ህብረ ቀለማት

@getmnaleloch


ምርጥ ግጥሞችን፣
አጫጭር ታሪኮችን፣
የተለያዩ ልቦለዶችን፣
አነቃቂ መልዕክቶችን፣
አስተማሪና አዝናኝ ፁፎችን፣
ከፈለጉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።

ህብረ-ቀለማት
የሁሉ ድምቀት

Cross & comment 👉 @Natiaba

ህብረ ቀለማት

22 Oct, 08:19


ባልተቤትህ የአስቤዛ ወጭ ስትልህ
ኪችኑ ሙሉ ነው፣አንች ድንቅ ነሽ ትለያለሽ፣ እንዳውም የአስቤዛ መሸጫ ሱቅ አለሽ። እኔ ድንቅ፣ ሁላችንም ድንቅ ነን...... ዳዊት ድሪምስ

ህብረ ቀለማት

22 Oct, 08:19


አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል

ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል

በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው በኃላ እይነ ስውሩን አስፈቅዶት ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ገልብጦት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት

ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ሞላው

የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል

"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው: እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት

ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው ።


@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

22 Oct, 07:35


Class ውስጥ ካለማውራቴ የተነሳ ማውራት ከማይችሉት ጎራ ተመድብያለሁ🙆‍♂

This fake world😕

ህብረ ቀለማት

22 Oct, 06:53


ይህ የሆነው ሩቅ ሀገር አይደለም። እዚህ ጎረቤታችን ሀገር ኬንያ ነው። ይህች በስልክ እንጨቱ ላይ ያለችው ወፍ ግንደ ቆርቁር ( woodpecker ) ትባላለች። ግንድ ቆርቁራ ጎጆዋን ትቀልስና በዛ ለአመታት ትኖራለች። ቤተሰብ መስርታ ልጆቿንም በዛው ታሳድጋለች።

በፎቶው የምታዩዋት woodpecker በዚህ የመብራት ፖል ላይ ቆርቁራ መኖር ከጀመረች ቆይታለች ። እና የኬንያ መብራት ሀይል መስሪያ ቤት ይህን ያረጀ ፖል በኮንክሪት ሊቀይረው ይመጣል..እና ልክ ፖሉን ለመጣል አስረው ማዝመም ሲጀምር ከተቆረቆረው ግንድ ውስጥ አንድ woodpecker ወፍ ትወጣለች። ነገር ግን ከዛ መራቅ አልቻለችም ትወጣና መልሳ ለመግባት ትሞክራለች ሰራተኞቹ ፖሉን ነቅለው አስቀመጡት በዚህ ጊዜ ወጥታ የነበረችው ወፍ መጥታ ተቀመጠች ሰራተኞች ቀርበው አዩ። ተቆርቁሮ በተሰራው የወፍ ቤት ውስጥ ጫጩቶች ነበሩ።

ልክ ይህን እንዳዩ መልካም ልብ ያላቸው የመብራት ሀይል ሰራተኞች ይህችን ወፍ ከነልጆቿ ቤት ማሳጣት ጭካኔ እንደሆነ ተሰማቸውና ቤቷ ያለበትን አካባቢ ሳይነኩ ከረዥሙ የመብራት ፖል ላይ የተወሰነውን ትንሽ ክፍል ቆርጠው ከአዲሱ የኮንክሪት ፖል ጋር በዚህ መልኩ አያያዙት ። አውጥተው ሊጥሏት ሲችሉ አዘኑላት ለልጆቿ ልባቸው ራራ....

እንኳን ክቡር ለሆነው ለሰው ልጅ፤ ለወፍ እንኳን የሚራራ ማንነት እዚሁ ጎረቤት ሃገር ኬንያ አለ።

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

22 Oct, 03:47


የቀናልህ
የሞላልህ
ባለ ካባ
ባለ ሞገስ
ስምህ ዘመን አልፎ
ምዕተ ዓመት የሚዳረስ
አዋቂ
ታዋቂ
ያደረጀህ ነዋይ
በራሪ በሰማይ
ደስታህ የሚተመን ፣ ሆኖልህ አለቀጥ
በከፍታ እርካብ ፣ ክብርህ የሚያስቀምጥ ፤
ውብ እና ሸበላ
ዓይነ ውብ ከብላላ
ዘርህን ያበዛህ ፣ በብዙ መሰጠት
መናዋን የበላህ ፣ የምድርን በረከት ፤
ሁሉህ ሙሉ
እጅህ ያለ ፣  የዓለም ውሉ …
መሆንህን አይቼ
የማልገረመው
“ከዛስ ?” ብዬ ሳስብ
ትርጉም ቢያጣብኝ ነው ።
እሺ ከዛስ ?
አንተ አላፊ !🤔

