ስነ-ልቦናዊ ህይወት @psychological_mind Channel on Telegram

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

@psychological_mind


ስነ-ልቦናዊ ህይወት (Amharic)

ስነ-ልቦናዊ ህይወት አዲስ ማህበረሰብ ማየት እርሻ ነህለ ምርምር እንዲሆን፣ ምኞትን፣ ሻምባንን በአማርኛ ፣ ትልቅ ትምህርት መሆን ይችላሉ። እያንዳንዱ ትምህርት ያልዎ የህዝባችንን መዳህን በቀላሉ ማስወድ ይችላሉ። በምርመራ ውስጥ ከእርሻ የሚከናወን የፊት ቤተ ሰብ እና እያንዳንዱ በህይወት ለመቅረብ የሚያሰቅራት ረድፍ ይችላሉ። ስነ-ልቦናዊ ህይወት በሽብር ላይ እንዲሁም በተለያዩ ሚሊዮንስ ገብቶ ብቻ ቦታዎች አድርገለዋል።

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

10 Feb, 04:33


ጥበብን አስቀድም !

አንድ ነገር እወቅ ጥበብ ማለት በማንኛውም ሁኔታ የሰበሰብከውን እውቀት በተግባር ላይ ማዋል ነው።

ካልሆነ እውቀት ስላለህ አዋቂ ተብለህ ሰው ያጨበጭብልሃል እንጂ ጥበበኛ አትሆንም። ደሞ እኮ በ ሁለት ብር ኢንተርኔት የምታገኘውን መረጃ ማወቁ ብቻ ምን ይጠቅምሃል ?

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

06 Feb, 04:51


ማረጋገጫ አትጠብቅ 💪

አንተ ላመንክበት ራስህን ለሰጠኸው ህልምህ መጓዝህን ብቻ እርግጠኛ ሁን ማንም ላይቀበልህ ይችላል ነገር ግን አሁንም መራመድህን ቀጥል በቃ አለመቆም ይከፍላል

ማንም የልብህን አያውቅም አንተ ያመንክበትን ማንም ሊያምንበት አይችልም ስለዚህ ፈጣሪህን ያዝ እና ወደፊት 🏃‍♂🏃‍♂

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

01 Feb, 14:43


ወደፊት ብቻ 🏃‍♀

መቆም ባለህበት ቦታ ብቻ እንድትቀር ያደርግሀል በየቀኑ የሆነ ለውጥ ማምጣት ካልቻልክ ደግሞ ይባስ ወደኋላ እየተጎተትህ ነው ስለዚህ ነቃ በል እና ሁሌም ወደፊት ብቻ የሚያስኬድህን እውቀት ስራ !

የተባረከ ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

28 Jan, 13:23


ባንተ ሳይሆን በፈጣሪ ብርታት !

የሆነ ሁኔታ ውስጥ ገብተህ እወጣው ይሆን ወይ ብለህ ከተጨነቅህ አንድ ነገር አስታውስ እስካሁን ያደረግከውን ሁሉ ያደረገልህ የሆነው ሁሉ የሆነው ነገራቶችህን በሙሉ ያስተካከለልህ ያንተ አቅም ሳይሆን እርሱ ፈጣሪህ አብሮህ ስላለ ነው ዛሬንም እርሱን ይዘህ የማትወጣው ነገር የለም

ሁሉም በርሱ ሙሉ ነው !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

25 Jan, 06:04


አይቻልም !

እውነት ነው አንዳንዴ ነገሮች ባሰብንበት መንገድ አይሄዱም ፤ ባልጠብቀነው ሰዓት ያላሰብነው ነገር ይከሰታል በዚህ ሰዓት የምናልመው ነገር እንደማይቻል እናስባለን ፤

የዛሬ ጥያቄ : እውነት ግን ያሰብከው አይቻልም ነው ? ወይስ የሚቻልበት መንገድ እስከአሁን ስላልታየን ነው ?

መልካም ቀን ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

22 Jan, 03:06


እውነተኛውን ተከተል !

ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር ብቻ ይምራህ አለም ላይ ብዙ ነገር ሰምተሀል አይተሀል ከዚህም በኋላ ገና በጣም ብዙ ነገሮችን ታያለህ ነገር ግን ሁሉም አይጠቅሙህም ዛሬህን የሚገነባልህ ነገህንም የሚያራምድህ መልካምና ትክክለኛ የሆነውን የፈጣሪ መንገድ እየተከተሉ ማደግ ብቻ ነው !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

16 Jan, 05:29


ከሰው አትጠብቅ !

ህልምህን ለማሳካት ሩቅ መሄድ አይጠበቅብህም ሁሉ ነገር ያለው አንተ ውስጥ ነው ፤ ማንም ተነስቶ መጥቶ ህይወቴ ላይ ለውጥ ይፈጥርልኛል ብለህ አትጠብቅ ችሎታህ ላይ ትኩረት አድርግ አቅምህን ፈትሽ ከዚያም ጥረትህን ጀምር !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

14 Jan, 08:00


ከራስህ ጋር ተገናኝ !

