ችግር ከገጠመው ሞተሩ ጠፍቷል ፣ እንቅልፍ ወስዶታል ፣ ወይም ወሬ እያወራ ነው ሶኬቱ ተነቅሏል ብለው ያምናሉ ።
የዚህ አይነቱ እምነት ዐቂዳን የሚነካ ከባድ ሽርክ ነው ። ከዚህም ውጪ በቀዳእና ቀደር እምነት ላይ አደጋ ነው ። ማንኛውም ነገር የሚሆነው በአላህ ውሳኔ ሲሆን የእገሌ መተኛት ወይም ወሬ ማውራት ውጤት ከዚህ ጋር ግንኙነት የለውም ። በውስጥ መገናኘት የሚባል እምነት የሱፍዮች ሲሆን ከእስልምና አስተምሮ የራቀ ነው ።
ተመድቦ የወጣው ጀማዓ በሄደበት ቦታ ምንም አይነት ሙንከር ቢያይ ኢንካር ማድረግ አይችልም ። ለምሳሌ ወንድና ሴት አንድ ላይ ቁጭ ብለው ሙዚቃ ከፍተው ጫት ሲቅሙ ቢያዩ ይሄ ተግባር ክልክል ነው አይሉም ምክንያቱ ደግሞ በዳዕዋ አዳብ አይፈቀድም የሚል ነው ። ይህን ሙንከር እያዩ ዛሬ በአዱንያ ነገ በአኼራ ፈላሕና ነጃ የምንወጣው ብለው ይህን በተመለከተ ከመጝሪብ በኋላ በያን ስላለ ብትመጡ ምን ይመስላችኋል ይላሉ ። ቶሎ በሄዱልን የሚሉት ጎረምሶች ኢን ሻ አላህ ብለው በመጮ ቶሎ ሂዱልን ብቻ የሚል መልእክት ያስተላልፋሉ ። ይህ ደግሞ የእስልምናን ትልቅ መርህ የሚጥስ ነው ። አላህ በተከበረው ቃሉ ስለ ነብዩ ኡማህ ምርጥነትና ምርጥ ያደረገው ምን እንደሆነ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎ ነግሮናል :–

« كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ ۗ وَلَوْ آمَنَ أَهْلُ الْكِتَابِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُم ۚ مِّنْهُمُ الْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ الْفَاسِقُونَ »
آل عمران
" ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ኾናችሁ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ ፤ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ ፤ በአላህም (አንድነት) ታምናላችሁ ፡፡ የመጽሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በኾነ ነበር ፡፡ ከነርሱ አማኞች አሉ ፡፡ አብዛኞቻቸው ግን አመጸኞች ናቸው "፡፡

የተብሊግ ጀማዓዎች ይህንና መሰል አንቀፆች ቦታ አይሰጡዋቸውም ። ከዚህ ይልቅ መሻኢኽ የሚሏቸው የሚናገሩትን ነው ቦታ ሰጥተው ስራ ላይ የሚያውሉት ። ከመጝሪብ እስከ ዒሻእ በሚደረገው ሙሓደራ አላህ ያናግርሀል የተባለው ስው ፊት ቆሞ ላብ በላብ ሆኖ ፀጉሩን እያከከ ምንም አላውቅም የአሚር ትእዛዝ ሆኖብኝ ነው የተነሳሁት ሲል ጀማዓው አላህ እንዲያናግረው ሁሉም አይኑን ጨፍኖ አስተጝፊሩላህ ይላል ።
ምናልባት የተመደበው ሰው የሶሓባ ባህሪይ የሚሏቸውን ስድስቱ ነጥቦች የሸመደደ ከሆነ የነጥቦቹን ቱሩፋቶች እየዘረዘረ ስድስተኛው ላይ ሲደርስ የቻለውን ሁሉ ብሎ ለዳዕዋ እንዲነይቱ ያደርጋል ። በፈላ ውሃ የገባው በሚቀጥለው ዙር ህዝብ ፊት ቆመህ ተናገር ሊባል ይችላል ።
ይህ የተብሊግ ጀማዓ የዳዕዋ ነጥብ ያየንበት ሲሆን 20 አዳብ የሚባሉትን ጀማዓው እንዳጠቃላይ የሚመራበት መርህ አላህ ካለ በሚቀጥለው የምናየው ይሆናል ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