(ሚካኤል አ)

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

21 Oct, 19:50


"ወገን ደሞዝ እየተጨመረ ስለሆነ ከእንግዲህ በርትተን ብንማር ይሻለናል" ያሉት የዶርም 03 አባላት ናቸው😑

ህብረ ቀለማት

21 Oct, 16:09


5ኛ class አብረን ስንማር እኔን ደብድቦኝ ለተባረረው ልጅ ሁለት ሲኖትራክ መኪና ሦስት ቢላ ቤት አንድ ቆንጆ ሚስት አሉ,..እኔ ግን🥺🙄

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

21 Oct, 09:58


ደራሲ ሲዲኒ ሸልደን "The other Side of me" የሚል የግለ ታሪክ መፅሐፍ አለው። እንዲህ ገናና ስም ከመገንባቱ በፊት እንዴት ያለ ፈተናን እንደተጋፈጠ እና ተስፋ ለመቁረጥ ተዳርጎ እንደነበር አብራርቷል።

በወጣትነት ዘመኑ በድብርት ህመም ይሰቃይ ነበር። ሙከራው ደጋግሞ ይከሽፍበታል፥ አሸነፍኩ ሲል ይሸነፋል፥ አገኘው ባለ ማግስት ያጣል።
አንድ ቀን ጨለማ የነገሰበት የሚመስለውን አታካች ኑሮውን አሰላሰለ። ያኔ መኖር አታክቶት ራሱን ሊያጠፋ ወሰነ።

ራሱን ለማጥፋት ከሞከረ በኋላ አባቱ የማይዘነጋ ምክር ለገሰው። "ህይወት መፅሐፍ ናት፥ እያንዳንዱ ቀን የመፅሐፉ አንድ ገፅ ነው። መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አትዝጋው" አለው።

ከዚህ በኋላ ቆም ብሎ አሰበ። "በገዛ ፈቃዴ ራሴን በመግደል የህይወቴ ገፅ እንዳይነበብ አላደርግም" አለ። ከዚህ በኋላ በመላው አለም ስሙ የናኘ ደራሲ ሆነ።

በእርግጥ ህይወታችን መፅሐፍ ብትሆን እያንዳንዱ ቀናት የመፅሐፉ ገፅ ናቸው። በመከራ መካከል ብንሆንም መፅሐፉ ተነቦ ሳያልቅ አንዘጋውም። ነገ ሌላ ቀን ነው፥ በድንግዝግዝ መሐልም ብንሆን እንኳ ሽራፊ ተስፋ አለ። እውነት መስሎ ባይታይም ጨለማው ይገፈፋል።

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

21 Oct, 03:45


ገጣሚው
ማንም ያላየውን
ማንም ያልፃፈውን
በፊት ያልነበረ …
ስንኝ ለማዋቀር
መወጠን ጀመረ ።
ሆኖም ግን አንድ አጣ
ያልተፃፈ በሰው
ሁሉን ቢያሰላስል
ቢያወጣ ፣ ቢያወርደው
አንድም አልነበረ
ሌላው ያልጀመረው ።
አሰበ ገጣሚው
አወረደ ፣ አወጣ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ የጀመረ
ገጣሚ ግን አጣ።
እናም ይሄን ጊዜ
የሱን ክታብ ሲቃኝ
ቀለሙን ሲያዋድድ
ከዝርጉ ወረቀት
'አዲስ ነገር ልፃፍ'
የሚል ነበረበት ።
ስንኙ አበቃ
ብዕር ተሰለበች
ታጠፈች ወረቀት
ግጥም ቀን ወጣላት ፤
አዲስ ነገር ፃፈ
አዲስ ነገር ልፃፍ
ብሎ በመነሳት ።

(ሚካኤል አ )

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

20 Oct, 17:19


ወላይታ ሶዶ ኦቶና ሆስፒታል የወለደ ሰው ለመጠየቅ ሄድኩ😊.. ባሏ አጠገቧ ተቀምጦ አጥሚት ይጠጣል። እሷ ሞባይል እየጎረጎረች ነው። የሱ እናት ህፃኑን ይዛለች። መርቄ እንደተቀመጥኩ ባልዬው

"እንጠጣ አጥሚት" አለኝ

'አጥንትህ ይውለቅ' አልኩ በልቤ። እሱ አምጦ የወለደ ይመስል ተዘርጥጦ አጥሚት መጠጣቱ ሲያናደኝ እንጠጣ ይለኛል ደግሞ😊። ጭራሽ ደግሞ ከፊታችን የቆመችውን የሚስቱን እህት

