Últimas publicaciones de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ (@rohatv1) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ
ትኩስ ወቅታዊና ታአማኒ መረጃዎችን የሚያገኙበት
ሮሃ ቴቪ የሀገሬው
8,730 Suscriptores
727 Fotos
95 Videos
Última Actualización 06.03.2025 17:16

Canales Similares

AL JAZEERA ENGLISH
18,205 Suscriptores
ሀገሬ ሚዲያ
11,454 Suscriptores

El contenido más reciente compartido por Roha Tv/ሮሃ ቴቪ en Telegram

Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 18:48

1,162

ደንደገብ_ባሶሊበን!

ዛሬ በ05/06/2017ዓ/ም የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ከጥዋቱ 1:00 ከበባ በማድርግ በሶሊበን ወረዳ በደንደገብ ቀበሌ ልዮ ስሙ ከብዳም ጎጥ ከአቶ ገድፈውን ቤት ከ70 በላይ ኩንታል ስንዴ ጭኖ ወስዷል::

አቶ ገደፍው የባሶ ሊበን ወረዳ የደንደገብ ቀበሌ ጊዜያዊ አስተዳደር ሲሆን ከትግል ማንም አያቆመኝም በማለት የአማራ ፋኖ በጎጃም የሀሐዲስ አለማሁ ክ/ጦር  የአብራጅት ብርጌድ ጋር በመሆን ስርዓቱን እታገላለሁ ብሏል:: ከጠላት ያበራችሁ በተለይ ሚሊሻ አዳም ብተና እና ፓሊስ የፋኖን በትር መቋቋሞ ሲያቅታችሁ ዝራፊያ የማያወጣ እንደሆነ  ብትረድ ጥሩ መሆኑን እያሳወቅን አደብ ያዙ እንላለን:: ለፈፀማችሁት አስነዋሪ ተግባር ነገ  እንጠያየቃለን!      
           
©አብራጅት ብርጌድ!!!!
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 17:07

1,579

https://youtu.be/tvtNEXcjaZM?si=UydyCdAPJ6f2NxPj
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 15:57

1,827

🔥አርበኛ ቃለአብ ወርቅዬ‼️

አርበኛ ቃለአብ ወርቅየ ይባላል።አማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ምዕራብ ወሎ ኮር አምሓራ ሣይንት መቅደላ ክፍለ ጦር ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ነው።

ጥንቅቅ ያለ ምሁር፣ እንደ ሼህ ሼረፈድን ያለ ቁጥብ ተናጋሪ፣ እንደ መምህር አካለወልድ አሰላሳይ እና እንደ ንጉሥ ሚካኤል ቆፍጣና እንዲሁም ስሩፍ ጀግና ነው።

በፋኖ ትግል ውስጥ በፖለቲካውና በኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ከሚገኙ ጀግኖች መካከል አንዱ የምዕራብ ወሎ ክስተት የሆነው አርበኛ ቃለአብ ነው።
ድል ለአንተና ለጓዶችህ!
ድል ለአማራ ሕዝብ!


መረብ ሚዲያ
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 13:04

2,124

በአዲስ አበባ የተሰራጨው መርዝ

አገዛዙ ከአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ አገልግሎት ላይ ያዋለው አደገኛ መርዝ ጉዳይ ስጋት ደቀነ

