آخرین پست‌های Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) در تلگرام

پست‌های تلگرام Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 مشترک
727 عکس
95 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 17:16

کانال‌های مشابه

ሪፖርተር ET
24,247 مشترک

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Roha Tv/ሮሃ ቴቪ در تلگرام

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 12:31

1,646

በሸዋ ግንባር ከጠላት ሠራዊት የሚደረገው ትንቅንቅ ቀጥሏል።

በሸዋ ግንባር የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ባሉት ሁሉም ክፍለ ጦሮች ባለፉት ቀናቶች ተከታታይ አውደ ውጊያዎች እየተደረጉ ይገኛል።

በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ አስቴጎማ ክፍለ ጦር 6ኛ ቀኑን በያዘ አውደ ውጊያ ተጋድሎ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በቅርብ ርቀት ኤፍራታና ግድም ወረዳ 3ተኛ ቀኑን በያዘ አውደ ውጊያ 7ለ70 ክፍለ ጦር ከአገዛዙ ሠራዊት ጋር በመፋለም ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም ምኒልክ ክፍለ ጦር በመንዝ ቀጠና ተጋድሎ ሲያደርግ ፤ደጅ አዝማች ተሰማ እርገጤ ክፍለ ጦር ሸዋሮቢት ዙሪያ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር 7ለ70 ክፍለ ጦር ከጠላት ብልፅግና ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ የኦሮሞ ብሄረሰብን መደበቂያ አድርጎ ተደጋጋሚ ጥቃት ለማድረስ ሙከራ ከሚያደርገው ከስርዓቱ አረመኔ ሠራዊት ጋር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ በርካታ ድሎችን በማስመዝገብ ላይ ነው።

ከትናንት በስቲያ ማምሻ የጀመረውና ማክሰኞ ረፋዱን የተቀጣጠለው አውደ ውጊያ በአጣዬ ከተማ በላይኛው አጣዬ ፈረደ ውሃ ላይ እየተደረገ ሲሆን ትንቅንቁ እስከዚህ ሰዓት ድረስ በከፍተኛ ተጋድሎ ቀጥሏል። በአውደ ውጊያው በርካታ የአገዛዙ ሠራዊት ተደምስሷል። በጀግንነት ከጠላት ሠራዊት ጋር ተናንቀው ከ30 በላይ የብልፅግናን ሠራዊት በእርሳስ ቀለበታቸው ሸኝተው ለወገን ክብር "2 ጀግኖች" በክብር ሰማዕት ሆነዋል።  አውደ ውጊያው አሁንም የቀጠለ ሲሆን የጠላት ሀይል እየተገረፈ የወገን ሀይል በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል።

በሌላ ግንባር ወደ መንዝ አቅጣጫ ያቀናው የብልፅግና ሠራዊት አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተመልሷል። ከትናንት ወዲያ ማምሻውን በደፈጣ የጀመረው አውደ ውጊያ በመንዝ ላሎ አጎ ላይ በምኒልክ ክፍለጦር አናብስቶች የጠላት ሠራዊት ተቀጥቅጧል። ከዚህ ባሻገር አገዛዙ በለብ ለብ አሰልጥኖ ደብረብርሃን ያዘጋጃቸውን የሠራዊት አባላት በሁሉም ግንባሮች በማሰማራት  እና የአየር ጥቃት ለመፈፀም እያደረገ ባለው ጥረት ከፍተኛ ውጥረቶች ያሉ ሲሆን የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ 8ቱ ክፍለጦሮች በሁሉም ግንባር ዝግጁነታቸውን ጨርሰው በተጠንቀቅ ላይ ቆመዋል ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በገጹ ሰፍሯል።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 12:05

1,765

#የችሎት_መረጃ
ዛሬ የካቲት 19/2017 ዓ.ም በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ህገመንግስታዊና ሽብር ወንጀል ችሎት፤ በዋለው ችሎት ፤ በኤርሚያስ መኩሪያ ላይ በተነበበው ውሳኔ ከተከሰሰባቸቸው ሁለት ክሶች በአንድኛው ነፃ ሲባል በሁለተኛው ጥፋተኛ የሚል ብይን ተሰጥቷል። ጥፋተኛ በተባለበት ክሰላይ የጥፋተኝነት የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት የፊታችን ማክሰኞ ማለትም የካቲት 25/2017 ዓ.ም ለጠዋት 3 00 ሰዓት ፍ/ቤቱ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

