Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

@ortodoxmezmur27


ortodoxs mezmur

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

11 Sep, 07:04


🌼እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገረን!
ከዓመት ዓመት ያደረሰን ፈጣሪ ቀጣዩን እንድናይ ይርዳን !

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

05 May, 05:27


ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!

ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!

ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!

ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!

ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!

ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡


"ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።"
- ሉቃስ 24፥5

እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችንና ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

03 May, 05:09


"አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ"

2ኛ ቆሮ 5 : 4

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

03 May, 04:41


#አልፋና ኦሜጋ

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በካሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ

ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉሀ
ጽድቅን ስለ ሠራህ በወንጌል ከሰሱህ
ለአዳም ልጅ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
………አዝ…………..
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትክ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
………አዝ…………..
በዓውደ ምኲናን ከጲላጦስ ፊት
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከሄሮድስም ዘንድ አቀረቡህ በዋጅ
………አዝ…………..
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ
………አዝ…………..
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አሁዶች በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ፤

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

03 Apr, 17:52


አቡነ አብርሃም

የእውነት አባት በረከቶ አትለየን ።

“እስከ ትበጽህ ለሞት ተበዓስ በእንተ ጽድቅ እስመ እግዚአብሔር አምላክከ ይትበአስ
በእንቲአከ”

“እስክትሞት ለእውነት ታገል። እግዚአብሔር ላንተ ይታገልለሀልና”

           ሲራክ 4 ፡ 2

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

20 Jan, 08:41


እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አመታዊ የጥምቀት በአል አደረሳችሁ በአሉንም ስናከብር እኛም ንስሐ በመግባትና ከኃጢአታችን ታጥበን በሰላም በፍቅር እናከብር ዘንድ ፈቃዱ ይሁንልን ።

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

28 Sep, 09:47


" መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡ መስቀል የአብ ፈቃድ ፣ የወልድ ክብር ፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ ፣ የመላእክት ጌጥ ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ ፣ የቅዱሳን ጋሻ ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡ "

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

04 Sep, 09:10


በዓለ ወልድ*

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየወሩ በዚህች በ29ኛይቱ ዕለት ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በድንቅ ልደት የተወለደበትን በዓል ትዘክራለች። እለቱም በዓለ ወልድ ይባላል።*

ሃይማኖተ አበው ስለዚህ ድንቅ ልደት እንዲህ ያስተምረናል* ፦

ከህሊናት ሁሉ ለራቀ እና ለረቀቀ ለዚህ ድንቅ ልደት ለዚህ ድንቅ ምስጢር አንክሮ ይገባል! ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው! እርሱም እናቱን ፈጠረ፤ ከእርሷም እርሱ የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ*  ::
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም 47:2

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም ለመለኮት በሚገባ ልደት ተወለደ:: ይህ ምስጢር ታላቅ ነው!*

ሰማያዊው አምላክ የምድራዊውን ሰው ሥጋ የለበሰበት፤ ምድራዊው ሰው የሰማያዊ አምላክነትን ክብር ያገኘበት ይህ እለት እንደምን ድንቅ ነው!*

በእውነቱ በዚህ ድንቅ ልደት አምላክን ለመውለድ የታደለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንደምን ድንቅ ናት!*

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ይህ የአምላክ እናት ድንቅነት ቀድሞ ቢታየው፤ ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ! እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ! ብሎ ከፊቷ ወድቆ አመሰግኗታል።*

ይህን ልደት ስንዘክር፡ ከትህትናው እና ለእኛ ካለው ፍጹም ፍቅር የተነሳ: በከብቶች በረት የተኛውን ጌታችንን፣ በፍጹም ድንግልና የወለደችው እናቱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በፊታቸው ወድቀን በማመስገን እና በመማጸን ነው።