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መቃረቡን ተከትሎ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በታገደ መርዝ በርካታ ሺህ ውሻዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየተገደሉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በአለም ጤና ድርጅት አገልግሎት ላይ እንዳይውል በታገደ መርዝ በርካታ ሺህ ውሻዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየተገደሉ መሆኑን ከተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱን ጥቆማዎች ያሳያሉ።
በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደ ፒያሳ እና ካዛንችስ ያሉ ቦታዎች መፍረሳቸውን ተከትሎ መንገድ ላይ የቀሩ በርካታ ውሻዎች መኖራቸው ይታወቃል።
ይሁንና ቀጣዩን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶች "ጎዳና ላይ እንዳያዩዋቸው" በሚል ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ሺህ ውሻዎች በመርዝ እየተገደሉ እንደሆነ ታውቋል።
ባለፈው ወር የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሊመጡ ሲልም በተመሳሳይ ብዙ ውሻዎች በመርዝ መገደላቸው ታውቋል።
"መርዙ በአለም ጤና ድርጅት አገልግሎት ላይ እንዳይውል የታገደ ነው፣ እንዴትስ ወደ ሀገራችን ገባ የሚለው ጉዳይ አጠያያቂ ነው" ያሉት አንድ ጉዳዩን የሚከታተሉ ግለሰብ መርዙ ሰዎች እጅ ቢገባ ከአንድ የሻይ ማንኪያ እሩብ በታች በሆነ መጠን አንድ ሺህ ህዝብ ሊጨርስ ይችላል ብለዋል።
"መርዙ ሽታ የሌለው በመሆኑ በምግብም ሆነ መጠጥ ውስጥ ሊገባና ሰዎችን ለመጉዳት ሊውል ይችላል። በዚህ መርዝ ያለ ሃጢያታቸው እየተገደሉ ያሉ ውሾች የሚጣሉበት ቦታ ሌላው አውሬ ምግብ ያገኘ መስሎት የሞተውን በድን ሲበላ እንደሚሞት፣ ተያይዞም አሞራዎች በልተውት የተረፋቸውን ወንዝ ላይ ቢጥሉት ውሃው የሚመረዝ መሆኑ ሊታወቅ ይሀገባል" በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።
አክለውም ውሃው የከተማም ሆነ የገጠር የወንዝ ዳር አትክልት ልማት ላይ ሊውል ስለሚችል ተያያዥነቱ ረጅም በመሆኑ ህዝብ ሁሉ ይህንን ድርጊት እንዲኮንን ተማፅነዋል።
ሰውን ግድሎ አልጠግብ ያለው ብልጽግና አሁን ላይ ደግሞ የጭካኔ ግድያውን ወደ ውሻ ማዞሩ ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡ ይህ የግድያ ሱስ ያለበት የዐቢይ አህመድ አሰተዳደር በውሻ መርዝ ሰበብ የአዲስ አበባን ህዝብ እንዳይጨርስም ተሰግቷል፡፡
https://t.me/rohatv1
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 11:44

2,178

መረጃ ወሎ ቤተ አማራ

የአማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አማራ) ልጅ እያሱ ኮር ሁሉም ክፍለጦሮች በሚባል ደረጃ ከጧቱ 1:00ስዓት ጀምረው ከአገዛዙ ጥምር ጦር ጋር ከፍተኛ ትንቅንቅ እያደረጉ ይገኛሉ።

በዝህም ራምቦ ክ/ር  አምባሰል ወረዳ አበስ ቀበሌ ላይ ሀይለኛ ውጊያ እያደረገ ሲሆን ራስ አሊ ክ/ር ከሮቢት እስከ ድብል እንዲሁም ራምቦ ክፍለ ጦር አርባዎቹ ሽአለቃ ማርዬ ከተማ በመግባት የጨበጣ ውጊያ እያደረጉ ሲሆን  እንዲሁም ኩታበርና አካባቢው ላይ ቤተ አማራ ክፍለ ጦር ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ እንገኛለን ሲል ፋኖ ሙሃመድ ፈንታው ለቢዛሞ ሚዳያ ገልጿል።

በተያያዘ ዜና ከውርጌሳ ወደተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች መድፍና ሞርተር ዘፈቀ እዬተኮሰ እንደሚገኝ ገልጾ የአማራ ፋኖ በወሎ(ቤተ አማራ) ከፍተኛ አመራሮች  አምባሰል ወረዳ ላይ ስብሰባ እያደረጉ ነው አፍናለሁ ብሎ ሀይሉን በገፍ አሰልፎ የመጣውን ጥምር ጦር እንዳመጣጡ እያስተናገድነው እንገኛለን ሲል ፋኖ ሙሃመድ ፈንታው ገልጿል።

ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ
ድል ለክንደ ነበልባሉ ፋኖ
የካቲት 05/2017ዓ.ም
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

12 Feb, 08:56

2,285

https://youtu.be/HvBwZfHsV5I?si=2PGOa9mqiBLkTD6U
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 17:39

2,743

በዛሬው እለት በአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገውምድር(03ኛ) ክፍለጦር ውስጥ የምትገኘዋ የቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ እንጅባራ ብርጌድ የነበሩ አለመግባባቶችን በመፍታት በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ፖለቲካዊና ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ ስትራቴጂ ነድፈዋል። ጉዳዩንም ሲከታተሉ የቆዩት የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የዘመቻ መምሪያ ኃላፊው ጀግናው መቶ አለቃ ማርቆስ አሞኘ በብርጌዷ አሁን ለተደረሰው የጋራ ስትራቴጂ ንድፍ እና ለጠበቀው ትስስር ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ!!

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! 
የአ/ፋ/ጎ/03ክ/ጦር/የቀኝአዝማች ስሜነህ ደስታ እንጅባራ ብርጌድ የሕ/ግንኙነት ክፍል
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 17:29

2,464

https://youtu.be/AE4aMqUzi74?si=ELl1Lq-OBJzOKpUk
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 17:18

2,310

የአዲስአበባ ውሾች ግድያ!

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ መቃረቡን ተከትሎ አገልግሎት ላይ እንዳይውል በታገደ መርዝ በርካታ ሺህ ውሻዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየተገደሉ መሆኑ ታወቀ

- መርዙ ወንዝ ዳር የሚበቅል ምግብ ሊበክል እንደሚችል ተሰግቷል

(መሠረት ሚድያ)- በአለም ጤና ድርጅት አገልግሎት ላይ እንዳይውል በታገደ መርዝ በርካታ ሺህ ውሻዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየተገደሉ መሆኑን ከተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱን ጥቆማዎች ያሳያሉ።

በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደ ፒያሳ እና ካዛንችስ ያሉ ቦታዎች መፍረሳቸውን ተከትሎ መንገድ ላይ የቀሩ በርካታ ውሻዎች መኖራቸው ይታወቃል።

ይሁንና ቀጣዩን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶች "ጎዳና ላይ እንዳያዩዋቸው" በሚል ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በርካታ ሺህ ውሻዎች በመርዝ እየተገደሉ እንደሆነ ታውቋል።

ባለፈው ወር የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሊመጡ ሲልም ሲባልም በተመሳሳይ ብዙ ውሻዎችን በመርዝ መገደላቸው ታውቋል።

"መርዙ በአለም ጤና ድርጅት አገልግሎት ላይ እንዳይውል የታገደ ነው፣ እንዴትስ ወደ ሀገራችን ገባ የሚለው ጉዳይ አጠያያቂ ነው" ያሉት አንድ ጉዳዩን የሚከታተሉ ግለሰብ መርዙ ሰዎች እጅ ቢገባ በአንድ የሻይ ማንኪያ እሩብ በታች ሆነ መጠን ሺህ ህዝብ ሊጨርስ ይችላል ብለዋል።

