ATC UEE PREPARATION @atc_uee Channel on Telegram

ATC UEE PREPARATION

@atc_uee


ATC UEE PREPARATION (English)

Are you dreamt of becoming an Air Traffic Controller (ATC) in the United Earth Empire (UEE)? Look no further than the ATC UEE PREPARATION Telegram channel! This channel is dedicated to helping aspiring ATCs prepare for the rigorous selection process and training required to excel in this exciting career field. Whether you are a seasoned veteran looking to brush up on your skills or a newcomer eager to learn the ropes, ATC UEE PREPARATION has the resources and support you need. From practice exams and study guides to insider tips and tricks, this channel covers it all. The moderators are experienced ATCs themselves, so you can trust that the information provided is accurate and up-to-date. Join the ATC UEE PREPARATION channel today and take the first step towards achieving your dreams of working in the UEE airspace!

ATC UEE PREPARATION

06 Jan, 07:15


ዩትዩብ ላይ የጥሪ ማስታወቂያዎችን ስታዩ ቪድዮው የተለቀቀበትን ቀን ተመልከቱ 🙏

ATC UEE PREPARATION

05 Jan, 05:52


#EntranceExam #2017

የ2017 ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ ሁኔታ ከ9 - 12ኛ ክፍሎች እንዲሁም የ 8 ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከ7- 8ኛ ክፍሎች የሚሸፍን ይሆናል።

👉እያንዳንዱ ተማሪ በተማረበት የክፍል ደረጀ የተማረውን የተማሪ መጽሐፍን መሠረት አድርጐ ሊዘጋጅ ይገባል። ፈተናዎቹ ተማሪዎቹ የተማሩትን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ይሆናል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

02 Jan, 09:28


Wollo University Mid Exam schedule

ATC UEE PREPARATION

24 Dec, 10:54


አዲሱ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሜኑ

ATC UEE PREPARATION

21 Dec, 04:39


አዲሱ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የምግብ ሜኑ

ATC UEE PREPARATION

12 Dec, 20:02


#Update #MealMenu

ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመሳሳይ የተማሪዎች የምግብ ሜኑ ይፋ ተደርጓል‼️

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁሉም የመንግስት ዩንቨርስቲዎች ያስተላለፈው የተማሪዎች የምግብ ሜኑ መግለጫ 👇

<በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች የተመደበው ዕለታዊ የምግብ በጀት በየጊዜው እየጨመረ ያለውን የምግብ ዋጋ ንረት ሊሸፍን ባለመቻሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ጥናት በማካሄድ በጀቱ እንዲሻሻል ለመንግስት ጥያቄ በማቅረብ የተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ በጀት ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 (መቶ ብር) እንዲሆን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት በቁጥር መከ/0-721/1 በቀን 25/03/2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን አሳውቋል፡፡

በዚሁ መሠረት የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በወጥነት እንዲከናወን ሚኒስቴር መስሪ ቤታችን ከምግብ ተመን ማሻሻው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት 3 ገጽ አባሪ በማድረግ የላክን መሆኑን እየገለጽን ይህ የምግብ ሜኑ ዝቅተኛውን መስፈርት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን ተቋማት ከባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታን ከግምት ውስጥ በማስገባት በአንድ ተማሪ ሳምንታዊ ወጪው ከ700 (ሰባት መቶ) ብር ባልበለጠ መልኩ ስራ ላይ መዋል ያለበት መሆኑን አሳስባለሁ፡፡> (ሚንስትር ዴኤታው)

[የምግብ ሜኑውን ከምስሉ ይመልከቱ]

Click

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

12 Dec, 15:25


ለዘንድሮ ፍሬሽማን ናቹራል ተማሪዎች ብቻ 👂

@muedu

ATC UEE PREPARATION

08 Dec, 19:58


አንድ ባህርዳር የሚኖር ልጅ ይህን ምናባዊ የስራ ማስታወቂያ አይቶ በቴሌግራም apply ያደርግና ከጥቂት ቀናት በኋላ ለሱና አብረውት ላመለከቱ ጓደኞቹ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ተመርጣቹሃል የሚል መልዕክት ይደርሳቸውል።ከዚያም የስራ ምደባ ይባልና እሱና ጓደኞቹ የተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ ተመድባቹሃል ምደባችሁን ለማስቀየር የምትፈልጉ 2000ብር በመክፈል ማስቀየር ትችላላቹህ ይባላሉ።

የባህርዳሩ ልጅ ስራ አገኘሁ ብሎ በፕሌን አዲስ አበባ ይመጣና ወደ ተመደበበት ድሬደዋ ለመሄድ ትራንስፖርት ሲያማርጥ የተባለው ስራ ምናባዊ ብቻ እንደሆነ ይገባዋል....

