VICTORY OFFICIAL @victorytutor_7 Channel on Telegram

VICTORY OFFICIAL

@victorytutor_7


የማያልቁ ገፆች በአጭር ተተንትነው
ረዥም ፅሁፎች በአጭር ተበትነው
በቀላል አረዳድ በቀላል ሁኔታ
ብዙ ጥያቄዎች ከነመልስ በተርታ
ውጤትን ለመስቀል ከልብ ከፈለጉ
የ victoryን tutor አሁን join ያርጉ።

ለመመዝገብ
@victoryacademy_Bot

ለበለጠ መረጃ @VICTORY_TUTOR_TEAMS ላይ ያናግሩን

የተማሪ አስተያየት=> https://t.me/victorystcom_7

VICTORY OFFICIAL (Amharic)

በቀላል ስልክቺት ማህበረሰብ በአጭርም ላይ ነው። ይሔን በአጭርም ለበለጠ መረጃን እና አስተያየትን ለመመልከት በትምህርት ለመስራት እና ድምር ያግኙ። VICTORY OFFICIAL የእንስሳትን አሁን ታዘነናላችሁ። የተዘጋጀም እና የተሞላችሁ አስረድተናል። ለምን መረጣችሁ እና ለማህበረሰብዎ እፈልጋለሁ። የበለጠ መረጃን @VICTORY_TUTOR_TEAMS ላይ ያናግሩ።

VICTORY OFFICIAL

08 Jan, 12:37


VICTORY OFFICIAL pinned «💎Victory Tutorial Support @VICTORY_TUTOR_TEAMS ☎️0914633658»

VICTORY OFFICIAL

08 Jan, 12:37


💎Victory Tutorial Support
@VICTORY_TUTOR_TEAMS
☎️0914633658

VICTORY OFFICIAL

08 Jan, 10:16


💔መንቀልና ❤️መትከል

በልጁ ጸባይ ደስ ያልተሰኘው አባት ወደ አንድ ሽማግሌ ይወስደውና። አባባ እንደው ይሄ ልጅ አስቸግሮኛል ይቆጡት ብሎ ሰጣቸው። መቆጣትማ ተገቢ አይደለም ልጄ ጨዋ ነው ምናምን ብለው አባብለው ወደቤታቸው ወሰዱትና ምግብ እንዲበላና እንዲጫወት አደረጉት።

ከተረጋጋ በኋላ ወደ ቤታቸው ጀርባ ወሰዱትና እፅዋቶችን ያሳዩት ጀመር። እሱም ደስ እያለው ያደንቃል።

እስኪ ይችን ንቀላት አሉት መሬት ላይ ተለጥፋ ወደበቀለችው እፅዋት እያሳዩት።
እሱም በሁለት ጣቱ ብቻ ነቀላት። ትንሽ ሄዱና እስኪ ይችንም ንቀላት አሉት ከመጀመሪያው ከፍ ያለ ስለነበር በሙሉ ጣቶቹን ተጠቅሞ ነቀለው። አሁንም እየተራመዱ እስኪ ይችን ንቀላት አሉት። ያሁኑ መካከለኛ ቁመት ያለው ስለነበር በሁለት እጆቹ ነቀለው። በመጨረሻም ወደ ትልቁ ዛፍ እየጠቆሙ እስኪ ያንን ንቀለው አሉት። እሱም እንዳያዩት ሳቅ ብሎ፣ ስለታዘዘ ብቻ ሄደና ለመንቀል ሞከረ።

ይሄኛውን ልነቅለው አልቻልኩም አላቸው። አየህ መጥፎ ፀባይም ልክ እንደዚህ ነው። ልጅ እያለህ በቀላሉ ልታቆማቸው ትችላለህ። እድሜህ ከገፋ በኋላ ግን ለማቆም እጅግ ትቸገራለህ። ስለዚህ ልጄ ካሁኑ መጥፎ ፀባይህን ተወው።

ልጄ በተቃራኒው ደግሞ አሁን ጀምረህ ጥሩ ፀባይን ከተለማመድክ እስከመጨረሻው ያንተ ባህርይ ይሆናል። ምክንያቱም ይሄ የምታየው ትልቁ ዛፍ እንደዚህ ሊሆን የቻለው በአንድ ቀን አይደለም። ሁለት ዓመት ሙሉ ተንከባክበን ነው።

ለዚህም ነው መንቀልና መትከል ያልኩህ። በል ልጄ አሁን ወደ አባትህ ተመለስ አለው። ልጁም ከዚያ ቀን ጀምሮ ጥሩ ፀባይ ያለው ሆነ።

እናንተስ? መንቀልና መትከል አይገባንም ትላላችሁ?

መዘናጋትን፣ systematic ያልሆነ የአጠናን ዘዴን፣ ሃሳብን ሰብስቦ ማንበብ አለመቻልን ፣ የመሳሰሉ መጥፎ ልማዳችሁን ሳያድጉና ትልቅ ዛፍ ሳይሆኑ ብትነቅሏቸው የተሻለ ለውጥ ማምጣት የምትችሉ አይመስላችሁም?

ይልቁንም በprogram ማንበብን፣ ለወላጆቻችሁ መታዘዝን፣ ሀሳቡን እየተረዱና ሀሳብን ሰብስቦ ማጥናት የመሳሰሉ ጥሩ ልምዶችን ካሁኑ ውጤታማነትን ያጎናፅፋችኋል

ጊቢ ከሚያጋጥሙ ነገሮች አንዱ የመጀመሪያውን semester (freshman) ሁሉም በ tension ሌላው ሲያጠና እያጠና አሪፍ ውጤት ይሰራል። ሁለት ዓመት፣ ሶስት ዓመት እየሆኑ ሲመጡ ግን ውጤታቸው ይቀንሳል። ለምን? ሲባሉ ፦ "field ከመረጥክ በኋላ እኮ እንደ freshman አይሰራም" ይሉሀል።

መልሱ ግን ያን ጥሩ habit (ልማድ) የተከሉት ጊቢ እንደገቡ ስለነበረ፣ ለመንቀልም ስለማያስቸግር ነው። ነገር ግን እናንተ ከአሁኑ ጥሩውን ከተከላችሁት እስከ መጨረሻ ዓመታችሁ ጥሩ ውጤት ይኖራችኋል።

ለዚያም እኮ ነው አንዳንዶቹ ሲመረቁ በጣም በከፍተኛ ማዕረግ 4.00፣ 3.91 የመሳሰሉ ውጤቶችን የሚያመጡት።

እንግዲህ እናንተም የምትነቅሏቸውን እና የምትተክሏቸውን habit(ልምዶች) ዘርዝሯቸውና 💔የመንቀል እና መትከል strategy-ን ተከተሉ።

መልካም ቀን

VICTORY OFFICIAL

07 Jan, 18:56


ለ2ቱ ተሳታፊዎች ካርዱን ልከንላቸዋል

በዚህ ውድድር የተሳተፋችሁ በርካቶች ናችሁ ለመለየትም ተግዳሮት ገጥሞን የነበር ሲሆን በዚህም በተለያዩ መስፈርቶች አሸናፊዎቹን ልንመርጥ ችለናል

🦋በዚህም ቢያንስ ከ10 በላይ ለሚሆኑ ግሩፖች share ያደረጉትን

🦋መልዕክቱን በትክክልም እንዲደርስ ለተፈለጉት ትክክለኛ ግሩፖች የላኩትን

🦋እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተከፈቱ ግሩፖች ላይ ብቻ ያላኩትን መርጠን አውጥተን 2 ተሸላሚዎችን ለይተናል