ልክ እረፍት ስታገኝ ከራስህ ጋር በደንብ ተገናኝ አዳምጠው አዋራው ምን እያደረግኩ ነው ምን ላድርግ ምን ይቀረኛል ደስተኛ ነኝ ወይ ወይስ ይቀረኛል? ብዙ ልትጠይቃቸው የሚገቡ ጥያቄዎች አሉ ጠይቅ እንደዚህ ስታደርግ ህይወትህ በተለየ መልኩ ይስተካከላል !

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

11 Jan, 04:17


ጊዜ ጠብቅ !

ወዳጄ ፈጣሪ
በአንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር የማይሰጥህ ነገን ማየት እንድትጓጓ ነው፤ ስለዚህ ጎደለኝ ብለህ አታማር! ያንን ጉድለት ለመሙላት ስትል መኖርህ ብቻውን ትርጉም ይሰጥሀል።

ግሩም ቀን ተመኘን 🙏

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

08 Jan, 08:31


የፈጣሪ ትልቅ አደራ አለብን !

እዚህች ምድር ላይ ሰው አድርጎ በአምሳሉ ሲፈጥረን ትልቅ ቦታ እና ዋጋ ሰጥቶናል አደለም ፈጣሪ የምናቀው የሆነ ሰው ሲያከብረን እና የሆነ ቦታ ሲሰጠን እርሱን  ላለማሳፈር የተሻለ ሆነን ለመገኘት እንለፋለን አይደል ?

ስለዚህ እርሱም የጣለብንን አደራ ለመፈፀም መቼም ወደኋላ አንበል !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

07 Jan, 10:34


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የ ስነ ልቦናዊ ህይወት ቤተሰቦች

እንኳን ለ ገና በዓል አደረሳቹ🙏

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

06 Jan, 16:20


በድሮህ አትታሰር !

ድሮ ባጠፋኸው ጥፋት እስረኛ አትሁን ያንን ስህተት ተማርበት እንጂ የቁም እስረኛ አትሁን። ሁሌ የተለየሺውን ፍቅረኛ እያሰብሽ ማዘን አልሰለቸሽም?

ሁሌ ስለ ከዳህ የልብ ጓደኛህ እያሰላሰልክ መኖሩ አልታከተህም? ተንቀሳቀስ ወዳጄ! ቆመህ ከቀረህ ሁሉም ጥሎህ ነው የሚነጉደው፤ በሚገጥምህ ነገር ተደሰት አመስግን አለበለዚያ እንዳስቀመጥከው የምታገኘው ስቀህ የተነሳኸውን ፎቶ ብቻ ነው።

የደስታ ምሽት ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

04 Jan, 11:04


እየጠበቀን ነው !

አንተ ራስህን ከምትጠብቀው ችግር በላይ ፈጣሪ የሚጠብቅህ ትልቅ ነው ፤ አንዳንዴ ትናንሽ ነገሮች በህይወታችን ሲከናወኑ ለምን እንዲ ሆነብኝ ለምን ይሄ ተፈጠረ ምናምን እያልን እናማርራለን !

ነገር ግን ከዚያ ሁሉ ነገር መሀል ፈጣሪ ከምን እያወጣን እንደነበር ብናውቅ ሁሉን ትተን ይቅር በለን ባልን ነበር ከምናውቀው በላይ የሚያውቅልን ያላየነውን የሚያይልን ድንቅ አምላክ ነውና ያለን በሆነልን ነገር ሁሉ እናመስግን !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Jan, 03:06


ፈጣሪ አለልን !🙏

ፈጣሪ አይተውም ቀን አለው እየሆነ ስላለው ስለሚሆነው ስለሆነውም ሁሉ የእርሱ መልካም ፍቃድ ከጎናችን ነው ትቶን የማያውቅ መቼም አይተወንም !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

29 Dec, 04:19


ተመስገን 🙏

መንቃት በጣም ደስ ይላል ዛሬን ማየት አዲስ ቀን መመልከት አዲስ እድል ማግኘት ዛሬን የሰጠንን አምላካችንን እስኪ ከልብ እናመስግነው ! በቀናችን እንጠቀምበት የሚገባውን እናድርግ !