አዲስ ተመራቂዎች ለስራ ካላቹህ ጉጉት የተነሳ የህጋዊ ሌቦች ኢላማ እየሆናቹህ ነው እና አትቸኩሉ‼️

የስራ ማስታወቂያ ከምን አይነት ምንጭ እንደሚገኝ ለዩ ቅድሚያ 👍

ATC UEE PREPARATION

08 Dec, 04:04


Freshman Mathematics (Social): https://www.youtube.com/playlist?list=PLmLB1GTouHXzZx-hMvZgpWWCMEp48Z0Mk

ATC UEE PREPARATION

08 Dec, 04:04


Freshman Mathematics Natural: https://www.youtube.com/playlist?list=PLmLB1GTouHXz39S7CAUmSLULjqFfgQjlv

ATC UEE PREPARATION

08 Dec, 04:04


General Physics Mid Exam: https://www.youtube.com/playlist?list=PLmLB1GTouHXx5z_Be18rsSOInF0zA5HDT

ATC UEE PREPARATION

07 Dec, 19:43


የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ተደረገ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ለገንዘብ ሚኒስቴር የፃፉት ደብዳቤ 👇

< ከመ/ቤታችሁ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 1/143/150/17 በተጻፈ ደብዳቤ አሁን በስራ ላይ ያለው የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ከወቅቱ የገበያ ዋጋ አኳያ ተማሪዎችን ለመመገብ በቂ ባለመሆኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት በማካሄድ የተመን ማሻሻያው እንዲፈቀድ መጠየቃችሁ ይታወሳል:: የቀረበውን የምግብ በጀት ተመን ማሻሻያ ጥናት ከወቅቱ የገበያ ዋጋና ከመንግሥት የመክፈል አቅም አኳያ በማየት የተማሪዎች የምግብ በጀት ተመን በቀን በአንድ ተማሪ የነፍስ ወከፍ ወጪ 100 ብር (አንድ መቶ ብር ) ሆኖ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲውል ተወስኗል።

በዚህም መሰረት የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የምግብ አቅርቦት በወጥነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲከናወን መስሪያ ቤታችሁ ከምግብ በጀት ተመን ማሻሻያው ጋር የተጣጣመ ስታንዳርድ የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ዩኒቨርስቲዎች አንዲጠቀሙበት እና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ክትትል እንድታደርጉ በጥብቅ አስታውቃለሁ፡፡ >


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

30 Nov, 17:52


ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ተማሪዎች በታዋቂዉ በሊሴ ገብረማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እድል የሚሰጠዉ ስምምነት ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ አደረጉ።

በኢትዮጵያ ከ 77 ዓመታት በላይ በመማር ማስተማር ዘርፉ ላይ የሚገኘዉ ታሪካዊዉ ትምህርት ቤት እንደሆነ የሚነገርለት ሊሴ ገብረማሪያም በአዲሱ አሰራር ከመላዉ ሀገሪቱ የሚመጡ ተማሪዎች መቀበል እንደሚጀምር ተገለፀ።

ይህ ስምምነት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ኖኤል ባሮት ጋር ተፈራርመዋል።

የፈረንሳይ የዉጪ ጉዲይ ሚኒስትሩ ጂያን ኖኤል የዚህን ስምምነት ዓላማ ሲናገሩ " ምንፈርመው ከ77 ዓመታት በፊት የተጀመረውን ሥራ ለማራዘም ያስችላል" ብለዋል ።

