zemedkun_Bekele(ዘመዴ) @zemdkunb Channel on Telegram

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

@zemdkunb


zemedkun_Bekele(ዘመዴ) (Amharic)

የzemedkun_Bekele(ዘመዴ) የቴሌግራም ክፍል ስለስራ ይጠቀሙ!
zemedkun_Bekele(ዘመዴ) በአለምአቀፋዊ ቴሌግራም የመረጃ መድረክ ለመከናከልና ለማንበብ ይረዳል። ይህ በመጠቀም ለሌሎች በጣም ግንዛቤ እና የሕዝብ ገጽ አሉት። አዘገጃጀቱን ለመመልከት እና አልተገኘም የቴሌግራም መመልከት እና ሰልጥናት መጽሆ። nnየzemedkun_Bekele(ዘመዴ) ቴሌግራም ክፍል ደግሞ በድምፅ ከተጻፍና ከመከታተል በኋላ በታከምላ ውስጥ ለእናንተ እና ለተለያዩ ጎበኛዎች ሳይበላ፣ ታከምላለህ። zemedkun_Bekele(ዘመዴ) አሁን ይሄን ስራዎችን ለመቀበል እና በመሣሪያ አሰባሰብ ሚድያ።

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


"…አይ ሂዊ…😂😂😂

"…በእርሷ ቤት ኦሮሞ የዋህ ነው ብላ ማጀዘቧም ማጃጇላም ነበር… ዐማራ ግን ወጥር፣ ሁለቱንም አንድ አድርገህ ቁጠር፣ ከዚያም በአንድ ላይ አበጥር።

"…የሂዊና የኦነግ ሸኔ አክቲቪስቶች አንድ ላይ ገጥመው በአንድ ፖፖ ካልተጸዳዳን፣ በአንድ ግልገር ሱሪም ካላጌጥን ብለው ሲዋከቡ ኢገርመኝ ነበር። ምድረ ኦነግ በሂዊ ተከሽኖ ሁሏ።

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


ዐማራ ሆይ ይሄን ስማ…!

"…ታዬ ደንደአ የራሱ ጉዳይ ነው፣ ሳህለወርቅ ዘውዴም ለደንታቸው። ከፈለጉ ይበጣበጡ፣ ይገለባበጡ፣ ይዣለጡ። ይናኮሩ። ይራኮቱ።  እንደፍጥርጥራቸው። ሥራቸው ያውጣቸው።

"…አንተ ግን ዐማራ ሆይ ስማኝማ ልንገርህ… ይሄን በቁምህ አፈር ያስበላህን አረመኔ የኦሮሙማ አገዛዝ በቁሙ አፈር ማስጋጥህን ቀጥል። አንተን አፍር ዱቄት አድርጎ እሱ ገነት መንግሥተ ሰማያት የመሰለ ኑሮ እንዲኖርም አትፍቀድለት። የፋራ አረዳውን የበሻሻ ሰገጤውን ሴራውን አፍርስለት።

"…ሰማኸኝ ዐማራዬ… በድሮን የሚጨፈጨፉትን ንፁሐን ዐማሮች ደም ለመበቀል እንቅልፍ አጥተህ ታገል። ጦርነቱን ከክልልህ አውጥተህ አቢይ አሕመድንና ሠራዊቱን በራሱ ሜዳ እሬቻ ለማስጋጥ በጀመርከው መንገድ ወጥር። ቀጥል። ድልድዮችህ ተሰብረው እንዳይቀሩ፣ የአንተ ሆስፒታል ወድሞ፣ ትምህርት ቤትህም ፈርሶ፣ ሰብልህ በእሳት ነድዶ አጨብጭበህ ፈጣሪ ይፍረድ ብለህ እንዳትቀመጥ።