26 Feb, 09:08

1,982

https://youtu.be/ToerHIYDf6U?si=NckvaWc0MpdtBgH6
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

25 Feb, 17:58

2,379

https://youtu.be/CdbndIKMnoQ?si=gH6E0Szzu_0c4Iqw
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

25 Feb, 16:34

2,214

ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ኮር (፩ኛ ኮር) የኮር ምሥረታ መግለጫ

የአማራ ፋኖ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ዘርፈ ብዙ የሕልውና ጥቃት ለመመከት ከአባቶቹ የወረሰውን ለፍትሕ የመቆም የሞራል ልዕልና ተንፍሶ በይፋ ነፍጡን ካነሳ እነሆ 20 ወራትን አሥቆጥሯል። የአማራ ሕዝብ በአራቱም የኢትዮጵያ አቅጣጫዎች በጅምላ ሢገደል፣ በጅምላ ሢፈናቀል፣ በጅምላ ሢሠደድ፣ የፖለቲካ ሤራ ሲተወንበት፣ ርሥቱን ሢቀማ፣ ማንነቱ ሢሠረዝበት፣ በኢኮኖሚው ደካማ እንዲሆን ሢደረግ፣ መዋቅርን መሠረት ያደረገ ዘርፈ ብዙ የሕልውና ጥቃት ሢፈጸምበት፣ ቤተ ዕምነቶቹ ሢወድሙበት፣ የአማራ አርሶ አደር ማዳበሪያ ሲከለከል፣ በደሙና በክቡር መሥዋዕትነቱ ያመጣውን የ2010 ዓ.ም ለውጥ በሴረኞች ቁማር የትግል ባለቤትነቱን ሲነጠቅ፣ በመሠረታት ሐገሩ እንደ ባይተዋር ተቆጥሮ ተቅባዥና አገር አልባ ሢደረግ፣ ከአማራ ክልል ውጭ ባሉ አማሮች ላይ ይፈጸም የነበረ የጅምላ ጥቃት ቤቱ ድረሥ አንኳኩቶ በጅምላ ሢገደልና በአገዛዙ አሉ የተባሉ መሣሪያዎች ሁሉ በአማራ ሕዝብ ላይ በጭካኔ ሢፈጸም ጥበበኛው የጥበብ ልጅ ታላቁ የአማራ ፋኖ ብዕር ንቀል ሢል ነፍጡን አነሥቷል። የአማራ ፋኖ የተቀደሰውን የፋኖ ትግል በመቀላቀል የሕዝቡን ሰቆቃ ለመከላከል ራሱን አሳልፎ በመሥጠት ከትምሕርትም ሆነ ከሐብት ታላቁን ነጻነት አሥቀድሞ በክቡር መሥዋዕትነቱ አምሐራዊ ነጻነቱን ለማረጋገጥ ዱር ቤቴ ብሏል።

የአማራ ፋኖ ባንክና ታንክ የታጠቀውን አገዛዝ ለመግጠም በቂ አመክንዮው አምሐራዊ መገፋት ነው። የአማራ ልጆች ከተለያዬ አቅጣጫ በዬመዳረሻቸው ለአማራነት ተሰባሰቡ፣ ሠለጠኑ፣ ተደራጁ፣ መዋቅርን ዘረጉ። በአጭር ጊዜና በፈታኝ ሁኔታ ከትንሿ አሃድ ጀምረው እሥከ ዕዝ ብሎም አንድ ማዕከል ያለው አማራዊ ተቋም በመሥራት ላይ ይገኛሉ። የአማራ ልጆች ባዶ እጃቸውን ወጥተው አሁን ላይ ከነፍሥ ወከፍ መሣሪያ እሥከ ትልልቆቹ የቡድን መሣሪያዎች ለመታጠቅ ችለዋል። ይህ ትግል ሁለገብ ትግል እንደመሆኑ መጠን አማሮች በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ሆነዋል።

የትግሉ ባለቤት መሬት ላይ እዬተዋደቀ ያለው የአማራ ፋኖ እንደሆነ አሥረግጦ ያሣውቃል። ''የነጻነት ተፋላሚው ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ እንዳለው ይህ የታጋይ ሥብሥብ ተጠሪነቱ ለታላቁ አማራ ሕዝብ እንጅ ለግለሰቦች፣ ለቡድኖች፣ ለዳያሥፖራዎች፣ ለቁማርተኛ ፖለቲከኞች፣ ለሀሳዊ ሚዲዬዎችና ለደም ነጋዴ ታጋይ ነን ባይ ጥቅመኞች አይደለም።'' ፋኖ የአማራ ሕዝብ መዳኛነቱን በደሙ፣ በአጥንቱና በክቡር መሥዋዕትነቱ እያረጋገጠ ይገኛል።

