Wcu main campus @wachemoo Channel on Telegram

Wcu main campus

@wachemoo


Wcu main campus (English)

Are you a student, faculty member, or just interested in what's happening on the main campus of West Coast University? Look no further than the 'Wcu main campus' Telegram channel, also known as '@wachemoo'! This channel is the go-to place for all information, updates, events, and announcements related to the main campus. Whether you are looking for details on upcoming lectures, campus events, student organizations, or important announcements from the administration, this channel has you covered. With regular updates and real-time information, you can stay connected and informed about everything happening on the WCU main campus. The 'Wcu main campus' channel is not just for students and faculty members; it's also a great resource for anyone interested in the university and its activities. From virtual campus tours to highlights of student achievements, this channel offers a glimpse into the vibrant and engaging community at West Coast University. Joining the 'Wcu main campus' Telegram channel is easy – simply search for '@wachemoo' on Telegram and hit the 'join' button. Once you're a member, you'll have access to exclusive content, behind-the-scenes updates, and the latest news from the main campus. Don't miss out on this valuable resource for all things related to the WCU main campus. Join the 'Wcu main campus' Telegram channel today and stay connected with the heart of West Coast University!

Wcu main campus

18 Jul, 15:40


መልካም ዜና

የመዉጫ ፈተና ያለፉም ያላላፉም ተመራቂ ተማሪዎች ሐሙስ 13/11/2015 ዓ.ም በሚደረገው የምርቃ መርሃ ግብር ለይ እንድሳተፉ የተወሰነ በመሆኑ ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ።

Congratulations!

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

Wcu main campus

16 Jul, 11:37


የመውጫ ፈተና ውጤት መታየት ጀመረ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን በ " ኦላን ላይን " ማየት መጀመራቸውን ማረጋገጥ ችሏል።

ምንም እንኳን ትምህርት ሚኒስቴር ውጤት መታየት የሚጀምረው ከማታ ጀምሮ መሆኑን ቢገልጽም ከዚህ ሰዓት አንስቶ ተማሪዎችን የፈተናውን ውጤት እያዩ መሆኑን አረጋግጠናል።

የመውጫ ፈተና ውጤት የሚታየው በ result.ethernet.edu.et ላይ Username እና Password በማስገባት ነው።

ድረገፁ ተመራቂዎች ፈተናውን ማለፍ አለማለፋቸውን ካገኙት ውጤት ጋር Pass / fail እያለ ያሳውቃቸዋል።

Wcu main campus

16 Jul, 02:44


ተማሪዎችየመዉጫ ፈተና ውጤታችሁን ከእሑድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣችሁን Username በመጠቀም በዚህ ሊንክ በ https://result.ethernet.edu.et በመግባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን ።

Wcu main campus

16 Jul, 02:44


https://result.ethernet.edu.et

Wcu main campus

04 Jul, 07:48


@wachemoo

Wcu main campus

02 Jul, 16:03


Exam rule for Remedial Students

Wcu main campus

02 Jul, 16:03


Good Luck!

Wcu main campus

30 Jun, 17:23


@wachemoo

Wcu main campus

30 Jun, 17:23


#MoE

161 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጀመሪያ ዲግሪ ዕጩ ተመራቂዎቻቸው የመውጫ ፈተና ይሰጣሉ።

በተጨማሪም 44 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ በትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ ኢዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

በዚህም 95,755 ተማሪዎች ከግል እና 74,706 ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በድምሩ 170,461 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ ብለዋል።

ተማሪዎች ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ በሚባሉት ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተናው መዘጋጀቱን ኃላፊው ጠቁመዋል።

በመውጫ ፈተና አዘገጃጀት መመሪያ መሰረት ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች ዝግጁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና በቀጣይ በድጋሜ እንደሚፈተኑ ገልጸዋል። #ኢዜአ
@wachemoo

Wcu main campus

28 Jun, 03:00


ለመላም የእስልምና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1444ው የዒድ አል-አድሀ(አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

መልካም የዒድ አል- አድሃ (አረፋ) በዓል

ዒድ ሙባረክ
@wachemoo

Wcu main campus

14 Jun, 16:31


4_5787204578634108844.xls
Tentative 2015 E.C Exit Exam schedule
@wachemoo

Wcu main campus

19 May, 04:24


የ2015 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ለመስጠት ማቀዱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
*******

በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመ
ዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን እና ባለፉት ዓመታት የህግ መውጫ ፈተና ወስደው የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ ብቻ ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ 13 ባሉት ቀናት ሰጥቶ ለማጠናቀቅ መወሰኑን መስሪያ ቤቱ ያሳወቀ ሲሆን፤