እንዲሁም ተጨማሪ 2 ተሸላሚዎችን በተሳታፊነታቸው የማበረታቻ ሽልማት አበርክተንላቸዋል

VICTORY OFFICIAL

07 Jan, 17:11


አንዱ ተሸላሚ የቪክትሪን ቱቶሪያል በነፃ የተቀላቀለ ሲሆን
2ተኛው ተሸላሚ ግን የኛ ተማሪ ስለሆነ 400ብር አስገብተንለታል

VICTORY OFFICIAL

07 Jan, 16:38


ሰሞኑን ባዘጋጀነው ውድድር በርካታ ተማሪዎች ተሳትፋችኋል ነገር ግን አብዛኞቻችሁ share ያደረጋችሁት ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተብለው ለተከፈቱ ግሩፖች ነው።

በዚህም ውድድር ሁለት ተሳታፊዎች ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተብለው ለተከፈቱ ግሩፖች share በማድረጋቸው በአንደኝነት እና በሁለተኝነት ያጠናቀቁ ሲሆን

በተጨማሪ ደግሞ ከተሳታፊዎች ውስጥ 2 ተማሪዎችን መርጠን ለእያንዳንዳቸው የ50 ብር ካርድ የምንሸልማቸው ይሆናል

1️⃣@AMBESSA2024
2️⃣
@Abu8014

3️⃣
@blntbp
4️⃣
@Firaolu

ሽልማቱ ከምሽቱ 2ሰዐት ላይ የሚከናወን ይሆናል

VICTORY OFFICIAL

02 Jan, 17:31


ትክክለኛው መልስ ይሄን ይመስላል
.
.
.
ከቪክትሪ ቱቶሪያል የተወሰደ

VICTORY OFFICIAL

02 Jan, 15:15


እስከ ማታ ሞክሯት

VICTORY OFFICIAL

02 Jan, 11:37


ለኢንትራንስ ዝግጅት የጀመርሽው መቼ ነበር?

VICTORY OFFICIAL

01 Jan, 16:41


ብዙ ተማሪዎች ትኩረት የማጣት እና የመሰላቸት ስሜት በብዙ እየፈተናቸው ይገኛል እና ይህንን ችግር በምን አይነት መንገድ የፈቱታል ብለሽ ታስቢያለሽ?

VICTORY OFFICIAL

01 Jan, 12:07


ዝግጅት በምታደርጊበት ወቅት ችግር የሆኑብሽ ነገሮች ነበሩ? ካሉስ በምን አይነት መንገድ እነዛን ችግሮች ፈታሻቸው?

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 17:36


አሁን ላይ ያሉ ተማሪዎች በምን አይነት መንገድ ዝግጅት ቢያደርጉ ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ ?

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 17:03


ካሁን ጥናት ብንጀምር እንደርሳለን ወይ?

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 16:57


Entrance ይህን አይነት አሪፍ ውጤት እንድታመጪ ያስቻለሽ በምን አይነት መልኩ ዝግጅት ማድረግሽ ነው?  ምን አይነት የጥናት ስልቶችንስ ትጠቀሚ ነበር?

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 16:57


እሁድ ከብርክታዊት ጋር በነበረን live program የተነሱትን ሀሳቦች በ10 voice ከፋፍለን አዘጋጅተንላችኋል

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 16:56


የጥያቄው ትክክለኛ መልስ ከነ ማብራሪያው

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 12:18


ይህን የኢንትራንስ ጥያቄ ሞክሩት

VICTORY OFFICIAL

31 Dec, 09:27


https://t.me/VICTORY_TUTOR_TEAMS/s/47

VICTORY OFFICIAL

29 Dec, 18:17


Live stream finished (1 hour)

VICTORY OFFICIAL

29 Dec, 16:25


https://t.me/VictoryTutor_7?livestream=a69534d0549ee2bd0d

VICTORY OFFICIAL

29 Dec, 16:21


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

29 Dec, 16:00


Live stream scheduled for

VICTORY OFFICIAL

29 Dec, 15:00


ዛሬ ማታ 1ሰዐት ከተማሪ ብሩክታዊት ጋር live ቆይታ ይኖረናል። በዚህም በ2016 የነበራትን የኢንትራንስ ተሞክሮ የምታካፍለን ይሆናል።

በተጨማሪም ከኢንትራንስ ዝግጅት ጋር በተገናኘ እንድንጠይቃት የምትፈልጉትን ጥያቄዎች comment ላይ አስቀምጡልን

ብዙ የምትማሩበት ፕሮግራም ስለሆነ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

VICTORY OFFICIAL

25 Dec, 17:27


ዛሬ የሰጠናችሁ ጥያቄ ለተማሪዎቻችን ካዘጋጀነው የ5አመት የኢንትራንስ ጥያቄ ከነ ተብራራ መልሶቻቸው ውስጥ ከ 2012 UEE የተወሰደ ሲሆን አብዛኞቻቹ መልሱን በትክክል አግኝታችሁታል።👏👏👏

እንዲሁም የ25% ቅናሹ ሊጠናቀቅ 2 ቀን ብቻ ስለቀረው የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ እንጋብዛለን

ስለ ቪክትሪ ቱቶሪያል መረጃ ለመጠየቅ👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

VICTORY OFFICIAL

25 Dec, 15:42


እስቲ እቺን የኢንትራንስ ጥያቄ ሞክሯት

VICTORY OFFICIAL

22 Dec, 17:16


⚡️Victory Tutorial⚡️

🔥ይሄ ዕድል እንዳያመልጣችሁ 🔥

‼️ 3ኛ ዙር ምዝገባ አጠናቀን 4ኛ ዙር ምዝገባ ጀምረናል
(በ25% ቅናሽ) ለመጀመሪያ 200 ተመዝጋቢ ተማሪዎች ብቻ የምንሰጠው እድል ስለሆነ ከዛሬ ጀምሮ እስከ አርብ መመዝገብ የምትችሉ ይሆናል።

‼️ማሳሰቢያ: ይሄ ዕድል ለ 200 ተማሪዎች ብቻ ነው ከዛ ቡኃላ ለምትመዘገቡ ተማሪዎች ግን ክፍያው ይጨምራል!

🔥እስካሁን ያልጀመራችሁ ትምህርቶቹ ሳይደራረብባችሁ  ቀድማችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን🙏

በኢትዮጲያ ቱቶሪያል ከሚሰጡት ውስጥ ትምህርት የሚሰጥበትን መንገድ sample የሚያሳይ እና ክፍያውን ውድ አድርጎ ጥቂት አቅም ያላቸውን ተማሪዎች ለፈተና ከማብቃት ይልቅ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ ማንኛውም smart phone ያለው ሰው መክፈል በሚችለው ዋጋ ሁሉንም ተማሪዎች ያሳተፈ እንዲሆን በማሰብ በአሁን ሰዐት ከ1000 በላይ የ12ኛ እና ሬሚዲያል ተማሪዎችን ስትራቴጂካል በሆነ መንገድ ለፈተና ብቁ እያደረገ የሚገኝ ብቸኛው ቱቶሪያል Victory ነው።

Sample ለማየት ፣ መረጃ ለመጠየቅ እንዲሁም ለመመዝገብ 👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

VICTORY OFFICIAL

21 Dec, 16:34


🎉 Welcome to Victory Academy

ከተማሪዎቻችን የተሰጡ አስተያየቶች👇
https://t.me/victorystcom_7

ስለ Victory academy አጠቃላይ መረጃ
🌟የኢንትራንስ ተፈታኞች እንዲሁም የ 11ኛ ክፍል Natural science ተማሪዎች ቪክትሪን ስትጠቀሙ የምታገኟቸው የትምህርት አይነቶች