ሊሴ በአዲስ አበባ የሚገኝ የፈረንሳይ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት ሲሆን ትምህርት ቤቱ የተከፈተው እኤአ በ1947 መሆኑን የታሪክ ማህደሩ ያሳያል ። በዚህ ትምህርት ቤት ያለፉ ተማሪዎች በሀገሪቷ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ትልቅ ተፅዕኖ መፍጠር እንደቻሉ ይነገራል ።

ዛሬ የተደረገዉ ስምምነት አዲስ አሰራር እንደሆነ የተናገሩት ሚኒስትሩ በዚህም ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ተማሪዎች የሊሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀላቀሉ እድል የሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል ።

ይህም በሁለቱ ሀገራት ቅድሚያ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት ለሁሉም ተደራሽ እንደሚያደገዉ የገለፁ ሲሆን ስምምነቱ ሁለቱን ሀገሮቻችንን የሚያስተሳስረው አዲስ የመተማመን ግንኙነት መገለጫ ጭማር መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዉበታል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ነጻ የትምህርት እድሎችን ለመስጠት፣ እንዲሁም በሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት የስኮላር ሺፕ መርሃ ለማጠናከር ያስችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

ከፈረንሳይ መንግስት ጋር የተደረሰው ስምምነትም ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ የያዘችውን ዓላማ ከግብ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

30 Nov, 11:57


ሴት ልጃቸውን ለትዳር የጠየቀ ቻይናዊ እና የሀበሻ ቤተሰብ ቅፈላ ....

አሸማጋዩ ቻይና- " ...ልጆቹ ስለተዋደዱ ጉዳዩን ወደፊት ለማስኬድ ነው የመጣነው"

እናት- "ገቢው ምን ያህል ነው?"

አሸማጋዩ ቻይና-"በኢትዮጵያ ብር ሲመነዘር 93,000ብር ወርሃዊ ገቢ አለው።የራሱ መኪና እንዲሁም ቤትም አለው።"

እናት-"አግብቷል?"

አሸማጋዩ ቻይና- "ከዚህ በፊት አግብቶ ፈቷል"

እናት-"ልጅ አለው?"

አሸማጋዩ ቻይና-"ሁለት ልጆች አሉት"

እናት-በህጋዊ መንገድ ነው የተፋታው?"

አሸማጋዩ ቻይና-"አዎን። የፍቺ ሰርተፊኬት ይዘናል።"

እናት- "ልጃችንን አግብቶ ቻይና ከወሰዳት በኋላ ለቤተሰቦቿ ምን ያህል ተቆራጭ ያስባል?"

አሸማጋዩ ቻይና- "በወር 5000ብር ያስብላቹሃል"

እናት- 5000ብር በቂ አይደለም"(ሙሉ ቤተሰቧ ማጉረምረም ጀመሩ)

አሸማጋዩ ቻይና-"ከገቢው አንፃር ነው 5000ብር ..."

እናት-"በወር 40,000ብር አድርጉት"

አሸማጋዩ ቻይና- "40,000ብር የሚቻል አይደለም። 7000ብር እናድርግ"

እናት-"10,000ብር አድርጉት በቃ"

አሸማጋዩ ቻይና-"እሺ። ስለሚወዳት የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል።"

በቀጣይ ስለ ሰርጉ ወጪ ሂሳብ ይጀምሩና ቪዲዮው ይቋረጣል።

ቪዲዮውን ለምትፈልጉ 👇
https://www.facebook.com/share/v/19s4DTELx9/

ATC UEE PREPARATION

30 Nov, 05:50


ወሎ ዩንቨርሲቲ

ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ መቀየር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ከነገ አርብ (20/03/2017 _ 24/03/2017) ድረስ የ12ኛ ክፍል ውጤት ወይም የሪሜዳል ውጤታችሁን ከማመልከቻችህ ጋር በማያያዝ ፍሬሽማን ቢሮ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

28 Nov, 13:30


🔥

ATC UEE PREPARATION

27 Nov, 13:26


ጋሼን እናበረታታቸው 🙏

👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@mehreteabyhannes1952?feature=shared

ATC UEE PREPARATION

26 Nov, 10:00


Hawassa university

ATC UEE PREPARATION

18 Nov, 20:37


It doesn't matter how successful or unsuccessful you are right now. What matters is whether your habits are putting you on the path toward success. You should be far more concerned with your current trajectory than with your current results. If you're a millionaire but you spend more than you earn each month, then you're on a bad trajectory. If your spending habits don't change, it's not going to end well. Conversely, if you're broke, but you save a little bit every month, then you're on the path toward financial freedom-even if you're moving slower than you'd like.

📖 Atomic Habits

ATC UEE PREPARATION

17 Nov, 11:11


👆የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ለ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የዶርም ድልድል

ATC UEE PREPARATION

13 Nov, 10:17


ማስታወቂያ
በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም
የማታ መርሀ - ግብር ትምህርት ፈላጊ ተማሪዎች በሙሉ፡-
የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በ2ዐ16 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈትነው በትምህርት ሚኒስተር ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የወጣውን የማለፊያ ነጥብ የሚያሟሉ አመልካቾችን በማታ (Extension) መርሃ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በ2ዐ17 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም በማህበራዊ ሳይንስ (Social Science) እና በተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Science) የትምህርት መስኮች መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ከህዳር 04 ቀን 2017 ዓ/ም አስከ ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የመግቢያ መስፈርት
በ2ዐ16 ዓ.ም የ12 ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው በትምህርት ሚኒስቴር ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል የወጣውን የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፤
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፣
የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ
ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ
ሁለት 3×4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ
የማመልከቻ ክፍያ፤ 3ዐዐ.ዐዐ (ሶስት መቶ) ብር
የመመዝገቢያ ክፍያ፤ 1ዐዐ.ዐዐ (አንድ መቶ) ብር
የትምህርት ክፍያ፤ ለተፈጥሮ ሳይንስ 2,2ዐ0 (ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ብር) እና ለማህበራዊ ሳይንስ 1,80ዐ (አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር) ይዘው መቅረብ አለባቸው

የማመልከቻ ቦታ፤
ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ርቀትና ተከታታይ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድንቅነሽ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 12፡፡


ማሳሰቢያ፡-
በቂ የተማሪ ቁጥር ያላመለከተበት የትምህርት መስክ አይከፈትም፡፡

#ባሕርዳር_ዩኒቨርሲቲ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

12 Nov, 15:47


የገፅ ለገፅ ቲቶርያል ለምትፈልጉ ተማሪዎች

👉የፍራሽማን ማትስ እና ፊዚክስ ሁለቱንም ኮርስ በ200ብር አንድ ጊዜ ክፍያ
👉የሪሜዲያል ማትስ ለናቹራልም ለሶሻልም በ200ብር አንድ ጊዜ ክፍያ ቀርቦላቹሃል።


ቲቶርያሎቹ በሙሉ በቪድዮ ሲሆኑ ክፍያ በፈፀሙ ቅጽበት ሁሉም ቪዲዮዎች የተጫኑበት የቴሌግራም ቻናል ሊንክ ይላክላቹሃል።

ቪዲዮዎቹን የምትፈልጉ 👉@muedu

ATC UEE PREPARATION

08 Nov, 18:51


🎤VACANCY ANNOUNCEMENT

[TRAINEE CABIN CREW]

Ethiopian Airlines Group would like to invite qualified applicants for Trainee #Cabin_Crew position.

➡️REQUIRED EDUCATIONAL QUALIFICATION: A MINIMUM OF ETHIOPIAN UNIVERSITY ENTRANCE EXAM CERTIFICATE (EUEEC) WITH A MINIMUM 200 RESULT.

➡️AGE LIMIT: 19-30 YEARS’ OLD INCLUSIVE.

➡️HEIGHT: A MINIMUM OF 1.58 METER AND AN ARM RICH OF 212 CM FOR FEMALE AND A MINIMUM OF 1.70 METER FOR MALE.

