አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በአካቶ ትምህርት ትግበራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅና ተቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበትም ተገልጿል::
******** ************
ይህ የተገለጸው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ከEthiopian Center for Disability and Development/ECDD/ ጋር በመተባበር ከፊንላንድ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህበረት (SYL) እና ከፊንላድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተገኘ ድጋፍ ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ከኮሌጆች፣ ከት/ም ቤቶችና ከየዲፓርትመንት ለተወጣጡ መምህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ልዩ ፍላጎት ላለባቸው አካላት ሰሞኑን ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው የስልጠና መድረክ ላይ ነው፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲ ልዩ ፍላጎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ጳውሎስ ዴኣ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው "Disability Rights, Disability Inclusion and Awareness and Sexual Reproductive Health Training for students with Disability" የሚሉት የሥልጠናው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መሆናቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ከአካል ጉድልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካለት ተሳትፎ እና የጋራ ርብርብ የሚያስፈልግ በመሆኑ ዘላቂነነት ባለው አግባብ በትብብር መስራት ተገቢ መሆኑን ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
አካል ጉዳተኞች ምንም ሳያግዳቸው በነፃነት አደባባይ ላይ ወጥተው ራሳቸውን እንዲገልጹ፣ ከማኅበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እና የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ለማስቻል የተለያዩ ጥረቶች ያስፈልጋል ያሉት ዶክተር ጳውሎስ ዴኣ በተለያዩ የሥራ መስኮች በመሳተፍም ራሳቸውን ለመቻል የሚያደርጉትን ጥረት ማበረታታት ተገቢ ነውም ብለዋል ።
በመድረኩ ከEthiopian Center for Disability and Development/ECDD/ ወክለው የተገኙት አቶ ዮሃንስ ተክላይ በበኩላቸው የራሳቸውን የህይወት ልምድ ለተሳታፊዎች አጋርተው ዛሬም በርካታ አካል ጉዳተኞች ለተለየዩ ችግሮች ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በከፍተኛ በትምህርት ተቋማት ረገድ ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች እየገጠሟቸው እንደሚገኝም ያብራሩት አቶ ዮሐንስ ECDD ይህንን ክፍተት ለመሙላት ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት ጋር እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ የወጡ የሕግ ማዕቀፎች በሙላት እንዲተገበር በማድረግ አገሪቱ ከምትከተለው እኩል የትምህርት ዕድል መርህ ጋር በሚጣጣም መልኩ ምቹ የመማር ማስተማር ዕድል የሚፈጥር እና በሥራ ላይ የሚደርስባቸውን መድሎ መከላከል እንዲቻል ቁጥጥሩ የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል አቶ ዮሐንስ።
በስልጠናው በሁለት ቀናት ቆይታው የተለያዩ ሰነዶች የቀረቡ ሲሆን ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት በማድረግና ስልጠናው በስፋት ለሁሉም አካላት በመስጠት በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሁሉንም ባለድርሻ አካለት ተሳትፎ እና የጋራ ርብርብ እንዲደረግ በማውሳት ስልጠናው መቋጫውን አግኝቷል ።
«ዕውቀትን በተግባር!!»
የዩኒቨርሲቲው ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/
ቴሌግራም፡https://t.me/WolaitaSUniversity
ዩቲዩብ፡ https://www.youtube.com/.../UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos
ዌብሳይት፡ http://www.wsu.edu.et/
ትዊተር፡ https://twitter.com/WSodoUniversity...
ኢንስታግራም፡ https://instagram.com/wolaita_sodo_university?igshid=YmMyMTA2M2Y=
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን