Últimas publicaciones de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 Suscriptores
727 Fotos
95 Videos
Última Actualización 06.03.2025 17:16

Canales Similares

Ethiopia Insider
15,446 Suscriptores
AACRA
10,040 Suscriptores
ጦብያን በታሪክ
7,786 Suscriptores

El contenido más reciente compartido por Roha Tv/ሮሃ ቴቪ en Telegram

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 17:12

2,153

አብይ አህመድ የጎረቤት ሀገራትን ወታደራዊ ድጋፍ ጠይቋል።

በፋኖ እየተሸነፈ ያለው አብይ ግራ ቀኝ አማራን በማስወረር ነፍስ ለመግዛት እየተጋጋጠ ነው።

ለዚህ ሙከራው ማሳያ:-

1ኛ. ከሁለት ሳምንት በፊት አፋርን በድሮን ጨፍጭፎ ጅቡቲ አጠቃች ተብሎ ተዘገበ።

2ኛ. ቀጥለው ኬንያ እና ብልፅግና በትብብር ሸኔን ደመሰሱ ሲሉ ዘገቡ።

3ኛ. እንደገና ኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን ዶላር ለሱዳን በእርዳታ መልኩ ሰጠች ተባለ

ይህ ሲተረጎም: በ 15 ሚሊዮን ዶላር የተገዛ የሱዳን ወራሪ በመተማ በኩል ይመጣል ማለት ነው።

አብይ ወደ መተማ በርካታ ሃይል እያስጠጋ ነው። በሱዳን በኩል የግዥ ወራሪ ሊያመጣ ይችላል።

የቀጠናው ፋኖ ተዘጋጅቶ ጠላትን መቀጥቀጥ አለበት።

አብይ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመሸራረፍ ለጎረቤት ሀገራት በማጎንበስ ታላቂቱን ሀገር አዋርዷል። ለነጮች በማጎብደድ ነባር እምነቶችን እየሸረሸረ የብልጽግና ወንጌልን በመስበክ ቅዳሴ እና አዛን እረበሸን ብሏል። ይህን እርኩስ በጋር ታግሎ ማስወገድ ተገቢ ነው።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 14:52

2,159

አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ ) ምዕራብ ወሎ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የደቡብ ወሎ ብልፅግና ዶሮ ጭራ የምታወጣው መላ እና ሴራ ቢያሴርም፣ ሲያሴርበት የነበረው እና ሙሉ የኦፕሬሽን ዕቅዱ በፋኖ እጅ ገብቷል::

በዚህም ዕቅዳቸው ለማስመሰል እና ዋሽተው ለማውራት እና ለማቀድ ቢሞክሩም ከራሳቸው እንኳን እንደሆነው የሥርዓቱ ግባ ተመሬት መድረሱን የሚያሳይ መሆኑን ማየት ችለናል፣ በየዘርፉ ሲገማገሙ እንደነበረው በራሳቸው የውሸት ሥሌት እንኳ በዞኑ ካሉ ወረዳዎች ከ217 በላይ ቀበሌዎችን ፋኖ እንደተቆጣጠረ አጉልተው አሳይተዋል።

ከተወያዩበትም ሥጋት ቆፈን አስገባቸው የፋኖ ዉጤቶች
1. በፋኖ ትግል ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እንደተሸነፈ አሳይተዋል ::

2. በስሩት የውሸት ዶክመተሪ ቪዲዮ ህዝብ እንደታዘባቸው ታማኝነት እንደጡ አሳይተዋል።

3. የህዝብ ንብረት መዝረፋቸው ከመንግስትነት ይልቅ ዘለፊና ሽፍታ እንደሆኑ አመላክተዋል::

4. በትጥቅና ሬሽን ከፋኖ እንደሚያንሱ አምነዋል::
5. ዞኑን በራሳቸው ፀጥታ ለማስከበር ከአቅማቸው በላይ መሆኑን አምነዋል::

ሆኖም የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሸምድምድ ቡድን 45 ቀን የሚቆይ የኦፖሬሽን ዕቅዱ ከየካቲት 03 - መጋቢ 30 ዕቅዱን ከመጀመር ይልቅ በጭንቀት ቆፈን ውስጥ ገብቶ እየተርበተበተ ይገኛል::

