በኢትዮጵያና ኬንያ አዋሳኝ በቱርካና ሀይቅ ዳርቻ በቶዶንያንግ የድንበር መሻገሪያ ቦታ ላይ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ታጣቂዎች በትናንትናው ዕለት በኬንያ ዓሣ አጥማጆች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የኬኒያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።
ሪፖርቱ "ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሳነች ሚሊሻዎች ዓሣ አጥማጆቹ በቱርካና ሀይቅ ላይ በሚሰሩበት ወቅት አካባቢውን በመውረር በዘፈቀደ ተኩስ ከፍተዋል" ይላል።
በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከአካባቢው ፖሊስ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ ቅዳሜ ማለዳ በቱርካና ውስጥ አንድ የታወቀ ሽፍታ ሶስት የዳሳነች ዓሣ አጥማጆችን በመግደሉ ምክንያት የተፈጸመ የበቀል እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
"የውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ሚኒስቴር በዳሳነች ሚሊሻዎች በቱርካና ሀይቅ ቶዶንያንግ አካባቢ ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የሚያሳዝኑ ሪፖርቶችን እየደረሰን ነው። ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ ይችላል" ሲሉ ናቡይን ተናግረዋል።
"ሁኔታው በጣም የከፋ ነው፣ አዳኞች ህዝባችንን ለመጠበቅ በፍጥነት መንቀሳቀስ አለባቸው። እልቂቱ በኬንያ ምድር ላይ እየተፈጸመ ነው፣ በደንብ በታጠቁ ሚሊሻዎች (ዳሳነች) የተያዘው።" ሲሉም አክለዋል። ክስተቱ ትናንት ቅዳሜ ምሽት በሎፔይሙካት እና ናቲራ በኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ ተከስቷል።
በጥቃቱ አምስት ጀልባዎች ተደብድበው በጀልባዎቹ ላይ የነበሩት በሙሉ ተገድለዋል።