"መርዙ ሽታ የሌለው በመሆኑ በምግብም ሆነ መጠጥ ውስጥ ሊገባና ሰዎችን ለመጉዳት ሊውል ይችላል። በዚህ መርዝ ያለ ሃጢያታቸው እየተገደሉ ያሉ ውሾች የሚጣሉበት ቦታ ሌላው አውሬ ምግብ ያገኘ መስሎት የሞተውን በድን ሲበላ እንደሚሞት፣ ተያይዞም አሞራዎች በልተውት የተረፋቸውን ወንዝ ላይ ቢጥሉት ውሃው የሚመረዝ መሆኑ ሊታወቅ ይሀገባል" በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ውሃው የከተማም ሆነ የገጠር የወንዝ ዳር አትክልት ልማት ላይ ሊውል ስለሚችል ተያያዥነቱ ረጅም በመሆኑ ህዝብ ሁሉ ይህንን ድርጊት እንዲኮንን ተማፅነዋል። (መሰረት ሚዲያ)
Roha Tv/ሮሃ ቴቪ

11 Feb, 15:18

2,386

የቀጠለው ውጊያና ውይይት

በሸዋና በወሎ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በጎጃም ቀጠና ደግሞ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው
ከየካቲት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በዘጠኝ የአውደ ውጊያ ሜዳዎች ሲገረፍ የሰነበተው የአገዛዙ ቡድን የአምስት ንፁሀን ግለሰቦችን ቤት አቃጥሎ መሸሹን የአማራ ፋኖ በሸዋ ለሮሃ በላከው መረጃ አሳውቋል።
ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ በመነሳት ወደበረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ ወታደራዊ ሬሽን ለማቀበልና የፖለቲካ አመራሮችን ለማሸሽ የሞከረው የአገዛዙ ጦር በከሰም ክፍለጦር ፋኖዎች በዘጠኝ የተለያዩ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ላይ ተመትቶ አስከሬኑን ጥሎ ቁስለኛውን ተሸክሞ ተመልሷል፡፡
ከየካቲት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ያህል በቆስጤ፣አክርሚት፣ምንታምር፣ራዩ፣ሜጢ፣ተሬ፣ወርቁአገር፣ጉራምባ እና አጉራቻ በተባሉ ቦታዎች የብልጽግናን ጦር ሲመቱት የሰነበቱት የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር ነበልባል፣ተስፋገብረስላሴና ሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ በከፊል ባደረጉት የተቀናጀና ኩታገጠም ኦፕሬሽን የአገዛዙ ቡድን ከፍተኛ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራን አስተናግዷል።
ይህ መረጃ እስከተላከበት ሰዓት ድረስ ውጊያው እንደቀጠለ መሆኑን የገለጸው የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለጦር ዋና ቃል አቀባይ ፋኖ ወርቁ ደርቤ የአገዛዙ ሃይል በምድር ላይ አለኝ ያለውን ከባድ መሳሪያና የሰማይ ድሮን ተጠቅሞ መንገዱን ለማስከፈት ቢሞክርም የከሰም ፋኖዎች ከሚያውቁት መልክዓምድራዊ አቀማመጥ ጋር በመዋሀድ ሙትና ቁስለኛ እያደረጉት ነው ብሏል፡፡
ሆኖም ሽንፈት ያስተናገደው አገዛዙ የአምስት ንፁሀን ግለሰቦችን ቤት አቃጥሎ አራት የቁም እንስሳትን ገድሏል ሲል ገልጿል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በመሃል ሳይንት ወረዳ ምክትል ሻለቃ አዛዥ እና ሁለት የሻንበል መሪዎችን ጨምሮ ከ30 በላይ የአገዛዙ ጦር መመታቱን የአካባቢው ምንጮች ለሮሃ ተናግረዋል፡፡
ትናንት ከማለዳ ጀምሮ ጀንበር እስኪገባ ከብልጽግና ጦር ጋር ሲፋለሙ የዋሉት የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አ/ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ብርጌድ ከፍተኛ ድል ማግኘታቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በሌላ መረጃ የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች እርስ በርሳቸውና ከወታደሮቻቸው ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡ የአንደኛ ክፍለጦር ሰብሳቢ ፋኖ መንግስቱ አማረ በሜጫ ከኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ አለማየሁ ከቤ ሻለቃ ፋኖዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

https://roha-tv.com/article_detail/489/