ባወጣው ዕቅድም ውስጥ አሁንም በዋናነት ንፁህንን የማስቃየት እና የማንገላታት ዋነኛ ዕቃዱ ነው።
ከዚህም መካከል

1. የግለሰብ ትጥቅ መውረስ
2. የፋኖ ዘመድ ቤተሰብ ማሰር ፣ ማስቃየት እና ሀብት ንብረት መዝረፍ፣ ማቃጠል የሚል
3. በፋኖ ስም ማህበረሰቡ ላይ ፀያፍ ስራ በመስራት ፋኖን ከህዝብ መነጠል የሚሉት እና ሌሎች ፀያፍ ድርጊቶች ታቅደዋል።

አሸባሪ ቡድኑ በአጠቃላይ 113 ገፅ ያለው Power Point በሽብር ሥራው አዘጋጅቶ እንደጨረሰ እጃችን ገብቷል።

ከዚህም ተያይዞ የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ ) አንድነት ጉባኤ የምዕራብ ወሎ ኮር ባደረገው መብረቃዊ እና አስደንጋጭ የሆነ የአብይ አህመድ ወንበር ጠባቂ ወታደር መማረክ እና መደምስስ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ብሎም ከወረዳወች አልፈው ዞኑ ድረስ ማርበትበታቸው ይባስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው እንኳን ለማሰብ ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ከውስጥ ካሉ ታማኝ የማረጃ ምንጮች ማረጋገጥ ችለናል።

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)
የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 13:56

2,151

የአዛዡ መግለጫ ስለክፍለጦሩ

ከ6 ሺህ በላይ የታጠቀ ሃይል ያለውን የጉና ክፍለጦር ማፍረስ አይቻልም ሲል ጦር አዛዡ አሳወቀ
የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የሎጀስቲክ ሃላፊና የጉና ክፍለጦር ወታደራዊ አዛዥ ሻምበል አምሳሉ ማዘንጊያ የጉና ክፍለጦር ከእነ ሙሉ አቅሙና ክብሩ እንደቀጠለ ነው ሲል ሮሃን ጨምሮ ለሚዲያዎች በሰጠው መግለጫ ተናግሯል፡፡
ክፍለጦሩ የሚመጥነው መሪ አላገኘም ፣ አቅሙ የተዳከመ ሆኗል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ሃሰት ነው ያለው ሻምበል አምሳሉ ይህን የሚሉት ክፍለጦሩን ለምን እኛ አልመራነውም የሚሉ ናቸው ብሏል፡፡
ጉና ክፍለጦር ባለበት ቁመና ለምን ቀጠለ በሚል ለማፍረስ የሚሰሩ ሃይሎች ያሰራጩት መረጃ ነው የሚለው አዛዡ አሁን ላይ ከስድስት ሺህ በላይ የታጠቀ ሃይል ያለው ክፍለጦር ነው ሲልም ገልጿል፡፡


https://roha-tv.com/article_detail/490/
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 11:44

2,166

ጨፍጫፊው የብልጽግና ሰራዊት በህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ዘረፋ ፈፀመ።

በየደረሰት ንፁሀንን በመረሸን እና ንብረቶችን በማውደም የሚታወቀው የአብይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ የብርሀኑ ጁላ ጦር በዳንግላ ወረዳ አቫድራ ቀበሌ በህብረተሰቡ መገልገያ ተቋማት እና በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ዝርፊያ ፈፅሟል።

በተለይ የጨፍጫፊው ጦር ወደ አቫድራ ሲገባ በተደጋጋሚ ንፁሀንን ስለሚገድል የአካባቢው ማህበረብ ከቀበሌው በመውጣት ወደተለያዩ አካባቢዎች ይሰደዳል ለአብነትም ከሳምንት በፊት ወጣት አይተነው ደሴ የተባለ የወንደፋይ ተከስተ ቀበሌ ኑዋሪ እና የ18አመት ታዳጊ በበርሀ እርሻ ቆይቶ ወደ ቤተሰቦቹ ሲመለስ በአገዛዙ ተይዞ በበረሀ ሰርቶ ያጠራቀመውን ብር ከዘረፉ በውሀላ ወጣቱን ገድለው መንገድ ላይ ጥለውታል።