"…ሰማኸኝ ዐማራ… ኮንቪንስ እና ኮንፊዩዝድ የሚባል የኦሮሙማ መጫወቻ ካርድ አለ። እናም የትናንቱን የመካነ ሰላም የድሮን ጭፍጨፋ እያሰብክ አቢይና ብልፅግናን ለመበቀል መዘጋጀት እንጂ ታዬ ደንደአ ገለመሌ እያልክ አጀንዳ አትቀየር። ዜናውን ከሰማህ ይበቃል። ውነት ይሁን ውሸት ለደንታቸው። ነገርኩህ የራሳቸው ጉዳይ። ታዬ ቢሳደብ አይታሰር፣ አይገደል። አዋሽ አርባ አይሄድ። እህዕ ታዬ ምንም ቢሆን ኦሮሞ እኮ ነው። እደግመዋለሁ የራሱ ግዳይ።

• ሰማኸኝ ዐማራ አፈር ያበላህን ይሄን አፓርታይድ አገዛዝ በቁሙ አፈር ለማብላት ተዘጋጅ። ታዲያ አፈር ማብላቱን ከብአዴን ጀምር አባቴ። 

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


የቱለማ ኦሮሞን መምታት ተጀምሯል…!

"…ትናንት በመረጃ ቴሌቭዥን የነጭ ነጯን መርሀ ግብሬ ላይ በነገርኳችሁ መሠረት የቱለማ ኦሮሞዎችን ሳይውል ሳያድር መምታት ተጀምሯል። በቀጣይ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን የማስወገድና የመተካት እንቅስቃሴም እንዲደረግ አረመኔው አቢይ አሕመድ አዟል። 

"…ለማስታወስ ያህል አቶ ታዬን በተመለከተ በድብቅ የወጣውን የአቢይ አሕመድና የኦሮሙማውን ግምገማ በተመለከተ እንዲህ ነበር ያለው። ● ጊዜ የለንም።  ሸገርን ማፅዳት የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ሳታስብ ፊንፊኔን ከሴማቲክና ከኦርቶዶክስ ተጽእኖ ነፃ ለማድረግ ወደ ሁለተኛው ውስብስብ ሥራ ለመሄድ ከ3 ወር በላይ ሊወስድ አይገባም። ትልቁ ፈተና የሚጀመረው የቱለማን መሬት ለግንባታና ለልማት መውሰድ ስንጀምር ነው። በውስጣችን ያሉ እንደ ታዬ ደንደአ አይነቱ እንኳን አሁን ስለ ቱለማ መሬት ማውራት ጀምረዋል። ይህ መታፈን ያለበት አደገኛ መስመር ነው።  ቱለማዎችስ መሬታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑ የሸገር ፕሮጀክት አይኖርም። በሸገር ከተማ ዙሪያ የጉጂ ዓይነት ብጥብጥ እንዲኖር አንፈልግም።

"…ዐማራን ለመከፋፈል ቅማንትንና አገው ሸንጎ የሚባል የሴራ ካርድ ያዘጋጁት የትግሬ ነፃ አውጪዎች በአክሱም ጉዳይ ከእስላሙ ማኅበረሰብ ጋር፣ በውስጥም አንደርታ፣ ኢሮብና ሽሬ ወዘተ ተባብለው ይፋጃሉ። ቅማንት፣ የወሎ ኦሮሞ፣ አገው ሸንጎ እያለ በOMN በኩል ሲያላዝን የሚውለው ኦሮሞውም በወለጋ ክልልነት፣ በቱለማ ኦርቶዶክስና በአሩሲ፣ በባሌ፣ በጅማ ፅንፈኛ የወሀቢይ እስላም ተባብሎ መባላት ይጀምራል። ሱማሌም፣ አፋርም ዝግጁ ናቸው። ደቡብ አልበላም አልዋጥም ብሎ መሸፈቱ አይቀርም። ሌላውን አውድሜ እኔ ገነት ሆኜ በምድር እኖራለሁ ባይዋ ኦሮሚያ በቅርቡ አይኗ እያየ ምድራዊ ሲኦል ትሆናለች።

• አቢዮትም ልጆቹን መብላቱን ይቀጥላል።

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


ፍተሻ በአዲስ አበባ…

• ክፈት ስልክህን…!