➡️WEIGHT: PROPORTIONAL TO HEIGHT

➡️ENGLISH LANGUAGE PROFICIENCY: LEVEL III



🗓 REGISTRATION DATE: - NOVEMBER 18, 2024 – NOVEMBER 22, 2024


📍REGISTRATION PLACES/ LOCATIONS

👉ADDIS ABABA, ONLINE (APPLICATION LINK WILL BE UPDATED DURING THE APPLICATION PERIOD)

👉ASTU, ADAMA
👉GONDAR UNIVERSITY, GONDER
👉HAWASSA AIRPORT, HAWASSA
👉AMBO UNIVERSITY, AMBO
👉JIGJIGA UNIVERSITY, JIGJIGA
👉ARBAMINCH UNIVERSITY, ARBAMICH
👉JIMMA UNIVERSITY, JIMMA
👉ASSOSA UNIVERSITY, ASSOSA
👉MEKELLE UNIVERSITY, MEKELE
👉BAHIR DAR UNIVERSITY, BAHIR DAR
👉WOLLEGA UNIVERSITY, NEKEMETE
👉WOLLO UNIVERSITY, DESSIE
👉MEDA WELABU UNIVERSITY, ROBE
👉DIRE DAWA UNIVERSITY, DIRE DAWA
👉SEMERA UNIVERSITY, SEMERA
👉GAMBELLA UNIVERSITY, GAMBELLA
👉WOLKITE UNIVERSITY, WOLKITE


📌NB
MAKE SURE YOU FULFILL ALL THE ABOVE STATED QUALIFICATIONS.

DURING REGISTRATION, PLEASE ATTACH ORIGINAL SCAN COPY OF ALL YOUR SUPPORTING DOCUMENTS & EDUCATIONAL CREDENTIALS INCLUDING BUT NOT LIMITED TO:

8TH GRADE MINISTRY CARD & BIRTH CERTIFICATE

GRADE 12 CERTIFICATE

KEBELE ID CARD (BACK AND FORTH)


ለጥቆማ @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

07 Nov, 20:30


#𝑱𝒊𝒈𝒋𝒊𝒈𝒂𝑼𝒏𝒊𝒗𝒆𝒓𝒔𝒊𝒕𝒚

For 𝑵𝒆𝒘 𝑹𝒆𝒎𝒆𝒅𝒊𝒂𝒍 𝑷𝒓𝒐𝒈𝒓𝒂𝒎 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕𝒔!

በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባቹህ የሬሚዲያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ታህሳስ 01-03/2017 ዓ.ም. መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

📄 𝐏𝐥𝐞𝐚𝐬𝐞 𝐛𝐫𝐢𝐧𝐠 𝐭𝐡𝐞𝐬𝐞 𝐞𝐬𝐬𝐞𝐧𝐭𝐢𝐚𝐥 𝐝𝐨𝐜𝐮𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐢𝐭𝐞𝐦𝐬:
* Educational Documents: Original and photocopies of certificates from Grades 8 through 12.
* Photographs: Eight recent passport-sized photos.
* Personal Essentials: Blankets, bed sheets, and sportswear.

⚠️ 𝐈𝐦𝐩𝐨𝐫𝐭𝐚𝐧𝐭 𝐍𝐨𝐭𝐢𝐜𝐞: Only students who report within the specified dates will receive services from the University.

ለዘንድሮ ሬሜድያል ተማሪዎች 👇
https://t.me/ATC_EUEE/90
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

07 Nov, 20:30


#𝑱𝒊𝒈𝒋𝒊𝒈𝒂𝑼𝒏𝒊𝒗𝒆𝒓𝒔𝒊𝒕𝒚

For 𝑵𝒆𝒘 𝑭𝒓𝒆𝒔𝒉𝒎𝒂𝒏 𝑺𝒕𝒖𝒅𝒆𝒏𝒕𝒔!

በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባቹህ ፍሬሽማን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ህዳር 07-09/2017 ዓ.ም. መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።

📄 𝐏𝐥𝐞𝐚𝐬𝐞 𝐛𝐫𝐢𝐧𝐠 𝐭𝐡𝐞𝐬𝐞 𝐞𝐬𝐬𝐞𝐧𝐭𝐢𝐚𝐥 𝐝𝐨𝐜𝐮𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐚𝐧𝐝 𝐢𝐭𝐞𝐦𝐬:
* Educational Documents: Original and photocopies of certificates from Grades 8 through 12.
* Photographs: Eight recent passport-sized photos.
* Personal Essentials: Blankets, bed sheets, and sportswear.