በዚህ የፍርሀት ቆፈን ውስጥ የገባው ህዝብ ቤቱን ጥሎ ሲሰደድ የአገዛዙ ሰራዊት የተዘጉ የግለሰብ ቤቶችን ሰብሮ በመግባት ከፍተኛ ዝርፊ ፈፅሟል ።

በዚህ ዝርፊያ ላይ ከግለሰብ ቤቶች በተጨማሪ የህዝብ መገልገያ ተቋማትም የድርጊቱ ኢላማዎች ነበሩ በዚህም የቀበሌው አገልግሎት ለማህበረብ ለማሰራጨት በማህበር የመጣ ስኳር የአቫድራ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ኮምፒውተሮች የላብላቶሪ እቃዎች እና የአቫድራ ጤና ጣቢያ ሙሉ በሙሉ እና በከፊል ተዘርፈዋል ።
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 10:28

2,097

https://youtu.be/fRfNQwmUAsw?si=sZ0l4HYyLBGfxBPb
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 10:23

2,020

13.አርበኛ ሄኖክ አዲሴ ----ምክ/ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ
14.አርበኛ ሞገስ አበራው ----የፖለቲካ ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ
15.አርበኛ አራጋው ያለው-----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ
15.1.አርበኛ ፍቅር መንግስቱ----የስትራቴጅክ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
16.አርበኛ ሽመልስ ትዛዙ -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ
16.1.አርበኛ አብደላ አያሌው -----የውጭ ጉዳይ መምሪያ ምክትል ኃላፊ
17. አርበኛ አበበ ቀዬ -----የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ
17.1.አርበኛ አሰፋ መሰለ -----የአደረጃጀት መምሪያ ምክትል ኃላፊ
18.አርበኛ አበበ ፈንታው ----የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ
18.1.አርበኛ ናትናኤል አክሊሉ ---የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ምክ/ኃላፊ
18.2.አርበኛ ምኒልክ ፈንታሁን --ሚዲያና ኮሚኒኬሸን ኃላፊ
19.አርበኛ ዚነት አደም-----የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ
19.1.አርበኛ አበበች ሲሳይ---የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ምክ/ኃላፊ
20.አርበኛ ደስታው መለሰ -------የጽ/ቤት ኃላፊ
20.1.አርበኛ አለባቸው ቀስቅሴ --ምክትል የጽ/ቤት ኃላፊ
21.አርበኛ ንጉስ አዳነ ----የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
21.1.አርበኛ አማረ አያሌው --የፋይናንስና ግዥ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
22.አርበኛ ረዳ ውበቱ ----------የሐብት አፈላላጊ መምሪያ ኃላፊ
23.አርበኛ እስራኤል እሸቴ ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
23.1.አርበኛ ፍቅሩ ፈንታ---የሕዝብ አስተዳደር መምሪያ ምክ/ኃላፊ
24.አርበኛ አክሎግ ሲሳይ-------የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ መምሪያ ኃላፊ
25.አርበኛ ****-የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ
25.1.አርበኛ *****-ምክ/የመረጃና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ መሆናቸውን ለሰራዊታችንና የኅልውና ትግላችንን በስስት ለሚመለከተው በአገር ውስጥና በውጭው ዓለም ለሚኖረው ሕዝባችን መግለጽ እንወዳለን።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ለትግሉ ደጋፊዎች በሙሉ፣ ለአማራ ሕዝብ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለሥራዓቱ ደጋፊዎች የሚከተለውን መልዕክት ማስተላለፍ እንወዳለን!