~ ይኸው ከፈትኩ…

• የዘመድኩን ቴሌግራም፣ የፋኖ ፎቶ፣ የአጼዎቹ ፎቶ፣ ልሙጡ ባንዲራ በስልክህ ውስጥ አለ…?

~ የዘመድኩን ቴሌግራም አለኝ፣ ባንዲራም አለኝ።

• ቀጥል ወደ አዋሽ አርባ፣ ወደ ፎሊስ ጣቢያ…

"…ጉድ እኮ ነው። የአንድ ሰው የቴሌግራም ገጽ፣ የዐማራ ፋኖ ፎቶ፣ የቀድሞ ነገሥታት የአጼዎቹ ምሥል፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፈንጅ፣ ከደማሚት እና ከቦንብ ይልቅ እንዴት በዚህ መጠን የሚፈሩ ሆኑ…?

"…ማስታወሻ…

"…እኔ ሓላፊነት የሚሰማኝ ሰው ነኝ። የምጽፈው ለላይክና ለፎሎወር ማብዛት አይደለም መረጃ ለመስጠት ነው እንጂ። እናም በእኔ በዘመዴ የቴሌግራም ገፅ ምክንያት አንድም ሰው ለሰከንድም ቢሆን እንዲንገላታና እንዲታሰር አልፈልግም።

"…ብልህ ሁኑ እናንተም ከቤት ስትወጡ ገፄን ለቃችሁ ውጡ። ወደ ቤት ስትገቡ ስትመለሱ ደግሞ ጫኑት። ለጊዜው መፍትሄው ይሄ ብቻ ነው። እደግመዋለሁ ለአንድም ደቂቃ ቢሆን በዚህ 100 ኪሎ ሰገጤ ፋራ አገዛዝ ምክንያት ቅንጣት ታህል መከራ እንዲገጥማችሁ አልፈልግም። በዚያውም ፖሊሶቹ ምርጥ ስልክ ከሆነ የያዛችሁት ይወስዱባችኋል። ተጠንቀቁ ወገኖቼ።

• አክባሪወንድማችሁ አሸበርቲው ዘመዴ ነኝ።

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


"…ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ የእግዚአብሔር ስም ቡሩክ ይሁን። ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስም ይመስገን። መዝ 113፥

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


"…ጽዮን በፍርድ ከእርስዋም የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ። በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፥ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ። በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ ስለ መረጣችኋትም አትክልት እፍረት ይይዛችኋልና፤ ቅጠልዋ እንደ ረገፈ ዛፍ፥ ውኃም እንደሌለባት አትክልት ትሆናላችሁና። ኃይለኛውም እንደ ተልባ ጭረት፥ ሥራውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ አብረውም ይቃጠላሉ እነርሱንም የሚያጠፋ የለም። ኢሳ 1፥ 27-31

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር የተሰኘው የመረጃ ተለቭዥን ሳምንታዊው መርሀ ግብራችን ሰዓቱን ጠብቆ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ እናንተ ይደርሳል።

• ጠብቁነ…!

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


ኢንጪኒ እና ዳንግላ

• ኢንጪኒ

"…ከአዲስ አበባ አቅራቢያ ከሆለታና ሙገር ከተማ መሃል በእንጪኒ ከተማ ትናንት ሌሊት ኦነግ ሸኔ ገብቶ ባንክ ዘርፎ፣ እስረኞችም አስፈትቶ፣ 5 የኦህዴድ ብልጽግና አመራሮችንም ገድሎ ከተማዋን ለቅቆ ወጥቷል። ይህ ሁሉ ኦፕሬሽን ሲደረግ የሀገር መከላከያ ተብዬው የኦሮሙማው መከላከያ እዚያው ትንሽ ራቅ ብሎ ቲአትሩን እየሳቀ ይመለከት ነበር ተብሏል። ኦነግ ሸኔዎቹ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ መግባታቸው እንጂ ጥፋታቸው አልተገለፀም።