የተባረከ ሰንበት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

26 Dec, 15:09


አንዳንዴ በህይወታችው እየፈጠራችሁት ያለውን ነገር አታውቁም በጣም ቀላል ተብላ የተናቀች ነገር ምን ያህል ዋጋ አውጥታ የምትገኝበት በጣም ያገዘፍነው ደግሞ ዋጋ የሌለው የሚሆንበት ጊዜ አለ እናም

" ለእያንዳንዱ ነገር ጥንቃቄ ማድረግ እና አስተውለን መስራት እንልመድ "

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

24 Dec, 04:03


ከእኛ ይልቅ ፈጣሪ ይቅደም ፤ ከምናስበው በላይ ያሰበልንን ይሰጠን ፤ እንደኛ ሳይሆን እንደሱ ይቅናልን ፤ ከፈለግነው በላይ ያስፈለገን ሁሉ ይሁንልን !

    አሜን በሉ እንጂ እየመረቅኳችሁ እኮ ነው
😁 አዎ ከእኛ ሁሉ ነገር የእረሱ ጥቂት ትበልጣለች እና...

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

20 Dec, 04:29


ከፈጣሪ ደግነት ውስጥ በጣም ትልቁ ግርም የሚለኝ ነገር ምርጫ መስጠቱ ነው ፤ አለማስመረጥ እኮ መብቱ ነው ግን ያስመርጠናል በፈለግነው መንገድ እንድንሄድ በራሳችን መንገድ ውጤት እንድናመጣ ፈቅዶልናል መልካም የሆነ እና ያልሆነውንም ነግሮናል ከእኛ የሚጠበቀው መምረጥ ብቻ ነው !

  ምርጫችን ላይ ትኩረትእናድሮግ !

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

17 Dec, 05:45


አመስግን !

በጠዋት ተነስተህ ማማረር አትጀምር ነቅተሀል እኮ ስለዚህ ለተሰጠህ ትልቅ እድል ፈጣሪህን አመስግን ደስ ይበልህ ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ ይሄ ጎድሎኝ ያን አጥቼ አትበል ከሁሉም በላይ ህይወት አግኝተሀል እኮ ስለዚህ ደጋግመህ አመስግን !

ደስ የሚል ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

15 Dec, 06:32


ሞክረው !

እስኪ በቃ ዝም ብለህ ምንም ምክንያት ሳትፈልግ አመስግን ዝም ብለህ ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳታዘጋጅ ለፈጣሪህ ምስጋናህን ለግሰው እመነኝ ምክንያቶቹ ሮጠው ይመጣሉ !

ቆንጆ የምስጋና ቀን ተመኘው 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

12 Dec, 14:05


ሰጥቶናል !

የጠየቅከውን ጥያቄ የሚመልስልክ ፈጣሪ ወርዶ አይደለም እድል ይሰጥካል መንገድ ይከፍትልካል ሰዎችን ያመጣልካል ያኔ የተሰጠህን በአግባቡ ተጠቀምበት ምነው ፈጣሪዬ ዝም አለኝ አትበል አካባቢህን ቃኝ እና ምን ምን ተሰጠኝ ብለህ እይ ! 

የተሰጠንን የምታይበት ጥበብ ማስተዋሉን ፈጣሪ ያድለን !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

11 Dec, 11:03


86390 ብርህን ጠብቅ !

86400 ብር 💸💰 ቢኖረን እና አንድ ሰው መጥቶ 10 ብሩን ቢወስድብን በጣም ተናደን 86390 ብሩን እንጥለዋለን ? ታዲያ በቀን ውስጥ 86400 ሰከንድ አለን ለምን 10 ሰከንድ መጥፎ ነገር አየን መጥፎ ነገር ሰማን ብለን የቀረንን ጊዜ እናጠፋለን ???

መልካም ቀነ ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

09 Dec, 08:13


ሁሉም ያልፋል !

ከባድ ጊዜያት ይመጣሉ ግን ለዘላለም አይዘልቁም የመጡት ሊያልፉ ነው !

"ከእኛ በላይ ለእኛ የሚያስብልን ፈጣሪ ነው ያለን " ስለዚህ ምንም ነገር ሊያስፈራን እና ወደኋላ ሊወስደን አይገባም ! ሁልጊዜም ፈጣሪን ይዞ ወደፊት መጓዝ ነው!

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

05 Dec, 07:07


ውብ ጊዜያትን ለማሳለፍ!

🔴ሁለት ነገር ቀናችንን ያበላሽብናል
         1. ስለ ትናንት ማሰብና
         2. ከሰው ጋር ውድድር

🟡ሁለት ነገር ቀናችንን ያስተካክልልናል
         1. ያለንን ማመስገንና
         2. ዛሬን መኖር

🟢ሁለት ነገር ነጋችንን ያሳምርልናል
         1. እቅድ ማውጣትና
         2. በቂ ምክንያት ማስቀመጥ

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 17:28


አሸናፊ ለመሆን!

እነዚህን 3 ነገሮች አድርግ

1. ጥፋቶችህን በሰው አታመካኝ
2. ራስህን አትውቀስ
3. ስለተደረገልህም ስላልተደረገልህም  ነገር አመስግን

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

29 Nov, 05:49


ተስፋ !