📌English , Maths , Physics Chemistry , Biology 

📌English , Maths , Economics , Geography , History  ናቸው።

🌟የትምህርቶቹ አወቃቀር
ኢንትራስ ከ 600 በላይ ባመጡ ተማሪዎች እና መምህራን የሰፊ ጊዜ ጥናት በማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ካላቸው ልምድ እና ከሌሎችም መረጃዎችን በመሰብሰብ ትምህርቶቹ ከ9-12ኛ ክፍል በሚከተለው መንገድ ተዋቅረዋል።

1️⃣ኢንትራንስ ተኮር(entrance targeted technique)፦ ይህ ማለት በኢንትራንስ ላይ ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን እና በዩኒቨርሲቲም ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ምዕራፎችን በማውጣት ተማሪዎች የተወሰኑ ምዕራፎችን በምንበብ ብቻ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ነው።

በዚህ መንገድ(ስልት) በተለይም ኢንትራንስ 3 እና 2 ወር ሲቀራቸው አንብበው የገቡ ልጆች ከማለፍ አልፈው ለማመን የሚከብዱ ውጤቶችን ሲያመጡ ያየንበት እና ልጆችም የመሰከሩለት መንገድ ነው።

2️⃣ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማካተት(Marging and Integration technique) :- ይህ አይነቱ ስልት በተለያየ ክፍል ላይ ያሉ ምዕራፎች ሆነው ነገር ግን ተመሳሳይ (አንድ አይነት) ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማድረግ ከቀላሉ ወደ ከባዱ በመሄድ አያይዞ መስጠት ነው። በዚህ የማቀናጀት ሂደት ውስጥ ተማሪው በትንሹ ሁለት ምዕራፎችን ሳያውቀው እና ሳይሰለቸው ይጨርሳል።

ለምሳሌ፦ የፊዚክስ(Physics) እና ኬሚስትሪ(Chemistry) ትምህርቶች አብዛኛው ምዕራፎች በዚህ አይነቱ ውጤታማ ስልት የተዘጋጁ ናቸው።

3️⃣በአንድ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምዕራፎችን በማካተት (Inclusion technique):- ይህኛው ስልት በትንሽ ልፋት ፣ ብዙ ምዕራፎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተፈትኖ የቀረበ ግሩም ስልት ሲሆን በዚኛው ስልት ተማሪዎች አንድ ሰፋ ያለ ምዕራፍ ያነበቡ ቢመስላቸውም በውስጡ ግን ከ 5-7 የሚጠኑ በተለያዩ ክፍሎች በዋናው መፅሃፎቻቸው የተቀመጡ ምዕራፎችን የሚያነቡ ይሆናል።

በትንሽ ጊዜ ብዙ እና ሰፊ የነበሩ ምዕራፎችን ያለ ሃሳብ(concept) መጎራረድ በማንበብ ለትልቅ ውጤት ያበቃቸዋል።

4️⃣ከመሰረቱ በመጀመር(Starting from the basics technique)፦ በዚህ ስልት ከባባድ ለሚባሉ ምዕራፎች እንደ ግብዐት የሚያገለግሉ ነገር ግን ቀላል ሆነው ሸዋጅ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን ምዕራፎችን ጥናት በማድረግ ተዘጋጅቷል።

በተለይም የኢንትራንስ ጥያቄዎች ቀላል እና ሸዋጅ ከመሆናቸው አንፃር ትኩረት ተሰጥቶበታል።  

5️⃣ከባድ ፣ ሰፊ እና ጥልቅ ሃሳብ ያላቸውን ምዕራፎች በማካተት(Difficult, vast and deep chapters technique):- እንደ derivative ,integration , Genetics, Chemical bonding, rotational motion , Electrostatics እና የመሳሰሉትን ምዕራፎች በውስጣቸው ሌሎች ብዙ ምዕራፎችን እንደ ግብዐትነት የያዙ እና ጥልቅ እንዲሁም ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸው በመሆኑ በእኛ የትምህርት አሰጣጥ ላይ አካተነዋል። 


       🌟የትምህርት አሰጣጥ
እንደ ቪክትሪ በዋነኝነት የምናምነው የሚሰጡት ትምህርቶች ሳይሆን ትምህርቶቹ የሚሰጡባቸው መንገዶች የተማሪዎች ውጤት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለን እናምናለን።

በመሆኑም ከሰፊ ጊዜ ጥናት በኋላ ትምህርቶቹን በብዙ ውጤታማ እና ባልተለመደ መንገዶች አዘጋጅተነዋል።

1️⃣ልቦለዳዊ እና አዝናኝ በሆነ መንገድ ፦ አንድ ተማሪ 300 ገፅ ያለውን ልቦለድ መፀሀፍ በ ቀናት ሲጨርስ በሌላ በኩል 300 ገፅ ያለውን ትምህርታዊ መፅሃፍ ወራት እንዲፈጅበት የሚያደርገው ዋነኛው ልዩነት ልቦለዱ ሲዘጋጅ ምስል ከሳች ፣ ልብ አንጠልጣይ፣ ያልተለመዱ ቋንቋዎችን በመጠቀሙ እና በሳቅ የተሞላ አዝናኝ ጨዋታን በመፍጠር ነው።

እኛ ትምህርቶቹን ስናዘጋጅ በዚህ ስልት መሰረት በማዘጋጀት ብዙ ተማሪዎች እኛጋ እየተሳቀቁ ሳይሆን እየሳቁ በቀላሉ ትምህርቶቹን እንዲጨርሱ አስችለናቸዋል። ብዙ ተማሪዎችም በእጅጉ እየተደሰቱ ሲመሰክሩለት ታይቷል።

2️⃣የማገናኘት እና የማዛመድ ጥበቦችን በመጠቀም
Chemical bonding-ን ከጋብቻ እና ከጥሎሽ ስረዐት ጋር ፣ Atomic structure-ን ከትልቅ ሰፈር እና ግቢ ጋር ፣ Economics-ን ገበያ ላይ ከምትሸጥ አንድ እናት ጋር\…. ወዘተ በእነዚህ እና በመሳሰሉት መንገዶች ትምህርቶቹን ከነባራዊው አለም ጋር በማዛመድ አገናኝተነዋል።

አንድ ተማሪ የChemical Bonding ሃሳቦችን ቢረሳ እንኳን የጋብቻ እና የጥሎሽ ስርዐትን ስለማይረሳ አዛምዶ እንዲይዝ ያስችለዋል።

በውስጡ ስለሚገኘው ሃሳብ (concept) በቀላሉ በመረዳት በአንድ ጊዜ ንባብ ለረጅም ጊዜ እንዲያስታውሰው ይረዳዋል።

3️⃣ሽምደዳን ሳይሆን ሃሳብን (concept) የተከተለ የትምህርት አሰጣጥ ፦ በርካታ ተማሪዎች ብዙ አንብበው ለመውደቃቸው ትልቁ ምክንያት የትምህርቶቹን ሃሳብ ባለመረዳታቸው ነው።

የኛ ትምህርቶች ሃሳብን ከማስጨበጥ አንፃር ባለፉት 2 አመታት ያስተማርናቸው ተማሪዎች ትልቅ ምስክር ናቸው።

4️⃣በቃል ለመያዝ ወይም ለመሸምደድ የሚያስችሉ መንገዶችን በመጠቀም
ለምሳሌ፦ ባዮሎጂ ላይ የማትቀር የኦርጋኒዝሞች (organism) አመዳደብ አለች (ሁሌ ፈተና ላይ አትቀርም) ታዲያ ይህንን አመዳደብ ከትልቁ ወደ ትንሹ ሲቀመጥ Kingdom, Phylum, Class, Order, Family, genius , species ይሆናሉ።

ብዙ ተማሪዎች ይህን በቅደም ተከተል ለማስታወስ ይከብዳቸዋል ። ስለዚህ እኛ አንዳንድ ፊደል በመውሰድ ልዩ ቃል በመፍጠር በቅደም ተከተላቸው እንዲያስታውሱ አድርገናል። \“KPCOFGS\” (ኬፒሶፋገስ) በማለት። ይህንን የመሳሰሉ ልዩ የማስያዣ መንገዶች እንጠቀማለን።

5️⃣የትምህርቶቹ አፃፃፍ ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች እና ሌሎችም በግራፊክስ እና በኤዲቲንግ ለማንበብ የሚመቹ እንዲሁም ለአይን የሚያምር ሆነው መዘጋጀታቸው የትምህርት አሰጣቱ ልዩ እና ተመራጭ ያደርገዋል።


      🌟ተጨማሪ አገልግሎቶች

1. ለኢንትራንስ የሚያበቁ አስደሳች ቻሌንጆች
2.ሳምንታዊ የጥናት ፕሮግራሞችን
3.የ live ጥያቄ እና መልሶች
4.ምክሮችን እና ውይይቶችን
5.በነፃ የ5 አመት የኢንትራንስ ጥያቄዎችን ከነ ተብራራ መልሶቻቸው እና አሰራር ቴክኒኮች የምታገኙ ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ 👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS
.
.
.