ያለፉትን ክፍሎች ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5550

https://t.me/bahruteka

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 19:21


 አስሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

አዲስ ኦንላይን (የቀጥታ ስርጭት)የቂርኣት ፕሮግራም ለሴቶች ብቻ ከአልኢስላሕ መድረሳ

እነሆ አልኢስላሕ መድረሳ በተለያዩ ቦታዎች ከሀገር ውስጥም ከውጭም የሚገኙና በአካል ደርስ መከታተል ለማይችሉ እህቶች በቴሌግራም የቀጥታ ስርጭት (ኦንላይን) ደርስ አዘጋጅቶ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም በቀጥታ ስርጭቱ ደርስ ተሳትፋችሁ መማር የምትችሉ እህቶች መድረሳው በሚያስቀምጠው መስፈርት ተመዝግባችሁ መማር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

አጠቃላይ የኪታብ ማስተማሪያ ግሩፑ ከታች ያለው ሲሆን የእያንዳንዱ ሙስተዋ ተማሪ የራሱ ግሩፕ ይኖረዋል።

https://t.me/alislaahwomenonlineders

ማስታወሻ:-

1) ይህ የቂርኣት ፕሮግራም በአልኢስላሕ መድረሳ አስተባባሪነት የመድረሳውን ትምህርቶች በአካል መከታተል ለማይችሉ እህቶች የተዘጋጀ ነው።

2) በዚህ ቂርኣት ፕሮግራም የሚሳተፉት ሴቶች ብቻ ናቸው።

3) በዚህ ፕሮግራም ኦንላይን የሚሰጡ ቂርአቶችን ከሚማሩ ተማሪዎች ምንም አይነት ክፍያ መድረሳው አይጠይቅም። አይሰበስብም።

4) ማንኛዋም ተማሪ መድረሳው በሚሰጠው ትምህርት ላይ ለመሳተፍ መመዝገብ ግዴታ ነው። ያልተመዘገበ ተማሪ አይማርም።

5) ማንኛውዋም ተማሪ የምትማረው ያለችበት የቂርኣት ደረጃ (ሙስተዋ) ተለይቶ ስለሆነ ትክክለኛ ያለችበትን ሙስተዋ ለመለየት እንዲያግዝ ስለራሷ የቂርኣት ደረጃ ትክክለኛ መረጃ መስጠት አለባት።

6) በጠቅላላ ሁሉንም ሙስተዋ የሚመለከቱ የኪታብ ደርሶች የሚሰጡት በወንድ ኡስታዞች ይሆናል።

7) የቁርኣን፣ የተጅዊድና ከዚህ ጋር ተያያዥ የሆኑ ቂርአቶች የሚሰጡት በሴት አሳቲዛዎች ብቻ ይሆናል።

8) ተማሪዎች በየጊዜው የሚሰጠውን የሙከራ ፈተና በስርዓት መፈተን ይኖርባቸዋል።

ለመመዝገብና ለመማር የምትፈልግ ማንኛዋም ተማሪ ከታች ያለውን ፎርም በትክክል በመሙላት መላክ ይኖርባታል።
👇👇👇

https://docs.google.com/forms/d/1PJwh0gz-gENe7JABvDeXlYjx3r0YvBc3979-OnoN-eI/edit?usp=drivesdk

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 19:21


🔷 የተብሊግ ጀማዓዎች ማን ናቸው

ክፍል ስድስት

ዳዕዋ ኢለላህ

የተብሊግ ጀማዓዎች ትልቁ ትኩረታቸው ኹሩጅ ፊ ሰቢሊላህ የሚል ነው ። እንደሚታወቀው እነዚህ ጀማዓዎች የዳዕዋቸው ዋናው ነጥብ ፈዳኢልን ( ቱሩፋትን ) ማሳወቅ ነው ። ዳዕዋቸው ትኩረቱ ፈዳኢል ላይ ያተኩራል ። ይህ ማለት ደግሞ አላህ የሰው ልጆችን ከኩፍርና ሽርክ ጨለማ ለማውጣት 124 ሺህ ነብያት የላከበትን መርህ ይቃረናል ። ምክንያቱም አላህ ነብያቶች የላከው ለህዝቦቻቸው አልህን ብቻ እንዲያመልኩና ጣኦታትን እንዲርቁ እንዲያስተምሩ ስለሆነ ነው ። ይህን አስመልክቶ ቁጥር ስፍር የሌለው የቁርኣን አንቀፆች መጥቷል ። ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን እንይ : –

« وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلَالَةُ ۚ فَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ »
النحل ( 36 )
" በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል ፡፡ ከእነሱም ውስጥ አላህ ያቀናው ሰው አልለ ፡፡ ከእነሱም ውስጥ በእርሱ ላይ ጥመት የተረጋገጠበት ሰው አልለ፡፡ በምድርም ላይ ኺዱ ፤ የአስተባባዮችም መጨረሻ እንዴት እንደ ነበረ ተመልከቱ "፡፡

« لَقَدْ أَرْسَلْنَا نُوحًا إِلَىٰ قَوْمِهِ فَقَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ »
الأعراف ( 59 )
ኑሕን ወደ ወገኖቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ አላቸውም፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ለእናንተ ከርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁ፡፡»

« وَإِلَىٰ مَدْيَنَ أَخَاهُمْ شُعَيْبًا ۗ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ قَدْ جَاءَتْكُم بَيِّنَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ ۖ فَأَوْفُوا الْكَيْلَ وَالْمِيزَانَ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَاحِهَا ۚ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ »
الأعراف ( 85 )
" ወደ መድየንም (ምድያን) ወንድማቸውን ሹዓይብን (ላክን)፤ አላቸው ፡- «ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ በቀር ምንም አምላክ የላችሁም ፡፡ ከጌታችሁ ዘንድ ግልጽ ማስረጃ በእርግጥ መጥታላችኋለች ፡፡ ስፍርንና ሚዛንን ሙሉ፡፡ ሰዎችንም አንዳቾቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) አታጉድሉባቸው ፡፡ በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ ፡፡ ይህ ምእምናን እንደኾናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው ፡፡»

« وَإِلَىٰ ثَمُودَ أَخَاهُمْ صَالِحًا ۚ قَالَ يَا قَوْمِ اعْبُدُوا اللَّهَ مَا لَكُم مِّنْ إِلَٰهٍ غَيْرُهُ ۖ هُوَ أَنشَأَكُم مِّنَ الْأَرْضِ وَاسْتَعْمَرَكُمْ فِيهَا فَاسْتَغْفِرُوهُ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي قَرِيبٌ مُّجِيبٌ »
هود ( 61 )
" ወደ ሰሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን (ላክን) ፡፡ «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ አምላክ የላችሁም፡፡ እርሱ ከምድር ፈጠራችሁ ፡፡ በውስጧ እንድታለሟትም አደረጋችሁ ፡፡ ምሕረቱንም ለምኑት፡፡ ከዚህም ወደእርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ ቅርብ (ለለመነው) ተቀባይ ነውና» አላቸው " ፡፡

እነዚህ ከብዙ ነብያቶች ለምን እንደተላኩ ከሚገልፁ አንቀፆች ጥቂቶቹ ናቸው ። ነብያቶች ስራቸው ዳዕዋ ነበር ስለዚ ዳዕዋ አደርጋለሁ የሚል አካል ዳዕዋው ነብያቶች ያደረጉት ዳዕዋ መሆን ይነርበታል ። ወደ ተውሒድ መጣራትና ከሽርክ ማስጠንቀቅ ። የተብሊግ ጀማዓዎች ግን በተቃራኒው ወደ ተውሒድ የሚጣሩትን ጠላት አድርገው ሰው እንዳይሰማቸው ያስጠነቅቃሉ ። ወሀብይ እያሉ ያጠለሻሉ ። ዳዕዋ ብለው ይወጡና መሻኢኾች ያስቀመጡት አዳብ ብለው በስድስቱ የሶሓባ ባህሪይ በሚሉዋቸው ነጥቦች ብቻ ሙሓደራ ያደርጋሉ ።
አብዛኞቹ ዳዕዋ ብለው የሚወጡ ሰዎች ከተለያየ ቦታ የሚሰበሰቡ ስለሆኑ ስለእስልምና እንኳን በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ናቸው ። እነዚህ ሰዎችን አሳምነው እንዲወጡ ያደርጉዋቸውና ተመድበው የሆነ መስጂድ ይሄዳሉ ። እዛ ከደረሱ በኋላ አሚር ተብሎ በተመደበው ሰው አማካይነት የስራ ክፍፍል ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ የወጣውን ሰው ዛሬ በያን ( ሙሓደራ) አንተ ታደርጋለህ ይባላል ። ሰውየው ላብ በላብ ሆኖ እኔ ምንም አላውቅም እንዴት ሰው ፊት እቆማለሁ ሲል አብሽር አላህ ያናግርሃል መርሀባ በል የአሚር ትእዛዝ ነው ይባላል ።