"ገንፎ አትሰሪልኝም እንዴ ቆንጆ?" አለ

'እግዚኦ ትንሽ ከቆየሁ ይህ ቀሚሴን አምጪልኝ' ይላል ብዬ ልወጣ አሰብኩ😊

ግን ሌላ ቀን ይህ 'ሰውይት' ባለበትማ ስለማልመጣ ትንሽ ልቆይ ብዬ ወሰንኩ። አጥሚቱን ጠጥቶ ሱቅ ደርሼ ልምጣ ብሎ ወጣ። ሲመለስ ጭራሽ ማስቲካ ገዝቶ እያኘከ በአፉ ያፈነዳልኛል😊

ያልተደወለ ስልክ እያወራሁ ወጥቼ በዛው ሄድኩ

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

20 Oct, 17:19


ይህ አርቲፊሻል ማህጸን ነው!
ይህ ቴክኖሎጂ ሴቶች በሆዳቸው* ማርግዘን የሚያስቀርላቸው ቴክኖሎጂ ሲሆን ከወንዱም ከሴቷም ዘራቸው ተወስዶ ልክ በሴቷ ሆድ እንደሚያድገው አድጎ ልጅ ለመሆን የሚያስችል ነው።

መሳሪያው በሆስፒታሎች አቅም ካለ ደግሞ በቤትም መቀመጥ የሚችል ሲሆን የልጁን ሁኔታ በስልክ በቀጥታ መከታተል የሚያስችል ስርዓት ተዘርግቶለታል።

በወሊድ ጊዜ ሴቶች ላይ የሚደርሰውን ሰቃይ ለመቀነስ ያስችላል የሚል ድጋፍ እንዳለው ሁሉ ነቀፌታም አላጣም።

እናንተ ከየትኛው ወገን ናችሁ? ማማጥ ወይም ኦፕራሲዮን መደረግ ቀረልን ትላላችሁ ወይስ የልጄን ህይወት ፈጣሪ በሰጠኝ ፀጋ በሆዴ አርግዤ እፈጥራለሁ ትላላችሁ?
Am
Haileyesus Desta

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

20 Oct, 04:40


አካሄድ

የስንፍናን ጡዘት
ካንሸዋረሩበት
ከአካሄዱ ጀርባ
ሀፍረትን ቢመርጡም
ወደው ለሄዱበት
ነፃነት አይቀሙም
...
ግና................
ተዘክረው ቢመጡም
እንደአካሄዳቸው
ምህረትን ፍለጋ
ዳር ዳር ቅኝታቸው...
ልዝቡን ሹክሹክታ
ሽቅብ ቢያደምጡም
ባልኖሩት ንሰሃ
ፍቅርን አያቀልሙም።

           By ኢያሱ ከበደ
      @getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

19 Oct, 04:59


እረሳው እረሳውና
ተመልሼ ራሴን እዛው አገኘዋለሁ
እሱ እንዳሻው ነው
አለ ስል የለም
የለም ብዬ መንገድ ስጀምር
ወንበሩ፣ አየሩ ፣ ምግቡ መጠጡ ....
ብቻ ሁሉም ነገር እርሱ ነው
ሳጣው ዕርቃኔን የቀረው ይመስል ውስጤን ይበርደኛል
ቅዝቅዝ እላለሁ
ሲመጣ ሚጢጢ ልቤን ደስታ ያፍናታል የስሜት ከፍ እና ዝቅ የሚሉት ይሄ ይሆን?
እሱ እና እኔ እሳት እና ውሃ
.....
እንዲህም እንዲያም ነን...
ሲለው መንገድ ላይ ዘግቶኝ ያልፋል
ደግሞ በሌላ ቀን በዶፍ ዝናብ ከቤታችን አንድ ቅያስ በኋላ ካለች ትንሽዬ ሻይ ቤት በረዶ እስኪሰራ ተቀምጦ ዝናቡ
አባርቶ ወጥቼ እስካገኘው አርባ ግዜ ይደውላል
ለምን መጣህ?
ናፍቀሽኝ ምነው መምጣት አልነበረብኝም?
አላልኩም
እኮ ወተሽ አግኚኛ
ዝናቡ ያባራ ብርድ ልታስመታኝ ነው እንዴ
ነው
አዎ...ጢጥ ጢጥ ጆሮዬ ላይ ድርግም አርጎት ተነስቶ
እየበሰበሰ ይሄዳል
ይቺን ሰበብ አርጎ ወይ ቀጣይ ቀጠሯችንን ይሰርዘዋል አልያም ቀጥሮ ለሰዐታት ያስጠብቀኛል ያው የፍቅር ቁልፉ
ትዕግስት ነው .....እጠብቀዋለሁ
አንዳንድ ጥበቃ ዘላለም ይመስላል
የዚህን ግዜ ታድያ ብስጭት እልና
ልሔድ እነሳለሁ
ከትዝታው፣ ከፍቅሩ ፣ ከእልሁ ሽሽት
"እሱ ማን ስለሆነ ነው " አይምሮዬ ልቤን ሊያጀግን
ይህንን ቃል ይወረውራል
አንድ ሁለት ሳምንት......እደውላለሁ
እንደማልጨክን ያውቃል
እንዳይቆርጥልኝ ሆኛለሁ
ሳር ቅጠሉ ሁሉ እሱን ይመስለኛል እመለሳለሁ
አንድን መንገድ ቢመላለሱበት ይደክሙበታል እንጂ አዲስ
ነገር አያገኙበትም ድካም ብቻ........
[koki] -ሽራፊ ሀሳብ.....