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ከፍል ማጠቃለያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 30 የሚሰጥ ሆኖ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከሐምሌ 15 ቀን ጀምሮ ለዚሁ ስራ ብቻ ዝግጁ እንዲሆኑ እንዲሁም፤

በ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍልን አጠናቀው ፈተና በመውሰድ በልዩ ሁኔታ የሬሜዲያል ኘሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ተማሪዎች ለአንድ ሴሚስተር የተሰጠው ትምህርት በማዕከል የጋራ ፈተና ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ፤ ተቋማት ፈተናውን የማስተዳደር ውጤት የመግለፅና በ2016 ፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ ሆነው የተገኙት (ማለትም በተቋማት የውስጥ ፈተና 50 ከመቶ፣ በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና 50 ከመቶ) ተደምሮ 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡቱን እንዲያሳወቁ፣ ይህ አጠቃላይ ሂደት እስከ ሰኔ 30 ቀን ድረስ እንዲጠናቀቅ ብሎም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም የትምህርት ተቋማት የትምህርት የጊዜ ሰሌዳቸውን (Academic Calendar) በዚህ ማዕቀፍ ያስተካክሉ ዘንድ ትምህርት ሚኔስቴር ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በመሆኑም ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም መሰረት ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅት እንድታደርጉ እየጠየቅን ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ መሆኑን እንገልፃለን።


@wachemoo

Wcu main campus

21 Apr, 06:17


የ1 ሺህ 4 መቶ 44ኛው የኢድ-አል ፈጥር በዓል በማስመልከት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የእንኳን  አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!!

ለ1 ሺህ 4 መቶ 44ኛው የኢድ-አል ፈጥር በዓል በማስመልከት  የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ የእንኳን  አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንኳን በ2015 ዓ/ም የሚከበረውን  ለ1 ሺህ አራት መቶ 44ኛው ኢድ-አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያልኩ  በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ እንዲሆን እመኛለሁ።

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በፆም ወቅት  የአላህ ትዕዛዝ በማክበር ያሳየውን መልካም ተግባር በሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እንደሚያሳይ ይጠበቃል።

በሀይማኖቱ አስተምሮ መሠረት ጾም የተራቡና የተቸገሩ ሰዎችን ሕይወት የሚካፈሉበትና ዓመቱን ሙሉ በችግርና በሰቆቃ የሚያሳልፉትን ድሆች ሁኔታ የሚያስታውሱበት የአምልኮ ዘርፍ   መሆኑን ታላቁ ቁርአን ይናገራል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ በፆም ወቅት በጋራ የአፍጥር ስነስርዓት ማካሄድ እና በአላህ ትዕዛዝ  መጓዝ የሚያስተምረው ትልቁ ምስክር ከአላህ በርከት መቀበልን፣ በጋራ መቆም እንዲሁም ለድሆች ማሰብን ያስተምራል ብዬ አስባለሁ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አይነት ግጭቶችና አለመግባባትን በማስተናገድ ዜጎችን እጅግ አዋራጅ ከሆነው ድህነት ጋር እንድንኖር  እና አልፎ አልፎ የኃያላን ስውር እጆች እንድናይ እያደረገ ይገኛል።

በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ሁላችንም በጋራ በመቆም የእምነቱ  ተከታዮች በፆም ያገኛችሁትን ፅናት እና ለአላማ የመኖር ትርጉም ይዘን ለሀገራችን ብልፅግና እና ሰላም ዘብ  መቆም ይጠበቅብናል።

በእስልምና ሃይማኖት መሠረት ፆሙ ከሚያስገኛቸው ትሩፋቶች መከከል በአላህ አምኖ፣ ትዕዛዙንም አክብሮ፣ በረመዳን ትሩፋት ዙሪያ የተላለፉ ጉዳዮችን እውነት ብሎ ተቀብሎ እንዲሁም አላህ ዘንድ የሚያገኘውን ምንዳ በመከጀል ረመዳንን የጾመ፣ ቀደም ሲል የሰራው ወንጀሉ ይማርለታል፡፡

ምስጥሩ ይቅር በመባባልና በይቅርታ ማመን ሲሆን ሀገራችንን በይቅርታ  መሻገር እና በዓሉን ለመክበር ያልቻሉ ወገኖቻችንን በማሰብ ልሆን ይገባል እያልኩ  ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን፣የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብና ተማሪዎች እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

መልካም የኢድ-አል ፈጥር
ኢድ ሙባረክ!

ዶ/ር ሀብታሙ አበበ
የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

ሚያዝያ 2015 ዓ.ም
@wachemoo

Wcu main campus

16 Apr, 15:09


@wachemoo

3,480

subscribers

185

photos

3

videos