"ተስፋ ያለው ሰው የሚመለከተው መከራዎቹን ሳይሆን መከራዎቹን እንዲያሸንፍ የሚያደርገውን ፈጣሪውን ነው !"

ነገሮች እንዳሰብካቸው እየሄዱልህ ባይሆንም ,እዳ ውስጥ ተዘፍቀህ መውጫው የጠፉህ ቢመስልም መንገዱን ፍለጋ ስትወጣ ፈጣሪን በእምነት ያዘው ያኔ አይሆንልኝም ያልከው ሁሉ ሆኖልህ ታየዋለህ !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

26 Nov, 15:21


የአንተም ጊዜ አለ!

ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አያበሩም፤ እኩል እናብራም ቢሉ ተፈጥሮ አትፈቅድላቸውም ግን ሁለቱም በራሳቸው ጊዜ ማብራታቸው አይቀርም።

አንተም አጠገብህ ያለ ሰው ሲሳካለት አይተህ የእኔስ ቀን መቼ ነው ? ምነው ፈጣሪ ዘገየ ካልክ እንደፀሀይ በቀን እንደጨረቃም በጨለማ የምታበራበት ቀን አለና በተስፋ ተራመድ !

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

22 Nov, 12:54


ብቻ አትቁም !

'መሮጥ ቢያቅት ተራመድ...መራመድ ቢያቅትህ ዳዴ በል....ዳዴ ማለት ቢያቅትህ ተኝፏቀቅ...ግን እንዳታቆም' ይለናል ማርቲን ሉተር።

ወዳጄ ያበቃልህ የተሳሳትክ ወይም የወደክ ጊዜ አይደለም...የሚያበቃልህ በቃኝ ብለህ ያቆምክ እለት ነው።

"ስለዚህ የጀመርከውን በፍፁም እንዳታቆም! እንዳታቆሚ! አናቆምም!"

ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

19 Nov, 13:22


ህግ ይኑርህ !

የማትደራደርበት ህግ አውጣ ማንም የማይጥስብህ ፣ምንም ነገር ቢፈጠር የማትቀይረው ፣ በማንኛውም ሁኔታ ልታከናውነው የሚገባ ወደ ስኬትህ ለመጓዝ መርህ የሚሆንህ ህግ ይኑርህ !

ወደኋላ ላለመመለስ ቆራጥ መሆን አለብህ!

መልካም ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

17 Nov, 06:19


ለራስህ ሁን !

ለራሱ ያልሆነ ሰው
ለማንም አይሆንም! ሰዎች ለራሳችን የምንሰጠውን ቦታ አይተው በቀላሉ የሚንቁን ወይ የሚያከብሩን ለዛ ነው፤ ራሱን ከናቀ እኔ እንዴት አከብረዋለሁ ብለው ያስባሉ።

ስለዚህ ታናሽ ወንድምህን ከመምከርህ በፊት ምክሩን ራስህ እንደተገበርከው እርግጠኛ ሁን። ራሳችንን ካልቀየርን ማንንም መቀየር አንችልም ከብዙ ሺ ቃላት አንድ ድርጊት ሰው ልብ ውስጥ ይቀራል። ለራስህ ስትሆን ለሌሎችም ትተርፋለህ።

አርኪ ምሽት ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

15 Nov, 09:06


ይቅርታ !

አንድን ሰው ይቅርታ ስትጠይቀው ተሳስተሀል ማለት አይደለም፤ ግን ትክክል ከሆነው ሀሳብህ በላይ ያንን ሰው ታስበልጠዋለህ ማለት ነው። ስለዚህ ይቅርታ ማለት በፍፁም እንዳትፈራ ወዳጄ!

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ ☺️

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

12 Nov, 12:16


ትላንት አልፏል!

ፈጣሪ ጊዜን ከፈጠረበት አንዱ ምክንያት 'ድሮ' የሚባል ላጠፋሀቸው ጥፋቶች ሁሉ መቀበሪያ ጉድጓድ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ እዛ የመቃብር ስፍራ ምን ታረጋለህ ወዳጄ? ለምን ስለትላንት እያሰብክ ራስህን ታስጨንቃለህ?! ወዳጄ አሁንን መኖር ጀምር! አጠገብህ ያለውን በረከት እይና ተመስገን በል፤ ተደሰት!

@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

09 Nov, 07:28


ጠዋትህን ጠብቃት!

ህይወት የምርጫ ጉዳይ ናት ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነቃ ቀናችንን የሚወስን አማራጭ ይቀርብልናል ፤ ያኔ ግን ተጠንቅቀን መወሰን የእኛው ምርጫ ነው ቀናችን ብሩህ እንዲሆን ከተመኘን ጠዋታችንን በፍቅር እና ደስ በሚል መንፈስ  ከእኛ አልፈን ለሌሎች ሰላምን ፍቅርን እና መልካምነትን በመስጠት እንጀምረዋለን ያኔ ቀኑ የእኛ ሲሆን እና በእኛ ላይ ሲያበራ ይውላል በተቃራኒውም ከመረጥን እንደዛው ስለዚህ ቀናችንን እንድንገዛው እና የእኛ እንድናረገው ጠዋታችንን እናስተካክለው!