• ዳንግላ

"…ከሂዊ ፈጠሩ አገው ሸንጎ ጋር በቀጣይ የሞት ሽረት ፍልሚያ ለማድረግ የተዘጋጁት የአገውና ዐማራ ፋኖዎችም ትናንት በተመሳሳይ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ባደረጉት የተለየ አስደናቂ ኦፕሬሽን ማረሚያ ቤቱን ሰብረው የፖለቲካ እስረኞችን በማስለቀቅ የጦር መሣሪያም ካወጡ በኋላ የብልፅግናን አድማ ብተና ፖሊስ እና ውኃ አይገቤ ሚሊሻን እጅ ወደ ላይ በማስባል ማርከው በድል ወደ ማዘዣ ጣቢያቸው መመለሳቸው ተነግሯል። ፋኖ እነደ ሸኔ የዘረፈው ባንክ ግን የለም። የዐማራ ክልል ኮማንድ ፖስት ማዘዣ በሆነው ከተማ ይሄ ሁሉ ሱፈጸም የኦሮሙማው መከላከያ ድርጊቱን በርቀት ከማየት በቀር ለትናንት የእሳት ራት መሆን እንዳልፈለገም ተሰምቷል።

"…በቀደም ደብረታቦር ከተማ ላይ የፎከሩት አረጋ ከበደ፣ ጄነራል ብራኑ በቀለ እና አንድ ሌላ የእሳት ራት የሆኑ ሰው በአሚኮ ላይ ድንፋታቸውን ከለጠፉ በኋላ አሚኮ አንስቶታል። በአማሪካ አይዞሽ ባይነት የተበረታታችው የትግሬ ነፃ አውጪዋ ሂዊም ለዳግም ወረራ ዝግጅቷን አጠናክራ ቀጥላለች። በቅርቡ ከወደ ሰሜን ሰማይና ምድር ይጣበቃል። ከታሕሳስ 19 በፊትም ሁሉ ነገር ይለይለታል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። የዐማራ ብልጽግና እና የአቢይ መከላከያ ያሉት ዳንኤል ክብረት ፌስቡክ ላይ ብቻ ነው።

• ማኔቴቄልፋሬስ…!

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


አላችሁ አይደል…?
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

• ጀምረናል ገባ ገባ በሉማ

"…ሻሎም !  ሰላም !

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

11 Dec, 18:35


"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር

"…ዘወትር እሑድ በመረጃ ተለቭዥን የሚተላለፈው “ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር” የተሰኘው ሳምንታዊው መደበኛ የቀጥታ ስርጭት መርሀ ግብራችን አሁን ይጀምራል።

•በዩቲዩብ 👉 https://www.youtube.com/watch?v=lRZiUkrvPGA

•በራምብል 👉 https://rumble.com/Mereja/live

"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።

👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።

"…ሻሎም !  ሰላም !

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

09 Dec, 19:46


ስደት

"…በጦርነት ምክንያት ለራብ የተዳረጉት የትግራይ ተወላጆች ከሞት ለመትረፍ በገፍ ወደ አዲስ አበባ መፍለሳቸው፣ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች፣ መንደሮችም ከትግራይ እና ከዐማራ ክልሎች እንዲሁም ከወለጋ ተፈናቅለው በሚመጡ ዜጎች መሞላታቸውም እየተነገረ ነው።

• በዚህ በኩል ኦሮሙማው እየተሳካለት ነው።

zemedkun_Bekele(ዘመዴ)

09 Dec, 19:46


"…እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። ሰው በስውር ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል እግዚአብሔር። ኤር 23፥ 23-24

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