1. የበሰበሰውን የብልጽግና ሥርዓት በመደገፍ ወይም የሥርዓቱ አመራር በመሆን እያገለገላችሁ ያላችሁ አካላት፣ በብልጽግና መንግሥት መከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ተቋማት ያላችሁ መሪዎችና የሰራዊት አዛዦች ብዙ የሥራ ባልደረቦቻችሁ እንዳደረጉት የአማራን ሕዝብ የኅልውና ትግል እንድትቀላቀሉ ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) ጥሪ ያቀርብላችኋል፡

2. ውዱ የአማራ ሕዝብ - የሥርዓቱ ሕይወት የሆነውን መንግሥታዊ መዋቅር በማፈራረስ፣ የሥርዓቱ ጠባቂ የሆነውን የብርሃኑ ጁላን ሰራዊት በማግለል ከትጥቅ ትግልህ ጎን ለጎን በሁሉም ከተሞቻችን በሕዝባዊ ማዕበል ስርዓቱን ለመገርሰስ ዝግጁ እንድትሆን እናሳስብሃለን።

3. ውድ ኢትዮጵያዊያን - አብይ አህመድ ሁሉም አባገነኖች እንደሚያልፉት በቅርብ ቀን ያልፋል! የማያልፉት ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያ ናቸው! የአማራን ሕዝብ የኢትዮጵያ አካል ነው ብሎ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ፋሽስቱን አብይ አህመድንና የገማውን ሥርዓቱን እንዲቃወምና ከአማራ ሕዝብ ጎን እንዲሰለፍ በአማራ ሕዝብ ስም የትግል ጥሪ እናቀርባለን።

4. በውጭው ዓለም የምትኖሩ ወገኖቻችን የሥርዓቱን ሁለንተና ለመገርሰስና ከሕዝባችን ጫንቃ ላይ ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ አውርዶ ለመጣል የምናደርገውን ትግል በገንዘብ እንድትደግፉ፣ የዘር ጭፍጨፋውን በዲፕሎማሲና በአደባባይ ሰልፎች ለዓለም መንግሥታት፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለዓለም አቀፉ ማህበርሰብ ደጋግማችሁ እንድታጋልጡ እናሳስባለን።

ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)
ወሎ፣ አማራ፣ ኢትዮጵያ፤
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 10:23

1,731

ከአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የተሰጠ መግለጫ

ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፅመው ጭፍጨፋ የሕዝባችንን ትግል አይቀለብሰውም!!!
መንግሥት መር ጭፍጨፋው በሕዝባዊ የፋኖ ትግል ይቀለበሳል!!!

ፋሽስቱና ደም የጠማው የጠራራ ጋኒን አብይ አህመድ በሕዝባችን ላይ የከፈተውን መንግሥታዊ ጦርነትና እየፈፀመ ያለውን የዘር ማሳሳት፣ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት የሰማይ አምላክ ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ በተለይ ኢትዮጵያዊያን የተረዱት ጉዳይ ነው ብሎ ማሰብ ያስቸግራል። አምባገነኑ የብልፅግና ቁንጮ፣ የኢትዮጵያዊያን የዘመናችን ታላቁ መርገም አብይ አህመድ ሲፈልግ በምድር ጦር፣ ሲፈልግ በሰማይ ጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ሁለንተናዊ ፍጅት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዐይንና ጀሮ ሳይሰጠው እንደቀልድ ሁለት ዓመት እያለፈው ነው።