መልካም ቀን ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

07 Nov, 10:13


ምስጋና !

ማመስገን ምንም ጉልበት ሳናፈስ ብዙ ደሞዝ የምናገኝበት መንገድ ነው ! ለንዴት ፣ ለድብርት ፣ ለመጥፎ ስሜት በሙሉ መድኋኒት መዋጥ ሳይጠበቅብን የምንፈወስበት ትልቁ መዳኛችን ነው !

"ስለዚህ መድኋኒታችንን በየቀኑ ሳናዛንፍ እንዋጠው የእድሜ ልክ ፈውስን እናገኝበታለን !"

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

05 Nov, 05:16


ብቻ ወስን !

ፈጣሪ ሁሌም ቢሆን ያንተን ውሳኔ ነው የሚጠብቀው ፤ አየህ ወስነህ ከጀመርክ እርሱም ወስኖ ያግዝኋል የእውነት ከለፋህ የእውነት ውጤት ይሰጥኋል ከልብህ ካሻህ የልብህን የመሻትህን ታገኛለህ ብቻ የምትፈልገውን የምታደርገውን ወስን !

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

01 Nov, 07:39


መልካምነት ዋጋ ይጨምራል !

ለሰው መልካም መሆን በምንም ሁኔታ ይጠቅመናል እንጂ በፍፁም ሊጎዳን አይችልም ! እኛ ሀላፊነታችን ከእኛ የሚጠበቅብንን ማድረግ እንጂ ሌሎች የሚሰጡንን ምላሽ መቆጣጠር አይደለም ! መልካም በሆንን ቁጥር ውስጣችን ይፀዳል ክፋና መርዛማ የሆኑ ውስጣችንን የሚጎዱ ነገሮች ሁሉ ከላያችን ይወጣሉ ፣ በስተመጨረሻ እነሱ ከሚሰጡን ምላሽ በላይ እኛ የምናገኘው እርካታ ተወዳዳሪ የለውም ! ስለዚህ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን መልካምነትህን ዝም ብለህ ቀጥል!

ቆነጆ ቀን ተመኘን🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

31 Oct, 08:47


" ሁሉም ሰው ምቾት ይዞት ነው እንጂ ፊሪ አይደለም "

ምንም አማራጭ የሌለው ልጅ እና ሁሉ ነገር የተሟላለት ልጅ እኩል ፈተና ውስጥ ቢገቡ የመመለስ እድላቸው እኩል አይሆንም !

የሆነን አዲስ ነገር ለመጀመር ወደኋላ የምንለው ወደኋላ የምንልበት መደገፊያ ስላለን ነው መደገፍያ ባይኖረን ያለንን አማራጭ በሙሉ እንጠቀም ነበር

ቆንጆ ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

30 Oct, 09:27


ቀላሉ መንገድ !

መንገድህ ቀና እንዲሆን የፈጣሪህን ትዕዛዝ ተከተል አክብር ከትዕዛዛቶቹ ውስጥ አንዳቸውም ያለምክንያት አልታዘዙም እስኪ ልብ ብለህ ተመልከታቸው የስኬት የደስታ ሁሉ ቁልፍ እነርሱ ጋር አለ ካንተ የሚጠበቀዉ በአግባቡ መፈፀም ብቻ ነው 👼

መልካም ቀን ተመኘን 🙏
@Psychological_Mind
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ 😊

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

28 Oct, 18:43


ስነ-ልቦናዊ ህይወት pinned «ሁሉንም መቀየር! ትላንት ላይመለስ አልፏል ራስህን መውቀስ አቁም! አሁንን መኖር ጀምር፤ ዛሬ ቆራጥ ከሆንክ ሁሉንም መቀየር፣ ሁሉንም እንደ አዲስ መጀመር፣ ያበላሸኸውን ማስተካከል ትችላለህ። ወዳጄ እድልህን ተጠቀምበት ይሄንን ቀን ያላዩ ብዙዎች አሉ። @Psychological_Mind የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!🫡»

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

28 Oct, 17:55


ሁሉንም መቀየር!

ትላንት ላይመለስ አልፏል ራስህን መውቀስ አቁም! አሁንን መኖር ጀምር፤ ዛሬ ቆራጥ ከሆንክ ሁሉንም መቀየር፣ ሁሉንም እንደ አዲስ መጀመር፣ ያበላሸኸውን ማስተካከል ትችላለህ። ወዳጄ እድልህን ተጠቀምበት ይሄንን ቀን ያላዩ ብዙዎች አሉ።

@Psychological_Mind

የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!🫡

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

26 Oct, 12:53


👀 በሁሉም ምርጥ መሆን!