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

19 Oct, 04:38


ቤትህ…
በመኃልይ ልባስ
መልኩን የደበቀ
መልከኛ እዬዬ ገባ ተሸሽጎ
ለደጅህ የላኩት
እንዳማረ በቃ ላደባባይ ሸንጎ።

በተመስገን መዳፍ
በቡራኬ ከንፈር
ወደሰማይ ያልኩት ተቀላቅሎ ካ’ፈር
ለጓዳዬ አይበቃም እንኳንስ ለጠፈር።
አንተው በጣቶችህ
ጣራ ስር ከቀረ ዋይታዬ ስር አንሳኝ
ወይም ጸሎት ንሳኝ።

ዘመን ቢተራመስ እድሜ ቢቀናጣ
እንባዬ ቢጋለጥ ደስታዬ ቢሰጣ
አደባባይ መውጫ ግጥም ብቻ አልጣ።

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

18 Oct, 04:34


ሲሸሹኝ ስጎትት ሲርቁኝ ስጣራ፤
    ሲሄዱ ስከተል ሲዘጉኝ ሳወራ።

አሁንስ ዝም አልኩኝ ልቤን ደካከመው፤
    ሁለት እየሆነ አንድ ነው ያልኩት ሰው።

ብቻ በመንገዴ፥

ከነሳቸው ሠላም ከነሳቸው ጤና እኔ መከተሌ፤
ለበደለኝ ሁሉ ለበደልኩት ሁሉ ይቅርታ ነው ቃሌ።

ሄጃለሁ ከእንግዲህ በቃ ለልከተል🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️🚶‍♀‍➡️

ጦቢያ

@getmnaleloch

ህብረ ቀለማት

18 Oct, 04:26


አንጋፋና ትልቁን ፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ተንከባክቦ ያሳደገኝን ያንን የጥንቱን የኔን ሆስፒታል መልሱልኝ😭‼️

ኦ ቶ ና ሆ ስ ፒ ታ ል - O t o n a H o s p i t a l

✍️ #አሁን_አሁን ጥቂት የሚባሉ ሰዎች ፤ በግል የሚፈልጉት አገልግሎት ከሌለ ብቻ ወደ መንግስት ሆስፒታሎች ይመጣሉ ። #በርካታ_የደሀው_መሀበረሰብ ደግሞ አማራጭ ስለሌለውና በግል ከፍሎ መታከም ስለማይችል ወደ #መንግስት_ሆስፒታሎች_ይሄዳል ።

✍️ይሁንና ወደ ሆስፒታሉ ለሕክምና በሚመጡ በነዚህ ምስኪን ማሕበረሰብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና በደል ፤እጅግ ከባድና በጣም የሚያሳዝን ሆኖ አግኝቼዋለሁ 😭😭??። እኔም እየሆነ ያለውን ይህንን ትልቅ በደል ተመልክቼ ዝም ብዬ ማለፍ ስላልቻልኩኝ ትዝብቴን ለእናንተው ለማካፈልና ፤ በእናንተው ፊት የሆነ ነገር ብዬ ለማለፍ ወደድኩኝ‼️

✍️ #ዛሬ_ይህ_ሆስፒታል; ጎልተው በሚታዩ በርካታ ችግርች ምክንያት ለሕብረተሰቡ ተገቢውን እገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን ፤ በሆስፒታሉ በነበረኝ የአጭር ጊዜ ቆይታ ብዙ ጎደሎ ነገሮችን ለመታዘብ ችያለሁ ።