VICTORY OFFICIAL

19 Dec, 17:23


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7450169161721842949?is_from_webapp=1&sender_device=pc

VICTORY OFFICIAL

16 Dec, 16:46


ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ?

📌ዛሬ እስቲ ስለ victory tutorial ማወቅ የምትፈልጉትን ጥያቄዎች በዚህ username 👉
@VICTORY_TUTOR_TEAMS እየገባችሁ ጠይቁን በቂ መረጃ እንሰጣችኋለን።

VICTORY OFFICIAL

14 Dec, 17:44


እነዚህን የኢንትራንስ ጥያቄዎች ሞክሯቸው እና ስንት እንዳገኛችሁ comment ላይ አስቀምጡልን

VICTORY OFFICIAL

14 Dec, 17:44


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7448321011965119750?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7367363051

VICTORY OFFICIAL

18 Nov, 17:43


በቲክቶክ ስሙ "ኮንታ" ጋር የሰራነው ቪዲዮ ነው ገብታችሁ እየተዝናናችሁ like, share , copy link በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ እናድርግ🙏

VICTORY OFFICIAL

18 Nov, 14:53


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7438632282816089399?is_from_webapp=1&sender_device=pc

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 18:53


Live stream finished (2 hours)

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 16:43


live ተቀላቀሉ‼️‼️

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 16:42


https://t.me/VictoryTutor_7?livestream=411f940b69aaa95ccb

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 16:02


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 16:00


Live stream scheduled for

VICTORY OFFICIAL

17 Nov, 14:14


🎉የ2017 ኢንትራንስ ተፈታኝ ከሆናችሁ ዛሬ ማታ 1:00 እንዳትቀሩ

ያስጨነቋችሁን ጥያቄዎች የምትጠይቁበት እና መፍትሄ ምታገኙበት ቀን ዛሬ ነው።

VICTORY OFFICIAL

13 Nov, 17:16


💎ኢንትራንስ ሰቅለው ያለፉ ተማሪዎች ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ የምናዘጋጀው የእሁዱ live program ይቀጥል ተመችቷችኋል?
ሀባችሁን comment ላይ አስቀምጡልን
👇👇👇

VICTORY OFFICIAL

12 Nov, 17:45


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7436409473989627192?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7367363051111450117
https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7436409473989627192?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_id=7367363051111450117

VICTORY OFFICIAL

11 Nov, 16:44


VICTORY OFFICIAL pinned «»

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 18:16


Live stream finished (1 hour)

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 17:13


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 17:13


Live stream finished (4 seconds)

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 17:13


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 17:12


Live stream finished (1 hour)

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 16:09


አልያም ይሄን ሊንክ በመጠቀም live program ላይ መቀላቀል ትችላላችሁ👇👇
https://t.me/VictoryTutor_7?livestream

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 16:06


Live ላይ ለመቀላቀል ከላይ በፎቶው ላይ እንደምታዩት join የሚለውን በመንካት መሳተፍ ትችላላችሁ

VICTORY OFFICIAL

10 Nov, 16:00


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

07 Nov, 18:36


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7434548200305904952?is_from_webapp=1&sender_device=pc&web_i=7367363051111450117

VICTORY OFFICIAL

05 Nov, 17:26


Enezi metsihafoch betam redtewgnal share arglachew beterefe betam ameseginaleu 🙏

VICTORY OFFICIAL

05 Nov, 16:38


👆ከላይ ያስቀመጥንላችሁ record እሁድ በነበረን live program ላይ እንግዳችን ከነበረው Addisu Abitew ጋር ያደረግነው ቆይታ ሲሆን በርካታ ጠቃሚ እና ተስፋ ሰጪ መልዕክቶች ተጋርተውበታል።

ስለ Addisu Abitew ለማስታወስ ያህል
Entrance exam =651/700
Fresh man =4.00
5th year Software engineering  student


እንዲሁም ደግሞ እሱ ያነበባቸውን የውጪ መፅሀፎችንም ቃል በገባው መሰረት ልኮልናል ማታ 8:30 እናጋራችኋለን።

VICTORY IS A STATE OF MIND!

VICTORY OFFICIAL

05 Nov, 15:46


https://www.tiktok.com/@victorytutor_7/video/7433817190769495301?

VICTORY OFFICIAL

03 Nov, 18:15


Live stream finished (59 minutes)

VICTORY OFFICIAL

03 Nov, 17:50


የvictory team ለማናገር 👇👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

VICTORY OFFICIAL

03 Nov, 17:15


Live stream started

VICTORY OFFICIAL

03 Nov, 17:15


Live stream finished (1 hour)

VICTORY OFFICIAL

26 Oct, 17:23


ነገ እዚው official ቻናል ላይ እንግዳ ጋብዘን ልምዳቸውን እንዲያካፍሏችሁ ለማድረግ አስበናል እና ምን ያህል ሰው እንደሚገኝ ማወቅ እንፈልጋለን?

እገኛለው የሚል 👍 ያድረግ ከ100 ሰው  በላይ like ካደረገ ፕሮግራሙን እናዘጋጃለን

VICTORY OFFICIAL

26 Oct, 17:09


የዛሬ እንግዶቻችን
ናትናኤል ፀጋዬ የ2016 የቪክትሪ ተማሪ
Entrance exam = 455/600

ትንሳኤ ይትባረክ የ4ተኛ አመት architectural engineering ተማሪ
Entrance exam = 550/700
Fresh man = 4.00

ለቪክትሪ ተማሪዎች ስለሰጣችሁልን አስተማሪና አበረታች መልዕክት በተማሪዎቻችን ስም ልናመሰግናችሁ እንወዳለን

VICTORY OFFICIAL

25 Oct, 18:41


ሰላም ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ ቅዳሜ 2 እንግዶችን የኢንትራንስ ልምዳቸውን እንዲያካፍሏችሁ ጋብዘንላችኋል።

🎯አንደኛው እንግዳችን ትንሳዔ ይትባረክ ይባላል። በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ4ተኛ አመት architectural engineering ተማሪ ነው።

🛍Entrance exam =550/700
🛍Fresh man = 4.00 ነው ያመጣው።

✍️ቅዳሜ በሚኖረን ቆይታ አጠቃላይ የኢንትራንስ ዝግጅቱ ምን እንደሚመስል በስፋት ያጋራናል። እንዲሁም ስለ ዩኒቨርሲቲ በተወሰነ መልኩ share ያደርገናል።