ሙሉ ሰውነትህ ቢወፍር የተለመደ ነው፤ አንድ እጅህ ተነጥሎ ቢወፍር ግን እንግዳ ነገር ነው። አየህ መዝናናትና ፈታ ማለት ላይ ምርጥ ሆነህ ነገር ግን ስራህ ላይ፣ መንፈሳዊ ህይወት ላይ፣ የቤተሰብ ወይ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፈዘዝክ ይሄን ምሳሌ አስታውስ። ወዳጄ የሁሉንም ነገር ሚዛን ማስጠበቅ አለብህ።

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

25 Oct, 15:22


ያንተ ተስፋ ማነው?!

እንደ አንተ ጭንቀትና ሀሳብ ቢሆን ዛሬን ማየት የማይታሰብ ነበር፤ ያንን ጊዜ ማለፍ ቅዠት ነበር፤ ግን አለፍከው፤ ያልገመትከው ሁሉ ሆነ አንተ ተስፋ ቆርጠህ ስትጨርስ ፈጣሪ ጀመረ። ያንተ ተስፋ የዚህ አለም ተለዋዋጭ ነገር አይደለም! ያንተ ተስፋ የማይለወጠው፣ በዘመናት የማያረጀውና የማያልፈው ፈጣሪህ ነው!

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ቆንጆ ምሽት ተመኘን🙏🙏🙏

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

24 Oct, 07:48


ማቆም የለም!

ነገሮች ከፍ ዝቅ እያሉ ይሆናል፣ ከመቀጠል ይልቅ ማቆም የተሻለ የሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህ ግን ሁሉንም እርግፍ አርጎ መተው ቀላል ነው፤ ሀይል ሰብስቦ መቀጠል ነው ከባዱ!

ወዳጄ ለራስህ የምትሆነው ከዛ ለምትወዳቸው የምትደርሰው ተስፋ ሳትቆርጥ ከቀጠልክ ብቻ ነው። ለዛ ነው መበርታት ያለብህ፤ ዳይ ያቆምከውን ቀጥል አሁኑኑ!🙏🙏🙏

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

22 Oct, 14:37


በህይወት ስትኖር ማወቅ ያሉብህ 3 ነገሮች

1⃣ የምትፈልገውን ሳይሆን የሚገባህን ነው የምታገኘው ስለዚህ በሙሉ አቅም መጣር አለብህ
2⃣ ለብዙ ሰው የሚያስፈልገውን ስታረግ ላንተም የምትፈልገውን ሁሉ ታገኛለህ
3⃣ ስትፈልገዉ ያጣኸውን ነገር ትንሽ ከታገስክ በተራው ሲፈልግህ ታገኘዋለህ 🙏🙏🙏


@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

21 Oct, 16:35


መንገድ ጀምር !

አንተ ብቻ ሂድ እንጂ የሆነ የሚከፈትልህ በር አለ "አንኳኩ ይከፈትላችኋል እሹም ታገኙታላችሁ" አይደል አምላካችንስ ያለን ብቻ ተኝተህ አትጠብቅ ውጣ እና መንገድ ጀምር ያኔ  እግርህ ራሱ የት ሊመራህ እና ቦታህን ሊያገናኝህ እንደምትችል አታውቅም !

ምን እየጠበቅህ ነው ዳይ ውጣ እንጂ 😄
@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ቆንጆ ምሽት ተመኘን 🙏🙏

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

19 Oct, 19:33


ሁሉንም ታልፋለህ!

ለራስህ ምን አይነት ጀግና እንደሆንክ ማሳየት አለብህ! ለምትወዳቸው ትደርሳለህ እንጂ አንተ የሌላ ሰው እርዳታ ጠባቂ አይደለህም! ወዳጄ እድለኛ ነህ፤ ከማንም በላይ ፈጣሪ ይወድሀል፤ በህይወት አያልፉም ያልካቸውን ከባድ ጊዜያት ሁሉ አልፈሀል። አሁንም ታልፋለህ!


@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

18 Oct, 21:33


መጮህ አያስከብርም!

ሁሌም የሰጠነውን መልሰን እናገኛለን ፤ የናቅነው ይንቀናል ክበር የነፈግነው ሁሉ ይሸሸናል ቦታ ያልሰጠነው በትዕቢት ያስተናገድነው መልሶ ሊያየን አይሻም የሰደብነው ያወርደናል ዝቅ አርጎ ያየናል ሰው ሆነን ግን ሰው ያደረግነው የሰውነት ክብሩን የሰጠነው በማንነቱ በምንነቱ ሳንል ያከበርነው ግን ያከብረናል ስለዚህ የፈለግነውን ነገር ለማግኘት ተቃራኒውን ሳይሆን ተመሳሳዩን መስጠት ይጠበቅብናል! "ሰው ሁሉ የዘራውን ነው የሚያጭደው "

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

17 Oct, 19:41


ፍርሀት !