#እነዚህም
✍️የህክምና ስርአት አወቃቀር ችግር፣ የጤና ቁሳቁሶች አቅርቦት በበቂ ሆኔታ አለመኖር ፤ የተንዛዛ የቢሮክራሲ እና በርካታ አስተዳደራዊ ችግሮ ፤የሆስፒታሉ ፅዳት ሰራተኞችን ያለማበረታት ችግር፤ እንዲሁም ደግሞ፤በአንድ አንድ የጤና ባለሙያዎቹ ላይ የሚታዩ የስነምግባር ግድፈቶችም ይካተቱበታል። #እነዚህን_በወፍ_በረራ_እይታ_እንኳን_ካየነው.......
#በሽተኞች_አጣዳፊ_ህመም_ታመው_ወረፋ_ይጠብቃሉ::

✍️ ወረፋ ካልደረሳቸው ታካሚዎች መሬት ላይ መተኛት ወይም አለመታከም አማራጫቸው ሊሆን ይችላል:: በዚህ መሀል ግን ሞት ነጻ ፈቃድ ሊያገኝ ይችላል ማለት ነው‼️

✍️ #የመድኃኒት_አቅርቦት; በሆስፒታሉ ፋርማሲ ሊኖሩ ከሚገባቸው መድሃኒቶች ውስጥ ፤ መስፈርቱን አሟልቶ የሚገኘው 25 በመቶ ብቻ ነው :: ግላብ እንኳን ከውጪ ትገዛለህ‼️

✍️ #ስፔሻሊስትቶች አሉ ይሉናል ፤ግን እኛ በወሬ እንጂ በዓይናችን አላየናቸውም ‼️ካያችኋቸው #ኮንታ ትገባላችሁ ..፤ የተባለ ይመስል ግቢ ውስጥ እነርሱም የሉም እኛም አላየናቸውም ።

🤔 ምናላባት ይህ ነገር ሊሆን የቻለው ; በጤናው ዘርፍ ባለው ኢፍትሃዊነት ምክንያት..ማለትም የጤና ባለሙያዎች የአያያዝ ድክመት ፤ እንዲሁም ደግሞ የቢሮክራሲ መንዛዛቶች መኖሩ ይመስለኛል እንዲህ አይነት ነገሮች እንዲኖሩ ያደረገው። ብቻ እርግጠኛ አይደለሁም‼️

#ስነምግባር

✍️ #ሀኪሞች ; ታካሚዎቻቸውን ባለው ሀብት እና እውቀት በሙሉ ፤ሕብረተሰቡን የማገልገል ግዴታ አለበት ‼️ ፤ በዘር፣ በፆታ፣ በቀለም፣ በአካል ጉዳት ወይም በዕድሜ ላይ የተመሰረተ ልዩነት ሳይደረግባቸው ማለት ነው።

#ግን_ምን_ተመለከትኩኝ_መሠላችሁ... በሆስፒታሉ ለአንዱ ታካሚ #የለም_የተባለ_አገልግሎትና_አልጋ ፤ ለሌላው ታካሚ በዘመድና በትውውቅ #ካልነበረበት_ወደ_ነበረ ሲመጣ ለመታዘብ ችያለሁ።

✍️ #ሌላው ; እዚሁ ሆስፒታል እየታከመ ቆይቶ፤ወደ ጥብቅ ጥንቃቄ (ICU) ክፍል እንዲገባ በዶክተር የታዘዘ ታካሚ እያለ፤ሌላው ገና ለገና ከሌላ ቦታ ወይንም ወረዳ እስከሚመጣ አልጋው ተይዟል ተብሎ ፤ በአንድ የክፍሉ ባለሙያ ሲከለከል ተመልክቻለሁ ። በሰዓቱ ግን ትርፍ ሁለት የICU አልጋዎች ነበሩ ።ለትዝብት እንዲሆን ዘንድ ከታች በፎቶ አስቀርቼዋለው። እዚህ ያለው ህመምተኛ ፤ህመምተኛ አይደለምን????????

በመሀል ታካሚው ወደ ICU ክፍል ሳይገባ ያልፋል ማለት ነው😭

✍️ታዲያ በዚህ በህክምና ላይ በሚፈፀም ቸልተኝነት ወይም የሙያ ስነምግባር ችግር ፤ በታካሚው ላይ ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊነቱን የሚወስደው የህክምና ተቋሙ ነው ወይስ የህክምና ባለሙያው?????? ይህ በግልፅ መልስ የሚፈልግ ጥያቄ ነው‼️

#ፅዳት
ፅዳትን በተመለከተ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ...
በሚቀጥለው ፁሑፌ ይዤ እመለሳለሁ‼️
በፍጹም ዮናስ