የአማራ ሕዝብ በታንክና በመድፍ እንዲሁም በጀትና በሰው አልባ ድሮን ጥምረት የሚጨፈጨፍበት መሠረታዊ ምክንያት የሰው ልጅ በዴሞክራሲያዊው ዓለም ሊከበሩለት የሚፈልጋቸውን ልዩና የዴሞክራሲያዊ መብቶች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም የመንገድና መብራት፣ ፋብሪካና ዘመናዊ ከተሞች ስለጠየቀ አይደለም! ወይም በምከፍለው ግብር ልክ ልዩ ልዩ የጤናና የትምህርት ተቋማት ይከፈቱልኝ ስላለም አይደለም! የአማራ ሕዝብ የመብትና የኑሮ ማሻሻያ ጥያቄዎችን ይዞ ሳይሆን የወጣው ሰው ተብሎና ሰው ሆኖ መኖር በመከልከሉ የሕጋዊ ሰውነት እውቅናን፣ የሕግዊ ሰውነት ውክልናን እንዲሁም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በኢትዮጵያ ምድር ላይ በሕይወት መኖር መቻልን ለመጠየቅ የወጣ ህዝብ ነው፤ መንግሥታዊ ጦርነት የተከፈተበትም ተፈጥሮ በሰጠው ዘመን ውስጥ በሕይወት መኖርን ስለጠየቀ ብቻና ብቻ ነው። የአማራ ህዝብ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ውሎች ሁሉንም ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱና በሰውነቱ ልክ ይወቁት፣ ይዳኙት፤ እኔንም ሕጋዊ የዜግነት እውቅናና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ይስጡኝ፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋርም እኩል ይዳኙኝ የሚል የመኖር ያለመኖር ጥያቄ ነው። በሕዝባችን ጥያቄ ውስጥ በሀገራችን መንግስት በዘራችን ምክንያት ማንነታችን ሳይከዳ፣ ማንነታችን ሳይሳሳና ሳይጠፋ በሕግ ታውቆ መኖርን፣ እኩልነትን፣ ዲሞክራሲንና ፍትሕን የምናገኝ ሲሆን ይህም የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረት ነው። ኢትዮጵያዊያን ግን ልብ ያሉት አይመስልም።

የሰላም ኖቤል ተሸላሚው ሕዝብ ጨፍጫፊውና ጦረኛው አብይ አህመድ ግን እነዚህን የከበሩ የሕዝብ ጥያቄዎች የአማራን ሕዝብ በማንበርከክ ጥያቄዎቹን ድጋሜ እንዳይነሱ ማድረግ ካልሆነም የአማራን ሕዝብ ማጥፋትን ዓላማዬ ብሎ መያዙ ገሃድ የወጣ ሐቅ ነው። በአንዳንድ ፀሐፍት አምባገነኑ ሦስተኛው የዩጋንዳ ፕሬዝደንት ኤዲ አሚን ዳዳ ዘር መርጦ የሰውን ልጅ ስጋና ደም ላልተገባ ተግባር ያውላል ተብሎ እንደተጻፈው ጭራቁ አብይ አህመድን የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ ብሎ በከፈተው ጦርነት የአማራን ልጅ ስጋና ደም እየተመገበ ያለ ሰው በላ መሆኑን ኢትዮጵያውያንም ሆነ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊገነዘበው የሚገባ እውነት ነው። የአማራ ሕዝብ በማንኛውም የታሪክ አጋጣሚ በሀገሩ መሪና መንግሥት በዚህ ልክ የዘር ጭፍጨፋ ደርሶበት አያውቅም። ፋሽስቱ የጣልያን ወራሪ ክ1928 -33 ዓ.ም ካደረሰው በደል በማይወዳደር መልኩ በሕዝባችን ላይ በዚህ አምሳ ዓመት የደረሰበት በደል የላቀ ሲሆን የሀገር ልጅ በሆነው አብይ አህመድ የደረሰበት በደል ግን የሁሉ ቁንጮ ሆኖ በገሀድ የምናየው ጉዳይ ነው። የአማራን ሕዝብ ባሪያ አደርገዋለሁ ብሎ ቆርጦ የተነሳው አባገነን የገባበት ቅጀት ውስጥ ለመውጣት የሰላም ነጋሪት ቢጎሰምለትም መንቃት የሚፈልግ አይደለም።

ሰሞኑን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ)ን የጠቅላላ ጉባዔ ዓመታዊ ስብሰባን አደናቅፋለሁ ብሎ በማሰብ አመራሮቹ በሌሉበት በደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በጀትና በድሮን የፈፀመው የንጹሓን ጭፍጨፋ የዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። አማራ መሆናቸውን የማያውቁ ሕጻናት በአብይ አህመድ የግል ንብረት በሆነው አየር ኃይል አማራ ተብለው ተጨፍጭፈዋል።