🎯2ተኛው ናትናኤል ፀጋዬ ይባላል። የ2016 ተፈታኝ ሲሆን የቪክትሪ ተማሪም ነበረ።

🛍Entrance exam = 455/600 ነው ያመጣው

✍️ እሱም አጠቃላይ የኢንትራንስ ዝግጅት ጉዞው ምን እንደሚመስል እና ለናንተም ይጠቅማችኋል ሚላቸውን ሀሳቦች ያጋራችኋል።

📇እንዳያመልጣችሁ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል

VICTORY OFFICIAL

24 Oct, 17:41


ሰላም ቪክቶሪ Teams ለመናገር የምፈልገው አንድ ነገር አለ! በvictory ላይ የነበረኝ የጥናት ጊዜ(ያው አርፍጄ ብጀምርም) ዛሬ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁንና ትንሽም ቢሆን ለማለፊያ ውጤት በቅቻለሁ! ግን ዋናው ነገር ይሄ አይደለም! ከዚህ በፊት ሳጠና ፈተናውን ለማለፍ እንጂ እንዲህ ትምህርቱን ወደ ሕይወቴ አምጥቼ እገነዘበዋለሁ ብዬ አልነበረም ግን እናንተ ለትምህርት ያለኝን አመለካከት completely ቀይራችሁታል! ያው ለማመስገን ባረፍድም እናንተን appreciate ከማድረግ የሚያግደኝ ነገር የለም ! ጥናት ሒደት እንጂ መዳረሻ እንዳልሆነ እንዳውቅ ስላደረጋችሁኝ በጣም በጣም በጣም አመሰግናለሁ !

VICTORY OFFICIAL

24 Oct, 16:31


ዓለም modern የሚያስብላትን ኑሮ ስትጀምር ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

🌎እኛ ከምንጠቀምበት ስልክ እስከ satellite መገናኛዎች፣ በቤታችን ካለ tv እስከ ግላችን pc፣ ከከርሰ ምድር እስከ ጠፈር፣ ከየብስ እስከ ባህር፣ ከ electricity እስከ ከፍተኛ የኃይል ማመንጫዎች፣ በየትኛውም ዘርፍ ያሉ ማሽነሪዎች በሙሉ ያለሱ አልተከናወኑም።

↗️ዛሬ አለምን በአስገራሚ ሁኔታ ከቀየሩ technology-ኦች ጀርባ ያለውን engineer እናስተዋውቃችኋለን አብራችሁን ቆዩ።

✍️ታሪኩ በትክክል ከየት እንደሚጀምር የታወቀ ነገር የለም። አንዳንድ መላምቶች ግን ከ600 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ እስከ 300ዓመተ ዓለም ድረስ በግሪክ ፈላስፎች እንደተጀመረ ይናገራሉ።

🛫ነገር ግን ራሱን አሳድጎ በ16ተኛውና በ17ኛው ክፍለ ዘመን አሁን ላለበት ቅርፅ መሰረት የጣሉለትን ሂደቶች አከናውኗል።

🎯ይህ ጊዜ scientific revolution በመባል ይታወቃል። እነ Galileo Galilei, Johannes kepler, isacc newton አዳዲስ ህጎችን ያፀደቁበት ጊዜ ነው።


ስለማን እንደማወራ መቼም ገብቷችኋል። ስለ Physics ነው።

🔡physics በቀመር ወረቀት ላይ የተፃፈ subject ብቻ አይደለም። ከአለማችን ህልውና ጋር የተጣመረ የገሀዱ ዓለም አስደናቂ የተግባር ውጤት እንጂ

🤔physics ለዓለማችን ምን የተለየ ነገር ፈጠረ? ልትሉ ትችላላችሁ

እስኪ ትንሾቹን እንዘርዝር።

❶ኛ electronics፡ እንደ ስልክ፣computer, television , even internet ራሱ magnetism
, electricity , semi-conductors የመሳሰሉ የphysics ፅንሰ ሀሳቦችን ይዟል።

transportation፡ አስባችሁታል physics ባይኖር እንዴ አይነት ኑሮ እንደሚኖረን። መኪና የለ፣ ባቡር የለ፣ plane የለ በቃ መንቀሳቀስ ቅንጦት ይሆን ነበር።

🔡ዓመት የሚጨርሱ መንገዶች በphysics ብቻ በደቂቃዎች ውስጥ የሚደረስባቸው ሆነዋል።
ይሄም እንደ motion,force,energy የመሳሰሉ ጽንሰ ሀሳቦች አሉት።

➌ ህክምና፡ ብዙዎቻችሁ physics ከ medicine ጋ የሚገናኝ አይመስላችሁም ። ነገርግን እንደ x-ray, MRI, radiation therapy የመሳሰሉት ሁሉ የዚሁ ድንቅ subject ውጤቶች ናቸው።

✍️ይሄም ray , wave , optics የመሳሰሉ ፅንሰ ሀሳቦችን መሰረት ያደርጋል።

astronomy: physics ኮከብ , ጨረቃ, planet-ኦች የመሳሰሉን የspace አካላት እንድንረዳ አግዞናል።

↗️በጣም የበለፀጉ ሀገራት ብዙ በጀታቸውን ለዚህ field ሲመድቡም ይስተዋላል። ይሄም ውስብስብ የphysics theory-ኦችን ለምሳሌ፦ እንደ quantem mechanics, nuclear physics, cosmology, relativity የመሳሰሉትን ይይዛል።

climate change: physics... green house effect ወይም የozone መሳሳትን የመሰሉ ቃላቶች ዓለም እንዲረዳቸው እና የሰው ልጆች በclimate ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ እንዲያውቁ ያደረገ field ነው።

➤ physics modern world ከቆመችባቸው ምሰሶ አንዱ እንደመሆኑ መጠን impact-ኦቹን በቀላሉ ለመዘርዘር ያስቸግራል።

🧾ዋና ዋናዎቹን ለመጨመር ያክል ግን:- በconstruction ዘርፍ, በሙዚቃ, ሌሎች field-ኦችን በማገዝ፣ በስፖርት ወዘተ የማይገባበት የለም።እዚህ ጋ እንዴት በስፖርት እያላችሁ ይሆናል።

👀physics ካመጣቸው impact-ች አንዱ በsport ላይ ነው። ለምሳሌ በathletics,  principle of force , motion , energy የመሳሰሉ concept-ኦችን በመጠቀም athlet-ኦች እንዴት ራሳቸውን እንደሚያሻሽሉ፣ ሲጀምሩ ምን አይነት energy መጠቀም እንዳለባቸው ፣ የሚለብሱት ጫማ ሳይቀር ትንሽ እንዲያግዛቸው፣ የሚያደርጉት ሰዓት ወዘተ የphysics ውጤቶች ናቸው።

ለዚህም ነው
physics in not merely a subject
ያልነው።

⚡️physics አንድ theory-ኦች ተሰብስበው የተቀመጡበት መጽሐፍ ብቻ አይደለም።
.
.
.
ይቀጥላል...

VICTORY OFFICIAL

23 Oct, 17:20


ዛሬ ለቪክትሪ ተማሪዎች ከሰጠናቸው ዳታ የፊዚክስን እናጋራችሁ

VICTORY OFFICIAL

23 Oct, 17:19


↗️ከላይ የምታዩዋቸው ከ2014/2015 & 2015 ከየ ዩኒቶቹ ምን ያህል ጥያቄዎች እንደወጡ ሲሆን በተለይም 9th & 10th ክፍል ላይ ምን ያህል ጥያቄ እንደወጣ ማወቃችሁ ምን ላይ focus ማድረግ እንዳለባችሁ ጥሩ አቅጣጫ ጠቋሚ ናቸው።

እንዲሁም victory tutorial ላይ organize ተደርጎ የሚሰጣችሁ ቶፒኮች ምን ያህል አጋዥ እንደሆኑ ምታረጋግጡበት ነው።

VICTORY OFFICIAL

23 Oct, 16:33


👨‍🏫መምህሩን ያስገረመው ተማሪ!!!