ለአማራ ሕዝብ ትልቁ የማሸነፊያ ቁልፍ መንገድ አንድነት ነው። የአማራ ፋኖ የትግል መንገድ የተቀደሰ ነው። ሌሎችን በመጉዳትና በመጥላት ሳይሆን ራሥን በማዳንና በመውደድ የሚደረግ ተጋድሎ ነው። በዚህ ሠዓት አምሐራ ዋጋ እዬከፈለ ያለው በነገደ ማንነቱ ነውና አማራ ሆኖ ከመቆምና ከመታገል ውጭ አማራጭ የለውም። ሥለዚህ እንደ አማራ ለመቆም መሠባሠብና መደራጀት የግድ ይላል። ፊት ለፊታችን ላይ የተደነቀረው ጨለማ የሚገለጠው በብርሃን ነውና የሕልውና መጠቃታችን የሚመከተው አማራዊ ሆኖ በመቆም ነው። ሥለሆነም በየትኛውም መዳረሻ ያሉ አማሮች ወደ አንድነት እየተሰባሰቡ ይገኛሉ። ከ5ቱ እዞች አንዱ ''የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር'' ነው። ይህ ተቋም በመላው አምሐራ ጭፍጨፋ እዬፈጸመ ያለውን የፋሽሥተ ናዚዝሙ የአቢይ አሕመድ አገዛዝ ለማምበርከክ ከሌሎች አማራ ደሞቹ ጋር በመሆን ፊቱን ወደ አራት ኪሎ ለማድረግ በቀጠናው ላይ ያሉ ክፍለ ጦሮች በኮር እንዲሰባሰቡ አድርጓል። የዚህ ኮር መፈጠር አሥተዋጽኦ በቀጠናው ላይ ያለውን የተናጠል ጉዞ አንድ ማድረግ፣ በፋኖ ሥም የተሰባሰቡ ወንጀለኞችን ለመያዝ፣ ሕዝቡን እዬዘረፉ፣ እያገቱ፣ እየገደሉና በቀል እዬፈጸሙ ያሉ የወገን ጠላቶችን እጅም ለመቁረጥ ሢሆን በዋነኝነት በአንድነት አገዛዙን ለማምበርከክ ነው።

በዚህም መሠረት በአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ሥር ያሉት ክፍለ ጦሮች፦
አጼ ፋሢል ክፍለ ጦር
ኢንጅነር ሥመኘው ክፍለ ጦር
ጉና ክፍለ ጦር
ጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር እና
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር
በአንድነት ራሣቸውን ''ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር
(1ኛ ኮር) ሢሉ አደረጃጀት ፈጥረዋል። በዚህ መሠረትም የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር መዋቅሩን በሚከተለው መልኩ ሠርቷል።

ሜ/ጀ/ውባንተ አባተ ኮር ሥራ አሥፈጻሚዎች፦
1. ኮር ሠብሣቢ- አርበኛ አመኑ ዓለም አንተ
2. ኮር ምክትል ሠብሣቢ -አርበኛ መምሕር ጌታቸው አዱኛ
3. ዋና ወታደራዊ አዛዥ-አርበኛ በላይነህ ዳኛው
4. ም/ወታደራዊ አዛዥ- 100 አለቃ ኃይለኢዬሡሥ ታደሰ
4. ዋና ወታደራዊ ዘመቻ-አርበኛ ቢራራ ደምሴ
5. ዋና ፖለቲካ መምሪያ ኃላፊ- አርበኛ ዘመነ እረኛው
6. ም/ፖ መምሪያ አዛዥ- አርበኛ አንዱዓለም አሰፋ
7. ወታደራዊ አሥተዳደር - አርበኛ ኃብታሙ ወርቄ
8. ሎጂሥቲክሥ- አርበኛ አብዩ ማሩ
9. ሕዝብ ግንኙነት-...
10. ሥልጠና መምሪያ-አርበኛ አሠፋ አውለው
11. ፅ/ቤት ኃላፊ- አርበኛ ይበልጣል ጣፈጠ
12. መረጃ...
.
.
.
24
የሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር በሚንቀሳቀሥባቸው ቀጠናዎች ውሥጥ ፈጽሞ የተከለከሉ ድርጊቶች