በእርግጥ የተሸነፈ ስነ ልቦና ባለቤት የሆነውና የስልጣን ጥሙ ከአካሉ የሚገዝፍበት - ከአዕምሮው የሚሰፋበት ይህ የዘመኑ የአፍሪካ አባገነኖች ቀንዲል ከምድር ጦር በዘለለ ሰው አልባ አውሮፕላንና ጀት የሚጠቀመው የሽንፈት ፅዋውን እየተጎነጨ ስለሆነ ነው። ኢትዮጵያዊው ኤዲ አሚን ዳዳ በሕዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ጭፍጨፋ ሕዝባዊ ትግላችንን አይቀለብሰውም፤ የተከፈተብን መንግሥት መር ጦርነትም እንደሕዝብ መደራጀታችንን፣ መታጠቃችንን፣ አምባገነናዊ የብልፅግና ሥርዓትን ማስወገዳችንን አያስቀረውም። ሥርዓቱ በሕዝባችን ላይ የሚፈፅመው በደል ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ የሚያበረታን እንጅ ክንዳችንን የሚያዝለው አይሆንም።

ስለሆነም ይህንን የአብይ አህመድን ሰይጣናዊ ተግባር ለመቀልበስ በቤተ አማራ (ወሎ) የምንገኝ ፋኖዎች በቀን 14/05/2017 ዓ.ም ወደ አንድነት መምጣታችን ይታወቃል። በመሆኑም ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) የመጀመሪያውን የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባውን በማድረግ በስኬት ያጠናቀቀ ሲሆን የማዕከላዊ ምክር ቤትንና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውንም አዋቅሯል፤ በሥራ አስፈጻሚና በልዩ ልዩ መምሪያዎች ደረጃ የተመደቡ አመራሮችና ምደባውም የሚከተለውን ይመስላል።

1.ዋርካው ምሬ ወዳጆ --------ሰብሳቢ
2.አርበኛ ድርሳን ብርሃኔ ------ምክ/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ
3.አርበኛ ሀብታሙ ደምሴ -----ምክ/ወታደራዊ አዛዥ
4.ኮሎኔል አባይ ባየው--------ወታደራዊ እቅድና ስትራቴጅ መምሪያ ኃላፊ
5. አርበኛ በለጠ ሸጋው ------ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
5.1. ኮሎኔል ፈንታው መኩዬ ----ምክትል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
6.ሺ ዓለቃ ያረጋል አሰፋ-----ወታደራዊ አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ
6.1. አምሳ ዓለቃ ሲሳይ ገላነው---ምክትል ኃላፊ - ለሰው ሃብት አስተዳደር መምሪያ
6.2. ዶ/ር አቡበክር ሰይድ---ምክትል ኃላፊ - ለጤና ጉዳይ
7.መቶ አለቃ በሪሁን ደምሌ---ሎጂስቲክስ መምሪያ ኃላፊ
7.1.አርበኛ ሞላ ሰማው ------ምክትል ኃላፊ - ለስንቅና ትጥቅ ስርጭት
7.2. አርበኛ ኢሳይያስ መልኩ----ምክትል ኃላፊ - ለኦርዲናንስ ክፍል
7.3. አርበኛ ኑረዲን አበበ ----ምክትል ኃላፊ - ለትራንስፖርት ስምሪት
8.መቶ ዓለቃ ዮሴፍ አስማረ ---ወታደራዊ ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
8.1. አርበኛ ጌታቸው ሲሳይ ----ምክትል የሥልጠና መምሪያ ኃላፊ
9.አርበኛ ** ---ወታደራዊ መረጃ መምሪያ ኃላፊ
10. አምሳ ዓለቃ አደም አሊ ----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን (ስርጸት) መምሪያ ኃላፊ
10.1.አርበኛ ሙላት አላምረው-----ወታደራዊ ኢንዶክትሪኔሽን መምሪያ ምክ/ኃላፊ
10.2.አርበኛ ተመስገን በቀለ ----የኪነትና መዝናኛ ክፍል ኃላፊ
11.አርበኛ ተሾመ ፈንታዬ -----ልዩ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ
12.ኮሎኔል ሞገስ ዘገዬ -----ወታደራዊ አማካሪ
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