🧑‍🎓ተማሪው class መገኘት ከነበረበት ሰዓት 10ደቂቃ አርፍዷል። በሩን አንኳኳ መምህሩ ብስጨት ብለው ከፈቱለት። እንደ ገባ ፊት ለፊት ካገኘው ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ አይኑን ወደ white board-ኡ ሲልክ ሶስት ጥያቄዎች ጎላ ብለው ተጽፈዋል።

✍️መምህሩ ከማጥፋቱ በፊት ሶስቱንም ጥያቄዎች ደብተሩ ላይ ገለበጣቸው እና ወደ ቤቱ አቀና።

🏠ቤት እንደገባም ደብተሩን ገልጦ ሶስቱን ጥያቄዎች መስራት ጀመረ። እስካሁን እንደሚሰጣቸው የቤት-ስራዎች በቀላሉ ሊሰራቸው ግን አልቻለም። በጣም ሞከረ  በመጨረሻም ሶስቱንም ጥያቄዎች ሰርቶ በቀጣዩ ቀን በድጋሚ አርፍዶ class ሄደ።

😠መምህሩ አሁን ሊታገሱት የፈለጉ አይመስሉም። ለምን እስካሁን አረፈድክ? አሉት ቆጣ ብለው። እየተንተባተበ ይቅርታ teacher የቤት ስራ እኮ ሰርቻለሁ እባክህ አስገባኝ አለው።

👀መምህሩም ግራ በመጋባት የምን የቤት ስራ እስኪ አሳየኝ አሉት። እነዚያን ሶስት ጥያቄዎች ከነመልሳቸው ደብተሩ ላይ ተመለከቱ።አላመኑም ደጋግመው አረጋገጡ።

👏ወደ ተማሪዎች ዞረው እስኪ ሁላችሁም አጨብጭቡለት። በጣም ጎበዝ አሉ።

😲ምን እየተፈጠረ እንዳለ ቆይቶ ነው የገባው።

ትናንት white-boardኡ ላይ የተጻፉት ጥያቄዎች ለካ በeconomics proof ያልተገኘላቸው ከባድ ጥያቄዎች ነበሩ።

ማርፈድም ለካ አንዳንዴ መዘግየት አይደለም፣ መፍጠንም ደግሞ የተሻለ ሆኖ መገኘት አይደለም።
.
.
.
ይቀጥላል...

VICTORY OFFICIAL

22 Oct, 17:55


😊ዛሬ ፈገግ በሚያደርግ መልኩ 3 የተማሪ አይነቶችን ላጋራችሁ comment ላይ እናንተ ከየትኛዎቹ እንደሆናቹ ፃፉልን

ተማሪዎች የተለያየ አይነት የአጠናን መንገድ ይከተላሉ ከነዛም ውስጥ በጥቂቱ እንመልከት

🌟የመጀመሪያወቹ ሁሉን ብላ ይባላሉ። የቀረበለትን ሳያስተርፍ እንደሚበላ ሰው ማለት ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች መፅሐፉ ላይ የተፃፈውን ነገር አንድም ሳያስቀሩ የሚቀረጣጥፉት ናቸው።

ምንም ነጥብ አይዘሉም። የመፅሀፉን ገፅ ሁሉ ሳይቀር ሸምድደውታል።

🛫ታዲያ እነዚህ ተማሪዎች ጥያቄው concept የሆነ ቀን ጉዳቸው ፈላ።

🎯ሁለተኛዎቹ ሚስጥረኞቹ የሚባሉት ሲሆኑ የሚያነቡትን የሚያውቁ፣ ሁሉን የማያግበሰብሱ ናቸው። በቃ ከሚቀርብላቸው ትንሽ ተመግበው። ኩኪስ፣ ቡና ምናምን እንደሚሉ አይነት ማለት ነው።

እነዚህ አይነት ተማሪዎች ፈታ ማለት ያበዛሉ። ብዙ አያነቡም። ፈተና ሲደርስ ግን እንደነሱ ጥያቄውን የሚሰራው የለም።

ይሄ አይነት strategy በጣም የሚመከር ቢሆንም። ከህፃንነት ጀምሮ የዳበረ ትልቅ ልምድን ይጠይቃል። ለአዲስ ጀማሪዎች የሚመከር አይደለም።

✍️ሶስተኛዎቹ ደግሞ ብዕረኞቹ ይባላሉ። ለነዚህ ትምህርት ማለት የፅሑፍ ሂደት ነው።

✍️class ውስጥ ይፅፋሉ፣ ሲያጠኑ ይፅፋሉ✍️፣ ደብተራቸውም ሆነ  እጃቸው ጀማሪ ሰዓሊ የተለማመደበት ሸራ ነው ሚመስለው።

😊አስረዳኝ ብለህ ስትጠጋቸው ደብተርክ የእነሱ እስኪመስል ይጠበቡበታል። የእነሱ strategy ጊዜ ይፈልጋል እንጂ ማንም ሰው ቢሞክረው ቀላል ነው።

የትኞቹ ተማሪ ናችሁ? comment ጋ ፃፉልን።

VICTORY OFFICIAL

22 Oct, 16:11


🔗Volcanism
🔸Types of volcanoes
🔸Importance of volcanic eruptions:
🔗Earthquake

VICTORY OFFICIAL

22 Oct, 16:11


CHAPTER THREE

⭐️DYNAMICS

💎Newton 1st law
💎Newton 2st law
💎Newton 3st law
💎Types of force

VICTORY OFFICIAL

20 Oct, 17:35


🐻ካሁኑ ተስፋ የቆረጣችሁ ተማሪዎች አይምሯችሁ ላይ ያለውን ጭንቀት የፈጠረው አለብን ብላችሁ ያሰባችሁት 97&101 unit ነው።

🎯ከላይ እንደጠቀስንላችሁ ለማለፍ እና ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሁሉንም unit cover ማድረግ አይጠበቅባችሁም።

↗️በ2016 ካስተማርናቸው ተማሪዎቻችን ውስጥ 3 ወር ሲቀረው ጀምረው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች አሉ።

🐂ይህ የሚያሳየው ከተጠቀማችሁበት ትልቅ እድል እና ገና ሰፊ ጊዜ እንዳላችሁ ነው።

ለምሳሌ በ Victory tutorial ለአንድ subject ቢበዛ 10 ቻፕተር ነው እንዲያነቡ ምንሰጣቸው እነዛ ቻፕተሮች entrance targeted ቶፒኮችን የያዙ ሲሆኑ ተማሪዎቻችን እየተዝናኑ ልብ ወለዳዊ በሆነ አገላለፅ በርካታ ቶፒኮችን ባለፉት 3ወራት ብቻ cover አድርገዋል።


ስለ victory tutorial አሰጣጥ መረጃ ለማወቅ👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

VICTORY OFFICIAL

20 Oct, 16:53


.
.
.
✍️በ2014 እና 2015 ከወጡ ኢንትራንስ ጥያቄዎች ከሰበሰብነው ዳታ አንድ አስገራሚ መረጃ እናጋራችኋለን።

📇ለምሳሌ በፊዚክስ subject በነዚህ 2 አመቶች በአመካይ ከ29 unit 50ጥያቄ ወጥቷል።

ከወጡት 50ጥያቄዎች ውስጥ
🐂40ጥያቄ የወጣው  ከ19 unit
🐻10 ጥያቄ የወጣው ደግሞ ከ10 unit ነው።

🎉ይህ ማለት 80/100 ጥያቄ የወጣባቸውን ቶፒኮች ከ28unit ውስጥ 18unit አንብባችሁ cover ታደርጋላችሁ ማለት ነው።

ስለዚህ አንድ ተማሪ እነዚህን 18unit
ከስር ከስር ሳይሸመድድ ካጠና
ቢያንስ የ5አመት ኢንትራንስ ጥያቄ ከሰራ
በቀን ለጥናት ቋሚ ሰዐት መድቦ ጊዜውን በአግባባቡ ከተጠቀመ
ሳይኮሎጂካሊ እራሱን ካዘጋጀ እና እንደሚያልፍ ካመነ

↗️ድካሙን እጅጉን አቅልሎ ስትራቴጂካል በሆነ መንገድ ውጤታማ መሆን የሚችል አይመስላችሁም?