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

24 Aug, 04:57


ድንግል ማርያም ዘማሪት እየሩሳለም ጌታቸው

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

12 Aug, 04:50


እናቴ አርሴማ ዘማሪት እየሩሳለም ጌታቸው

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

03 Aug, 05:08


" ሥላሴ ለእኔ " ዘማሪት ሰላማዊት መኮንን

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

22 Jul, 17:20


የቤተክርስቲያን አካሏ ይህ ነው። ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም የተመሠረተች ንጽሕት ቅድስት ናት። ለመዳን ወደእርሷ የተጠጉ ሰዎች ግን ከጨዋ እስከ ፓትርያርክ እስከ ሲኖዶስ ሊሳሳቱ ይችላሉ። በእነርሱ ምክንያት እርሷን መስደብና መንቀፍ ይቁም። ክርስቶስንምኮ ይከተሉት ከነበሩት አምስት ገበያ ሕዝብ ዓላማቸው ልዩ ልዩ ነበረ። አንዳንዶቹ ለከርሣቸው፣ አንዳንዶቹ ለትምህርቱ ተከትለውታል።
                           ።
አካሏ ክርስቶስ የሆነላትን ቅድስት ቤተክርስቲያን ደግሞ አንዳንዱ ለሆዱ፣ አንዳንዱ ለፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለሙ፣ አንዳንዱ ለመዳን ይጠጓታል። ለመዳን የተጠጓት ነፍሳቸውንም ሥጋቸውንም ጠቀሙ። ለሌላ ዓላማ የተጠጓት ግን ራሳቸውን ከመጉዳት የዘለለ ምንም አያመጡም። ሰይፍን ቢመረኮዙ ራሳቸው ይጎዳሉ እንጂ።

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

25 Jun, 20:43


#ቸርነትህ_ነው

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ
ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከዛሬ
ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

        #አዝ ………………
መክሊቴን ቀብሬ ባሳዝንህ
መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ
በታላቅ ይቅርታ እዳትረሳኝ
በፍቅር ጎብኝተህ ከሞት አዉጣኝ
ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ
በርሀብ በርዛት ተቸገርኩኝ
አምናለሁ ከምላኬ እድትምረኝ
በይቅርታ መጣሁ ተቀበለኝ

       #አዝ ………………
አንዳች እዴለለኝ አዉቀዋለሁ
ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ
የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል
ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል
በመቅደስህ ቁሜ ለመዘመር
ስራህን ለትዉልድ ለመመስከር
እኔ ማነኝ ብየ አስባለሁ
አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ
       
          #አዝ ………………
በሰዉ እጅ መመካት አቁሚያለሁ
እረዳቴ አንተ ነህ አዉቄያለሁ
አንተ ከጠበከኝ በህይወቴ
ቅጥሬ አይደፈርም መድኃኒቴ
የኔን ስራ ተወዉ ተግባሬንም
የመስቀሉንም ነገር መርሳቴንም
አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

24 Jun, 18:15


ሰንበተ ክርስትያን

እሑድ ማለት"አሐደ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲኾን ትርጉሙ የመጀመሪያ እንደማለት ነው። ይኽች ዕለት በመጽሐፍ ቅዱስ "ከሳምንቱ በፊተኛው ቀን " በመባል ትታወቃለች።

ዮሐንስም በራዕዩ "የጌታ ቀን" ያላት ናት
(ራዕይ 1፥10)

ቅዱስ ያሬድም በድጓው ላይ "ዕለተ እግዚአብሔር" የሚላት ዕለተ እሑድ ናት።

መልካም ዕለተ ሰንበት ይኹንልን

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

18 May, 10:16


[       ለምን ትቀናለህ ?      ]

" ... በጆሮው የሆነ ነገር ነግሮት ወዲያው ተሰናብቶት ወጣ። ይህን ጊዜ አጋንንቱ እያዩት መነኩሴው መንፈሳዊ ገጽታው ተገፎ ፊቱ በቁጣና በንዴት ሲለዋወጥ ተመለከቱት። ... "


" እንዳትበድል አትቅና።" [ መዝ. ፴፯ ፥ ፰ ]

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

09 May, 05:06


"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ፤ ወሰማዮሙኒ አስረቀት ፀሐየ" እንዳለ ደራሲ።
ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱ፤ ሰማይቷም ፀሐይን ወለደች።
ፀሐይ ጽድቅ ክርስቶስን የወለደችው ሰማይ ተወለደች!!
ልደትሽ ልደታችን ነው!
እንኳን አደረሳችሁ።

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

16 Apr, 10:52


ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
++++++++++++++++++++
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም የትንሳኤ በዓል

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

20 Mar, 10:16


መልአከ ሰላም ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ "የሁሉም አይን" የንስሃ መዝሙር

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

24 Feb, 17:48


የተሰቀለውን ኢየሱስን ሳየው ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

Ethiopia Ortodox Mezmur Video🤲👏

05 Feb, 04:12


https://youtube.com/@EOTCTV?si=EnSIkaIECMiOmarE
ሰብስክራይብ በማድረግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቭዥን ጣቢያን እናግዝ።