15 Feb, 09:46

2,191

??#ለጠላት ሊቀርብ የነበረው ሬሽንና ባንዳው በቁጥጥር ስር ዋለ‼️

በቀደም የስራ ዘመኑ የመከላከያ አባል የነበረው መጋቢ ሻለቃ ባሻ ሞላ ፈረደ የተባለ ግለሰብ አሁን ከ 4 በላይ መታወቂያ በማሰራት ስሙን በመቀያዬር በባንዳነት መረጃ እና የሬሽን አቅርቦት መንገዶች በማሳለጥ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን  የአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ዳሞት ሻለቃ መንጋው ከፋለ ሻበል ጥብቅ ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት7/6/2017 ዓም ይህ ባንዳ ወደ ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ ለጠላት የሚውል ሬሽን ማለትም 9 የቀንድ ከብቶች (በሬ) ጭኖ ሲንቀሳቀስ ከነመኪናው በአናብስቶች ቁጥጥር ስር ውሏል💪
         መረጃውን የሰጡን የአረዛው ዳሞት ብርጌድ ፍኖተ ዳሞት ሻለቃ ም/ሰብሳቢ10 አለቃ አብርሀም ናቸው።
       አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
@የአፋጎ 5ኛ ክ/ጦር የሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሰፍ ሀረገወይን
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

14 Feb, 18:06

2,321

https://youtu.be/hQtcLkjB02Q?si=dmSft1A0any0w1Xb
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 20:06

667

ሰበር ዜና!
ቦካክሳ ከተማ በፋኖ ተያዘች!

የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ የምስራቅ አማራ ኮር 1 በአርበኛ እንድሪስ ጉደሌ የሚመራው  ባለሽርጡ ክፍለጦር  እና ልጅ እያሱ ኮር ራስ  አሊ ክፍለ ጦር 1ኛ ሻለቃ  የደቡብ  ወሎ ዞን ቦከክሳ ከተማን ታላቅ ጀብድ በመፈፀም ከወራሪውና ከዘራፊው ስርዓት ነፃ በማውጣት ተቆጣጠሩ፡፡

በተደረገው ተጋድሎ የስርዓቱ ዙፋን ጠባቂ  ሰራዊት እንዲሁም ሆድ አደር  ሚሊሻና አድማ ብተና ሙትና ቁስለኛ  ማድረግ ተችሏል፡፡

በዚህም ከሞት የተረፈው የዙፋን ጠባቂው ሰራዊት ከቦከክሳ ወደ ቢስቲማ  እየፈረጠጠ ይገኛል፡፡  

በዛሬው የህልውና ተጋድሎ 18 የዙፋን ጠባቂው ኃይል እስከወዲያኛው  ሲደመሰስ 10 የሚሆነውን ኃይል  ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዚህም ተጋድሎ  1500 የክላሽ ተተኳሽ እስከ ነፍስ ወከፍ መሳሪያ መመረክ ተችሏል።

የጀግኖቹን  በትር መቋቋም ያቃተዉ የባንዳ ጥርቅም የግለሰብን ሀብትና ንብረት እየዘረፈ፣ እያወደመ እና የዘወትር ልምዱ የሆነዉን በንፁሀን  ላይ በርካታ ግፎችን እየፈፀመ፣ የግለስብ ቤቶችን እያቃጠለ ፈርጥጧል፡፡

ይህን አመርቂ ድል እንድንጎናፀፍ ያደረገን አስቻይ ሁኔታ ደግሞ በቅርቡ የተመሰረተው የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ አንድነት ነው፡፡ ይሄን የሰሩና ይህ እንዲሆን ለተጉ የድርጅታችን አመራሮች ከልብ እናመሰግናለን።

"ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን"

ፋኖ መምህር መሀመድ ሞገስ 
የአማራ ፋኖ በወሎ /ቤተ-አማሓራ/ የምስራቅ አማራ ኮር 1 ባለሽርጡ ክፍለጦር   ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

የአማራ ፋኖ በወሎ/ቤተ-አማሓራ/
የካቲት 05/2017 ዓ.ም