ሲኒዬር ሶፍትዌር ኢንጅነር መሆን በራሱ ማንኛውንም ሲስተም፣ ዌብሳይትም ሆነ ሞባይል አፕ በቀላሉ ትሰራለህ ማለት አይደለም። ከራሴ ድርጅት ባሻገር አሁንም Cyprus ዋናከተማ ኒኮሽያ ለሚገኝ ኤክሴሊያ ለሚባል ድርጅት እሰራለሁ። የምንሰራቸው ሲስተሞች በአብዛኛው ከመርከብ ጋር የተያያዙ ናቸው። እኔ በቲም ሊደርነት የምመራው ሉብሊክ የተሰኘ ፕሮዳክት አለን። ታድያ ሶስትዌሩ ከሞላ ጎደል ወደ መጠናቀቁ ነው።
መርከቦች lubricant አለያም oil ሲፈልጉ rondomly ሲገዙ ብዙ ኪሳራ ይደርስባቸዋል። ያንን ወጭ ለመቀነስ የኛን ሲስተም ይጠቀማሉ። በቅናሽ የትኛው ወደብ ላይ ማግኘት እንደሚችሉ፣ ከቶታል መግዛት ፈልገው ቢወደድባቸው ከGazprom አለያም ከexon, chevron or gulf ሊሆን ይችላል equivalent product እንሰጣቸዋለን። መረጃ ከምንለዋወጥበት አንዱ መንገድ ኢሜይል ነው። በርግጥ ኢሜይል የሚልክላቸው ሲስተሙ ነው። ትላንት አንድ ችግር ተገኘ ተብሎ በአስቸኳይ እንዳስተካክል ተጠየቅኩ። በአንድ ቀን ውስጥ 😊
ኮዱን የጻፍኩት እኔ ራሴ ስለሆንኩ በቀላሉ የማስተካክለው መስሎኝ ነበር። ታገልኩ ወጣሁ ወረድኩ፣ የበላይ አለቃዬ በፊት ኮዲንግ ይሰራ ስለነበር አብረን እንየው አለኝ። አየነው መፍትሄ ግን ወፍ ።
ሰላሳ ደቂቃ እርፍት እናድርግና ድጋሚ እንሞክረዋለን ተባብለን ልክ 9 ሰዓት ድጋሚ ተገናኘን። ያኔ ችግሩ ከኔ ኮድ ሳይሆን ከተጠቀምኩት ላይብረሪ እንደሆነ ገባኝና refactoring ሰርቸ ስጨርስ የቀጠሮ ሰዓታችን ደርሶ የሰራሁትን ድጋሚ ቴስት ማድረግ ጀመርን። It worked like a charm 👌
አንዳንድ ችግሮች ምንጫቸውን ስላላወቅነው ብቻ የማንችላቸው መስለውን አንችልም ብለን እናልፋለን አይደል። የችግሮቻችንን ምንጭ ማወቅ ቅድሚያ ብንሰጠው መፍትሄ አይጠፋም።
"ብር የለኝም እንደት ማግኘት እችላለሁ ?" ብሎ ከማሰብ ብር የማላገኘው ለምንድነው የሚለውን ጥያቄ መመለስ የተሻለ መልስ ይሰጣል።
ሰናይ ቀን 👌