አላህ ካለ ይቀጥላል ።

ክፍል አንድን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5508

ክፍል ሁለትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5510

ክፍል ሶስትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5519

ክፍል አራትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5530

ክፍል አምስትን ለማግኘት

https://t.me/bahruteka/5537

https://t.me/bahruteka

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 19:21


🟢በአንድ ድንጋይ ሁለት ሂዝቢይ

ከላይ ያለውን ድምፅ ሙመይዑ ኢብኑ ሙነወር
"ሐጃዊራ እና ሸይኽ ረቢዕ" ብሎ በለቀቀበት፡
እነ አብራር ሸይኽ ረቢዕን አስመልክቶ  ያንፀባረቁትን ሂዝቢያ ሲኮንን እንዲህ ብሎ  ነበር:"በአሁኑ ሰዓት የሐጁሪ ጭፍራዎች አጥብቀው ከሚኮንኗቸው ዑለማዎች ውስጥ ሸይኽ ረቢዕ አንዱ ናቸው። የውግዘታቸው ቀዳሚ ምክንያት ሸይኽ ረቢዕ የሕያ አልሐጁሪን ክፉኛ ማብጠልጠላቸው ነው። ይሁን እንጂ ለጀምዒያ ጉዳይ ሲሆን የኚህን ክፉኛ የሚያብጠለጥሏቸውን ሸይኽ ንግግር ከነ ኢብኑ ባዝ፣ ከነ ኢብኑ ዑሠይሚን እና መሰል ብዙሃን ዑለማኦች አቋም በተለየ ያስጮሃሉ። ለምን? የሳቸው ንግግር ለተብዲዕ ጥማታቸው ግብአት ይሆነናል ብለው ስለሚያስቡ። ደግሞኮ ንግግራቸውን በልኩ በተጠቀሙ። ..."

በአሁኑ ሰዓት ጠማማዎቹ ሙመይዓዎች ሸይኽ ረቢዕን እና መሰል የጀርህ ወተዕዲል ዑለሞችን የሚያጣጥሉበት ሚስጥር የመሪዎቻቸውን ጥመት አበጥረው በመረጃ ስላጋለጡ የተሀዙቡ ተቆርቋሪነት ይዟቸው ነው። እነ ኢሊያስና  ኢብኑ ሙነወር ራሱ፣መሰሎቻቸውም በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚተፋት ይሀው ለሙብተዲኦች  ያላቸውን ጥብቅና ነው። አቅምና አቋም ያለው ሸይኹ የለመረጃ የተቹትን ሰው በፍትህ ያምጣ።አልቻሉም አይችሉም።
ሚዛናዊ መሳይ የሙብተዲዕ ጠበቆች ሙግት ግን  ከንቱ ተሀዙብ መሆኑ ከተጋለጠ ውሎ አድሯል።
በዘመናችን ለሰለፊየህ ዘብ የቆሙ ፣ ለሂዝቢያ የእግር እሳት የሆኑ ታጋይ ኡለማዎችን የሚያንቋሸሽና የሚያማቃልል ሁሉ ማንነቱን እያጋለጠ እንደሆነ ልብ ይሏል።
قال أبو حاتم الرازي:
«علامةُ أهل البدع الوقيعةُ في أهل الأثر،...»[عقيدة السلف (١٠٥)]
"የቢድዐህ ሰዎች ምልክት ሀዲስና የሰለፎችን ፈለግ የሚከተሉትን (አህሉልአሰርን) ማንቋሸሽ ነው።"
https://t.me/Abuhemewiya/3609

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 19:18


👆👆👆
#በአላህ ﷻ ላይ የማጋራት አፀያፊነት በ13 አቅጣጫዎች የሚለው ሪሳላህ ማብራሪያ ክፍል 1

የኪታቡን PDF ለማግኘት
https://t.me/shakirsultan/1903

🔶
በማአከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ቃጥባሬ ቀበሌ ታላቁ አሊፍ መስጂድ የተሰጠ ኮርስ ።

🎙በኡስታዝ ሻኪር ቢን ሱልጣን (ሀፊዘውላህ)

🌐 https://t.me/shakirsultan

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 17:20


Live stream finished (26 minutes)

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 16:53


Live stream started

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 16:53


Live stream finished (1 hour)

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 15:44


Live stream started

Abu hatim Abduselam Assalefiy

15 Nov, 15:41


ሰምንተዊ የቁሪአን ተፊስር ልጀምር ነዉ
ገባ
       ገባ
                በሉ
https://t.me/abuhatimaselefiy

1,511

subscribers

209

photos

21

videos