⚠️ 𝐈𝐦𝐩𝐨𝐫𝐭𝐚𝐧𝐭 𝐍𝐨𝐭𝐢𝐜𝐞: Only students who report within the specified dates will receive services from the University.

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

04 Nov, 19:22


#HawassaUniversity

የጥሪ ማስታወቂያ


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች   የምዝገባ  ጊዜ ኀዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
• የማህበራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ:-

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

                   
                   
ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

04 Nov, 12:50


የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ምደባ ይፋ ተደረገ

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት የሚችሉ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስለዚህም ተማሪዎች፡-
Website: https://placement.ethernet.edu.et
Telegram: https://t.me/moestudentbot ላይ ምደባውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የሪሜዲያል ቲቶርያል ለምትፈልጉ 👇
https://t.me/ATC_EUEE/90


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

28 Oct, 08:37


📹እየተዝናናቹህ ብዙ የህይወት ልምድ የምታገኙበት ምርጥ ፖድካስት ልጋብዛቹህ

ይህ ሰው እናቱ በልጅነቱ አሜሪካ ሄዳ ከአያቱ ጋር በቅንጦት ያደገ ሲሆን እስከ 12 ኢትዮጵያ ውስጥ ከተማረ በኋላ የኮሌጅ ትምህርቱን የአሜሪካ ስኮላርሺፕ በማግኘት ተምሯል። የአሜሪካን ወታደር ሆኖም ብዙ መልካም ትውስታዎች አሳልፏል።ከውትድርና ህይወት በኋላም በፍቅር ታውሮ ካናዳ ድረስ በመሄድ የህይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ገብቷል። ከካናዳ ህይወቱ መልስ አሜሪካ ላይ ከማይሆኑ ሰዎች ጋር ጓደኛ ሆኖ ወንጀል ውስጥ በመግባቱ(ዕፅ ዝውውር) በኛ አቆጣጠር 1997 ላይ ከአሜሪካ deport ተደርጓል።<የዚህ ስህተት ፀፀት ከፊቱ ይነበባል😭>

🇺🇸ከአሜሪካ deport ከተደረገ ከ20 ምናምን አመታት በኋላ አሁንም ድረስ የአሜሪካ ወታደር ሲሰደብ ወይም የአሜሪካ ሰንደቅ ዓላማ ክብሩ ዝቅ ሲል ያመዋል።

ይህ ሰው አሜሪካ ላይ በአፍላ እድሜው ከዝነኞች ጋር እስከ ጥግ ተቀራርቧል።ጀርመን ላይ የአሜሪካ ወታደር ሆኖ ብዙ ቆይቷል። ኳታር በረሃ ላይ ሳዳምን ለመጣል ዘምቷል።ሳዑዲ ላይ በሳዑዲ ህግ እርምጃ ሲወሰድ ቆሞ አይቷል። አምስተርዳም ከተማ ላይ በአጭሩም ቢሆን ፏ ብሏል።ካናዳ አግብቶ ወልዶ ኋላም ተፋቶ ህይወትን አይቷል።

📌 ይህ ሰው ያሳለፋቸውን ታሪኮች የሚተርክበት መንገድ እጅጉን ማራኪ ሲሆን ሲበዛ ግልፅ እና ተጫዋች ነው።

የዚህ የ69 ዓመት ሰው ታሪክ ለወጣቶች በተለይም ውጭ ሀገር ለምትሄዱ ሰዎች በብዙ አስተማሪ ነው።

በመጨረሻም እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ....ምክር ምከር ብትባል የምትመክረው ምክር ምንድነው?