ፍራ በደንብ አድርገህ ፍራ ከምትሄድባቸው ከምታስባቸው መንገዶች በፍርሀትህ ምክንያት ቅር ከዚያም ግን አስብ መቅረትህ ምን እያሳጣህ ነው ?

የልጅነት ህልምህን ? ለእናትህ የገባህላትን ቃል? አባትህ ከአንተ ሲጠብቅ የነበረውን ነገር ? ሁሉን ተወዉ እና ካለህበት ከዚህ ህይወት በእጥፍ ወደአደገ ህይወት የመሄድ እድልህን ሁሉ :-
   
ለማይጠቅም ፍርሀት ስታጣው እና ስታበላሸው ምን ይሰማሀል ? ከዚህ በላይ ምን እንዳይመጣ ነው የምትፈራው ?

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

16 Oct, 03:18


ታገስ !

በለሱን የጠበቀ ፍሬውን ይበላል የታገሰም እንዲሁ ይከብራል  ምሳ 27:18

በጊዜው የማይሆን አንዳች ነገር ስለሌለ እባክህ በችኮላ ለፀፀት የሚዳርግህ ነገር ውስጥ ፈፅሞ አትግባ።  ለሚያልፈው ዛሬ የማያልፍ ታሪክን አትፃፍበት።

እራስህ ላይ እየሰራህ ማንነትህን ገንባ። እመነኝ በችኮላ የምታተርፈው ነገር ቢኖር ወድቀትን ብቻ ነው።

እይታህ ይቀየር! አለቱ ሳይሆን በውስጡ ያለው ማዕድን ይታይህ።  ወድቀቱ ሳይሆን ስኬቱ ይሽተትህ።
ስራ ከዛ እስኪበስል ታገስ!

አዎ ማድረግ እንችላለን


@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

04 Jul, 17:51


ራስህን ለመለወጥ የሚያስገድድህ ቀን እስኪመጣ ለምን ትጠብቃለህ? አሁን ነቃ ብለህ ራስህን ጠይቀው
1. ነገ ምንድነው የምሆነው?
2. ምን አይነት አለማዊና መንፈሳዊ ህይወት ነው የሚኖረኝ?
3. ከማን ጋር ነው የምኖረው?
4. ደስተኛ የምሆነው ምን ባሳካ ነው?
ብለህ ጠይቅ፤ ፈጣሪ በአንድም ይሁን በሌላ መልስ ይሰጥሀል።

መልሱ ግልፅ እስኪሆን ግን ነገን አስበህ ራስህን ሁሌም አሳድግ፤ ገንዘቡን አስቀምጥ፣ መፅሀፉን አንብብ፣ ተማር፣ ገቢህን ለማሳደግ የሚጠበቅብህን አድርግ! ወዳጄ ስንፍናህን ቆፍረህ ቅበረው፤ የዚህ አለም ስኬት ለተኙ አይደለም ለነቁ ነው፤ ለፈዘዙ አይደለም ለባነኑ ነው!

መልካም ምሽት ይሁንላቹ 🙏

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

04 Jul, 17:50


ስነ-ልቦናዊ ህይወት pinned «ራስህን ለመለወጥ የሚያስገድድህ ቀን እስኪመጣ ለምን ትጠብቃለህ? አሁን ነቃ ብለህ ራስህን ጠይቀው 1. ነገ ምንድነው የምሆነው? 2. ምን አይነት አለማዊና መንፈሳዊ ህይወት ነው የሚኖረኝ? 3. ከማን ጋር ነው የምኖረው? 4. ደስተኛ የምሆነው ምን ባሳካ ነው? ብለህ ጠይቅ፤ ፈጣሪ በአንድም ይሁን በሌላ መልስ ይሰጥሀል። መልሱ ግልፅ እስኪሆን ግን ነገን አስበህ ራስህን ሁሌም አሳድግ፤ ገንዘቡን…»

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

22 Jun, 12:49


አይምሮን ማሳመን!

እግርህ በተግባር እንዲራመድ አይምሮህና ልብህ ቀድሞ በሀሳብ መራመድ አለበት፤ ሁሉ ነገርህን የሚያዘው አይምሮህ ነው። ራስህን መቀየር ወይ መወሰን ስትፈልግ አስቀድመህ ለአይምሮህ ስትቀየር የሚኖርህን ደስታ ደጋግመህ አስበው ንገረው፤ ከዛ የሆነ ጊዜ አንተ ራሱ ሳታውቀው ቆራጥ ሆነሀል፣ ጠንካራ ሆነሀል ምክንያቱም አይምሮህ ካመነ የማይቀየር ነገር የለም!

