የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia

@pdc_ethiopia


ኢኮኖሚውን በረዥም እና በመካከለኛ የልማት ዕቅድ በመምራት፥ በፈጣን መዋቅራዊ ለውጥ ዘላቂ ልማት ለማምጣት ይሠራል

ወደ ቻናላችን ስለመጡ እናመሰግናለን

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia

19 Oct, 16:43


 
ሰራተኞች ሙስናን በመጸየፍ ሀላፊነታቸው እንዲወጡ ለማስቻል ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ይገባል፡፡

****

ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም አዳማ (የፕ.ል.ሚ)

ኢትዮጵያ በማስመዝገብ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ዕድገት በብቃት ለመወጣት እንዲቻል ብቁ፣ በመልካም ስነ-ምግባር የታነጹ እና ሙስናን በመጸየፍ ሀላፊነታቸው በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ለተቋሙ ሰራተኞች በስነ-ምግባር ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ግንዛቤአቸውን በማዳበር መልካም ስነምግባርን በመላበስ ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በተዘጋጀ አውደ ጥናት መክፈቻ ላይ ክብርት ሚነስቴር ዲኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ እንደገለጹት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሀገሪቱ ላስመዘገበችው እና በማስመዝገብ ላይ ላለችው የኢኮኖሚ ዕድገት የአንበሳውን ድርሻ እንደሚይዝ ይታወቃል፡፡

በቀጣይም የበለጠ እድገት ለማመዝገብና በመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት እንዲቻል ብቁ፣በመልካም ስነ-ምግባር የታነጹ እና ሙስናን በመጸየፍ ሀላፊነታቸው በአግባቡ የሚወጡ ሰራተኞች መቅረጽ ወሳኝ በመሆኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮችን በሀገር አቀፍና በተቋም ደረጃ በሚዘጋጁ የልማት ዕቅዶች ውስጥ አካቶ በመተግበር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ድርሻቸው ከፍተኛ በመሆኑ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ግንዛቤያቸውን ማሳደግ ወሳኝ ነዉ ብለዋል፡፡
 
የተዘጋጀው ስልጠና ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታዋ የስነ-ምግባር መከታተያ የስራ ክፍል ከሴቶች፣የማህበራዊ ጉዳዮች አካትቶ ትግበራ የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር የተቋሙ ሰራተኞች በስነ-ምግባር ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በየጊዜው በመፈተሸ የታየውን ለውጥ እንዲሁም ክፍተትን በማረም በመልካም ስነምግባር ከሙስና እና ብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት መስጠት የግድና አስፈላጊ ጭምር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አገራዊ የልማት ዕቅድ አውጪ ተቋም እንደመሆኑ የስነምግባርና የሴቶች፣ በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ሰራተኞች ግንዛቤያቸውን በየጊዜው   በማሳደግ የሚያከናውኑት ተግባር በተቋሙም ሆነ በሀገር ደረጃ ወደፊት ለሚመዘገቡ ውጤቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው እምነታቸው መሆኑን ገልፀዋል፡  

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia

19 Oct, 10:14


የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር በስነምግባርና ፀረ-ሙስና እና በሴቶችና ስርዐተ ጾታና የአካቶ ትግበራ  ጉዳዮች ዙሪያ ለተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ያዘጋጀውን ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ ። ****

ጥቅምት 09/2017 ዓ.ም (የፕ.ል.ሚ) 

ስልጠናው በተቋሙ የስነምግባርና ፀረሙስና እና የሴቶች ማህበራዊ ጉዳይና የአካቶ ትግበራ በጋራ የተዘጋጀ ነው ።

ስልጠናው በዘርፉ ዕውቅ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር | Ministry of Planning and Development - Ethiopia

15 Oct, 18:56


https://www.facebook.com/MoPDETH?mibextid=LQQJ4d

10,102

subscribers

1,909

photos

25

videos