VICTORY OFFICIAL

19 Oct, 12:10


Cont...


👩‍🏫3ኛ... prepare To Do list ....

✍️focused ሆነው ማጥናት የማይችሉ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው የሚያጠኑትን አለማወቅ ወይም በእቅድ አለመመራት ነው።

🧑‍🎓እነዚህ ሰዎች ዛሬ የሚያነቡትን፣ ስንት chapter መጨረስ እንዳለባቸው፣ ከጥናት ውጭ ሌላ ምን ስራ እንዳለባቸው፣ አጥንተው ሲጨርሱ ደግሞ ከግባቸው እንደደረሱ እንዲሁም ያልጨረሱትን የሌላ ቀን schedule-ኣቸው ላይ arrange ማድረግን እና የመሳሰሉትን ያልተለማመዱ ናቸው።

To Do list ማለት በአጭሩ ዛሬ ሊሰሩ የታሰቡ ነገሮችን ዘርዝሮ መጻፍ እና ቀኑ ሲያልቅ ያከናወኗቸውን ተግባራት መገምገም ማለት ነው።

ይህ techniqe ሁለት ህግ አለው። ከፊት ለፊቱ square box የመሰለች ቅርጽ ያስቀምጣል። ስራው ከተሰራ ተሰርቷል ካልሆነ ግን አልተሰራም ብሎ judge ያደርጋል። ይሄም ተማሪዎች ከበፊቱ የበለጠ ጥረት እንዲያደርጉና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ያደርጋል።

☺️አብዛኛወቹ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የbusiness ሰዎች ይሄን technique ይጠቀሙታል።

ለማስታወስ ያክል፦
🍀1ኛ- ረጅም ሰዓት ለማጥናት አጠቃላይ ሰዓቱን በመከፋፈል እና መሀል መሀል ላይ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ እረፍት መውሰድ።

🍀2ኛ, ጸጥታ የሰፈነበት ቦታ መሄድ፣ ስልክን ማጥፋት

🍀3ኛ, በቀን ውስጥ ሊሰሩ የታሰቡ task-ኦችን መዘርዘር እና መገምገም።

➤ እነዚህን 3tip-ኦች በአግባቡ የተጠቀመ ሰው። focused ሆኖ ለረጅም ሰዓት ለማጥናት አይቸገርም።

ከሶስቱ እስከዛሬ የትኛውን ነበር የምትጠቀሙት?
.
.
.
.


ከተማሪዎቻችን የተሰጡ አስተያየቶች👇
https://t.me/victorystcom_7

የvictory team ለማናገር👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

VICTORY OFFICIAL

18 Oct, 16:11


🔓እስቲ እርፍ በሉ

🙇ሃሳቤን መሰብሰብ አልቻልኩም.....
🙅‍♂️ ጥናቴ ላይ ማተኮር አልቻልኩም...
🤦‍♀️ብዙ አነባለሁ ግን ረሳለሁ....

💬የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ። በዚህ ፅሁፍ እንዴት focus ሁናችሁ እንደምታነቡ 3 tip-ኦችን እናጋራችኋለን።

🧑‍🎓1ኛ..... pomodoro technique.....
ሳይንስ እንዳረጋገጠው ከሆነ ለረጅም ሰዓታት ያለ ዕረፍት የሚያጠኑ ሰዎች ያነበቡትን የማስታወስ እድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው።

✍️ካነበቡት ውስጥ የሚያስታውሱት ጥናት ሲጀምሩ እና ሲጨርሱ አካባቢ ያለውን ብቻ ነው ። አስቡት ከ6 ሰዓታት በላይ ያለ ዕረፍት አጥንተው focus የሆኑ ሰዎች በ30 ደቂቃ ያጠኑትን ያክል እንኳን አያስታውሱም እንደ ማለት ነው።

🎁ለዚህም መፍትሄው pomodoro technique ነው።

✍️ምን ማለት መሰላችሁ ሙሉውን ሰዓት እየከፋፈሉ ማጥናት ማለት ነው።
ለምሳሌ ለ2 ሰዓት focused ሆኖ ለማጥናት ከ40 እስከ 45 ደቂቃ ማጥናት ከዛ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ማረፍ።

✍️ይሄንኑ በመደጋገም ስኬታማ የሆነ የጊዜ ቆይታ እንዲኖር ማድረግ እንደሚቻል ያስረዳል።

🫂አብዛኞቹ አሁን ላይ በትምህርታቸው ጥሩ የሚያመጡ ተማሪዎች ይሄን technique ይጠቀሙታል። አንዳንዶቹ እንዲያውም ከዚህ የበለጠ በመክፈል.... 25 ደቂቃ ጥናት ፣  5 ደቂቃ እረፍት እያደረጉም ይጠቀሙታል።

✍️ነገሮችን በቶሎ ለመረዳት፣ ፈተና ላይ ጥሩ ለመስራት፣ እና ያጠኑትን ለማስታወስ ጠቃሚ technique ነው።

.
.
.
.
ይቀጥላል....

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:36


ከተማሪዎቻችን የተሰጡ አስተያየቶች👇
https://t.me/victorystcom_7

የትምህርቱን አሰጣት Sample ለማየት👇
https://t.me/VictorySample7

Victory team ለማናገር👇👇👇
@VICTORY_TUTOR_TEAMS

☎️0914633658

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:33


5️⃣የትምህርቶቹ አፃፃፍ ፣ ስዕላዊ መግለጫዎች እና ሌሎችም በግራፊክስ እና በኤዲቲንግ ለማንበብ የሚመቹ እንዲሁም ለአይን የሚያምር ሆነው  መዘጋጀታቸው የትምህርት አሰጣቱ ልዩ እና ተመራጭ ያደርገዋል።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:32


4️⃣በቃል ለመያዝ ወይም ለመሸምደድ የሚያስችሉ መንገዶችን በመጠቀም
ለምሳሌ፦ ባዮሎጂ ላይ የማትቀር የኦርጋኒዝሞች (organism) አመዳደብ አለች (ሁሌ ፈተና ላይ አትቀርም) ታዲያ ይህንን አመዳደብ ከትልቁ ወደ ትንሹ ሲቀመጥ Kingdom, Phylum, Class, Order, Family, genius , species ይሆናሉ።

ብዙ ተማሪዎች ይህን በቅደም ተከተል ለማስታወስ ይከብዳቸዋል ። ስለዚህ እኛ አንዳንድ ፊደል በመውሰድ ልዩ ቃል በመፍጠር በቅደም ተከተላቸው እንዲያስታውሱ አድርገናል። \“KPCOFGS\” (ኬፒሶፋገስ) በማለት። ይህንን የመሳሰሉ ልዩ የማስያዣ መንገዶች እንጠቀማለን።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:29


3️⃣ሽምደዳን ሳይሆን ሃሳብን (concept) የተከተለ የትምህርት አሰጣጥ ፦ በርካታ ተማሪዎች ብዙ አንብበው ለመውደቃቸው ትልቁ ምክንያት የትምህርቶቹን ሃሳብ ባለመረዳታቸው ነው።

የኛ ትምህርቶች ሃሳብን ከማስጨበጥ አንፃር ባለፉት 2 አመታት ያስተማርናቸው ተማሪዎች ትልቅ ምስክር ናቸው።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:26