👉 ለጊዜው የከፋ ነገር ቢሆንም ቤተሰቦችህንም የሚያስከፋ ቢሆንም Be honest ከሁሉም ነገር በላይ እውነታውን ተናገር።

👉 ያለህን ነገር ስጥ። እንደ መስጠት ጥሩ ነገር የለም። ምክርም ይሁን ያለህን አንድ ዳቦ ማካፈል ይሁን ስጥ።

👉 በቀን ውስጥ ቢያንስ አንድ ሰው ለማሳቅ(ደስተኛ ለማድረግ) ሞክር።

👉 ከሰው የተቀበላችሁትን እቃ እንደነበረው አድርጋቹህ መልሱ። አታቆዩት።


ሙሉ ፖድካስቱን ለመስማት 👇
https://youtu.be/qIODzbIMq5o?feature=shared

ATC UEE PREPARATION

26 Oct, 20:12


😂#ተጠንቀቁ

ቴሌግራም inbox ላይ ከማንም ቢሆን ምስሉ ላይ ያለውን አምሳያ ሊንክ ከተላከላቹህ በፍፁም አትንኩ ‼️

ይህን መሰል ሊንኮችን ከነካቹህ የቴሌግራም አካውንታችሁን ታጣላቹህ። አካውንታችሁን ስታጡ ብዙ ፋይሎችን አንድ ላይ ታጣላቹህ። ከዚህም በላይ የቴሌግራም አካውንታቹህ በቫይረሱ ምክንያት ከቁጥጥራቹህ ውጭ በመሆን ለሁሉም contact መሰል ቫይረስ እናንተ እንደላካቹህ አድርጎ በመላክ የናንተ ሰዎች አካውንት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ይዳርጋል።

ይህን መሰል ሊንክ ከማንም ቢላክላቹህ ከፍታቹህ ወደ ውስጥ አትግቡ‼️

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

25 Oct, 03:34


#ተቀይሯል #Remedial

ከዚህ በፊት ለሪሚዲያል ተማሪዎች በተቋማት የሚሰጠው ውጤት 30% ሲሆን 70% ደግሞ የሚሰጠው ከት/ት ሚኒስቴር ነበር።

አሁን ግን ይህ አሠራር ተሻሽሎ 100% ከማዕከል(በትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጡ ምዘናዎች) በኩል እንዲሰጥ ተወስኗል።

ተማሪዎች በሚማሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው 30% የውጤት ምዘና  አሰጣጡ ወጥነት ስለሚጎድለው ይሄን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።

Remedial Mathematics Tutorial 👉 Click

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

24 Oct, 12:32


#ምደባ

የ2017 ዓ. ም የዪኒቨርሲቲ ምደባን ይመለከታል


በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

🙅‍♂️የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር አያስተናግድም‼️


የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች👇

🌐WEBSITE:
https://placement.ethernet.edu.et

TELEGRAM
https://t.me/moestudentbot


ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

22 Oct, 12:42


በኢፌዲሪ ትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ፈቃድ ያላቸው ዓለም አቀፍ እና የማህብረሰብ ት/ቤቶች ዝርዝር


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

21 Oct, 12:37


#ማስታወቂያ

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጻል።

በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ስለሚገለጽ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እናሳውቃለን።


(ትምህርት ሚኒስቴር)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

21 Oct, 10:21


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

⬇️

የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤



ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

19 Oct, 15:35


ማስታወቂያ
ከአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎቸ በሙሉ፣
በሚተርፉን ውስን የመኝታ ቦታዎች ላይ እንደየርቀታቸሁ ሁኔታ አይተን መኝታ ለመስጠት እንድንችል ለትምህርት በየተመደባችሁበት ግቢ ትራንስክብሪታችሁን/ ሌሎች ደጋፊ ሰነዶች ካሏችሁ transecript/ ጨምሮና በመያዝና አባሪ በማድረግ ከጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 15/2/2017 ዓ.ም ድረስ በየኮሌጃችሁ በግንባር በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ፡፡

ማሳሰቢያ: የመኝታ ምዝገባው የግል/ self-sponsorship አመልካቾችንም ይመለከታል፡፡
@addisababauniversityofficial

ATC UEE PREPARATION

18 Oct, 12:25


#TVT

የኢፌዴሪ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በዲግሪ ፕሮግራም ከታች ባሉት ፕሮግራሞች ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

1. Electrical/Electronics and ICT Faculty

👉Electrical Automation & Control Technology

👉Electronics and Communications Technology

👉ICT

2. Mechanical Technology Faculty

👉Automotive Technology

👉Manufacturing Technology

3. Civil Technology Faculty

👉Building Construction Technology

👉Road Construction Technology

👉Water Supply and Sanitation Technology

👉Surveying Technology

👉Architectural Design Technology

👉Wood Science Technology

4. Textile and Apparel Fashion Technology Faculty

👉Garment Technology

👉Textile Technology

👉Fashion Design Technology

👉Leather and Leather Products Technology

5. Agro-Processing Technology Faculty

👉Dairy Processing Technology

👉Fruit & Vegetable Processing Technology

👉 Meat Processing Technology


💥Application Requirements:

1. For First Degree Program: Applicants must fulfill the following requirements:

📌The applicant should be from the Natural Science Stream.