1.ፋኖነትን ምሽግ በማድረግ በዜጎቻችን ላይ የሚፈጸሙ ዝርፊያዎች፣ እገታዎችና ግድያዎች ላይ ለናኖ ሰከንድ ትዕግሥት የለንም።

2.ከኮሩ እና በኮሩ ውሥጥ ካሉ ክፍለ ጦሮች ዕውቅና ውጭ በግለሰብም ይሁን በቡድን የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈጽሞ የተከለከለ ነው።

3. በኮሩ ቀጠና ያለ ማሕበረሰብ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የኮሩን የትግል እንቅሥቃሤ ለአገዛዙ አሣልፎ ለመሥጠት(እንቅፋት ለመሆን የምትሰሩ ሁሉ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ)።

4. በኮራችን አደረጃጀታችን ውሥጥ ያለ ማንኛውም አባል የሐሳብ እንጅ የአላማ ልዩነት ካለ ከአላማችን ውጭ ሢንቀሣቀሥ ቢገኝ ተቋማችን አሥፈላጊውን ርምጃ ይወሥዳል።

አማራ በልጆቹ የተባበረ ክንድ ያሸንፋል።
ሜ/ጀ ውባንተ አባተ ኮር
አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር
ጎንደር/አማራ/ ኢትዮጵያ
የካቲት 18 ቀን 2017 ዓ.ም.
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

25 Feb, 13:03

2,488

በዛሬው ዕለት አሸባሪው የብርሀኑ ጁላ ጦር ከሰከላ ወደ ቲሊሊ ዙ-23 በመያዝ ተንቀሳቅሶ የነበር  ሲሆን  ግዮን ብርጌድ አናብስቶቹ አባግስ ሻለቃ፣ ግትም ሻለቃ እና ሀይሌ አድማሱ ሻለቃ በጋራ ወደ ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ዘልቀው በመግባት ባንዳ ሚኒሻ እና ፖሊስ ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።

በዚህ አውደ ውጊያ ባንዳ ሚኒሻ ሙት እና ቁስለኛ ሆኗል። አባግስ ሻለቃ እና ግትም ሻለቃ ጠላት ከሰከላ ግሽ አባይ ወደ አምቢሲ በሚንቀሳቀስበት ሰአት በረው ወደ ከተማ በመግባት ጠላትን በተደጋጋሚ እያሽመደመዱት ይገኛል።

ፋኖ ከተማ ከመግባቱ በፊት  አሸባሪው ሀይል ቀድሞ ባዘጋጃቸው  ባንዳ ሚኒሻን የፋኖን ልብስ በማልበስ ሁለት የንግድ ባንክ ተቋማትን ሲዘርፉ  ያዩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የግሽ አባይ ከተማ ኗሪዎች ለፋኖ ተናገሩ።

አሸባሪው ሀይል በግዮን ብርጌድ የደረሰበትን ኪሳራ መቋቋም ሲያቅተው ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል የማያደርገው ነገር እንደሌለ እና የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም። ከአሁን በፊት መስከረም 29/2017 የብርሃኑ ጁላ ጦር ከንግድ ባንክ ከ3 ሚሊዮን ብር ባላይ መዝረፉ ይታወቃል ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለጦር የግዮን ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት የቻለ አድማሱ ገልጿል ።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

24 Feb, 18:39

2,685

https://youtu.be/2uJdNLAj7YI?si=BjrwFBzk7iyqlORn
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

24 Feb, 15:33

2,892

በትናንትናው ዕለት አሸባሪው የብርሀኑ ጁላ ጦር ወደ አምቢሲ ለደፈጣ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለ ጦር አይበገሬዎቹ ግዮን ብርጌድ መብረቁ ሻለቃ፣ ናደው ሻለቃ፣ ሀይሌ አድማሱ ሻለቃ እና ዘንገና ብርጌድ ጥምረት በመፍጠር ጠላት ምሽግ ወደ ያዘበት ቦታ በመሄድ 5 የአገዛዙን ወታደር የደመሰሱ ሲሆን በርካታ የጠላት ሀይልም ሊቆስል ችሏል።

የካቲት 15/2017 ከሞት የተረፈው የድባቤ ጦር በትናንትናው ዕለት የአናብስቶቹን ምት መቋቋም ሲያቅተው ግማሹ ወደ ግሽ ሲፈረጥጥ ግማሹ ደግሞ መውጫ አጥቶ አምቢሲ ጊወጊስ ቤተክርስቲያን በመግባት የቤተክርስቲያኑን ካብ ምሽግ በማድረግ ህይወቱን ታድጓል።