2️⃣የማገናኘት እና የማዛመድ ጥበቦችን በመጠቀም
Chemical bonding-ን ከጋብቻ እና ከጥሎሽ ስረዐት ጋር ፣ Atomic structure-ን ከትልቅ ሰፈር እና ግቢ ጋር ፣ Economics-ን ገበያ ላይ ከምትሸጥ አንድ እናት ጋር\…. ወዘተ በእነዚህ እና በመሳሰሉት መንገዶች ትምህርቶቹን ከነባራዊው አለም ጋር በማዛመድ አገናኝተነዋል።

አንድ ተማሪ የChemical Bonding ሃሳቦችን ቢረሳ እንኳን የጋብቻ እና የጥሎሽ ስርዐትን ስለማይረሳ አዛምዶ እንዲይዝ ያስችለዋል።

በውስጡ ስለሚገኘው ሃሳብ (concept) በቀላሉ በመረዳት በአንድ ጊዜ ንባብ ለረጅም ጊዜ እንዲያስታውሰው ይረዳዋል።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:22


    🌟የትምህርት አሰጣጥ
እንደ ቪክትሪ በዋነኝነት የምናምነው የሚሰጡት ትምህርቶች ሳይሆን ትምህርቶቹ የሚሰጡባቸው መንገዶች የተማሪዎች ውጤት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለን እናምናለን።

በመሆኑም ከሰፊ ጊዜ ጥናት በኋላ ትምህርቶቹን በብዙ ውጤታማ እና ባልተለመደ መንገዶች አዘጋጅተነዋል።

1️⃣ልቦለዳዊ እና አዝናኝ በሆነ መንገድ ፦ አንድ ተማሪ 300 ገፅ ያለውን ልቦለድ መፀሀፍ በ ቀናት ሲጨርስ በሌላ በኩል 300 ገፅ ያለውን ትምህርታዊ መፅሃፍ ወራት እንዲፈጅበት የሚያደርገው ዋነኛው ልዩነት ልቦለዱ ሲዘጋጅ ምስል ከሳች ፣ ልብ አንጠልጣይ፣ ያልተለመዱ ቋንቋዎችን በመጠቀሙ እና በሳቅ የተሞላ አዝናኝ ጨዋታን በመፍጠር ነው።

እኛ ትምህርቶቹን ስናዘጋጅ በዚህ ስልት መሰረት በማዘጋጀት ብዙ ተማሪዎች እኛጋ እየተሳቀቁ ሳይሆን እየሳቁ በቀላሉ ትምህርቶቹን እንዲጨርሱ አስችለናቸዋል። ብዙ ተማሪዎችም በእጅጉ እየተደሰቱ ሲመሰክሩለት ታይቷል።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:19


5️⃣ከባድ ፣ ሰፊ እና ጥልቅ ሃሳብ ያላቸውን ምዕራፎች በማካተት(Difficult, vast and deep chapters technique):- እንደ derivative ,integration , Genetics, Chemical bonding, rotational motion , Electrostatics እና የመሳሰሉትን ምዕራፎች በውስጣቸው ሌሎች ብዙ ምዕራፎችን እንደ ግብዐትነት የያዙ እና ጥልቅ እንዲሁም ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸው በመሆኑ በእኛ የትምህርት አሰጣጥ ላይ አካተነዋል። 

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:18


4️⃣ከመሰረቱ በመጀመር(Starting from the basics technique)፦ በዚህ ስልት ከባባድ ለሚባሉ ምዕራፎች እንደ ግብዐት የሚያገለግሉ ነገር ግን ቀላል ሆነው ሸዋጅ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን ምዕራፎችን ጥናት በማድረግ ተዘጋጅቷል።

በተለይም የኢንትራንስ ጥያቄዎች ቀላል እና ሸዋጅ ከመሆናቸው አንፃር ትኩረት ተሰጥቶበታል።  

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:16


3️⃣በአንድ ምዕራፎች ውስጥ ብዙ ምዕራፎችን በማካተት (Inclusion technique):- ይህኛው ስልት በትንሽ ልፋት ፣ ብዙ ምዕራፎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ተፈትኖ የቀረበ ግሩም ስልት ሲሆን በዚኛው ስልት ተማሪዎች አንድ ሰፋ ያለ ምዕራፍ ያነበቡ ቢመስላቸውም በውስጡ ግን ከ 5-7 የሚጠኑ በተለያዩ ክፍሎች በዋናው መፅሃፎቻቸው የተቀመጡ ምዕራፎችን የሚያነቡ ይሆናል።

በትንሽ ጊዜ ብዙ እና ሰፊ የነበሩ ምዕራፎችን ያለ ሃሳብ(concept) መጎራረድ በማንበብ ለትልቅ ውጤት ያበቃቸዋል።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:14


2️⃣ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማካተት(Marging and Integration technique) :- ይህ አይነቱ ስልት በተለያየ ክፍል ላይ ያሉ ምዕራፎች ሆነው ነገር ግን ተመሳሳይ (አንድ አይነት) ይዘት ያላቸውን ምዕራፎች አንድ ላይ በማድረግ ከቀላሉ ወደ ከባዱ በመሄድ አያይዞ መስጠት ነው። በዚህ የማቀናጀት ሂደት ውስጥ ተማሪው በትንሹ ሁለት ምዕራፎችን ሳያውቀው እና ሳይሰለቸው ይጨርሳል።

ለምሳሌ፦ የፊዚክስ(Physics) እና ኬሚስትሪ(Chemistry) ትምህርቶች አብዛኛው ምዕራፎች በዚህ አይነቱ ውጤታማ ስልት የተዘጋጁ ናቸው።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:12


ስለ Victory academy አጠቃላይ መረጃ

🌟የኢንትራንስ ተፈታኞች እንዲሁም የ 11ኛ ክፍል Natural science ተማሪዎች ቪክትሪን ስትጠቀሙ የምታገኟቸው የትምህርት አይነቶች

📌English , Maths , Physics Chemistry , Biology 

📌English , Maths , Economics , Geography , History  ናቸው።

🌟የትምህርቶቹ አወቃቀር
ኢንትራስ ከ 600 በላይ ባመጡ ተማሪዎች እና መምህራን የሰፊ ጊዜ ጥናት በማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ካላቸው ልምድ እና ከሌሎችም መረጃዎችን በመሰብሰብ ትምህርቶቹ ከ9-12ኛ ክፍል በሚከተለው መንገድ ተዋቅረዋል።

1️⃣ኢንትራንስ ተኮር(entrance targeted technique)፦ ይህ ማለት በኢንትራንስ ላይ ብዙ ጥያቄዎች የሚወጣባቸውን እና በዩኒቨርሲቲም ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚባሉ ምዕራፎችን በማውጣት ተማሪዎች የተወሰኑ ምዕራፎችን በምንበብ ብቻ ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል ነው።

በዚህ መንገድ(ስልት) በተለይም ኢንትራንስ 3 እና 2 ወር ሲቀራቸው አንብበው የገቡ ልጆች ከማለፍ አልፈው ለማመን የሚከብዱ ውጤቶችን ሲያመጡ ያየንበት እና ልጆችም የመሰከሩለት መንገድ ነው።

VICTORY OFFICIAL

15 Oct, 17:10


📌ዛሬ ስለ ቪክትሪ ማወቅ ለምትፈልጉ ተማሪዎች አጠቃላይ መረጃ ምንሰጣችሁ ይሆናል።

📌ይህም የ2017 ተፈታኞች ምን ያህል ጭንቀት አቅላይ በሆነ መንገድ እንደተዘጋጀ ግልፅ የሆነ መረጃ ምታገኙበት ይሆናል።

📌እንዳይበዛባችሁ እየቆራረጥን እንለቅላችኋለን ተከታተሉ