📌The applicant should have achieved a pass mark (50%) in the University entrance exam results in the year 2015 E.C. or 2016 E.C.

📌Alternatively, the applicant should have completed a Remedial program in the year 2014 or 2015 E.C.

⚡️Training will be conducted in Addis Ababa, with additional language training in Chinese and Korean to enhance students global communication skills.

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

16 Oct, 16:56


ማስታወቂያ ለግል አቅም ማሻሻያ (Private Remedial) ትምህርት ፈላጊዎች:-

ደባርቅ ዩኒቨርስቲ በ2016 ዓ.ም በተሰጠው ሃገር አቀፍ ፈተና 155 ከ 500፣ 186 ከ600፣ 2017 ከ700 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያመጡ አመልካቾን በተፈጥሮ ሳይንስ እና ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የአቅም መሻሻያ ፕሮገራም ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከጥቅምት 11-29/ 2017 ዓ.ም ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ይገልፃል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

14 Oct, 20:15


ጌጅ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለ2017 የትምህርት ዘመን ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ።

ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ ዛሬ በስሩ የሚተዳደሩ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎች ተቋማቱን አስመልክቱ ለሚዲያ ተቋማት መግለጫ ሰጥቷል።

ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ በስሩ ከያዛቸው ተቋማት መካከል:- ጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ሶፍትኔት የሥልጠና ማዕከል፣ ኤል ኤም ኢንተርናሽናል ሆቴል ስኩል፣ ግሬስ ኮሌጅ፣ ጌጅ አካዳሚ፣ MGK printing enterprise፣ AGET (African Global education & Technology )፣ AIHD (African international humanitarian development )፣ SMS trading plc ሲሆኑ በነዚህ ተቋማት ለበርካታ ዜጎች የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ እንደቆየ ተገልጿል።

በ2017 የትምህርት ዘመን የክፍያ ቅናሽ መደረጉን የጌጅ ሰርቪስና ትሬዲንግ ሃውስ ፔኤልሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞገስ ግርማ አስታውቋል በዚህ መሰረት:- ለቴክኒክ እና ሞያ ወራዊ ክፍያ 800 ብር የነበረው 600 ብር ሆኗል፣ ለመጀመሪያ ዲግሪ 900 ብር የነበረው 700 ብር፣ ለሁለተኛ ዲግሪ 1800 ብር የነበረው ወደ 1400 ብር መቀነሱን አቶ ሞገስ በመግለጫቸው አስታውቋል።

በተለያዩ ምክንያት መማር እየፈለጉ በአቅም ምክንያት መማር ያልቻሉ ዜጎች እስከ 50% ቅናሽ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ በመስጠት በኮሌጃቸው እያስተማሩ እንደሆነ እና ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተነግሯል።

#FastMereja
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

ATC UEE PREPARATION

14 Oct, 10:26


የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ለምትፈልጉ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ፤

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም. በግል የሪሚዲያል ትም/ት ተምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር የሚያስችል ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በወሎ ዩኒቨርሲቲና በሌሎች የግልና የመንግስት የትም/ት ተቋማት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም. ድረስ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ደሴ ግቢ ብሎክ 20 ሙሉ መረጃችሁን ይዛችሁ በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሣውቃለን፡፡

የመግቢያ መስፈርት፡-

✓ በትም/ት ሚኒስቴር የሚሰላ (7ዐ %) እና በተማራችሁበት ትም/ት ተቋም የሚሰላ (3ዐ %) በድምሩ 5ዐ% እና በላይ ውጤት ያስመዘገባቹህ፡፡

[የተከታታይ ርቀት ትምህርት ዳይሬክቶሬት]


ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news