መልካም ምሽት ይሁንላቹ 🙏

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

22 Jun, 12:49


ራስን የመግዛት የመጀመሪያው ግብዓት ረሃብ ነው። የምትበላውን እና የምትጠጣውን መቆጣጠር ከቻልክ ሁሉንም ነገር ትቆጣጠራለህ!

@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 20:23


መልካም ምሽት 🙏 ፈጣሪ የነገ ሰዉ ይበለን

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 20:21


Live stream finished (26 minutes)

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 19:59


Welcome to Live🙏

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 19:54


Live stream started

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

02 Dec, 18:28


ካላዛለቃችሁ ልቀቁት!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
አሸናፊዎች እንደሆናችሁ ታስባላችሁ ነገር ግን ተሸናፊነታችሁንም ማመን አለባችሁ፤ ነገሮችን ሁሉ ማሳካት እንደምትችሉ ይሰማችኋል ነገር ግን አንዳንድ ነገሮች ከአቅማችሁ በላይ እንደሆኑ መረዳት ይጠበቅባችኋል። አቅምን አውቆ መኖር፣ በልክ መራመድ ታላቅ ጥበብ እንደሆነ ተገንዘቡ። በስቃይ የተሞላ የፍቅር ህይወት ዘላቂ የመሆን እድሉ በጣም ጠባብ ነው፤ ክፍያው ያነሰና የማያስደስት ስራ ህይወትን የመቀየር አጋጣሚው በጣም አናሳ ነው፤ በተበታተነ ትኩረት ውስጥ የሚፈፀም፣ ከስሜት ጋር እየታገሉ የሚከናወን ተግባር ውጤታማነቱ አጠራጣሪ ነው። ሰጥቶ በመቀበል፣ ተቀብሎ በመስጠት እንጂ እንዲሁ እንደዋዛ በመብከን የሚቀየር ነገር የለም።

አዎ! ካላዛለቃችሁ ልቀቁት፣ ካላዋጣችሁ ተውት። ህይወታችሁን በማይሆን ስራም ሆነ ግንኙነት ላይ አታባክኑ። ሁለት አይነት ብክነት አለ፦ አንደኛው አውቀን የምባክነው ሌላኛው ባለማወቅ እንዲሁ የምንደክመው። ባለማወቅ የምንባክነው ይቅርና ውጤት እንደሌለው፣ የትም እንደማያደርሰን፣ ስኬት እንደማይጨምርልን ብሎም ደስታና እርካታን እንደማያጎናፅፈን እያወቅን የምንደክመውን ድካም ብንቀንስ ምንያክል ሸክም፣ ምንያክልስ ጭንቀት ከእራሳችን ላይ እንደምናወርድ አስቡት። ትግላችሁ ውጤት ያምጣ አያምጣ፣ ጥረታችሁ ትርጉም ይኑረው አይኑረው፣ ግንኙነታችሁ ጠቃሚ ይሁን አይሁን ብዙ ሳትደክሙ በቀላሉ ልባችሁ ይነግራችኋል፣ ውስጣችሁ እውነታውን ያውቀዋል።

አዎ! ጀግናዬ..! ላንተ የሚሆንህን ለማወቅ ማንንም አትጠብቅ፣ ለእራስህ ለመወሰን ማንም እንዲደግፍህ አትመኝ። በምታውቀው ልክ ለእራስህ ህይወት ትርጉም ስጠው፣ በገባህ፣ በተረዳሀው መጠን ጠቃሚዎቹ የህይወት መንገድህ ላይ አተኩር። እድገትህ በምትወደው ዘርፍ እንጂ በምትጠላው ዘርፍ አይመጣም፣ ደስታና እርካታ በሚያስደስትህ ተግባር እንጂ በሚያሰለችህ ተግባር ሊገኝ አይችልም። ልብህ በሚያውቀው ጎጂ ግንኙነት ውስጥ እራስህን አታባክን፣ ግልፅ በሆነልህ አሰልቺ ድግግሞሽ ስሜትና ተነሳሽነትህን አትግደለው። በሚታይህ ልክ ወደፊትህን ለማስተካከል ሞክር፣ እንዳቅምህ እራስህን ለምትወደውና ትርጉም ለሚሰጥህ ነገር ስጥ።
ድንቅ ምሽት ይሁንልን! 🏞🌞🌅


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@Psychological_Mind
@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

11 Sep, 13:06


🌼 እንኳን ለ 2016 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
        🌼 New year 🌼
         መልካም አዲስ አመት

@Psychological_Mind
@Psychological_Mind

ስነ-ልቦናዊ ህይወት

26 Aug, 08:14


ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ጀግናዋ አትሌት አማኔ በሪሶ #ወርቅ ፤ ጀግናዋ አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ #ብር ለሀገራቸው አስገኝተዋል