አሸባሪው ሀይል በተደጋጋሚ ቤተክርስቲያንን እና የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ለምሽግነት እየተጠቀመባቸው ይገኛል።

በዚህ ሀፍረትን የተከናነበው የድባቤ ጦር ሰከላ ወረዳ አምቢሲ ቀበሌ ኗሪ የሆኑ ንጹሀንን እና የሀይማኖት አባት ቄስ አንዷለም የተባለ የ60 ዓመት ካህን፣ተሻገር የተባለ የ50 ዓመት ንጹሀን እና  አስሬ የተባለ የአዕምሮ ህመምተኛ  እርቃኑን የሚጓዝ እብድ  በአሸባሪው ሀይል ከቤት እያወጣ  ከምሽቱ 12:0ዐ የረሸናቸው  ሲሆን የሽ የተባለች የ35 ዓመት እናት በአሸባሪው ሀይል ቆስላለች ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ ክፍለጦር የግዮን ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ የቻለ አድማሱ
ኢትዮ 251 ሚዲያ
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

24 Feb, 10:35

2,868

ደጋዳሞት ብርጌድ በዚህ ሳምንት!!!

በመደበኛ ተዋጊነቱ ጠላቶቹ ጭምር የሚመሰክሩለት ደጋዳሞት ብርጌድ ከቅርብጊዜ ወዲህ የሰርጎ ገብ ጥቃቶችን እየፈፀመ  ይገኛል።

ለአብነትም በቀን 15/6/2017 ዓ.ም ለበርካታ ጊዜያቶች ሚሊሻ በመመልመል እና በማሰልጠን አገዛዙን ሲያገለግል የቆዬ ይሌ ልንገረው የተባለ ባንዳ በተናዳፌዎቹ የብርጌዱ አባላት እሰከ ወዲያኛው ተሰናብቷል።

በዕለቱም ገብያው ክንዴ የተባለ አንድ ወጣት ያለምንም መሳሪያ ዱላ ብቻ ይዞ ፈረስቤት ከተማ ውስጥ በመግባት ልዩ ስሙ ጠጠር ድንጋይ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ የአገዛዙን ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት አባል አናቱን ፈንክቶ አንድ ማይካ ክላሽ በመንጠቅ የደጋዳሞት ብርጌድ 1ኛ ሻለቃን ተቀላቅሏል። ሌላው በዚህ ዕለት የተከናወነው አበይት ተግባር ላለፉት አንድ አመት ከሰባት ወራት ከብርጌዱ ጋር ሲዋደቁ የከረሙት አርሷ አደሮቻችን ለቀጣይ ግዳጅ ዝግጁ መሆናቸውን ለማሳየት የሚያስችል ተሀድሶ አድርገዋል።

በተሀድሶው ላይም የአስር ቀበሌ የጦር መሳሪያ ባለቤት አርሷደሮች የተገኙ ሲሆን በክብር እንግድነት ደግሞ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው፣ የአደረጃጀት መምሪያ ሀላፊ አርበኛ እሸቱ ጌትነት፣ የሠው ሃይል ክፍል ሃላፊ መቶ አለቃ እሱባለው፣ የአደረጃጀትመምሪያ ምክትል  ሃላፊ አርበኛ ስለሺ ከበደ፣ የመረጃ እና ደህንነት መምሪያ ምክትል ሃላፊ ዶ.ር ጋሹ እንዲሁም የደጋዳሞት ብርጌድ አመራሮች ተገኝተዋል። በሌላ በኩል ደግሞ የደጋዳሞት ብርጌድ እና የሻለቃ አመራሮች በቀን 16/6/2017 ዓ.ም ጥልቅ የስራ ግምገማ  ያደረጉበትን ውይይት አከናውነዋል።

በውይይቱ ላይም የትግሉ አሁናዊ ፈተናዎች፣ ዕድሎች እንዲሁም ደግሞ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ሃሳቦች ተነስተው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶባቸዋል።

አዲስ ትውልድ፣
አዲስ አስተሳሰብ፣
አዲስ ተስፋ!!!

የአማራ ፋኖ በጎጃም 2ኛ ክ/ጦር ደጋዳሞት ብርጌድ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

24 Feb, 07:37

2,791

https://youtu.be/TCUCLgoXPGw?si=oaldIcsMqxKk0kiE